Space Science and Geospatial Institute
1.61K subscribers
5.43K photos
147 videos
21 files
501 links
Download Telegram
ጳጉሜ 5 ቀን የነገው ቀን
     ======= SSGI =======

ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን  ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰልሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል።

በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን በኩራት ያበስራል!

የክቡር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት

ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
                ከምድር እስከ ህዋ …
                           SSGI
❤3
ጳጉሜ 5 የነገ ቀን «ነገን ዛሬ መገንባት» የኢትዮ ስፔስ እና ጂኦስፓሻል ታዳጊዎች ክለብ (ESKC) የ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠና አጠናቀቀ።
           ======= SSGI =======
      (ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም፣ SSGI) 

በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) አዘጋጅነት ከክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች ጋር በመተባበር ላለፉት ሁለት ወራት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮ ስፔስ እና ጂኦስፓሻል ታዳጊዎች ክለብ (ESKC) የ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠና በታላቅ ስኬት ተጠናቋል።

በዘንድሮው ስልጠና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተጨማሪ በ10 ክልሎች በሚገኙ 25 ማዕከላት አማካኝነት ከ4,000 በላይ ታዳጊዎች ተሳትፈዋል።

ይህም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በክልል ደረጃ ከፍተኛ የተሳታፊዎች ቁጥር እድገት የታየበት እና የፕሮግራሙን ተዳራሽነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ ሆኗል።

ስልጠናው ከዚህ ቀደም ሲሰጡ በነበሩት እንደ ሳተላይት ቴክኖሎጂ፣ ስፔስ እና ፕላኔታሪ ሳይንስ፣ አስትሮኖሚ እና አስትሮፊዚክስ፣ ጂ.አይ.ኤስ (GIS)፣ ድሮን (UAV)፣ ሮኬት ሳይንስ፣ ሮቦቲክስ እና ፓይተን ፕሮግራሚንግ ባሉ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በዘንድሮው ዓመት አዲስ ተጨማሪ ዋና የትምህርት ዘርፍ በመሆን "የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ (AI & Machine Learning)" መሰረታዊ እና የተጠናከረ ስልጠና በስፋት ተካቶ ተሰጥቷል።

በማጠናቀቂያ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ (ኢ/ር) ለታዳጊዎች ጥልቅ መልዕክት እና የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል። ም/ዋና ዳይሬክተሯ በንግግራቸው የከፍተኛ ደረጃ (Senior) ተማሪዎች ያበለፀጓቸውን የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች አድንቀዋል።
በተለይም ተማሪዎቹ ያሳዩት የትምህርት ዘርፎች ቅንጅት (Interdisciplinary integrity) እጅግ አስደናቂ መሆኑን ጠቁመው፤ ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ እስከ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ቴክኖሎጂ፣ ከዘመናዊ ግብርና (Smart-Farming) እስከ ባለብዙ አገልግሎት ሰው አልባ አውሮፕላን (UAV) ልማት ድረስ የሰሯቸው ስራዎች ኢንስቲትዩቱ እና ሀገር ትልቅ ተስፋ የሚጥልባቸው የነገ ተስፋዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ መደበኛ የክረምት ስልጠና ጎን ለጎን፣ በኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ስር የተመረጡ ተማሪዎች በመጪው ኖቬምበር 2026 በሩሲያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ አስትሮኖሚ ኦሎምፒያድ(OWAO 2026) ላይ ሀገራቸውን በብቃት ለመወከል ተጠናክረው በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።

ለዚሁ ውድድር ተማሪዎቹን ብቁ ለማድረግ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች እና የክለቡ አስተባባሪዎች ከተማሪዎቹ ጋር በቅርበት በመስራት ላይ ይገኛሉ።

የማጠናቀቂያ ዝግጅቱ ተማሪዎች ያበለፀጓቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በክብር እንግዶች ከተጎበኙ በኋላ በታላቅ ድምቀት ተጠናቅቋል

#SSGI #ESKS
❤2