ኢንስቲትዩቱ ጳጉሜ 4 «በሕብር ቀን» ለሲኒየር ሠራተኞች የሽኝትና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ።
======= SSGI =======
(ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም SSGI)
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ለበርካታ ዓመታት ኢንስቲትዩቱን ብሎም ሀገራቸውን በትጋትና በቁርጠኝነት ያገለገሉ እና በቅርቡ ወደ ጡረታ የተሸጋገሩ ሲኒየር ሠራተኞችን የሸኚትና የምስጋና መርሃግብር አካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ (ዶ/ር) ተገኝተው፣ የሲኒየር ባልደረቦች ኢንስቲትዩቱን ብሎም ለሀገራቸው ዕድገትና ስኬት ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ እንዲሁም ባሳዩት የሥራ ትጋትና ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል።
ዶ/ር አብዲሳ አክለው ሲኒየር ሠራተኞቹ ያካፈሉት የሥራ ልምድና ዕውቀት ለኢንስቲቲዩቱ አሁናዊ አቅምና ለወደፊት እድገት ጠቃሚ መሠረት መሆኑን ገልጸው፣ በታማኝነት ላበረከቱት አገልግሎት
ኢንስቲትዩቱ ስም አድናቆታቸውንና አክብሮታቸውን ገልጸዋል።
በመርሃግብሩ ለይ ሲኒየር ባልደረቦችም በኢንስቲትዩቱ ያሳለፉትን የሥራ ዘመን በማስታወስ ስሜታቸውንና ተሞክሯቸውን አጋርተዋል።
በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ባሳለፉት የሥራ ዘመን ያገኙትን የሙያ ልምድ፣ ከባልደረቦቻቸው ጋር የገነቡትን ግንኙነት እና በሥራ ሂደታቸው ያሳለፏቸውን የሥራ ልምዶች በማንሳት እንዲሁም ይህንን መርሃግብር ኢንስቲቲዩቱ በማዘጋጀቱ ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል።
ከምድር እስከ ህዋ …
#SSGI

❤4
ጳጉሜ 5 ቀን የነገው ቀን
======= SSGI =======
ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል።
በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን በኩራት ያበስራል!
የክቡር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት
ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
ከምድር እስከ ህዋ …
SSGI

❤3
ጳጉሜ 5 የነገ ቀን «ነገን ዛሬ መገንባት» የኢትዮ ስፔስ እና ጂኦስፓሻል ታዳጊዎች ክለብ (ESKC) የ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠና አጠናቀቀ።
======= SSGI =======
(ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም፣ SSGI)
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) አዘጋጅነት ከክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች ጋር በመተባበር ላለፉት ሁለት ወራት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮ ስፔስ እና ጂኦስፓሻል ታዳጊዎች ክለብ (ESKC) የ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠና በታላቅ ስኬት ተጠናቋል።
በዘንድሮው ስልጠና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተጨማሪ በ10 ክልሎች በሚገኙ 25 ማዕከላት አማካኝነት ከ4,000 በላይ ታዳጊዎች ተሳትፈዋል።
ይህም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በክልል ደረጃ ከፍተኛ የተሳታፊዎች ቁጥር እድገት የታየበት እና የፕሮግራሙን ተዳራሽነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ ሆኗል።
ስልጠናው ከዚህ ቀደም ሲሰጡ በነበሩት እንደ ሳተላይት ቴክኖሎጂ፣ ስፔስ እና ፕላኔታሪ ሳይንስ፣ አስትሮኖሚ እና አስትሮፊዚክስ፣ ጂ.አይ.ኤስ (GIS)፣ ድሮን (UAV)፣ ሮኬት ሳይንስ፣ ሮቦቲክስ እና ፓይተን ፕሮግራሚንግ ባሉ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በዘንድሮው ዓመት አዲስ ተጨማሪ ዋና የትምህርት ዘርፍ በመሆን "የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ (AI & Machine Learning)" መሰረታዊ እና የተጠናከረ ስልጠና በስፋት ተካቶ ተሰጥቷል።
በማጠናቀቂያ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ (ኢ/ር) ለታዳጊዎች ጥልቅ መልዕክት እና የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል። ም/ዋና ዳይሬክተሯ በንግግራቸው የከፍተኛ ደረጃ (Senior) ተማሪዎች ያበለፀጓቸውን የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች አድንቀዋል።