Space Science and Geospatial Institute
1.61K subscribers
5.43K photos
147 videos
21 files
502 links
Download Telegram
PhD Dissertation Defense!
Mr. Abdissa Yilma Tiky from College of Humanities and Social Sciences, Department of Technology and Innovation Management has successfully defended his PhD dissertation titled, “An Integrated Framework for AI-Driven Flood Susceptibility Mapping and Technology Acceptance in Adama City, Ethiopia."

Congratulations Dr. Abdissa Yilma Tiky!

#ASTU
#SSGI
🏆14❤4👍4👏2
የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት የኢትዮጵያ መንሠራራት በሚል መሪ ሐሳብ፣ በአምስቱ የጳጉሜን ቀናት ስያሜዎች ይከበራል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
                ከምድር እስከ ህዋ …
                           SSGI
❤3
ጳጉሜ አንድ የእምርታ ቀን

"የስፔስ እና የጂኦስፓሻል ዘርፍ የተልዕኮ ስኬት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት"

ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
                ከምድር እስከ ህዋ …
                           SSGI
🏆1
‎በአርባ ምንጭ እና በወላይታ ሶዶ ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ሥልጠና ተጠናቀቀ!
        ======= SSGI =======
‎በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ ከተሞች ለተለያዩ ዘርፎች ለተውጣጡ የቴክኒክ ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ሲሰጥ የቆየው የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት (DAS) ስልጠና ተጠናቀቀ። ስልጠናው ከነሐሴ 23 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በሁለት ዙር በተከታታይ ቀናት በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ ከተሞች ተካሂዷል።

‎በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመሬት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ዳንኤል ዳሌ፣ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ለከተሞች እድገትና ለዲጂታላይዜሽን ቁልፍ መሠረተ ልማት መሆኑን ገልጸዋል።
‎
‎የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት በከተሞች ውስጥ አንድን ቦታ በቀላሉና በትክክል ለመለየት ከማስቻሉ ባሻገር፣ በከተሞች የሚሰጡ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማዘመንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ ሚና እንዳለውም አመልክተዋል።
‎
‎በሁለቱም ከተሞች የዲጂታል አድራሻ መረጃ መሰብሰብ ሥራ በይፋ መጀመሩን የገለጹት ዶ/ር ዳንኤል፣ የመረጃ መሰብሰብ ሥራው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅም የሥራ መመሪያና አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።
‎
‎በተጨማሪም በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ ከተሞች የተሰጠው ስልጠና በቀጣይ በዲላና በጂንካ ከተሞች እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
‎
‎ዶ/ር ዳንኤል በመጨረሻም ስልጠናውን ላመቻቸውና ላዘጋጀው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI)፣ ለአርባ ምንጭና ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደሮች፣ ለክልሉ ፕላንና መሬት ቢሮ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም ለአርባ ምንጭና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ላደረጉት አስተዋጽኦና ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። እንዲሁም ለአሰልጣኞችና ለስልጠናው አስተባባሪዎች አድናቆታቸውን ገልጸዋል።