እንኳን ደስስ አለን!!
በአንድ ጀምበር 805.3 ሚለዮን ችግኝ ከተባበርን ፣ አንድ ላይ ከቆምን የማንችለው የማናሳካው ነገር የለም።
ይኼ ስኬት በጥቃቅን አጀንዳ ኢትዮጵያን መከፋፈል ለሚፈልጉ ጥሩ ማስተማሪያ ነው።
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችም የድርሻቸውን ተወጥተዋል።
ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
ከምድር እስከ ህዋ …
SSGI

❤2👍1
በሀገራችን የሚከሰቱ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ከከባድ ዝናብ፣ ከዳገታማና ተዳፋት መልክዐ-ምድራዊ አቀማመጥ፣ ከአፈሩ አይነት አና የአለት መዋቅር ሁኔታዎች፣ ከውሃ ተፋሰስ ጥግግት እንዲሁም ከመሬት አጠቃቀምና አያያዝ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የሚከሰቱ መሆናቸውን ጥናቶች ያመላክታሉ።
ምንም እንኳን አሁን ባለው የኤልኒኖ ተፅዕኖ ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች ከመደበኛ በታች የሚጠበቅ የዝናብ ሁኔታ ቢኖርም፣ በከባድ እና በተራዘመ ዝናብ ምክንያት በተለይ የመሬት መንሸራተት ተጋላጭነታቸዉ ከፍተኛ ተብለዉ በተለዩ ስፍራዎች ላይ አደጋ የመከሰት እድል ሊኖር ይችላል ።
በመሆኑም ከዚህ አኳያ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን ለመከላከል ነዋሪዎች ከተለመደው በላይ ከባድ የዝናብ መጠን ሲኖር አንዲሁም ይህን መሰሉ ዝናብ ለረጅም ጊዜ በሚቆይበት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደረግና የሚመለከታቸው አካላትም የቅድመ ማስጠንቀቂያና የአደጋ ስጋት ቅነሳ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንመክራለን።
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) ቀደም ሲል ባካሄዳቸው የመሬት መንሸራተት ተጋላጭነት ጥናቶች፣ ተጋላጭ ቦታዎችን ለይቶ ተደራሽ ያደረገ ሲሆን በየጊዜዉ የሚወጡ ሳይንሳዊ ትንተናዎች እና ምክረ-ሃሳቦችን በድህረ-ገፅ https://disaster.ssgi.gov.et/advisory እንዲከታተሉ እናሳስባለን።

disaster.ssgi.gov.et
React App
Web site created using create-react-app
❤1
They are discovering how to communicate ideas, challenge assumptions, and transform concepts into real world solutions.
This is what STEM education should look like.
Hands on. Purpose driven. Inspiring.
At FASESA, we are not simply preparing students for careers in science and engineering.
We are empowering a generation of African problem solvers who will shape the future of space exploration and technological innovation.
The future is not waiting for them. They are already building it.
ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
ከምድር እስከ ህዋ …
SSGI
This is what STEM education should look like.
Hands on. Purpose driven. Inspiring.
At FASESA, we are not simply preparing students for careers in science and engineering.
We are empowering a generation of African problem solvers who will shape the future of space exploration and technological innovation.
The future is not waiting for them. They are already building it.
ለተጨማሪ መረጃ:-
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች
YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi
Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr
LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
ከምድር እስከ ህዋ …
SSGI
X (formerly Twitter)
Space Science and Geostatial Institute (SSGI) (@ssgi2022) on X
Established in 2021
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Every great achievement in space begins with an idea, a team, and the courage to solve a problem.
Watching these students SSGI (Ethiopian Space Science and Geospatial Institute) collaborate during the FASESA and The Boeing Company Pathways to Space 2026 programme is a reminder that the future of African innovation is already taking shape in classrooms across the continent.
Through teamwork, creativity, critical thinking, and engineering design, these young innovators are learning that the greatest breakthroughs are rarely achieved alone.

❤1🔥1
ቶሽካ “የግብጽ የውሃ ሮቶ”
በምስሉ የምትመለከቱት ግብጽ የአባይን ወንዘ የተፈጥሮ የፍሰት አቅጣጫ በክፊል በማስቀየስ (Diversion) በተንጣለለው የሰሃራ በረሃ ላይ ያከማቸችው እኛ “የግብጽ የውሃ ሮቶ” ብለን የሰየምነው ቶሽካ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ነው፡፡
ቶሽካ የአባይን ውሃ በትላልቅ የውሃ መሳቢያ ቱቦዎች በማጓጓዝ በደቡባዊ ግብጽ ለበረሃው ንዳድ ሲሳይ እንዲሆን ተደርጎ ጎርጎድ ባሉ ስፍራዎች ላይ ለተፈጠሩ ግዙፍ የውሃ ክምችቶች የተሰጠ የወል ስያሜ ነው፡፡
ግብጽ በአመት እስከ ሶስት ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃን በትነት እያባከነች ሀይቁን ለአርሻ ስራ በማዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿን በአካባቢው በማስፈር ላይ ትገኛለች፡፡
በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂስፓሺያል ኢንስቲትዩት የውሃ መቆጣጠሪያ ማዕከል የተሰበሰበው የሳተላይት ምስል ላይ የተደረገው ትንተና፤ የቶሽካ ሐይቅ የውሃ ሽፋን በየጊዜው እያደገ እንደሚገኝ ያመላክታል፡፡
የህዳሴ ግድባችንን ሙሌት ከማከናወናችን አንድ አመት ቀደም ብሎ የሀይቁ ስፋት 86.63 ካሬ ኪሎ ሜትር የነበረ ሲሆን፤ የውሃ ሙሌታችንን ባጠናቀቅንበት አመት ደግሞ ስፋቱ በ41 እጥፍ አድጎ 3,531.45 ካሬ ኪሎ ሜትር ደርሷል፡፡
ክርክር የማይገጠምበት ሊደበቅ የማይችለው የሳተላይት ምስል ትንተና የሚያሳየው ሳይንሳዊ ሀቅ ይህ ሆኖ ሳለ፤ “ከኢትዮጵያ የሚለቀቀው የውሃ መጠን ቀነሰብን” እየተባለ በየጊዜው የሚነሳው አታካች ትርክት ከእውነታው ያፈነገጠ እና ዘመኑን የማይመጥን ነው፡፡
ይህንን የግብጽ በተቃርኖ የተሞላ አቀራረብ በምርምርና ጥናት ውጤቶች ልንሞግተው ስለሚገባ ተዛማጅ መረጃዎችን በተከታታይ የምናጋራችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ከምድር እስከ ህዋ …
#SSGI

❤5😁1
ከ800 በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከዓለም አቀፉ “Pathways to Space” የስፔስ ሳይንስ ፕሮግራም ተመረቁ።
የወደፊቱ የአፍሪካ ስፔስ ተመራማሪዎች STEM አካደሚ (FASESA) ከዓለም አቀፉ የኤሮስፔስ ኩባንያ ቦይንግ ጋር በመተባበር የሚያካሂደው 3ኛው ዓመታዊ "Pathways to Space" መርሃ-ግብር 832 ኢትዮጵያንን ጨምሮ 2,626 አፍሪካውያን ተማሪዎችን አስመርቋል።
ለአምስት ወራት በተካሄደው በዚህ የስልጠና መርሃ-ግብር ተማሪዎቹ በኤስትሮኖቲክስ፣ ሲስተምስ ኢንጂነሪንግ፤ በማቴሪያል ሳይንስዐ
ላይ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ በከፍተኛ ከፍታ ላይ በሚለቀቁ ባሉኖች አማካኝነት የተግባር ልምድ እና የመረጃ ትንተና ክህሎት አዳብረዋል ተብሏል።
ተመራቂ ተማሪዎቹ ፦
🇿🇦 ከደቡብ አፍሪካ 1,313 ተማሪዎች፣
🇪🇹 ከኢትዮጵያ 832 ተማሪዎች፣
🇳🇬 ከናይጄሪያ 431 ተማሪዎች፣
🇰🇪 ከኬንያ 50 ተማሪዎች የተወጣጡበት ነው።
ተማሪዎቹ ከናሳ (NASA) ጆንሰን ስፔስ ሴንተር፣ ከፋይናል ፍሮንቲየር ዲዛይን እና ከተለያዩ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ የስፔስ ባለሙያዎች እና የቀድሞ ኤስትሮኖቶች ጋር በቪዲዮ የመገናኘት እድል አግኝተዋል።
ፕሮግራሙ እ.ኤ.አ. በ2024 ከተጀመረ ወዲህ በአጠቃላይ ወደ 3,500 ለሚጠጉ አፍሪካውያን ተማሪዎች ተዳራሽ ማድረግ ችሏል።

Forwarded from የደ/ኢ/ክ/መ/ኢኖቨሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ,ና ምርምር እና የፈጠራ አቅም ግምባታ ዳይሮክቶሬት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተለያዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡና በሳይንስና በሂሳብ ትምህርቶች እንዲሁም በፈጠራ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች የተዘጋጀ ስልጠና በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ ነው
አርባምንጭ፣ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ከጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በክልሉ ካሉ ከተለያዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች በአስትሮኖሚ፣ በሮኬት ሳይንስ፣ በድሮን (UAV)፣ በጂአይኤስ እና በሳተላይት ሲስተም ዙሪያ ያዘጋጀውን ለ45 ቀናት የሚቆይ የንድፈ-ሐሳብ እና የተግባር ስልጠና በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ መስጠት ጀምሯል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ምክትል ኃላፊና ኢኖቬሽንና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ህብረት አታራ እንደገለፁት የስልጣናው ዋና ዓላማ በሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶችና በፈጠራ ልዩ ተስጥኦ ያላቸውን ልጆች በማገዝ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ ነው።
በሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች የላቀ ውጤት ያመጡና የፈጣራ ተስጥኦ ያላቸው እነዚህ ተማሪዎችን በማቃት በቀጣይ በአለም አቀፍ መድረኮች ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚያስጠሩ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ኃላፊው አስገንዝበዋል።
ይህንንም ግብ ለማሳካት የተለያዩ አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንዳለባቸው ያስገነዘቡት ኃላፊው በዚህ ረገድ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎችም ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ቀደም ሲል በየትምህርት ቤቶቻቸው በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የሚያውቁትን በዩኒቨርስቲው ባላቸው ቆይታ በተግባር በማጠናከር ለቀጣይ ሃገር እድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ዶ/ር ህብረት አሳስበዋል።
በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስቴም/STEM/ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ብንያም ወንደዓለም በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው ከምርምርና ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን በተለያዩ ዘርፎች ለአካባቢው ህብረተሰብ የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ዛሬ በክልሉ ካሉ ከተለያዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች መሰጠት የተጀመረው ስልጠናም የዚሁ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት አንዱ አካል እንደሆነ አስተባባሪው አስረድተዋል።
በቀጣይም ተማሪዎቹ ያላቸውን የንድፈ ሃሳብና የተግባር ዕውቀት ይበልጥ እንዲያሳድጉ በኢትዮጵያ ካሉ ከ8ቱ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወጣ ዶ/ር ብንያም ተናግረዋል።
የጋሞ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ታመነ ተስፋዬ ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ለማስጠታቅ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ተማሪዎች ያላቸውን ተሰጥኦ ይበልጥ እንዲያሳድጉ ዞኑም የበኩል ጥረት እንደሚያደርግ የተናገሩት አቶ ታመነ ሠልጣኞች ያገኙት ዕድል በሚገባ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።
ተመሳሳይ ስልጠና በክልሉ ባሉ በ4ቱም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲም በጋሞ፣ በአርባምንጭ ከተማ፣ በጎፋ፣ በኮንሶ፣ በኮሬና በአሌ ዞኖች ካሉ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡትን ከ40 በላይ ባለተስጥኦ ተማሪዎች ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል።
ዛሬ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው ስልጠና ለቀጣይ 45 ቀናት ያህል በቲዎሪና በተግባር የሚሰጥ ሲሆን በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ፣ የጋሞ ዞንና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል።
በመላኩ ማሞ

❤1👏1