Space Science and Geospatial Institute
1.46K subscribers
5.05K photos
138 videos
21 files
412 links
Download Telegram
ታህሳስ 11 ቀን 2015ዓ.ም
-------------------------
የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የመጀመሪያዋን የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት (ETRSS-1) ወደ ህዋ የመጠቀችበትን 3ኛ አመት አስመልክቶ በብይነመረብ ቻይና ሀገር ከሚገኘው አጋር ድርጅት ጋር ቀኑን በማሰብ ባለፉት ሶስት አመታት የተገኙ ውጤቶችን እና የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ውይይት ተደረገ፡፡
ETRSS_1 የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ሎንግ ማርች 2B በተሰኘ የቻይና መንኮራኩር ወደ ህዋ ከተላኩ ሳተላይቶች አንዷ መሆኗ ይታወሳል።
👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታህሳስ 12 ቀን 2015ዓ.ም
---------------------------
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት እንጦጦ ተራራ ላይ በሚገኝው የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል በግራና ቀኝ 15 ሄክታር የሚሆን የማስፋፊያ መሬት ላይ የዘራው ገብስ ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም የክብር እንግዶች የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች ፣ሰራተኞች እና የአካባቢው አርሶአደሮች በተገኙበት ምርቱን የመሰብሰብ እና ለተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ተግባር ይከናወናል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ አሰፋ እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ ባለፈው ክረምት መሬቱ ፆም እንዳያድር በማሰብ መንግስት በግብርና ምርት እራሳችንን ለመቻል ለያዘው እቅድ የራሳችንን አስትዋጾ ለማበርከት በ15 ሄክታር መሬት ላይ ገብስ ዘርተን ምርቱ የሚሰበሰብበት ወቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሽያል ኢንስቲትዩት ታኅሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም የብሄራዊ የስፔስ እና ጂአይኤስ ቀንን በአገርአቀፋዊ የምክክር መድረክ እና በዲጅታል ኤግዚብሽን በሳይንስ ሙዝየም ያከብራል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
SSGI’S SPACE AND GIS DAY: SCIENCE MUSEUM: DECEMBER 26TH: 5 DAYS TO GO

SPACE FUN FACT OF THE DAY: The first ever picture from the outer space has been taken 70 years on ago on October, 24th, 1946 with a camera installed on a rocket that launched from White Sands Missile Range, New Mexico

GEOSPATIAL FUN FACT OF THE DAY: The first aerial images were captured using hot air balloons, kites, and even pigeons. In 1909 the first aerial photographs from an airplane were taken by Wilbur Wright.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
SSGI’S SPACE AND GIS DAY: SCIENCE MUSEUM : DECEMBER 26TH: 3 DAYS TO GO
SPACE FUN FACT OF THE DAY: Astronauts grow taller in space. As of 2021, more than 600 people have been in space.
GEOSPATIAL FUN FACT OF THE DAY: The first attempts to use light as a means of measuring distance was in the 1930s. Scientists used searchlights to measure the atmosphere and the height of clouds.
👍2
ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም
---------------------------------
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ለቱሪዝም ሚኒስቴር ያበለጸገውን “ቪዚት ኢትዮጵያ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና የአድሚኒስትሬተር ዳሽቦርድ ለሚኒስቴር መስራቤቱ በማበርከት በዛሬው እለት አጋር ተቋሟት በተገኙበት በይፋ አስመርቋል፡፡ ይህ መተግበሪያ የሃገር ውስጥ እና የውጭ የቋንቋ አማራጮችን በመያዝ ለአንድሮይድ እና iOS ስልክ ተጠቃሚዎች የሚሰራ ነው፡፡
ይህ መተግበሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን በGPS መገኛቸው ፣ በአቅራቢያ የሚገኙ ሰርቪስ ሰጭ ተቋማትን፣ የግብይት ቦታዎችን፣ የአካበቢው የአየር ንብረት ሁኔታ የሚያሳይ እና ሌሎች አስፈላጊ የቱሪስት ጥቅሎችን ያካተተ መተግበሪያ ነው፡፡ በተጨማሪም ጎብኝዎች የሚጎበኟቸውን ቦታዎች ለሌሎች ልምድን ለማካፈል እንዲረዳ እና ሌሎችም ቦታውን ሂደው እንዲጎበኙ ለማበረታታት “Experience sharing ” የሚል ጎብኝዎች ወይም ተጠቃሚዎች ስለጎበኟቸው ስፍራዎች ሃሳቦችን፣ ምስሎችን እና ቪዲዮችን የሚለዋወጡበት ፊቸር የያዘ ነው፡፡
በዚህ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) እየተጠቀሙ የተለያዩ ቦታዎችን ሲጎበኙ፣ የጎበኙትንም ስፍራ ለሌሎች ሲያካፍሉ፣እንዲሁም ሌሎች ያጋሩትን “ላይክ እና ሼር” በሚያደርጉበት ወቅት የሽልማት ነጥቦችን መሰብሰብ ያስችላል፡፡
የሞባይል መተግበሪያውን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፡፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.essti.visitethiopia
👍3
FM 96.3
👍1
Forwarded from Eyasu Mesele
17.pdf
287.4 KB
Audio
አስትሮኖሚ ሬዲዮ ፕሮግራም፥ ስለ ሰማይ አካላት (celestial bodies - ዶ/ር ገመቹ ሙለታ)
ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት ለአቅመ ደካሞች የአደሰውን ቤቶች ርክክብ አከናወነ
ⓈⓈGⒾ🌎🌏🌍ⓈⓈGⒾ🌎🌏🌍
ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት በተጓዳኝ የኢንስትቲዩቱን ባለሙያዎች እና አመራሮች በማስተባበር ማህበራዊ እና ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ከሚያከናውናቸው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አንዱ የሆነውን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጫንጮ ከተማ አስተዳደር የአምስት አቅመ ደካማ አባወራ ቤት ማደስ አና ማዕድ ማጋራት ሲሆን በዛሬው ዕለት የከተማው አመራሮች፣ ነዋሪዎች፣ የገዳ አባቶች፣ የኢስትቲዩቱ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ታድስው የተጠናቀቁትን የሁለት አቅመ ደካማ አባወራ ቤቶችን ርክክብ አና የማዕድ ማጋራት ተግባራትን አከናውኗል።

በዚህ ዝግጅት ላይ መልክት ያስተላለፉት የስሳጂኢ ዋና የዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ አንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ ከቆመላቸው ተግባራት በተጨማሪ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በተግባር እየተወጣ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች የጀመርናቸውን ማህበራዊ አገልግሎት በአግባቡ እደሚወጡ በመግለፅ ሌሎች አቅም ያላቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ይህን ተግባር እንደመነሻ ወስደው የመደጋገፍ ባህላቸውን በማሳደግ በአከባቢው ለሚኖሩ አቅመ ደካሞች እገዛ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ በማስተላለፍ ለተግባራዊነቱ አስተዋጽኦ ላደረጉትን ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጫንጮ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የገዳ አባቶች፣ ድጋፍ የተደረገላቸው አቅመ ደካሞች እና የከተማው ነዋሪዎች ኢንስቲትዩት ላደረገው ድጋፍ ከፍተኝ የሆነ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
1👍1