Space Science and Geospatial Institute
1.46K subscribers
5.05K photos
138 videos
21 files
412 links
Download Telegram
👏1
Audio
ከምድር እስከ ህዋ… ሬዲዮ ፕሮግራም ታህሳስ 2ቀን 2015 ዓ.ም
👏1
ታህሳስ 5ቀን 2015ዓ.ም
------------------
ኢንስቲትዩቱ ጥራቱን የጠበቀ ቶፖግራፊክ ካርታ አምርቶ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ የሚያስችል ስልጠና መስጠት ጀመረ
----------------------------

ኢንስቲትዩቱ ለካርታ ስራ መሪ ስራአስፈፃሚ 24 ያህል ለሚሆኑ ባለሞያዎች ጥራቱን የጠበቀ ቶፖግራፊክ ካርታ አምርቶ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ የሚያስችል ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
ስልጠናውን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡን የስፔስና ጂኦስፓሻል ስታንደርዳይዜሽን መሪ ስራአስፈፃሚ አቶ እስራኤል ገብረመስቀል እንዳሉት ስልጠናው እርስ በርስ ልምድ ከመለዋወጥ ባለፈ በክፍሉ የሚገኙ ባለሞያዎች በቀጣይ ጥራቱን የጠበቀ ቶፖግራፊክ ካርታ አምርቶ ለተጠቃሚዎች ከማቅረብ አኳያ ትልቅ አቅም ይፈጥርላቸዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
👏1
ታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም
---------------------------------
የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የመጀመሪያዋን የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት (ETRSS-1) ወደ ህዋ የመጠቀችበትን ታህሳስ 10 ቀንን እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ የሚከበረውን የጂኦግራፊክ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (GIS) ቀን በአንድላይ በማጣመር በአንድ በኩል “ETRSS-1 እናመሰግናለን” በተጓዳኝ “የጂኦስፓሻል ኢንደስትሪ በኢትዮጵያ” በሚል እሳቤ ታህሳስ 17 ቀን 2015ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች እና የኢንስቲትዩቱ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም በተለያዩ ኩነቶች በደማቅ ሁኔታ ያከብራል፡፡
👍2👏1
Audio
ከምድር እስከ ህዋ… የታህሳስ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የሬዲዮ ፕሮግራም
የስፔስና የጂኦግራፊክ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (GIS) ቀን አስመልክቶ የተዘጋጀ ፕሮግራም ያድምጡት
👏1
ታህሳስ 11 ቀን 2015ዓ.ም
-------------------------
የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የመጀመሪያዋን የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት (ETRSS-1) ወደ ህዋ የመጠቀችበትን 3ኛ አመት አስመልክቶ በብይነመረብ ቻይና ሀገር ከሚገኘው አጋር ድርጅት ጋር ቀኑን በማሰብ ባለፉት ሶስት አመታት የተገኙ ውጤቶችን እና የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ውይይት ተደረገ፡፡
ETRSS_1 የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ሎንግ ማርች 2B በተሰኘ የቻይና መንኮራኩር ወደ ህዋ ከተላኩ ሳተላይቶች አንዷ መሆኗ ይታወሳል።
👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታህሳስ 12 ቀን 2015ዓ.ም
---------------------------
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት እንጦጦ ተራራ ላይ በሚገኝው የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል በግራና ቀኝ 15 ሄክታር የሚሆን የማስፋፊያ መሬት ላይ የዘራው ገብስ ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም የክብር እንግዶች የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች ፣ሰራተኞች እና የአካባቢው አርሶአደሮች በተገኙበት ምርቱን የመሰብሰብ እና ለተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ተግባር ይከናወናል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ አሰፋ እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ ባለፈው ክረምት መሬቱ ፆም እንዳያድር በማሰብ መንግስት በግብርና ምርት እራሳችንን ለመቻል ለያዘው እቅድ የራሳችንን አስትዋጾ ለማበርከት በ15 ሄክታር መሬት ላይ ገብስ ዘርተን ምርቱ የሚሰበሰብበት ወቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሽያል ኢንስቲትዩት ታኅሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም የብሄራዊ የስፔስ እና ጂአይኤስ ቀንን በአገርአቀፋዊ የምክክር መድረክ እና በዲጅታል ኤግዚብሽን በሳይንስ ሙዝየም ያከብራል።