Space Science and Geospatial Institute
1.46K subscribers
5.05K photos
138 videos
21 files
412 links
Download Telegram
Lists_of_Msc_PhD_Applicants_Selected_Enterance_Exam.pdf
33.5 KB
Space Science and Geospatial Institute
Lists of M.Sc. and PhD applicants selected for Entrance Exam for 2022/23 Academic Year
👍2
Accepted_PhD_Msc_Candidate_Post.pdf
177.8 KB
List of Accepted MSc and PhD Applicants in 2022/23
🔥2
Audio
እሁድ ማለዳ ጥቅምት 13/2/15 ዓ.ም አየር ላይ የዋለው የኢንስቲትዩቱ የሬዲዮ ፕሮግራም
🏆2👍1
በመሬት መሰረተ ልማት መረጃ ስርአት ማዘመን ዙሪያ ለ20 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
( ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩቱ )
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ እየተተገበረ ያለውን የመሬት መሰረተ ልማት መረጃ የማዘመን ፕሮጀክቶች፣ በሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይት መረጃዎች እና በጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ለማስቻል የሚረዳ ስልጠና፣ ከመስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩቱ ሲሰጥ ቆይቷል።

በተለይ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ አስፈላጊና አጅግ ጠቃሚ የሆነው ይህ ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የምስጋና፣ ለሰልጣኞች የሥራ መመሪያ እና የምስክር ወረቀት የመስጠት መርሃ ግብር በማካሄድ ተጠናቋል።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጉታ ላቾሬ እንደገለፁት፤ በክልሉ በርካታ ግዙፍ የልማት ሥራዎች እንደሚሰሩና ነገር ግን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ የመሬት አሰተዳደር መሰረተ ልማቶችን መንከባከብ፣ ከጥፋት መጠበቅና በቀጣይነት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ብሎም አንዳቸው ከሌላይኛው ጋር ተጋግዞ በመስራት፤ በክልሉ የመሬት አስተዳደር የመሰረተ ልማትን የማዘመን ስርዓት ላይ አመርቂ ውጤት ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የቢሮ ሀላፊ አክለውም ስልጠናውን የወሰዳችሁ የቢሮ ባለሙያዎችም በክልሉ በሚሰሩ የመሬት መሰረተ ልማት ሥራዎችን በማዘመን ሂደት ላይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በወሰዳችሁት መሰረታዊ ስልጠና እውቀት ልክ፣ እንደ አንቂ ደውል ሆናችሁ በመንቀሳቀስና ውጤታማ ሥራ በመስራት፤ በክልሉ የመሬት አስተዳደር መሰረተ ልማት መረጃ የማዘመን ሥራዎች ላይ በጋራ ውጤታማ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባችኋል በማለት አሳስበዋል፡፡

በመድረኩም ለ20 ቀናት ስልጠናውን ሲሰጥ የቆየው የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ እንደተናገሩት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ መሬት ቢሮ ጋር በቀጣይ በትብብር መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ እና አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍ በማድረግ በዘርፉ የሚታዩትን ተግዳሮቶች ለመፍታት በትብብር ኢንስቲትዩታቸው እንደሚስራ በመግለፅ ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደረጉትን የክልሉ መሬት ቢሮ አባላት እና የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎችን አመስግነዋል፡፡

ስልጠናውን የወሰዱ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች እደገለፁት በዘርፉ ከጠበቁት በላይ ግንዛቤ እዳገኙ እና ለቀጣይ ስራቸው መነሳሳት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።
👏1
ከኢንስቲትዩታችን የተወገዱ የተለያዩ የቢሮ ቁሶች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ለጫንጮ ከተማ አስተዳደር የኢንስቲትዩታችን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ በተገኑበት ተበርክቷል።

የጫንጮ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፤ ሥራተኞች፤ የአከባቢው የገዳ አቦቶች እና ከተለያዩ የማህበረሰብ አካላት በተገኙበት ርክክብ የተደረገ ሲሆን ሰለተበረከተላቸው ቁሶች በአከባቢው ወግና ባህል መሠረት ለኢንስትቲዩታችን ዋና ዳይሬክተር የክብር ጋቢ በማልበስ ፍቅራቸውን እና ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
👍1👏1