Space Science and Geospatial Institute
1.46K subscribers
5.05K photos
138 videos
21 files
412 links
Download Telegram
ለኢንስቲትዩቱ ባለሞያዎች በጂኦዴቲክ ዳተም፣ በጂኦዴቲክ ኔትዎርክ እና GNSS ዳታ ፕሮሰሲንግ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
----------------------------------

ኢንስቲትዩቱ ከሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከጂኦዴሲ፣ከምድር ቅየሳ ፣ ከጂኦዴሲና ጂኦዳይናሚክስ ዳይሬክቶሬቶች ለተወጣጡ አስራ ስምንት ያህል የዘርፉ ባለሙያዎች በጂኦዴቲክ ኔትወርክ፣ GNSS ዳታ ፕሮሰሲንግ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ዶ/ር ቱሉ በሻ እንደተናገሩት ለኢንስቲትዩቱ ባለሞያዎች የተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ከዚህ ቀደም ያለውን ቴክንካል ክፍተቶችን ለመሙላት ጉልህ ሚና ይኖረዋል በማለት አሁን የተገኘው ዕውቀት እና ክህሎት እየተባዛ መሄድ አለበት በማለት ሠልጣኞች ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር ላይ በማዋል ሁል ጊዜ ማዘመን ይጠበቅባቸዋል በማለት ስልጠናውን ለሰጠው ለአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምስጋና አቅርበዋል።

በስልጠናው አስመልክተው የኢንስቲትዩቱ ጂኦዴሲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ገረመው እንደተናገሩት የተለያዩ የጆኦስፓሻል መረጃዎችን ለማምረት መሠረታዊ የመረጃ ግበዓት ሆኖ የሚያገለግለው የጆኦዴቲክ የአገድመት እና የከፍታ መረጃ ነው። ይህ የሁሉ መሠረት የሆነውን የጂኦዴቲክ መረጃን የማምረት ሂደት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንና መረጃ የመተንተን ዜደዎችን በመጠቀም እንዲተገበር ለማስቻል የሚረዳ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለተቋሙ ባለሙያዎች መሰጠቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ሲሉ ገልፀው የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አሰልጣኞች በስልጠና ወቅት ዘርፉን ለማሳደግ ላሳዩት ትልቅ አገራዊ ስሜትና ቁጭት ምስጋናቸውን አቅርበው በስልጠናው በርካታ ዕውቀትና ክህሎት የተገኘበት መሆኑን በመግለጽ ሰልጣኞችም በቀጣይነት ያለቸውን ዕውቀትና ክህሎትን አውጥተው እየተጠቀሙ አዳዲስ ልምድና ዕውቀት እንዲቀስሙ አሳስበዋል።

የጂኦሰፓሻል ኢኖቬሽንና አናሊቲክስ ማዕከል ኃላፊ አቶ ሙሉለም የሺጥላ በበኩላቸው ይህ ስልጠና የተዘጋጀው የተለያዩ ሶፍትዌሮችን ማስተዋወቅና የጂኦስፓሻል ኢንዲስትሪው ላይ ምን አይነት ነገሮች አሉ የሚለውን ለማስተዋወቅ ብቻ የተዘጋጀ አይደለም ያሉት አቶ ሙሉአለም የ10 ዓመቱን የጂኦዴቲክ መሠረተ ልማት በማዘመን በዕውቀትና በክህሎት ላይ ተመስርቶ ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን በመግለጽ የዕውቀት ሽግግር መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። ስፔስ ሳይንና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት
ከምድር እስስከ ህዋ …

የስፔስ ሳይንና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት የማህበራዊ ትስስር ገጾች

Twitter: https://twitter.com/ssgi2022
Facebook: https://www.facebook.com/spacegeospatial/ LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/ssgi-37b48623a
Telegram: https://t.me/spacegeospatial
YouTube: https://www.youtube.com/.../UCiFzlJraHEdMPH6FikA.../featured
👍2
Happening now: Training on Basic Gender Concept and Gender Mainstreaming for SSGI Management Members

Organized: Womens, Children & Youth Affairs Directorat

Venue: Bin International Hotel (03-04 September 2022)
Lists_of_Msc_PhD_Applicants_Selected_Enterance_Exam.pdf
33.5 KB
Space Science and Geospatial Institute
Lists of M.Sc. and PhD applicants selected for Entrance Exam for 2022/23 Academic Year
👍2
Accepted_PhD_Msc_Candidate_Post.pdf
177.8 KB
List of Accepted MSc and PhD Applicants in 2022/23
🔥2
Audio
እሁድ ማለዳ ጥቅምት 13/2/15 ዓ.ም አየር ላይ የዋለው የኢንስቲትዩቱ የሬዲዮ ፕሮግራም
🏆2👍1
በመሬት መሰረተ ልማት መረጃ ስርአት ማዘመን ዙሪያ ለ20 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
( ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩቱ )
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ እየተተገበረ ያለውን የመሬት መሰረተ ልማት መረጃ የማዘመን ፕሮጀክቶች፣ በሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይት መረጃዎች እና በጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ለማስቻል የሚረዳ ስልጠና፣ ከመስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩቱ ሲሰጥ ቆይቷል።

በተለይ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ አስፈላጊና አጅግ ጠቃሚ የሆነው ይህ ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የምስጋና፣ ለሰልጣኞች የሥራ መመሪያ እና የምስክር ወረቀት የመስጠት መርሃ ግብር በማካሄድ ተጠናቋል።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጉታ ላቾሬ እንደገለፁት፤ በክልሉ በርካታ ግዙፍ የልማት ሥራዎች እንደሚሰሩና ነገር ግን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ የመሬት አሰተዳደር መሰረተ ልማቶችን መንከባከብ፣ ከጥፋት መጠበቅና በቀጣይነት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ብሎም አንዳቸው ከሌላይኛው ጋር ተጋግዞ በመስራት፤ በክልሉ የመሬት አስተዳደር የመሰረተ ልማትን የማዘመን ስርዓት ላይ አመርቂ ውጤት ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የቢሮ ሀላፊ አክለውም ስልጠናውን የወሰዳችሁ የቢሮ ባለሙያዎችም በክልሉ በሚሰሩ የመሬት መሰረተ ልማት ሥራዎችን በማዘመን ሂደት ላይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በወሰዳችሁት መሰረታዊ ስልጠና እውቀት ልክ፣ እንደ አንቂ ደውል ሆናችሁ በመንቀሳቀስና ውጤታማ ሥራ በመስራት፤ በክልሉ የመሬት አስተዳደር መሰረተ ልማት መረጃ የማዘመን ሥራዎች ላይ በጋራ ውጤታማ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባችኋል በማለት አሳስበዋል፡፡

በመድረኩም ለ20 ቀናት ስልጠናውን ሲሰጥ የቆየው የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ እንደተናገሩት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ መሬት ቢሮ ጋር በቀጣይ በትብብር መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ እና አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍ በማድረግ በዘርፉ የሚታዩትን ተግዳሮቶች ለመፍታት በትብብር ኢንስቲትዩታቸው እንደሚስራ በመግለፅ ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደረጉትን የክልሉ መሬት ቢሮ አባላት እና የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎችን አመስግነዋል፡፡

ስልጠናውን የወሰዱ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች እደገለፁት በዘርፉ ከጠበቁት በላይ ግንዛቤ እዳገኙ እና ለቀጣይ ስራቸው መነሳሳት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።
👏1