ፕሮታጎራስ (Protagoras) vs ዮትለስ (Euathlus)
ቅድመ ሶቅራጥስ ግሪክ ነው አሉ። የሶፊስቶች ቁንጮ በመባል የሚታወቀው ፕሮታጎራስ (Protagoras)፣ ዮትለስን (Euathlus) ጎበዝ ጠበቃ እንዲሆን የንግግር ጥበብ (rhetoric) እንዲያሰለጥነው ውል ያስራሉ። ውላቸው ደግሞ ዮትለስ የስልጠናው ግማሹን ክፍያ በቅድሚያ ይከፍልና ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ደግሞ ዮትለስ የመጀመርያውን የችሎት ክርክር ካሸነፈ እንዲከፍል ነው። ሆኖም ዮትለስ በስልጠና ያገኘውን ክህሎት በተግባር የሚፈትሽበት ጊዜ እያጓተተው በመሄዱ፤ ስለ ዝናው እና ስለ ቀሪው ክፍያ ያሳሰበው ፕሮታጎራስ ዮትለስን ሊከሰው ወሰነ። በችሎት ፊትም እንዲህ ሲል ተከራከረ:-
ዮትለስ ቀሪውን ክፍያ ሊከፍለኝ እንደማይገባው ነው የሚከራከረው። ይሄ ግን የማይሆን ወለፈንድ ነው። አስቡት እስኪ ዮትለስ ይሄን የችሎት ክርክር አሸነፈኝ እንበል፤ ይህ ደግሞ ከስልጠናው በኋላ ያሸነፈው የመጀመርያው የችሎት ክርክሩ ስለሆነ በውላችን መሰረት ቀሪውን ክፍያ ሊከፍለኝ ይገባል ማለት ነው። በሌላ በኩል እኔ ካሸነፍኩት ደግሞ በችሎቱ ውሳኔ ይከፍለኛል ማለት ነው። ስለዚህ ዮትለስ ያለው አማራጭ ወይ ያሸንፋል ወይ ይሸነፋል ስለሆነ ሊከፍለኝ ይገባል።
ዮትለስ ሆዬ የንግግር ጥበቡን ከፕሮታጎራስ በደንብ ተምሮ ኑሯል እንዲህ ሲል ተከራከረ:-
ፕሮታጎራስ ልከፍለው እንደሚገባ ይከራከራል፤ ግን ይሄኛው ነው ወለፈንዱ መከራከርያ። አስቡት እስኪ ፕሮታጎራስ ይሄን የችሎት ክርክር አሸነፈኝ እንበል፤ ከስልጠናው በኋላ ያደረግኩት የመጀመርያው ክርክሬ ተሸነፍኩ ማለትም አይደል? ስለዚህ ልከፍለው አይገባም ማለት ነው። በሌላ በኩል እኔ ካሸነፍኩት ደግሞ በችሎቱ ውሳኔ አልከፍለውም ማለት ነው። ስለዚህ ፕሮታጎራስ ያለው አማራጭ ወይ ያሸንፋል ወይ ይሸነፋል ስለሆነ ልከፍለው አይገባኝም።
ይህ The paradox of the court በመባል የሚታወቅ ክርክር ነው። ለምን ትዝ አለኝ ግን😁
በዮናስ ታደሰ በርሄ

👍11❤3👏1
Forwarded from አረቦን
እነሆ አብዮት የተባለው ሁነት ከተከናወነ ድፍን ሃምሳ አመት ሞላው። ይህ ሁነት ሃገራችንን ከስሯ የነቀለና ፥ ከማንነቷ የመነገለ የመሆኑን ያህል በሃገራችን ውስጥ ያሉ ተዋስዖዎች የትኩረት ማዕከል ሲሆን አይስተዋልም። የተዋስዖ ርእስ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ የአቢዮቱን መቅድማዊ እሳቤዎች (presuppositions) የተቀበለና በዚያው ሜዳ የሚደረግ ነው። አብዮቱ የተቀበላቸውን ማርክሲስታዊ እሳቤዎችና መዳረሻዎች ተቀብሎ የሚደረግ ተዋስዖ ምን ረብህ ይኖረዋል? ማርክሲዝምና ዲያሌክቲካዊ ቁስ አካላዊነት ስሁት ከሆኑ ከኢህአፓና ከመኢሶን የቱ እንደሚሻል መከራከር ዋጋ ቢስ ከመሆን ውጭ ምን ምርጫ ይኖረዋል? ከተመሳሳይ ርእዮተ ዐለም የተወለዱና ተመሳሳይ ግብ የሚጋሩ ነገር ግን በአካሄድ የተለያዩ አካላትን ማወዳደርና ማነፃፀር የዝንጀሮ ቆንጆ የማወዳደር ያህል አይረቤ ልፋት ነው። ከአብዮቱ ማዕቀፍ ወጥተን ማሰብ መጀመር ካልቻልን ካለንበት አዘቅት ልንወጣ አይቻለንም።
ኤማሁሳዊው በርናባስ ሽፈራው የአብዮቱን መሰረታዊ መነሻዎች የሚያጠይቅ እጅግ ግሩም መጣጥፍ ይዞልን መጥቷል። አቢዮቱ ላይ ከተከተቡ መጣጥፎች እጅግ ጥልቅና ረቂቅ የሆነው ጽሑፍ ነው ማለት እችላለሁ። በኤማሁስ ፕሬስ የምናቀርባቸውን ጽሑፎች በዚህ masterpiece ጀምረናል። መጣጥፉ ሦስት ክፍሎች ያሉት ነው። የመጀመርያውን ክፍል እነሆ።
https://emmauspresset.com/%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%88%ad%e1%88%b5%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%ab%e1%88%8d%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%88%e1%88%b5%e1%8a%95%e1%89%a0%e1%89%b5-%e1%8a%a2%e1%8b%ae%e1%89%a4%e1%88%8d%e1%8b%a9/

👍9❤2
" ... The Philosophy of the Isolated " I " The Gnoseological Metaphysical individualism emanates from the unfinished science that being and knowing are disconnected, incompatible, and their connection a statement of dogmatism, prejudice. "
(Gasan Gusejnov : The Linguistic Aporia of Aleksei Losev's Mystical Personalism, PP 8 - Quote from Aleksei Losev)

👍1
" The depressive-narcissistic subject has no capacity for conclusion. Yet without a conclusion, everything dissolves and becomes a blur. It is not by chance that indecision, or inconclusiveness (Unentschlossenheit)—the inability to arrive at a decision or finish anything (die Unfähigkeit zum Ent-Schluss)—constitutes a symptom of depression. Depression characterizes our age; thanks to excessive openness and unlimitedness, the capacity to close and conclude has disappeared. "
(Byung Chul Han, The Agony of Eros ; as quoted from The Article " The Narcissification of the Self " By Treydon Lunot)

እውነታ(Reality) እና ምናብ(Fantasy) በአሁናዊ ሕላዌያችን በጨረፍታ ሲታይ ...
በጥንት ግሪክ ፍልስፍና ገናና በሆነው ፕሌቶ ዲበ አካላዊ(Metaphysics) ትንተና መሠረት The world of Being and The World of Becoming የሚለው አለው ። በዚህ አሁናዊ ዓለም ላይ የምናያቸው ማንኛቸውም ምንነቶች(World of Becoming) በላይኛው ዓለም(World of Being(Forms)) እውነተኛ ማንነት አላቸው ። በመሆኑም በዚህ ምድር ያለው ማንነታቸው ምናባዊ እንጂ እውነተኛ አይደለም ። እውነተኛው ማንነታዊ እውነታቸው በላይኛው ዓለም እውነታ ውስጥ ያለ ነው ።
በዘመናዊው ፍልስፍና ውስጥ በ18ኛው መ.ክ.ዘ የተነሣው እና በፍልስፍናው ልዩ የሆነ ታላቅ አንቱታን ያተረፈው ጀርመናዊው ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት በነገረ እውቀት(Epistemology) ትንተናው ውስጥ የፕሌቶን ሀሳብ ትይዩ በሆነ መልኩ ያስቀምጣል ። ይኸውም በውጪ ያለው በራሱ የሆነው(Neumena - Things in themselves) አለ ። እኛ በአእምሯችን ውስጥ ስለውጪው ነገር የሚፈጠርልን ደግሞ(Phenomena - Things as They Appear to us.) አለ። የመጀመሪያው የፕሌቶን World of Forms ይመስላል ፤ ምክንያቱም እውነታ ለፕሌቶ በላይኛው ያለው ዓለም እንደሆነ እና ነገሮች እውነተኛው ማንነታቸው እና ምንነታቸው በዛ እንዳለ ሁሉ ለካንት ደግሞ ነገሮች በራሳቸው ያላቸው ምንነት እና ማንነት(Neumena) እንዲሁ እውነታነታቸው ስለሆነ ነው ። የፕሌቶ The World of Becoming ደግሞ የእውነታው ዓለም ነጸብራቅ እንጂ ራሱ እውነታው እንዳልሆነ ሁሉ የካንት Phenomena ነገሮች በራሳቸው እንደሆኑት እንደእውነታነታቸው ሳይሆን የእነርሱ ነጸብራቅን የሚወክል በመሆኑ በዚህ የሁለቱ ፈላስፎችን ትይዩዋዊ ዲበ አካላዊ ብሎም ነገረ እውቀታዊ አረዳድ መገንዘብ እንችላለን ።
የዚህ ጽሑፍ መሠረታዊ ዓላማ የፕሌቶን እና የኢማኑኤል ካንትን ፍልስፍና በንጽጽር ማሳየት ሳይሆን የእነርሱ ፍልስፍና በዘመናችን በሕይወታችን የተገለጠበትን መንገድ በጥቂቱ መጠቆም ብቻ ነው ።
ከላይ ያመጣነውን የሁለቱን ፈላስፎች ሀሳብ እስኪ በምንኖረው ሕይወት(ሕልውናችን) ውስጥ እንመልከተው - በፕሌቶ World of Becoming (በካንት Phenomena ዓለም) ውስጥ ነው? ወይስ በፕሌቶ The world of Beings (በኢማኑኤል ካንት Neumena ላይ ነው) ሕልውናችን ያለው ? ...
በእኔ መረዳት ሕልውናችን ያለው ምናባዊ በሆነው ምንነት እና ማንነት ላይ ነው ። የምንኖረው እውነታን(Reality) በሚሳተፍ(Experience) ሕልውናዊ አኗኗር ሳይሆን ምናባዊ(Fantasy) በሞላበት ፣ እውነታ ግን በሚመሥል ስሑት ሕልውና ውስጥ ነው ።
ምናባዊው ሕልውና ላስተዋለው በጠባዩ ምቾትን የሚሰጥ ፣ ስቃይ እና ሕመምን የሚቀንስ ፣ ደስታን ያለማቋረጥ ማጣጣምን የሚያበረታታ አነዋወር ነው ። ይህንንም በተለይ በዚህ ዘመን ማኅበራዊ ሚዲያን መጠቀማችን ውስጥ በሚገባ የምንታዘበው ነገር ነው ። ይኸውም ማኅበራዊ ሚዲያ በመጠቀማችን በማያቋርጥ የደስታ ጫፍ ላይ መድረስን ራሳችንን በማስለመድ በእውኑ ዓለም የሌለ ምናባዊ ቅዠታዊ ሕይወትን(ሕልውናን) ተለማምደናል ። በዚህም ለእውኑ ዓለም ስልቹ ፣ ሐሞተ ፈሰስ ፣ ደካማ ፣ በቀላሉ የሚበገር ፣ ትእግስት የጎደለው ፣ በጥቂት መከራ ተስፋ ቆርጦ ራሱን እስከማጥፋት የሚደርስ ፣ ለውሳኔ የሚቸገር ኑባሬን ገንብተናል ። ከራሳችን ወጥተን ወደ እውናዊው ዓለም ከመሄድና እውነታን ከመሳተፍ ፣ እውነታን በእውነታነቷ ከማግኘት ይልቅ እውነታን በምትመስል በውስጣችን በምንፈጥራት ምናብ እውነታን እናጣለን ።
እውነታ በአንጻሩ ተግባራዊ መውደቅ መነሳትን ፣ ተስፋ አለመቁረጥን ፣ አለመበገርን ፣ ስቃይ እና መከራን ለተሻለ ነገር ሲባል መቀበልን የሚያመጣ እውነታዊ ሕልውናን የሚያጎናጽፍ ኑባሬ ነው ። ሕይወት(ሕልውና) በማኅበራዊ ሚዲያ እንደምናየው አይደለም ። በዚያ እንደምናየው የማይጨበጥ ፣ የማይዳሰስ ፣ ሀሳባዊ ሳይሆን በተግባር ዕለት ዕለት የሚሳተፉት ፣ የሚጀምሩት ፣ የሚሄዱበትና የሚደርሱበት አጠቃላይ የሰው ልጅ ጉዞ ነው ። ይህን እውነታዊ ሕልውና ታዲያ መቼ ነው መኖር የምንጀምረው ? ...
ሰዎች ወደምናባዊ ሕልውና የሚወስዳቸውን መንገድ ለይተው አውቀው በተቆጣጠሩበት በመጨረሻም በቆረጡበት መጠን ከእውነታ ጋር መገናኘት መሳተፍ ብሎም መኖር ይጀመራሉ ። ለምናብ በሞቱበት መጠን ለእውነታ ሕያው ይሆናሉ ።
በአጠቃላይ ምናባዊ ሕልውና በተለያዩ ምክንያቶች(ማኅበራዊ ሚዲያ በእኔ መረዳት ዋናው ምክንያት ነው።) እውነታዊ ሕልውና ባላቸው ሰዎች ላይ የሚፈጠር ኑባሬ ቢሆንም ሰዎች በራሳቸው እውነታ እንደመሆናቸው እውነታዊ ሕልውና ብቻ የሚያስፈልጋቸው እንዲሁም የሚጠቅማቸው ነው ። ይህን እውናዊ ሕልውና በኖሩበት መጠን ደግሞ ምናባዊው ኑባሬ የሚቆጣጠሩት ገፋ ካለም የሚቆርጡት የሚተዉት ነው ። ከምናብ ወደእውነታ እንምጣ !

👍14❤4🔥2
Interviewer : " What is Philosophy ? "
Lord Bertrand Russell :
" Well that is a very controversial question. I think no two Philosophers will give you the same answer. My own view would be that Philosophy consists of speculations about matters where exact knowledge is not yet possible. ''
(An Interview with B. Russell)

👍12❤2
Philosophy Now - Issue 168, June/July 2025
Philosophy Now is a lively and readable magazine for everyone interested in ideas. It isn't afraid to tackle all the major questions of life, the universe and everything.
Published every 2 months, it tries to corrupt innocent citizens by convincing them that philosophy can be exciting, worthwhile and comprehensible, and also to provide some enjoyable reading matter for those already ensnared by the muse, such as philosophy students and academics.

❤3
Philosophy Now - August/September 2025

❤8👍1👏1
" The whole history of recent times in relation to science and technology shows that if you plant the seed of applied science and technology , it proceeds to grow and grows according to the laws of it's own being and the laws of it's being arenot necessarily the same as our being ; hence many people in societies sense that man is being subjected to his own inventions , that he is now the victim of his own technology, the victim of his own applied science. Instead of being in control of it.
The development of recent social and scientific history has created a world in which man seems to be made for technology rather than the other way around. We have to start to think about this problem very seriously and see how we could reestablish control over our own inventions. "
(Aldous Huxley - 1894 - 1963 G.C)

❤2👍1