Watch "Richard Rorty on Language #philosophy #rorty #postmodernism #epistemology" on YouTube
https://youtube.com/shorts/S-tLpr3zgH0?si=4374ml0DwYegCmQ1
https://youtube.com/shorts/S-tLpr3zgH0?si=4374ml0DwYegCmQ1
YouTube
Richard Rorty on Language #philosophy #rorty #epistemology #language
Richard Rorty does his typical anti-authoritarian, neopragmatist spiel in this interview clip from the 1998 Εxαminϵd Life series. #philosophy #rorty #postmod...
ፍልስፍና - Sophia
No.Country.For.Old.Men.2007.@IrisMovies(Telegram).mkv
Taste of Cinema - Movie Reviews and Classic Movie Lists
10 Reasons Why “No Country for Old Men” Is A Nihilistic Masterpiece of American Cinema
“No Country for Old Men”, the 2007 movie directed by Joel and Ethan Coen, can be seen as a diagnosis of a century in which we live. It portrays nihilism
👍1
“Being that can be understood is language.” In this sense, understanding is also always a matter of language, and understanding itself is a matter of interpretation...እንዲል Gadamer ዶ/ር እጓለን ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ተረዳናቸው (ተረጎምናቸውም)።አስተያየታችሁን ከመጠበቅ ጋር።
https://youtu.be/ndoxtHOuP1I?si=TL_u_m8dKBuPcTUQ
https://youtu.be/ndoxtHOuP1I?si=TL_u_m8dKBuPcTUQ
YouTube
"ብፁዓን ንጹሐነ ልብ-ስለክርስቲያን ሥነምግባር መሠረት"በዶ/ር እጓለ | ኤማሁስ ዳሰሳ 1
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
❤2
" ... And I do believe that very many of the statements which we hold for Truth are True. I also believe that very many statements that we hold for Truth are False. And I don't believe there is a criteria to distinguish with certainty between True statements and False statements. And this is the deepest reason for the fallibility of Man. This doesn't mean that we shouldn't try to find Truth And It doesn't mean we shouldn't get nearer and nearer to the Truth , It doesn't even mean we cannot know that we have got nearer to the Truth. We can know we have got nearer to the Truth. But it means that we can never know that we have had reached the Truth. "
[Karl Popper : Karl Popper and John Eccles in Discussion (1971) , Philosophy Overdose]
[Karl Popper : Karl Popper and John Eccles in Discussion (1971) , Philosophy Overdose]
👍5
ፕሮታጎራስ (Protagoras) vs ዮትለስ (Euathlus)
ቅድመ ሶቅራጥስ ግሪክ ነው አሉ። የሶፊስቶች ቁንጮ በመባል የሚታወቀው ፕሮታጎራስ (Protagoras)፣ ዮትለስን (Euathlus) ጎበዝ ጠበቃ እንዲሆን የንግግር ጥበብ (rhetoric) እንዲያሰለጥነው ውል ያስራሉ። ውላቸው ደግሞ ዮትለስ የስልጠናው ግማሹን ክፍያ በቅድሚያ ይከፍልና ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ደግሞ ዮትለስ የመጀመርያውን የችሎት ክርክር ካሸነፈ እንዲከፍል ነው። ሆኖም ዮትለስ በስልጠና ያገኘውን ክህሎት በተግባር የሚፈትሽበት ጊዜ እያጓተተው በመሄዱ፤ ስለ ዝናው እና ስለ ቀሪው ክፍያ ያሳሰበው ፕሮታጎራስ ዮትለስን ሊከሰው ወሰነ። በችሎት ፊትም እንዲህ ሲል ተከራከረ:-
ዮትለስ ቀሪውን ክፍያ ሊከፍለኝ እንደማይገባው ነው የሚከራከረው። ይሄ ግን የማይሆን ወለፈንድ ነው። አስቡት እስኪ ዮትለስ ይሄን የችሎት ክርክር አሸነፈኝ እንበል፤ ይህ ደግሞ ከስልጠናው በኋላ ያሸነፈው የመጀመርያው የችሎት ክርክሩ ስለሆነ በውላችን መሰረት ቀሪውን ክፍያ ሊከፍለኝ ይገባል ማለት ነው። በሌላ በኩል እኔ ካሸነፍኩት ደግሞ በችሎቱ ውሳኔ ይከፍለኛል ማለት ነው። ስለዚህ ዮትለስ ያለው አማራጭ ወይ ያሸንፋል ወይ ይሸነፋል ስለሆነ ሊከፍለኝ ይገባል።
ዮትለስ ሆዬ የንግግር ጥበቡን ከፕሮታጎራስ በደንብ ተምሮ ኑሯል እንዲህ ሲል ተከራከረ:-
ፕሮታጎራስ ልከፍለው እንደሚገባ ይከራከራል፤ ግን ይሄኛው ነው ወለፈንዱ መከራከርያ። አስቡት እስኪ ፕሮታጎራስ ይሄን የችሎት ክርክር አሸነፈኝ እንበል፤ ከስልጠናው በኋላ ያደረግኩት የመጀመርያው ክርክሬ ተሸነፍኩ ማለትም አይደል? ስለዚህ ልከፍለው አይገባም ማለት ነው። በሌላ በኩል እኔ ካሸነፍኩት ደግሞ በችሎቱ ውሳኔ አልከፍለውም ማለት ነው። ስለዚህ ፕሮታጎራስ ያለው አማራጭ ወይ ያሸንፋል ወይ ይሸነፋል ስለሆነ ልከፍለው አይገባኝም።
ይህ The paradox of the court በመባል የሚታወቅ ክርክር ነው። ለምን ትዝ አለኝ ግን😁
በዮናስ ታደሰ በርሄ

👍11❤3👏1
Forwarded from አረቦን
እነሆ አብዮት የተባለው ሁነት ከተከናወነ ድፍን ሃምሳ አመት ሞላው። ይህ ሁነት ሃገራችንን ከስሯ የነቀለና ፥ ከማንነቷ የመነገለ የመሆኑን ያህል በሃገራችን ውስጥ ያሉ ተዋስዖዎች የትኩረት ማዕከል ሲሆን አይስተዋልም። የተዋስዖ ርእስ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ የአቢዮቱን መቅድማዊ እሳቤዎች (presuppositions) የተቀበለና በዚያው ሜዳ የሚደረግ ነው። አብዮቱ የተቀበላቸውን ማርክሲስታዊ እሳቤዎችና መዳረሻዎች ተቀብሎ የሚደረግ ተዋስዖ ምን ረብህ ይኖረዋል? ማርክሲዝምና ዲያሌክቲካዊ ቁስ አካላዊነት ስሁት ከሆኑ ከኢህአፓና ከመኢሶን የቱ እንደሚሻል መከራከር ዋጋ ቢስ ከመሆን ውጭ ምን ምርጫ ይኖረዋል? ከተመሳሳይ ርእዮተ ዐለም የተወለዱና ተመሳሳይ ግብ የሚጋሩ ነገር ግን በአካሄድ የተለያዩ አካላትን ማወዳደርና ማነፃፀር የዝንጀሮ ቆንጆ የማወዳደር ያህል አይረቤ ልፋት ነው። ከአብዮቱ ማዕቀፍ ወጥተን ማሰብ መጀመር ካልቻልን ካለንበት አዘቅት ልንወጣ አይቻለንም።
ኤማሁሳዊው በርናባስ ሽፈራው የአብዮቱን መሰረታዊ መነሻዎች የሚያጠይቅ እጅግ ግሩም መጣጥፍ ይዞልን መጥቷል። አቢዮቱ ላይ ከተከተቡ መጣጥፎች እጅግ ጥልቅና ረቂቅ የሆነው ጽሑፍ ነው ማለት እችላለሁ። በኤማሁስ ፕሬስ የምናቀርባቸውን ጽሑፎች በዚህ masterpiece ጀምረናል። መጣጥፉ ሦስት ክፍሎች ያሉት ነው። የመጀመርያውን ክፍል እነሆ።
https://emmauspresset.com/%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%88%ad%e1%88%b5%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%ab%e1%88%8d%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%88%e1%88%b5%e1%8a%95%e1%89%a0%e1%89%b5-%e1%8a%a2%e1%8b%ae%e1%89%a4%e1%88%8d%e1%8b%a9/

👍9❤2