ፍልስፍና - Sophia
1.65K subscribers
361 photos
1 video
26 files
148 links
Download Telegram
"can always choose, but I ought to know that if I do not choose, I am still choosing.”

— Jean-Paul Sartre
👍52
አንድ ወንድማችን ለጠየቅከው ለነገረ እውቀት (Epistemology) መግቢያ ይሆን ዘንድ እነሆ !
“Being that can be understood is language.” In this sense, understanding is also always a matter of language, and understanding itself is a matter of interpretation...እንዲል Gadamer ዶ/ር እጓለን ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ተረዳናቸው (ተረጎምናቸውም)።አስተያየታችሁን ከመጠበቅ ጋር።

https://youtu.be/ndoxtHOuP1I?si=TL_u_m8dKBuPcTUQ
2
" ... And I do believe that very many of the statements which we hold for Truth are True. I also believe that very many statements that we hold for Truth are False. And I don't believe there is a criteria to distinguish with certainty between True statements and False statements. And this is the deepest reason for the fallibility of Man. This doesn't mean that we shouldn't try to find Truth And It doesn't mean we shouldn't get nearer and nearer to the Truth , It doesn't even mean we cannot know that we have got nearer to the Truth. We can know we have got nearer to the Truth. But it means that we can never know that we have had reached the Truth. "

[Karl Popper : Karl Popper and John Eccles in Discussion (1971) , Philosophy Overdose]
👍5
ፕሮታጎራስ (Protagoras) vs ዮትለስ (Euathlus)

ቅድመ ሶቅራጥስ ግሪክ ነው አሉ። የሶፊስቶች ቁንጮ በመባል የሚታወቀው ፕሮታጎራስ (Protagoras)፣ ዮትለስን (Euathlus) ጎበዝ ጠበቃ እንዲሆን የንግግር ጥበብ (rhetoric) እንዲያሰለጥነው ውል ያስራሉ። ውላቸው ደግሞ ዮትለስ የስልጠናው ግማሹን ክፍያ በቅድሚያ ይከፍልና ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ደግሞ ዮትለስ የመጀመርያውን የችሎት ክርክር ካሸነፈ እንዲከፍል ነው። ሆኖም ዮትለስ በስልጠና ያገኘውን ክህሎት በተግባር የሚፈትሽበት ጊዜ እያጓተተው በመሄዱ፤ ስለ ዝናው እና ስለ ቀሪው ክፍያ ያሳሰበው ፕሮታጎራስ ዮትለስን ሊከሰው ወሰነ። በችሎት ፊትም እንዲህ ሲል ተከራከረ:-

ዮትለስ ቀሪውን ክፍያ ሊከፍለኝ እንደማይገባው ነው የሚከራከረው። ይሄ ግን የማይሆን ወለፈንድ ነው። አስቡት እስኪ ዮትለስ ይሄን የችሎት ክርክር አሸነፈኝ እንበል፤ ይህ ደግሞ ከስልጠናው በኋላ ያሸነፈው የመጀመርያው የችሎት ክርክሩ ስለሆነ በውላችን መሰረት ቀሪውን ክፍያ ሊከፍለኝ ይገባል ማለት ነው። በሌላ በኩል እኔ ካሸነፍኩት ደግሞ በችሎቱ ውሳኔ ይከፍለኛል ማለት ነው። ስለዚህ ዮትለስ ያለው አማራጭ ወይ ያሸንፋል ወይ ይሸነፋል ስለሆነ ሊከፍለኝ ይገባል።

ዮትለስ ሆዬ የንግግር ጥበቡን ከፕሮታጎራስ በደንብ ተምሮ ኑሯል እንዲህ ሲል ተከራከረ:-

ፕሮታጎራስ ልከፍለው እንደሚገባ ይከራከራል፤ ግን ይሄኛው ነው ወለፈንዱ መከራከርያ። አስቡት እስኪ ፕሮታጎራስ ይሄን የችሎት ክርክር አሸነፈኝ እንበል፤ ከስልጠናው በኋላ ያደረግኩት የመጀመርያው ክርክሬ ተሸነፍኩ ማለትም አይደል? ስለዚህ ልከፍለው አይገባም ማለት ነው። በሌላ በኩል እኔ ካሸነፍኩት ደግሞ በችሎቱ ውሳኔ አልከፍለውም ማለት ነው። ስለዚህ ፕሮታጎራስ ያለው አማራጭ ወይ ያሸንፋል ወይ ይሸነፋል ስለሆነ ልከፍለው አይገባኝም።

ይህ The paradox of the court በመባል የሚታወቅ ክርክር ነው። ለምን ትዝ አለኝ ግን😁

በዮናስ ታደሰ በርሄ
👍113👏1