ፍልስፍና - Sophia
1.65K subscribers
361 photos
1 video
26 files
148 links
Download Telegram
" If the truth shall kill them let them die. "

[Immanuel Kant : German Philosopher]
👍21👎1
"የሚኖርለት "ለምን" ያለው ሰው ፣ ማንኛውንም "እንዴት" ይቋቋማል ፡፡"


ኒቼ
የፍልስፍና መግቢያ(introduction to philosophy)
ሐሳባዊነት (Idealism)
በዓለም በጥቅሉ ሐሳብ (አእምሮ) እና መንፈሳዊ ፋይዳዎች (እሴቶች) መሠረታዊ ናቸው የሚል ፍልስፍናዊ አቋም ነው፡፡ በተጨማሪ በዘልማድ የሚታወቀውን ማለት ቁሳዊ ነገሮች ከሐሳብ ወይም ከአእምሮ የተለየ ህልውና አላቸው የሚል እይታንም ይክዳል፡፡
በጆርጅ ቤርክለይ ፍልስፍና ተጽዕኖ ሥር የወደቁ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ፈላስፎች ሐሳባዊነትን ቁስ-አካል ወይም ውጫዊው ዓለም ራሱን ችሎ የቆመ እውነታ አይደለም፤ ወይም ቢያንስ እንደ እውነታ ሊታወቅ አይችልም የሚል አሉታዊ የሜታፊዚክስና የሥነ-ዕውቀት ተአምኖት አድርገው ያቀርቡታ፡፡ይህን ከመሰለ ቁንጽል እይታ ጋር ተያይዞ ሐሳባዊነት ከኢ-ቁስአካልነት (immaterialism) ወይም ከጠርጣሪነት (skepticism) ጋር ተሠናኝቶ ይቀርባል፡፡በዚህ ሳይበቃ "ሐሳባዊነት" ከአያሌ አሻሚ ዓላማዎች ጋር ተያይዞ ጥቅም ላይ ሲውል ይስተዋላል፡፡ ገና ከጅምሩ ቃሉ በአጠቃላይ ኢ-እውንነትን (anti-realism) ለማመልከት ጥቅም ላይ ሲውል ይስተዋላል፡፡ትልቁ ችግርም ከዚህ ግንዛቤ የሚመነጭ ይመስላል፡፡"አምሳላዊው" ለብዙ ትላልቅ ፈላስፎች፣ በተለይ ለፕሌቶ በማያሻማ መልኩ "እውነታ" ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዘመናዊው ፍልስፍና በተገላቢጦሽ ሆነና "ሐሳባዊነት" በተጨባጭ እውን ላልሆነ አምሳል የሚወክል ትርጉም በመላበስ አሉታዊ ሜታፊዚካዊ አንዳንዴም ሥነ-ዕውቀታዊ አቅጣጫ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ከአሉታዊው ትርጉም በተጨማሪ አብዛኛዎቹ በልማድ እውነት የሚመስሉን ነገሮች እውነት አይደሉም፣ ማለትም ቢያንስ በሚታሰበው ሁኔታ ህልው አይደሉም የሚል አንድምታ አለው፡፡
ከአዎንታዊው ትርጉም አንጻር "ሐሳባዊነት" ከአጉዳይ ሚና ይልቅ አጎልባች ሚና አለው፡፡ በአካለ-ስሜታችን ደረጃ ህልው ናቸው ብለን ስለምናስባቸው አብኛዎቹ ነገሮች ሁኔታ ስናወሳ ከፍ ያለ፣ይበልጥ "አምሳላዊ" ተፈጥሮ ያለው ህልውና ስለመጎናጸፋቸውም ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያሻል የሚል አንድምታም አለው፡፡ ጀርመናዊያን የሐሳባዊነት ፈላስፎች እነዚህ "አምሳላዊ" ህልውናዎች የግድ "በሌላኛው" ዓለም ያሉ ህልውናዎች ናቸው የሚል ጥንታዊው የፕሌቶ እይታ ወደጎን ትተው "አምሳላዊው" እንደ ፍጹማዊና የመጨረሻ ሞዴል ወይም ዓይነት የተጨባጩ ዓለም ነገሮች ውቅረት ወይም አምሳል ናቸው በማለት ይገልጹታል፡፡የጀርመን የሐሳባዊነት ፈላስፎች የሐሳባዊነትን አሉታዊ ሜታፊዚካል ፍቺ ማለትም የአደባባይ ምሥጢር የሆነው የቁስ-አካል ነገሮች ህልውና የሚክደው ፍልስፍናዊ ዝንባሌን አይቀበሉም፡፡ይህም ሆኖ አዎንታዊው እይታቸው በራሱ እጅግ ሥርዓታዊ ከመሆኑ አኳያ ማንኛውም ነጠላ፣ ቋሚ ያልሆነና ውስን ውቅረት ያለው ህልውና ግምት ውስጥ በማያስገባ መልኩ ሁሉንም ነገር በአንድ ጥቅል "ሐሳባዊ" የማድረግ ከፍ ያለ ተምኔት የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
የቀደምት ሐሳባዊያን እንቅስቃሴ ፍልስፍናዊ ዳራ በኢማኑኤል ካንት ሒሳዊ ፍልስፍና እንዲሁም ራሳቸውን እንደ እውነተኛ የካንት የመንፈስ ተከታዮች በሚቆጠሩት የጀርመን ሐሳባዊያን ተጠቃሎ ቀርቧል፡፡ ነገሮችን በአጠቃላይ እንደ የሐሳብ ውጤት አድርገው ይገነዘቧቸዋል ሐሳባዊያን፡፡ በእርግጥ ይህን ማለት ዓለም የፈጠራ-ኅሊና (creative mind) ውጤት ነው ማለት አይደለም፤ በአንጻሩ የፍጹማዊ ባለቤት (absolute subject) ውጤት መሆኑ ያሳያል፡፡ ለሐሳባዊያን በጥቅሉ እውነታ ማለቂያ በሌለው እሳቦት ወይም አመክንዮ ራስን መግለጽ ወይም ራስን ማቅረብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ፍጹም ሐሳብ ወይም አመክንዮ እንደ ድርጊት፣ በዓለም ላይ ራሱን እንደሚገልጽ አመክንይ ይቆጠራል፡፡ እንግዲህ እውነታ ፍጹም ሐሳብ ወይም አመክንዮ ራሱን የሚገልጽበት አንድነት ያለው ሂደት ነው ከተባለ ሊታወቅ የሚችል ነው ማለት ነው፡፡ እናም ይህን አእምሮ እንደ በራሱ ላይ የሚያሰላስል የፍጹም መሳሪያ ከተወሰደ በሰው አእምሮ ሊታወቅ የሚችል ነው፡፡ስለዚህ ሐሳባዊ ፍልስፍና የዚህን ዳይናሚክ ድርጊት፣ የዚህን ቀስ በቀስ ራሱን የሚገልጽ ወሰን አልቦ ሕይወት ሐሳባዊ ግንባታ ነው፡፡ ማሰላሰል በታከለበት ግንዛቤ ለዚህ ሕይወት ሥርዓታዊ ገለጻ ማላበስ፣ ሂደቱን እንደገና ማኖር፣ የፍልስፍና ተልዕኮ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ምክንያታዊ ሂደት በራሱና በሰው ፍልስፍናዊ ማሰላሰል እውነታ ይሆናል፡፡ በዚህ ሁኔታ የፍልስፍና ታሪክ የፍጹሙ አመክንዮ የራስ ማሰላሰል ታሪክ ነው፡፡ በሌላ አባባል ምልዓተ ዓለሙ በሰው አእምሮ በኩል ራሱን የሚያውቅ(የሚገልጽ) ነው ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ፍልስፍና እንደ የፍጹሙ ሐሳብ የራስ እውቀት ሊገለጽ ይችላል፡፡ ዋና ዋና የሐሳባዊነት ወካዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ጆአን ጎትሌብ ፊቼ (1762-1814) ፣ ፍሬድሪክ ቮን ሼሊንግ (1775-1854) ፣ እና ጆርጅ ቬልሄልም ፍሬድሪክ ሄግል (1770-1831)፡፡

"የፍልስፍና መግቢያ" ፀሐዬ ይኄይስ

https://t.me/sopphilo
👍1
የፍልስፍና መግቢያ(introduction to philosophy)
ጆርጅ ቬልሄልም ፍሬድሪክ ሄግል
የሐሳባዊነትን ተአምኖት በአጠቃላይ የጀርመንን የሐሳባዊነት ተአምኖት ደግሞ በተለየ በእውቁ ጀርመናዊ ፈላስፋ ሄግል ተብራርቶ ቀርቧል። ሄግል ስቱትጋርት በተሰኘች የጀርመን ከተማ በ1770 ዓ/ም ተወለደ። የመጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአካባቢው በሚገኝ ት/ቤት ከጨረሰ በኋላ በሃይማኖታዊው የቱቢንገን ዩኒቨርሰቲ ገብቷል። በዚህም ሼሊንግ ከመሳሰሉ የዘመኑ ሊቃውንት ለመገናኘትና ከፈረንሳይ አብዮት ጋር ተያይዘው በሚነሱ ሙግቶች ለመሳተፍ ዕድል አግኝቷል። በአምስት ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታው ፍላጎቱ ቀስ በቀስ የፍልስፍናና የሥነ-መለኮት ግንኙነት ላይ አዘንብሏል፤ በመጨረሻም ከዩኒቨርስቲ ለቀቀና ከሞላ ጎደል ፊቱን ወደ ፍልስፍናው ለማዞር ችሏል። በቀጣዮቹ ዓመታት በበርንና ፍራንክፈርት በማስተማር ሞያ ላይ በመሰማራት በተጓዳኝ አንዳንድ ጽሑፎችን ጽፏል። በዚህ ወቅት የጀርመን ሐሳባዊነት በሁለት ትላልቅ ፈላስፎች እየተመራ ነበር፤ እነዚህም ፊትቼና ሼሊንግ ናቸው። በጄና ዩኒቨርሲቲ የኃላፊነት ሥፍራ አግኝቶ በሚሰራበት ወቅት የፊትቼን ፍልስፍናዊ አቋም የተቸበት የመጀመሪያው ሥራ አሳትሟል። ከተጽዕኖ የጸዳና የራሱ አዲስ መንገድ ይዞ የቀረበው ግን The phenomenology of Mind (1807) በሚባለው እውቅ መጸሐፉ ነው። የጄናን ዩኒቨርሲቲ መዘጋት ተከትሎ የአንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳሬክተር ሆኖ በሚሰራበት ጊዜ Science of logic(1811) የተባለ ሥራውን ጽፏል። የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆኖ ወደበርሊን ዩኒቨርሲቲ ከተቀላቀለ በኋላ አብዛኛዎቹ ከህልፈቱ በኋላ የታተሙ ተጠቃሽ ሥራዎችን ለመስራት በቅቷል፣ ከነዚህም ውስጥ Philosophy of right(1821)፣ ከሞተ በኋላ ከታተሙ ደግሞ Philosophy of history እና Philosophy of religion ይገኙበታል። ሄግል በኮሌራ በሽታ ም/ት በ1831 ዓ/ም ሕይወቱ አልፏል።
ሄግል እውነታን በሁሉም ነገሮች መሠረታዊ አንድነት ነው የምትገኘው የሚል አቋም ያንጸባርቃል። የሐሳብ ዓለም - የተጨባጭ ነገሮች ዓለም፣ ክስተቶች(የሚታወቀው) - "ኑሜነም"(የማይታወቀው)፣ ማወቅ - መረዳት እና የመሳሰሉት የነፕሌቶና ካንት ሜታፊዚካልና ሥነ-ዕውቀታዊ ክፍፍል ይቃወማል። እርግጥ ነው ከልማደ -ሕይወትና ትዝብት አንጻር በነገሮች ላይ ብዙኅነትና ክፍፍል ስለመኖሩ አይክድም፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች ውጫዊ እይታና ብዥታ እንጂ እውነታ አይደሉም ሲል ውድቅ ያደርጋቸዋል። ለምን ቢባል ያልተያያዘ አንዳች ነገር የለማ (Nothing is unrelated)፣ የተለያዩና የተከፋፈሉ ነገሮችን በትኩረት ስንመረምራቸው ወደ ተያያዙበት ሌላ ነገር ይመሩናል፤ በመጨረሻ በዚህ የነገረ-ሐተታዊ ሂደት አማካኝነት የፍጹሙን ሐሳብ ዕውቀት ላይ እንደርሳለን። ይህ ፍጹም ሐሳብ ዳይናሚክ ሂደት ነው፣ የተለያዩ አካላት ያሉት ጥርቅም፣ ግን ደግሞ ወደተወሳሰበ ሥርዓት የሚደራጅ ውሁድ ነው። ፍጹሙ ሐሳብ ሊታወቅ የሚችል ነው፣ ምክንያቱም በተፈጥሮ ውስጥና በሰው አእምሮአዊ ድርጊቶች በኩል ራሱን የሚገልጽ በመሆኑ ነው። ሦስቱም ማለትም ፍጹሙ ሐሳብ፣ ተፈጥሮና የሰው ልጅ አእምሮ የሚያስተሳስራቸው ባሕሪ ሐሳብ(thought) ራሱ ነው።የሰው አስተሳሰብ መንገድ ከተፈጥሮ ውቅረት አንጻር የተደራጀ ወይም ነገሮች በተጨባጭ ከሚስተናበሩበት አንጻር የተበጀ ነው፣ ነገሮች በዚህ መልኩ የሚደራጁት ወይም የሚስተናበሩት ፍጹሙ ሐሳብ በተፈጥሮ ውቅረት በኩል ራሱን ስለሚገልጽ ነው። ስለዚህ ሰው ስለተፈጥሮ የሚያስበው ፍጹሙ ሐሳብ በተፈጥሮ ላይ ራሱን በሚገልጽበት መንገድ ነው። ፍጹሙ ሐሳብ ዳይናሚክ ሂደት እንደሆነ ሁሉ ተፈጥሮም በዳይናሚክ ሂደት ላይ ነው፣ እንዲሁም የሰው ሐሳብም በነገረ-ሐተታዊ ሂደት ላይ ነው።
ሥነ-አመክንዮ ከተጨባጭ እውነታ ተመኩሮ ፍጹሙን ሐሳብ ለመግለጽ የሚያስችሉ ፈርጆችን የምናመጭበት ሂደት ነው። የሄግል ነገረ-ሐተታዊ ፍልስፍና የተቀኘው በዚህ ምንጨታዊ ሂደት ነው። ነገረ-ሐተታዊው ሂደት በሦስትዮሽ ጣምራዊ እንቅስቃሴ ነው የሚገለጸው ከአንብሮ ወደ ተቃርኖ፣ ከተቃርኖ ወደ አስተጻምሮ። በዚህ መልኩ የተገነባው አስተጻምሮ ከጊዜ በኋላ አንብሮ በመሆን ሌላ የሦስትዮሽ ውቅረት ይገነባል፤ ይህ ሂደት በፍጹሙ ሐሳብ ላይ ደርሶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሰንሰለታዊ የሦስትዮሽ ውቅረት በመገንባት ይቀጥላል። በዚህ ነገረ-ሐተታዊ ሂደት ሄግል በዋነኝነት የሚያስገነዝበው "ሐሳብ" በመሆን ሂደት ላይ ያለ (የሚንቀሳቀስ) መሆኑና ተቃርኖም እውቀትን የመግታት ሚና ከመጫወት ይልቅ አዎንታዊ አንቀሳቃሽ ኃይል እንደሆነ ነው።


Share and join 👉 https://t.me/sopphilo
👍1