On line Ethiopian passport service
387 subscribers
8 photos
17 links
Download Telegram
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የአገልግሎቱን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ መግለጫ ሰጡ።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም

የደንበኞችን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ በ6 ወር ውስጥ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌት ወደሀገር በማስገባት በ6 ወራት ውስጥ ለአዲስ አበባ 260,371፣ በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣ በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 በድምሩ 646,539 ፖስፖርት ታትሞ ማሰራጨት መቻሉን ገልፀው ይህ የሆነውም የህትመት አቅም በማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡትን በማመቻቸት እና ሠራተኞችን 24/7 በማሰራት የየቀን የማተም አቅም 2000 ከነበረበት ወደ 10,000 በላይ በማሳደግ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ምንም አይነት የተጠራቀመ ፍላጐት የሌለ ስለሆነ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ ዜጎች በተሰጣቸው የቀን ቀጠሮ መሰረት ፓስፖርታቸውን መረከብ ይችላሉ ብለዋል።
አሁን ያለዉን የፓስፖርት ቡክሌት ወደ ኢ-ፓስፖርት በመቀየር በሀገር ውስጥ እንዲመረት ውል በመያዝ የዲዛይን ስራዎች መጠናቀቁንና የግዥ ትዕዛዝ አልቆ ወደስራ የተገባ በመሆኑ በ1 አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ኢ-ፖስፖርት የሚገባበት ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በ6 ወር ውስጥ ከዋና ቢሮ፣ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ ከቦሌ፣ ከኬላዎች በድምሩ 205 የሚሆኑ ሠራተኞች ውጭ ካሉ ደላሎች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ የነበሩና መረጃ የተገኘባቸውን ለህግ አካላት የማቅረብና እንደየጥፋታቸው ከስራ እንዲታገዱና የህግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የውጭ ዜጐች ቁጥጥር ጋር በተገናኘ በኢትዬጵያ ለቱሪስትም ሆነ ለቢዝነስ የሚገቡትን በስፋት ለማስተናገድ 180 ሀገራት ቪዛ ኦን አራይቫል ተከፍተው እየተሰራ መሆኑንና በዚህ 6 ወር ውስጥ በአየር ኬላ ወደሀገር የገቡ 973,552 ከሀገር የወጡ 1,169,316 በድምሩ 2,142,868 መንገደኛ እና በየብስ ኬላ ወደሀገር የገቡ 215,176 ከአገር የወጡ 167,001 በድምሩ 382,177 መንገደኛ አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ለአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስብሰባ ከ8,100 በላይ፣ ለ2ኛ ትውልደ ኢትዬጵያዊያን ጥሪ ከ75,000 በላይ የገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ5,ዐዐዐ በላይ ለሚሆኑ ትውልደ ኢትዬጵያዊ መታወቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከመደበኛ የውጭ ዜጐች አገልግሎት ጋር በተያያዘ 81,761 ለሚሆኑ የውጭ ዜጐች አገልግሎት መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡

ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም በሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የውጭ ዜጐችን አገልግሎቱ ጥሪ በማድረግ 10,467 የውጭ ዜጐች የተመዘገቡ መሆኑንና ወደህጋዊ መንገድ የማስገባት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡

ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ኢሚግሬሽን፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም የአቪዬሽን ደህንነት የመሳሰሉ በርካታ ተቋማት በቅንጅት አገልግሎት የሚሰጡበት መሆኑንና ኢሚግሬሽን የሚሰራው ገቢና ወጭ መንገደኞች በአለምአቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ሰነዶቻቸው ትክክል ስለመሆናቸው የማረጋገጥ ለገቢ መንገደኞች ቪዛ ፖስፖርት እና ሌሎች ለመግባት የሚያስችሉ ሰነዶችን የማረጋገጥ እና የመመዝገብ፣ ለሀገር ስጋት ያለመሆናቸውን የማረጋገጥ ከሆኑም ህጋዊ እርምጃ መውሰድን ጨምሮ ስራ የሚሰራና ወጭ መንገደኞች ላይ ወደሚሄዱበት ሀገር ለመግባት የሚያስችል ቪዛ፣ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው መሆኑንና ወደሚሄዱበት ሀገር ለመሄድ የሚያስችል ቦርዲንግ ፖስ መኖሩን የማረጋገጥ ስራ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ 6 ወር ውስጥ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ Departure በ11 ካውንተር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን 15 ካውንተር በመጨመር ወደ 26 ካውንተር፣ Arrivale በ21 ካውንተር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን 14 ካውንተር በመጨመር ወደ 35 ካውንተር በማሳደግ የተሻለ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ቅርንጫፎችን የማጠናከር ስራ በተመለከተ ሁሉም ቅርንጫፍ ቢሮዎች በተሟላ መልኩ ወደስራ የማስገባት ስራ የመስራት እና የቦርደር ቁጥጥር የማጠናከር ስራዎች በስፋት እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ህብረተሰቡ ተመሳስለው ከተሰሩ ዌብሳይቶች ራሱን እንዲጠብቅ እና በግለሰብ አካውንት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳያደርግ፣ ዜግነት ማጣራት ጋር በተያያዘ ሂደት ያለው ስለሆነ የሚጠየቁ ሰነዶችን በትዕግስት እንዲያቀርብና እንዲተባበር፣ ፖስፖርት ውሰዱ ተብለው የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው በተባለው ቀን እና ሰዓት እንዲወስዱ፣ አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማይሰጥ ስለሆነ አስቸኳይ የሚያሰጥ ሰነድ ያላቸው ተገልጋዬች በዋናው ቢሮ ብቻ በአካል በመገኘት መስተናገድ ያለባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም በ6 ወር ሪፎርሙን ከመፈፀም አኳያ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዬጵያ አየር መንገድ እና ሌሎችንም ተቋማት አመስግነዋል፡፡
ፓስፖርቶን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይውሰዱ, ኦን ላይን ቀጠሮ አሁን እኛ እጋ ያስይዙ! 0962206195
Congratulations for all !
Share our channel for ur loved ones,