ስለ ፍቅር ብቻ 💞💞
1.32K subscribers
140 photos
1 video
9 links
የተለያዩ የፍቅር ዘፈኖች 🎶🎶🎵
የፍቅር ታሪኮች💔
ግጥሞችን💗💗💗
እዚህ ቻናል ያገኛሉ
Download Telegram
ትመስክር ጨረቃ
እንዴት እንደምወድህ፣ትናገር ጨረቃ፣
ጠብቀህ ጠይቃት፣ስትወጣ ደምቃ፣
የሆዴን በሙሉ፣ አንዳች ሳልደብቅ፣
አዋያት ነበረ ፣ጠብቂያት በድብቅ፣
አሷም አታሳፍር፣ታዳምጠኛለች፣
ከከዋክብት ጋር ፣ተገርማ እያዬች፣
ደመናው አይሎ ፣እንዲያው የቀረች ቀን፣
አይሻም ምሽቱ፣ጭራሽም አይሆን፣
አሁን አሁንማ......
ክረምቱም ደረሰ ፣ደመናው አየለ፣
የእኔና እሷ ነገር፣ከእንግዲል ታጎለ፣
እንጃ ግን ሰሞኑን፣አንዳች ግር ብሎኛል፣
.........
መለየት

( )

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻዋን ሄደች ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንተና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለህ
ከፊትህ ቁጭ ብዬ
ክንድህን ከአንገቴ ጥለህ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወራው ሳይገባኝ
የማወራህ ሳይገባህ
ለይስሙላ ጥርስህ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብህ
ደህና ኹኚ ሲልህ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለኔ፣
ሁሉም ሰው የምትሰጠውን ያህል አይመልስልህም የምትጨነቅለት ያህል አያስብልህም ዓለም እንደዚ ናት አንተም ለመቀበል ከሆነ አትስጥ ከተቻለህ ለማይመልሱልህ ግን ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች መልካሙን ነገር ሁሉ አድርግ
ፍቅርን ታተርፋለህ
ሁሌም ቢሆን ለምትወደው ሰው ጊዜ ስጥ የራሳቸውን ነፃነትም ስጣቸው ግን ማንንም ሰው ካንተ ጋር እንዲቆይ አትለምን። ያንተ የተባለ መቼም ቢሆን ያንተ ነውና።

@Anstiyana
እንደ ቀላል 🥀💔
@Slefikrbcha
♥️​​በልብ ያለን ነገር ሁሉ መናገር ይከብዳል
ለዛም ነው ፈጣሪ ጩኸት፣እምባ፣
እንቅልፍ እና ቀዝቃዛ ፈገግታ የፈጠረልን🙏

@Anstiyana
. የገሀነም መዝገብ

አንድ ጦማር አንድ መዝገብ
አምልጦ ወድቆ ከሠማይ
ወደገሀነም የሚገቡ
ሰዎች ዝርዝር የሚያሣይ
አነሣሁትና ሥበር
ከራሤ ሥም አሥቀድሜ
የፈለኩት ያንቻን ነበር
​​እሱን ተይው ..... 🤦‍♀

ስትወጅው ካልወደደሽ
ስትቀርቢው ካልቀረበሽ
ስትጠጊው ካልተጠጋ
ስለፍቅር ካላወጋ

አይሆንሽም እሱን ተይው
አትድከሚ ላታገኚው
ማፍቀርሽን እያወቀ
በፍቅራችሁ ካልፀደቀ

በቃልሽ ላይ ካላመነ
ጥርጣሬ ከሰፈነ
በመውደድሽ እየኮራ
የውሸት ፍቅር ከሚሰራ
ልብሽ ይቁረጥ እሱን ተይው
ላንች ላይሆን አትወትውችው



━━━━━━✦✗✦━━
የኔ ፍቅር ለምን እንደወደድኩህ ታውቃለህ ውሀዬ ስለሆንክ ነው ምክንያቱም አበባውን ውሀ ስታጠጣው እንደሚለመልመው አንተም በየቀኑ ከጎኔ እንደሆንክ ሳስበው እኔም ልክ እንደ አበባው በየቀኑ አለመልማለሁ ላጣህ አልፈልግም
❤️❤️
ከምትወደው ሰው ልብ በስተቀር ሁሉንም ነገር መተው ትችላለህ
ሕመም እስኪሰማህ ድረስ ውደድ
እውነተኛ ፍቅር ሁልጊዜም በሕመምና
በስቃይ የተሞላ ነውና


@guwadegnaye
አላወራም ♥️

ስላንተ ፍቅር አላወራም። ስለፍቅርህ አላልኩም አልያም ስለአንተነትህ ግን ህይወቴ እኔ አላወራም። ስንት ግዜያትን ይሁን በሲቃ እንባ ያስለቀስከኝ? ስንት ግዜያትንስ ነው በደስታ እንባ ያጠብቀኝ?? በመከፋቴ ይሁን በደስታህ ውስጥ እንዳገኘሁህ ባላውቅም ግን ሀሴቴ ነህ። የኔ ጌታ የምልህ ከማስብልህ ያንስብኝና ምንም እንዳልል ያስገድደኛል። አዎ ፍቅሬ ስለእኛ ብለን ስለእኛ በሚሆነው ምንም ነገር አላወራም።

ህይወቴ በፍቅርህ ጠፍቻለሁ፤ ዳግም እንዳይታየኝ ታውሬልሀለሁ። ለዛም ነው መሰለኝ ብዙ እያለምኩኝ ዝምታን የመረጥኩት ግን ስለ ስሜቴም ልነግርህ አልፈልግም። ኧረ በፍፁም አላወራምም። አንተ አንተ እኔነቴ ነህ የመከፋቴ ምትክ♥️ የኔ ፍቅር ከራስ በላይ ከምታፈቅረኝ በላይ እኔ አፈቅርሀለሁ።

ፀሀፊ፥ ጓደኛዬ


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
ጓደኛዬ የኔ ፍቅር የኔ ጌታ
═❖•🌺🌸•❖═
❤️

❤️
❤️
❤️
❤️
ሁላችንም ያለፈ ትናንት አለን።😢😔😍😘☺️😡😊💔😄.....
ሁላችንም ልክ ያልሆኑ ወሳኔዎችን ወስነናል።
ማንኛችንም ንፁ አይደለንም።
ግን ሁሌም ከትናንቱ የተሻልን ሁነን ለመገኘት አዲስ ዕድል ፣ አዲስ ቀን አለን እንጠቀምበት።

@guwadegnaye
እንባ ምንም ክብደት ባይኖረውም ከባድ ህመሞችን እና አስከፊ ስሜቶችን ግን መሸከም ይችላል

@guwadegnaye
ከምንም በላይ አንተን ማፍቀሬ ለኔ ትልቁ የህይወቴ ፀጋ ነው!!

አንተን በማፍቀሬ እራሴን ፈልጌ እንዳገኝ አድርገህኛል!!

💞💞💞