ᔑᏆᖇᗩᒍ ቴክ
577 subscribers
412 photos
435 videos
353 files
521 links
ቴክኖሎጂ በፈረው አለምን ለማወቅ ወደኛ እንደ መጡ እርግጠኛ ነን።

እኛን ይቀላቀሉ እና ስለ ቴክኖሎጂ አዳዲስ ዘዴዎችን እና ምክሮችን ይማሩ።
ከሁሉም የቴክኖሎጂ ዜናዎች በዓለም ዙሪያ ያግኙ ፡፡ በቴሌግራም

http://t.me/share/url?url=t.me/daily_tech2
🔶 @yourtech_bot
🔶 @techgroup9
Via siraj
Download Telegram
SD ፣ HD ፣ 4K እና 8K ምንድን ናቸው?

የቴክኖሎጅ ርቀት እና ምጥቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን በተለይ ከእይታ(ምስል) ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች ደግሞ ለማመን የሚከብዱ ተአምራት እየሆኑ መጥተዋል ።
የምስል ጥራት በፒክስል የሚለካ ሲሆን በ3 ዋና ዋና ደረጃዎች ይከፈላል።

እነሱም፦
➀ SD [standard_definition]-መደበኛ ጥራት
➁ HD [High definition] - ከፍተኛ ጥራት
➂ UHD [Ultra high definition ]- ከመጠን ያለፈ ጥራት ናቸው።

ፒክስል ስንል አንድን ምስል ለመስራት የሚያስችል ትንሿ ነጥብ(ስኩዌር )ማለታችን ነው።
የፒክስሎች ስብስብ ሪዞሉሽን ሊሰኝ ይችላል።

ለምሳሌ ፦ ከአንድ ምስል ላይ አንድ ስኩየር (ልክ ኬሚስትሪ ላይ atom እንደምንለው) ወስደን ብንመለከት የወርድ ነጥቦች ስብስብ ብዛት × የቁመት ነጥቦች ስብስብ ብዛት ፒክስል ይባላል ማለት ነው ።

🔴720 × 480 pi ሲባል
720=የወርድ(w)ነጥቦች ብዛት እና
480= ቁመት(h) ነጥቦች ብዛት በአንድ ሊከፈል በማይችል ስኩዌር ውስጥ ማለታችን ነው ። ፒክስል በበዛ ቁጥር ጥራት ይጨምራል። በሌላ በኩል የምስሉ MB ም ይጨምራል ።

በየዘመናቱ የመጡ የምስል ጥራት እድገትን ብንመለከት ከመጀመሪያው እስከ አሁን ድረስ የሚከተሉትን ይመስላል።

SD= 720 × 480
PAL= 768 × 576
NTSC= 720 × 534 (የድሮ ሪሲቨሮች)
HD= 2K
HD = 1280 × 720
Full HD =1920 x 1080
UHD=
4K= 3840 × 2160 (16:9 YouTube size)
5K= 5120 × 2700
6K = 6144 × 3160
8K = 7680 × 4320 አሁን የደረስንበት የመጨረሻው ቴክኖሎጅ።

ሀገራችን ላይ በስፋት በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው ሰው ቤት የሚገኘው Full HD እና 4K ሪሲቨር ሲሆን አልፎ አልፎ 8Kም ይኖራል። ነገር ግን እዚ ላይ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ቢኖር ባለ 8K ቻናልን ለመመልከት ሪሲቨራችን እንዲሁም ቲቪያችን የግዴታ 8K ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ የቻናሉ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ ለመለየት እንቸገራለን ። ያ ማለት HD ቻናሎችን በAV ኬብል እንደመመልከት ይሆናል ማለት ነው።
#Ratnik

ራሺያ Ratnik ብላ በሰየመችው የሚሊተሪ ፕሮግራም 4th generation የውጊያ ልብስ ውይም battle armour በቅርቡ ሰርታለች--- ይህ ልብስ 12.7mm የ'caliber ስፋት ያለቸው እንደነ M2 ከተባሉ heavy machine gun በቅርብ እንዲሁም direct shot ብንመታ መከላከል እንዲችል ሆኖ የተሰራ armour suit ነው::
Ratnik እንዳስታወቀውም ይህ ልብስ game changing ተብሎ ለሚገመተው ከ'2025 ቡሃላ ላለው የጦር ነት አይነት ሲሆን ልብሱም ሚያገለግለው ለልዩ ሀይሉ ሳይሆን ለተራው የእግረኛው ጦር ነው::
📌Musketeer በመባል ሚታወቅ የ'video እና audio communication እንዲሁም GLONASS ሚባል እንደ GPS አይነት የ'navigation technology አብሮት ተካቷል።

#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
  ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

  @droneethiopia
@droneethiopia
True meaning of the #Facebook logo.
🔥ለበአሉ ስለሆነ ፍጠኑ 1ሰው ስትጋብዙ 2birr ይሰጣችሁኋል Start በሉትና የሚመጣላችሁን ቻናል ጆይን በሉ ከዛ ለሰው በጋበዛችሁ ቁጥር 2birr ይሰጣችኋል ለ5 ሰው ብጋብዙ 10birr አረ ፍጠኑ😄👇👇
💸Online birr💸:
💸ONLINE BIRR💸

https://t.me/onlinebir_bot?start=r0012083974 ይህን ሊንክ ኮፒ ያድርጉና ለጓደኞቻቹ ይላኩ አንድ ሰው በእርስዎ ሊንክ ገብቶ ስታርት ካለው 1ብር ያገኛሉ።
እስካሁን 34 ሰው በእርስዋ ሊንክ ገብቷል።
ይህን ቦት ስለተጠቀሙ ከልብ እናመሰግናለን።💝💝💝
የኮምፒውተር ክፍሎችና ምንነታቸው
1.✳️ MotherBoard:
◽️Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡
◽️ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ (Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
2.✳️ Central Processing Unit (CPU):
◽️ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡
◽️ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡
◽️ የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
3.✳️ Random Access Memory (RAM):
◽️RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡
◽️RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
◽️የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል።
4.✳️ Hard Drive:
◽️Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ ሙዚቃዎችን፤ ምስሎችን፤ ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡
◽️Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
5.✳️ Power Supply Unit:
◽️Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡
Forwarded from Abdisa Bancha Jara (Abdisa Bancha Jara)
#icciitii tokko isinitti himanna: nu deeggaraa:-

#Biyya kana keessatti dhaabbilee #Tekinoolojii kamiinuu waliin #Dorgomuuf qophoofnee as baane, Dhaabbata zHorn ICT Solutions dhaabbata siyaasdiinagdee hawaasabkeenyaa cimsuuf Addunyaa Tekinoolojii keessatti hawaasni keenya akka dorgomaa tahu goonal jenne #gareen gurmoofnee hundeessine, kana yoo goonu #dhaabbilee Habashaa kaappitaala Miliyoonotaan qaban waliin qoma dhiibnee dorgomuuf deemna, #kaappitaala waan qabnuuf osoo hin taane hawaasa #xiiqeffatee moo'achuu danda'u ofduubaa akka qabnu waan beeknuuf.
Waan biraa isinirraa hin barbaarnu, #page #zHornICTSolutions @zhorn.ict isa gubbatti eere kana qofa share godhaa #hordoftoota heddu akka argannu nu cinaa dhaabbadhaa.

Page keenya:👇👇
https://www.facebook.com/zhorn.ict/

#Ulfaadhaa!
#speedup_pc
ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 9 ዘዴዎች

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች #ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ# አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ
ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን #ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም
ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡

4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ #ይሰርዙ (uninstall) ያድርጉት
5. ዴስክቶፕ ላይ #ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት
የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት
አፕሊኬሽኖች ካሉ #disable ያድርጉ

7. Recycle binን ሁሌም #ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት #ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ #ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::

@sirajtech
​​📌ቀለል ባለ መንገድ ኮምፒውተርን ወይንም☛ላፕቶፕን ፍላሽ ዲስክ ተጠቅመን አዲስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እንዴት መጫን እንደምንችል ነው።

🔸🔸ማዘጋጀት ያለብን ነገሮች🔸🔸

1. 4 ጂቢ ወይንም ከዛ በላይ የሆነ ፍላሽ ዲስክ

2. Rufus የተሰኘ Software

3. መጫን የምንፈልገውን በ ISO format የተዘጋጀ ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ
ሲስተም( WINDOWS XP 7,8,8.1 or 10) ስንገዛ ወይም ስናወርድ እንደዛ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።

4. ይሄን ስራ የምንሰራበት ላፕቶፕ

🔹🔹አስራሩ እንዴት ነው?🔹🔹

▪️Rufus የሚባለው ፕሮግራም አሉ ከሚባሉ ለዚ ስራ የሚያገለግሉ ቀለል ያለ እና ፈጣን ስለሆነ ለዛሬ በሱ እንዴት እንደምንሰራ እናያለን:-

▪️ያዘጋጀነውን 4ጂቢ ፍላሽ ዲስክ ኮምፒተራችን ላይ እንሰካለን።▪️

1.ፕሮግራሙን ዳውንሎድ ካረግን በኀላ መጫን ሳያስፈልገን ራይት ክሊክ አርገን ራን አስ አድሚንስትሬተር
ብለን እንከፍተዋለን ከዛ አብዴት ሲጠይቅ no እንመርጣለን።

2.ፕሮግራሙ ከተከፈተ በኅላ ፍላሽ ዲስኩን ዲቫይስ የሚለው ሜኑ ተጭነን እንመርጠዋለን።

3.ከዛ iso image የሚለው ቦታ ሄደን ቅድም ይዘጋጀነውን የዊንዶውስ ሶፍት ኮፒ አስገብተን ድራይቭ ሌተሩን እንመርጣለን።

✏️ ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ ራሱ ሁሉን ነገር አውቶማቲካሊ ስለሚያዘጋጅ ሌላ የምናስተካክለው ነገር የለም ማለት ነው።

4. ከዛ start የሚለውን በተን ስንጫን ፍላሽ ላይ ያለ ማንኛውም ዳታ ይጠፋል ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል
የምንፈልግው ፍይል ፍላሽ ላይ ካለ ባክአፕ ማድረግ አለብን።
እሱን ካረጋገጥን በኅላ ok እንለዋለን።

5. በስተመጨረሻ ፕሮግራሙ የዊንዶውን ሴትአፕ ወደ ፍላሽ ዲስኩ ኮፒ በማድረግ ስራውን መስራት ይጀምራል።

✏️ ፕሮግራሙ ኮፒ አድርጎ ሲጨርስ
close የሚለውን በተን ክሊክ መጫን የምንፈልገው ኮምፒተር ላይ ወስደን እንጠቀማለን።

🔸🔸በUSB ኮምፒውተሮን እንዴት ፎርማት ማረግ ይችላሉ🔸🔸

1.ኮምፒውትሮን turn off ያርጉ

2.ቅድም ከላይ ያዘጋጀነውን USB ፍላሽ አስገብትው turn on ያድርጉ።

3.F2 ወይም F12 ን (እንደ ኮምፒውተሩ ሞዴል ይለያያል) ይጫኑ እና ቀጣይ ትዕዛዙን ይከተሉ።

4." install windows " የሚለው ሲመጣልዎ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና ሌሎች ዝርዝሮችን ይሙሉ ከዛም next ን ክሊክ ያድርጉ።

5."Please read the license terms" የሚለው ሲመጣልዎ
"I accept the license terms" የሚለውን ክሊክ ያርጉ

6."Which type of installation do you want?" ሲልዎት Custom የሚለውን ይምረጡ።

7."Where do you want to install Windows?" የሚለው ፔጅ ላይ "Drive options" የሚለውን ክሊክ

8.ፎርማት ማድረግ የሚፈልጉትን "partition" ይምረጡና "format" ላይ ክሊክ ያድርጉ

9.ፎርማት አድርገው ሲጨርሱ "next" ላይ ክሊክ ያድርጉ

10. ከዛ በመቀጠል ትዕዛዙን (instruction ) በመከተል window install ያድርጉ።
═══════════════

╚═════📌Share📌════╝
ኢድ ሙባረክ-IId Mubaarak

«ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አዕማል»።አላህ መልካም ሥራችንን ይቀበለን።አላህ ኢዳችንን በፍቅር፣ በአንድነት፣ ፍጹም ሰላማዊሆኖ የሚያልፍ የተባረከ ኢድ ያድርግልን።

"Taqabbal Allaahu minna waminkum saalihal a'emaal"Rabbin hoji gaari keenya nurraa haqeebalu. Allaahin Iidi keenya jaalalan, tokkumaan, nagaa guutuun kan darbuufi kan barakaa nuuf hagoodhu.
✳️ Telebirr

▪️ነፃ 15birr ካርድ ለሚፈልግ

ይሄ አዲሱ የቴሌ መተግበሪያ ነው ቴሌብር ይሰኛል የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት ይጠቅማል እና ለመጀመሪያ ጊዜ ስትመዘገቡ ነፃ 15birr ይሰጣችኋል አጠቃቀሙ ቀላል ነው ከፍታችሁ #Create account ማለት ነው ስትጨርሱ ብሩን ይልክላችሆል።
@sirajtech
ኢትዮ ቴሌኮም ትናንት ምሽት የተፈጠረው የኢንተርኔት መቋረጥ ከእኔ እውቅና ውጭ ነው አለ

ከትናንት ግንቦት 8 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሁሉም ቦታዎች ፌስቡክን ጨምሮ ኢንስታግራም ዋትስ አፕ እና ሌሎች የማህበራዊ ትስስር መገልገያዎች ተቋርጠው ነበር።
ይህን ተከትሎ አል ዐይን አማርኛ ስለ ጉዳዩ የጠየቀው ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱ ከኩባንያው እውቅና ውጭ መቋረጡን አስታውቋል፡
ይሁንና ከትናንት ሌሊት አንስቶ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ በተወሰኑ የማህበራዊ ትስስር መገልገያዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት መመለሱን ገልጿል።
አገልግሎቱ ዛሬ ከረፋድ 4፡30 ጀምሮ ወደ ነበረበት መመለሱንም ነው ኩባንያው ያስታወቀው።
🔐ቴሌግራምን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ?

ሁላችሁም የኔ ቻናል ተከታዮች ቴሌግራማችሁን Secured ማድረጋችሁን አትርሱ አትጎዱም።

📿መፍትሄውን እነሆ


❖ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc
📌ቴሌግራም እንደ whatsapp, viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል

ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ....

በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉ
❶Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

■Note: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።

📌ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
☛ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

⓶ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***..ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

❖ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

❖ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
====================
❖ ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
====================
❖ ማንም ሰው ለመግባት በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።

⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት።

⚠️ከላይ ያሳየናችሁ ዘዴ ቴሌግራማችሁን በቀላሉ ኮዱን ወስደው በናንተ ቁጥር እንዳይጠቀሙ ነው እንጂ የተለያዩ hacking ዘዴን በመጠቀም ሃክ ከመደረግ አያግደውም::
አዲሱ ቴሌግራም መጣላችሁ። ሁሉግራም ተለቀቀ 🎉!

ብዙ አስደሳች ነገሮችን ይዞ!

➢ • በቀላሉ እቃ መግዛት እና መሸጥ የሚችሉበት
➢ • ስቶሪ ( Story ) ማጋራት የሚችሉበት
➢ • ፕሮፋይል ፎቶዎችን ላይክ የሚያደርጉበት
➢ • የተላከሎትን መልእክት ወደ ፈለጉበት ቋንቋ የሚተረጉሙበት
➢ • በአቅራቢያዎ ያለን የሁሉግራም ተጠቃሚ ማውራት ይሚችሉበት
እና ብዙ ሌሎችም ነገሮችህን ያካተተ....

HULUGRAM ን ያውርዱ እና የቴሌግራም አጠቃቀሞን ያሻሽሉ

አፑን ከታች ያገኙታል👇
Hulugram.apks
37.3 MB
✳️Hulugram app ለጠየቃኝ ይሀው Download አድርጋቹ መጠቀም ትችላላችሁ።

🔺Play Store link🔻
https://play.google.com/store/apps/details?id=plus.ride.huluchat