ᔑᏆᖇᗩᒍ ቴክ
691 subscribers
412 photos
435 videos
353 files
520 links
ቴክኖሎጂ በፈረው አለምን ለማወቅ ወደኛ እንደ መጡ እርግጠኛ ነን።

እኛን ይቀላቀሉ እና ስለ ቴክኖሎጂ አዳዲስ ዘዴዎችን እና ምክሮችን ይማሩ።
ከሁሉም የቴክኖሎጂ ዜናዎች በዓለም ዙሪያ ያግኙ ፡፡ በቴሌግራም

http://t.me/share/url?url=t.me/daily_tech2
🔶 @yourtech_bot
🔶 @techgroup9
Via siraj
Download Telegram
#parts_of_computer

❖አንዳንድ የኮምፒውተር #ክፍሎች ማብራሪያ

❶. #RAM (Random Access Memory)

ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል::
(1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል::

❷. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot)

ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን::

❸. #Heat_sinker

ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም
#Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል::

❹.#Fan

ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው::

#CPU

#CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን::

#CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው::
ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው::

#CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም
:
▫️1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው::
:
▫️2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል::
:
▫️3. #Regster
ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው::
ይሂም #Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው::

#Port (ፓርት)
:
port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው::

መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ::

የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ #ኤሌክትሪክ #ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው::

#Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል)

power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው::

የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል::


#ሞደም (Modem):-

ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው::
:

#ኪቦርድ Keybord:-

መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት ቁጥሮች ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን::