ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊየቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው እኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችንን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንተ ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊየቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደስታ የምታስገኝ ሐዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ሕያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባሕርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው እኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳዕና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በኃጥያት የመረረውን ሕይወታችንን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪይ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪይ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንተ ባህሪይ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ኃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ሕይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ጊዜ የወይራ ዘይት ለመሥዋዕትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡

#ሼር

👉ለመቀላቀል 👇👇👇@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret