ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
801 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
<<< በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ >>>

<<< ታሕሳስ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት >>>

+"
#ቅድስት_አንስጣስያ "+

=>እስኪ ዛሬ በጥቂቱ የተባረኩ (ቡሩካት) እናቶቻችን እንዘክር:: "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም
ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ 'ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን:
ኅሪት እምኅሩያን ናትና::

+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና
ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ
ናትና::

+እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::

1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች
ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ
ማርያም)

2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን
ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-
ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው::
እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና
ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

+የእመ ብርሃን ይቆየንና ደግሞ ሌሎች ቅዱሳት እናቶቻችንን እንመልከት:: እናቶቻችን ስናከብር የምንጀምረው በቅድስት ሔዋን ነው:: ብዙ ጊዜ የእናታችን ሔዋን ጥፋቷ እንጂ
በጐ ነገሯ: ደግነቷ: ንስሃዋ አይነገርላትም:: ሆኖም እናታችን ቅድስት ሔዋን ክብር የሚገባት ሴት ናት::

*ክርስቶስ ሰው የሆነ እርሷንና ልጆቿን ለመቀደስ ነውና::

"ከመ ይስዓር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፅ ተሰቅለ" እንዲል::(ድጓ)

+ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን እነ ሐይከል: እድና: ሣራ: ርብቃ: አስኔት: ሲፓራ: ሐና: ቤርሳቤህን የመሰሉ እናቶቻችን
በበጐው መንገድ ፈጣሪን ደስ አሰኝተዋል:: በዘመነ ሥጋዌም
ቅዱሳቱ ሐና: ኤልሳቤጥ: ማርያም: ሶፍያ: ሰሎሜ: ዮሐና እና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በጐነታቸው ያበራል::

+ከዚያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለ2,000 ዓመታት የተነሱ አእላፍ ቅዱሳት እናቶቻችንን ግን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም:: በቅድስናቸው አራዊትን ያሰገዱ: ነገሥታትን ያንቀጠቀጡ:
አጋንንትን የረገጡ: በዘንዶ ላይ የተጫሙ ብዙ እናቶችን ቤተክርስቲያን አፍርታለች::

+ዛሬም ቢሆን በበርሃና በከተማ በጐውን ጐዳና የተከተሉ ብዙ እናቶች እንዳሉን እናውቃለን:: አንድም እናምናለን::
ግን በከተሞች የምንመለከተው ሥርዓቱን የለቀቀው የበርካታ እህቶቻችን አካሔድ ለሃገርም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ ስጋት
ነው:: ክብርና ነውር የማይለይበት ዘመን ይመስላል::

+ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ እህቶቼ! አንድ ነገር ልንገራችሁ:: በመልካቸው ብዙዎችን ያጋጩ: አጊጠው
በመታየታቸው ብዙዎችን ያሰናከሉ: ለብዙ ምዕመናንም የጥፋት ምክንያት የሆኑ ብዙ ሴቶች በታሪክ ነበሩ::

+የሚያሳዝነው ግን ዛሬ ያሉት ከመሬት በታች ነው:: አፈር በልቷቸዋል:: ስም አጠራራቸውም ጠፍቷል:: በጣም
የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬ በዘለዓለማዊው እሳት እየተቃጠሉ በሲኦል:በጥልቁ ውስጥ አሉ::

+እናም ወገኖቼ! ይህን አውቀን እንንቃ:: ይህ ዓለም ጠፊም: አጥፊም ነውና:: እድሜአችን ቢረዝምና ከዚህ
በኋላ ለ100 ዓመታት ብንኖርም እርሱም ማለቁ አይቀርምና::ምርጫችን ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን!!!

+" #ቅድስት_አንስጣስያ "+

+ይህች ቅድስት እንደ በርካቶቹ ቅዱሳት እናቶቻችን ሁሉ የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ናት:: በቀደመችው ታናሽ እስያ
አካባቢ ተወልዳ: የነገሥታት ዘር በመሆኗ ያደገችው በቤተ መንግሥት ነው:: አባቷ ከክቡራኑ አንዱ ቢሆንም ሙያው ጣዖትን ማምለክ ነበር::

+ጊዜው የመከራ በመሆኑ ብዙ ሴቶች የሚኖሩት ክርስትናቸውን ደብቀው ነው:: ከእነዚህ መካከል አንዷ ደግሞ የቅድስት
አንስጣስያ እናት ናት:: ማንን እንደምታመልክ አረሚ ባሏ አያውቅም ነበር::

+አንስጣስያን በወለደች ጊዜም በድብቅ አስጠመቀቻት:: ከሕጻንነቷ ጀምሮም ፍቅረ ክርስትና እንዲያድርባት ነገረ ሃይማኖትን
አስተማረቻት:: ቅድስት አንስጣስያ ወጣት በሆነች ጊዜ ግን ከውበቷ የተነሳ ተመልካቿ በዛ:: እርሷ ግን ይህ ሁሉ
የዓለም ኮተት አይገባትም ነበር::

+በፈጣሪዋ ፍቅር ከመጠመዷ የተነሳ ለመሰል ነገሮች ትኩረት አልነበራትም:: ትጾማለች: ትጸልያለች: ነዳያንና እሥረኞችን ትጐበኛለች:: በዚህም ዘወትር ደስ ይላት ነበር:: ነገር ግን አባቷ ባላሰበችው ጊዜ ለአንድ አረማዊ አጋባት:: በጣም አዘነች: ግን ተስፋ አልቆረጠችምና መፍትሔ ፈለገች::

+ድንግልናዋን እንዳያረክስ በጫጉላዋ ቀን ታመምኩ ብላ ተኛች:: ከዚያ በኋላም አንዴ በልማደ አንስት: አንዴ በሕመም እያመካኘች አላስቀርብ አለችው:: እርሱ የጦር አለቃ በመሆኑ ወደ ጦርነት ሲሔድ እርሷ ታጥቃ ስለ ቀናች እምነት የታሠሩ
ክርስቲያኖችን ታገለግል ነበር::

+ቁስላቸውን እያጠበች: አንጀታቸውን በምግብ እየደገፈች ደስ ታሰኛቸውም ነበር:: ባሏ ሲመለስ ግን ይህንን በመስማቱ ድጋሚ እንዳትወጣ ቆልፎባት ወደ ጦርነት ተመለሰ:: ፈጽማ ስላዘነችበትም እግዚአብሔር በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠውና ሞተ::

+እርሷም ከነ ድንግልናዋ ቀሪ ሕይወቷን ስትመራ መከራው ወደ እርሷ ደረሰ:: ተይዛ ቀርባ በአረማውያን እጅ ብዙ ተሰቃየች:: በዚህች ቀንም ስለ ክርስቶስ ተገድላ ክብረ ሰማዕታትን ተቀዳጀች::

#ቅዱስ_አቦሊ_ጻድቅ

+ቅዱሱ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የክርስቶስን ሕማማት ለመሳተፍ ሲተጉ ከኖሩ ጻድቃን አንዱ ነው:: መሉ ጊዜውን በበርሃ ሲያሳልፍ ብዙ ተጋድሎን ፈጽሟል:: በተለይ ሲጸልይ እግሩን ከዛፍ ላይ አስሮ: ቁልቁል ከባሕር ውስጥ ሰጥሞ ነው:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ዕረፍቱን ታስባለች::

=>አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን: ክብሩን ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::

=>ታሕሳስ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅድስት አንስጣስያ ሰማዕት
2.ቅዱስ አቦሊ ጻድቅ
3.ቅድስት ዮልያና ሰማዕት

=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

++"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ::ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3፥3)
††† #ቅድስት_ኢላርያ †††

††† "ኢላርያ" ማለት "ፍሥሕት (ደስ የተሰኘች)" እንደ ማለት ነው:: ከተባረኩ ቅዱሳት አንስት ትልቁን ሥፍራ ትይዛለች:: ማን እንደ እርሷ!

ቅድስት ኢላርያ ማለት:-
*የታላቁ ንጉሠ ነገሠት: የደጉ ዘይኑን (Emperor Zenon) የበኩር ልጅ
*በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደች
*ትምሕርተ ሃይማኖትን: ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የተማረች
*ምድራዊ ንግሥናን ንቃ ፍቅረ ክርስቶስን የመረጠች
*የአባቷን ቤተ መንግስት ትታ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ (ገዳመ አስቄጥስ) የወረደች:
*ስሟን ከኢላርያ ወደ ኢላርዮን ቀይራ በወንዶች ገዳም የመነኮሰች
*ራሷን በፍጹም ገድል ቀጥቅጣ ከወንዶቹ በላይ በሞገስ ከፍ ከፍ ያለች
*ትንሽ እህቷን ጨምሮ በርካቶችን የፈወሰች
*በእርሷ ምክንያት ለግብጽና በመላው ዓለም ለሚገኙ ገዳማት ብዙ ቸርነት በዘይኑን የተደረገላት ታላቅ እናት ናት::

ቅድስት ኢላርያ ማንም ሴት መሆኗን ሳያውቅባት: አባ ኢላርዮን እንደ ተባለች በዚህች ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያንም እነሆ ላለፉት 1,400 ዓመታት: ቅድስቲቱንና የተባረከ አባቷን ዘይኑንን: ስለ በጐነታቸውና ውለታቸው ታስባቸዋለች::

††† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: †††

††† ጥር 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት

1.በዓለ አስተርዕዮ ማርያም (እመቤታችን ከእረፍቱዋ በሁዋላ ለደቀ መዛሙርት በዚሁ ቀን ተገልጣ ነበር)
2.ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ (ታላቅ ሊቅና ጻድቅ)
3.ቅድስት ኢላርያ እናታችን (የዘይኑን ንጉሥ ልጅ)
4.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ሰማዕት
7.አባ ፊቅጦር

††† ወርሐዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ ምዕመነ ድንግል
2.አባ አምደ ሥላሴ
3.አባ አሮን ሶርያዊ
4.አባ መርትያኖስ
5.አበው ጎርጎርዮሳት

††† "ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን::
እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን::
አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ::
አንተና የመቅደስህ ታቦት::
ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ::
ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው::
ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት. . ."
(መዝ. 131፥7)

††† "ወዳጄ ሆይ! ተነሺ::
ውበቴ ሆይ! ነዪ::
በዓለት: በንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ!
ቃልሽ መልካም: ውበትሽም ያማረ ነውና:
መልክሽን አሳዪኝ::
ድምጽሽንም አሰሚኝ::"
(መኃ. 2፥13)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ  ]

💚💛
@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
#ቅድስት_አንስጣስያ

በ5ኛው መቶ ክ/ዘ ከቁስጥንጥንያ ወደ ግብጽ ወርዳ ፡ ንግሥናን ንቃ በበርሃ ስትጋደል የኖረች ሰውነቷን ለክርስቶስ ሰጥታ የዚህን ዓለም ክብር የተወች ቅድስት እናት ነች።

ደምግባት ያላት እጅግ ያማረች ስለነበረች ንጉሡ ሊያገባት ቢፈልግ እርሷ ግን ይኽን አልወደደችምና ለንጉሡ ሚስት አስረድታት እርሷም በመርከብ ወደ ግብጽ በሥውር አሳፈረቻት።

ንጉሡም ባስፈለጋት ጊዜ ወንድ መስላ አባ ዳንኤል አበምኔቱ በዋሻ ለብቻዋ አኖራት። ሴት መሆኗን ከአበምኔቱ ውጪ የሚያቃት የለም ነበር።

በጾም በጸሎት 28 ዓመት ስትጋደል ኖራ ልታርፍ ስትል መልእክት ልካ አበምኔት አባ ዳንኤል ና ደቀ መዝሙራቸው ከእርሷ ተባርከው አርፋ ሊገንዟት ሲሉ ደቀ መዝሙሩ ሴት መሆኗን አወቀ።

እርሱም አባ ዳንኤልን ታሪኳን ይነግረው ዘንድ ለመነው አባ ዳንኤልም ነገረው ድንቅ!!

ከተጋድሎ በረከቷን ጽናቷን በጸጋ ያድለን።

@zeortodox_kidusan_pic
† እንኳን ለቅዱሳት አንስት ሶፍያ ወአዋልዲሃ: ኦርኒ ወማኅበራኒሃ እና ለሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

#ቅድስት_ሶፍያና_ልጆቿ

† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታዋቂ ከሆኑ የእናቶቻችን ስሞች "ሶፍያ" ቀዳሚው ነው:: ቃሉ በጥሬው ሲተረጐም "ጥበብ (ጥበበ ክርስቶስ) Wisdom of God" ማለት ነው:: ከጻድቃንና ከሰማዕታት ወገን በዚህ ስም የተጠሩ እናቶች አሉ::

ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆነችው በዕለቱ የምናስባት እናት ቁጥሯ ከሰማዕታት ነው:: ዋናው ዘመነ ሰማዕታት ከመጀመሩ በፊት የነበረችው ቅድስት ሶፍያ ከሕግ ትዳር 3 ሴቶች ልጆችን አፍርታለች::

ስማቸውንም:- ጲስጢስ (ሃይማኖት) : አላጲስ (ተስፋ) : አጋጲስ (ፍቅር) ስትል ሰይማቸዋለች:: እንደሚገባም በሥርዓቱ አሳድጋ እድሜአቸው 9 : 10 እና 12 ሲደርስ ለሰማያዊ ሙሽርነት አጭታቸዋለች::

በዘመኑ "ክርስቶስን ካዱ" የሚል መሪ ተነስቶ ነበርና ቅዱሳቱ በመድኃኒታችን አምነው : ጣዖትን ዘልፈው አንገታቸውን ሰጥተዋል:: ክብረ ሰማዕትን : ሃገረ ክርስቶስንም ወርሰዋል::

††† #ቅድስት_ኦርኒ_ሰማዕት †††

††† "ኦርኒ" ማለት በምሥራቃውያን ልሳን "ሰላም" ማለት ነው:: ቅድስቲቱ አርበኛ የዘመነ ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ፍሬ ስትሆን ተወልዳ ያደገችውም በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ነው::

ምንም ዛሬ ያለ ትውልድ ቢዘነጋት ቅድስት ኦርኒ ተወዳዳሪ የሌላት ሰማዕት : ሐዋርያዊት : ድንግል ናት:: እርሷ ውበቷን : ንግሥናዋን : ክብሯን : ሃብቷን : ወጣትነቷንና ያላትን ሁሉ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ሰውታለችና ክብርት ናት::

በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ቤተ መንግስት የተወለደችው ቅድስት ኦርኒ እስከ ወጣትነቷ ድረስ ክርስቶስን ልታውቀው አልተቻላትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ ንጉሡ አባቷ ጣዖትን ማምለኩ ነበር::

ንግሥት እናቷ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ክርስትና ልትነግራት አልደፈረችም:: ይህን ብታደርግ የሚደርስባትን መከራ ታውቃለችና:: ግን ደግሞ ውስጥ ውስጡን ትጸልይላት ነበርና ፈጣሪ መንገዱን ሊከፍት ጀመረ::

መምለኬ ጣዖት አባቷ ሰው እንዳያያት ቤተ መንግስት ሠርቶ : 12 ሞግዚቶችን መድቦ ጣዖት ከፊቷ አቁሞ ለዘመናት ዘጋት:: የሚገርመው ግን መልኳን እንዳያይ በበር ሆኖ የሚያስተምራት ፈላስፋ ተቀጥሮ ነበርና የዚህ ሰው ማንነቱ ነው::

መምለኬ ክርስቶስ ደግ ሰው ነበርና ፈሊጥን ይሻላት ገባ:: በዚህ መካከል ቅድስት ኦርኒ ራዕይን ታያለች:: የቤቷ መስኮቶች ተከፍተው ሳሉ በስተምሥራቅ ነጭ ርግብ : የዘይት (የወይራ) ዝንጣፊ ይዛ ገብታ : ከማዕዷ ላይ ጥላው ወጣች::

እርሷን ተከትሎ ቁራ በምዕራብ ገባ:: እባቡን ማዕዷ ላይ ጣለው:: በ3ኛው ደግሞ ንስር ገብቶ አክሊል ትቶላት ወጣ:: ቅድስቲቱም እየገረማት አረጋዊ መምህሯን "ተርጉምልኝ" አለችው::

††† እርሱም:-
"•ርግብ=ጥበብ (መንፈስ ቅዱስ)
•ዘይት=ጥምቀት
•ቁራ=ክፉ ንጉሥ
•እባብ=መከራ
•ንስር=ድል ነሺነት (ልዑላዊነት)
•አክሊልም=ክብረ ሰማዕታት ነው" ብሎ ተርጉሞ : ክርስቲያን ሆና ይህ ሁሉ እንደሚደረግ ነግሮ ተሰናበታት::

እርሷም ስትጸልይ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አጽናናት:: ያጠምቃትና ያስተምራት ዘንድም ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ልኮላታል:: ሐዋርያውም የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ : ለሰማያዊ ሙሽርነት የሚያበቃ ትምህርትና ጥምቀትን ሰጥቷት ሔዷል::

ቅድስት ኦርኒም የአባቷን ጣዖታት ቀጥቅጣ ሰብራ ከአባቷ ጋር ተጣላች:: እርሱም "እገድላታለሁ" ብሎ በእንስሳት ጅራት ላይ ጸጉሯን ሲያስር እንስሶቹ ደንብረው : እጁን ገንጥለው መሬት ላይ ጥለው ገደሉት:: ቅድስት ኦርኒ ግን ጸሎት አድርሳ አባቷን ከሞት አስነሳችው:: እጁንም ቀጠለችለት::

በዚህ ምክንያት በዚያች ዕለት ብቻ አባቷና 30,000 የከተማው አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል:: ቅድስት ኦርኒ ግን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ታጥቃ ክርስትናን ሰበከች:: ብዙም ተሰቃየች:: ንጉሡ ዳኬዎስ : ልጁና ሌሎች 2 ያህል ነገሥታት በእሳት : በአራዊት : በግርፋትና በጦር ፈትነዋታል::

እርሷ ግን ሁሉን በኃይለ ክርስቶስ ድል ነስታለች:: ሙታም የተነሳችበት ጊዜ አለ:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ወደ ሰማያዊ ርስት (ገነት) ተመስጣለች:: በዘመነ ስብከቷ ካሳመነቻቸው ባሻገር 130,000 የሚያህሉ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁም ምክንያት ሆናለች::

††† #ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ታኦሎጐስ †††

††† ቅዱሱ:-
•የዘመነ ሊቃውንት ፍሬ:
•የእንዚናዙ ኤጲስ ቆጶስ:
•የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ:
•የጉባዔ ቁስጥንጥንያ (በ381 ዓ/ም) 3ኛ ሊቀ መንበር:
•ባለ ብዙ ድርሳን:
•የቂሣርያ (ቀጰዶቅያ) ኮከብ:
•ብሩህ ገዳማዊ:
•መልካም እረኛ የነበረ አባት ነው::
መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በጻፋቸው ብዙ መጻሕፍትና በስብከቱ ከሊቃውንት ወገን "ታኦ(ዎ)ሎጐስ" ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው:: ትርጉሙም በግዕዙ "ነባቤ መለኮት" ማለት ነው:: በአማርኛም "አንድነትን : ሦስትነትን የተናገረ (ያመሠጠረ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱሱ ዛሬ ዕረፍቱ ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
በመጽናታቸውም ያጽናን፡፡


††† እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ጥርን አስፈጸመን:: ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::

ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል (ሙተዋል):: እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪውን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::

††† ወርኀ ጥርን በቸር ያስፈፀመ አምላከ ቅዱሳን ወርኀ የካቲትን እንዲባርክልን እንለምነው::

††† ጥር 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ሶፍያና ሦስቱ ሰማዕታት ልጆቿ (ጲስጢስ አላጲስና አጋጲስ)
2.ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት ( (በ5 ነገሥታት እጅ የተሰቃየች : የሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተከታይና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀች እናት)
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.አባ አክርስጥሮስ
5.አምስቱ ደናግል ሰማዕታት (ጤቅላ: ማርያ: ማርታ: አበያ: ዓመታ)
6.ጻድቃነ ዴጌ (የተሠወሩበት)
7.አባ ሚናስ ሊቀ ጳጳሳት
8."130,000" ሰማዕታት (የቅድስት ኦርኒ ማኅበር)

††† ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
3.አባ ሣሉሲ ክቡር

††† "ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ::" †††
(፩ጴጥ. ፫፥፫)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ  ]

💚💛
@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
#ቅድስት_ኦርኒ_ሰማዕት

+በ5 ነገሥታት እጅ የተሰቃየች :

+የሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተከታይና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀች እናት)

<<በረከቷ በዝቶ ይደርብን።>>
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

††† እንኩዋን ለእናታችን "
ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት" እና "ቅዱስ አቡሊዲስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

+*"
#ቅድስት_ማርያም_እንተ_ዕፍረት "*+

=>ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለን በስምዖን ቤት የመድኃኔ ዓለምን እግር በእንባዋ አጥባለች:: በፀጉሯም አብሳ የ300 ብር ሽቱ ቀብታዋለች:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የቀደመ ኀጢአቷን ይቅር ብሎ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ደምሯታል:: (ሉቃ. 7:36-50)

+ስለዚህች ቅድስት ሙሉ ታሪክ:-
1.ትርጉዋሜ ወንጌልን
2.ተአምረ ኢየሱስን
3.ስንክሳርን እና
4.መጽሐፈ ግንዘትን በማንበብ ማግኘት ይቻላል::

+እንት ዕፍረት (ባለ ሽቱዋ ማለት ነው) ማርያም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን (በዘመነ ስብከቱ) የነበረችና ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ሴት ነበረች:: ግን መልክ የመልካም ነገሮች ምንጭ ሲሆን አይታይም::

+በመልካቸው ማማር የጠፉና ያጠፉ ብዙ ሴቶችን ዓለማችን አስተናግዳለች:: ከክሊዎፓትራ እስከ ዘመናችን "ሞዴል" ነን ባዮች : እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ የሰይጣን መደሰቻ : የገሃነም መንገድ አድርገውት ማየት (መስማት) እጅግ ያሳዝናል::

+በአንጻሩ ደግሞ ብዙዎችን ያስደመመ መልካቸውን ንቀው : ሰማያዊ ሙሽርነትን የመረጡትን ቅዱሳቱን:- አርሴማን : ቴክላን : ጤቅላን : መሪናን : ጣጡስን : ሔራኒን : ኢራኒን : አትናስያን : ሶፍያን : ኢላርያን . . . ስናስብ ደስ ይለናል:: ዛሬም ጌታ በሚያውቀው ብዙ እናቶቻችን (እህቶቻችንም) ተመሳሳዩን በጐ ጐዳና መርጠው እየተጉዋዙ መሆኑን እናውቃለን::

+ቅድስት ማርያምም ከፈጣሪዋ በተሰጣት ቁንጅና ክፋትን ትሠራ ዘንድ ሰይጣን ሲያገብራት "እሺ" ብላ የእሱ ወጥመድ ልትሆን ተራመደች:: ለዘመናትም ዓይነ-ዘማ : ልበ-ስስ የሆኑ ወንዶችን ወደ ኃጢአት ጐዳና ማረከች::

+ለመልኩዋ ከነበራች ስስት የተነሳም ቶሎ ቶሎ ራሷን በመጽሔት (መስታውት ማለት ነው) ትመለከት ነበር:: መቼም አምላካችን ለሁሉም የመዳን ቀን ጥሪ አለውና (የሚያስተውለው ቢገኝ) ለማርያም ጥሪውን ላከላት:: ጥሪው ግን በስብከት : በመዝሙር : በመጽሐፍ . . . አልነበረም::

+እንዳስለመደች ውበቷን ለመመልከት መስታውት ፊት ቆማ የራሷን ጸጉር : ግንባር : ዐይን : አፍንጫ : ጥርስ . . . እየተመለከተች ተደመመች:: ወዲያው ግን ይህ አካል አፈር እንደሚበላው የሚያስብ ልቡና መንፈስ ቅዱስ አምጥቶባት በጣም አዘነች:: የመኖር ተስፋዋ እንዳይቆረጥ ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዜና ሰማች::

+መወሰን ነበረባትና ከሞት ወደ ሕይወት : ከጨለማ ወደ ብርሃን ልትሔድ ቆረጠች:: በአምላኩዋ ፊት የሚቀርቡም 3 ስጦታዎችን አዘጋጀች:: ሰይጣን ሊያጣት አልፈለገምና ወደ ክርስቶስ እንዳትደርስ ብዙ መሰናክልን ፈጠረባት:: ግን ውሳኔዋ የእውነት ነበርና እያሳፈረችው ወደ አምላኩዋ ገሰገሰች::

+የስምዖን ዘለምጽ በረኞችም ሊያስቀሯት አልተቻላቸውም:: ወደ ውስጥ ዘልቃ የያዘችውን ሁሉ ለመድኃኒታችን ሰዋች::
1.ከውስጧ እንባዋን:
2.ከአካሏ ጸጉሯን:
3.ከንብረቷ ውድ የሆነውን ሽቱ አቀረበች::

+ብዙ ወዳለችና ብዙ ኃጢአቷ ተሠርዮ ቅድስት እናታችን ሆነች:: ብዙ አዝማናትን ከሐዋርያት ጋር አገልግላም በዚህች ቀን ዐርፋለች::

+*" #ቅዱስ_አቡሊዲስ_መምህረ_ኵሉ_ዓለም "*+

=>የዓለም ሁሉ መምህር:
¤ባለ ብዙ ድርሳንና ተግሣጽ:
¤የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ:
¤38 ሕግጋትን የደነገገ:
¤ስለ ቀናች እምነት የተጋደለ:
¤መራራ ሞትን በደስታ የተቀበለ:
¤የቀደመችዋ ሮም ሊቀ ዻዻሳት የነበረና:
¤ሐዋርያትን የመሰለ አባት ነው::

+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ያበራው ይህን ኮከብ ካቶሊካውያን ክደውታል:: እነርሱ "አቡሊዲስ የሚባል ዻዻስ አልነበረም" ቢሉም ምክንያታቸው ግን ከሰይጣን ነው:: ሃይማኖታቸውን ከመለወጣቸው 250 ዓመታት በፊት ስለተናገረባቸውና አንድ ባሕርይን ስላስተማረ መሆኑን ዓለም ያውቃል::

+አባታችን ቅዱስ አቡሊዲስ የተገደለ የካቲት 5 ሲሆን የካቲት 6 ሥጋው የተገኘበት ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ከቅድስት ማርያም ንስሃዋን : ከአባ አቡሊዲስ ምሥጢረ ቅድስናውን ያድለን::

=>የካቲት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
2.የዓለም ኁሉ መምሕር ቅዱስ አቡሊዲስ (ብዙ መንፈሳዊ ድርሳናትን የደረሰ ሊቀ ዻዻስና ሰማዕት)
3.ቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ (ሰማዕታት)
4.ቅድስት አትናስያና 3ቱ ሰማዕታት ልጆቿ (ቴዎድራ : ቴዎፍናና ቴዎዶክስያ)

=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=>ከበረከተ ቅዱሳን ይክፈለን::

=>+"+ . . . አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም:: እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች:: ስለዚህ እልሃለሁ : እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአቷ ተሰርዮላታል:: ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል:: እርስዋንም:- 'ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል' አላት:: ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው:- 'ኃጢአትን እንኩዋ የሚያስተሰርይ ይህ ማነው' ይሉ ጀመር:: ሴቲቱንም:- 'እምነትሽ አድኖሻል: በሰላም ሒጂ' አላት:: +"+ (ሉቃ. 7፥46)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ  ]

💚💛
@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
<<< #ቅድስት_ጣቢታ_(ዶርቃስ) >>>።

የካቲት 12 በዓሏ ነው::

36 "' በኢዮጴ ጣቢታ የተባለች አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጓሜ ዶርቃ ማለት ነው። እርሷም ዘወትር በትጋት በጎ ነገር እያደረገችና ድኾችን እየረዳች ትኖር ነበር።

37 በዚያ ጊዜም ታማ ሞተች፤ ሰዎችም አስከሬኗን አጥበው በሰገነት ላይ ባለው ክፍል አስቀመጡት።

38 ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች፣ ደቀ መዛሙርትም ጴጥሮስ በልዳ መሆኑን በሰሙ ጊዜ፣ ሁለት ሰዎች ልከው፣ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና” ሲሉ ለመኑት።

39 ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ እዚያ በደረሰ ጊዜም ሰገነት ላይ ወዳለው ክፍል አወጡት። መበለቶቹም ሁሉ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር በነበረችበት ጊዜ ያደረገቻቸውን ቀሚሶችና ልብሶች እያሳዩት ዙሪያውን ከበው ያለቅሱ ነበር።

40 ጴጥሮስም ሁሉንም ከክፍሉ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ፤ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ፣ “ጣቢታ፤ ተነሺ” አለ። እርሷም ዐይኗን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች፤

41 እርሱም እጇን ይዞ አስነሣት፤ አማኞችንና መበለቶቹንም ጠርቶ ከነሕይወቷ አስረከባቸው።

42 ይህም ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ። "'
(ሐዋ. 9፥36)

<< ዛሬ የካቲት12 በዓለ ዕረፍቷ ነውና ከበረከቷ ይክፈለን:: >>
Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
ስም አጠራሯ የከበረ፡ የብርሃን ዘመን ሰማዕት እና ድንቅ አድራጊዋ #ቅድስት መሪና (St. Marina)

☞የካቲት15 በዓለ ልደቷ ነው!

"" ከበረከቷ ይክፈለን! ""
Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
እንኳን አደረሳችሁ

☞እናታችን #ቅድስት #ፍቅርተክርስቶስ ከባለቤቷ ቅዱስ #ዘርዓክርስቶስ ጋር ሰማዕትነትን የተቀበለችው የካቲት15 (አሪንጎ ላይ) ነበር፡፡

"" ጣዕመ ፍቅሯ፡ ረድኤቷ፡ በረከቷም ይደርብን! ""
የካቲት 16

እንኩዋን ለእናታችን
ቅድስት ኤልሳቤጥ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+"
#ቅድስት_ኤልሳቤጥ "+

=>በወንጌላዊው አንደበት የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ ትውልዷ ከነገደ ሌዊ ነው:: ሐረገ ሙላዷም ከቅዱስ አሮን ካህን ወገን ይመዘዛል:: ከአሮን በቴክታና በጥሪቃ ወርዶ ሔርሜላ ላይ ይደርሳል::

+ይህቺ ሔርሜላ የምትባል ደግ ሴት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል የተባረከ ሰው አግብታ 3 ቡሩካት ልጆችን ወለደች:: የመጀመሪያዋን 'ማርያም' አሏት:: እርሷ ቅድስት ሰሎሜን ወለደች:: ሁለተኛዋን 'ሶፍያ' አሏት:: እርሷ ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች::

+ሦስተኛዋ ግን የተለየች ናት:: 'ሐና' ብለው ሰየሟት:: እርሷም የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ወለደች:: በዚህም መሠረት ድንግል ማርያም: ቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሰሎሜ የእህትማማች ልጆች ናቸው::

+ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ጊዜ ስም አጠራሩ የከበረ: ደግ ካህን ለሆነ: ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት:: እርሷ የሊቀ ካህናቱ ሚስት ናትና ክብሯ ከፍ ያለ ነበር:: ምንም ልጅ ባይኖራትም ዘወትር በጸሎትና በጾም: ምጽዋትንም በማዘውተር: ነዳያንንም በማሰብ የምትኖር እናትም ነበረች::

+ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

+ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ቅድስቲቷ መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች::

+ድንግል እመቤታችን ወደ እርሷ መጥታ 'ሰላም' ባለቻት ጊዜ ምንም ያሳደገቻት ልጇ ማለት ብትሆን: መንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላባት እመ ብርሃንን አመስግናታለች:: ቡርክት: ብጽእት: ከፍጥረተ ዓለሙ የከበረች መሆኗንም መስክራለች::

+በማሕጸኗ ያለ የ6 ወር ጽንስም የእመ አምላክን ድምጽ ቢሰማ በደስታ ዘሏል:: ለፈጣሪውም ስግደተ-ስባሔ አቅርቧል:: ቅድስት ኤልሳቤጥ አክላም "ወምንትኑ አነ ከመ ትምጽኢ ኀቤየ እሙ ለእግዚእየ-የጌታየ እናቱ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይገባኛል?" ስትል በትኅትና ተናግራለች:: ከጌታ እናት ጋር ለ3 ወራት በአንድ ቤት ቆይታለች::

+ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

+እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: ኤልሳቤጥ ማለት 'እግዚአብሔር መሐላየ ነው': አንድም 'የጌታ አገልጋይ' ማለት ነው::

+ሊቃውንትም:-
+"+ ሰላም ለኤልሳቤጥ እንተ ወደሳ ወአልዓላ:
ሉቃስ ወንጌለ ሶበ ጸሐፈ ለታኦፊላ:
ሐገረ ይሁዳ አሜሃ ሶበ በጽሐት እምገሊላ:
ተሐስየ በውስተ ከርሣ ወአንፈርዓጸ ዕጉዋላ:
ለማርያም ድንግል ሶበ ሰምዓት ቃላ:: +"+ ሲሉ አወድሰዋታል::

=>ከቅድስት እናታችን ክብሯንና በረከቷን ይክፈለን::

   ወስብሐት ለእግዚአብሔር