ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
Forwarded from ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ (🕊Dawit🕊)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መንፈሳዊ ፊልም===መጽሐፈ አስቴር ክፍል 1

https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
Forwarded from ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ (🕊Dawit🕊)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መንፈሳዊ ፊልም===መጽሐፈ አስቴር ክፍል 2

https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
Forwarded from ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ (🕊ኢዮአታም🕊)
"#በጥያቄ_ቀን_ጥያቄ_እንጠያየቅ" በጥያቄ ቀን 3:30 ላይ ይጠየቁ ራሶን ይፈትሹ ይማሩ!!!!😍

#ቻናሉን_ከወደዱት_ሼር_ያድርጉት!

https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo

እኔ ብቻ ሳልሆን ጓደኞቼም ይሞክሩት ካሉ ይጋብዟቸው!😊
እንደ በሬ ሣር በመጋጥ ሰባት ዓመት የተቀጣው ንጉሥ ማነው??
Anonymous Quiz
11%
ሀ. ዳርዮስ
62%
ለ. ናቡከደነጾር
18%
ሐ. ብልጣሶር
8%
መ. ኢዮርብዓም
በብሉይ ኪዳን በትንቢት የመጽሐፍ ክፍል ውስጥ ስንት መጽሐፎች አሉ?
Anonymous Quiz
12%
ሀ. 10
31%
ለ. 12
32%
ሐ. 8
25%
መ. 16
ሰንሰለትን ለብሳ የተጋደለች
ለሃይማኖቷ ቆርጣ የታገለች
የሱስንዮስ ክኅደት ፍጹም ያላስፈራት የእምነት አርበኛ ይህች ቅድስት እናት በሉ እስኪ ንገሩኝ ማናት?
Anonymous Quiz
23%
ሀ. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
26%
ለ. ቅድስት አርሴማ
50%
ሐ. ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ
1%
መ. መልስ አልተሰጠም
ርዕሰ መነኮሳት በመባል የሚታወቀው አባት ማን ነው?
Anonymous Quiz
26%
ሀ. አባ መቃርዮስ
20%
ለ. አባ ጳውሊ
51%
ሐ. አባ እንጦንስ
3%
መ. አባ ጳኩሚስ
ለዛሬ እዚህ ጋር ይብቃን እንዴት ነበር ጥያቄ እና መልሱ? ከጨረሳችሁ በኋላ እስቲ ሀሳብ አስተያየታችሁን ጻፉልን።
ሳምንታዊው #በጥያቄ_ቀን_ጥያቄ_እንጠያየቅ መርሐ ግብር እንዴት ነው?
Anonymous Poll
72%
በጣም ጥሩ ነው
22%
ጥሩ ነው
5%
ምንም አይልም
1%
ጥሩ አይደለም
https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo

        🕐 ​ታኅሣሥ 25/04/2016 ዓ.ም🕖
 
   በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
   መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፵፬፥፲፯(144፥17)
ጻድቅ እግዚአብሔር በኵሉ ፍናዊሁ
ወኄር በኵሉ ምግባሩ
ቅሩብ እግዚአብሔር ለኵሎሙ እለ ይጼውዕዎ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፮፥፳፮-፴(6፥26-30)
ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ...

ምንባባት ዘቅዳሴ

           👉  ዲያቆን
📖ኀበ ቲቶ ፪፥፲፫-፲፭(2፥13-15)
ወትሜሕረነ ከመ ንትናከራ...

            👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፪፥፲፪-፲፰(2፥12-18)
እጽሕፍ ለክሙ ደቂቅየ...

             👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፬፥፴፩-፴፯(4፥31-37)
ወእንዘ ይጼልዩ አድለቅለቀ...

            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም
ወከዐዉ ደሞሙ ከመ ማይ ዐውዳ ለኢየሩሳሌም
ወኀጥኡ ዘይቀብሮሙ

               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፸፰ ቊ. ፪ - ፫

፪ የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤

፫ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ።
      

            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፫ ቊ. ፴፮ - ፵፬
ወእምዝ ኀደጎሙ ለአሕዛብ...

        📜ቅዳሴ


👉ግሩም


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
እንኳን ለ5ቱ "ቅዱሳን መቃብያን" እና "ቅዱስ ዮሐንስ ከማ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*"
#5ቱ_መቃብያን "*+

=>እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን: 22ቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ: በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ: ነቢይና ካህን አድርጐ: ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው::

+አባታችን አዳም ግን ስሕተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በሁዋላም ለ100 ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድኅነትን ሰጠው::

+ስለዚህም ምክንያት ለ5,500 ዓመታት ትንቢት ሲነገር: ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር: ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ: የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ::

+ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ::

+ከእርሱም ይስሐቅ: ከዚያም ያዕቆብ ደጋጉ ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ረሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው::

+በዚያም ለ215 ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው::

+ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ9 መቅሰፍት: በ10ኛ ሞተ በኩር: በ11ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ::

+አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ::

+ከዚህ በሁዋላ ለ300 ዓመታት ያህል መሣፍንት እየተቀያየሩ አስተዳደሩዋቸው:: ሲበድሉ ጠላት እየገዛቸው: ሲጸጸቱ በጐ መሥፍን እየመጣላቸው ከነቢዩ ሳሙኤል ደረሱ::

+በዚህ ጊዜም ሕዝቡ እንደ አሕዛብ ሥርዓት ንጉሥ በመፈለጋቸው ክፉው ሳዖል ለ40 ዓመት ገዛቸው:: ቀጥሎ ግን እንደ አምላክ ልብ የሆነ ቅዱስ ሰው ዳዊት ነግሦላቸው እሥራኤል ከፍ ከፍ አሉ:: ከቅዱስ ዳዊት እስከ ሮብዓም ቆይተው ግን እሥራኤል ከ2 ተከፈሉ::

+10ሩ ነገድ በሰማርያ ሲኖሩ ግፍን ስላበዙ ስልምናሶር ማርኮ አሦር አወረዳቸው:: ባሮችም አደረጋቸው:: 2ቱ ነገድ ደግሞ ከብረው: ገነው በኢየሩሳሌም ቢኖሩም እነርሱም አመጸኞች ነበሩና ናቡከደነጾር ወስዶ የባቢሎን ባሪያ አደረጋቸው::

+እግዚአብሔር ግን እንደ ነቢያቱ ቃል 70ው ዘመን ሲፈጸም በኃይል ወደ ርስታቸው መለሳቸው:: በዚያም ዘሩባቤል የሚባል ደግ ንጉሥ ነግሦላቸው: ቤተ መቅደስ ታንጾላቸው ኖሩ:: ክፋታቸው ግን ማብቂያ አልነበረውምና ከዘሩባቤል በሁዋላ ቅን ንጉሥን ማግኘት አልቻሉም::

+እግዚአብሔር ግን ምሕረቱንና መግቦቱን አይተውምና አልዓዛርን የመሰሉ ደጋግ ካህናትን እያስነሳ ሰው እስከሚሆንባት ቀን ድረስ አቆይቷቸዋል:: በዚህም ምክንያት ይህ ዘመን "ዘመነ ካህናት" ተብሏል::

+በዚህ በዘመነ ካህናት ውስጥ ደግሞ በጐነታቸው የታወቀላቸው: ግን ደግሞ መከራው የበዛባቸው እሥራኤላውያን ነበሩ:: ብዙ ጊዜ የሚጠሩት "መቃብያን" በሚል ስም ነው::

+በያዕቆብ እሥራኤል: በዔቦር ዕብራውያን: በይሁዳ አይሁድ: በፋሬስ ፈሪሳውያን: በሳዶቅ ሰዱቃውያን እንደተባሉት ሁሉ እነዚህም በአባታቸው በመቃቢስ ምክንያት መቃብያን ተብለዋል:: ታሪካቸው ሰፊና በመጽሐፈ መቃብያን የተጻፈ ሲሆን እኛ ግን በአጭሩ አንዷን የታሪክ ዘለላ ብቻ እንመለከታለን::

+በዘመኑ መቃቢስ የሚባል ደግ ሰው 5 (3) ወንዶች ልጆችን (መቃብያንን) ወልዶ ነበር:: እነዚህም በመልክ ይህ ቀራችሁ የማይባሉ: በጠባይ እጅግ የተመሰገኑ: በኃይላቸው ጽናትም የተፈሩ ነበሩ::

+በተለይ 3ቱ ከግሩማን አራዊት አንበሳና ድብ ታግለው ያሸነፉ: በጦርነትም ጠላትን ያንበረከኩ ነበሩ:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተሰጣቸው ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና ፈጣሪያቸውን በንጹሕ ልብ ያመልኩት ነበር::

+በዘመኑ ደግሞ ሞዐባውያንና ሜዶናውያን አካባቢውን ያስገብሩ ነበር:: በተለይ የሞዐቡ ንጉሥ ጺሩጻይዳን ከክፋቱ ብዛት 70 ጣዖታት በወንድና በሴት ምሳሌ አስቀርጾ ያመልክ ነበር:: ከዚያም አልፎ ሕዝቡን "አምልኩ" እያለ ያውክ: ይቀጣ: ይገድልም ነበር::

+ቅዱሳን መቃብያን ይህንን ሲሰሙ ወደ እርሱ ገሰገሱ:: ምንም እንኩዋ ሊያጠፉት ኃይል ቢኖራቸውም አላደረጉትም:: ይልቁኑ ቀርበው ዘለፉት እንጂ::

+እርሱም "ጣዖትን አናመልክም" ስላሉ ለአንበሳ ጣላቸው:: አንበሶቹም ለቅዱሳኑ ሰግደው የንጉሡን ወታደሮች ፈጇቸው:: እርሱም 3ቱን ወደ እሥር ቤት ጣላቸው:: በዚህ ጊዜ 2ቱ ወንድሞቻቸው መጥተው ተቀላቀሉ::

+ቀጥሎም 5ቱንም አስወጥቶ በሰይፍ አስመታቸው:: ከተገደሉ በሁዋላም ወደ ውሃ ጥሏቸው: በእሳት አቃጥሏቸው ነበር:: ባይሳካለት ስለ ተቆጣ ሳይቀበሩ እንዲጣሉ አዘዘ:: ከ14 ቀናት በሁዋላም የቅዱሳኑ አካል እንደ መብረቅ እያብለጨለጨ ተገኝቶ በክብር እንዲቀበር ሆኗል::

<< ቀሪው ታሪካቸው በመጽሐፈ መቃብያን የተጻፈ አይደለምን !! >>

+*" #አባ_ዮሐንስ_ከማ "*+

=>ቅዱስ ዮሐንስ ከማ በዘመነ ጻድቃን (በተለይም በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ከተነሱ አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ድንቅ ሕይወት ስለ ነበረው በዜና አበው በስፋት ተጠቅሷል:: መጽሐፈ ስንክሳር "ከማ" የሚለውን ቃል "ከማ ብሒል ካም - 'ከማ' ማለት 'ካም' ማለት ነው" ይላል::

+"ካም" የሚለው ቃል ደግሞ ብዙ ጊዜ መልካቸው ጠቆር ላሉ ሰዎች የሚሰጥ ስም ነው:: ምናልባት የድሮ የኢትዮዽያ ግዛት በነበረው ደቡብ ግብጽ የነበረ አባት እንደ መሆኑ የዘር ሐረጉ ከኢትዮዽያ የተመዘዘ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል::

+ቅዱሱ በስፋት የሚታወቀው በድንግልና ሕይወቱ ነው:: መልካም ቤተሰቦቹ በሥርዓት አሳድገው "እንዳርህ" አሉት:: እንቢ ቢላቸው ብቸኛ ልጃቸው ነውና ፈጽሞ ሊያዝኑበት ነው:: ደስታውን ለቤተሰቦቹ ሰውቶ በተክሊል ተዳረ::

+እርሱ የሚሻው በድንግልና መኖርን ነውና ጥበበኛ እግዚአብሔር ሚስቱ የተቀደሰች እንድትሆን አደረጋት:: በሰርጋቸው ምሽት ቅዱስ ዮሐንስ ከማ መልከ መልካሟን ሙሽራ በድንግልና ይኖሩ ዘንድ ቢጠይቃት በደስታ አነባች::

+ምክንያቱም እርሷም ያገባችው ቤተሰብን ለማስደሰት እንጂ ፈቃዷ በድንግልና መኖር ነበርና:: 2ቱም ስላደረገላቸው ፈጣሪን እያከበሩ የድንግልና ሕይወት ተጋድሎን ቀጠሉ:: ቅዱሳኑ በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንዲት ምንጣፍን እያነጠፉ: አንድ ልብስንም በጋራ ለብሰው እያደሩ ድንግልናቸውን ጠበቁ::

+አምላከ ድሜጥሮስም ቅዱስ መልአኩን ልኮላቸው በመካከላቸው ያድር: ክንፉንም ያለብሳቸው ነበር:: ክብራቸውን ይገልጥ ዘንድም በቤታቸው መካከል ታላቅ ዛፍን ያለ ማንም ተካይነት አበቀለ::
+በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ዮሐንስ ከማ ድንግሊቱን ሚስቱን "የከተማ ኑሮ ይብቃን: ወደ በርሃ እንሒድ" አላት:: እርሷም "ፈቃድህ ፈቃዴ ነው" ስላለችው እርሷን ወደ ደናግል ገዳም አስገብቶ እርሱ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ተጉዋዘ::+ቅድስቲቱ አስቀድማ ጸጋው በዝቶላት ነበርና ድውያንን ትፈውስ ነበር:: የገዳሙ እመ ምኔት ሆና መርታ በክብር አረፈች:: ቅዱስ ዮሐንስ ከማም በቅዱስ መልአክ መሪነት መጀመሪያ ወደ አባ ዳሩዲ ሔዶ መነኮሰ::

+በመጨረሻም በቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም ጐን ማደሪያን አነጸ:: በዚያም በመቶ የሚቆጠሩ ደቀ መዛሙርትን አፍርቶ በአበ ምኔትነት አገለገለ:: ለእመቤታችንና ለቅዱስ አትናቴዎስ ልዩ ፍቅር የነበረው ቅዱሱ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በሁዋላ በዚህች ቀን በክብር ዐርፎ ተቀብሯል::

=>አምላከ ቅዱሳን ይራዳን: ይባርከን: ይቀድሰን:: ከወዳጆቹ በረከትም ያሳትፈን::

=>ታሕሳስ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅዱሳን 5ቱ መቃብያን
2.ቅዱስ ዮሐንስ ከማ (እና የተቀደሰች ሚስቱ)
3.ቅዱስ ዳንኤል መነኮስ
4.ቅዱስ ኒቆላዎስ መኮንን

=>ወርሐዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
7.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ

=>+"+ ቃሌን የሚጠብቅ: በትዕዛዜም ጸንቶ የሚኖር: በረከቴን የሚያገኝ: በእኔ ዘንድ የሚከብር እርሱ ነው::
ቃሌን የሚጠብቅ: በትዕዛዜም ጸንቶ የሚኖር ሰው ሁሉ ከምድር የተገኘውን ድልብ ይበላል:: ቅን ልቡና ያላቸው ደጋጎች ነገሥታት ወደ ገቡበት ወደ ገነትም ገብቶ ይኖራል
:: +"+ (መቃ. 12፥43)

 † ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ  ]

💚💛
@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
✞እንኳን አደረሳችሁ!

❖በዓለ ቅዱሳን ሐዋርያት!

☞በየአክፋለ ዘመናቱ መሸጋገሪያ ዕለት (መስከረም ፳፭፥ ታኅሣሥ ፳፭፥ መጋቢት ፳፭ እና ሰኔ ፳፭) የቅዱሳን #ሐዋርያት በዓል ይከበራል!

ከበረከታቸው ይክፈለን!
https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo

        🕐 ​ታኅሣሥ 26/04/2016 ዓ.ም🕖
 
   በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
   መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፲፰፥፷፯(118፥67)
ወአንሰ ዘእንበለ እሕምም ነሣሕኩ
ወበእንተዝ አነ ዐቀብኩ ነቢበከ
ኄር አንተ እግዚኦ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፯፥፴-፴፯(7፥30-37)
ወፈቀዱ የአኃዝዎ ወባሕቱ...

ምንባባት ዘቅዳሴ

           👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ም ፯፥፴፬-፵(7፥34-40)
ወብእሲትኒ ማዓስብ...

            👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፭፥፲፬-፳፩(5፥14-21)
ወዛቲ ይእቲ እንተ ብነ ገጽ...

             👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፲፬-፲፮(16፥14-16)
ወነበርነ ወአኀዝነ...

            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት


               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፱

፱ የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
      

            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፭ ቊ.፩ - ፲፬
አሜሃ ትመስል መንግሥተ ሰማያት...

        📜ቅዳሴ


👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
<<< በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ >>>

<<< ታሕሳስ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት >>>

+"
#ቅድስት_አንስጣስያ "+

=>እስኪ ዛሬ በጥቂቱ የተባረኩ (ቡሩካት) እናቶቻችን እንዘክር:: "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም
ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ 'ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን:
ኅሪት እምኅሩያን ናትና::

+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና
ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ
ናትና::

+እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::

1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች
ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ
ማርያም)

2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን
ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-
ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው::
እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና
ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

+የእመ ብርሃን ይቆየንና ደግሞ ሌሎች ቅዱሳት እናቶቻችንን እንመልከት:: እናቶቻችን ስናከብር የምንጀምረው በቅድስት ሔዋን ነው:: ብዙ ጊዜ የእናታችን ሔዋን ጥፋቷ እንጂ
በጐ ነገሯ: ደግነቷ: ንስሃዋ አይነገርላትም:: ሆኖም እናታችን ቅድስት ሔዋን ክብር የሚገባት ሴት ናት::

*ክርስቶስ ሰው የሆነ እርሷንና ልጆቿን ለመቀደስ ነውና::

"ከመ ይስዓር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፅ ተሰቅለ" እንዲል::(ድጓ)

+ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን እነ ሐይከል: እድና: ሣራ: ርብቃ: አስኔት: ሲፓራ: ሐና: ቤርሳቤህን የመሰሉ እናቶቻችን
በበጐው መንገድ ፈጣሪን ደስ አሰኝተዋል:: በዘመነ ሥጋዌም
ቅዱሳቱ ሐና: ኤልሳቤጥ: ማርያም: ሶፍያ: ሰሎሜ: ዮሐና እና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በጐነታቸው ያበራል::

+ከዚያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለ2,000 ዓመታት የተነሱ አእላፍ ቅዱሳት እናቶቻችንን ግን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም:: በቅድስናቸው አራዊትን ያሰገዱ: ነገሥታትን ያንቀጠቀጡ:
አጋንንትን የረገጡ: በዘንዶ ላይ የተጫሙ ብዙ እናቶችን ቤተክርስቲያን አፍርታለች::

+ዛሬም ቢሆን በበርሃና በከተማ በጐውን ጐዳና የተከተሉ ብዙ እናቶች እንዳሉን እናውቃለን:: አንድም እናምናለን::
ግን በከተሞች የምንመለከተው ሥርዓቱን የለቀቀው የበርካታ እህቶቻችን አካሔድ ለሃገርም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ ስጋት
ነው:: ክብርና ነውር የማይለይበት ዘመን ይመስላል::

+ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ እህቶቼ! አንድ ነገር ልንገራችሁ:: በመልካቸው ብዙዎችን ያጋጩ: አጊጠው
በመታየታቸው ብዙዎችን ያሰናከሉ: ለብዙ ምዕመናንም የጥፋት ምክንያት የሆኑ ብዙ ሴቶች በታሪክ ነበሩ::

+የሚያሳዝነው ግን ዛሬ ያሉት ከመሬት በታች ነው:: አፈር በልቷቸዋል:: ስም አጠራራቸውም ጠፍቷል:: በጣም
የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬ በዘለዓለማዊው እሳት እየተቃጠሉ በሲኦል:በጥልቁ ውስጥ አሉ::

+እናም ወገኖቼ! ይህን አውቀን እንንቃ:: ይህ ዓለም ጠፊም: አጥፊም ነውና:: እድሜአችን ቢረዝምና ከዚህ
በኋላ ለ100 ዓመታት ብንኖርም እርሱም ማለቁ አይቀርምና::ምርጫችን ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን!!!

+" #ቅድስት_አንስጣስያ "+

+ይህች ቅድስት እንደ በርካቶቹ ቅዱሳት እናቶቻችን ሁሉ የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ናት:: በቀደመችው ታናሽ እስያ
አካባቢ ተወልዳ: የነገሥታት ዘር በመሆኗ ያደገችው በቤተ መንግሥት ነው:: አባቷ ከክቡራኑ አንዱ ቢሆንም ሙያው ጣዖትን ማምለክ ነበር::

+ጊዜው የመከራ በመሆኑ ብዙ ሴቶች የሚኖሩት ክርስትናቸውን ደብቀው ነው:: ከእነዚህ መካከል አንዷ ደግሞ የቅድስት
አንስጣስያ እናት ናት:: ማንን እንደምታመልክ አረሚ ባሏ አያውቅም ነበር::

+አንስጣስያን በወለደች ጊዜም በድብቅ አስጠመቀቻት:: ከሕጻንነቷ ጀምሮም ፍቅረ ክርስትና እንዲያድርባት ነገረ ሃይማኖትን
አስተማረቻት:: ቅድስት አንስጣስያ ወጣት በሆነች ጊዜ ግን ከውበቷ የተነሳ ተመልካቿ በዛ:: እርሷ ግን ይህ ሁሉ
የዓለም ኮተት አይገባትም ነበር::

+በፈጣሪዋ ፍቅር ከመጠመዷ የተነሳ ለመሰል ነገሮች ትኩረት አልነበራትም:: ትጾማለች: ትጸልያለች: ነዳያንና እሥረኞችን ትጐበኛለች:: በዚህም ዘወትር ደስ ይላት ነበር:: ነገር ግን አባቷ ባላሰበችው ጊዜ ለአንድ አረማዊ አጋባት:: በጣም አዘነች: ግን ተስፋ አልቆረጠችምና መፍትሔ ፈለገች::

+ድንግልናዋን እንዳያረክስ በጫጉላዋ ቀን ታመምኩ ብላ ተኛች:: ከዚያ በኋላም አንዴ በልማደ አንስት: አንዴ በሕመም እያመካኘች አላስቀርብ አለችው:: እርሱ የጦር አለቃ በመሆኑ ወደ ጦርነት ሲሔድ እርሷ ታጥቃ ስለ ቀናች እምነት የታሠሩ
ክርስቲያኖችን ታገለግል ነበር::

+ቁስላቸውን እያጠበች: አንጀታቸውን በምግብ እየደገፈች ደስ ታሰኛቸውም ነበር:: ባሏ ሲመለስ ግን ይህንን በመስማቱ ድጋሚ እንዳትወጣ ቆልፎባት ወደ ጦርነት ተመለሰ:: ፈጽማ ስላዘነችበትም እግዚአብሔር በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠውና ሞተ::

+እርሷም ከነ ድንግልናዋ ቀሪ ሕይወቷን ስትመራ መከራው ወደ እርሷ ደረሰ:: ተይዛ ቀርባ በአረማውያን እጅ ብዙ ተሰቃየች:: በዚህች ቀንም ስለ ክርስቶስ ተገድላ ክብረ ሰማዕታትን ተቀዳጀች::

#ቅዱስ_አቦሊ_ጻድቅ

+ቅዱሱ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የክርስቶስን ሕማማት ለመሳተፍ ሲተጉ ከኖሩ ጻድቃን አንዱ ነው:: መሉ ጊዜውን በበርሃ ሲያሳልፍ ብዙ ተጋድሎን ፈጽሟል:: በተለይ ሲጸልይ እግሩን ከዛፍ ላይ አስሮ: ቁልቁል ከባሕር ውስጥ ሰጥሞ ነው:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ዕረፍቱን ታስባለች::

=>አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን: ክብሩን ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::

=>ታሕሳስ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅድስት አንስጣስያ ሰማዕት
2.ቅዱስ አቦሊ ጻድቅ
3.ቅድስት ዮልያና ሰማዕት

=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

++"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ::ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3፥3)