ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
በዋሽንግተን የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተደረገውን መፈንቅለ ሲኖዶስ ለመቃወምና ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የአላቸውን ድጋፍ ለመሳየት በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን በኤምባሲው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተነግራል።

በዕለቱ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በሰልፉ ተወካይ አባቶችንና አስተባባሪዎችን በማነጋገር ጥያቄዎቻቸውን ተቀብለዋቸዋል።

አምባሳደሩም የቀረቡትን ጥያቄዎች ተቀብለው ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል።
በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በመደገፍ የተካሄደው ሠልፍ ፎቶ
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ጥር 26/05/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፷፩፥፲፩(61፥11)
ምዕረ ነበበ እግዚአብሔር ወዘንተ ክመ ሰማዕኩ
እስመ ዘእግዚአብሔር ሣህል
ወዚአከ እግዚኦ ኃይል

📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፲፥፳፪-፴፩(10፥22-31)
ወኮነ በውእቱ መዋዕል...

ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፪ ም ፪፥፩-፰(2፥1-8)
ወዘንተ እንከ መከርኩ በነፍስየ...

👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፱-፲፬(5፥9-14)
አጽንዑ ቀዊመ በሃይማኖትክሙ...

👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፲፬-፲፮(16÷14-16)
ወነበርነ ወአኀዝነ ከመ ንንግር ለአንስት...


📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እበውእ ቤተከ ምስለ መባዕየ
ወእሁብ ብፅዐትየ ዘነበብኩ በአፉየ
ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም ፷፭ ቁ ፲፫-፲፬

፲፫-፲፬ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን ከንፈሮቼም ያሉትን ስእለቴን ለአንተ እፈጽማለሁ።


📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፩ ቊ. ፩ - ፲፱
ወእምዝ ጸለየ በአሐቲ መካን...

📜ቅዳሴ


👉ዘዲዮስቆሮስ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
† እንኳን ለቅዱሳን አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አረጋውያን ሰማዕታት †††

††† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን
ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

የእነዚህ ሰማዕታት ቁጥራቸው 49 ሲሆን አባ ቢስዱራ የሚባል ጻድቅ ሰው 50ኛ ሁኖ ይመራቸው ነበር:: መኖሪያቸው ገዳመ አስቄጥስ (ግብጽ) ሆኖ ዘመኑ 5ኛው መቶ ክ/ዘ ነበር::

ሃምሳውም ሙሉ ዘመናቸውን በምናኔና በቅድስና ፈጽመው በስተእርጅና ደግሞ ሰማዕትነት መጣላቸው:: በ430ዎቹ አካባቢ
የዚያን ጊዜ በርበር ይባሉ የነበሩት አረማውያኑ (የዛሬዎቹ አሕዛብ አባቶች) "ሃይማኖት ካዱ" እያሉ ሰይፍን መዘዙባቸው::

በጊዜው አባ ቢስዱራ በማረፉ ሃላፊነቱን የወሰዱት አባ ዮሐንስ ከአርባ ስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ተስማምተው በበርበር እጅ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል:: ከንጉስ ቴዎዶስዮስ (ትንሹ) ተልኮ የነበረ አንድ ክርስቲያንም በፍቅረ ክርስቶስ ተስቦ ከወጣት ልጁ ጋር ተሰይፏል:: የብርሃን አክሊልም ለሃምሳ አንዱም ወርዷል::

††† አምላከ ቅዱሳን ከተከፈተ ገነት : ከተነጠፈ ዕረፍት በቸርነቱ ያድርሰን::

††† ጥር 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት (ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ)
2.ቅድስት አንስጣስያ (በ5ኛው መቶ ክ/ዘ ከቁስጥንጥንያ ወደ ግብጽ ወርዳ ፡ ንግሥናን ንቃ በበርሃ ስትጋደል የኖረች ቅድስት
እናት ናት::)
3.ቅዱስ ዮሴፍ (መፍቀሬ ነዳያን)
4.አባ ጽሕማ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ኢትዮጵያዊ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ
ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ (ካቶሊኮስ) ባስሊዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ የሕገ ወጡን ሲመተ ኤጲስቆጶሳት በማውገዝ ለቅዱስ ፓትርያርካችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ለሕጋዊዉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያላቸውን ድጋፍ በደብዳቤ ገልጸዋል።

የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጻፉት ደብዳቤ በክርስቶስ የተወደዱ ወንድማችን ለሆኑ ቅዱስነትዎ በሚመሩት ሲኖዶስ ላይ በተከሰተው ክስተት ጥልቅ ኃዘን ይሰማናል ብለዋል።

እኛ ከማላንካራ ኦርቶዶክስ ሶርያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ራሱን ፓትርያርክ በማድረግ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነጠለው ቡድን ድርጊት እጅግ አዝነናል ያሉት ቅዱስነታቸው። በውግዘት የተለዩት ግለሰቦች ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ 26 ኤጲስ ቆጶሳትን መሾም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የተቀደሰ እና ጥንታዊ አስተምህሮና ቀኖና ውጪ ነው ብለዋል።

የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና እርሳቸው ለሚመሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ድጋፏን  ትቀጥላለች ብለዋል።

በደብዳቤው በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ችላ በማለት በተከሰተው ኢ ቀኖናዊ ድርጊት ቤተክርስቲያኗ በጽኑ ታወግዛለች ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ሰላምና አንድነት ትጸልያለች ብለዋል። . "በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጊጉ" (ኤፌሶን 4፡3) እንዳለ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን፣ ኤጲስ ቆጶሳትንና ምእመናንን ሁሉ የጌታ ጸጋ እንደሚደግፋቸውና እንደሚያበረታታቸው ተስፋ እናደርጋለን። የጥንቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ትውፊት ለማስጠበቅ ሊሠሩ እንደሚገባ ችግሩም እንደሚወገድ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል
"በቤተ ክርስቲያናችን እና በሀገራችን የመጣው ችግርና መከራ መፍቻው ቁልፍ ሁለት ነገር ነው እሱም ጾምና ጸሎት እንዲሁም በሰማዕትነት በክርስትና ሞት መሞት"የአንድነት ገዳም ኅብረት መልእክት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአንድነት ገዳም ኅብረት ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም መልእክት አስተላልፈዋል።

አምላክ ሆይ የቤተ ክርስቲያናችንን እና የሀገራችንን ጥፋት አታሳየን!!!!
ዋዛና ፈዛዛ ማስታወቂያን የያዘ ዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ለማድረግ እንደምንጣደፈው ሁሉ #ሃይማኖታዊ_የሆኑ #የሕይወትን_ቃል #የነፍስን_ምግብ የያዙ ዩቲዩብ ቻናሎችን ለመቀላቀል የሚያግደን ነገር ምን ይሆን?

ለማንኛውም ይህቺን ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ መልሱን ከራሳችሁ ጋር ተማከሩበት

https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ጥር 27/05/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፳፮፥፲፫(26፥13)
እትአመን ከመ አርአይ ሠናይቶ ለእግዚአብሔር በብሔረ ሕያዋን
ወተሰፈዎ ለእግዚአብሔር
ተዐገሥ ወአጽንዕ ልበከ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፳፪፥፴፩-፸፩(22፥31-71)
ወይቤሎ እግዚእነ ለስምዖን...

ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብእ ዕብራውያን ፲፩፥፭-፰(11፥5-8)
በተአምኖ ፈለሰ ኄኖክ...

👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ይሁዳ ፩፥፲፩-፲፯(1፥11-17)
አሌ ሎሙ እስመ በፍኖተ ቃየን ሖሩ...

👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፯፥፲፬-፳፪(17÷14-22)
ወፈነውዎ ለጳውሎስ ቢጹ...


📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ አሚረ
ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ
ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፫ ቊ. ፳፪ - ፳፫

፳፪ ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥ እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።

፳፫ አቤቱ፥ ንቃ፤ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን።


📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፩ ቊ. ፰ - ፲፮
ወምንትኑመ ወፃእክሙ ትርአዩ...

📜ቅዳሴ


👉ተንሥኡ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
† እንኳን ለቅዱሳን ቅዱስ ኄኖክ: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ: ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኄኖክ †††

††† ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ቅዱስ ኄኖክ ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ ነው:: አዳም: ሴት: ሔኖስ: ቃይናን: መላልኤል: ያሬድ ብለን ሰባተኛው ኄኖክ ነውና::

ቅዱሱ የማቱሳላ አባትም ነው:: አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረጉም ሞትን ያላየ: ብሔረ ሕያዋን የገባ የመጀመሪያው ሰው ሁኗል:: ለአዳም ልጆችም ተስፋ ድኅነት እንዳለ ማሳያ ሁኗል:: "በአቤል አፍርሆሙ: ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለ ሊቁ::

ቅዱስ ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል (መጽሐፈ ኄኖክን) ከመጻፉ ባሻገር በብዙ ሥፍራ በክብር ተጠቅሶ ይገኛል::

††† ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ †††

††† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መብራት ነው:: ወደ ክርስትና የመጣው በ40ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ሲሆን አሳምኖ ለቅድስና ያበቃው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ነው::

በጊዜውም በነበረው ትጋትና ተጋድሎ ፍሬ አፍርቷል:: ሆዱንም እጅግ ያመው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ሲጠራው "የምወድህ ልጄ" እያለ ነበር:: በኤፌሶንም ጵጵስናን ሹሞ 2 መልዕክታትን ልኮለታል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት አገልግሎ በሰማዕትነት ዐርፏል::
ዛሬ ሥጋው ከኤፌሶን ወደ ቁስጥንጥንያ የፈለሰበት ነው፡፡ ጊዜውም 330ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደሆነ ይታመናል፡፡

"መድኃኒታችን እግዚአብሔር: ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ: በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ::
ከእግዚአብሔር ከአባታችን: ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን: ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን . . ."
(፩ጢሞ. ፩፥፩)

††† ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት †††

††† ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::

በሦስቱ ሰማያት ካሉት ዘጠኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: ለኖኅ መርከብን ያሳራው: ከጥፋት ውኃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው::

††† የይቅርታ ጌታ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አይተወን . . . አይጣለን!

††† ጥር 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገበት)
2.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
3.ቅዱስ አባ ቢፋሞን ሰማዕት
4.ቅዱስ ሰራብዮን ሰማዕት
5.ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት (ከሰባቱ ሊቃናት አንዱ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ
2.አቡነ መባዐ ጽዮን
3.አባ መቃርስ ርዕሰ መነኮሳት
4.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
5.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
6.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ

††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" †††
(፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)