ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
+አባ አብርሃም ጥር 9 ቀን ሲያርፉ አባ ገዐርጊ ግንቦት 18 ቀን ዐርፎ ተቀብሯል:: በዓታቸው በግቢግም ዛሬ ድረስ በምድረ ግብጽ አለች::

=>አምላከ ቅዱሳን አበው በፍቅሩ ይገለጥልን:: ከአባቶቻችን ጸጋ በረከትም አይለየን::

=>ጥር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ አብርሃም ገዳማዊ
2.አባ ገዐርጊ ጻድቅ
3.ቅዱስ ዲዮስቅርስ ዘሮሜ
4.አባ ኪናፎርያ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኹሉ አባት)
3.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

=>+"+ በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል:: +"+ (ምሳሌ 10:6)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

እንኩዋን "ለጾመ ገሃድ" እና "አባ ታውብንስጦስ" ዓመታዊ የእረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ጾመ ገሃድ "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::

+"7ቱ" አጽዋማት:-
1.ዓቢይ ጾም
2.ጾመ ፍልሠታ
3.ጾመ ሐዋርያት
4.ጾመ ነቢያት
5.ጾመ ድኅነት
6.ጾመ ነነዌ እና
7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::

+በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለውና ይቆየን:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል::

+ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን::

+ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት: ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2) አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ. 13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን::

=>"ገሃድ" የሚለው ቃል በቁሙ "መገለጥን : መታየትን : ይፋ መሆንን" የሚያመለክት ሲሆን በምሥጢሩ ግን "የማይታይ አምላክ መታየቱን : የማይዳሰሰው መዳሰሱን" ያመለክታል::

+ወይም በሌላ ልሳን ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም በተዋሕዶ ሰው ከሆነ በሁዋላ ለ30 ዓመታት ራሱን ሳይገልጥ ቆይቶ ነበርና በ30 ዓመቱ ራሱን ለእሥራኤል በዚህ ሰሞን መግለጡን ልብ የምንልበት በዓል ነው::

+መድኃኒታችን ሁሉን ነገር የሚሠራው በጊዜው ነውና ከሥጋዌው በሁዋላ ለ30 ዓመታት: ከስደት መልስ ደግሞ ለ25 ዓመታት የሰውነቱን ምሥጢር በይፋ ሳይገልጥ ቆይቷል:: ያም ሆኖ የሰውነቱን ምሥጢር እርሱ: የባሕርይ አባቱና ቅዱስ መንፈሱ ለድንግል ማርያም ገልጠውላት ታውቀው ነበር:: እርሷ ግን መዝገበ ምሥጢር ናትና ሁሉን ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር:: (ሉቃ. 2:52)

+መድኃኒታችን ከሥጋዌው (ሰው ከሆነባት) ደቂቃ ጀምሮ መግቦቱን አላቁዋረጠም:: ምንም በግዕዘ ሕጻናት ቢኖርም እርሱ በዘባነ ኪሩብ የሚሠለስ ቸር ጌታ ነውና መግቦናል::

+እንደ እሥራኤል ባህል 30 ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ሥግው አምላክ መሆኑን ገለጠ:: የተገለጠውም በጥምቀቱ ሲሆን በዕለቱ ከአብ: ከመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ ልጅነቱን አስመስክሯል:: በባሪያው በዮሐንስ እጅም ተጠምቆ ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶልናል::

+የእዳ ደብዳቤአችን ቀዶ ልጅነታችንን መልሶልናል:: ይህ ሁሉ የተደረገ ለእኛ ነውና በዓለ ኤዺፋንያን (እለተ አስተርእዮቱን) በድምቀት እናከብራለን::

+ነገር ግን ልክ በቅርብ ጊዜ እያየነው እንደሚገኘው በዘፈንና ከአምልኮ ባፈነገጠ መንገድ እንዳይሆን ቤተ ክርስቲያን አበክራ ታሳስባለች:: የመድኃኒታችንን የማዳን ሥራ ከማዘከርና ለእርሱ ከመገዛት ይልቅ ራስን ዘፈን በሚመስል መዝሙር መቃኘቱና ለልብስ ፋሽን መጨነቁ የሚጠቅም አይደለም::

+በዓላት በሚዲያ ታዩ: ተመዘገቡ ብለን ከመዝናናት ትውፊታችንን እያጠፉ ያሉ ድርጊቶቻችን ብንታዘባቸውና ብናርማቸው ይመረጣል:: ስኬታችን ሁሉም ክርስቲያን ለእግዚአብሔር መንግስት መብቃቱ እንጂ በዓል አከባበራችን ዝነኛ መሆኑ አይደለም::

+ጉዳዩ መለኮታዊ እንጂ ፓለቲካዊ አይደለምና ጥንቃቄን ይሻል:: ዛሬ ለታቦተ እግዚአብሔር ክብርን የማይሰጥና ተጋፊ ትውልድን እየፈጠርን ነው:: ካህናትን አለመስማትና ታቦታትን አግቶ አላስገባም ማለት በክርስትና ትርጉሙ ከሰይጣን መወዳጀት ነው:: ስለዚህም በዓል አከከባበራችንን እንታዘብ:: ደግሞም እናርመው::

+*" ጾመ ገሃድ "*+

=>ቤተ ክርስቲያን ጾመ ገሃድን የደነገገች ለ3 ምክንያት ነው:-

1.የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጥሙና እያሰብን በጾም እንድናመልከው::
2.በዓል አከባበራችን እንደ አሕዛብ በተድላ ሥጋ: በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳይሆንና ሰውነታችንን በጾም እንድንገራው::
3.ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ ሲውሉ እህል በነግህ (በጧት) መቀመስ ስላለበት የእርሱ ቅያሪ (ተውላጥ) እንዲሆን ነው::

+ጾመ ገሃድን የሠሩት አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ ያጸኑት ደግሞ ቅዱሳን ሊቃውንት ናቸው:: አጿጿሙም ጥምቀት ከማክሰኞ እስከ ቅዳሜ ከዋለ በዋዜማው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" እንዲሉ አበው እስከ ምሽት 1 ሰዓት ድረስ ይጾማል::

+በዓለ ጥምቀት እሑድ ሲሆን ዐርብን አዘክሮ: በዕለተ ቅዳሜ ደግሞ ከጥሉላት ተከልክሎ መዋል ይገባል:: በተመሳሳይ ሰኞ ቢውል ዐርብን አዘክሮ: ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት (ከሚያገድፉ ምግቦች) ሁሉ ተከልክሎ መዋል ይገባል::

+ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ ነውና የተለየ ግለሰባዊ ችግር እስከሌለ ድረስ ሊጾም ግድ ይላል:: ችግር ካለ ደግሞ ከንስሃ አባት ጋር ሊመክሩ ይገባል::

+*" አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት "*+

=>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም የተነሳ
+ከልጅነቱ መጻሕፍትን የተማረ:
+በክህነት አገልግሎቱ ለብዙዎች አባት የሆነ:
+በምናኔ ወደ ግብጽ የወረደ:

+በእስክንድርያ አካባቢ አበ ምኔት ሆኖ ብዙ መነኮሳትን የመራ::
+በዘመነ ሰማዕታት የተሰደደ:
+ብዙ አሕጉራትን ዞሮ ያስተማረ:

+በትምሕርተ ክርስቶስ ያላመኑትን አሳምኖ : ያመኑትን ያጸና:
+ሽፍቶችን እየገሠጸ ለንስሃ ያበቃ የነበረ ታላቅ አባት ነው::

+በዘመነ ሰማዕታት ስደትን ታግሦ: በሁዋላም በደብረ ሲሐት ተወስኖ ኑሯል:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::
=>አምላከ ቅዱሳን ፍቅሩን: ምሥጢሩን ይግለጥልን:: ከጾመ ገሃድ በረከትም አይለየን::

=>ጥር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ጾመ ገሃድ
2.አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት
3.ቅዱስ ኪናርያ
4.ቅድስት ጠምያኒ

=>ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
7.ቅዱስ እፀ መስቀል

=>+"+ እነርሱ እሥራኤላውያን ናቸውና:: ልጅነትና ክብር: ኪዳንም: የሕግም መሰጠት: የመቅደስም ሥርዓት: የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና:: አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና:: ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ:: እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው:: አሜን:: +"+ (ሮሜ. 9:4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
=>"አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ /የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች"
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ / ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)

=>አምላከ ቅዱሳን በጥምቀቱ ይቀድሰን:: ከበረከተ ጥምቀቱም ያድለን::

=>ጥር 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት
1.በዓለ ኤጲፋንያ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
3.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
4.አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ጳጳሳት
6.ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ቅድስት ሐና ቡርክት

=>"ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ:: እነሆም ሰማያት ተከፈቱ:: የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ: በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ:: እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ:- 'በእርሱ ደስ የሚለኝ: የምወደው ልጄ ይህ ነው' አለ::"
(ማቴ. ፫፥፲፮)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
✞✞ ኃያል ቴዎድሮስ በናድሌዎስ ✞✞+በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ (በአንጾኪያ) ያበራ:
*ድንግልናውን በንጹሕ የጠበቀ:
*ቅዱሳን መላእክት የሚያነጋግሩት:
*የአንጾኪያ ሠራዊት ሁሉ አለቃ የነበረ:
*በጦርነት ተሸንፎ የማያውቅ:
*አሕዛብ ስሙን ሲሰሙ የሚንቀጠቀጡለት:
*ከአማልክት ወገን ነው እያሉ የሚፈሩት
*እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የሚያመልክ የወቅቱ
ወጣት ክርስቲያን ነው::

ዲዮቅልጢያኖስ በካደ ጊዜም ጌታ ከባልንጀሮቹ
ለውንድዮስና ኒቆሮስ ጋር መላእክት ወደ ሰማይ
አሳርገውታል:: በዚያም
መድኃኒታችን ክርስቶስን ፊት ለፊት አይቶ: በእሳት ባሕርም
ተጠምቁዋል:: በዚህች ቀንም ከቅዱሳን ለውንድዮስና
ኒቆሮስ:
እንዲሁ ከ2.5 ሚሊየን ሰራዊቱ ጋር ለመከራ ተሰጥቷል::
እርሱንም በ153 ችንካር ወግተው ገድለውታል::

✞አምላከ ቅዱሳን ወይነ ቃና ፍቅሩን ያሳድርብን::
ከድንግል እናቱ ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::

✞ጥር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቃና ዘገሊላ
2.ቅዱስ ያዕቆብ እሥራኤል
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
4.ቅዱሳን ለውንድዮስ እና ኒቆሮስ
5."2.5 ሚሊየን" ሰማዕታት (የቅዱስ ቴዎድሮስ ማሕበር)

በ 12 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

"+" አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ
አደነቀ:: ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም:: ውሃውን የቀዱት
አገልጋዮች
ግን ያውቁ ነበር:: አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ:- 'ሰው
ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል::
ከሰከሩም
በኋላ መናኛውን:: አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ
አሁን አቆይተሃል' አለው:: (ዮሐ. 2:9)

✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
+በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው:: እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::

+ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል" በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ:: (ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው)

+በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም: ሊቀ ዻዻሱም (አባ ቴዎድሮስ ይባላል) ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው: 7ቱንም ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ ነበር:: 7ቱም ለ7 ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ: ሰውን ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::

+ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ መናፍቃን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ ሃይማኖት ተመልሰዋል:: 7ቱ ቅዱሳን ግን በ7ኛው ቀን በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ በ7 የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
ጥር 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ኢትዮዽያዊ (እረፍታቸው)
2.ሰባቱ ደቂቅ ቅዱሳን (ከኤፌሶን)
3.ቅዱስ አባ ነካሮ
4.ቅዱስ ቃሮስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ቅዱስ አስከናፍር
4."13 ግኁሳን ጻድቃን"
5.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ
6.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት

=>+"+ በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ:: ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል:: የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+ (2ቆሮ. 13:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
ወደ ምድረ ሶርያ ደርሰው በታላቁ ደብረ ሮማኖስ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ:: በእጃቸው የነበረውን 200 ዲናር ወርቅም ለገዳሙ አበረከቱ:: ለጥቂት ጊዜ በገዳሙ ካገለገሉ በሁዋላም ጾማዕት (በዓት) ተሰጣቸው::

በዚህ ጊዜም "እንግዲህ ወደ ዓለም አልወጣም:: የሴቶችን መልክም አልመለከትም" ሲሉ ቃል ገቡ:: በተጋድሏቸውም በጾምና በጸሎት: በትጋሃ ሌሊት ለ12 ዓመታት ቀጠሉ:: ጾማቸውም 7 ቀን ነበር:: አምላክ ጸጋውን ስላበዛላቸውም ብዙ ድውያንን ፈወሱ::

ዜናቸውም እስከ ምድረ ሮሜ ተሰማ:: እናታቸው (ሰንደሊቃ) የመርከቡን ዜና ከሰማች በሁዋላ የሞቱ መስሏት አልቅሳ ቤቷን የእንግዳ ቤት አድርጋ: በበጎ ምግባር ትኖር ነበርና አንድ ቀን የልጇን ዜና ሕይወት ሰማች::

ከደስታዋ የተነሳ ፈጥና ወደ ደብረ ሮማኖስ ደርሳ "ልጄን ልይ" አለች:: ግን "ሴትን አላይም" ብለው አባ አርከሌድስ ቃል ገብተዋልና ምን ይሁን! ሰንደሊቃም "አራዊት ይብሉኝ እንጂ ልጄን ሳላይ አልሔድም" አለች:: ወዲያው ግን "አባ አርከሌድስ ፈቅደዋልና ግቢ" የሚል መልእክት መጥቶላት ገባች::

ግን ያገኘችው የጻድቁን ልጇን ሥጋ ነበር:: ምክንያቱም የፈጣሪንም: የእናታቸውንም ልብ ላለማሳዘን እንዲወስዳቸው ለምነውት ዐርፈው ነበር:: እናትም በልጇ ሥጋ ላይ እያለቀሰች እዚያው ዐረፈች:: "አብራችሁ ቅበሩን" የሚል ቃል ከቅዱሱ ሥጋ ስለ ተሰማም አብረው ቀብረዋቸዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

††† ጥር 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ አባ መክሲሞስ
3.ቅዱስ አባ አርከሌድስ
4.ቅድስት እምራይስ
5.ቅድስት ምሕራኤል
6."4034"ሰማዕታት (ማሕበራነ ቅዱስ ቂርቆስ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ስምዖን
2.አባ ዮሐንስ
3.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ (ሙሽራው)
4.ቅዱስ ሙሴ
5.ቅዱስ ፊልዾስ (ከ72 አርድዕት)
6.ቅድስት ነሣሒት

††† "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. 36:28)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
††† እንኳን ለሰማዕታት ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ: ወነቢይ አብድዩ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

ቂርቆስ ወኢየሉጣ

††† ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሏት ዐበይት ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ ቂርቆስ ነው:: በተለይ በዘመነ ሰማዕታት ተነስተው እንደ ከዋክብት ካበሩትም አንዱ ነው:: ቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይላል:- "መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራል::" (ማቴ. 7:17)

መልካም ዛፍ ቅድስት ኢየሉጣ መልካም ፍሬ ብጹዕ ቂርቆስን አፍርታ ተገኝታለችና ክብር ይገባታል:: ቡርክተ ማሕጸንም እንላታለን:: የተባረከ ማሕጸኗ የተባረከ ልጅን ለ9 ወር ተሸክሟልና::

በዚያ ክርስቲያን መሆን መከራ በነበረበት ዘመን ይህንን ደግ ሕጻን እርሷን መስሎ: እርሷንም አህሎ እንዲገኝ አስችላለችና:: አበው በትውፊት እንዳቆዩልን ከሆነ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን እናታችን ቅድስት ኢየሉጣ ብጹዕ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስን ወልዳለች::

በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ክርስትና ቢስፋፋም በዚያው ልክ መምለክያነ ጣዖቱ የገነኑ ነበሩ:: በተለይ ከነገሥታቱ ጀምሮ ዋና ዋና የሥልጣን ቦታዎች በአሕዛብ እጅ በመሆናቸው ለዘመኑ ክርስቲያኖች ፈታኝ ነበር::

ማንኛውም ክርስቲያን መሠረታዊ ፍላጐቶቹ እንዲሟሉለት አሕዛብ ላቆሟቸው ጣዖቶች መንበርከክ ነበረበት:: መብቱን ከመገፈፉ ባሻገር "ተበድያለሁ" ብሎ ወደ ፍርድ ቤት ሔዶ እንኩዋ የመጮህ እድል አልነበረውም:: ምክንያቱም የሚሰማው አልነበረም::

በዚያ ላይ በየጊዜው ለክርስቲያኖች ፈታኝ የሆኑ አዋጆች ይወጣሉ:: የክርስትናን ጐዳና ይበልጥ የሚያጠቡ ሕጐችም ዕለት ዕለት ይፈበረኩ ነበር:: ስለዚህም በወቅቱ የነበረ አንድ ክርስቲያን ሃይማኖቱን ከወደደ ወይ እስከ ሞት መታገስ: ካልሆነ ደግሞ ሃገርን ጥሎ በዱር: በገደል መሰደድ ነበረበት::

እውነት ለመናገር ዜና ሰማዕታትን የማያውቅ ክርስቲያን ክርስቶሳዊ ነው ሊባል አይችልም:: ምክንያቱም ዛሬ እንዲህ እንደ ዋዛ የያዝናት ሃይማኖታችን እንዴት እንደ መጣችና ምን እንደ ተከፈለባት አብዛኛው ትውልድ አያውቅምና::

ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ብጽዕት ኢየሉጣም የዚህ ዘመን (የዘመነ ሰማዕታት) ፍሬ ናቸው:: በጊዜው በሮም ግዛት ሥር እስክንድሮስ የሚሉት ክፉ ንጉሥ ነግሦ ነበርና ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ:: ጣዖትን ላለማምለክም ተሰው::

በዚህ ጊዜ አንጌቤናይት (ኢጣልያዊት) ብጽዕት ኢየሉጣም በመበለትነት (ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ) ትኖር ነበር:: ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ምንም ገና 3 ዓመቱ ቢሆንም ነገረ ሃይማኖትን ታስተምረው: ፍቅረ ክርስቶስን ትስልበት ነበር::

እስክንድሮስ የክህደት አዋጅን ሲያውጅም ቅድስቲቱ ለሕጻን ልጇ ራርታ ሽሽትን መረጠች:: ሃብት ንብረቷን: ወገንና ርስቷንም ትታ: ሕጻን ልጇን ተሸክማ ተሰደደች:: መከራው ግን በሔደችበት አለቀቃትም::

እስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታም አገኛት:: ወታደሮች ልጇን ሳያገኙ እርሷን ብቻ ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧት:: መኮንኑም "ስምሽን ንገሪኝ" ቢላት "ስሜ ክርስቲያን ነው" አለችው:: ተቆጥቶ "ትክክለኛውን ስምሽን ተናገሪ" ቢላት "እውነተኛው ስሜ ክርስቲያን ነው:: ሞክሼ (ሞክሲ) ስም ከፈለግህ ኢየሉጣ እባላለሁ" አለችው::

"ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል" ሲላትም "እውነትን ይነግረን ዘንድ የ3 ዓመት ሕጻን ፈልገህ አምጣና ተረዳ" ስላለችው ወታደሮቹን እንዲፈልጉ ላካቸው:: የሃገሩ ሰዎች ልጆቻቸውን ስለደበቁ የተገኘ ቅዱስ ቂርቆስ ነበር::

ቅዱሱ ሕጻን በወታደሮች ተይዞ ሲቀርብ መልኩ ያበራ ነበርና መኮንኑ "በሐከ ፍሡሕ ሕጻን - ደስ የተሰኘህ ሕጻን እንዴት ነህ" ቢለው "ትክክል ነህ! እኔ በጌታየ ክርስቶስ ዘንድ ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን በክህደትህ ወደ ገሃነም ትወርዳለህ" አለው::

በሕጻኑ ድፍረት የደነገጠው መኮንኑ በብስጭት "እሺ! ስምህን ንገረኝ" አለው:: ያን ጊዜ "ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ: ስሜ ክርስቲያን ነው:: እናቴ የሰየመችኝን ከፈለክ ግን ቂርቆስ ነው" ሲል መለሰለት::

ከዚያም እየደጋገመ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በመጮሁ መኮንኑ ስቃይን በቅዱሱ ሕጻን እና በቡርክት እናቱ ላይ አዘዘ:: ከዚህ በሁዋላ በእነርሱ ላይ የተፈጸመውን ግፍና የወረደባቸውን የመከራ ዶፍ እናገር (እጽፍ) ዘንድ ግን የሚቻለኝ አይመስለኝም::

በግርፋት የጀመረ ስቃይ ሊሰሙት ወደ ሚጨንቅ መከራ ቀጠለ::
*7 ብረት አግለው በዐይናቸው: በጆሯቸው: በአፋቸውና በልባቸው ከተቱ::
*በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው::
*በእሳት አቃጠሏቸው::
*ጸጉራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈፉ::
*ከዚህ በላይ ብዙ ስቃይንም አመጡባቸው::

እናትና ልጅ ግን ለክርስቶስ ታምነዋልና ጸኑ:: ቅድስት ኢየሉጣ ብትደነግጥ ልጇ አጸናት:: ከብዙ ስቃይና መከራ በሁዋላም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት ሲያርፉ ጌታ እንደ ቃሉ የሕጻኑን ሥጋ በሠረገላ ኤልያስ አኑሮታል:: ለእኛ የሚጠቅም ብዙ ቃል ኪዳንንም ሰጥቶታል::

††† ቅዱስ አብድዩ ነቢይ †††

††† "አብድዩ" ማለት "የእግዚአብሔር አገልጋይ" ማለት ነው:: ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን የቅዱስ ኤልያስ ታላቁም ደቀ መዝሙር ነው:: ቅዱሳን ነቢያት ዮናስና ኤልሳዕም ባልንጀሮቹ ነበሩ::

ቅዱስ አብድዩ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የከሃዲው ንጉሥ የጦር መሪ ሆኖ በሃምሳ አለቃነት አገልግሏል:: ግፈኛዋ ኤልዛቤል ነቢያተ እሥራኤልን ስታስፈጅ 50ውን በአንድ ዋሻ : 50ውን ደግሞ በሌላ ዋሻ አድርጐ አትርፏቸዋል:: 900ው ግን ተጨፍጭፈዋል::

ያተረፋቸውንም ክፉ ዘመን እስኪያልፍ ድረስ መግቧቸዋል:: አክአብና ኤልዛቤል ከሞቱ በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስን ተከትሎ ሹመቱን ትቷል:: እግዚአብሔር ገልጾለትም ትንቢት ሲናገር: ሕዝቡንም ሲገሥጽ ኑሯል::

በብሉይ ኪዳን ካሉ የትንቢት መጻሕፍትም በጣም አጭሩን የጻፈው ይሕ ነቢይ ነው:: ትንቢተ አብድዩ ባለ አንድ ምዕራፍ ብቻ ናትና:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወገኖቹ ቀብረውታል::

††† አምላከ ሰማዕታት በምሕረቱ ይማረን:: በይቅርታው ኃጢአታችንን ይተውልን:: ከበረከተ ሰማዕታትም ይክፈለን::

††† ጥር 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ
2.ቅዱስ አብድዩ ነቢይ
3.ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
4.ቅድስት ሶፍያ
5.ቅድስት አድምራ
6."11,004" ሰማዕታት (ከቅዱስ ቂርቆስ ጋር በሰማዕትነት ያለፉ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
2.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
3.ቅድስት ክርስጢና
4.ቅድስት እንባ መሪና

††† "በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር: ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ: በልብህም:- 'ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው?' የምትል አንተ ሆይ! የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል:: እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ: ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን: 'ከዚያ አወርድሃለሁ' ይላል እግዚአብሔር::" †††
(አብድዩ 1:3)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር
†††

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
ቅዱስ ፊላታዎስ ግን ላሙን አስገድሎ: ወላጆቹን ከሞት አስነስቶ ከአካባቢው ሰው ጋር በስመ ሥላሴ አስጠምቁዋቸዋል::

+በድንግልና ኑሮም ዘመነ ሰማዕታት ሲጀምር በርጉም ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ብዙ ተሰቃይቷል:: በጸሎቱም ጣዖታቱን (እነ አዽሎንን) ከነ አገልጋዮቻቸው ወደ ጥልቁ አስጥሟቸዋል:: እርሱም በዚህች ቀን በሰይፍ ተከልሎ ለክብር በቅቷል:: ለእኛ ለኃጥአን የሚሆን ቃል ኪዳንንም ከጌታው ተቀብሏል::

=>የቅዱሳን አባቶቻችን አማናዊት ርስት ድንግል ማርያም አትለየን::

=>ጥር 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት
2.አባ ዸላድዮስ ገዳማዊ
3.ማር ዳንኤል ሶርያዊ
4.አባ ዮሐንስ መሐሪ (ሊቀ ዻዻሳት)
5.11,004 ሰማዕታት (የቅ/ቂርቆስ ማሕበር)
6.11,503 (የቅ/ፊላታዎስ ማሕበር)
7.አባ ጽሕማ (ከተስዓቱ ቅዱሳን አንዱ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.በዓለ ኪዳና ለድንግል
2.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.ቅድስት ኤልሳቤጥ
5.አባ ዳንኤል
6.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
7.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ

=>+"+ ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል::
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል::
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል::
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ::
ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ::
ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ:: +"+ (መዝ. 91:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
+በተመሳሳይ ቅዱሳኑ ሲወስዱት 2ቱንም ቅዱሳን ታላቁ
መቃርስ በበዓታቸው ቀብሯቸዋል:: ቦታውም ደብረ
ብርስም (በርሞስ)
ተብሏል:: ትርጉሙም የሮማውያኑ ቅዱሳን ደብር እንደ
ማለት ነው::

✞አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም
ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን::
ክብራቸውንም አያጉድልብን::

✞ጥር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን እና ክቡራን የሚሆኑ አባቶቻችን "መክሲሞስ
እና ዱማቴዎስ"

በ 17 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

++"+ ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር
አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም::
ብቻዬን
ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን
አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ
ደስ
አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን
ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል:: +"+ (1ቆሮ. 13:4)

✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)