ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ማስረጃ_3
በመጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔር_ነው

ሕይወትን የሚሰጥ መግደልም ማዳንም የሚችለው የባሕርይ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ራሱን በብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ላይ የገለጠ ሲሆን ፣ በተመሳሳይ መልኩ ይህንን ሕይወትነቱን በሙሴ መጻህፍት ያናገረው ርሱ እግዚአብሔር ሥጋን ተዋህዶ ዘላለማዊ ሕይወትን የሚያድል ርሱ እንደሆነ ሲናገር ፦

"አሁንም እኔ ብቻዬን እንደሆንሁ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ ፡#እኔ_እገድላለሁ_አድናለውም_እኔ_እመታለው_እፈውስማለው፣ ከእጄም የሚያድን የለም " (ዘዳ32:39)

"አብ ሙታንን እንደሚያነሳ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው ፡እንዲሁ #ወልድ_ደግሞ_ለሚወዳቸው_ሕይወትን_ይሰጣቸዋል... እኔም #የዘላለም_ሕይወትን_እሰጣቸዋለሁ፡ለዘላለምም አይጠፋም ፡ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም ።(ዮሐ5:21)
ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ህይወት ያላቸው ነገሮችን የፈጠረ ህይወትም የሚሰጥ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው

Comment @zekidanemeheretbot

🕊👉@zekidanemeheret
#ማስረጃ_4
በመጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔር_ነው

በብላቴናነቱ በእግዚአብሔር የተጠራው ካህኑ ሳሙኤልም ሕዝበ እስራኤልን ሰብስቦ እግዚአብሔርን መከተል እንደሚገባቸውና፣ ያም መልካም እንደሆነ ነግሯቸዋል ፤ ዘመኑ ሲፈፀም ነቢዩ ሳሙኤል ይህንን የተናገረለት እግዚአብሔር ሰውን ሆኖ የሚከተለው የሕይወት ብርሃን እንደሚሆንለት ሲያስተምረን ፦

"እግዚአብሔርን ብትፈሩ ብታመልኩትም ቃሉንም ብትሰሙ በእግዚአብሔርም ትዕዛዝ ላይ ባታምፁ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ #አምላካችሁን_እግዚአብሔርን_ብትከተሉ መልካም ይሆንላቹዋል ። "(1ኛሳሙ12:14)

"ደግሞም ኢየሱስ ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ፣ #የሚከተለኝ_የሕይወት_ብርሃን_ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው ። (ዮሐ8:12)

Comment @zekidanemeheretbot

🕊👉@zekidanemeheret
#ማስረጃ_6
በመጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ(ዶ/ር)

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔር_ነው

ከሕፃንነቱ ዠምሮ ጥበብ የተቸረው ፣ በ12ዓመቱ የነገሠው ሰሎሞን ፤ ቤተ መቅደሱን ሰርቶ በፈፀመ ጊዜ እግዚአብሔር ብቻ ሰዎች በልቡናቸው ያሰቡትን የሚያውቅ መሆኑን መስክሯል ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊም በተመሳሳይ መልኩ የሰውን ሥጋ የተዋሐደው ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልቡና የታሰበውን ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አስረግጦ ሲተነትንልን ፦

#አንተ_ብቻ_የሰውን_ልጆች_ሁሉ_ልብ_ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው"(1ኛነገ 8:39)

"#ነገር_ግን_ኢየሱስ_ሰዎችን_ሁሉ_ያውቅ_ነበር ፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸው ነበር ፤ #ራሱ_በሰው_ያለውን_ያውቅ_ነበርና" (ዮሐ 2:25) ። ስለዚህ የሰውን ልብ የሚያውቀው እሱ ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው

comment @zekidanemeheretbot

🕊👉@zekidanemeheret
#ማስረጃ_7
#ኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔር_ነው
በመጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)

የባሕርይ አምላክ ለሆነው ለርሱ ብቻ ለልዑል እግዚአብሔር የአምልኮት ስግደት የሚገባው ነውና የሰማይ ሰራዊት እንደሚሰግዱለት ነህምያ የመሰከረ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ መልኩ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ለሆነው ለሥግው ቃል ለክርስቶስ መላእክት የአምልኮት ስግደት እንደሚሰግዱለት ቅዱስ መጽሐፍ ሲገልጥልን ፦

"አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሰራዊታቸውንም ሁሉ ምድሩንና በርሷ ላይ ያሉትን ሁሉ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ ፈጥረሀል ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል #የሰማዩም_ሰራዊት_ለአንተ_ይሰግዳሉ" (ነህ9:6)

"ደግሞም በኩርን ወደ ዓለም ሲያገባ #የእግዚአብሔር_መላእክት_ሁሉም_ለርሱ_ይስገዱ" (ዕብ 1:6)
"ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች #ያሉት_ሁሉ_በኢየሱስ_ስም_ይንበረከኩ_ዘንድ ነው ። (ፊሊጵ 2:10)
ስለዚህ ጉልበት ሁሉ የሚሰግዱለትና የሚንበረከኩለት #ኢየሱስ_ክርስቶስ እርሱ #እግዚአብሔር ነው

comment @zekidanemeheretbot

🕊👉@zekidanemeheret
#ማስረጃ_8
በመጋቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔር_ነው

ሀብተ ዝማሬ የተሰጠው ቅዱስ ዳዊት ፣ የእግዚአብሔር ሕግ ፍፁምና ርሱንም መጠበቅ እንደሚገባን በመዝሙሩ ሲመሰክር ፤ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት እግዚአብሔር ነውና ሕጉን መጠበቅ እንዲገባ እንዲህ ሲል ይመሰክራል ፦

#የእግዚአብሔር_ሕግ_ፍፁም_ነው ነፍስን ይመልሳል ።(መዝ 19:7)

#ከእናንተም እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም #የክርስቶስን_ሕግ_ፈፅሙ (ገላ 6:2)። ክርስቶስ ህግን የሰራልን እግዚአብሔር ነው

comment @zekidanemeheretbot

🕊👉@zekidanemeheret