ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
Voice message
ለሃሳብ አስተያየት
👉 @zekidanemeheretbot ላይ ላኩልኝ፡፡
👉 @zekidanemeheretbot ላይ ላኩልኝ፡፡
3.በግድ ለመፈቃቀር የሚደረግ ጥምረት
ብዙ ወጣቶች በግድ ፍቅር ለማምጣት ይሞክራሉ፣ ፍቅርን መቆጣጠር እንደማይቻል እያወቁ በግድ ሳያፈቅሩ ለማፍቀር፣ ሳይፈቃቀሩ ለመፈቃቀር ይሞክራሉ፡፡ እንዲህ አይነት ወጣቶች የፍቅር ጓደኛ ያልያዙ "በሴት(በወንድ) ልጅ ለመፈቀር ምን ላድርግ፣ ሴትን(ወንድን) የመማረክ ጥበብ፣ የማፍቀር/ የመፈቀር ጥበብ..." የሚሉ መጣጥፎችን ካገኙበት እያፈላለጉ በመተግበር በግድ ለማፍቀር እና ለመፈቀር ይሞክራሉ፡፡ በብዛት እንዲህ አይነት ወጣቶች ፍላጎታቸውና ጥረታቸው ለመፈቀር እንጂ ለማፍቀር አይደለም፡፡ ያን ሰው እንዴትም ካሳመኑ እነሱ ያን ሰው ለማፍቀር ቀላል ይመስላቸዋል፡፡ሊማርኩ ያሰቡትን ሰው በልዩ አነጋገር፣ በአለባበስ፣ በልዩ አስተሳሰብ፣ በድርጊት....ለመሳብ ይጥራሉ፡፡ እንደነዚህ አይነት ወጣቶች ተሳክቶላቸው እንኳን የፍቅር አጋር ቢይዙም ሁሉ ነገራቸው አርቴፊሻልና ከልብ ያልመነጨ ነው፡፡ የሚጠቀሟቸው ቃላት አርቴፊሻል የሆኑ ናቸው (የኔ ማር፣ የኔ ፍቅር፣ የኔ ህይወት፣ ቁርስ በላሽ፣ እራት በላሽ፣ ነፍሴ፣ ውዴ፣ ህይወቴ፣ አንቺን አጥቼ መኖር አልችልም....) አርቴፊሻል የሆኑ ልባዊ ጣዕም የሌላቸው ቃላት፡፡ ተግባራቸውም ልባዊ የሆነ አይነት አይደለም (የተለያዩ ግብዣ ማድረግ፣ የከንፈር ወዳጅ መሆን፣ ሲኒማ ቤቶች እና ጭፈራ ቤቶች መሄድ...) በአብዛኛው የአርቴፊሻል ፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሁለቱም ጋር ልባዊ የሆነ ኃያል ስሜት ንፁህ ፍቅር የለም፡፡ እውነተኛ ፍቅር በዕቅድ ወይም በፕሮቶኮል የሚመራ ሳይሆን በሁሉም ግንኙነት እንዲሁ መደሰት ነው፡፡
4......
ይቀጥላል ......
👉ሼር ይደረግ
ለሃሳብ አስተያየት 👇👇👇👇👇
@zekidanemeheretbot
የተለያዩ ትምህርቶች ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
@zekidanemeheret

4.ፍትወትን መሠረት ያደረገ ፍቅር
የአንዳንድ ወጣቶች ስሜት ወደድኩ የሚሉትን ሰው በስጋ ለማወቅ የሚደረግ ችኩልነት ነው፡፡ ያ መተዋወቅ ይዞ የሚመጣውን መዘዝ ካለማስተዋል ነገ ችግር ይዞ ይምጣም አይምጣም እሱን ሳያስቡት የሚያስደስታቸውና የሚናፍቁት "ወደድኩት/ ወደድኳት" ካሉት ሰው ጋር በፍትወት መውደቅ ብቻ ነው፡፡ በአብዛኛው ወጣቶች ዘንድ ብዙም ባይታይም በጥቂቶች ውስጥ ግን ስር የሰደደ ፍላጎት ሆኖ ተቀምጧል፡፡አንዳንድ ሴቶች "ክብሬን ብሰጠው ምን ያህል እንደማፈቅረው ይገልጽልኛል" የሚል በወንዶች ደግሞ "ይህን ብንፈጽም መቼም ብትለየኝም አትረሳኝም" የሚል ከንቱ ከፍቅር የመነጨ ሳይሆን ከራስ ወዳድነትና ካልተገባ አጉል መስዋዕትነት የመነጨ ክፉ አስተሳሰብ አለ፡፡ ሁለቱም ደግሞ "ፍቅርን ያጠነክራል" በሚል ክፉ አስተሳሰብ ይህን ለመፈፀም ያስባሉ፡፡ በስጋ ፈቃድ መተዋወቅ ከትዳር በፊት ሲሆን ፍቅርን አጥፍቶ ጥላቻን ያመጣል እንጂ ፍቅርን አያጠነክርም፡፡ይህን ከዳዊት ልጅ ከአምኖን እንማራለን፡፡ አምኖን ከትዕማር በፍቅር በመጠመዱ እስከመታመም ደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን የስጋ ፈቃዱን አታሎና አስገድዶ ከፈጸመ በኋላ ቅድምያ ከወደዳት መውደድ በላይ በኋላ የጠላት ጥላቻ በለጠ 2ኛ ሳሙ 13÷1-30 የአምኖን ፍቅር እውነተኛ አልነበረም የዝሙት ፍላጎት እንጂ! ዛሬም አንዳንድ ወጣቶች በአምኖናዊ ጾር በመነደፋቸው የሌላውን ሕይወት ለማበላሸት ላይ ታች ይላሉ፡፡ በጣፋጭ ቃላት በፍቅር ስም ይሸነግላሉ ያታልላሉ፡፡ አንዴ የስጋ ፈቃዳቸውን ከፈጸሙ በኋላ ግን ሌላ ሰው ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ መንፈሳዊያን ወጣቶች ይህን ልናውቅና ልንጠቀቅ ልናስተውልም ይገባል፡፡ ከሚታለሉትም ከሚያታልሉትም ፈፅሞ መሆን የለብንም፡፡
መንፈሳዊያን ወጣቶች ከላይ በተዘረዘሩት ጥምረት ካልገቡ መጠንቀቅ ከገቡ ደግሞ መውጣት አለባቸው፡፡

❤️❤️ ክፍል 14
❤️❤️ ማጠቃለያ
👉ፍቅር እውር አይደለም ምክንያቱም "ፍቅር የማይገባውን አያደርግም"
1ኛ ቆሮ 13÷5
👉ሰው ክብሩን በልብስ ይገልጣል፡፡
እግዚአብሔር የሚወደደው ከራስ በላይ ነው፡፡
"የውሃ ብዛት ፍቅርን አያጠፋትም"
የውሃ ብዛት ማለት የመከራ ብዛት ነው፡፡ጽኑ ፍቅርን የመከራ ውሃ አያጠፋትም፡፡ በስሜት የተነሳ ፍቅር ስሜቱን የሚያቀዘቅዝ በመጣ ጊዜ ይጠፋል፡፡
👉ባል👈 ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በሚወድበት መጠን ሚስቱን መውደድ አለበት፡፡
👉 ሚስት👈 ቤተክርስቲያን ክርስቶስን በምትወድበት መጠን ባሏን መውደድ አለባት፡፡
🕊ከመጀመሪያው ጀምሮ በማስተዋል ማንበባችሁን አስተውሉ!
እግዚአብሔር አምላክ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው መንገድ ሰጥቶ ጥምረቱን ይባርክ!!🙏🙏🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለሃሳብ አስተያየት👇👇👇👇👇
@zekidanemeheretbot
የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት

♦♦መሳሳም ይቻላል?♦♦
ሁለት እጮኛሞች ከጋብቻ በፊት ራሳቸውን ገዝተው መቆየት እንደሚኖርባቸው አስባለሁ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች መሳሳም ምንም አይደል የፍቅር መገለጫ ነውና ይቻላል ይላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ወጣቶችን ወደ ሌላ ሊወስድ ይችላል እናንተስ ምን ትላላችሁ
✍✍ መልስ፡- ✍✍
‹‹የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ ነው›› እንደሚባለው እና እንዳሳሰብዎትም ይህ የጠቀሱት አባባል አግባብ አይደለም፡፡ ራስን መግዛት እና የስጋን ፍላጎት መግታት በሚያስቸግርበት የወጣትነት ዘመን ራስን ለፈተና ማጋለጥ ይሆናል፡፡ ብዙ ወጣቶችም ‹‹ምን አለበት? እኔና አንቺ እስከተዋደድን፣ እኔም ያንቺ አንቺም የኔ›› በሚል ሰበብ ራሳቸውን መጠበቅ ተስኗቸው ወድቀዋል፡፡ ሁልጊዜ ምድጃ ዳር የሚያንቀላፋ ሰው አንድ ቀን መቃጠሉ አይቀርም፡፡ እና አቅምን አውቆ መጠንቀቁ ይበጃል፡፡ የዝሙትን ፈተና በመሸሽ እንጂ ቆሞ በመታገል ማምለጥ አይቻልም፡፡ ዘፍ.39÷9፣ 1ኛ ቆሮ 6÷18
ባለመጠንቀቅ እና ነገን ካለማሰብ ብዙ ወጣቶች ንጽህናቸውን አጥተዋል፡፡ ከቅድስት ቤተክርስቲያንም ርቀዋል፡፡ ከዚያን አልፎ የብዙ እህቶቻችን ሕይወት በአጭር እስከመቀጨት ደርሷል፡፡ በመሆኑም አንድ ችግር ከመከሰቱ በፊት ራስን በመግዛት ዘላቂውን ኑሮ በማሰብ የጋብቻን እለት በትዕግስት መጠበቅ ይገባል፡፡ የመተጫጨት ዋና አላማ መዳራት እና የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም አይደለም እየተሳሰቡ እና እየተጠባበቁ ለቅዱስ ጋብቻ የሚበቁበትን እለት መጠበቅ ነው እንጂ!!
👉 " የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።"
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4 ÷3

ፍቅር ካለ እግዚአብሔር አለ።እግዚአብሔር ካለ ደግሞ ሁሉ ነገር አለ። ፍቅር ማለት ፍጹም ሰው ፈልጎ ማግኘትና መውደድ ሳይሆን፣ ጎዶሎውን ሰው ፍጹም አድርጎ መቀበል ነው።
የሕይወት አጋሬን እንዴት ልምረጥ
“ፍቅር ይዞኛል” “አፍቅሬአለሁ” ማለት በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ወጣትነትወንዶች ሴቶችን ሴቶችም ወንዶችን ለፍቅር የሚመርጡበት እድሜ ነው፡፡ በወጣትነት ዘመንበተቃራኒ ጾታ መሳብ፤ የራስን ሰው ለማግኘት ጊዜ ወስዶ ማሰብና መጨነቅ የተለመደ ክስተትነው፡፡ መፈላለግ ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ሁሉም ለቁም ነገር ነው ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ በዚህየተነሣ ወጣቶች ተቃራኒ ጾታን ለጓደኝነት የሚመርጡባቸውን ምክንያቶች በሚገባ ማወቅ አስፈላጊያቸው ነው፡፡ የተወሰኑትን ምክንያቶች በዚህ ትምህርት ለማየት እንሞክራለን፡፡
1. ወጣቶች የተቃራኒ ጾታ ጓደኛ የሚይዙባቸው ምክንያቶች
ሀ. ጓደኛ የለውም (የላትም) እንዳይባሉ፤
ለ. ሌሎች ሲይዙ በማየት፤
ሐ. ለሩካቤ ሥጋ ፍላጎት (ለዝሙት) (2 ሳሙ 13፡11)፤
መ. በፍቅር ስለወደቁ (ዘፍ. 34፡3)፤
ሠ. የትዳር ጓደኛ ፈልገው (ዘፍ. 29፡18)፤
ረ. ለቁሳዊ ጥቅም ብለው (መሳ. 16፡5)
ሰ. በፉክክር ስሜት፣ ሌሎችም ለማናደድ ሲፈልጉ ወ.ዘ.ተ፡፡
2. የሕይወት አጋርን የምንመርጥባቸው ደረጃዎች፡-ወጣቶች የፍቅር ጓደኛ መፈለጋችሁ ኃጢአት ሳይሆን ተፈጥሮአዊ እና ጤናማ ስሜት ነው፡፡ነገር ግን ይህን የተቀደሰ ፍላጎት ያለ ጊዜው፣ በተሳሳተ ምርጫ እና ጤናማ ባልሆነ ፍላጎት እንዳናበላሸው ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መመዘኛዎችና ደረጃዎችን ማጤን ትክክለኛ ውሳኔ እንድንወስን ያስችለናል፡፡ እንዲሁም ያለጊዜው ባደረግነው ያልተገባ ግንኙት ወይምበተሳሳተ ምርጫችን እንዳንጸጸት ያደርገናል፡፡
2.1. አካላዊ ብቃት፦
ወንዶች ለአቅመ አዳም ሴቶች ለአቅመ ሔዋን መድረሳችንን፤ ሰውነታችን ሌላ ሰውን ለመቀበል የተዘጋጀ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡
2.2. መንፈሳዊ ብስለት፡-
በመንፈሳዊ ሕይወት ጠንካራ መሆናችንን እንዲሁም ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ መንፈሳዊብስለት እንዳለን ለማረጋገጥ ራሳችንን ማየት ተገቢ ነው፡፡ በሕይወታችን ወይም በኑሮአችን ሁሉእግዚአብሔርን እንደምናስቀድም፣ የጸሎት ሕይወታችን ምን እንደሚመስል፣ መጽሐፍ ቅዱስንየማንበብና ለቃሉ ያለንን ፍቅር፣ የመንፈሳዊ ሕይወታችንን ጥንካሬ … ወ.ዘ.ተ ያጠቃልላል፡፡
2.3. የኢኮኖሚ ብቃት፦
ፍቅር ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ያለበት ግንኙነት ነው፡፡ ገንዘብ ለዚህ ዓለም ኑሮ አስፈላጊ ነገርነው፡፡ ስለዚህ ከራሳችን አልፈን ሌላ ሰው ማኖር እንዲሁም መንከባከብ የሚያስችል አቅም አለኝ ወይብለን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ ለመተዳደሪያ የሚሆን በቂ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ አለን ወይ? የሚለውን ጥያቄ በአስተማማኝ ሁኔታ መመለስ ይገባናል፡፡
2.4. የሥነ ልቡና ዝግጅት ፦
አንድን ሰው ለማፍቀር ከመነሣታችን በፊት ሥነ ልቡናዊ ዝግጅት ማድረግ አለብን፡፡ ፍላጎታችንን መመርመር፣ ሌላ ሰውን ለመቀበል የመንፈስ ዝግጅት ማድረግ፣ በስሜት ሳይሆንበእርጋታና በሰከነ መንፈስ ምርጫችንን ማጤንን አስፈላጊ ነው፡፡
ወጣቶች የሕይወት አጋራችሁን ስትመርጡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላታችሁን አረጋግጡ፡፡ ፍቅር የከበረ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ተገንዝባችሁ በስሜታዊነትየፍቅር ጓደኛ ከመምረጥና በኋላ ከመጸጸት ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ከክፉ የጎልማሳነት (የወጣትነት) ምኞት በመራቅና በመሸሽ እያንዳንዱን ጉዞአችሁን በእግዚአብሔር ቃል እየመረመራችሁ እና ፈቃዱን እየጠየቃችሁ በመንፈስ የምትመሩ ሁኑ፡፡

- By _ 9nP4d7lOjsk.m4a
6.3 MB
✞ ኒቆዲሞስ
ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌሊቱን በብርሃን የሚማር መምህር(፪)
በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምሕር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትሕትና ተዋርዶ አደረቀ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ
ከመቅደሱ አንቀጽ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
፨ ትርጉም ፦
በሌሊት አጋማሽ መምህር ለመምህር ሰገደ ፤
ጣትስ ከጣት ይልቅ አይደለምን?
መዝሙር
ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
"ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ
ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ"
ዮሐ፫፥፩-፴፮
ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌሊቱን በብርሃን የሚማር መምህር(፪)
በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምሕር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትሕትና ተዋርዶ አደረቀ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ
ከመቅደሱ አንቀጽ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
፨ ትርጉም ፦
በሌሊት አጋማሽ መምህር ለመምህር ሰገደ ፤
ጣትስ ከጣት ይልቅ አይደለምን?
መዝሙር
ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
"ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ
ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ"
ዮሐ፫፥፩-፴፮
"ጌታ ሆይ ጌታ ሆኖ ያለ ምህረት ባርያ ሆኖ ያለኃጢአት የለምና ይቅር በለን"🙏
ተወዳጆች...መቼም ቢሆን በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ይኑረን😊
@zekidanemeheret
ተወዳጆች...መቼም ቢሆን በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ይኑረን😊
@zekidanemeheret
አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ!
ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡
("ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ - ገፅ 86)

ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ "እንደኛ ስላልሆንክ አብደሃል" የሚሉበት ዘመን ይመጣል"
🕊🕊ቅዱስ እንጦንዮስ
🕊🕊ቅዱስ እንጦንዮስ
የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን። ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን። ዕለት ዕለት ሐጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም። #መቼ_ይሆን_የምንነቃው?🤔
ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው /ዘፍ. 3፥20/። ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው?🤔
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል #የሚኖርበትን_ቤት_በቆሸሸ_ቁጥር_የማያጸዳው_ማነው?
ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን #በንስሐ_መወልወያ #የምናጸዳው_መቼ_ነው?🤔
ልጆቼ #ንስሐ_ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ።
ወዳጄ ሆይ! #ማፈር_የሚገባህ #ኃጢአት_ስትሰራ_እንጂ_ንስሐ_ስትገባ_አይደለም።
#ኃጢአት_ሕመም ነው። #ንስሐ_ደግሞ_መድኃኒቱ_ነው። ከኃጢአት ቀጥሎ ህፍረት አለ ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን።
☞☞#የቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #መልካም_ምክሮች

‹‹መዳን በሌላ በማንም የለም›› (ሐዋ 4÷12)
ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው በዕድሜ በጸጋና በመንፈሳዊ አገልግሎት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሸመገለው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሆን መጽንኢ (አጽናኝ)፣ መስተፈስሒ (አስደሳች)፣ መንጽሒ (የሚያነፃ)፣ መስተሰርይ (የሚያስተሰርይ)፣ እና ከሳቲ (ገላጭ) የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ በዕለቱ በዙሪያው ተሰብስበው ለነበሩት ለቤተ አይሁድ በ72 ቋንቋ ወንጌልን በመስበክ 3000 ነፍሳትን አሳመነ፡፡ በዘጠኝ ሰዓትም ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ሲሄዱ በቤተመቅደስ በር ላይ ተቀምጦ ሲለምን የነበረውን አንድ አንካሳ ሰው ወደ እኛ ትኩር ብለህ ተመልከት ብሎ በናዝሬት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ በማለት ፈወሰው፡
ነገር ግን በነጋው ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን የካህናት አለቆች (ሐናና ቀያፋ) ና የመቅደስ አዛዦች በምን ኃይል ወይም በማን ስም ይህን አደረጋችሁ? ባሉት ጊዜ ነበር ‹‹እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው ግንበኞች የናቁት የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና›› (ሐዋ 4÷6-12) በማለት የመለሰላቸው፡፡
በመሆኑም የዚህ ጽሁፍ መሠረታዊ ዓላማ ሉተራውያን ፕሮቴስታንትና ተረፈ አርዮሳውያን ‹‹መዳን በሌላ በማንም የለም›› የሚለውን ጥቅስ እንደ መፈክር በመያዝ ዝም ብለን ‹‹ኢየሱስ›› በማለት ብቻ እንድናለን ፕሮሰስ አያስፈልግም በማለት የመዳንን ትርጉም ባለመረዳት የቅዱሳንን፣ የመላዕክትን የመስቀልን፣ የዕምነትን፣ የጠበልንና ሌሎችን የመዳን መንገዶችን በመቃወም የስህተት ትምህርት ሲያስተምሩ ይስተዋላሉና፣ ይህ የመናፍቃን ስህተት በሊቃውንት አስተምህሮ ሲመረመር ምን እንደሚመስል ለተዋህዶ ክርስቲያኖች ማስተማርና በቂ ግንዛቤ በማስጨበጥ ትውልዱን ከስህተት ትምህርት ከጥርጥር መታደግ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ መዳንን በተመለከተ ያስተምረናል ነገር ግን መዳንን በተመለከተ የእኛ የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ለሁሉም አንድ ዓይነት ቃል ነው የሚጠቀመው ከዚህም የተነሣ ምስጢርን የማያስተውሉ ሰዎች መጻሕፍትን በትርጉም ሳይሆን በጥሬ ንባብ ለመረዳት የሚሞክሩ ወገኖች በሁለት መልኩ ሲስቱ እናስተውላለን፡፡
ሀ/ የመጀመሪያዎች መዳንን ጠቅልለው ቅዱሳንንም፣ መላዕክትንም ኢየሱስ ክርስቶስንም በተመለከተ የተናገረው ቃል አንድ ዓይነት ትርጉም ያለው የሚመስላቸው ናቸው፡፡
ለ/ በሌላው መልኩ ደግሞ መላዕክት ቅዱሳን ያድናሉ ብለን ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያድነው ዓይነት ማዳን ያለ የሚመስላቸው ወገኖችም አሉ፡፡
መዳን የሚለው ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በሦስት ዓይነት ፍቺ ወይም ትርጉም አመስጥረን እናየዋለን:-
ይቀጥላል......

፩ኛ. የዓለም መድኃኒት የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ
የመጀመሪያውና ዋነኛው እግዚአብሔር አዳምንና ልጆቹን ከወደቁበት ውድቀት አንስቶ ከጠፉበት ከባዘኑበት መልሶ ወደ ነበሩበት ክብር ያደረገው ጉዞ ማዳን ይባላል፡፡ አዳም በዕለተ አርብ ወደ ተፈጠረበት ክብር መመለስ ከባርነት ታድጎ ከሲኦል ነፃ አውጥቶ አዲስ አድርጎ መሥራቱ ማዳን ነው (2ቆሮ 5÷15)
ከዚህም የተነሣ ነው እግዚአብሔር አዳነን የባርነታችንን ቀንበር ሰበረ ከእስራታችንም ፈታን የምንለው ‹‹ፊል 2÷8-11 በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን ይገልፅልናል የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ የውርደት ሞት (የመስቀል ሞት) ሞቶ እኛን አዳምና ልጆቹን እንዴት እንደ አዳነን ነው የሚያስተምረው›› በዚህ ምክንያት ደግሞ "እግዚአብሔር እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው ከስም ሁሉ የሚበልጥ ስምንም ሰጠው፡፡ ይህም በሰማይና በምድር በቀላያትና ከምድር በታች ያለ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰግድ ዘንድ ነው፡፡ አንደበትም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ክብር ጌታ እንደሆነ ያምን ዘንድ ነው››
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም ከስም ሁሉ የከበረ ስም መሆኑን ሐዋርያው ያስተምረናል እንዲሁም ፍጥረት ሁሉ ይድንበት ዘንድ የተሰጠው ስም ይህ ስም እንደሆነም አስረግጦ ይነግረናል፡፡
ይህ የእግዚአብሔር ማዳን የሚተካ(ሌላ ፍጡር የሚጋራው) ነገር አይደለም እግዚአብሔር በከሐሊነቱ በእግዚአብሔርነቱ የሚያደርገው ብቻ ነው ለምን አዳምን ከሲኦል ግዛት ነፃ ማውጣት እንደገና በአዲስ ተፈጥሮ በሥጋ ተፈጥሮ መስራት የእግዚአብሔር ብቻ ገንዘብ ስለሆነ፣ የተዘጋውን ገነት መክፈት የእግዚአብሔር ብቻ ገንዘቡ ስለሆነ ይህ ማዳን የማይተካ ነው በቅዱሳን መላዕክት በቅዱሳን ጻድቃን በድንግል ማርያም ሊደረግ የማይቻል ማዳን ነው ይህ ማዳን ደግሞ በዓለም ላይ በዘመናት መካከል የተደረገ ማዳን ነው በቀራኒዮ አደባባይ ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ ያደረገው ማዳን ነው፡፡
ሌላው ማዳን ሁሉ ከዚህ የሚገኝ በረከት ነው፣ ይህ የመጀመሪያው ማዳን ነው የቅዱሳን ማዳን፣ በጠበል መዳን በእምነት መዳን፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ተሻሽቶ ተሳልሞ መዳን፣ በመስቀል መዳን የምንላቸው ሁሉ በዚህ መዳን ምክንያት የተገኙ ናቸው ይህን ማዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ብለን ቅዱሳን መላዕክት ያድናሉ ስንል ልዩነት አለው ይህንን አውቀን ነው እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንናገረው ሉተራውያን ወይም መናፍቃኑ እንደሚሉት ጠቅልለን አይደለም የምንናገረው፣ ምን ማለታችን እንደሆነ አውቀን ተረድተን ነው የምንመሰክረው፡፡
ለምሣሌ (በመዝ 33÷7) ላይ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› የኢየሱስ ክርስቶስን ያድናል ያለው መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ሥፍራ ደግሞ ቅዱሳን መላዕክት ያድናሉ ይላል፣ ይህ ማለት መላዕክት አዳምን ከሲኦል አውጥተው ወደ ገነት ይመልሱታል ማለት አይደለም ይህን ማድረግ ለፍጥረታት ስላልተቻለ ነቢዩ ዳዊትም ሆነ ነቢዩ ኢሳይያስ እጅህን፣ ቀኝህን ከአርያም ላክ አድነንም ሰማዮችን ቀደህ ውረድ (መዝ 143÷5-7 ፣ ኢሳ 64÷1) በማለት ተናግረዋል፡፡

አዳምን ከወደቀበት የሚያነሣ ወደ ጥንት ክብሩ የሚመልስ አልተገኘም ነበርና እግዚአብሔር ቀኙን ማዳኑን ጥበቡን አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው አዳምን ለማዳን አበው እንስሳት በመስዋዕት፣ ነቢያት በጽድቃቸውና በለቅሶ በጸሎት እንዲያውም ደማቸውን በማፍሰስ አጥንታቸውን በመከስከስ ሞክረዋል ግን ስላልቻሉ እንዲህ ነው ያሉት ‹‹ጽድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፣ በደላችን እንደ ነፋስ አፍገምግሞ ወስዶናል›› ኢሳ 64÷5 ምክንያቱም የሰው ልጅ መዳን ወደ ጥንተ ተፈጥሮ መመለስ በእነዚህ ቅዱሳን በአብርሃም፣ በይስሐቅ፣ በያዕቆብ በሰሎሞን በዳዊት በነቢያቱ የሚሆን አልነበረም የሚከፈል ካሣ ይጠይቅ ነበረ ስለዚህም ነው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ራሱ ሊቀ ካህን፣ ራሱ በግ፣ ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ፣ በአንድ ጊዜ ሦስቱንም ሆኖ መስዋዕት ሰውቶ፣ መስዋዕት ተቀብሎ፣ ራሱ ደግሞ መስዋዕት ሆኖ ድኅነትን ፈጸመልን፡፡ ይህንን ማዳን ማንም ሊያደርገው አይችልም፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን የተለየ ማዳን ነው የኦሪቱም ሊቀ ካህናት የሐዲሱም ሊቀ ካህናት ሦስት ነገር ይፈልጋሉ ክህነት ይፈልጋሉ፣ መስዋዕት ይፈልጋሉ፣ መስዋዕትን የሚቀበላቸውም ይፈልጋሉ፡፡ በሐዲስ ኪዳን በቤተመቅደስ ካህኑ በክህነቱ፣ መስዋዕቱን ኅብስቱንና ወይኑን ያቀርባል፣ መስዋዕቱን የሚቀበል እግዚአብሔር ነው እርሱ ካህን ነው፣ መስዋዕቱ በግ ነው መስዋዕቱን የሚቀበል እግዚአብሔር ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ልዩ ካህን ነው (ዕብ 8÷2) ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ ሁሉ ሦስት ነገሮች (መስዋዕት፣ ክህነት፣ መስዋዕት ተቀባይ) ሲፈልጉ እርሱ ግን አላስፈለገውም፡፡
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንደመሰከረ ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር›› የእግዚአብሔር በግ የተባለ መስዋዕቱ ራሱ ነው ፣ ሊቀ ካህን ነው መስዋዕቱን አቀረበ፣ እግዚአብሔር ነው መስዋዕቱን ተቀበለ (2ቆሮ 5÷16-21) ይህንን ነው የኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን በፍጡር ሊደረግ የማይችል ድኅነት የምንለው ስለዚህም መዳን በሌላ በማንም የለም በደላችን የተደመሰሰው፣ መርገማችን የተሻረው ፣ አዳምና ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብራችን የተመለስነው በኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን ነው፡፡
፪ኛ.
ይቀጥላል....

+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +
የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው
ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::
እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::
ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር::ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::
ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::
ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::
ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::
የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::
ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?
እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::
ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

፪ኛ. የመላዕክት ማዳን፣ የቅዱሳን ማዳን፣ የመስቀል ማዳን የጠበል ማዳን ፣ በመስቀልና በእምነት በቅዱሳት መጻሕፍት በመተሻሸት መዳን የምንለው ነው::
ሀ/ የመላዕክት ማዳን
ከላይ ከፍ ብለን እንደጠቀስነው የመላዕክትን ማዳን በተመለከተ ቅዱስ ዳዊት ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› (መዝ 33÷7) ይላል መላዕክት ያድናሉ ብለን ስንል ምን ማለታችን ነው ብለን ብንጠይቅና ብንጠየቅ የመላዕክት ማዳን የጸጋ ነው፡፡
በአጠቃላይ የመላዕክት ማዳን የምንለው ሦስት ነገሮችን ነው፡-
1. ጥበቃቸውን (መላዕክት በመጠበቅ ያድናሉ ይታደጋሉ)
‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋል›› መዝ 90÷11 ‹‹ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ እርሱ እነዚህን ብላቴናዎች ይባርክ›› (ዘፍ 48÷16) ሰዎች ክፉ ነገር እንዳይደርስባቸው ክፉም ነገር እንዳያደርጉ ከዲያብሎስ ተንኮልና ፍላጻ መጠበቅ ነው የመላዕክት ማዳን የተባለው (ዘፍ 19÷15 ፣ ዳን 3÷23-30)
2. ሁለተኛው ማዳን ደግሞ በምልጃቸው በጸሎታቸው የሰው ልጆች ከወደቁበት የኃጢዓት ውድቀት እንዲነሱ ማድረግ ወደ እግዚአብሔር ምልጃን በማቅረብ መታደግ ማዳን ዘካ 1÷12-16 "አቤቱ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከመቼ ነው?›› በማለት ወደ እግዚአብሔር ምልጃን ሲያቀርብ ‹‹እግዚአብሔርም ወደ ኢየሩሳሌም በምህረት ተመልሻለሁ በኢየሩሳሌም ላይ ቤቴ ይሠራባታል ገመድም ይዘረጋባታል›› ‹‹ገብርኤል እየበረረ መጣ፣ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ..›› (ዳን 9÷21 ፣ ዳን 10÷13)
ይህንን ለማብራራት በሚገባን ምሳሌ ብንገልጸው አንድ ሰው በደዌ ታሞ ወደ ሐኪም ቤት ቢሄድና በጤና ጣቢያው ያለው ሐኪም ምርመራ አድርጎ የተለያዩ መድኅኒቶችን ሰጥቶ ቢመልሰውና ይህ ታማሚ ቢድን ሐኪሙ ራሱ መድኅኒት ሆኖ አዳነው ማለት አይደለም፣ የመረመረው ምርመራ፣ የታዘዘለት መድኅኒትና ሙያዊ ምክር ባንድ ላይ ሆነው ነው ይህ ሰው የዳነው እንደዚሁ ሁሉ ቅዱሳን መላዕክት ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ ሲያድኑ እግዚአብሔር ሆኑ ማለት አይደለም፣ በምልጃቸው በጸሎታቸው በተሰጣቸው ጸጋ ይታደጋሉ ያድናሉ ማለት ነው ‹‹ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?››ዕብ 1÷14

3. ሦስተኛው መላዕክት በሚፈሯቸው ዙሪያ ይሰፍራሉ ያድናሉ (ይመራሉ) ማለት ነው፡፡ እስራኤል ከግብፅ ምድር ከባርነት ነፃ ከወጡ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል ከፊት ከፊታቸው ይመራቸው ነበር (ዘጸ 23÷20)
በመሆኑም የእግዚአብሔር መላዕክ መምራቱ ማዳን ይባላል ለምን ሕዝቡ ወደ ክፉ ነገር ከመግባታቸው በማይሆን አቅጣጫ ከመሄዳቸው በፊት መንገዱን ማሳየቱ ማዳን ነው ይህንን ማማለዳቸውን፣ መጠበቃቸውን መምራታቸውን ነው ማዳን ያለው ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› መዝ 33÷7 ሲል እንጂ አዳምን በጥንተ ተፈጥሮ ወይም በአዲስ ተፈጥሮ ወደ ቀደመ ክብሩ ይመለሳል ማለት አይደለም፣ ያን ያደረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
ለ/ የቅዱሳን ጻድቃን የቅዱሳን ሰማዕታት ማዳን
ስለ ቅዱሳን አዳኝነትም ስንናገር ልክ እንደመላዕክት ሁሉ በጸሎታቸው በምልጃቸው በተሰጣቸው ቃል ኪዳን ያድናሉ ይራዳሉ ከክፉ ይታደጋሉ ማለት ነው እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ በተለያየ ዘመን ቃል ኪዳን ሰጥቷል፣ ወደፊትም ይሰጣል ደግሞም እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ይታደጋል ያድናል፡፡
‹‹ከመረጥኳቸው ጋራ ቃል ኪዳኔን አደረግሁ›› መዝ 88÷3 ብሎ እንደተናገረ ቅዱስ ዳዊት፣ ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቃል ኪዳን ስለተገባላቸው ስለተመረጡት ስለቅዱሳን የመከራው ቀን ፈተናው እንደሚቀንስ ጊዜው እንደሚያጥር እንዲህ በማለት አስተምሯል ‹‹እውነት እላችኋለሁ እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት (ስለ ቅዱሳኑ) ሰዎች ያጥራሉ›› (ማቴ 24÷22) በዚያ ቃል ኪዳን ለሚታመኑት ሁሉ ከሲኦል ግዛት ከዲያብሎስ ግርፋት ያድናል ይታደጋል ይሁን ይደረግልን አሜን ቅዱሳን በተሰጣቸው ጸጋ በነፍሳቸው ተወራርደው እባክህ ማርልኝ ብለው ይለምናሉ ይጸልያሉና ‹‹ሊቀነቢያት ሙሴ ሕዝቡ በበደለ ጊዜ እግዚአብሔር ሊያጠፋ ሲነሣ ይህን ሕዝብ ከምታጠፋ እኔን ከሕይወት መዝገብ ደምስሰኝ በማለት እንደጸለየ›› (መዝ 105÷23)
ማዳን የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው ቅዱሳን ግን ይህንን በጸጋ ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ተቀብለዋል፣ በመሆኑም የጸጋ አምላክ እስከመባል የደረሱ ቅዱሳን ወገኖቻቸውን ወንድሞቻቸውን የመርዳት ጸጋ ተቀብለዋል (ዘጸ 7÷1)
ነገር ግን በቅዱሳን አማላጅነት ለመጠቀም የመጀመሪያውን ማዳን አምኖ መቀበል ግድ ይላል ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በገዳመ ቆሮንቶስ ጾሞ ጸልዮ በዲያብሎስ ተፈትኖ በ30 ዘመኑ በባሕረ ዮርዳኖስ ተጠምቆ በዕለተ አርብ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ ማዳኑን ማመን አለበት፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳኑ የሚያማልዱት በዚህ መንገድ ሲጓዙ የደከሙትን ነው ሐዋርያው በዕብራውያን መልዕክቱ ይህንን ግልጽ አድርጎ ጽፎታል (ዕብ 1÷14) ‹‹ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?›› ይህ ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምነው ሥጋውና ደሙን ተቀብለው ተጠምቀው ወደ እግዚአብሔር መንገድ ሲሄዱ የሚደሙትን የሚሰናከሉትን ወደ ኋላ የሚቀሩትን የሚወድቁትን እነዚህን በጸሎታቸው በምልጃቸው ያግዛሉ ይራዳሉ ያለው ይህን ነው ምክንያቱም መራዳት መተካት ማለት አይደለምና አንድን ሰው ተክተን ከሰራን ረዳን አይባልም፣ ቅዱሳን መላዕክት ፣ ጻድቃን ይራዱናል፣ ያግዙናል መቼ ነው የሚራዱን የሚያግዙን ቢባል ንስሐ ለመግባት ሥጋ ወደሙን ለመቀበል ፈልጎ ነገር ግን ካልቻለ ከአቅሙ በላይ ከሆነ ሰይጣን ማህበራዊ ችግር ቤተሰባዊ ችግር የትዳር ችግር የንግድ ችግር የትምህርት ችግር የጤና ችግር እያመጣ ካሰናከለው ነገር ግን ቅዱሳን መላዕክት ቅዱሳን ጻድቃን በጸሎታቸው በምልጃቸው ይራዱንና ከዚህ ወጥመድ እንድንወጣ ያደርጉናል ይህ ማዳን ይባላል ‹‹በዳን 3 ላይ ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን አዳነ›› የጻድቃን የሰማዕታትም ማዳን ይህ ነው፣ እኛ በምናደርገው ተጋድሎ እንደክማለን፣ ያቅተናል ከአቅማችን በላይ ሲሆን በምልጃቸው በጸሎታቸው አምነን ተማምነን ተማጽነን ይረዱናል ያግዙናል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንኳን አገልግሎቱ የተሳካ እንዲሆንና እንዲሰፋ እግዚአብሔር ከክፉ ሰዎችም ያድነው ዘንድ ጸልዩልኝ ይል ነበር "ወንድሞቻችን ሆይ ጸልዩልን"1ኛ ተሰ 5÷25 ‹‹አሁንም ወንድሞቻችን በእናንተ ዘንድ እንደሆነው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፋጠንና እንዲከብር ጸልዩልን፡፡ ከክፉዎችና ከከሐዲዎች ሰዎችም እንድን ዘንድ ጸልዩልን›› (2ኛ ተሰ 3÷1) ቅዱስ ጳውሎስ ጸልዩልኝ ያለው የማይጸልይ ሆኖ ሳይሆን ሥጋን የለበሰ ሁሉ ድካም ስላለበት ከሊቅ እስከ ደቂቅ ጸሎት የማያስፈልገው እርዳታ የማያስፈልገው አለመኖሩን ሲነግረን ነው፡፡
ጸሎተኛ የሚባለው እንኳ በጸሎት እንዳይደክም ጸሎት እርዳታ ያስፈልገዋል በክርስትና አንዱ አንዱን መርዳት ያለ የነበረ የሚኖር ነው ይህንን ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹እያንዳንዱ ስለሌላው ይጸልይ፣ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች›› (ያዕ 5÷16)
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘላለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኗልና፡፡ እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ›› (ዮሐ 4÷36-38) ይህ ማለት ከእኛም በፊት ሆነ ከእኛ ጎን የበረቱ ብዙ ብርቱዎች አሉ፣ በእነሱ ድካም እኛ እንገባለን ይህ የክርስትና ሕይወት ነው ብርቱዎች ይደክማሉ ሰነፎች ደግሞ በብርቱዎች ድካም ይገባሉ፡፡ ሰነፎች ማለት ሲጸልዩ ሲጾሙ ሲሰግዱ አቅም ያነሳቸው ማለት ነው እንጂ ምንም ሳይሰሩ ሳይንቀሳቀሱ የተቀመጡትን አይደለም ክርስትና እንቅስቃሴ ነው የሩጫ ሕይወት ነው ቁጭ ብሎ ክርስትና የለም ሰው መጸለይ ሊያቅተው ይችላል መጾም ሊያቅተው ይችላል፣ በጤናና በተለያየ ምክንያት መስገድ ሊያቅተው ይችላል፣ እነዚህ በብርቱዎች ምልጃ እርዳታና ጸሎት ይገባሉ፡፡

መጸለይ አለመቻልና መጸለይ አለመፈለግ የተለያዩ ናቸው መጸለይ ያልቻለ ሰው ጌታ ሆይ መጸለይ እፈልግ ነበር ነገር ግን አልቻልኩም ማለት ይኖርበታል ቅዱሳንም የሚራዱት እየሞከሩ አቅም ያጡትን የደከሙትን ነው ስለዚህም መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን የሚራዱ ያለው ሐዋርያው ይህንን ነው ፡፡
ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ አንዱ አንዱን ያድናል እርስ በእርስ በወንጌል ስንማማር ወንድማችንን ከክፉ ስንመልሰው ከኃጢዓት መክረን ስናመጣው ተስፋ ከመቁረጥ ስንመልሰው ማዳን ይባላል ይሄ ማዳን ማለት ደግሞ በድኅነቱ መንገድ ማሳየታችን ነው ማዳን የተባለው ወዳጄ ከክፉ ነገር አወጣኝ ከጸጸት አተረፈኝ ተስፋ ከመቁረጥ አዳነኝ ብለን የምንናገረው ማለት ነው ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በመልዕክቱ ይህን አይነቱን ማዳን እንዲህ ጽፎታል ‹‹ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ማንም በእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው ኃጢዓተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኃጢዓትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ›› (ያዕ 5÷20)
ይሄ ማዳን ግን እንደ ቅዱሳኑ ያለ ማዳንም አይደለም፣ እንደ ጠበሉና እምነቱ ያለም ማዳን አይደለም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዳነውም ያለ አይደለም፣ መምከር ማስተማር መመለስ ሲሆን ይህ ማዳን ይባላል፡፡
በመሆኑም ማዳን ብለን ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል፣ መስቀል ያድናል፣ ቅዱሳን ያድናሉ፣ መላዕክት ያድናሉ፣ ስንል ዓይነቱንና ልዩነቱን ተረድተን ነው፣ መጻሕፍትም ይህን ቀላቅሎ አይደለም የጻፈው ሁሉን በምስጢር በዓይነትና በልዩነት ነው በአጠቃላይ የሁሉም ማዳን ከእግዚአብሔር ማዳን የሚመነጭ ነው እግዚአብሔር በባሕርይው ያለውን ለቅዱሳን በጸጋው ስለሰጠ አምላክ ነው በባሕርይው አማልክት ዘበጸጋ ይባሉ ዘንድ ሰጥቷል፣ ሕያው ነው በባሕርይው ሕያዋን እንሆን ዘንድ ሰጥቷል፡፡ ዘላለማዊ ነው በባሕርይው ዘላለማዊውን ሕይወት እንድንወርስ ፈቅዷል ሰማያዊ ነው ሰማያውያን እንድንሆንም ፈቅዷል ያልፈቀደውና ያልተሰጠን ጸጋ የለም ነገር ግን በትዕቢት በኩራት በኑፋቄ ወይም በጥርጥር አናገኘውም እንጂ በጽድቅ በትህትና የማናገኘው ምንም ነገር የለም በመሆኑም ማዳን የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ቢሆንም እንኳን ቅዱሳን በጸሎታቸውና በምልጃቸው መላዕክት በተራዳኢነታቸው መምህራን በትምህርታቸው ባልንጀሮች በምክራቸው በተግሳጻቸው እንዲያድኑ ፈቅዷል ጸጋውንም ሰጥቷል፡፡