ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
858 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ አቀረበች፡፡

አባቷ የምግብ ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡ ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡

በድስቶቹ ውስጥ ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር በአንዱ ድስት ውስጥ ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት መጠበቅ ጀመረች፡፡

ከ20 ደቂቃ በኀላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡

"ልጄ አሁን ምን ይታይሻል? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ "በቁጣ ስሜት ሁና ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡

"በደንብ ተመልከች፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡

"እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡

በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡

"አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡

አባት ማብራራት ጀመረ፡፡ "ድንቹ፣ እንቁላሉ እንዱሁም የቡናው ዱቄት ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡

ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡

እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡

ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡

አንቺ የትኛው ነሽ?" ችግር ስገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? እንደ ድንቹ መልፈስፈስ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር? አልያም ችግሩን ለአዲስ ነገር መፍጠሪያ መጠቀም?"

በህይወት ውስጥ ነገሮች በአካባቢያችን ይከናወናሉ፤ ነገሮች በእኛ ላይ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ትልቁና ወሳኙ በእኛ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ነው!"

የትኛው ነህ? ነሽ?

አስተማሪ ሆኖ ካገኙት #ላይክ እና #ሼር ያድርጉት
👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
💠 ሳለቅስ በተመለከተችኝ ጊዜ አለቀሰች


እመቤታችን በታላቅ ክብር ባረገችበት ጊዜ ቶማስን አጋንንትን እያወጣ ካለበት ከሕንደኬ መንፈስ ቅዱስ ጠርቶት በደመና ላይ ተጭኖ በሰማይ አግኝቷት ነበር፡፡ ይህንንም ለሐዋርያት ሲተርክ እንዲህ አለ፡-“…እኔ ልናገረው /ልገልጸው/የማይቻለኝ ታላቅ ብርሃንም ከቧት ነበር፡፡ ቶማስ ሆይ ታውቀኛለህን? አለችኝ፡፡ አንችን ማየት አልቻልሁም አልኋት፡፡ያን ጊዜም በፊቷ የነበረው ብርሃን ተወገደ፡፡ያን ጊዜም በግልጽ አየኋት፡፡የልዑል እናት ነሽ አልኋት፡፡ ብዙ ስግደትንም ሰገድሁላት፡፡ምን ሁነሽ ነው አልኋት፡፡ ሁሉንም በየክፍሉ ነገረችኝ፤ እኔም አለቀስሁ፡፡ እሷም ሳለቅስ በተመለከተችኝ ጊዜ አለቀሰች፡፡” (ድርሳነ ማርያም ፣ መ/ር ተስፋ ሚካኤል ታከለ ፣ በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.በሰ.ት.ቤ.ማ.መ.ማኅበረ ቅዱሳን ፣ የካቲት 2003 ዓ.ም. ፣ አዲስ አበባ ፣ ገጽ 128-129)

የእመቤታችንን አዛኚትነትና ርኅርኅትነት በአንደበት ነግሮ መፈጸምአይቻልም፡፡ በተለያየ አነጋገር ፣ በተለያየ ምሳሌ ፣ በረቂቅ ዘይቤ ፣ በመሳጭ ታሪክ ፣ በአበውና በመጻሕፍት ምስክርነት ብንማረውም ፣ ከፍታውን ለማሳየት ከብዙ ፍጡራን ርኅራኄ ጋር ብናነጻጽረውም አሁንም እጅግ ምጡቅ ነው፡፡ከላይ በተጠቀሰው ታሪክ ቶማስን በዕርገቷ ጊዜ ልታነጋግረው ፈቅዳ ከሕንደኬ እንዲመጣ አምላክን የለመነችው እርሷው ነች፡፡ ከቶማስ በላይ ነችና ስለቶማስ በደንብ የምታውቅ ስለሆነች ስሜቱን በደንብ ትረዳዋለች፡፡ በምትነግረው ነገር የሚያለቅስ ቅዱስ ልቡና እንዳለው ታውቃለች፡፡ ነገር ግን ነግራው ሲያለቅስ አብራው አለቀሰች፡፡ እርሱ ከሌሎቹ ሐዋርያት ጋር ያልነበረ በመሆኑ ለእነርሱ የተገለጸ ምሥጢር የቀረበት መስሎት ሲያለቅስ ለሐዋርያት ያልተገለጠው ዕርገቷን እርሱ ብቻ እንዳየው እያወቀች እንኳን አብራው አለቀሰች፡፡ ክብሩን ነግራ ሳታለቅስ ለቅሶውን ማስቆም ስትችል አብራው አለቀሰች፡፡ በዕርገቷ ጊዜ በአስደናቂ ብርሃን ታጅባ ያያት እርሱ ብቻ መሆኑን ነግራ የለቅሶ ዕንባውን ወደ ሐሴት ዕንባነት መለወጥ ስትችል እርሷ ግን አብራው አለቀሰች፡፡ እልፍ አዕላፋት መላእክት አጅበዋት ማረጓን አብሳሪ እርሱ መሆኑን ከመንገርዋ በፊት አብራው አለቀሰች፡፡ ለማስተዛዘን በሚል ፈሊጥ ሳይሆን ስሜቱ ስሜቷ ሆኖ አብራው አለቀሰች፡፡ ሕፃን ልጅ ሲያለቅስ “በቃበቃ” ብለው እንደሚያባብሉት ሳይሆን ከእርሷ ቅድስና አንጻር በጽድቁ ሕፃን የነበረው ቶማስ ሲያለቅስ እርሱን ለማባበል አብራው አለቀሰች፡፡

ድንግል እንዲህ ነች…አብራ አልቅሳ የምታከብረን ውድ ንግሥት ፤ አብራ አልቅሳ የምታማልደን አዛኝት እመቤት ፤ አብራ አልቅሳ የምታበሥረን ቅድስት ፍጥረት ፤ አብራ አልቅሳ የምታባብለን…. ርኅርኅት እናት፡፡

ወዳጄ ሆይ በሕይወትህ ስንት ጊዜ ከልብህ አልቅሰኻል?የምትበላው አጥተህ የምትጠጣው አጥተህ ስንት ጊዜ አልቅሰኻል? ላንተ ምግብንና መጠጥን ከመስጠቷ በፊት ርኀብህን መጠማትህ ተሰምቷት አብራህ አለቀሰች፡፡ሰው አጥተህስ ፣ ብቸኝነት ተሰምቶህ ስንት ጊዜ አልቅሰህ ይኾን? ብቸኝነትህ ተሰምቷት ላንተ ሰው ከመስጠቷ በፊት አብራህ አለቀሰች፡፡ ሥራ አጥተህስ ስንቴ የሐዘን ዕንባህን አውጥተኻል? ላንተ ሥራ ከመስጠቷ በፊት አብራህ አለቀሰች፡፡ ተበድለህና ተገፍተህ ብቻህን የቀረህ መስሎህ ስታለቅስም ይህን ጊዜህን ወደ ደስታ ከመለወጧ በፊት አብራህ አለቀሰች፡፡ ምድር የተደፋችብህና ምንም ተስፋ የሌለህ መስሎህ አቀርቅረህ ስታነባም አብራህ አነባች፡፡ የዓለም መከራ ሁሉ ወደ አንተ የተላከ መስሎህ ስትንሰቀሰቅ ባንተ ስሜት አብራህ ተንሰቀሰቀች፡፡ የሠራኸው ነገር ልክ አለመሆኑን ተረድተህ በጸጸት ዕንባ እየተንገበገብክ ስታለቅስም አብራህ አልቅሳ ዕንባህን አበሰች፡፡ ሰዎች የሰጡህን ተስፋ ሳይፈጽሙልህና ያለህን አጭበርብረው ባዶህን ስትቀር ያነባኸውን ዕንባ አብራህ አነባች፡፡ ኃጢአትህ መሮህ በተነሳሒ ልቡና ስታለቅስም እያለቀሰች አዛኝቱ አብራህ ነበረች፡፡ ምንም እንኳን መከራህና መገፋትህ ፣ ብቸኝነትህና ሮሮህ ጊዜያዊና ባንተ ማስተዋል ችግር ቢያስለቅስህም እርሷ ግን ዕንባህን ስታብስ አብራህ አለቀሰች፡፡

እንዲህ ነች እንግዲህ አዛኝቱ…

ያኔ “ማርያም ፣ ማርያም” የሚል ምግብ የሆነ ቃልን እየሰማሁ ስወለድ አልቅሼ ነበር፡፡ ለቅሶዬን ሐኪሞች የጤንነት ምልክት ብለው ቢደሰቱም ፣ እናቴና አባቴ በሐሴት ጥርስ በጥርስ ሆነው ሊያቅፉኝ ቢጓጉም ፣ የከበቡኝ ሁሉ እልል እያሉ ወደ ምድራቸው መምጣቴንና የጤንነቴን ለቅሶ ቢያጅቡም ፣ ርኅርኅቷ እናቴ ግን “ጨቅላ ነው” ሳትል ፣ “የጤንነት ምልክት ነው” ሳትል…ዐዋቂዎቹ ሳያዩኝ እኔን ከማጫወቷ በፊት ከማኅፀን ስወጣ የተሰማኝ ስሜት ተሰምቷት አብራኝ አለቀሰች፡፡ በልጅነት ዕድሜዬ የሚያስለቅሱኝ ነገሮች በበዙ ቁጥር “ልጅ ነው” ብላ ሳትንቀኝ አብራኝ አልቅሳ ዕንባዬን ታብስ ነበር፡፡ ርኃብ አንጀቴን አጥፎት ይሉኝታ ባስለቀሰኝ ጊዜም አብራኝ አልቅሳለች፡፡ የምፈልጋቸውን አላገኘሁም ብዬ ልጇን በለቅሶ ባማረርኩ ጊዜ እንኳን ዕንባዬን በዕንባዋ አብሳ አካሔዴን አስተካክላለች፡፡ የብቸኝነት ክረምት ውጦኝ ፀሐየ ሰብእን በማጣት አንገቴን ደፍቼ ሳለቅስም ከእኔ ጋር ለማልቀስ እርሷ መች ሰለቸችኝ…?“ ለምን እኔን ” ብዬ ስማጸን የዐይነ ልቡናዬን የሐዘን ፈሳሽ ለማበስ እርሷ መች ተወች? የቀረቡኝን ሳጣቸው ፣ ወንድምነት ትርጉሙ ሲጠፋኝ ፣ እኅትነት ቅኔ ሲሆንብኝ ፣ አባትነት ረቂቅ ፣ እናትነትም ተስፋ ሆነው ቀርተው ሳነባ ውስጠ ውስጠቴን ተረድታ በእኔ ስሜት እኔን ዐውቃ አብራኝ አነባች እንጂ፡፡ ብቻ ለኔ ብቻ የተተወውን ጸጋ ከማየቴ በፊት በጅምላ ሳነባ ጸጋዬን ከማሳየቷ በፊት አብራኝ በጅምላ አነባች - አዛኝቱ ፣ ርኅርኅቱ ፣ ቅድስቲቱ ፣ ንጽህቲቱ ፣ አማላጅቱ…፡፡

እናም ወዳጄ ሆይ…የምታለቅስልህን እያት ፣ የምታመለክትህን ያንተን ብቻ ጸጋ ተመልከትላት ፤ ይህን ካደረክ እንደ ቶማስ ያየኸውን ሔደህ ለወዳጆችህ ትነግራለህ፡፡ “ሳለቅስ በተመለከተችኝ ጊዜ አለቀሰች” ማለት ትችላለህ፡፡ ከዛ በፊት ግን በምልጃዋ ታያት ዘንድ አንቺን ማየት አልቻልኩም በላት፡፡ እርሷም እንድትመለከታት ትገለጽልሀለች፡፡ ከዛም ብዙ ስግደትን ስገድላት፡፡ እርሷም ልብህን የሚኮረኩር ምሥጢር ትነግርሀለች፡፡ አንተም ታለቅሳለህ፡፡ ስታለቅስ በተመለከተች ጊዜም አብራህ ታለቅሳለች፡፡

የአዛኝቱ ክብር ይገለጽልን ዘንድ የቅዱስ ቶማስ ምልጃ አይለየን


#ሼር
__

#share #share ⤵️

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret