ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
እናታችን ቅድስት ዮሐና

☞ጌታን ለ3 ዓመታት ያገለገለች:: (ሉቃ. ፰:፪)
☞ከሕማሙ ያልተለየች::
☞ከመስቀሉ እግር የተገኘች::
☞ትንሣኤውን ተመልክታ የሰበከች::
☞በዘመነ ሐዋርያትም ስመ ጥር የነበረች ቡርክት እናት ናት:: (ሉቃ. 24:10)
☞ግንቦት 24 ዓመታዊ በዓሏ ነው::

☞እናታችን ቅድስት ዮሐና ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት፡፡

✿በረከቷ በዝቶ ይደርብን፡፡✿

'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
ታላቁ ነቢይ ቅዱስ እንባቆም

"እግዚኦ ሰማዕኩ ድምጸከ ወፈራህኩ::
ርኢኩ ግብረከ ወአንከርኩ . . . " (ዕን. 3:1)

☞ግንቦት 24 ዕረፍቱ፡ ቅዳሴ ቤቱም ነው፡፡

ከአረጋዊው ነቢይ በረከት አምላኩ አይለየን::

'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 25/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፶፥፲፬(50፥14)
አድኅነኒ እምደም እግዚአብሔር አምላከ መድኃኒት ይትፌሣሕ ልሳንየ በጽድቀ ዚአከ እግዚኦ
ትከሥት ከናፍርየ ወአፉየ ያየድዓ ስብሓቲከ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፱፥፳-፳፯(9፥20-27)
ወናሁ ብእሲት እንተ ደም ይውኅዛ…

ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፪፥፰-፲፭(2፥8-15)
ወእፈቅድ ለኵሉ ሰብእ ይጸልዩ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖 ጴጥሮስ ፩ ም ፬፥፲፪-፲፱(4፥12-19)
አኃዊነ ኢታንክርዋ ለእንተ ትመጽአክሙ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፰-፲፭(16፥8-15)
ወአስተርአዮ ለጳውሎስ በሌሊት…


📖ምስባክ ዘቅዳሴ

ዘአቀመ ስምዐ ለዮሴፍ
አመ የሐውር ብሔረ ግብጽ
ወሰምዐ ልሳነ ዘኢየአምር

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፹ ቊ. ፬ - ፭
፬ ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ።

፭ ከግብጽ በወጣ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክር አቆመው። ያላወቅሁትን ቋንቋ ሰማሁ።


📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የማርቆስ ወንጌል ም. ፲፭ ቊ. ፵ - ፵፪
ወሀለዋ አንስት ይቀውማ...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
እንኳን ለእናታችን ቅድስት ሰሎሜ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል እና ለበዓለ ቅዱስ ሜሮን በሰላም አደረሳችሁ

+"+ ቅድስት ሰሎሜ +"+

=>የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ከመረጣቸው 36ቱ ቅዱሳት አንስት የቅድስት ሰሎሜን ያሕል ያገለገለ: ክብርም የተቀበለ የለም:: ከእመቤታችን ቀጥሎ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ ያልተለየች ብቸኛዋ ሰው ናትና::

+ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ቅድስት ሰሎሜ ከነገደ አሮን በሚመዘዝ የዘር ሐረግ እናቷ ማርያም ትባል ነበር:: አባቷ ደግሞ ክቡር አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ነው:: ቅድስት ሰሎሜና እመቤታችን የእህትማማች ልጆች ናቸው::

+ቅድስት ኤልሳቤጥም ዝምድናዋ ተመሳሳይ ነው:: የ3ቱ እናቶች (ሐና: ማርያምና ሶፍያ) የማጣትና የሔርሜላ ልጆች በመሆናቸው እህታማቾች ናቸው::

+<< ጥቂት ነገሮች ስለ እናታችን ቅድስት ሰሎሜ >>+
1.የአረጋዊ ዮሴፍ ልጆችን (ወንድሞቿን) እንደሚገባ አሳድጋለች::

2.ጌታችን በተወለደ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረች:: የእመቤታችን መውለድ እንደ ሌሎች ሴቶች መስሏት ድንግልን ስለ ነካች እጆቿ ተቃጥለዋል:: ምሕረት ጠይቃ ጌታን ስትዳስሰው ግን ተፈወሰች::

3.እመ ብርሃን ስደት ስትወጣ ቅድስት ሰሎሜ "ባንቺ የደረሰ በኔም ይድረስ" ብላት አብራ ተሰዳለች:: ረሐቧን ተርባለች:: ጥሟን ተጠምታለች:: በሐዘኗ አዝናለች:: አብራት አልቅሳለች:: ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ያን ሁሉ ጭንቅ አብራ ተካፍላለች::
+ድንግል እመቤታችን እሾህ ሲወጋት ታወጣላት: እንቅፋት ሲመታት ደሟን ትጠርግላት ነበር:: ባለቤቱ አድሏታልና ጌታችንን አንዴ በጎኗ ታቅፈው: አንዴም በጀርባዋ ታዝለው: አንዳንዴም ትስመው ነበር::

<< መለኮትን ማቀፍ: ማዘልና መሳም ምን ይደንቅ! ለቅድስት እናታችን አንክሮና ምስጋና በጸጋ ይገባል! >>

+ከስደት ከተመለሱ በሁዋላም ለ25 ዓመታት ከጌታና ከድንግል ማርያም ጋር ኑራለች: አገልግላቸዋለችም::
+ጌታችን ተጠምቆ ማስተማር ሲጀምርም ተከተለችው:: እርሱም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ደምሯታል:: ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከዋለበት ውላ: ካደረበት አድራ ተምራለች:: እንደሚገባም አገልግላለች::

+አምላክ ሲሰቃይ ከጐኑ: ሲሰቀልም ከእግረ መስቀሉ ነበረች:: ብርሃነ ትንሣኤውም ከተገለጠላቸው ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: ከመድኃኔ ዓለም ዕርገት በሁዋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላ በሐዋርያት ዘመን የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን አገልግላለች::

+እድሜዋ ምን ቢገፋ ለወንጌልና ለማዕድ ተግባር ተግታለች:: ወገኖቿ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋት በዚህች ዕለት በመልካም ዕረፍት ወደ ፈጣሪዋ ሔዳለች::

+"+ ቅብዐ ሜሮን +"+

=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ የምንከብርበትን ቅብዐ ሜሮን አፍልቆልናል::

+በስደቱ ጊዜ ጌታችን በምድረ ግብፅ ደክሟቸው ካረፉበት ቦታ ላይ የዮሴፍ በትርን ቆራርጦ: በኪነ ጥበቡ ውሃ አፍልቆ: አጠጥቶ: ትልልቅ ዛፎች አደረጋቸው:: እዛውም ላይ ቅብዐ ሜሮንን አፈለቀ:: ቅብዐ በለሶንም ይሏቸዋል::
+በሁዋላም የጌታችን ወዙ በታጠበ ጊዜ ተቀላቅሎበታል:: ዛሬ እኛም: ንዋየ ቅድሳትም የምናከብረው በዚሁ ቅዱስ ቅብዐት ነው::

=>አምላካችን እግዚአብሔር በቅድስት ሰሎሜ ላይ ያሳደረውን ጸጋ በእኛም ላይ ያሳድርልን::

=>ግንቦት 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እናታችን ቅድስት ሰሎሜ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት)
2.ታላቁ አባ ሔሮዳ ሰማዕት
3."30,000" ሰማዕታት (የአባ ሔሮዳ ማሕበር)
4.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
5.ቅዱስ ቅብዐ ሜሮን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

=>+"+ ሰንበትም ካለፈ በሁዋላ መግደላዊት ማርያም: የያዕቆብም እናት ማርያም: ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ:: ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በሁዋላ ወደ መቃብር መጡ . . . ወደ መቃብርም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል አዩና ደነገጡ:: እርሱ ግን አትደንግጡ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ:: ተነስቷል: በዚህ የለም . . . አላቸው:: +"+ (ማር. 16:1-8)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 26/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፲፰፥፫-፬(18፥3-4)
አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ
ውስተ ኲሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ።

📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፳፥፳፬-፴፩(20፥24-31)
ወቶማስ ፩ዱ እም፲ወ፪ አርዳኢሁ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፰፥፳፪-፴፩(8፥22-31)
ናአምር ከመ ኵሉ ዓለም ሕሙም…


         👉ንፍቅ ዲያቆን
📖 ይሁዳ ፩፥፲፯-፳፭(1፥17-25)
ወአንትሙሰ አኃዊነ ተዘከሩ ቃለ…


         👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፭፥፳፬-፴፬(5፥24-34)
ወሰሚዖሙ ዘንተ ነገረ…

             📖ምስባክ ዘቅዳሴ

ብፁዕ ብእሲ ዘእምኀቤከ ረድኤቱ እግዚኦ
ወዘይሄሉ በልቡ ዘበላዕሉ።
ውስተ ቈላተ ብካይ ብሔር ኀበ ሠራዕኮሙ


መዝሙረ ዳዊት ም. ፹፫ ቊ. ፭ - ፮

፭ አቤቱ፥ርዳታው፡ከአንተ፡ዘንድ፡የኾነለት፥በልቡም፡የላይኛውን፡መንገድ፡የሚያስብ፡ሰው፡ምስጉን፡ነው።

፮ በልቅሶ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡በወሰነው፡ስፍራ፡የሕግ፡መምህር፡በረከትን፡ይሰጣልና።

                📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የዮሐንስ ወንጌል ም. ፲፬ ቊ. ፩ - ፲፫
ኢይደንግጽክሙ ልብክሙ...

📜ቅዳሴ


👉ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+

=>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::

+ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሣኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው::

+መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::

+ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)

+ጌታችን ትንሣኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-

1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::

+ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::

+ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::

+ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::

+በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::

+በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::

+ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::

+በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::

+እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::

=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::

=>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ)
3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን ::

+" አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ "+

=>እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::

+ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::

+ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::

+ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::

+የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::

+ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::

*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::

*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)

*በ40 ቀናት : ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::

*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::

*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)

*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::

*በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም::

+በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከትሎ መጥቶ አላቸው::

"1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ:
2.ስለ ምናኔሕ:
3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ:
4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ:
5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ:
6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ:
7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

+"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::

+ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}

=>አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::

=>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን ::

"" ግንቦት 26 ""

+*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+

=>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::

+እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::

+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::

+ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::

+አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::

+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::

+በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::

+በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::

+ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

+ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::

+በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::

+ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::

+ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::

+እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከመኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::

+ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}

<< ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! >>

=>+"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: +"+ (1ዼጥ. 5:3)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>