ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 23/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፬፥፲፪-፲፫(44፥12-13)
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
በዘአጽፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፥፲፮-፴፪(10፥16-32)
ወናሁ አነ እፌንወክሙ ከመ አባግዕ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፲፮፥፯-፲(16፥7-10)
አምኁ እንድሮኒቆን……


         👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ይሁዳ ፩፥፳-፳፭(1፥20-25)
ወአንትሙሰ አኃዊነ ሕንጹ ርእሰክሙ……


         👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፩፥፲፭-፳፩(21፥15-21)
ወእምድኅረ እማንቱ መዋዕል…


             📖ምስባክ ዘቅዳሴ

ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ


👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፱ - ፲

፱ የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።

፲ ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤


📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፲፯ - ፳፭
ወተመይጡ እልክቱ ፸...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ሐዋርያት ዮልዮስና አፍሮዲጡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ ዮልዮስ ወአፍሮዲጡ ሐዋርያት ✞✞✞

=>ቅዱሳን ሐዋርያትና አርድእት በቁጥር 84 ቢሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪኩ በዝርዝር የተጻፈለት ቅዱስ ዻውሎስ ነው:: የሌሎቹ አልፎ አልፎ የተጠቀሰ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ግን የት እንደ ደረሱም አልተጻፈም::

+በዚሕ ምክንያት ወደድንም ጠላንም አዋልድ መጻሕፍትን መጠቀማችን አይቀርም:: ምክንያቱም "ሑሩ ወመሐሩ" ያላቸው ሁሉንም ሐዋርያትና አርድእት ነውና::

+የቅዱሳን ሐዋርያትን ሕይወት ከያዙ ቅዱሳት መጻሕፍት መካከል በቀዳሚነት ዜና ሐዋርያትና ገድለ ሐዋርያት የሚጠቀሱ ሲሆን ስንክሳራችንም አልፎ አልፎ ያወሳቸዋል:: በዚሕም መሠረት ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከ72ቱ አርድእት የሚቆጠሩትን ቅዱስ ዮልዮስንና ቅዱስ አፍሮዲጡን ታከብራለች::

+ሁለቱም ከጌታችን እግር ሥር ለ3 ዓመታት ተምረው: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው: ከባልንጀሮቻቸው ሐዋርያት ጋር ለወንጌል አገልግሎት ሃገራትን ዙረዋል:: በሐዋርያት ሲኖዶስም ዽዽስናን ተሹመዋል::

+በአገልግሎት በነበሩባቸው የእስያና አውሮዻ ሃገራት አእላፍ ነፍሳትን ወደ ሕይወት ሲማርኩ ግፍን በአኮቴት ተቀብለዋል:: ከጌታቸውም የማይጠፋ የሕይወት አክሊልን ተቀዳጅተዋል::

+በተለይ ቅዱስ ዮልዮስ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር መከራን በመቀበሉ በሮሜ መልዕክቱ (16:7) ላይ አወድሶታል:: ከቅዱስ እንድራኒቆስ ጋርም በጣም ይዋደዱ ነበርና ትናንት እርሱን ገንዞ ቀብሮ በእንባ ወደ ጌታው ፀለየ:: ጌታችንም በማግስቱ (ማለትም ዛሬ) አሳርፎታል::

=>አምላከ ቅዱሳን ከሐዋርያቱ ትጋትና በረከት ያድለን::

=>ግንቦት 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮልዮስ (ዮልያን) ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ አፍሮዲጡ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
3.ቅዱሱ ሕጻን ሰማዕት (በዘመነ ሰማዕታት ገና የ2 ወር ሕጻን ቢሆንም ጌታችን አፉን ከፍቶለት ክርስቲያን ነኝ በማለቱ ከእናቱ ጋር ተሠይፏል)
4.አባ አንስያ ሰማዕት
5.ቅዱስ ታኦድራጦስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.አባ ሳሙኤል
6.አባ ስምዖን
7.አባ ገብርኤል

=>+"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ: ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና ዮልዮስ) ሰላምታ አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ወበዛቲ ዕለት ተወልደ አብ ክቡር አረጋዊ፡ ወሰማዕተ ጽድቅ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፡፡ በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ታዴዎስ ተወለዱ

#አቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽ

ትውልድ ሀገራቸው ጽላልሽ (ዞረሬ) ነው። አባታቸው ሮማንዮስ እናታቸው ማርታ ይባላሉ። አባታቸው ሮማንዮስ ቄስ ነው። የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት ናቸው።
በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ በጽላልሽ ረሀብ ፀንቶ ነበር። እሳቸው ግንቦት ፳፫ ቀን በመንፈቀ ሌሊት በልብሰ ብርሃን ተጠቅልለው ተወለዱ። ቤታቸው በበረከት ተመላ። ለሀገሬው ዝናብ ዘንቦለት ህዝቡ ከፃድቁ እናትና አባት የተመፀወቱትን ከፍለው ዘሩ።

አቡነ ታዴዎስ በተወለዱ በ፵ ቀናቸው ሐምሌ ፪ ቀን ሲጠመቁ የተዘራው እህል አንድ ሳይቀር አፍርቶ ተገኝቷል።

ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለሊቀ ካህናቱ ለሕይወት ብነ ሰጥተዋቸው ሲማሩ አደጉ። አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞት (ወላይታ) ተሻግረው መተሎሚን አስተምረው “በእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ጸሎት መተሎሚን በሃይማኖት ወልጄዋለሁ። በምግባር አሳድጌዋለሁና እህትህን ይዘህ በቶሎ ና፤” ብለው ላኩባቸው።
እህታቸው ትቤጽዮን ትባላለች። የመተሎሚን ወንድም ዝግናን አግብታ አባ ኤልሳዕን ወልዳለች። ከባሏ ተጣልታ ነበርና እሷን ከባሏ አስታርቀው እሳቸው አቡነ ተክለሃይማኖትን እያገለገሉ ፱ ዓመት ኖረዋል።

በኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲሄዱ እሳቸውም ወደ ጽላልሽ ተመልሰው ስለነበር አፄ ይኩኖ አምላክ እንድትመክረኝ እንድትገስፀኝ ከቤቴ ተቀመጥ ብለው ከቤተመንግሥት አስቀመጣቸው።
ሰይጣን ለፀብ ለምቀኝነት አያርፍምና ጠላ ቤቷን ክፉ የሚገድል ሽታ አሸተታትና ሞተች። አባ ታዴዎስ ወንዝ ገብተው ሲፀልዩ ሙቷ ተነሥታለች። ከዚህ በኋላ ውዳሴ ከንቱ ይሆንብኛል ብለው ወደ ደብረ ሊባኖስ ተመለሱ።

አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ጽጋጋ (ጅጅጋ) ሂድ አሏቸው። ለምን ቢሉ? አባ አኖሬዎስ ሄደው ሲያስተምሩ ያገሬው ሰዎች ደብድበው አስረዋቸው ነበርና እሳቸውን ለማስፈታት ነበር።
የአካባቢው ንጉሥ መዩጥ ይባላል። በነፋስ ሰረገላ ተጭነው ሄደው ከፊቱ ወርደው ሲቆሙ ደንግጦ ከሰማይ መላእክት ነህ ወይስ ከሰው ወገን? ቢላቸው። እኔ ከሰው ወገን ነኝ አሉት። ክርስትናንም አስተማሩት ጋኔን ከእሳት ላይ ጥሎት ሲሰቃይ የሚኖር ልጅ ነበረው አድነውለታል።
ይህን አይቶ አምኖ ሕዝቡም እንዲያምኑና ክርስትናን እንዲቀበሉ አዋጅ ነገረ።

እንደ ሐዋርያው ታዴዎስ ፳፭ ግመል በመርፌ ቀዳዳ በተአምራት አሳልፈው በማሳየታቸው አፍጃል የሚባል ያንድ ባለጠጋ ልጅ በምትሐት እንደሚያደርጉት አድርጎ በመናገሩ ከግመሎቹ አንዲቱ ረግጣው ሞተ፤ ይህን ሙሳ የሚባል ልጅም በተቀበረ በሦስተኛው ቀን «አልዓዛርን ከሙታን በአስነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ና ተነስ» ብለህ ይህንን መቋሚያዬን ወስደህ ከመቃብሩ ላይ አኑር ብለው በአፍጃል ሰጥተውት እንዳሉት ቢያደርግ አፈፍ ብሎ ተነስቷል።
ይህን አይተው ህዝቡ ሁሉ አምነዋል። ከዚህ በኋላ ሙሳን ሙሴ ብለው ሊቀ ካህናት አድርገው ፲፪ አብያተ ክርስቲያናት አሳንፀው አኖሬዎስን ይዘው ተመልሰዋል።

አቡነ ተክለሃይማኖትም ከንጉሡ ተማክረው ሊቀካህናት ዘጽላልሽ ብለው ሾመዋቸዋል።
ንጉሥ ዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አድሮበት የአባቱን ቅምጥ ቢያገባት ሄደው ገሰፁት። በዚህ የተናደደች የንጉሡ ሚስት የኋሊት አሳስራ ከጥልቅ ገደል አስጣለቻቸው።
በዚህ ጊዜ የመቶ ሃያ ዓመት አረጋዊ ነበሩ።

የታዘዘ መልአክ ገብረ እግዚአብሔርና ውቢት የተባሉ ደጋግ ሰዎችን አስነስቶ ሥጋቸውን ወስደው ከበዓታቸው ቀብረው የተሰጣቸውንም ቃል ኪዳን በዳግማዊ አፄ ዳዊት ዘመን በህዝቡ ፊት መስክረዋል።
ንጉሥ ዳዊትም ዜና ገድላቸውን አጽፈዋል፤ ሥጋቸውንም ወደ ከተማቸው በክብር አፍልሰው በተቀደሰ ስፍራ አኑረውታል።

የፃድቁ አባታችን ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን!!!

(Sisay Poul እንደጻፈው - ነፍሱን ይማር)
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ግንቦት 24/09/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፮፥፲፰(36፥18)
ወየአምር እግዚአብሔር ፍኖተ ንጹሐን
ወለዓለም ውእቱ ርስቶሙ
ወኢይትሐፈሩ በመዋዕለ እኩያት


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፥፵-፵፪(10፥40-42)
ዘኪያክሙ ተወክፈ ኪያየ ተወክፈ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ገላትያ ፬፥፬-፲፫(4፥4-13)
ወአመ በጽሐ ዕድሜሁ…


👉ዲያቆን
📖 ራእየ ዮሐንስ ፲፪፥፲፫-፲፰(12፥13-18)
ወሶበ ርእየ ዝክቱ አርዌ…

ዓዲ፦ 📖 ጴጥሮስ ፩ ም ፩፥፰-፲፫(1፥8-13)
ወይእዜኒ ትትፌሥሑ በፍሥሓ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፪፥፳-፳፭(12፥20-25)
ወእምዝ ወረደ እምይሁዳ…


📖ምስባክ ዘቅዳሴ

ዘገብረ ተአምረ በግብጽ።
ወመንክረ በሐቅለ ጣኔዎስ።
ወረሰየ ደመ ለአፍላጊሆሙ።

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፸፯ ቊ. ፵፫ - ፵፬

፵፫ በግብጽ ያደረገውን ተኣምራቱን፥ በጣኔዎስም በረሃ ያደረገውን ድንቁን።

፵፬ ወንዞቻቸውንም ወደ ደም ለወጠ፥ ምንጮቻቸውን ደግሞ እንዳይጠጡ።



📖ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፪ ቊ. ፲፫ - ፲፮
ወእምድኅረ ሐለፉ ናሁ...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::

+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕጽዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአምላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::

=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግሥተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

=>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ
3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)

=>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት
ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ:
ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ::
ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር
ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
እናታችን ቅድስት ዮሐና

☞ጌታን ለ3 ዓመታት ያገለገለች:: (ሉቃ. ፰:፪)
☞ከሕማሙ ያልተለየች::
☞ከመስቀሉ እግር የተገኘች::
☞ትንሣኤውን ተመልክታ የሰበከች::
☞በዘመነ ሐዋርያትም ስመ ጥር የነበረች ቡርክት እናት ናት:: (ሉቃ. 24:10)
☞ግንቦት 24 ዓመታዊ በዓሏ ነው::

☞እናታችን ቅድስት ዮሐና ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት፡፡

✿በረከቷ በዝቶ ይደርብን፡፡✿

'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/