ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​መስከረም 20/01/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፱፥፱(39፥9)
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ
ወናሁ ኢከላእኩ ከናፍርየ
እግዚኦ ለሊከ ተአምር ጽድቅየ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፯፥፲፬-፲፰(7፥14-18)
ወበማእከለ መዋዕለ በዓል ዓርገ …


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ቲቶ ፩፥፭-፲፪(1፥5-12)
ወእንበይነ ዝንቱ ኀደጉከ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ያዕቆብ ፩፥፪-፲፫(1፥2-13)
ኦ አኃው ኩኑ በኵሉ ፍሥሓ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፥፳፰-፴፩(20፥28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ…



📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፹፫ ቊ. ፮ - ፯

፮ በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰንኻቸው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።

፯ ከኃይል ወደ ኃይልም ይሄዳል፥ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።


📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የዮሐንስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፩ - ፳፪
አማን አማን እብለክሙ...

📜ቅዳሴ


👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ pinned «Watch ""ሥርዓተ ጸሎት ክፍል ፮ [ሰባቱ የጸሎት ጊዜያት እና ምሥጢሮቻቸው ክፍል ኹለት] |subscribe አድርጉ||"" on YouTube https://youtu.be/PBZXhq_XbaI»
††† እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ግሼን ደብረ ከርቤ †††

††† ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::"

ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል::

በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ::

የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል::

አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል::

††† አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል::
በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል::

በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው::

††† ብዙኃን ማርያም / ጉባኤ ኒቅያ †
††† ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጉባኤውን ዜና ግን ሕዳር 9 ቀን የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው ይበለን:: ይህች ቀን ለአባቶቻችን የሱባኤ መጀመሪያ ናት::

††† ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና †††

††† ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::

በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም ዮስቴና (የሴቶች እመቤት) ትባላለች:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::

በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ:: ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::

አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::

ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት-የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኳን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ:: "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ: ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::
ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::
አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም በዚህ ዕለት ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::

††† ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን::

††† መስከረም 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ግሼን ደብረ ከርቤ
2.ብዙኃን ማርያም
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት
4.ቅዱስ ቆዽርያኖስ ሰማዕት
5.ቅድስት ዮስቴና ድንግል
6.ቅዱስ ጢባርዮስ ሐዋርያ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
††† "እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል:: እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ:: ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ:: ከእናንተም ይሸሻል:: ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ:: ወደ እናንተም ይቀርባል::" †††
(ያዕ. ፬፥፮)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
St. Cyprian (Cyprianus) ቅዱስቆጵርያኖስ& St. Justina ቅድስት ዮስቴና
ጎረጎር ማርያም (ገዳመ ፮ቱ አበው ቅዱሳን)

☞ጎረጎረ ማርያም የምትገኝው ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሲሆን የተመሰረተችው በ6ቱ ደጋግ ቅዱሳን ስውራን አቦቶች ነው፡፡

      የነዚህ አባቶችም

1 አባ መርዓዊ
2 አባ ደንቆሮ
3 አባ አላሽኝ
4 አባ ሙሴ
5 አባ ምሰሶ
6አባ ሞዓብራ ናቸው፡፡ (መስከረም 21 6ቱም ቅዱሳን የተሠወሩበት ነው)

     አስደናቂው ነገር

+ገዳሙበ6ጎራ የተከበበ መሆኑ
+ቅዱሳኖቹ በገዳሙ ተሰውረው መኖራቸው
+ከገዳሙ ሲገቡ ከሰማይ ውጭ ሌላ አለመታየቱ
+የዮርዳኖስ ወንዝ መኖሩ
+ፀበሉ በራሱ አስሮ የሚገርፍ መኖሩ
+ስውር ዋሻ መኖሩ
+ስውር ባህር መኖሩ
+በገዳሙ ሱባይ ለገባ72ቋንቋ መገለጡ
+ከዮርዳኖስ የታጠበ የ40እናየ80ቀን ህፃን መሆን መቻሉ ፡፡

          የተሰጣቸው ቃልኪዳን

1እግር ያጠበ
2 ስማቸውን የጠራ
3 ቦታውን የተረገጠ
4 በስማቸው የዘከረ
6 ገድል የሰማ ያሰማ የተረጎመ እስከ 10 ትውልድ ምሬላቹአለው ተብለው ተቀብለዋል፡፡

☞ጎረጎር እኔ ለመግለፅ ያክል ሞከርኩት እንጂ የጎረጎር ታሬኳ ገራሚ ነው አስደናቂም ነው፡፡በተለይ እምነቱ ላነሰው ፍቱን መዳኒት ናት ጎረጎር ማርያም  ፡፡ያየም አይቀርባት ያላየም እንዲያያት የታመመ እንዲድንባት፡፡

   ምዕራፈ ቅዱሳን ጎረጎረ  ማርያም

(መረጃው "የኖኅ መርከብ" ከሚል የfb ገጽ ተወስዷል)

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
ጎረጎር ማርያም (ገዳመ ፮ቱ አበው ቅዱሳን)
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​መስከረም 21/01/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፳፭፥፲፩-፲፪(25፥11-12)
አድኅነኒ እግዚኦ ወተሣሃለኒ
እስመ በርቱዕ ቆማ እገርየ
በማኅበር እባርከከ እግዚኦ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፲፥፲፭-፳፭(10፥15-25)
ወባሕቱ ጢሮስ ወሲዶና…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ቆሮንቶስ ፩ ም ፭፥፫-፲፫(5፥3-13)
ወአንሰ ለእመ ኢሀለውኩ በሥጋየ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፪ ም ፩፥፬-፲፫(1፥4-13)
ወተፈሣሕኩ ጥቀ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፱፥፲፯-፳፩(19፥17-21)
ወተሰምዐ ዝ ነገር…



📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፱ - ፲

፱ የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።

፲ ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤



📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፩ ቊ. ፴፱ - ፶፯
ወተንሥአት ማርያም...



📜ቅዳሴ


👉ዘሠለስቱ ምዕት (ግሩም) አው እግዝእትነ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
አበዊነ ቅዱሳን : ወዻዻሳት ሔራን : ርቱዓነ ሃይማኖት : ሠለስቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ
(ሃይማኖታቸው የቀና : ምግባራቸው የጸና : የተመረጡ አባቶቻችን : 318ቱ ዻዻሳት)

¤ዛሬ በኒቅያ መልካሙን ጉባኤ መጀመራቸውን ቤተ ክርስቲያን ታስባለች::
¤ዕለቱም "ብዙኃን ማርያም" ይሰኛል::
¤እኛም እንደ አባቶቻችን
"በእንተ ማርያም ዻጦስ ጸዋሪተ ነድ::
ንዑ ንዑ መምህራን ትባርኩነ ለውሉድ::
እንዘ ትእህዙ መስቀለ በዕድ::" እንላቸዋለን::

<< አማላጅነታቸውም : በረከታቸውም በዝቶ ይደርብን !! አሜን!! >>
"" ቅድስት ዮስቴና ድንግል ""

ደስ የምታሰኝ
ስም አጠራሯ ያማረና የተወደደች እናት ናት::
ድንግልም : ጻድቅም : መናኝም : እመ ምኔትም : ሰማዕትም ናት::

እግዚአብሔር አምላክ በበረከቷ ይባርከን!!

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር
✿ደፈጫ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት✿ (ጎንደር)

✿መደብ = ከ፵፬ቱ (ከ44ቱ) ታቦታት አንዷ
✿ሠሪ = አፄ በካፋ (ዛሬ መስከረም 21 ዕረፍታቸው ነው)
✿ዘመን = ከ1713-1723 (ከዚያም ትቀድማለች የሚሉ አሉ)
✿አደጋ = በ1880ዎቹ የሰደድ እሳት ደርሶባታል፡፡
✿ቅርስ = ዝርዝሩን ለደኅንነት ጉዳይ ትተን የምታዩት ሕንጻ ጥንታዊው ነው፡፡

✿መገኛ = ከጎንደር በምስራቅ በግምት 5 ኪሎ ሜትር፡፡

✿ተግዳሮት = የውሃና የመንገድ አለመኖር (ያለው መንገድ አስቸጋሪ ነው)

✿ክብረ በዓል = የካቲት እና ነሐሴ 16፡፡

✿ከበረከቷ ይክፈለን፡፡✿

Deacon Yordanos Abebe

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መንፈሳዊ ፊልም 👉ቅድስት ዮስቴና እና ቅዱስ ቆጵርያኖስ - ክፍል 1 _Saints Justina & St. Cyprian (Cyprianus)