ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
853 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo

        🕐 ​ታኅሣሥ 24/04/2016 ዓ.ም🕖
 
   በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
   መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፶፥፲፬(50፥14)
አድኅነኒ እምደም እግዚአብሔር አምላከ መድኃኒት ይትፌሣሕ ልሳንየ በጽድቀ ዚአከ እግዚኦ
ትከሥት ከናፍርየ ወአፉየ ያየድዓ ስብሓቲከ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፩፥፳፭-፴(11፥25-30)
በውእቱ መዋዕል አውሥአ ኢየሱስ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

           👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ኤፌሶን ፬፥፲፩-፲፯(4፥11-17)
ወውእቱ ወሀበ ጸጋ ወከፈለነ...

            👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፩፥፲፫-፳፭(1፥13-25)
ወይእዜኒ ቅንቱ ሐቌ ልብክሙ...

             👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፱፥፲፩-፳፩(19፥11-21)
ወዐቢየ ኃይለ ይገብር...

            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ
በእንተ ጸላዒ
ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ


               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፰ ቊ. ፪

፪ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፰ ቊ. ፩ - ፲፪
ወበይእቲ ሰዓት ቀርቡ ኀቤሁ...



        📜ቅዳሴ


👉ዘሐዋርያት

☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ታኅሳስ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት: ቅዱስ አግናጥዮስ እና ቅድስት አስቴር ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  ✞✞✞

+*"
#ቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት_ሐዋርያዊ "*+

*ልደት*

=>መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ:  #‎ጸጋ_ዘአብ  ካህኑና  #‎እግዚእ_ኃረያ  ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

+በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው  #‎ቅዱስ_ሚካኤል : ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

+አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24, በ1206 (1196) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ 24, በ1207 (1197) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

*ዕድገት*

=>የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " #‎ፍሥሃ_ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ  #‎አባ_ጌርሎስ  ተቀብለዋል::

*መጠራት*

=>አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት  #‎ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ  አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

+የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:

"ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

*አገልግሎት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ ( #‎ጽላልሽ ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ  #‎ኢትዮዽያ  2 መልክ ነበራት::

1.ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::

2.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

+ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት  #‎ሐዲስ_ሐዋርያ  አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

*ገዳማዊ ሕይወት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

+እነዚህም በአቡነ  #‎በጸሎተ_ሚካኤል  ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ  #‎ኢየሱስ_ሞዐ_ዘሐይቅ  ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ  #‎ዮሐኒ  ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::

+በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ  #‎ዞረሬ  ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::

*ስድስት ክንፍ*

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ  #‎እሥራኤል  የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

+የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት  #‎አባ_ሚካኤል  ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

+ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
¤በቤተ መቅደስ ብሥራቱን
¤በቤተ ልሔም ልደቱን
¤በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
¤በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
¤በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው  #‎ቀራንዮ  ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ  #‎እመቤታችን_ድንግል_ማርያም  ፈጥና ደርሳ ተክለአብን ወደሰማይ አሳረገቻቸው::

+በዚያም:-
¤የብርሃን ዐይን ተቀብለው
¤6 ክንፍ አብቅለው
¤የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
¤ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
¤ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

*ተአምራት*

=>የተክለአብ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

+ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

*ዕረፍት*

=>ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24, በ1306 (1296) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

=>የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች :-

1.ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ
2.ፍስሐ ፅዮን
3.ሐዲስ ሐዋርያ
4.መምሕረ ትሩፋት
5.ካህነ ሠማይ
6.ምድራዊ መልዐክ
7.እለ ስድስቱ ክነፊሁ (ባለስድስት ክንፍ)
8.ጻድቅ ገዳማዊ
9.ትሩፈ ምግባር
10.ሰማዕት
11.የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
12.ፀሐይ ዘበፀጋ
13.የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
14.ብእሴ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ሰው)
15.መናኒ
16.ኤዺስ ቆዾስ (እጨጌ)

=>እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:

+" #ቅዱስ_አግናጥዮስ "+

=>ይህ ቅዱስ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠገበ በመሆኑ በመላው ዓለም ዝነኛ ነው:: እርሱ:-
*በክርስቶስ እጅ ተባርኩዋል
*ፈጣሪውን ፊት ለፊት አይቷል
*ሐዋርያትን አገልግሏል
*ከምሥጢር አባት ከዮሐንስ ወንጌላዊ እግር ተምሯል
*ስለ ክርስትና ለአንበሶች ተጥሎ በመገደሉ "ምጥው ለአንበሳ" ይባላል::

+ቅዱስ አግናጥዮስ የተወለደው በክርስቶስ አምላካችን መዋዕለ ስብከት (በ30 ዓ/ም አካባቢ) እንደ ሆነ ይታመናል:: በትውፊትም በማቴ. 18:1 ላይ ያለው ሕጻን እርሱ ነው ይባላል::
+ሐዋርያት ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ ሲጠይቁት አንድ ሕጻንን (አግናጥዮስን) ከመሃል አቁሞ "ካልተመለሳችሁ: እንደዚህም ሕጻን ካልሆናችሁ ከቶውንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አትገቡም" ብሏቸዋል::

+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ሐዋርያት ለወንጌል ሲፋጠኑ ሕጻኑ ቅዱስ አግናጥዮስ እየተከተለ አገልግሏል: ተምሯል:: ኢየሩሳሌም በጥጦስ አስባስያኖስ ቄሣር በጠፋችበት ዓመት (በ70 ዓ/ም) ቅዱሱ የአንጾኪያ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሹሟል::

+ከዚህ በሁዋላም ለ2 እና 3 አሠርት ዓመታት ከወንጌላዊ ዮሐንስ ጋር አብሮ ወንጌልን ሰብኩዋል:: የዚህ ቅዱስ ተጋድሎ ጫፍ የደረሰው ከ100 ዓ/ም በሁዋላ ሁሉም ሐዋርያት ሰማዕት በመሆናቸውና ትልቁን ኃላፊነት እርሱ በመሸከሙ ነው:: የወቅቷን ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳኑ ቀሌምንጦስ ዘሮምና ፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ ጋር ሆኖ እስከ ደም ጠብታ ጠብቁዋል::

+ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ አግናጥዮስ ለዘመናት ወንጌልን እየሰበከ በሕይወቱና በትምሕርቱ አስተማረ:: ብዙ መልእክቶችን (ድርሳናትንም) ጻፈ:: በመጨረሻው ግን በጠራብሎስ ቄሣር ተይዞ: በብረት ሰንሰለት ታስሮ: ከአንጾኪያ (ሶርያ) ወደ ሮም (ጣልያን) ተወሰደ::

+ደሙ እስኪፈስም ገረፉት:: ዛሬ በሮም ከተማ ግማሽ አካሉ ፈርሶ በሚታየው ስታዲየም (በአባቶቻችን አጠራር ተያጥሮን) እንዲገደል ተወሰነበት:: በወቅቱ ባደረገው ንግግርም ቄሣሩና ሕዝቡ ድፍረቱን አደነቁ:: በመጨረሻም ለአንበሳ እንዲሰጥ ተደርጐ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆነ::

+" #ቅድስት_አስቴር "+

=>ይህቺ ቅድስት እናት:-
*እሥራኤል በባቢሎን ምርኮ ሳሉ የነበረች
*አባቷ አሚናዳብ ባለ መኖሩ በአጐቷ መርዶክዮስ እጅ ያደገች
*እጅግ ውብ በመሆኗ የአርጤክስስ ሚስት (ንግሥት) ለመሆን የበቃች
*ራሷን መስዋዕት አድርጋ ወገኖቿን አይሁድን ከሞት ያተረፈች
*ለመርዶክዮስ ክብርን: ለአማሌቃዊው ሐማ ደግሞ ስቅላትን ያስፈረደች እና
*እግዚአብሔር ሞገስ የሆናት እናት ናት::
*ዛሬ ዕረፍቷ ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን ባጸናበት ቅዱስ መንፈሱ እኛንም ያጽናን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ታሕሳስ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱሳን ጸጋ ዘአብና እግዚእ ኃረያ
3.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያ
4.ቅድስት አስቴር
5.አባ ፊሎንጐስ ሊቀ ዻዻሳት
6.አባ ዻውሊ ጻድቅ
7.ጻድቃን ቅዱሳን ዘከዲህ

=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
2.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
3.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
4.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
5."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
6.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

=>+"+ ንግሥቲቱም አስቴር መልሳ:- 'ንጉሥ ሆይ! በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ: ንጉሡንም ደስ ቢያሰኘው: ሕይወቴ በልመናዬ: ሕዝቤም በመሻቴ ይሰጠኝ:: እኔና ሕዝቤ ለመጥፋትና ለመገደል: ለመደምሰስም ተሸጠናልና:: +"+ (አስቴር. 7፥3)

 † ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ  ]

💚💛
@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ