https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
🕐 ታኅሣሥ 22/04/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፴፯፥፩-፪(137፥1-2)
በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ
ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ
ወእገኒ ለስምከ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፩፥፳፮-፴፱(1፥26-39)
ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ...
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፪ ም ፩፥፰-፲፰(1፥8-18)
ወኢትኅፈር እንከ በእንተ ስምዑ...
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፬፥፱-፲፰(4፥9-18)
ወበዝንቱ ተዐውቀ ፍቅሩ...
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፪፥፯-፲፪(12፥7-12)
ወበይእቲ ዕለት እንተ ጸቢሖ...
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ
ወትሰይሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር
ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፲፮ - ፲፯
፲፮ በአባቶችሽ፡ፋንታ፡ልጆች፡ተወለዱልሽ፥በምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡ገዢዎች፡አድርገሽ፡ትሾሚያቸዋለሽ።
፲፯ ለልጅ፡ልጅ፡ዅሉ፡ስምሽን፡ያሳስባሉ፤
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ም. ፩ ቊ. ፴፱ - ፶፯
ወተንሥአት ማርያም ፍጡነ...
📜ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️

Telegram
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw

=>+"+ እንኳን "ለተአምረ እግዝእትነ ማርያም": "ቅዱስ ደቅስዮስ": "ቅዱስ አንስጣስዮስ" እና "ቅዱስ ገብርኤል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
† 🕊 ተአምረ ማርያም 🕊 †
=>"ተአምር" የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ): ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል::
+ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው "ኤልሻዳይ - ከሐሌ ኵሉ - ሁሉን ቻይ" እያልን የምንጠራው::
+እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ (1ኛ ነገሥት) እንደ ነበር ይታወቃል::
+እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. 10:8, 17:20, ማር. 16:17, ሉቃ. 10:17, ዮሐ. 14:12)
+እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: (ሐዋ. 3:6, 5:1, 5:12, 8:6, 9:33-43, 14:8, 19:11)
+በተአምራት ብዛት ደግሞ ከጌታ ቀጥላ ድንግል እመ ብርሃን ትጠቀሳለች:: ዛሬም የምናስበው የእርሷን ተአምራት ነው::
+የእግዝእትነ ማርያም ሙሉ ሕይወቷ ተአምር ነው:: አበው:- "ድንግል ተአምራት ማድረግ የጀመረችው ገና ሳትወለድ ነው" ሲሉ የሚጸንባቸው ሰዎች አሉ:: ከአዳም ውድቀት በሁዋላ በእርሷ እንደሚድን "ሴቲቱ" (ዘፍ. 3:15) በሚል ከተነገረው በሁዋላ ድንግል በብዙ ተአምራት (በምሳሌ) ተገልጣለች::
+ለአብነት ያህልም እግዚአብሔር ኖኅን ከጥፋት ውሃ እንዲሁ ማዳን ሲችል ተአምራቱን በመርከብ ገለጠ:: (ዘፍ. 7:1) ለሚያስተውለው ያቺ መርከብ ናት ድንግል::
+አብርሃም ይስሐቅን ሊሰዋ ሲል በተአምራት በግ በእፀ ሳቤቅ ተይዞ ተገኝቷል:: (ዘፍ. 22:13) ያዕቆብ በቤቴል ድንቅ መሰላልን ተመልክቷል:: (ዘፍ. 28:12) ሙሴ በጽላቱ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: (ዘጸ. 34:29, ዘሌ.10:1)
+የአሮን በትር ስትለመልም ድንቅ ተአምራቱ እመቤታችንን ያሳያል:: ኢሳይያስ የድንግልን መጽነስ "ምልክት (ተአምር) ይሰጣቹሃል" ሲል ገልጾታል:: (ኢሳ. 7:14)
+በሐዲስ ኪዳንም የድንግል:-
*ያለ በደል መጸነሷ:
*ንጽሕት ሆና መወለዷ:
*በቤተ መቅደስ ለ12 ዓመታት ምድራዊ ምግብን አለመመገቧ:
*ያለ ወንድ ዘር መጽነሷ (ሉቃ. 1:26):
*ያለ ምጥ መውለዷና
*በልደት ዕለት የታዩ ተአምራት (ሉቃ. 2:1):
*እናትም: ድንግልም መሆኗ (ሕዝ. 44:1) ሁሉ በራሱ ድንቅ ተአምር ነው::
+ከዚህ ባለፈም በቃና ዘገሊላ ያደረገችውን ዐይነ ልቡናው ከታወረበት ሰው ውጪ ዓለም ያውቃል:: (ዮሐ. 2:1) ባለ ራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ:-
"ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ:: ፀሐይን ተጐናጽፋ: ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት: በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች" ብሎ የእመቤታችን መገለጥ (መታየት) በራሱ ተአምር መሆኑን ነግሮናል:: (ራዕይ. 12:1)
+ድንግል እመቤታችን በሕይወተ ሥጋ ከሠራችው ተአምራት በበዛ መንገድ ላለፉት 2ሺ ዓመታት ስትሠራ ኑራለች:: እየሠራች ነው:: ገናም ትቀጥላለች:: ለሚያምናት ተአምራትን መሥራት ብቻ አይደለም: ነፍሱንም ከሲዖል ታድነዋለች::
+ሁሉን ቻይ ልጅ አላትና እርሷም ሁሉን ትችላለች:: እንኩዋን የፈጣሪ እናት ድንግል ማርያም የክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያቱም "የሚሳናችሁ የለም" ተብለዋል:: (ማቴ. 17:20)
† 🕊 ቅዱስ ደቅስዮስ 🕊 †
=>ይህ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ በዘመነ ጻድቃን አካባቢ እንደ ነበረ ይታመናል:: ከምናኔ ሕይወቱ ባሻገር በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ የጥልጥልያ ሃገር ዻዻስም ነበር:: ይሕ ቅዱስ ሰው በእውነቱ ያስቀናል::
+እመቤታችንን ሲወዳት መንጋትና መምሸቱ እንኩዋ አይታወቀውም ነበር:: ፍቅሯ በደም ሥሮቹ ገብቶ በደስታ ያቃጥለው ነበርና ዘወትር እያመሰገናት አልጠግብ አለ:: የሚያስደስትበትን ነገር ሲያስብ ደግሞ የተአምሯ ነገር ትዝ አለው::
+ከዚያ በፊት የእመቤታችን ተአምሯ በየቦታው ይነገራል: ይጻፋል: ይሰበካል:: ግን በአንድ ጥራዝ አልተያዘም ነበርና በሱባኤ: በፈጣሪው እርዳታ: በፍጹም ድካም የእመ ብርሃንን ተአምራት ሰብስቦ በአንድ ጠረዘውና ለአገልግሎት ቀረበ::
+እርሷን ከመውደዱ የተነሳ ይህንን አድርጉዋልና እመ ብርሃን ወደ እርሱ ወረደች:: "ወዳጄ ደቅስዮስ ደስ አሰኘኸኝ" አለችው:: መጽሐፉንም ተቀብላው ባረከችው:: "አመሰግንሃለሁ" ብላውም ተሰወረችው::
+በዚህ ጊዜ ቅዱሱ ሐሴትን አደረገ:: (እመቤታችን ማየት እንዴት ያለ ሞገስ ይሆን!)
ቅዱስ ደቅስዮስ ግን ፍቅሯ እንደ እሳት ልቡን አቃጠለው:: አሁንም ደስ ሊያሰኛት ምክንያትን ይሻ ነበር::
+እመቤታችን ጌታን የጸነሰችበት በዓል (መጋቢት 29) ሁሌም ዐቢይ ጦም ላይ እየዋለ ለማክበር አይመችም ነበርና ቅዱሱ ታሕሳስ 22 ቀን ሊያከብረው ወሰነ:: በሃገሩ ያሉ ክርስቲያኖችን ጠርቶ ታላቅ በዓልን ለድንግል አከበረ::
+ሕዝቡም ጸጋ በዝቶላቸው ስለ እመቤታችን ታላቅ ሐሴትን አደረጉ:: በዚያች ሌሊትም እመ ብርሃን በሞገስ ወረደች:: "ወዳጄ ደቅስዮስ! ዛሬም ፍጹም ደስ አሰኘኸኝ! እኔም ስለ ክብርህ ይህንን አመጣሁልህ" ብላ ሰማያዊ ልብስና ዙፋን ሰጠችው::
+ማንም እንዳይቀመጥበት ነግራው: ባርካው ዐረገች:: ከዚህች ዕለት በሁዋላ ቅዱስ ደቅስዮስ ፈጣሪውንና ድንግል እናቱን ሲያገለግል: ተአምሯን ሲሰበስብ: ምዕመናንን ሲመራ ኑሮ በዚህች ዕለት ዐርፏል:: ከእርሱ በሁዋላ የተሾመው ዻዻስም በድፍረት በእርሱ ዙፋን ላይ በመቀመጡ መልአክ ቀስፎ ገሎታል::
+የእመቤታችንን ተአምር መስማትና ማንበብ ያለውን ዋጋ የሚያውቅ ጠላት ሰይጣን ግን ዛሬም ድረስ ባሳታቸው ሰዎች አድሮ ተአምሯን ይቃወማል:: <እኛ ግን ለእመቤታችን እንሰግዳለን!! ተአምሯንም እንሰማለን!! ጥቅማችን እናውቃለንና!!>
+ለመረጃ ያህልም:-
*የእመቤታችን ተአምር የሰበሰበ (ቅዱስ ደቅስዮስ)
*የተአምሯን ሥርዓት ያዘጋጁ (ቅዱሳን አበው ማቴዎስ: ማርቆስና አብርሃም ሶርያዊ)
*እሰግድ ለኪን የደረሰው (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)
*የተአምሯን ሃሌታ (ቅዱስ ያሬድ)
*የዘወትሩን መቅድም (ቅዱሳን ሊቃውንት) ናቸው::
<< ልመናዋ ክብሯ በእውነት ለዘለዓለሙ ይደርብን !! >>
† 🕊 ቅዱስ አንስጣስዮስ 🕊 †
=>የግብጽ 36ኛ ፓትርያርክ የሆነው ይህ አባት በ6ኛው ክ/ዘ የተወለደ ሲሆን በትጋቱ: በትምሕርቱና በድርሰቱ ይታወቃል:: ምዕመናንን ለማስተማርም ከ12,000 በላይ ድርሰቶችን ደርሷል:: ብዙ መከራዎችን አሳልፎ በ7ኛው መቶ ክ/ዘ ዐርፏል::

† 🕊 ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል 🕊 †
=>ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከ7ቱ ሊቃናት አንዱ: በራማ አርባብ በሚባሉ 10 ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ: በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና: ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ: ሠለስቱ ደቂቅን: ዳንኤልን: ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::+ከምንም በላይ ቤተ ክርስቲያን "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: የስሙ ትርጏሜ "አምላክ ወሰብእ-እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::
መልዐኩ እመቤታችንን ከመጸነሷ ጀምሮ ባይለያትም ከእግዚአብሔር ተልኮ አብስሯታል::
+ቅዱስ ገብርኤል ዛሬ የብሥራቱ መታሰቢያና ዳናህ በተባለ ሃገር ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ነው::
"ገብርኤል ዜናዊ ምጽዓተ ክርስቶስ አንበሳ::
ለዛቲ በዓልከ በዘይትሌዓል ሞገሳ::
በዓለ ማርያም አንበረ ደቅስዮስ በርዕሳ::" እንዲል:: (አርኬ)
=>ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን : ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አዕምሮውን: ጥበቡን በልቡናችን አሳድሪብን::
=>ታሕሳስ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ተአምረ ማርያም
2.ቅዱስ ደቅስዮስ ጻድቅ
3.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
4.ቅዱስ አንስጣስዮስ ሊቅ
5.አባ አርኬላዎስ
=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.አባ እንጦንስ
3.አባ ዻውሊ የዋህ
4.ቅዱስ ዮልዮስ
5.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
=>+"+ የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው:: መንፈስ ግን አንድ ነው:: አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው:: ጌታም አንድ ነው. . . ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር . . . ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ: ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ . . . ይሰጠዋል:: +"+ (1ኛቆሮ. 12፥4)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ]
💚💛❤@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛❤
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

🕐 ታኅሣሥ 23/04/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፹፥፲፱(80፥19)
ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ
ወረከብክዎ ለዳዊት ገብርየ
ወቀባዕክዎ ቅብዐ ቅዱስ
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፪ ም ፪፥፰-፲፱(2፥8-19)
ተዘከሮ ለኢየሱስ ዘተንሥአ እሙታን...
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፪-፰(5፥2-8)
ረዐዩ ዘሀሎ ኀቤክሙ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፫፥፴-፵፬(13፥30-44)
ወአስተርአዮሙ ብዙኅ መዋዕለ...
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ለስሒት መኑ ይሌብዋ
እምኅቡዓትየ አንጽሐኒ
ወእምነኪር መሐኮ ለገብርከ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፲፰ ቊ. ፲፪-፲፫
፲፪ ስሕተትን፡ማን፡ያስተውላታል፧ከተሰወረ፡ኀጢአት፡አንጻኝ።
፲፫ የድፍረት፡ኀጢአት፡እንዳይገዛኝ፡ባሪያኽን፡ጠብቅ፤የዚያን፡ጊዜ፡ፍጹም፡እኾናለኹ፥ከታላቁም፡ኀጢአት፡
እነጻለኹ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፪ ቊ. ፴፩ - ፵፮
ወበእንተ ትንሣኤ ሙታንሰ...
📜ቅዳሴ
👉ዘሠለስቱ ምዕት (ግሩም)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🕐 ታኅሣሥ 23/04/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፹፥፲፱(80፥19)
ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ
ወረከብክዎ ለዳዊት ገብርየ
ወቀባዕክዎ ቅብዐ ቅዱስ
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፪ ም ፪፥፰-፲፱(2፥8-19)
ተዘከሮ ለኢየሱስ ዘተንሥአ እሙታን...
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፪-፰(5፥2-8)
ረዐዩ ዘሀሎ ኀቤክሙ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፫፥፴-፵፬(13፥30-44)
ወአስተርአዮሙ ብዙኅ መዋዕለ...
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ለስሒት መኑ ይሌብዋ
እምኅቡዓትየ አንጽሐኒ
ወእምነኪር መሐኮ ለገብርከ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፲፰ ቊ. ፲፪-፲፫
፲፪ ስሕተትን፡ማን፡ያስተውላታል፧ከተሰወረ፡ኀጢአት፡አንጻኝ።
፲፫ የድፍረት፡ኀጢአት፡እንዳይገዛኝ፡ባሪያኽን፡ጠብቅ፤የዚያን፡ጊዜ፡ፍጹም፡እኾናለኹ፥ከታላቁም፡ኀጢአት፡
እነጻለኹ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፪ ቊ. ፴፩ - ፵፮
ወበእንተ ትንሣኤ ሙታንሰ...
📜ቅዳሴ
👉ዘሠለስቱ ምዕት (ግሩም)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
Telegram
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኳን ለጻድቅ: የዋሕና ልበ አምላክ ቅዱስ #ዳዊት ንጉሥ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
✞✞✞ 🌷ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ🌷 ✞✞✞
=>ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- "እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ: አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:20) ብሎ ሲናገር ሰምተን እጅግ አደነቅን::
+እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ "ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ" (መዝ. 88:35) ይላል::
*አቤት አባታችን ዳዊት ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል* እንላለን::
+ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት:-
1.ሃብተ ትንቢት
2.ሃብተ መንግስት
3.ሃብተ ክህነት
4.ሃብተ በገና (መዝሙር)
5.ሃብተ ፈውስ
6.ሃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::
+በ7ቱ ስሞቹም:-
1.ጻድቅ
2.የዋህ
3.ንጹሕ
4.ብእሴ እግዚአብሔር
5.ነቢየ ጽድቅ
6.መዘምር እና
7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::
+"+🌷 ልደት🌷 +"+
=>ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለ ልደቱ ሲናገር "እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ-በኃጢአት ተጸነስኩ" ይላል (መዝ. 50:5) አበው እንደ ነገሩን የቅዱስ ዳዊት አባት ደጉ እሴይ ከነገደ ይሁዳ የኢዮቤድ ልጅ ነው::
+ሚስቱን ሰሊብን አንድ ጐልማሳ በዝሙት ዐይን ሲፈልጋት ተመልክቶ ነበር:: አንድ ቀንም መንገድ ሔድኩ ብሎ ግን ያንን ጐልማሳ መስሎ ተመልሶ አብሯት አድሯል:: በዚያች ሌሊትም ቅዱስ ዳዊት ተጸንሷልና እንዲህ ብሏል::
+"+ 🌷ዕድገት🌷 +"+
=>ቅዱስ ዳዊት ከሕጻንነቱ ጀምሮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ነበር:: ሕጻን ሳለ በእረኝነት በጐቹን አያስነካም ነበር:: አንበሳውን በጡጫ: ድቡን በእርግጫ: ነብሩን በሩጫ የያዙትን ያስጥላቸው ነበር:: በጥቂቱ በበግ እረኝነት ስለ ታመነ ለእሥራኤል እረኛ ሊሆን ተመርጧል::
+"+ 🌷መቀባት🌷 +"+
+እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሁዋላ ከእሴይ ልጆች መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ" ቢለው ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም ገብቷል::
+በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: 7ቱን የእሴይን ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ:: ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ::
+በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ::
+"+ 🌷ዳዊትና ጐልያድ🌷 ++
=>ኢሎፍላውያን በጠላትነት በተነሱባቸው ጊዜም ጐልያድ የሚሉት የጌት ሰው እሥራኤልን ሲያስጨንቅ ለ40 ቀናት ቆይቶ ነበር:: ለአምላኩ ስምና ክብር የሚቀና ቅዱስ ዳዊት ግን በድፍረት ገጥሞ በፈጣሪው ኃይል: በጠጠር ጥሎታል:: ከእሥራኤልም ሽሙጥን አርቁዋል:: ግን ቅዱሱ ብላቴና 3 ክንድ ከስንዝር: ጐልያድ ደግሞ 6 ክንድ (3 ሜትር) የሚረዝም ሰው ነበር::
+"+ 🌷ስደት🌷 +"+
=>ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ዙፋን አልጠበቀውም:: ጠላታቸውን ጥሎ ስላዳናቸው ፈንታ: ሳዖልን በገና እየደረደረ ስለ ፈወሰው ፈንታም ሊገደል ተፈለገ:: ፈጣሪው ከእርሱ ጋር ባይሆንም ይገድሉት ነበር::
+እርሱ ግን ለ18 ዓመታት በትእግስት ተሰደደ:: ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ጠላቱን ሳዖልን አሳቻ ሥፍራ ላይ አግኝቶ በምሕረት ተወው:: በዚህ የዋሕነቱም በብሉይ ሆኖ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ" የምትለውን ሕግ ፈጸማት:: (ማቴ. 7:45, መዝ. 16:4)
+"+🌷 ንግሥና🌷 +"+
=>ቅዱስ ዳዊት የስደት ዘመኑ ሲፈጸም ሳዖል ሞተ:: ምን ጠላቱ ቢሆን 'የሳዖል ገዳይ ነኝ' ያለውን ተበቀለ:: ስለ ጠላቱም አለቀሰ:: 30 ዓመት ሲሆነው ነግሦ ለ7 ዓመታት በኬብሮን: ለ33 ዓመታት በኢየሩሳሌም (ጽዮን) ሕዝበ እግዚአብሔርን ጠብቁዋል::
+በዘመኑም ጠላቶቹን ሁሉ ድል አድርጉዋል:: በልጁ አቤሴሎም እጅ መሰደድን: በሳሚ ወልደ ጌራ መሰደብንም ታግሷል::
+"+🌷 ንስሃ🌷 +"+
=>ቅዱሱ ንጉሥ ሁሉ ነገር የተሰጠው አባት ነው:: ሁሉ ሕይወቱም ለእኛ ት/ቤት ነው:: ሰው ነውና የኦርዮን ሚስት ቀምቶ: ኦርዮን አስገድሎ ነበር:: ጉዳዩን ነቢዩ ናታን በምሳሌ ሲነግረው ፍጹም ተጸጸተ::
+ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ አለቀሰ:: መሬትንም በእንባው ክንድ አራሳት:: ሐረግ እስከ ማብቀልም ደረሰ:: እግዚአብሔርም ንስሃውን ተቀብሎ ከፍ ከፍ አደረገው:: በንስሃ ለምትገኝ ጸጋም ምሳሌ ሆነ::
+"+ 🌷ነቢይነት🌷 +"+
=>በቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ቅዱስ ዳዊትን የሚያህል ነቢይ (ምሥጢር የበዛለት) አልተገኘም:: 'ከዓለም በፊት እንዲህ ነበረ' ብሎ: ከዚያ ከሥነ ፍጥረት እስከ ዳግም ምጽዓት የተናገረ እርሱ ነው::
+ስለ መላእክት: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግልና መነኮሳት ሁሉ መናገሩ ይደነቃል:: ስለ ድንግል ማርያምና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስም አምልቶ: አስፍቶ ተናግሯል:: 150 ምዕራፎች ባሉት መጽሐፈ ትንቢቱ ኃላፍያትንና መጻዕያትን ተመልክቷል::
+ስለዚህም አበው:-
"አልቦ ምስጢር ወአልቦ ትንቢት:
ዘኢተናገረ አቡነ ዳዊት" ይላሉ::
+"+🌷 መዝሙር🌷 +"+
=>ቅዱሱ ነቢይና ንጉሥ በጣም የሚታወቀው በዝማሬው ነው:: ለራሱ ባለ 10 አውታር : ለመዘምራኑ ደግሞ ባለ 8 አውታር በገናን አዘጋጅቶ ፈጣሪውን ያመሰግን ነበር:: 24 ሰዓት ሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር እንዳይቁዋረጥ 288 መዘምራንን በአሳፍ መሪነት መድቦ ነበር::
+ራሱም በፍጹም ተመስጦ: ማር ማር እያለው እግዚአብሔርን ያመሰግነው ነበር:: "ቃልህ ለጕረሮዬ ጣፋጭ ነው" እንዲል:: (መዝ. 118:103) የዳዊት መዝሙሩ ለአጋንንት ትልቅ ጠላት ነው:: ቅዱሳን መላእክትም በዳዊት መዝሙር ይዘምራሉ::
"በዘቦቱ ይሴብሑ ሰማያውያን ወምድራውያን" እንዲል::
+"+🌷 #ዳዊትና ጽዮን 🌷+"+
=>ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን አንጾ ጽላተ ኪዳኑን አመጣ:: ለአምላከ ያዕቆብ ማደሪያን ሊፈልግም ዐይኑ ከእንቅልፍ ተከለከለ:: (መዝ. 131:2) የፈጣሪውን ፈቃድ ሊጠይቅ ሱባኤ ቢገባ "አኮ አንተ ዘትነድቅ ሊተ ቤተ - አንተ ሳትሆን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው" አለው::
*አያይዞም የምሥጢረ ሥጋዌን ነገር ቢገልጥለት "ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ - እነሆ በኤፍራታ ሰማነው" ሲል ተናግሯል:: (መዝ. 131:6) የኪዳኑ ጽላት (ጽዮን) ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ከዙፋኑ ወርዶ: ከተራው ሕዝብ ጋርም ተቀላቅሎ በበገናና በመሰንቆ ተጫወተ::
*ስለ ፈጣሪው ክብሩን ተወ:: ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የሚገዛ ኃያል ንጉሥ ነበርና:: በጽዮን ፊት እየወደቀ: እየተነሳ: እየታጠቀ: እየፈታ ሲዘምርም ሚስቱ ሜልኮል ናቀችው:: እግዚአብሔር ግን ከፍ ከፍ አደረገው:: (ሳሙ. 6:16)
+"+🌷 ክብረ ዳዊት 🌷+"+
=>እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ኢየሩሳሌምን ብዙ ጊዜ ታድጉዋል:: ሰሎሞንና ሕዝቅያስን (ነገሥታቱን) ይቅር ያላቸው ስለ ባለሟሉ ስለ ዳዊት ነው::

*የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቃል "የዳዊት ልጅ . . . " የምትል ናት:: (ማቴ. 1:1) ጌታችን "ወልደ ዳዊት" መባልን ወዷልና:: እንዲያውም ራሱ "እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ" ሲል ተናግሯል:: (ራዕ. 22:16)
+"+🌷 ዕረፍት 🌷+"+
=>ነቢየ ጽድቅ: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እሥራኤልን ለ40 ዓመታት መርቶ አረጀ:: 'ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ?' ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና::
*በዚያውም ላይ አንድ ቀን ስለ ሕዝበ አሥራኤል ቤዛ ይሆናቸው ዘንድ በቀሳፊ መልአክ ፊት ቆሞ ነበርና (ዜና. 21:16) ሰውነቱ ደከመ:: በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ70 ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመት በፊት በዚህች ቀን ዐርፏል::
+"+ 🌷ዳዊት በሰማይ🌷 +"+
=>በራዕየ ጐርጐርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ 99ኙ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል:: ከርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሳ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል:: በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው::
*በነገረ ማርያም ትምሕርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው::
*እንግዲህ ምን እላለሁ! ስለ ቅዱስ ዳዊት ከዚህም በላይ መጻሕፍት ብዙ ይላሉ:: ክብሩ ታላቅ ነውና::
<< በእውነት . . . በእውነት . . . በእውነት . . . ያለ ሐሰት ለዳዊት ክብርና ምስጋና ይገባል >>
=>አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን:: በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን::
✞✞✞ ታሕሳስ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
3.አባ ሳሙኤል ጻድቅ
4.አባ ስምዖን ጻድቅ
5.አባ ገብርኤል ጻድቅ
6.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
2.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
3.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
=>+"+ ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ:: ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት::ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት::
እጄም ትረዳዋለች:: ክንዴም ታጸናዋለች::
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም::
የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም::
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ::
የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ:: +"+ (መዝ. 88፥20)