Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
🕊ቅድስት እለ እስክንድርያ🕊
✝በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት አምና ሰማዕት የሆነች
✝ቅዱስ ጊዮርጊስን ላሰቃየው ንጉሥ ለዱድያኖስ ሚስቱ የነበረች።
✝ ማመኗን ሰምቶ አሰቃይቶ በሰማዕትነት እንድታልፍ ያደረገ ባሏ ንጉሥ ዱድያኖስ ነው።
✝የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕተ ክርስቶስ በገድሉ ያፈራት ፍሬ።
<<ከቅድስት እለ እስክንድርያ በረከት ጽናት ያድለን::>>
@zeortodox_kidusan_pic

https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
🕐 ጥቅምት 24/02/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፲፩፥፱(111፥9)
ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ
ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም
ወይትሌዓል ቀርኑ በክብር
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፱፥፲፮-፳(19፥16-20)
ወናሁ መጽአ ፩…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ም ፲፬፥፳፮-፴፬(14፥26-34)
ወይእዜኒ አኃዊነ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፫፥፭-፲(3፥5-10)
ወከማሁ ትካትኒ ቅዱሳት አንስት…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፲፫-፲፮(16፥13-16)
ወነበርነ በይእቲ ሀገር ኅዳጠ መዋዕለ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም
ወከዐዉ ደሞሙ ከመ ማይ ዐውዳ ለኢየሩሳሌም
ወኀጥኡ ዘይቀብሮሙ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፸፰ ቊ. ፪ - ፫
፪ የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤
፫ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማርቆስ ወንጌል ም. ፲፫ ቊ. ፲፩ - ፳፬
ወሶበሂ ያበጽሑክሙ...
📜ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ አው ዘ፫፻
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️

Telegram
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ጥቅምት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †††
† 🕊 ቅዱስ አብላርዮስ ገዳማዊ 🕊 †
††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::
+ታላቁ ቅዱስ አብላርዮስ ደግሞ ካለ ማመን ወደ ማመን: ከማመን ወደ መመንኮስ: ከመመንኮስ ወደ መጋደል: ከመጋደል ወደ ትሕርምት: ከዚያም ወደ ፍጹምነት የደረሰ: በምድረ ሶርያም ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፋ አባት ነው::
+ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::
+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::
+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::
+ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጽሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::
+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ 'የባሕታውያን አባት' ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::
+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::
+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል:: ከእነዚህም አንዱና ዋነኛው ዛሬ የምናከብረው ታላቁ ጻድቅ አባ አብላርዮስ ነው::
+ቅዱስ አብላርዮስ ሶርያዊ ሲሆን የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ነው:: በቀደመ ሕይወቱ ክርስትናን ፈጽሞ የማያውቅ ሰው ነበር:: ለዚህ ምክንያቱ የወላጆቹ ኢ-አማንያን መሆን ነው::
+ገና በልጅነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልስፍና: የዮናናውያንን ጥበብ ተምሮ ፈላስፋ ሁኗል:: በ16 ዓመቱም በምድረ ሶርያ አሉ ከሚባሉ የጥበብ ሰዎች አንዱ ሆነ:: ቅዱሱ ማንበብና መጠየቅን አብዝቶ ይወድ ነበር::
+የሚያነበው ነገር በሶርያ ቢያጣ በ17 ዓመቱ ተጨማሪ ጥበብን (እውቀትን) ፍለጋ ወደ ግብጽ (እስክንድርያ) ወረደ:: በዚያ ግን ከሰማቸው ትምህርቶች አንዱ ልቡን ገዛው:: በወቅቱ በግብጽ ላይ ፓትርያርክ የነበረው ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ስለ ምድራዊው ያይደለ ስለ ሰማያዊው ጥበብ ሲያስተምር ሰምቶ ተገረመ::
+ቅዱስ አብላርዮስ በዚህ ሰዓት የሰበሰባቸውን የፍልስፍና መጻሕፍት ጥሎ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያነብ ጀመረ:: ቅዱስ እለ እስክንድሮስም የሚከብድበትን እያፍታታ ተረጐመለት:: በአጭር ጊዜም ክርስቲያን ሆኖ ተጠመቀ::
+በዚያው ዓመትም ከከተማ ወጥቶ ወደ በርሃ ገባ:: ከአባ እንጦንስ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርት አንዱ ሆኖ መነኮሰ:: በዚያም በጾምና በጸሎት: በመታዘዝና በትሕትና ለዓመታት ኖረ:: ቀጥሎም ወሬ ነጋሪ መጥቶ ወላጆቹ ማረፋቸውን ነገረው::
+በዚህ ጊዜ ቅዱስ አብላርዮስ ከአባ እንጦንስ ዘንድ ተባርኮ: ማኅበሩንም ተሰናብቶ ሶርያ ገባ:: የወላጆቹን ሃብትና ንብረት በሙሉ መጽውቶ ወደ ሶርያ በርሃ ወጣ:: በወቅቱ በአካባቢው ምንኩስና እየተነቃቃ ነበርና የቅዱሱ መምጣት ይበልጥ አጠናከረው::
+ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ኤዺፋንዮስን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፈራ:: በአካባቢውም ታላቅ መካሪ: ናዛዥ: አጽናኝ: መሪ ሆነ:: ከብዙ ተአምራቱ ባለፈ ሃብተ ትንቢት የተሰጠው አባት ነውና እጅግ ክቡር ነበር::
*የገድሉን ነገርማ ማን ተናግሮ ይፈጽመዋል!
+እርሱ ከዕለተ ሰንበት በቀር እህልን አይቀምስም:: ለዚያውም እሑድ በነግህ (ጧት) ትንሽ ሳር ነጭቶ ከመብላት በቀር ሌላ የሚበላው አልነበረውም:: እንዲህ ባለ የበርሃ ሕይወት ለ63 ዓመታት ኖረ:: በዓለም የኖረበትን 17 ዓመት ብንደምረው 80 ይሆናል:: ቅዱሱ በተወለደ በ80 ዓመቱ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚህች ቀን ዐርፏል::
+አምላከ ቅዱስ አብላርዮስ ጥበቡን: ፈሊጡን: ሕይወቱን ይግለጽልን:: ከበረከቱም አይለየን::
+ጥቅምት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አብላርዮስ ገዳማዊ
2.ቅድስት ጸበለ ማርያም
3.ቅድስት አውስያ
4.አባ ዻውሎስ ሊቀ ዻዻሳት
=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
6."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
++"+ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁን ተመልከቱ:: እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች: ኃይለኞች የሆኑ ብዙዎች: ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም:: ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝነት መረጠ . . . ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ:: ነገር ግን:- የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ:: +"+ (1ቆሮ. 1፥26)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ]
💚💛❤@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛❤
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

🕐 ጥቅምት 25/02/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ም ፲፩፥፲፫-፳፭(11፥13-25)
ለክሙ እብል ለአሕዛብ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ራዕይ ም ፲፪፥፲፫-፲፰(12፥13-18)
ወሶበ ርእየ ዝንቱ አርዌ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፩፥፩-፲፪(11፥1-12)
ወሰምዑ ሐዋርያት ወቢጾሙሂ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ዐፀደ ወይን አፍለስከ እምግብጽ፣
ሰደድከ አሕዛበ ወተከልከ ኪያሃ፣
ወፄሕከ ፍኖተ ቅድሜሃ።
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፸፱ ቊ. ፰ - ፱
፰ ከግብጽ፡የወይን፡ግንድ፡አመጣኽ፤አሕዛብን፡አባረርኽ፡ርሷንም፡ተከልኽ።
፱ በፊቷም፡ስፍራን፡አዘጋጀኽ፥ሥሮቿንም፡ተከልኽ፡ምድርንም፡ሞላች።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፩ ቊ. ፴፫ - ፵፮
ካልእተ ምሳሌሁ ስምዑ...
📜ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🕐 ጥቅምት 25/02/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ም ፲፩፥፲፫-፳፭(11፥13-25)
ለክሙ እብል ለአሕዛብ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ራዕይ ም ፲፪፥፲፫-፲፰(12፥13-18)
ወሶበ ርእየ ዝንቱ አርዌ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፩፥፩-፲፪(11፥1-12)
ወሰምዑ ሐዋርያት ወቢጾሙሂ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ዐፀደ ወይን አፍለስከ እምግብጽ፣
ሰደድከ አሕዛበ ወተከልከ ኪያሃ፣
ወፄሕከ ፍኖተ ቅድሜሃ።
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፸፱ ቊ. ፰ - ፱
፰ ከግብጽ፡የወይን፡ግንድ፡አመጣኽ፤አሕዛብን፡አባረርኽ፡ርሷንም፡ተከልኽ።
፱ በፊቷም፡ስፍራን፡አዘጋጀኽ፥ሥሮቿንም፡ተከልኽ፡ምድርንም፡ሞላች።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፩ ቊ. ፴፫ - ፵፮
ካልእተ ምሳሌሁ ስምዑ...
📜ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
Telegram
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞
=>+"+ እንኳን ለታላቁ "ጻድቅና ሰማዕት አቡነ አቢብ": "አባ ዕብሎይ" እና "ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
† 🕊 አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) 🕊 †
=>ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን!
¤እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል!
¤ቅዱሱ አባታችን:- "ቡላ - የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::
¤ዳግመኛም "አቢብ - የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::
¤እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::
¤አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ!
¤ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ!
¤ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ!
¤የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::
+"+ ልደት +"+
=>አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::
+በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"
+"+ ጥምቀት +"+
=>ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በሁዋላ ሳይጠመቅ ለ 1 ዓመት ቆየ::
ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኩዋን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ "አጥምቀው" አለችው::
+ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ:- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::
+"+ ሰማዕትነት +"+
=>የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ10 ዓመታት አሳድገውት ድንገት ኅዳር 7 ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ10 ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::
+በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና 2 ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ 18 ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::
+"+ ገዳማዊ ሕይወት +"+
=>ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በሁዋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::
+ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል::
ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::
+"+ ተጋድሎ +"+
=>አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::
+በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ42 ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::
+የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ (ሃቢብ) ይሁን" አለው::
"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ:
ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል::
+" ዕረፍት "+
=>አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎይን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::
+ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ "አምላከ አቢብ ማረኝ" ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኩዋ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::
† 🕊 ታላቁ አባ ዕብሎይ 🕊 †
=>ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት "ርዕሰ ገዳማውያን" ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በዕለተ ዕረፍቱ (የካቲት 3 ቀን) እንመለከተዋለንና የዚያ ሰው ይበለን::
† 🕊 ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት 🕊 †
=>ከሁሉ አስቀድሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ (አድናቆት): ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::
+ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘ) ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ እንኩዋን የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ - የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: (መዝ. 78፥3)
+እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና 300 አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::
+በወቅቱ የክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር::
በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::

+ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም ብለው ይመርቁት ነበር::+እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና ሰማዕታቱን ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፈለ::
+ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ ወደ ሃገረ ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ:: በተአምሩም መኮንኑና ሠራዊቱ አምነው ተከተሉት::
+በፍጻሜውም በሌላ ሃገር መኮንኑ ቅዱስ ዮልዮስን ከቤተሰቡና ከ1,500 ያህል ተከታዮቹ ጋር: 2ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል::
=>አምላከ ጻድቃን ወሰማዕት በቃል ኪዳናቸው እንዲምረን ቸርነቱ ይርዳን:: በረከታቸውንም አትርፎ ይስጠን::
=>ጥቅምት 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
2.አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
3.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
5.ቅዱሳን አሞኒና ሙስያ (የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች)
=>ወርሐዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
6.ታላቁ አባ ቢጻርዮን
=>+"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: +"+ (ማቴ 16፥24)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ]
💚💛❤@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛❤
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
+ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ ወደ ሃገረ ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ:: በተአምሩም መኮንኑና ሠራዊቱ አምነው ተከተሉት::
+በፍጻሜውም በሌላ ሃገር መኮንኑ ቅዱስ ዮልዮስን ከቤተሰቡና ከ1,500 ያህል ተከታዮቹ ጋር: 2ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል::
=>አምላከ ጻድቃን ወሰማዕት በቃል ኪዳናቸው እንዲምረን ቸርነቱ ይርዳን:: በረከታቸውንም አትርፎ ይስጠን::
=>ጥቅምት 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
2.አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
3.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
4.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
5.ቅዱሳን አሞኒና ሙስያ (የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች)
=>ወርሐዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
6.ታላቁ አባ ቢጻርዮን
=>+"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: +"+ (ማቴ 16፥24)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ]
💚💛❤@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛❤
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
🕐 ጥቅምት 26/02/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፰፥፬(108፥4)
ወአንሰ እጼሊ
ፈደዩኒ እኪተ ህየንተ ሠናይት
ወጸልዑኒ ህየንተ ዘአፍቀርክዎሙ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፫፥፶፬-፶፰(13፥54-58)
ወሖረ ሀገሮ ወመሀሮሙ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ገላትያ ፩፥፲፭-፳፬(1፥15-24)
ወአመ ሠምረ እግዚአብሔር ዘፈለጠኒ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፪፥፳፰(22፥28)
ወይእዜኒ ደቂቅየ ንበሩ ባቲ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፮፥፩-፰(6፥1-8)
ወውእተ ዓሚረ በዝኁ ሕዝብ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ይዌስክ እግዚአብሔር ላዕሌክሙ
ላዕሌክሙ ወላዕለ ውሉድክሙ
ቡሩካኑ አንትሙ ለእግዚአብሔር
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፲፫ ቊ. ፳፪-፳፫
፳፪ እግዚአብሔር በላያችሁ፥ በላያችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይጨምር።
፳፫ እናንተ ሰማይንና ምድርን ለሠራ ለእግዚአብሔር የተባረካችሁ ናችሁ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፩ - ፲፪
ወእምዝ አርአየ እግዚእነ ካልኣነ...
📜ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🕐 ጥቅምት 26/02/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፰፥፬(108፥4)
ወአንሰ እጼሊ
ፈደዩኒ እኪተ ህየንተ ሠናይት
ወጸልዑኒ ህየንተ ዘአፍቀርክዎሙ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፲፫፥፶፬-፶፰(13፥54-58)
ወሖረ ሀገሮ ወመሀሮሙ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ገላትያ ፩፥፲፭-፳፬(1፥15-24)
ወአመ ሠምረ እግዚአብሔር ዘፈለጠኒ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፪፥፳፰(22፥28)
ወይእዜኒ ደቂቅየ ንበሩ ባቲ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፮፥፩-፰(6፥1-8)
ወውእተ ዓሚረ በዝኁ ሕዝብ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ይዌስክ እግዚአብሔር ላዕሌክሙ
ላዕሌክሙ ወላዕለ ውሉድክሙ
ቡሩካኑ አንትሙ ለእግዚአብሔር
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፲፫ ቊ. ፳፪-፳፫
፳፪ እግዚአብሔር በላያችሁ፥ በላያችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይጨምር።
፳፫ እናንተ ሰማይንና ምድርን ለሠራ ለእግዚአብሔር የተባረካችሁ ናችሁ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፩ - ፲፪
ወእምዝ አርአየ እግዚእነ ካልኣነ...
📜ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
Telegram
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
#ጥቅምት_26
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ስድስት በዚህች ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ #ሐዋርያ_ቅዱስ_ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ፣ የጌታ ወንድም የተባለው #ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ መታሰቢያው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሐዋርያ_ጢሞና
ጥቅምት ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም ቅዱስ ጢሞና ሰማያዊ ሀብትን መለኮታዊ ኃይልን ገንዘብ አድርጎ በሽተኞችን ፈወሳቸው አጋንንትም ተገዙለት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ በምድር ሳለ አገለገለው። ወደ ሰማይም ከዐረገ በኋላ ሐዋርያትን አገለገላቸው በሃምሳኛው ቀንም ጰራቅሊጦስ በወረደ ጊዜ የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከእርሳቸው ጋር ተቀበለ።
ከዚህም በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ሐዋርያት ሾሙት እነርሱ መንፈስ ቅዱስን ዕውቀትንም የተመሉ እንደሆኑ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምስክር ሁኖአል።
በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት አስተማረ ከዮናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው።
የዚያች አገር ገዥም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዮሴፍ መታሰቢያ ነው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ የጌታችን ወንድም የተባለውና የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የነበረው ነው፡፡
እርሱም የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ሲሆን ከልጆቹ ሁሉ ትንሹ ነው፡፡ ድንግልና ንጹሕ ሆኖ ከጌታችን ጋር እየተጫወተ አብሮ አድጓል፡፡ የያዕቆብ ወላጅ እናቱ በልጅነቱ ስለሞተችበትና የብርሃን እናቱ የሆነች ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን ዮሴፍ አረጋዊ በ83 ዓመቱ ጠባቂ ይሆናት ዘንድ ወደቤቱ ሲወስዳት ድንግል ማርያም ያዕቆብን የሙት ልጅ ሆኖ አግኝታው ከወለደችው ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ጋር አብራ ተንከባክባ አሳድጋዋለች፡፡
ያዕቆብ ከጌታችን ጋር አብሮ እየተጫወተ እያለ አንድ ቀን ትግል ይገጥማሉ፡፡ ያዕቆብም ጌታችንን አንስቶ ጣለው፡፡ ድጋሚ ተያያዙና አሁንም ያዕቆብ ጌታችንን ጣለው፡፡ ሦስተኛ ጊዜም እንዲሁ ሆነና ያዕቆብ የልብ ልብ ተሰማው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ድጋሚ ትግል ሲያያዙ ግን ጌታችን ያዕቆብን ወደ ሰማይ ወርውሮ መሬት ላይ በኃይል ጣለው፡፡ ያዕቆብም እጅግ ደንግጦ "ኃይልህን ደብቀህ ቆይተህ አሁን ምነው እንዲህ ታደርገኛለህ?" ሲለው ጌታችንም "እኔኮ ካልጣሉኝ አልጥልም" አለው፡፡
ከጌታችን ዕርገት በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ አድርገው ሾመውታል፡፡ ብዙዎችንም አስተምሮ ወደ ቀናች ሃይማኖት መልሷቸዋል፡፡ ሕዝቡም የታመሙትን ድውያንን ሁሉ እያመጡለት ይፈውሳቸው ነበር፡፡ ከኢየሩሳሌምም ውጭ እየሄደ ያላመኑትንም አስተምሮ እያጠመቀ ቤተ ክርስቲያን ይሠራላቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በጾም በጸሎት ሆኖ በመቆም ብዛት እግሮቹ አብጠው ነበር፡፡
አንድ ቀን አይሁድ ተሰብስበው መጥተው ጌታችን የማን ልጅ እንደሆነ ይነግራቸው ዘንድ ወደ ያዕቆብ መጡ፡፡ እነርሱም ወደ ያዕቆብ የመጡት ጌታችን የዮሴፍ ልጅ እንደሆነና የእርሱም የሥጋ ወንድም እንደሆነ እንደሚነግራቸው አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ያዕቆብ ከፍ ካለው ከሦስተኛው መደብ ላይ ወጥቶ ጌታችን የራሱ የያዕቆብና የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን መሰከረባቸው፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ፍጹም አምላክ መሆኑን፣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና ከአብም ጋር ትክክል እንደሆነ መሰከረባቸው፡፡ ይህንንም በሰሙ ጊዜ አይሁድ እጅግ ተናደው በጽኑ ግርፋት ካሠቃዩት በኋላ ራሱን ቀጥቅጠው ገደሉት ሰማዕትነቱን ሐምሌ 18 ቀን በድል ፈጽሟል፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)