https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
🕐 መስከረም 30/01/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፲፯፥፳፭(17፥25)
ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ
ወምስለ ብእሲ ንጹሕ ንጹሐ ትከውን
ወምስለ ኀሩይ ኅሩየ ትከውን
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፬፥፲፰-፳፫(4፥18-23)
ወእንዘ ያንሶሱ መንገለ ባሕረ ገሊላ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ም ፱፥፳-፳፯(9፥20-27)
ወኮንክዎሙ ለአይሁድ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፪ ም ፩፥፰-፲፫(1፥8-13)
ዑቁ ርእሰክሙ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፥፳፰-፴፩(20፥28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም
ሶበ ይሄልዉ አኃው ኅቡረ
ከመ ዕፍረት ዘይውኅዝ እምርእሱ እስከ ጽሕሙ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፴፪ ቊ. ፩ - ፪
፩ ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።
፪ ከራሱ ጀምሮ እስከ ጢሙ፥ በልብሱ መደረቢያ ላይ፥ እስከሚወርደው እስከ አሮን ጢም ድረስ እንደሚፈስ
ሽቱ ነው።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማርቆስ ወንጌል ም. ፩ ቊ. ፲፮ - ፳፫
ወእንዘ የኀልፍ...
📜ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️

Telegram
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw

††† እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሊቀ ዻዻሳት እና ለአባ ሣሉሲ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
† 🕊 ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 🕊 †
††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያሕል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም::
††† ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው?
††† ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ (በ300 አካባቢ) እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር::
ሕጻን እያለ ለጭዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ብሏቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ::
ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት::
ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሳቱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ: የሚገባውን መንፈሳዊ ትምህርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚሕ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና::
ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው:: ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው::
ከዚሕ በኋላ የእስክንድርያ (የግብፅ) 20ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ:: ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ48 ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀበለ:: ለ5 ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ ሲያግዙት በስደት ከ15 ዓመታት በላይ አሳልፏል::
በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር (በደብዳቤ) ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚሕ ዘመን የተጻፈ ነው:: ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ370ዎቹ ዓ/ም አካባቢ አርፏል::
††† ቤተ ክርስቲያን
¤ሊቀ ሊቃውንት:
¤ርዕሰ ሊቃውንት:
¤የቤተ ክርስቲያን /የምዕመናን/ ሐኪም (Doctor of the Church):
¤ሐዋርያዊ ብላ ታከብረዋለች::
††† ይህች ዕለት ለታላቁ ሊቅ የስደቱ መታሠቢያ: ከስደቱም የተመለሰባት ቀን ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በወቅቱ የነበረው ንጉሥ (ትንሹ ቆስጠንጢኖስ) የአባቱን (ታላቁ ቆስጠንጢኖስን) ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ::
ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ነበር::
በተለይ አንድ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ (የልጆቹን) ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግሥት ገብቶ ተናገረው::
ሁለት አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ (ምዕመናን) መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ::
ቀዛፊ: መቅዘፊያ: ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ::
ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፉ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት በዚህች ቀን እስክንድርያ(ግብጽ) አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል::
† 🕊 አባ ሣሉሲ ክቡር 🕊 †
††† የእኒህ አባት ዜና ሕይወትን ሳስበው እጅግ ይገርመኛል:: የአባቶቻችን የሕይወት ፈሊጥ ምን እንደ ሆነ እንድረዳ ስላደረጉኝ በእውነቱ አመሰግናቸዋለሁ:: ጻድቁ የዘመነ ከዋክብት አንድ ፍሬ ናቸው::
በነበሩበት ገዳም የሚታወቁት ግን 'የማይጾመው: የማይጸልየው: ሥራ ፈቱ መነኩሴ' በሚል ነበር:: ገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንድም ቀን ቢሆን ሲጸልዩና ሲሰግዱ ያያቸው የለም:: ሁሌ ብቻ እንደ ሞኝ ቁጭ ብለው ያኝካሉ::
በዚህ ምክንያትም ሥጋ ወደሙን ወስደው አያውቁም:: አንድ ቀን ግን በገዳሙ በዓል ላይ አበምኔቱና መነኮሳቱ መከሩ:: 'አባ ሣሉሲን አሥረን አውለን ለቁርባን ቢያንስ እናብቃቸው' ሲሉ ወሰኑ:: በውሳኔው መሠረትም በጧት ሒደው ጻድቁን አሠሯቸው::
አባ ሣሉሲም "ፍቱኝ ቁርሴን ልብላበት" ሲሉ ተቆጡ:: መነኮሳቱ ግን "ሳትቆርብ አንለቅህም" አሏቸው:: በዚህ ጊዜ ጻድቁ ቆባቸውን አውልቀው " እመቤቴ የሰው ልጅስ ጨካኝ ነው:: አንቺ ግን ርሕርሕት ነሽ" ብለው በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለ2 ተሰነጠቀ::
እርሳቸውም 2 ክንፍ አውጥተው በረው ተሰወሩ:: ባዩት ነገር የደነገጡ መነኮሳት እያለቀሱ 300 ጊዜ "እግዚኦ . . ." አሉ:: በዚህ ጊዜ የጻድቁን ቆብ አገኙ:: በዚህች ቆብም አጋንንትን አሳደዱ ተአምራትንም ሠሩ::
††† ምሥጢሩስ ምንድን ነው ቢሉ: አባ ሣሉሲ:-
1. 24 ሰዓት ሙሉ በተመስጦ (በልባቸው) ስለሚጸልዩ::
2. በጧት ተነስተው የሚያኝኩት ደረቅ ሣር እንጂ ምግብ አልነበረምና ነው:: ከውዳሴ ከንቱ መራቅ ማለት ይሔው ነው:: ጻድቁ በዚህች ቀን ዐርፈው ተቀብረዋል::
††† አምላከ አበው ምሥጢራቸውን አይሰውርብን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
††† መስከረም 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
2.አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ
3.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ ሐዋርያት (ለወንጌል የተጠሩበት /ማር. 1፥19/)
4.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
5.አባ አብሳዲ ዘደብረ ማርያም
6.አባ አሮን ዘገሊላ
††† ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
††† "ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ: በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትንም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና::" †††
(ማቴ. ፭፥፲)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ]

✝✞✝ እንኳን ለቅዱስ እና ጻድቅ አባ ገሪማ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝
† 🕊 አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ 🕊 †
=>አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ::
+እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን #ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ : መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::
+አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው #አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር::
+ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን #ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::
+እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ #ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::
+አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም:: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ::
+ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ" (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "#አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ::
+አቡነ ገሪማ ወደ #መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል:: ይህም የተደረገው በዚህች ቀን (መስከረም 30) ነው::
+ጻድቁ ወንጌልን : ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:-
1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
"ነግሃ ይዘርዕ ኪነቶ:: ወሠርከ የዓርር ገራኅቶ::" እንዲል::
2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::
4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::
5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ (ወንጌለ ዮሐንስን ሲጽፉ) ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል::
+ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በሁዋላ #ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ : መታሰቢያህን ያደረገ : እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ #ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል::
=>ቸሩ አምላካችን ከታላቁ ቅዱስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::
=>+"+ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ::
ግርማው በእሥራኤል ላይ : ኃይሉም በደመናት ላይ ነው::
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::
የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን : ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል::
እግዚአብሔርም ይመስገን:: +"+ (መዝ. 67፥34)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ]
💚💛❤@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛❤
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

በስንክሳር ላይ እንደተዘገበው ግመል በመርፌ ቀዳዳ ያሾለከ ሐዋርያ
Anonymous Quiz
5%
ቅዱስ ጴጥሮስ
59%
ቅዱስ ታዴዎስ
27%
ቅዱስ ጳውሎስ
9%
ቅዱስ ቶማስ
ትክክለኛው የትኛው ነው?
Anonymous Quiz
8%
ሀ. ጸሎት
0%
ለ. ስላሴ
20%
ሐ. ሥላሴ
4%
መ. በዓል
0%
ሠ. በአል
12%
ረ. ፀሎት
0%
ሰ. ሀ፣ለ፣ሐ
4%
ሸ. መ፣ሀ፣ረ
52%
ቀ. ሀ፣ሐ፣መ
Forwarded from ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ (🕊ኢዮአታም🕊)
https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo
🕐 ጥቅምት 01 /02/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፵፭÷፮-፯ (145÷6-7)
ዘየዐቅባ ለጽድቅ ዘለዓለም
ወይፈትሕ ሎሙ ለግፉዐን
ዘይሁቦሙ ሲሳዮሙ ለርኁባን
📖ወንጌል
ሉቃ ፲፪፥፳፯-፴፪ (12፥27-32)
ናሁ ጽጌያተ ገዳም ርእዩ...
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ም. ፯ ቊ. ፴፪ - ፵
አንሰ እፈቅድ ለክሙ...
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ም. ፫ ቊ. ፩- ፭
ወከማሁ አንትንሂ አንስት...
👉ንፍቅ ካህን
📖የሐዋርያት ሥራ ም. ፲፯ ቊ. ፲ - ፲፫
ወቢጾሙሰ...
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ
ሰብእሰ ከመ ሣዕር መዋዕሊሁ
ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፪ ቊ. ፲፬ - ፲፭
፲፬ ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።
፲፭ ሰውስ በዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፮ ቊ. ፳፭ - ፴፬
ወበእንተዝ እብለክሙ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🕐 ጥቅምት 01 /02/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፵፭÷፮-፯ (145÷6-7)
ዘየዐቅባ ለጽድቅ ዘለዓለም
ወይፈትሕ ሎሙ ለግፉዐን
ዘይሁቦሙ ሲሳዮሙ ለርኁባን
📖ወንጌል
ሉቃ ፲፪፥፳፯-፴፪ (12፥27-32)
ናሁ ጽጌያተ ገዳም ርእዩ...
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ም. ፯ ቊ. ፴፪ - ፵
አንሰ እፈቅድ ለክሙ...
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ም. ፫ ቊ. ፩- ፭
ወከማሁ አንትንሂ አንስት...
👉ንፍቅ ካህን
📖የሐዋርያት ሥራ ም. ፲፯ ቊ. ፲ - ፲፫
ወቢጾሙሰ...
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ
ሰብእሰ ከመ ሣዕር መዋዕሊሁ
ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፪ ቊ. ፲፬ - ፲፭
፲፬ ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።
፲፭ ሰውስ በዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፮ ቊ. ፳፭ - ፴፬
ወበእንተዝ እብለክሙ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️ @sinkisar_gisawe_z_tewahedo ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
Telegram
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።
👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ጥቅምት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
† 🕊 ቅድስት አንስጣስያ ሰማዕት 🕊 †
=>በቀደመው ዘመን: በተለይም በሮም አካባቢ ይህ ስም በጣም የተለመደ ነበር:: በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳትም ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አልነበረም:: የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን ሃገረ ሮሜ እስከ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ የሁሉ መኖሪያ ነበረች::
+ደጉም ሆነ ክፉው: ኃጥኡና ጻድቁ: አረማዊና ምዕመኑ: ጨካኙና ርሕሩሁ: ወዘተ. . . በአንድ ላይ ይኖሩባት ነበር:: በዚህ ዘመንም ቦታዋ ብዙ ሐዋርያትን: ሰማዕታትን: ሊቃውንትንና ጻድቃንን አፍርታለች:: (ዛሬን አያድርገውና)
+ከእነዚህ ቅዱሳን አንዷ ደግሞ ሰማዕትነትን ከጽድቅና ድንግልና ጋር የደረበችው እናታችን አንስጣስያ ናት:: ቅድስቲቱ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዳ ያደገችው እዛው ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነቷ የክርስትናን ምንነት ጠንቅቃ አውቃለች::
+ወጣት በሆነች ጊዜም ይህቺ ዓለም ጠልፋ እንዳትጥላት ትጠነቀቅ ነበር:: ይህቺ ዓለም ወጥመዶቿ ብዙ ናቸውና:: በተለይ ደግሞ መልክ ስለ ነበራትና ወላጆቿም ባለጠጐች ስለ ነበሩ እርሷ ትኅርምትን ታበዛ ነበር::
+ድንግልናዋን በንጽሕና ትጠብቀው ዘንድ ጾምንና ጸሎትን ከስግደት ጋር አዘወተረች:: በሒደትም በውስጧ ፍቅረ ክርስቶስ እየተቀጣጠለ በመሔዱ ይህንን ዓለም ልትተወው አሰበች:: ነገር ግን ወላጆቿ "ልጃችን ለአካለ መጠን ደርሰሻልና እንዳርሽ" አሏት::
+እርሷም "እኔ ለሰማያዊው ሙሽርነት: ለመንፈሳዊውም ሰርግ ተጠርቻለሁና ተውኝ" ብላቸው ወደ ገዳም ሔደች:: በዘመኑ በሮም ከተማ ዙሪያ ብዙ የደናግል ገዳማት ነበሩና ከእነዚያው ከአንዱ ገባች::እንደ ገባች ለሰውነቷ ምክንያትን ልትሠጠው አልፈለገችም::
+ራሷን በጾም ትቀጣው ዘንድ በ48 ሰዓት (በ2 ቀን) አንዴ ብቻ ትበላ ነበር:: ምግቧም ቁራሽ ቂጣ በጨው ብቻ ነበር:: ዓቢይ ጾም በደረሰ ጊዜ ግን ከእሑድ በቀር እህልን አትቀምስም ነበር:: የጌታዋ ፍቅር አገብሯታልና ለሳምንት ራሷን ከምግብና ከምቾት ትከለክል ነበር::
+ይህም ሲሆን ቁጭ ብላ አይደለም:: በጸሎትና በስግደት እየተጋች: ለደናግሉ በሙሉ እየታዘዘች ነው እንጂ:: ለጥቂት ዓመታት በእንዲህ ያለ ገድል ቆይታ ከእመ ምኔቷ ጋር በዓል ለማክበር አንድ ቀን ከገዳማቸው ወጡ:: በመንገድ ላይ ሳሉ አረማዊ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ሰብስቦ ሲያሰቃይ ደረሱ::
+በእርግጥ ዐይተው እያዘኑ ማለፍ ቢችሉም ቅድስት አንስጣስያ ግን አልቻለችም:: የወገኖቿ ስቃይ ቢያንገበግባት በድፍረት ወደ መኮንኑ ቀርባ ዘለፈችው:: "አንተ አዕምሮ የጐደለህ! እንዴት በአምላካቸው ደም የተገዙ ክርስቲያኖችን እንዲህ ያለ በደላቸው ታሰቃያቸዋለህ?" አለችው::
+በድፍረቷ የተገረመው መኮንኑም ወደ እርሱ አስቀርቦ "ማንን ታምኚያለሽ?" አላት:: እርሷም ሰማዩንና ምድሩን: ባሕሩንና የብስን የፈጠረውን: ስለ ሰው ፍቅርም የሞተውንና የተነሳውን: ዘለዓለማዊ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልካለሁ" አለች:: እጅግ ስለ ተበሳጨም ስቃይን አዘዘባት:: በገድል የተቀጠቀጠ ለምለም አካሏን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ ወታደሮቹ አሰቃዩዋት:: በመጨረሻም ሞት ተፈርዶባት በዚህች ቀን ገደሏት::
+ቅድስት እናታችን አንስጣስያ የጽድቅን: የድንግልናን: የምስክርነትን አክሊል በእግዚአብሔር መንግሥት አገኘች:: ይህን ሁሉ ስትጋደል ግን እድሜዋ ገና ወጣት ነበር::
† 🕊 ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት 🕊 †
=>በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ 2 እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት-ከኃጢአት የተመለሰች': 2ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር-በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::
+በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል 12፥1 ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት (ድንግሊቱ) ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::
+ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::
+በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::
+ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ4ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ "እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እኁየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: (ዮሐ. 11)
+ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በሥልጣነ ቃሉ አዝዞ አልዓዛርን አስነሳው:: ከፋሲካ (ጌታ ከመሰቀሉ 6 ቀናት) በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: (ዮሐ. 12፥1)
+በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ300 ዲናር ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::
+በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል:: ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል:: ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስክሯል::
+ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል:: (ቅዳሴ ማርያም) ቅድስት ማርያም በጌታችን ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ: ሲቀብሩት ነበረች:: ትንሣኤውንም ዐይታለች::
+ከጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች:: ቅድስት እናታችን ማርያም እንተ ዕፍረት ዛሬ እንዳረፈች እናዘክራለን::
🕊 የእናቶቻችን ቅዱሳት አምላክ ፍቅራቸውን ያድለን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
=>ጥቅምት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አንስጣስያ (ድንግል: ጻድቅት: ሰማዕት)
2.ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
3.ቅድስት ሶስና ድንግል
4.ቅድስት ኅርጣን ድንግል
=>+"+ ሲሔዱም ወደ አንዲት መንደር ገባ:: ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው:: ለእርሷም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት:: እርሷም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች . . . ኢየሱስም መልሶ . . . 'ማርያምም መልካም እድልን መርጣለች:: ከእርሷም አይወሰድባትም' አላት:: +"+ (ሉቃ. 10፥38)