🌼እንኳን አደረሰን!
"መስቀልከ እግዚኦ ተሰብሐ
ኃይለ መስቀልከ ሙቁኃነ ፈትሐ
መስቀልከ እግዚኦ ተሰብሐ
ኃይለ መስቀልከ እለ ለምጽ አንጽሐ
መስቀልከ እግዚኦ ተሰብሐ
ኃይለ መስቀልከ አጋንንተ አውጽአ
መስቀልከ እግዚኦ ተሰብሐ
ኃይለ መስቀልከ ሙታነ አንሥአ
መስቀልከ እግዚኦ ተሰብሐ
ወሠርዓ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ
መስቀልከ እግዚኦ ተሰብሐ
ወቃልከ እሙን ፈድፋደ።"
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

https://t.me/zekidanemeheret
🕐 መስከረም 18/01/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፹፫፥፮-፯(83፥6-7)
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፭፥፩-፲፯(5፥1-17)
ወሶበ ርእየ ብዙኀነ አሕዛበ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፲፥፲፩-፳፩(10፥11-21)
ወይቤ መጽሐፍ ኵሉ ዘየአምን ቦቱ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፪ ም ፫፥፲፬-፲፰(3፥14-18)
ወይእዜኒ አኀውየ ዘንተ እንዘ ትሴፈዉ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፬፥፳፮-፳፰(14፥26-28)
ወእምህየ ነገዱ አንጾኪያ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
አንተ ትኴንን ኃይለ ባሕር
ወአንተ ታረምሞ ለድምፀ ማዕበላ
አንተ አሕሠርኮ ለዕቡይ ከመ ቅቱል
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፹፰ ቊ. ፱ - ፲
፱ የባሕርን ኃይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ።
፲ አንተ ትዕቢተኛውን እንደ ተገደለ አዋረድኸው፥ በኃይልህም ክንድ ጠላቶችህን በተንሃቸው።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፭ ቊ. ፰ - ፲
ከማሁ ብእሲትኒ ለእመ ባቲ ዐሥሩ...
📜ቅዳሴ
👉ዘሠለስቱ ምዕት (ግሩም)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞✞✞
✞✞✞ እንኳን ለአበው #ቅዱሳን_ኤዎስጣቴዎስ_አኖሬዎስና_ማር_ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
† 🕊 አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ረባን 🕊 †
=>ሐዋርያዊው ጻድቅ ኢትዮዽያዊ (ኤርትራዊ) ሲሆኑ በዓለም ደረጃ የሚታወቅ አገልግሎት ያላቸው አባት ናቸው:: በመካከለኛው ዘመን የኢትዮዽያ ታሪክ የኤዎስጣቴዎስንና የተክለ ሃይማኖትን ያህል ስሙ የጐላ ጻድቅ አይገኝም::
+ጻድቁ በ1265 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለዱ ሲታመን ወላጆቻቸው #ክርስቶስ_ሞዐ እና #ሥነ_ሕይወት ይባላሉ:: የጻድቁ የመጀመሪያ ስም #ማዕቀበ_እግዚእ (ለጌታ የተጠበቀ) ነው:: ኤዎስጣቴዎስ የተባሉ በኋላ ነው::
+ገና ከልጅነታቸው መንፈሰ እግዚአብሔር አድሮባቸዋልና ለዚህ ዓለም ግድ አልነበራቸውም:: ከመምህር ዘንድ ገብተው: ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው: ዲቁናን ተቀብለው ያገለግሉ ገቡ:: በዲቁና አገልግሎታቸው ስሉጥ በመሆናቸውም የዘመኑ አበው 'ዳግማዊ እስጢፋኖስ' እያሉ ይጠሯቸው ነበር::
+ከዚያ በወጣትነት እድሜአቸው ምናኔን መርጠው: ጾምና ጸሎትን ከስግደት ጋር አዘወተሩ:: እንዲህ ባለ ሕይወት ሳሉ አንድ ቀን ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ዘንድ መጣ::
+በዘባነ ኪሩብ: በግርማው ቢያዩት ደነገጡ:: ጌታ ግን "ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ! ገና ከእናትህ ማሕጸን መርጬሃለሁ:: ከኢትዮዽያ እስከ አርማንያም ሐዋርያ ትሆን ዘንድ ሹሜሃለሁ:: 'ዘኪያከ ሰምዐ: ኪያየ ሰምዐ . . . አንተን የሰማ እኔን ሰማ: አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ አለ" ብሏቸው ባርኩዋቸው ዐረገ::
+ጻድቁ ፈጣሪያቸውን ስለ ስጦታው እያመሰገኑ ቅስናን ተቀብለው ስብከትን ጀመሩ:: ስም አጠራራቸውም ፈጥኖ በሃገሪቱ ተሰማ:: በየቦታው እየዞሩ ያላመነውን አሳምነው እያጠመቁ: ያመነውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እያጸኑ: ሕይወተ ገዳምን እያስፋፉ ኖሩ::
+አሁን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘውንና እርሳቸው የመሠረቱትን ገዳም ጨምሮ ለገዳማዊ ሕይወት መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርገዋል:: በገዳማቸውም አባ አብሳዲን ጨምሮ በርካታ አርድእትን አስተምረዋል: አፍርተዋል::
+አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በተለይ የሚታወቁት #ቀዳሚት_ሰንበት እንዳትናቅ (እንድትከበር) ባደረጉት ጥረት ነው:: ደግሞም ተሳክቶላቸዋል:: ቅርብ ጊዜ ከምናየው የድፍረት ሥራ በቀር በሃገራችን 2ቱም ሰንበቶች ክቡር ናቸው::
+አቡነ ኤዎስጣቴዎስ 2 ጊዜ በእግራቸው ተጉዘዋል:: መሔዳቸው ግን ለመሳለም ብቻ አይደለም:: ይልቁኑ የወንጌል ዘርን እየዘሩ: ፍሬውንም እየለቀሙ እንጂ:: እርሳቸው መቼም ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ቸል አይሉምና::
+በመጨረሻ ሕይወታቸውም በገዳማቸው ላይ ደቀ መዝሙራቸውን አባ አብሳዲን ሹመው ለአዲስ ጉዞ ተነሱ:: እኩሎች ልጆቻቸውን በገዳማቸው ትተው እኩሎችን አስከትለው ጉዞ ወደ አርማንያ ተደረገ::
+በመንገድም ወደ ባሕረ #ኢያሪኮ ሲደርሱ የሚሻገሩበት መርከብ አጡ:: ድንቅ አባት ናቸውና በእምነት አጽፋቸውን (ኩታቸውን) አውልቀው ባሕሩ ላይ ጣሉት:: በላዩ ላይም በትእምርተ መስቀል አማትበው ተቀመጡበት::
+ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ባሕሩ ላይ በተነጠፈው ኩታ ላይ ከበው ተቀመጡ:: ከሰማይም ጌታችን ወርዶ በመካከላቸው ቆመ:: #ሚካኤል በቀኝ #ገብርኤልም በግራ ቆሙ:: ጻድቁ ደግሞ ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው: ይተረጉሙላቸው ገቡ::
+በመካከል ግን አንዱ (የማነ ብርሃን ይሉታል በቅኔ ቤት) በመጠራጠሩ እርሱ የተቀመጠባት ብቻ ተቀዳ ሰጠመ:: በሁዋላ ግን ጻድቁ ተመልሰው አውጥተው: ከሞት አስነስተውታል:: በዚህም ምክንያት 'ዘአደወ ባሕረ-ማዕበልን የተሻገረ' ይባላሉ::
+አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአርማንያ ለዘመናት ሰብከው: ሕይወተ ገዳምን አስፋፍተው: ብዙ ተአምራትን ሠርተው: በተወለዱ በ80 ዓመታቸው: በ1345 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: በብዙ ዝማሬ በመቅደሰ #መርምሕናም ተቀብረዋል:: ዛሬ #በኢትዮዽያ: #ኤርትራ: #ግብጽና #አርማንያ ይከብራሉ::
† 🕊 አቡነ_አኖሬዎስ_ጻድቅ 🕊 †
=>እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ 'ታላቁ አኖሬዎስ' ይባላሉ:: በዚህ ስም ከሚጠሩ አባቶች ዋነኛው እኒህ ናቸው:: ተወልደው ያደጉት #ሙገር አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 14ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::ወላጆቻቸውም #ሰላማ እና #ክርስቶስ_ዘመዳ ይባላሉ::
+ጻድቁ ከአቡነ #ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዛሙርት አንዱ ናቸው:: በወንጌል ትምህርት ከመሞላታቸው ባሻገር ፍጹም መናኝ ስለ ነበሩ እጅግ ደፋር ነበሩ:: የትኛውንም ስሕተት ፊት ለፊት ይናገሩም ነበር::
+አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲያርፉ ጌታ "በአንተ ፈንታ አኖሬዎስ ቀሪ ጣዖት አምልኮን ያጠፋል" ብሎ ነግሯቸው ነበር:: ይኸውም አልቀረ ጻድቁ ከ12ቱ ንቡራነ እድ እንደ አንዱ በተመረጡ ጊዜ በደቡቡ የሃገራችን አካባቢ ክርስትናን አስፋፍተዋል::
+#ደብረ_ጽጋጋ ገዳምንም የመሠረቱ እርሳቸው ናቸው:: ዛሬ '#ኑራ_ሑሴን' እየተባለ ታሪኩ ጠልሽቶ የሚነገርለት ዋሻ የጻድቁ በዓት ነው:: አቡነ አኖሬዎስ 2ቱን ነገሥታት (#ዓምደ_ጽዮንንና #ሰይፈ_አርእድን) በመገሰጻቸው ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል:: ጻድቁ ብዙ ፍሬ አፍርተው በዚህ ቀን ዐርፈዋል::
† 🕊 ማር_ያዕቆብ_ግብጻዊ 🕊 †
=>በግብጽ ገዳማት ውስጥ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተነስተው ካበሩ ቅዱሳን አንዱ ማር ያዕቆብ ነው:: ቅዱሱ ከተባረከ ቤተሰብ ተወልዶ: በሥርዓቱ አድጐ ገና በልጅነቱ ከመምህሩ ጋር መንኗል:: ከገድሉ ጽናት የተነሳ ሰይጣን በግልጽ ይፈታተነው ነበር::
+በተለይ ለ7 ዓመታት ያህል ይደበድበው መሬት ላይ ይጐትተው በጥፊ ይመታው ነበር:: እርሱ ግን በጸሎቱ መብረቅ አውርዶ አባርሮታል:: በበርሃው ምንም የሚበላ ነገር ባለ መኖሩ የዱር እንስሳትን ወተት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይጠጣ ነበር::
+ቅዱሱ ሰማዕት ለመሆን ሞክሮም ነበር:: ማር ያዕቆብ ገድሉና ተአምራቱ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ስሙ ከፍ ከፍ ብሏል:: እስኪ ጊዜውና እድሉ ካለዎት #መጽሐፈ_ስንክሳር ላይ የተጻፈውን ገድሉን እንዲያነቡ ልጋብዝዎት:: ጻድቁ ያረፈው በዚሁ ዕለት ነው::
=>አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹ ካሉበት ጉባኤ እንደ ምሕረቱ ታላቅነት ያድርሰን:: በረከታቸውንም ይሙላልን::
=>መስከረም 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን
2.አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ
3.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
4.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
5.ቅድስት እሌኒ ንግሠት
6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ መርቆሬዎስ ካልዕ (ሰማዕት)
8.ቅዱስ ቶማስ ሰማዕት
9.ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕት
10.አባ ፊልሞስ
11.ቅዱስ ሰልሖን ሰማዕት
12.ቅዱስ አክሳኤልስ ሰማዕት
13.ቅዱስ ይስሐቅ ሰማዕት
14.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀሲስ
15.ቅዱስ ነኪጣ ሰማዕት
16.አባ ፊላታውዎስ መንክራዊ
17.አባ ኖብ ባሕታዊ
18.አባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
19."60" ሰማዕታት (ማሕበረ ቅዱስ አቦሊ)
=>ወርሐዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም #ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም . . . መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: + (ማቴ. 5፥13-16)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

🌼የንህበት ቅድስት ጸበለ ማርያም ቤተ ክርስቲያን!
መስከረም 18 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓሏ ታስባ የምትውለው ቅድስት ጸበለ ማርያም በጎኗ ተኝታ የማታውቅ፣ በጌታችን 40 ጾም ወራት ከሰንበት በቀር ምንም የማትቀምስ፣ ነብሮች የእግሯን ትቢያ ይልሱላት የነበረች ታላቅ ኢትዮጵያዊት ቅድስት ናት። ቅድስት ጸበለ ማርያም ጌታችን በደሃ ሰው ተመስሎ ተገልጦ ቁራሽ እንጀራ የለመናት በኃላም በጀርባዋ አዝላ የሸኘችው ታላቅ እናት ናት። እርሷም ከነቢያት፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ዕድል የተሰጣት እናት ናት፡፡ ከደናግል መነኮሳትም ዕድል ተሰጣት-መነኩሲትም ድንግልም ናትና።
ቅድስት ጸበለ ማርያም ትውልዷ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ቀሐ አካባቢ ነው፡፡ ወላጆቿ አባቷ እንድርያስና እናቷ መስቀል ክብራ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጓት፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተከስተ ብርሃን የተባለ ደገኛ ባሕታዊ ወደ አባቷ ቤት መጥቶ ባደረበት መንፈስ ቅዱስ ኀይል የቅድስት ጸበለ ማርያምን ጸጋ አወቀ፡፡
ለወላጆቿም ‹‹ይኽቺ ልጅ ወደፊት ነፍሳት የሚድኑባት የከበረች ትሆናለች›› ብሎ በእርሷ ላይ ትንቢት ተናገረ፡፡
ቅድስት ጸበለ ማርያም ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወላጆቿ በጋብቻ ሕግ እንድትወሰን ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ቅድስት ጸበለ ማርያም ‹‹ቅዱስ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር አጭቶኛልና ፈጣሪዬን በድንግልና ለማገልገል ተስያለሁ›› በማለት ተቃወመቻቸው፡፡ ወደ አንድ ደገኛ ባሕታዊም ዘንድ ሄዳ በጸሎቱ ከዚህ ነገር እንዲያድናት ተማጸነችው፡፡ እርሱም ፈቃደ እግዚአብሔርን በጸሎት ከጠየቀላት በኋላ ማድረግ የሚገባትንና ወደፊት የሚገጥማትን ሁሉ ነገራት፡፡ እርሷም ለዕጣን እንዲሆን ጌጧን ሁሉ አውጥታ ሸጠችና ‹‹መሥዋዕቴን አሳርግልኝ›› ብላ ለባሕታዊው ሰጠችው፡፡ እርሱም ከጸለየላት በኋላ የጸሎቱን ምላሽ ነገራት፡፡
ወላጆቿም ያለፈቃዷ በሕግ ቢያጋቧትም ቅድስት ጸበለ ማርያም ግን በሌሊት ማንም ሳያያት ከጫጉላ ቤት ወጥታ ሄዳ በልዳው ፀሐይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ወደተሠራች ቤ/ክ ሄዳ እያለቀሰች ጸሎት አደረገች፡፡ እመቤታችንም ከሚካኤል ወገብርኤል እንዲሁም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተገለጠችላትና እንዲጠብቋት ነገረቻቸው፡፡ ቤተሰቦቿም እንዳያዝኑባት ፈርታ ተመልሳ ወደ ባሏ ዘንድ ብትገባም ባሏ በግብር እንዳያውቃት መላእክቱ ይጠብቋት ነበር፡፡ ባሏንም ሰውነቷ እንደእሳት ያቃጥለው ነበር፡፡ እርሱም አእምሮውን ከሳተ ከ3 ቀን በኋላ ሲነቃ የደረሰበትን ለቤተዘመዶቹ ባስረዳቸው ጊዜ ‹‹ከገዳም የመጣች ከሆነች ለእኛ ልትሆን አይገባም›› አሉና አስጊጠውና ሸልመው መልሰው ወደ ቤተሰቦቿ ላኳት፡፡
አባቷም ዳግመኛ ወደባሏ እንድትመለስ በማስገደድ ብዙ አሰቃቂ ግርፋት ቢገርፋትም በተአምራት ምንም እንዳላገኛት ሆነች፡፡ ከዚኽም በኋላ ወጥታ ወደ ምድረ በዳ ሄደች፡፡ ወደ ገዳምም ሄዳ ዋሻ ውስጥ ገብታ ስትጸልይ አድራ አረፍ ስትል ነብር መጥቶ የእግሯን ትቢያ ይልሳት ነበር፡፡ ከዚያም ወጥታ ንህበት ወደሚባል ሀገር መጥታ ቶማስ ከሚባል መነኩሴ ጋር በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ ቆማ ስትጸልይ እንባዋ መሬቱን ያርስ ነበር ነገር ግን ሰው እንዳያውቅባት አፈር በላዩ ትጨምርበታለች፡፡ በአንድ ዕለትም በቤ/ክ ቆማ ስትጸልይ በሁለቱ ማዕዘን የተቀበሩ ምውታን ሲጮኹ ሰማቻቸው፣ እነርሱ ግን በሲኦል ነበሩ፡፡ ጩኸታቸውንም በሰማች ጊዜ በእንባዋ ላይ እንባን በጸሎቷም ላይ ጸሎትን ጨምራ ስለእነርሱ ለመነች፡፡ ስለእነርሱም ሱባኤ ያዘች፡፡ በባሕርይው ቸርና ይቅርባይ የሆነ ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ እነዚያን ነፍሳት ማረላት፡፡
ቅድስት ጸበለ ማርያም በምግባርና በትሩፋት በጾም በጸሎት ጸንታ ከኖረች በኋላ የምንኩስና ቀንበርን ትሸከም (በምናኔ ትኖር) ዘንድ በብሕትውና ወደሚኖረው ታላቁ አባት ወደ አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ ዘንድ ሄደች፡፡ እርሱም ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር የደረሰው ነው፡፡
አቡነ ገብረ ማርያምም ካስተማራትና በኋላ አመነኮሳትና ስሟን ‹‹ጸበለ ማርያም›› ብሎ ሰየማት፡፡ ከዚኽም በኋላ ተጋድሎዋን እጅግ በማብዛት ትሕርምትን ገንዘብ አደረገች፡፡ ከዕንጨት ፍሬዎች ውጭ የማትመገብ ሆነች፡፡ በተቀደሰችው የጌታችን 40 ጾም ወራት ግን ከሰንበት በቀር እርሱንም ፈጽሞ አትቀምስም፣ እስከ ፋሲካም ድረስ ከበዓቷ ስለማትወጣ ማንም አያያትም ነበር፡፡ ከመነኮሰችም ጊዜ ጀምሮ በጎኗ ተኝታ አታውቅም፡፡ ባመማት ጊዜም ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፡፡ በውርጭ ቅዝቃዜ መከራን እየተቀበለች በባሕር ውስጥም ቆማ እየጸለየች ታድራለች፡፡ በስግደቷም በቀን እስከ 8 እልፍ ትሰግድ ነበር፡፡ ከወንድሟ ቶማስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ተማረች፡፡ የዮሐንስን ወንጌልና የራእዩን መጽሐፍ ዘወትር በማንበብ ትጸልያለች፡፡ የእመቤታችን በዓል በሆነ ጊዜ አርጋኖን ውዳሴዋን በቀን ሦስት ጊዜ ታነባለች፣ አንቀጸ ብርሃንንም በየሰባቱ ጊዜ ትጸልያለች፡፡ የዳዊትንም መዝሙር በፈጸመች ጊዜ የጌታችንን መከራ ግርፋት እያሰበች ራሷን ሺህ ጊዜ ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም አገዛዛቸው መልካም ይሆን ዘንድ ስለ ጳጳሱና ስለ ንጉሡ አንድ አንድ ሺህ ጊዜ፣ ስለ መነኮሳትም ሺህ ጊዜ፣ ስለኃጥአንም ሺህ ጊዜ ራሷን ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም ነጭ ዕጣን በእጇ ይዛ ሰባት ቀን እስኪሆን ድረስ ዕንባዋን ታፈስበታለች፣ ያም ነጭ ዕጣን ከዕንባዋ ብዛት የተነሣ ጥቁር ይሆናል፡፡ በዓል በሚሆንበት በሰባተኛው ቀን አስቀድማ ዐውቃ በመሠዊያ ያሳርገው ዘንድ ያን ዕጣን ለቄሱ ትሰጠዋለች፡፡ እግዚአብሔርም እንደሱራፌል የጽናሕ መዐዛና እንደኪሩቤል ዕጣን ሽታ አድርጎ ከቄሱ እጅ ሲቀበል በግልጽ ታያለች፡፡
ቅድስት እናታችን እሾህ ያለው የብረት ዛንዠር በወገቧ ትታጠቃለች፡፡ በወገቧና በጭኖቿ ያሰረችው ርጥብ የላም ቁርበት ከአጥንቶቿ ጋር ይጣበቃል፡፡ በደረቀም ጊዜ ሥጋዋ እየተቆራረጠ ይወድቃል፣ በምድርም ውስጥ ትቀብረዋለች፡፡ አምስት ጊዜም እንደዚህ እያደረገች ራሷን ጎዳች፣ ከዳነም መልሳ ታቆስለዋለች፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገለጠላትና ‹‹ወዳጄ ጸበለ ማርያም ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእንዲህ ያለ የቁስል መከራ መሠቃየት ይበቃሻል›› ካላት በኋላ ተሰወረ፡፡ እርሷ ግን ሰባት ጊዜ እስኪሆናት ድረስ ይህንን አደረገች፡፡ በዚህም ጊዜ ሥጋዋ እጅግ ታመመ፡፡ ሥጋዋ እንደ ድንጋይ ደርቆ ቢቀር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደተላለፈች ዐውቃ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ተወች፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅድስት ጸበለ ማርያም እየጸለየች ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቆሰለ ችግረኛ ደሃ ሰው ተመስሎ ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተገልጦ ወደ እርሷ በመምጣት ቁራሽ እንጀራ ለመናት፡፡ እርሷም ፈጥና ይዛ መጥታ ሰጠችው። እንጀራውንም ተቀብሎ ሲያበቃ ‹‹በመንገድ ብዛት ደክሜአለሁና በጀርባሽ አዝለሽ ትሸኚኝ ዘንድ እወዳለሁ›› አላት፡፡ እርሷም ለድሆች አዛኝ ናትና አዝላው የድንጋይ መወርወሪያ ያህል እንደወሰደችው ቁስሉ ይድን ጀመር፡፡ ወዲያውም ቁስሉ ድኖ ምንም እንዳላገኘው ፍጹም ደህነኛ ሰው ሆነ፡፡ ያንጊዜም ፊቱ እንደፀሐይ አበራ፣ ሁለንተናውም ተለወጠ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ከጀርባዋ ወርዶ በፊት ለፊቷ ቆመና ‹‹የከበርሽ አገልጋዬ ጸበለ ማርያም ሆይ! ምን እንዳደርግልሽ ትወጃለሽ?›› አላት፡፡ እርሷም ከድንጋጤዋ የተነሣ እንደበድን ሆና መሬት ላይ ወደቀች፡፡ ጌታችንም አበረታትና እጇን ይዞ አነሣትና ‹‹የልብሽን መሻት ለምኚኝ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላኬ ሆይ

! በፊትህስ ሞገስ ካገኘሁ በሲኦል ያሉ ነፍሳትን ይቅር በላቸው›› አለችው፡፡ በዚኽም ምክንያት በጌታችን ቸርነትና በእርሷም አማላጅነት ብዙ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቷት በክብር ዐረገ፡፡
ዳግመኛም ጌታችን ለቅድስት ጸበለ ማርያም ሦስት በትሮችን ሰጥቷት በእነርሱ እየተመረኮዘች እስከሲኦል ድረስ ትሄድና ነፍሳትን ታወጣና ታስምር እንደነበር ራሷ ተናገረች፡፡ ዳግመኛም ስትናገር ‹‹ሰማያውያን ብዙ ስሞች አወጡልኝ፣ ‹የወይን ፍሬ› እያሉ ይጠሩኛል፣ ‹የበረከት ፍሬ› የሚሉኝም አሉ፣ ‹የገነት ፍሬም› ይሉኛል›› አለች፡፡ ዳግመኛም ከልዑል ዘንድ ብዙ ጸጋዎች እንደተሰጣት በሕይወት ሳለች ለአንድ ደገኛ ቄስ ነገረችው፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አምላክን በድንግልና የወለደች ክብርት እመቤታችን ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተገለጠችላትና ‹‹ስሜን የተሸከምሽ ጸበለ ማርያም ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን›› አለቻት፡፡ እመቤታችንም ብዙ ምሥጢርን ከነገረቻት በኋላ ጡቶቿንም አጠባቻትና በጸጋ የከበረች አደረገቻት፡፡ በስሟም ብዙ ተአምራትን የምታደርግ ሆነች፡፡
ቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም ከነቢያት፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ዕድል የተሰጣት እናት ናት፡፡ እንደነቢያት የሚመጣውን ሁሉ እንዳለፈ አድርጋ ትናገራለች፡፡ ዳግመኛም የትምህርታቸውን ፍለጋ ስለተከተለችና ለሕጋቸው ስለተገዛች ከሐዋርያት ጋር ዕድል ተሰጣት፡፡ ሦስተኛ ግድ ሳይሏት በፈቃዷ ስለተቀበለቻቸው ግርፋቶቿና ስላገኛት መከራ የሰማዕታት ዕድል ተሰጣት፡፡ ከደናግል መነኮሳትም ዕድል ተሰጣት-መነኩሲትም ድንግልም ናትና፡፡ ቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም መልካም የሆነውን ተጋድሎዋን ከፈጸመችና ጌታችን ታላቅ ቃልኪዳን ከገባላት በኋላ በሰላም ዐርፋለች፡፡ እንደ ንግሥት ዕሌኒም የሞቷን መስቀል ተሸክማ ተጠብቆላት ወዳለ ተስፋዋ በክብር ሄደች፡፡ ዕረፍቷ መስከረም 18 ነው፡፡ ጥር 18ም ዓመታዊ በዓሏ ነው።
✞ ✞ ✞
የቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን!
(ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ጸበለ ማርያም፣ ደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት የንህበት ቅድስት ጸበለ ማርያም ቤ/ክ ያሳተመው፡፡
የገዳሙን ፎቶ የላከልን "የሰሚ በዕለቱ ወይን ዓምባ ቅዱስ ገብርኤል page" እናመሰግናለን።)
ምንጭ። በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን /ገብረ ሥላሴ/

"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"
#ቅዱስ_ፓሲዮስ
#ቅዱስ_ፓሲዮስ
https://t.me/zekidanemeheret
🕐 መስከረም 19/01/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፫፥፲፯(43፥17)
ወኢዐመፅነ ኪዳነከ
ወኢገብአ ድኅሬሁ ልብነ
ወኢተግኅሠ አሠርነ እምፍኖትከ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፰፥፴፬-፴፰(8፥34-38)
ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስለ አርዳኢሁ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ኤፌሶን ፪፥፲፫-፳፪(2፥13-22)
ወይእዜሰ ባሕቱ አንትሙ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፩-፭(5፥1-5)
ወለእለኒ ይትለሐቁ እምኔክሙ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፥፱-፳፬(10፥9-24)
ወበሳኒታ እንዘ የሐውሩ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ተመየጥከኒ ወአሕየውከኒ
ወእምቀላየ ምድር አውፃእከኒ
ወአብዛኅኮ ለጽድቅከ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፸ ቊ. ፳ - ፳፩
፳ ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና፥ ተመልሰህም ሕያው አደረግኸኝ፤ ከምድር ጥልቅም እንደገና አወጣኸኝ።
፳፩ ጽድቅህንም አበዛኸው። ደስ ታሰኘኝም ዘንድ ተመለስህ። ከምድር ጥልቅም እንደ ገና አወጣኸኝ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፪ ቊ. ፱ - ፳፪
ወፈሊሶ እምህየ ሖረ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🕐 መስከረም 19/01/2016 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፫፥፲፯(43፥17)
ወኢዐመፅነ ኪዳነከ
ወኢገብአ ድኅሬሁ ልብነ
ወኢተግኅሠ አሠርነ እምፍኖትከ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፰፥፴፬-፴፰(8፥34-38)
ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስለ አርዳኢሁ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ኤፌሶን ፪፥፲፫-፳፪(2፥13-22)
ወይእዜሰ ባሕቱ አንትሙ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፩-፭(5፥1-5)
ወለእለኒ ይትለሐቁ እምኔክሙ…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፥፱-፳፬(10፥9-24)
ወበሳኒታ እንዘ የሐውሩ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ተመየጥከኒ ወአሕየውከኒ
ወእምቀላየ ምድር አውፃእከኒ
ወአብዛኅኮ ለጽድቅከ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፸ ቊ. ፳ - ፳፩
፳ ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና፥ ተመልሰህም ሕያው አደረግኸኝ፤ ከምድር ጥልቅም እንደገና አወጣኸኝ።
፳፩ ጽድቅህንም አበዛኸው። ደስ ታሰኘኝም ዘንድ ተመለስህ። ከምድር ጥልቅም እንደ ገና አወጣኸኝ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፪ ቊ. ፱ - ፳፪
ወፈሊሶ እምህየ ሖረ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞✞✞
✞✞✞ መስከረም 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
† 🕊 ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ 🕊 †
✞✞✞ ይህ ቅዱስ አባት ከሰማዕታት: ከጻድቃን: ከሊቃውንትና ከዻዻሳት ዝርዝር
ውስጥ ይገኛል:: በቤተ ክርስቲያንም ዓበይት ከሚባሉ አበው አንዱ ነው:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሮማዊ ሲሆን ከክርስቲያን
ወላጆቹ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ
ክ/ዘመን) ነው::
+አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት
አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት
እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች
ነበሩበት:-
1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
2.ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::
+ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ
መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት
አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከ በመልኳ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ
ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::
+ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው::
በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ
ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ በጸሎት ድንግሏን
አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ
ተሰደደ::
+በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት
ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ
የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ
ለመውጣት ተገደደ::
+በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት
ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን
ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::
+ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ
ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::
+አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ
በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ
አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ
ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
+ወዲያው ደግሞ የቅዱስ ጐርጐርዮስ ማንነቱ በመታወቁ ይዘው
እስኪያልቅ ገረፉት:: በእሳትም አቃጠሉት:: በብዙ ስቃይም አሰቃዩት::
+በመጨረሻ ግን ከነ ሕይወቱ እንዲቀበር ተወሰነበት:: ወደ መጸዳጃ ቤት
ወስደውም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት:: ነገር ግን
የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ መተንፈሻ ቀዳዳን ሠራለት:: አንዲት
ክርስቲያንም በዚያች ቀዳዳ ቂጣ እየጣለችለት ለ15
ዓመታት ተቀብሮ ኖረ::
+አካሉና አፈሩ ተጣበቀ:: እርሱ ግን ፈጣሪውን እያመሰገነ ቆየ:: ከዚህ ሁሉ በኋላ ድርጣድስና
ባለሟሎቹ ለአደን
በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው::
+የንጉሡ እንስሳ /አውሬ መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ::
እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ
ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን-ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት
አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም በዚያች መሪነት ቆፍረው አወጡት::
+አካሉንም እግዚአብሔር መለሰለት:: ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም::
ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን
የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው::
ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::
+ወደ ሰውነትም መልሶ መላ አርማንያን ወደ ክርስትና መለሰ:: የንጉሡን እግር ግን የአውሬ አድርጐት ቀርቷል:: በመጨረሻም
ቅዱስ ጐርጐርዮስ የአርማንያ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሹሞ ብዙ መጻሕፍትን
ደረሰ:: ከ318ቱ ሊቃውንትም አንዱ ሆኖ ተቆጠረ::
ዕረፍቱ ታኅሣስ 15 ቀን ሲሆን ዛሬ ከተቀበረበት የወጣበት ነው::
† 🕊 ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ 🕊 †
+ቅዱሱ የ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቅ ሲሆን በዓለም ከመናፍቃን: በገዳም
ደግሞ ከአጋንንት ብዙ መከራን ተቀብሏል:: በወቅቱ
መለካውያን (የአሁኖቹ ካቶሊኮችና ምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) አባቶችን
ያሳድዱ ነበር:: ልክ 9ኙ ቅዱሳን በዚህ
ምክንያት ወደ ኢትዮዽያ እንደመጡት ቅዱስ ቂርቆስም ወደ ግብጽ በርሃ ከእርሷ ተሰደደ::
+በበርሃው ውሃም ሆነ ዛፍ ባለመኖሩ በረሃብና በጥም በመሰቃየቱ ወደ ፈጣሪ
ለመነ:: ጌታም አንዲት አጋዘን ልኮለት
ወተትን አልቦ ጠጣ:: እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም ምግቡ ይሔው የአጋዘን ወተት
ነበር:: በዚህ ምክንያት ይሔው ዛሬም ድረስ "ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ ዘሲሳዩ ሐሊበ ቶራ" እየተባለ ይጠራል::
+በበርሃው ውስጥ በኖረባቸው ዘመናትም አንድም ሰው አይቶ ካለማወቁ
ባለፈ አጋንንት በገሃድ እየመጡ ያሰቃዩት ነበር::
ቅዱሱ ግን በትእግስት ኑሮ በዚህች ቀን ሲያርፍ ብዙ ተአምራት በበዓቱ
ውስጥ ተገልጠዋል:: ይህንን ያዩት ደግሞ ከዻዻሱ
ዘንድ ተልከው የቀበሩት አበው ናቸው::
† 🕊 ቅድስት ሮማነ ወርቅ 🕊 †
+ይህቺ ቅድስት እናት ደግሞ ኢትዮዽያዊት ናት:: የነገሥታቱ ልጅ አባቷ
አፄ ናዖድ: እናቷ ደግሞ እሌኒ /ወለተ
ማርያም ይባላሉ:: ወንድሟ ደግሞ አፄ ልብነ ድንግል ይባላሉ::
+በቤተ መንግሥት ውስጥ ብታድግም መንፈሳዊነቷ የገዳም ያህል ነበር::
ከተባረከ ትዳሯም ቅዱስ ላዕከ ማርያምን አፍርታለች::
አብያተ ክርስቲያናትን ከማነጽ ባለፈ የነዳያን እናትም ነበረች:: በክርስትናዋ
ፈጣሪዋን ደስ አሰኝታ በዚህ ቀን ዐርፋለች::
✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን: ክብሩን አይንሳን:: ከወዳጆቹ በረከትም እንደ ቸርነቱ ያድለን::
✞✞✞ መስከረም 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
2.ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ
3.ቅድስት ሮማነ ወርቅ
4.ቅዱስ ዕጸ መስቀል
"+ ጻድቃን ጮሁ: እግዚአብሔርም ሰማቸው::
ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው::
እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው::
መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል::
የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው::
እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል::
እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል:: +" (መዝ. 33፥17)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ]
💚💛❤@sinkisar_gisawe_z_tewahedo
💚💛❤
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ