ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
836 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
👉 ትምክህተ ዘመድነ እንተ ይእቲ እግዝእትነ ማርያም 👉
ትርጓሜውም
✥ የባህርያችን መመኪያ እመቤታችን ማርያም ናት ✥
    ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🙏 እንኳን ለፃድቅ ንጉሥ ሕዝቅያስ ዓመታዊ በዓለ እረፍት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረስን 🙏

👉 ነሀሴ ፬(4) ሕዝቅያስ ንጉሥ ወፊልጶስ ወአኃዊሁ ወማቴዎስ 👉

👉 ዘነግህ ምስባክ 👉

ይስማዕከ እግዚአብሔር በዕለተ ምንዳቤከ
ወይቁም ለከ ስሙ ለአምላክ ያዕቆብ
ወይፈኑ ለከ ረድኤተ እመቅደሱ

❖ ትርጉም ❖

በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ
የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ
ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ

     መዝ ፲፱-፩
            19  1

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፩ ቁ ፱-፲፪
           1     9   12

የቅዳሴ ምንባባት

ሮሜ ም ፲፪ ቁ ፲፮-ፍ.ም
፩ ጴጥ ም ፭ ቁ ፮-፲፪
ግብ.ሐዋ ም ፲፯ ቁ ፳፫-፳፰

✥ ምስባክ ✥

እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ

🙏 ትርጉም 🙏

አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል
በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው

     መዝ ፳-፩
           20  1

✥ ወንጌል ✥

ሉቃ ም ፲፬ ቁ ፴፩-ፍ.ም
           14    31   ፍፃሜው

✥ ቅዳሴ ✥

ዘእግዝእትነ

" ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኀብስት በማመን ከርሱ ለሚቀበሉ ህይወትንና ደኅንነትን የሚሰጥ ነው "
      ቅዳሴ ማርያም
          ም ፩ ቁ ፺፩
              1     91

ፆሙን ፆመ ድኀነት ፆመ በረከት ያድርግልን ፆሙ ለማበርከት ያብቃን አምላክ ቅዱሳን ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ በምህረቱ ይማርን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ በቃል ኪዳኗ ትጠብቅን ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዱስ ያሬድ ማኀሌት ዓይን ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለአባ ህርያቆስ ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ለቅዱስ ቄርሎስ ዓምድ ሃይማኖት ለቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢ ለቅዱስ አትናቴዎስ ለአባ  አርክሡሉስ ለአባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት ለአባ ጽጌድንግል ለቅዱስ ደቅስዮስ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ለአቡነ ሃብተማርያም ለአቡነ ገብረመንፈስቅዱስ ለአባ ይስሐቅ ለቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ለአፄ ዳዊት የተለመነች በምህረት ትለመነን ሱባዔ ነቢያት ወሐዋርያት የተቀበለች የኛንም ሱባዔ በምህረት በድኅነት ትቀበልልን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
"የሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ነሐሴ 4/12/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፲፱፥፩(19፥1)
ይስማዕከ እግዚአብሔር በዕለተ ምንዳቤከ
ወይቁም ለከ ስሙ ለአምላከ ያዕቆብ
ወይፈኑ ለከ ረድኤተ እመቅደሱ…


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፩፥፱-፲፪(1፥9-12)
ወዖዝያንኒ ወለደ ኢዮአታምሃ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፲፪፥፲፮-፳፩(12፥16-21)
ወከመዝ ሐልዩ ምስለ ቢጽክሙ…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፮-፲፪(5፥6-12)
አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፯፥፳፫-፳፰(17፥23-28)
ወበጺሕየ ዝየ ርኢኩ ጣዖትክሙ…



            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ


               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፳ ቊ. ፩ - ፪

፩ አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።

፪ የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፬ ቊ. ፴፩ - ፴፭
ወእመኒ ፈቀደ ንጉሥ ይሑር ይጽብኦ...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ አው ዘቄርሎስ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ነሐሴ 5/12/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፷፰፥፲፰(68፥18)
ወአንሰ በጸሎትየ ኀበ እግዚአብሔር
ሣህሉ ለእግዚአብሔር በጊዜሁ
እንዘ ብዙኅ ሣህልከ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፮፥፭-፲፮(6፥5-16)
ወሶበሂ ትጼልዩ ኢትኩኑ ከመ መደልዋን…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፪ ም ፲፪፥፲-፲፯(12፥10-17)
ወበእንተ ዝንቱ ሠመርኩ በሕማምየ…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፭፥፲፬-፳፩(5፥14-21)
ወዛቲ ይእቲ እንተ ብነ ገጽ በኀቤሁ…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፭፥፩-፲፫(15፥1-13)
ወቦ እለ ወረዱ እምብሔረ ይሁዳ…


            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ
ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ


               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፲፯ ቊ. ፵፫ - ፵፬

፵፫ ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።

፵፬ በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤ የባዕድ ልጆች ደለሉኝ።



            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፭ ቊ. ፩ - ፲፩
ወሀለዉ ይቀርብዎ መጸብሐውያን...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
††† እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን #አባ_አብርሃም: #ቅዱስ_ዮሐንስ እና #አባ_ፊልዾስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† #አባ_አብርሃም_ክቡር ገዳማዊ †††

=>ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው::

+ሰርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ::

+በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ:: በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው::

+አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ::

+ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው:: ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው::

+ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ ውጪም ጣሉት::

+እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት::

+ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት::

+የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም ለመኑት::

+ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም #በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ (#ስብሐት_ብጡል) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ::

+እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ::

+ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ:: በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ:: ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች::

+በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ::

+ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት:: ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ::

+በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ ኑሯል::

+በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::

††† #ቅዱስ_ዮሐንስ_ጻድቅ †††

=>ይህ ቅዱስ የነበረው በዘመነ ሰማዕታት ቢሆንም እንደ ሰማዕታት ስቃይ አልደረሰበትም:: ክርስቲያኖችን እንዲገድሉና አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያቃጥሉ ከተመደቡ ወታደሮች አንዱ ነበረ:: ታዲያ እንዲገድላቸው የሚሰጡትን ክርስቲያኖች እየወሰደ ይደብቃቸው ነበር::

+የመከራው ዘመን እስኪያልፍ ድረስም ይንከባከባቸው ነበር:: ሌሎች ወታደሮች እንዳይነቁበት ሁሌም "ክርስቲያኖችን በጣም እጠላለሁ" እያለ ያወራ ነበር:: እርሱ በሌሊት ሁሌም ለጸሎት ይተጋ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ኑሮም በዚህች ቀን በሰላም ዐርፏል::

††† #አባ_ፊልዾስ #ዘደብረ_ቢዘን †††

=>#ደብረ_ቢዘን በቀድሞ የኢትዮዽያ ክፍለ ሃገር (አሁን #ኤርትራ) ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ገዳም ነው:: ገዳሙ #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም በስደቷ ያረፈችበት: ጌታችን የባረከውና የመረጠው ቦታ ነው:: #አባ_ዮሐንስን: #አባ_ናርዶስንና ሌሎች ከዋክብት አበውን ያፈራ ሲሆን የአባ ፊልዾስን ያሕል ግን አልተገኘም::

+ጻድቁ በግል የተጋድሎ ሕይወታቸው: ገዳሙን በአበ ምኔትነት በመምራታቸውና በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ምስጉን ነበሩ:: እርሳቸው ቅዱስ ሆነው አልበቃቸውምና ብዙ ቅዱሳንን ወልደዋል:: ይሕች ዕለትም የዕረፍታቸው መታሰቢያ ናት::

=>አምላከ ጻድቃን ገዳማትን ከመከራ ይጠብቅልን:: ከአባቶቻችን ቅዱሳን ጸጋ በረከትንም ይክፈለን::

=>ነሐሴ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ አብርሃም ገዳማዊ
2.ቅድስት ማርያ እህቱ
3.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ
4.አባ ፊልዾስ ዘደብረ ቢዘን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)

=>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ. . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ 11:23)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"የአርብ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የአርብ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ነሐሴ 6/12/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፯፥፲፩(47፥11)
ይትፌሥሓ አድባረ ጽዮን
ወይትሐሠያ አዋልደ ይሁዳ
በእንተ ፍትሕከ እግዚኦ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፳፥፲፩-፲፱(20፥11-19)
ወማርያምሰ ቆመት…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ም ፫፥፲-፳፪(3፥10-22)
ወበከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፫፥፩-፯(3፥1-7)
ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፲፫-፲፱(16፥13-19)
ወወፃዕነ በዕለተ ሰንበት እምአንቀጸ ሀገር…


            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ
ብዑላነ ምድር
ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን


               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፲፪ - ፲፫

፲፪ የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ።

፲፫ ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤ ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማርቆስ ወንጌል ም. ፲፮ ቊ. ፱ - ፲፱
ወተንሢኦ በጽባሕ በእሑድ ሰንበት...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅድስት #እናታችን_ማርያም_መግደላዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ #ቅድስት_ማርያም #መግደላዊት ✞✞✞

=>ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ "መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት (ወንጌላውያን) ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ:- በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች በአንዱ (በመግደሎን) ተወልዳ ያደገች ናትና::

+ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም 7 አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር:: በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች::

+በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም (ይቀበላል): አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት አልዘገየችም::

+ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ ሆነች:: ጌታም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ መርጦ ተከታዩ አደረጋት::

+ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች:: እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው::

ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች::

+ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ #መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ ነበረች:: (ዮሐ. 19:25) ቅዱሳኑ #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ጌታን ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች::

+እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን አልፈራችም:: ጌታችንም #ክእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ አደላት::

+በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም 2 መላእክትን (#ሚካኤልና_ገብርኤልን) ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም" አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት::

+ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት:: "ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን ለደጋጉ #ሐዋርያት ሰበከችላቸው::

+#ቅድስት_ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሣኤ በሁዋላ ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን: #ትምሕርተ_ኅቡዓትን ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ: በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥም ልዩ አገልግሎት ነበራት::

+ቅዱሱ #እስጢፋኖስ 8 ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ #መንፈስ_ቅዱስ የሚባርከውን #አጋፔ (የፍቅር ማዕድ) የምታዘጋጀው እርሷ ነበረች::

+እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል:: እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ #ቅዱስ_መልአክ ወርዶ ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ ይመግባቸው ነበር::

+እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን #ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች:: ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና ግርፋትን ታግሳለች::

+በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ (ከአንዳንዶቹ በቀር) ያከብሯታል::

+"+ #ቅድስት_ኢየሉጣ_ዘቂሣርያ +"+

=>በቀድሞው የግሪክ ግዛት (ቂሣርያ ውስጥ) በዘመነ ሰማዕታት አካባቢ የነበረችው #ቅድስት_ኢየሉጣ ክርስትናን የወረሰችው ከወላጆቿ ነው:: ገና ወጣት እያለች ወላጆቿ በማረፋቸው የሃብታቸው ወራሽ ሆነች::

+ነገር ግን አንድ ክፉ ሰው መጥቶ ሃብቷን ነጠቃት:: በዚህ አዝና "የዳኛ ያለህ" ልትል ወደ ፍርድ ቤት ስትሔድ የጠበቃት ግን የሚገርም ነበር:: የተገፋችው እርሷ ተከሳሽ: ገፊው ደግሞ ከሳሽ ነበር:: የክሱ ጭብጥ ደግሞ "ክርስቲያን ነሽ" የሚል ነበር::

+በወቅቱ በመኳንንቱ ፊት ክርስትናዋን ብትክድ በቀጥታ ሃብቷን ማግኘት ትችል ነበር:: እርሷ ግን ለአፍታ አሰበች:: "እንዴት ዘላለማዊ ሃብቴን (ሃይማኖቴን) በኃላፊው ንብረት እለውጣለሁ" ብላ ሁሉም እየሰሙ ጮክ ብላ "#ክርስቲያን_ነኝ" አለች::

+ወዲያውም ሞት ተፈርዶባት ተገደለች:: ታላቁ #ቅዱስ_ባስልዮስ ስለ #ሰማዕታት በጻፈው ድርሳን ላይ በስፋት አመስግኗታል:: ለሴቶችም ታላቅ ምሳሌ ናት ብሏታል::

=>ቅዱሳት እናቶቻችንን ያጸና ቸር አምላካቸው እኛንም በሃይማኖትና በምግባር ያጽናን:: ከበረከታቸውም አብዝቶ ያድለን::

=>ነሐሴ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ማርያም መግደላዊት (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት)
2.ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት (ዘቂሣርያ)
3.አባ ዊጻ (የታላቁ ሲኖዳ ደቀ መዝሙር)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=>+"+ #ጌታ ኢየሱስም:- "#ማርያም" አላት:: እርሷ ዘወር ብላ በእብራይስጥ:- "#ረቡኒ" አለችው:: ትርጉዋሜውም "መምሕር ሆይ!" ማለት ነው:: ጌታ ኢየሱስም:- "ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ:: ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሔደሽ . . . ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው" አላት:: #መግደላዊት_ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይሕንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች:: +"+ (ዮሐ. 20:16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
መናኔ መንግሥት አቡነ ኢዮስያስ  መንግሥታቸውን ንቀው የመነኑ።
  ደብረ በንኮል በቅዱስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ምንኩስናን የተቀበሉ።

በብዙ የቅድስና ተጋድሎ ኖረው ተአምራትን ያደረጉ
ቆመው በጸለዩበት ቦታ ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ ይዘንባል።
ጥር 6 ተወልደው። ዕረፍታቸው ነሐሴ 6 ነው።

           በረከታቸው ይደርብን።

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ነሐሴ 7/12/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፹፮፥፩-፪(86፥1-2)
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን።
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ።


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፩፥፩-፲፯(1፥1-17)
መጽሐፈ ልደቱ ለእግዚእነ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብእ ዕብራውያን ፱፥፩-፲፩(9፥1-11)
ወለቀዳሚትኒ ደብተራ…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፪፥፮-፲፰(2፥6-18)
እስመ ከመዝ ጽሑፍ ናሁ እሠይም…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፥፩-፴(10፥1-30)
ወሀሎ ፩ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ…


            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ
ወዘመሀርኮ ሕገከ
ከመ ይትገኀሥ እምዋዕለ እኩያት


               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፺፫ ቊ. ፲፪ - ፲፫

፲፪ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።

፲፫ ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ ለኃጥኣን ጕድጓድ እስኪቆፈር ድረስ።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፮ ቊ. ፲፫ - ፳፬
ወበጺሖ ኢየሱስ ብሔረ ቂሣርያ...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቁጽረታ (ጽንሰታ) ለማርያም †††

††† ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል::
ስለ ምን ነው ቢሉ:-
ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ::
"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ::"
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው::"
(መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)

ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል::
የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር::

ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ::

እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ"
"ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ::
(ቅዳሴ ማርያም)

††† ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት †††

††† ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ:: በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ::

የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር:: የዋሃን (ገና ምሥጢርን ያልተረዱ) ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ:: ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን:: ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት::

አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው:: "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው:: ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ::

ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ:: "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው:: እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ::

ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ:: ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና:: በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው:: (ማቴ. 16:16)

ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት (መሠረት) ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ:: ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ (ሥልጣን)" ተሰጠው::

††† ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ:: ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው::
ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ:
ወልደ ማርያም:
አካላዊ ቃል:
ሥግው ቃል:
ገባሬ ኩሉ:
የሁሉ ፈጣሪ"ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም::

††† አፄ ናዖድ ጻድቅ †††

††† ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት: ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት:: ከእነዚህ አንዱ ደግሞ አፄ ናዖድ ናቸው:: ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ/ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ:: ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል::

ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት (ሰላም ለኪ: እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .)
የደረሷት እርሳቸው ናቸው:: ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል:: ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው::

የጻድቁ ንጉሥ ሚስት (ማርያም ክብራ): ልጆቻቸው (አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ) እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ:: ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሳ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት::

እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው:: ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ" አሏት:: በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ/ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ/ም ዐርፈዋል::

††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖትና የአፄ ናዖድን በረከት ያሳድርብን::

††† ነሐሴ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር
4.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
6.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ)
7.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

††† "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . .
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::" †††
(መዝ. ፹፮፥፩-፮)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††