ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ሐምሌ 29/11/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፱፥፫(109፥3)
ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል
በብርሃኖሙ ለቅዱሳን
ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፪፥፩-፰(2፥1-8)
ወኮነ በውእቱ መዋዕል…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ገላትያ ፫፥፲፭-፳፱(3፥15-29)
ሕገ ሰብእ ንብል ሰብእ ጥቀ…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፬፥፱-፲፰(4፥9-18)
ወበዝንቱ ተዐውቀ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፱፥፳-፴፪(9፥20-32)
ወነበረ ደማስቆ ኅዳጠ መዋዕለ…


            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር የዐቅብ ኵሎ አዕፅምቲሆሙ ወኢይትቀጠቀጥ ፩ እምውስቴቶሙ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፴፫ ቊ. ፲፱ - ፳

፲፱ የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል።

፳ እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፪ ቊ. ፩ - ፲፫
ወተጋብኡ ኀቤሁ አእላፍ ሰብእ...

📜ቅዳሴ


👉ዘዲዮስቆሮስ (እምቅድመ ዓለም)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
"ከዚህ በፊት የዚህ ዓለም መሪዎች ስለ ምድራዊ ሥልጣን ሲሉ መልካም ምግባርን ሳይኾን ሀብትን፣ ዕድሜንና የዘር አድልዎን እንደ መመዘኛ ሲጠቀሙ በማየቴ ወቅሻቸው ዐውቃለሁ፡፡ ይህ ከንቱነት ወደ እኛ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መምጣቱን ስሰማ ግን የዓለማውያኑን ግብር መንቀፍ አቆምሁ፡፡ ...

በእነዚህ ነገሮች ሳይወቀሱ ራሳቸውን ነጻ ማድረግ የሚገባቸው የቤተክርስቲያን ሰዎች ከዓለም ሰዎች ተሽለው ካልፈጸሙት፥ ይልቁንም በሰማያዊ ግብር ላይ ተሰማርተው ሳለ ምድራዊ ሀብትን ወይም ይህን የመሰለ ነገር እንደሚቀራመቱ ኾነው ከተሻሙ፥ የዚህ ዓለም ሰዎች እንደዚህ ያለ ነገር ቢፈጽሙ'ማ ምን ይደንቃል?"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ በእንተ ክህነት መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ  የተረጎመው)
"ለነፍስህ የምታደርግላት ታላቅ ነገር አለ ይኼውም ራስህን በሚገባ መርምረህ ማወቅ ነው።"

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ
†††እንኳን ለቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ : ቅዱስ ዋርስኖፋ እና አባ ዮሐንስ ዘጐንድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

††† ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ †††

††† ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ3 ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል:: እንደ ዮሐንስ ወንጌላዊ ያሉት በ20ዎቹ ውስጥ : ቅዱስ ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ30ና በ40ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን እነ ቅዱስ ዼጥሮስ ደግሞ በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ::

ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም : ከጐልማሶችም : ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው:: ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) ስምዖን እና ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል::

ቅዱሱ ጌታችንን ተከትሎ : ከ12ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ : 3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ተምሮ : በዕርገቱ ተባርኮ : በበዓለ ሃምሳም 71 ልሳናትን ተቀብሎ : ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል::

ቅዱስ ታዴዎስ እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም ሐምሌ 2 ቀን ዐርፏል::

ቅዱሱ ሐዋርያ ያረፈው ሶርያ ውስጥ ሲሆን ከ250 ዓመታት በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ ታንጾለት በዚህች ቀን ወደ ቁስጥንጥንያ ፈልሷል:: ይህንን ያደረገው ደግሞ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነው:: ከሐዋርያው ዘንድም ብዙ ተአምራት ተደርገዋል::

††† ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት †††

††† ቅዱሱ በትውልድ ግብፃዊ ሲሆን ገና ከልጅነቱ ጣዕመ ክርስትና የገባው ነበር:: መጻሕፍትን በማንበብ: ክርስትናንም በመለማመድ ስላደገ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት የመወደድ ሞገስ ነበረው:: በእድሜው እየጐለመሰ ሲሔድ በተጋድሎውም እየበረታ ሔደ::

በወቅቱ እርሱ የነበረባት ሃገር ዻዻስ በማረፉ ሊቃውንቱና ሕዝቡ ተሰብስበው አምላክን ጠየቁ:: እንደሚገባም መከሩ:: በደንብ አስተውለዋልና እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው ሁሉም ቅዱስ ዋርስኖፋን መረጡ::

ዛሬን አያድርገውና በአባቶቻችን ዘመን ሕዝቡም ሆነ ሊቃውንቱ መሪ መምረጥን ያውቁ ነበር:: ተመራጮቹ ደግሞ እንኩዋን እንደ ዘመናችን "ሹሙኝ : ምረጡኝ" ሊሉ በአካባቢውም አይገኙም ነበር::

ቅዱስ ዋርስኖፋ ለዽዽስና እንደ መረጡት ሲያውቅ "ጐየ" እንዲል መጽሐፍ: ጨርቄን ማቄን ሳይል በሌሊት ጠፍቶ በርሃ ገባ:: (እንዲህ ነበሩ አበው) በገባበት በርሃ ውስጥ በዓት ሠርቶ በጾም: በጸሎትና በስግደት በርትቶ ዓመታትን አሳለፈ:: እርሱ በበርሃ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ጀምሮ ብዙ ክርስቲያኖች አልቀው ነበር::

እርሱ ግን ከዓለም ርቁዋልና ይህንን አላወቀም ነበር:: አንድ ቀን መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ "አንተ በስሙ ደማቸውን ለሚያፈሱ አክሊላት እየታደለ : ሰማያዊ ርስትም እየተካፈለ ነውኮ! አልሰማህም?" አለው::

ቅዱስ ዋርስኖፋም "ለካም እንዲህ ያለ ክብር አምልጦኛል" ብሎ: በርሃውን ትቶ ወደ ከተማ ወጣ:: መልአኩ እንዳለውም ክርስቲያኖች ሲሰቃዩ ደረሰ:: ቅዱሱም ሳያመነታ ስመ ክርስቶስን ሰብኮ: ብዙ ተሰቃይቶ በዚህች ቀን አክሊለ ሰማዕትን በአክሊለ ጻድቃን ላይ ደርቧል::

††† እጨጌ አባ ዮሐንስ ዘጐንድ †††

††† ጻድቁ ተወልደው ያደጉት በኢየሩሳሌም ሲሆን ነገዳቸውም እሥራኤላዊ ነው:: ነገር ግን ተጋድሏቸውን የፈጸሙት በሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ ነው:: እጨጌ አባ ዮሐንስ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ ባለ ረዥም እድሜ ጻድቅ መሆናቸው ይነገራል::

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያረፉት በ562 ዓመታቸው ሲሆን እጨጌ አባ ዮሐንስ ደግሞ በ500 ዓመታቸው ነው:: የሚገርመው ጻድቁ የታላላቁ ጻድቃን ገብረ መንፈስ ቅዱስ : ተክለ ሃይማኖት: ሳሙኤል: ዜና ማርቆስ እና ሌሎችም ባልንጀራ ነበሩ::

በዛ ዘመን ዘረኝነት በቅዱሳኑ ዘንድ አልነበረምና ነጭ ሆነ ጥቁር : ከየትም ይምጣ የሰው ልጅ መሆኑ ብቻ በቂ ነበር:: እጨጌ አባ ዮሐንስ በሃገራችን 5 በዓቶች የነበሯቸው ሲሆን በአንድ በዓት የሚኖሩት ለ50 ዓመት ነበር::

በዚህም በኢየሩሳሌም ለ50 ዓመት : በኢትዮዽያ ደግሞ ለ450 ዓመታት ኑረዋል:: ከበዓቶቻቸው አንዱ ደብረ ሊባኖስ ሲሆን በገዳሙ ለ50 ዓመታት አበ ምኔት(እጨጌ) ሆነው አገልግለዋል:: "እጨጌ" የሚባሉትም በዚህ ምክንያት ነው::

ጻድቁ የመጨረሻ ዘመናቸውን ያሳለፉት በጐንድ (ጉንድ) ተክለ ሃይማኖት ገዳም ነው:: ገዳሙ የሚገኘው በሰሜን ጐንደር ዞን : በለሳ ወረዳ ውስጥ ሲሆን የመሠረቱትም ራሳቸው ናቸው:: ነገር ግን በራሳቸው እንዲጠራ አልፈለጉምና ገዳሙ የሚጠራው በወዳጃቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም ነው::

ጐንድ እኛ ኃጥአን ሳይገባን ያየነው ገዳም ነው:: ዛሬም ድረስ ድንቅ የሆኑ አበው የሚኖሩበት : ተአምራትም የማይቋረጥበት : ፈዋሽ ጠበል ያለው ደግ ገዳም ነው:: ጻድቁ እጨጌ አባ ዮሐንስ ግን አስታዋሽ አጥተው እየተዘነጉ ካሉ ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ምንም ዛሬ አጽማቸው ፈልሶ ወደ ደቡብ ኢትዮዽያ አካባቢ ቢሔድም እርሳቸው በ500 ዓመታቸው ያረፉት በዚህ ገዳም ውስጥ ነው::

††† እግዚአብሔር ከሐዋርያው : ከሰማዕቱና ከጻድቁ ክብርን : በረከትን ያሳትፈን::

††† ሐምሌ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት
3.እጨጌ አባ ዮሐንስ (ዘጐንድ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

††† "ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል::" †††
(1ዼጥ. 5:3)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ሐምሌ 30/11/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፮፥፳፭(106፥25)
ይቤ ወመጽአ መንፈሰ ዐውሎ
ወተለዐለ ማዕበል
የዐርጉ እስከ ሰማይ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፮፥፵፯-፶፫(6፥47-53)
ወመስዮ ብሔር…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ም ፪፥፩-፱(2፥1-9)
ወአነሂ ሶበ መጻእኩ ኀቤክሙ…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፪ ም ፩፥፲፪-፲፯(1፥12-17)
ወበእንተዝ እጽሕቅ ለክሙ ዘልፈ…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፫፥፩-፲(3፥1-10)
ወዐርጉ ምኵራበ ጴጥሮስ ወዮሐንስ…


            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እምውኂዝ አምሠጠት ነፍስነ
አምሠጠት ነፍስነ እማየ ሐከክ
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክነ
ዘኢያግብአነ ውስተ መሥገርተ ማዕገቶሙ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፳፫ ቊ. ፬ - ፮

፬ በዚያን፡ጊዜ፡ውሃ፡ባሰጠመን፡ነበር፥በነፍሳችንም፡ላይ፡ፈሳሽ፡ባለፈ፡ነበር፤

፭ በዚያን፡ጊዜ፡የጐርፍ፡ውሃ፡በነፍሳችን፡ላይ፡ባለፈ፡ነበር።

፮ ለጥርሳቸው፡ንክሻ፡ያላደረገን፡እግዚአብሔር፡ይባረክ።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማርቆስ ወንጌል ም. ፬ ቊ. ፴፭ - ፵፩
ወይእተ ዓሚረ መስዮ ይቤሎሙ...

📜ቅዳሴ


👉ዘሐዋርያት


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
††† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም †††

††† ቸር #እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ #ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ #ጽድቅ መድረስ አይቻልም::

ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::

"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን " #ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: #እመ_ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::

ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው #ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::

ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::
*የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::
*ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::
*የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል::

††† በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::

††† #ጽንዕት_በድንግልና: #ሥርጉት_በቅድስና #እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
*ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::*

††† ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ †††

††† እጅግ የተወደዱ: ሞገስ የሞላላቸውና ፈጣሪያቸውን በክብር ገንዘው የቀበሩ አባቶች ናቸው::

††† ቅዱስ ዮሴፍ ዘአርማትያስ †††

††† ቅዱሱ በእሥራኤል ምድር ተወልዶ ያደገ: ኦሪትን የተማረ ባለጠጋ ሰው ነው:: የተማረ ደግ ሰው ነውና የክርስቶስን መምጣት በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ባገኘውም ጊዜ በአዳኝነቱ (በመሲህነቱ) አምኖ በስውር ተከታዩ ነበር::

††† ቅዱስ ኒቆዲሞስ †††

††† ወንጌል እንደሚነግረን ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ: መምህር: ዳኛ እና ሃብታም ሰው ነበር:: እነዚህ ሁሉ ማነቆዎች ግን እርሱን ከፈጣሪው ሊያስቀሩት አልቻሉም:: ሌሊት እየመጣ ከጌታችን እግር ይማር ዘንድም አድሎታል:: በመካከልም ከአይሁድ ጋር ብዙ ተጋጭቷል::

ሁለቱ አባቶች መድኃኒታችን ስለ እኛ ሲል ሞቶ ባለበት ሰዓት ላይ በእርሱ የደረሰ ይደርስብናል ሳይሉ በድፍረት ሥጋውን ከዺላጦስ ተካሠው ለመኑ:: እንባቸው በፊታቸው እየወረደ ከመስቀል አውርደው በዮሴፍ በፍታና በኒቆዲሞስ ሽቱ ገነዙት::

እንዲህ እያሉ:-
"ሙታንን የምታስነሳ ጌታ አንተ ሞትክን?! ደካሞችን የምታጸና ቸር አንተ ደከምክን?!"
*በዚያች ሰዓት ጐልጐታ አካባቢ ዝማሬ መላእክትን እየሰሙ የክብር ባለቤትን ቀብረውታል:: ጌታችንም ከተነሳ በሁዋላ በንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::

"እየሳማችሁ አክብራችሁ እንደ ገነዛችሁኝ እኔም በሰማይ በእንቁ ዙፋን ላይ አስቀምጣቹሃለሁ" ብሏቸዋል:: "አነ አብረክሙ ዲበ መንበረ ሶፎር" እንዲል:: ጻድቃን አበው ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በተረፈ ዘመናቸው ወንጌልን ሰብከው: ከአይሁድ መከራን ታግሰው: በበጐ ሽምግልና ዐርፈዋል::

††† ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት †††

††† ቅዱስ አቦሊ የሰማዕታቱ #ቅዱስ_ዮስጦስና #ቅድስት_ታውክልያ ልጅ ሲሆን በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ያበራ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ሰማዕት ነው:: የሚገርመኝ ሦስቱ የግማሹ ዓለም አስተዳዳሪዎች ነበሩ:: ዮስጦስ ንጉሥ: ታውክልያ ንግሥት: አቦሊ ደግሞ ልዑል ነው::

ነገር ግን ይህንን ክብራቸውን #በክርስቶስ ፍቅር ጐን: ሚዛን ላይ ቢያኖሩት በጣም ቀሎ ታያቸው:: 3ቱም ከዙፋናቸው ወርደው: ወገባቸውንም ታጥቀው: ባሮቻቸው በነበሩ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ብዙ ተንገላቱ:: መራራ ሞትንም ታገሱ::

በተለይ ቅዱስ አቦሊ ከአንጾኪያ ወደ ግብጽ (ብስጣ) ይዘው አምጥተው ክርስትናውን እንዲተው ያላደረጉት የለም:: በቁሙ ቆዳውን ገፈው: በቆዳው አቅማዳ ሰፍተው: ያንንም አሸክመው: የተገፈፈ አካሉን ጨውና ኮምጣጤ እየቀቡ አዙረውታል::

እርሱ ግን ጌታ በላከለት ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ረዳትነት ሁሉን ችሎታል:: በዘመኑ ብዙ ተአምራትን የሠራ ሲሆን አንድ ጊዜ ቤት ተንዶ 16 ሰዎች ቢያልቁ የተገፈፈ ቆዳውን እየጣለባቸው ተነስተዋል:: በተአምራቱና በተጋድሎውም ብዙ ሺህ አሕዛብን ለክርስትና: ብሎም ለሰማዕትነት አብቅቷል::

እርሱም ከብዙ የመከራ ጊዜያት በሁዋላ በዚህች ቀን አንገቱን ተከልሏል:: ጌታችን "ዜናሕን የጻፈውን: ያነበበውንና የሰማውን ይቅር እለዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጥቶታል::

††† ፈጣሪ ከጻድቃንና ሰማዕታት በረከትን አይለይብን:: ወርሐ ነሐሴንም ለበረከት ይቀድስልን::

††† ነሐሴ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

††† "የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ #ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ:: ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ #ጌታ_ኢየሱስ መጥቶ የነበረ #ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት::" †††
(ዮሐ. 19:38)

††† "በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" †††
(ኢዩ. 2:15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ነሐሴ 1/12/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፷፯፥፳፭-፳፮(67፥25-26)
በጽሑ መላእክት ወቦሙ መዘምራን
ማዕከለ ደናግል ዘባጥያተ ከበሮ
በማኅበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር

📖ወንጌል
ወንጌል ዘማቴዎስ ፳፭፥፲-፲፬(25፥10-14)
አሜሃ ትመስል መንግሥተ ሰማያት…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፭፥፩-፲፩(5፥1-11)
ሊቃናተ ኢታመጕዕ…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፭፥፩-፮(5፥1-6)
ኵሉ ዘየአምን ከመ ኢየሱስ ውእቱ መሢሕ…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፭፥፳፮-፴፬(5፥26-34)
ወእምዝ ሖረ መጋቤ ምኵራብ…


            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኃፈር
ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ
ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፲፰ ቊ. ፵፮ - ፵፰

፵፮ በነገሥታት ፊት ምስክርኽን እናገራለኹ አላፍርምም፤

፵፯ እጅግም በወደድዃቸው በትእዛዛትኽ ደስ ይለኛል።

፵፰ እጆቼንም ወደ ወደድዃቸው ወደ ትእዛዛትኽ
አነሣለኹ ሥርዐትኽንም አሰላስላለኹ።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የዮሐንስ ወንጌል ም. ፲፱ ቊ. ፴፰ - ፵፪
ወእምድኅረ ዝንቱ ሰአሎ ለጲላጦስ...

📜ቅዳሴ


👉ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ አው ዘእግዝእትነ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
"የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ነሐሴ 2/12/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፪፥፩(102፥1)
እምአይቴ ይምጻእ ረድኤትየ
ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር
ዘገብረ ሰማየ ወምድረ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፬፥፪-፲(4፥2-10)
ወመሀሮሙ ወመሰለ ሎሙ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፪፥፰-፲፭(2፥8-15)
ወእፈቅድ ለኵሉ ሰብእ ይጸልዩ በኵሉ…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፫፥፩-፯(3፥1-7)
ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና ለአም…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፲፫-፲፱(16፥13-19)
ወወፃእነ በዕለተ ሰንበት እምአንቀጸ ሀገር…


            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ
ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ
ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም ፵፬ ቁ ፲፬-፲፭

፲፬ በዃላዋ፡ደናግሉን፡ለንጉሥ፡ይወስዳሉ፥ባልንጀራዎቿንም፡ወዳንተ፡ያቀርባሉ፤

፲፭ በደስታና፡በሐሴት፡ይወስዷቸዋል


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የዮሐንስ ወንጌል ም. ፰ ቊ. ፩ - ፲፪
ወኢየሱስኒ ሖረ ደብረ ዘይት...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳት #እናቶቻችን #አትናስያ_እና_ኢዮዸራቅስያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ #ቅድስት_አትናስያ ✞✞✞

=>የዚህች ቅድስት ሕይወት በብዛት የእግዚአብሔርን ቸርነትና የንስሃን ፍጹምነት የሚያሳይ ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ቅድስት አትናስያ ግብፃዊት ስትሆን የነበረችውም #መኑፍ በሚባል አውራጃ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ይህ ዘመን "ዘመነ ከዋክብት" ይባል ነበር:: ከቁጥር የበዙ ቅዱሳንም በዘመኑ ነበሩ::

+ቅድስት አትናስያም ከክርስቲያን ወላጆች ተወልዳ: እንደሚገባ አድጋ: ገና በወጣትነቷ ሁለቱም ወላጆቿ ሞቱባት:: ነገር ግን ብዙ ሃብት ትተውላታልና ምን እንደምታደርገው ሃሳብ ሆናት:: #መንፈስ_ቅዱስ ግን መልካሙን ሕሊና አደላትና አብርሃማዊ ሥራን ለመሥራት ቆረጠች::

+መጀመሪያ አገልጋዮችን አዘጋጀች:: እንደየ ወገኑ ለእንግዶችና ለነዳያን ቤትን ሠራች:: በጐውን እድል መርጣለችና ለብዙ ዓመታት ለነዳያን በማድላት: እንግዶችን በመቀበል ተጠመደች:: በዚህ ሥራዋም እግዚአብሔርንም ሰውንም ደስ አሰኘች::

+ግብሯ እንዲህ ነው:: በሌሊት ጸሎት: በመዓልት ግን እንግዶችን መቀበል: እግር ማጠብ: ማስተናገድ: ማስተኛት: ስንቅ አሰንቆ መስደድ ነው:: በዚህ ግብሯ ከምንም በላይ የወቅቱን ጻድቃን አስደስታለች::

+በዚያው ልክ ግን ዲያብሎስ ተቆጥቶ ይከተላት ጀመር:: በብዙ ጐዳና አልሳካልህ ቢለውም በክፉ ጐረቤቶቿ አማካኝነት ግን ተሳካለት:: የአካባቢዋ ሰዎች ወደ እርሷ ተሰብስበው በብዙ ማታለል ከቅድስና ሕይወቷ ፈቀቅ እንድትል አደረጉ::

+እነርሱ መልካም ሥራዋን ያስተዋት በመልክ ቆንጆ ነበረችና ይህንን ተጠቅመው ነው:: "ውበትና ሀብትሽን አታባክኚ" ብለው ከጐዳና አስወጧት:: መጽሐፍ ክፉ ባልንጀርነትን የሚቃወመው ለዛ ነው:: መልካም #ክርስቲያን ማለት ባልንጀራውን የሚመርጥ ነው::

+የሚገርመው ያን ያህል እንግዳ ተቀብላበት ያላለቀ ገንዘብ አሁን ግን ተመናመነ:: ክፉዎቹ ምክራቸውን ቀጠሉ:: አካሏን እንድትሸጥ አሳምነው ሴተኛ አዳሪ አደረጉዋት:: ባንዴ ከዚያ የቅድስና ከፍታ ወርዳ አካሏን ለዝሙት የምትሸጥ ሆነች::

+ነገሩን የሰሙ ገዳማውያን ሁሉ አዘኑ: አለቀሱላት:: ይልቁኑ ለእነሱ የእናት ያህል ደግ ነበረችና ከዲያብሎስ ሴራ ሊታደጉዋት ቆረጡ:: ከመካከላቸውም #ቅዱስ_ዮሐንስ_ሐጺርን ለዚህ ተግባር መረጡ:: እርሱ በአጋንንት ላይ ሥልጣን ያለው ሰው ነውና::

+እነርሱ ሱባዔ ይዘውላት አባ ዮሐንስ ሐጺር ወደ መኑፍ ከተማ ሔደ: ወደ ቤቷም ደረሰ:: ጠባቂዋን አስፈቅዶ ሲገባ ለረከሰው ድርጊት የመጣ ሰው መስሏት ተዘጋጅታ ነበር:: አባ ዮሐንስ ሐጺር ግን አጋንንትን ያርቅ ዘንድ እየዘመረ ገባ::
"እመኒ ሖርኩ ማዕከለ ጽላሎተ ሞት . . . በሞት ጥላ ሥር እንኩዋ ብሔድ አንተ ከኔ ጋር ነሕና ክፉን አልፈራም" እያለ ቀረባት:: (መዝ. 22)

+ፈጠን ብሎ ከጐኗ ተቀምጦ ቅዱሱ ምርር ብሎ አለቀሰ:: አትናስያ ደንግጣ "ምነው?" አለችው:: "የአጋንንት ሠራዊት በራስሽ ላይ ሆነው እየጨፈሩኮ ነው" አላት:: አስከትሎም አጋንንቱን በጸሎቱ ቢያርቅላት በአንዴ ወደ ልቧ ተመለሰች::

+ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው የሠራችውን ሁሉ ማመን አቃታት:: ተስፋም ቆረጠች:: ቅዱስ ዮሐንስ ግን "ግዴለሽም: ንስሃ ግቢ:: ፈጣሪ ይምርሻል" ብሎ አሳመናት:: "እሺ አባቴ" ብላ ከቀደመው ዘመን ሥርዓት ያለውን አንዱን ቀሚስ ለብሳ: ጫማ ሳትጫማ: ሌላ ልብስ ሳትደርብ: ምንም ነገር ሳትይዝ ከቤት ወጣች::

+ቤቷን አልዘጋችም:: ዘወር ብላ ወደ ሁዋላም አልተመለከተችም:: ቅዱሱን ተከትላ ጉዞ ወደ በርሃ ሆነ:: ያ በእንክብካቤ የኖረ አካል እሾህና እንቅፋት: ብርድና ፀሐይ ጐበኘው:: ሲመሽ እጅግ ደክሟታልና "እረፊ" ብሏት ሊጸልይ ፈቀቅ አለ::

+መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ #መላእክት ከሰማይ የብርሃን ዓምድ ዘርግተው አንዲትን ነፍስ በዝማሬ ሲያሳርጉ አየ:: "የማን ነፍስ ትሆን" ብሎ ወደ #አትናስያ ሲሔድ መሬት ላይ ዘንበል ብላ ዐርፋ አገኛት:: ቅዱሱም "ጌታ ሆይ! ምነው ለንስሃ እንኩዋ ብታበቃት?" ብሎ አለቀሰ::

+ፈጣሪ ከሰማይ ተናገረ:- "ገና ከቤቷ ተጸጽታ ስትወጣ ነው ይቅር ያልኩዋትና ደስ ይበላችሁ" አለው:: ይህንን የአምላክ ቃል ሁሉም ገዳማውያን ሰምተው እጅግ ደስ አላቸው:: "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: 7 ጊዜ ይነሳል::"

+"+ #ቅድስት_ኢዮዸራቅስያ ድንግል +"+

=>ይህቺ ቅድስት እናት የ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ስትሆን ወደ ምናኔው የገባችው ገና በ6 ዓመቷ ነው:: አባቷ ገና በልጅነቷ የሞተባት ኢዮዸራቅስያ ከእናቷ ጋር ለሥራ ወደ ግብፅ ገዳማት ይሔዳሉ:: በዚያ #ደናግል ጌታችንና እመቤታችንን ሲያገለግሉ ተመልክታ ተደነቀች::

+ምክንያቱን ብትጠይቃቸው ስለ ሰማያዊ ተስፋ ነገሯት:: የሰማችው ነገር ቢመስጣት እዚያው ገዳም ውስጥ መኖርን መረጠች:: እናት ሥራቸውን ሲጨርሱ "እንሂድ" ብትላትም ያቺ የ6 ዓመት ብላቴና "እኔ ከእንግዲህ የክርስቶስና የድንግል እናቱ ንብረት ነኝና የትም አልሔድም" አለቻት::

+እናት የሕጻን ልጇን ነገር ሰምታ "ልጄ! አንቺ ያልፈለግሺው ዓለም ለእኔስ ምን ይሰራልኛል?" ብላ እርሷም እንደ ልጇ ገዳሙ ውስጥ ቀረች:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላም እናት ታማ ዐረፈች:: ቅድስት ኢዮዸራቅስያም ንጹሕ ተጋድሎዋን ቀጠለች::

+ትዕግስት: ትሕትና: ፍቅር: ደግነትና ታዛዥነት በእርሷ ሕይወት ላይ በዝተው መገለጥ ያዙ:: እህል የምትቀምሰው በ7 ቀን አንዴ ብቻ ሆነ:: ለጸሎት ስትቆምም እስከ 40 ቀናት በተመስጦ ትቆይ ነበር:: ያቺ ብላቴና ሰይጣንን ከነ ሠራዊቱ አሳፍራዋለችና ታገላት::

+በዱላና በመጥረቢያ ሳይቀር ይመታት ነበር:: እርሷ ግን ታገሰችው:: እጅግ ብዙ ድውያንን ከመፈወስ ደርሳ ድንቅ ተአምራትን ሠራች:: በዚህች ቀንም ዐርፋ ለክብረ መንግሥቱ በቃች:: ድንግል #ኢዮዸራቅስያ ለገዳሙ ሞገስ ነበረችና በዕረፍቷ ታላቅ ሐዘን ተደረገ::

=>የቅዱሳት አንስት አምላክ ከንጽሕናቸው: ከትጋታቸውና ከማስተዋላቸው በረከትን ይክፈለን::

=>ነሐሴ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አትናስያ ቡርክት
2.ቅድስት ኢዮዸራቅስያ ድንግል
3.ቅዱስ ዴሚና ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
7.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው:: ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ:: ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ:: +"+ (1ጢሞ. 1:15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ነሐሴ 3/12/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፶፩፥፰(51፥8)
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም
እገኒ ለከ ለዓለም እስመ ገበርከ ሊተ
እሴፈዎ ለምሕረትከ እስመ ሠናይትከ ኀበ ጻድቃኒከ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፯፥፳፩-፳፭(7፥21-25)
ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

         👉  ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ተሰሎንቄ ፩ ም ፫፥፩-፲፫(3፥1-13)
ወሥዒነነ ተዐግሦ አብደርነ ንንበር…


      👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፫፥፲-፲፭(3፥10-15)
ወዘሰ ያፈቅራ ለሕይወት ወይፈቱ…


      👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፬፥፳-፳፰(14፥20-28)
ወበሳኒታ ሖረ ምስለ በርናባስ…



            📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ
ብዑላነ ምድር
ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን


               👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፲፪ - ፲፫

፲፪ የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ።

፲፫ ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤ ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው።


            📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፰ ቊ. ፱ - ፲፰
ወይቤሎሙ ለእለ ያጸድቁ ርእሶሙ...

📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
"የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የማግሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
††† እንኳን ለታላቁ አባት አባ ስምዖን ዘዓምድ እና ቅድስት ሶፍያ ቡርክት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቁ አባ ስምዖን ዘዓምድ †††

††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ይህ ቅዱስ ነው:: ተወልዶ ያደገው በሶርያ (ንጽቢን) ውስጥ ሲሆን ዘመኑም 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: አባ ስምዖን ዘዓምድ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የልጅነትና የተማሪ ቤት ባልንጀራ ነው::

ሁለቱንም ያስተማራቸው ደግሞ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን ነው:: ቅዱሳኑ አባ ስምዖንና ቅዱስ ኤፍሬም ለአገልግሎት ከተለያዩ በኋላ አንድ ቀን ተገናኙ::
ቅዱስ ኤፍሬም ድንግል ማርያምን
"እመቤቴ" እያለ ደጋግሞ በጉባኤ ሲያመሰግናት በመስማቱ "ወንድሜ! ይህን ምሥጢር ማን አስተማረህ?" አለው::

ቅዱስ ኤፍሬምም "ተገልጾልኝ ነው" እንዳይል ውዳሴ ከንቱን ፈርቶ "ቅዱስ ያዕቆብ ነው ያስተማረኝ" ቢለው በአባ ስምዖን ጠያቂነት ወደ መቃብሩ ሔደው ቅዱሱን ከሞት ቀስቅሰውታል:: እርሱም የእመቤታችንን ክብርና የቅዱስ ኤፍሬምን ጸጋ መስክሮ ዙሮ ዐርፏል::

በዚህ የተገረመው ቅዱስ ስምዖን ለቅዱስ ኤፍሬም ሰግዶለት: እመቤቴን ስንቅ ይዞ ወደ በርሃ ሔደ:: ተጋድሎን: ጾምና ጸሎትን በእረኝነት ሕይወት (በሰባት ዓመቱ) የጀመረው ቅዱስ ስምዖን በርሃ ከገባ በኋላ በእጅጉ አሳደገው:: ቅዱሱ በወገቡ የሚሻክር ገመድ አሥሮ: ምግብ ሳይበላ ዕለት ዕለት ያጠብቀው ነበር::

ከጊዜ በኋላ ገመዱ ሆዱን ቆርጦት ወደ ውስጥ ገብቶ ነበርና ሲራመድ በእግሩ ደም ጠብ ጠብ ሲል ይታይ ነበር:: ይሕንን መመልከት ጭንቅ የሆነባቸው መነኮሳት ለአበ ምኔቱ ተናግረው ቁስሉን አድነውና ገመዱን አውጥተው ከገዳም አባርረውታል::

እርሱ ግን ይህንን የሚያደርገው ሕማማተ ክርስቶስን ለመሳተፍ ነው:: ከገዳም ከተባረረ በኋላ ቅዱሱ በበርሃ ውስጥ ወደ ሚገኝ ዋሻ ውስጥ ገብቶ አራዊት: እባብና ጊንጥ ከበውት ይጸልይ ነበር:: እግዚአብሔር ግን በራዕይ ለገዳሙ አበ ምኔት ተገልጾ "ወዳጄን ስምዖንን ካልመለስከው አልምርህም" አለው::

በዚህ ምክንያት መነኮሳት በጭንቅ ፈልገው አግኝተው: ከእግሩ ወድቀው ይቅርታ ጠይቀውታል:: እርሱ ግን ከመነሻውም የሚቀየም ልብ አልነበረውም:: ቅዱስ ስምዖን ወደ ገዳሙ ተመልሶ ለዘመናት በተጋድሎ ጸንቶ ቀጠለ::

እግዚአብሔር ግን ቅዱሱን ከገዳሙ ወጥቶ ወደ አንዲት ምሰሶ እንዲሔድ ስላዘዘው አሥራ አምስት ሜትር ያህል ርዝመት ባለው ምሰሶ ላይ ቆመ:: ከዚህች ቀን በኋላ ነው እንግዲህ "ስምዖን ዘዓምድ (የምሰሶው አባት)" የተባለው:: ቅዱሱ ከሃምሳ ዓመታት በላይ ያለ ምንም ዕረፍት እንቅልፍ እና መቀመጥ ቆሞ
ጸልዩዋል::

ቦታዋ ለከተማ ቅርብ በመሆኗ ብዙዎችን ፈውሷል:: በእርሱ ስብከት ወደ ሃይማኖት የተመለሱ: ንስሐ የገቡ ቁጥር የላቸውም:: አንዳንዴ ክፉ ሰዎች መጥተው እርሱን በማየት ብቻ ይለወጡ ነበር:: ከቆመባቸው ዘመናት አሥራ ሁለት ዓመታት ያህልን ያሳለፈው በአንድ እግሩ ቆሞ: ሌላኛው እግር ቆስሎ ነው:: ምክንያቱ ደግሞ የሰይጣን ዱላ ነበር::

ታላቁ አባ ስምዖን ዘዓምድ ከእነዚህ የተጋድሎ ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፏል:: የዕረፍቱ ዜናም ከቤተ መንግሥት እስከ ቤተ ክህነት ሁሉን አስደንግጧል:: እርሱ ለመንጐቹ ዕረፍት ያልነበረው ታላቅ አባት ነበርና:: ሊቃነ ጳጳሳት ገንዘውት: መኳንንት ተሸክመውት ሥጋው በክብር ዐርፏል:: ብዙ ተአምራትም ተደርገዋል::

††† ቅድስት ሶፍያ ቡርክት †††

††† ይሕች ቅድስት እናት ኢጣሊያዊት (የአሁኗ ጣልያን አካባቢ) ስትሆን የነበረችው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ነው:: ትውልዷ የነገሥታቱ ዘር ውስጥ እንደ መቆጠሩ እጅግ የተከበረች ሴት ነበረች:: ምንም ሥጋዊ ክብሯ እንዲህ ከፍ ያለ ቢሆንም መንፈሳዊነቷ የሚደነቅ ነበር::

ከነገሥታቱ ዘር ካገባችው ባሏም ሦስት ሴቶች ልጆችን አፍርታለች:: በሃይማኖት ምክንያት መከራ ሲመጣ ስለ ልጆቿ ስትል ሃገሯን ጥላ ተሰደደች:: ስለ ክርስትናም በባዕድ ሃገር መጻተኛ ሆነች:: ያም ሆኖ ክፉዎቹ እግር በእግር ተከትለው ደረሱባት::

ቅድስት ሶፍያ ከዚህ በላይ መሸሸትን አልፈለገችም:: ከልጅነታቸው ለተባረኩ ልጆቿ ገድላተ ሰማዕታትን ታስጠናቸው ነበርና አሁን የነገር መከናወኛ ደርሷል:: ልጆቿን ቁጭ አድርጋ አዋየቻቸው::

"ልጆቼ! ክርስቶስን የወደደ ክብሩ በሰማይ እንጂ በምድር አይደለም:: ገድላቸውን ያነበባችሁትን ቅዱሳት አንስትን አስቡ" አለቻቸው:: ሦስቱ ሕፃናትም "እናታችን አትጨነቂ:: እኛ ለአምላክ ፍቅር ተገዝተናል:: ስለ ስሙም ደምን ልንከፍል ቆርጠናል:: ብቻ የእርሱ ቸርነት: ያንቺም ምርቃት አይለየን እንጂ" አሏት:: ቅድስት ሶፍያ በሰማችው ነገር እጅግ ደስ አላት::

ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ አደረጉ:: ቅድስቷ እናት ሦስቱንም ሕፃናት በመኮንኑ ፊት አቀረበች:: አንድ በአንድ ጠየቃቸው:: ሁሉም ግን መልሳቸው የተጠናና ተመሳሳይ ሆነበት:: "እኛ የክርስቶስ ነን" ነበር ያሉት:: መኮንኑ በቁጣ ሦስቱንም እያከታተለ አስገደላቸው::

ቅድስት እናት ሶፍያ በእንባ እየታጠበች ልጆቿን
በየተራ ቀበረች:: ስለ ሃይማኖቷ ክብሯን: ሃገሯን: ሃብቷን: መንግሥቷን ሰጠች:: ከምንም በላይ ግን ልጆቿን ሰጠች:: ከዚህ በኋላ ግን በመጨረሻው ወደ ልጆቿ መቃብር ሒዳ በእንባ ለመነች::
"ልጆቼን አይ ዘንድ ናፍቄአለሁና ጌታ ሆይ! ውሰደኝ" አለች:: ከደቂቃዎች በኋላም እዚያው ላይ ዐረፈች:: የአካባቢው ሰዎች ደርሰው እርሷንም ከልጆቿ ጋር ቀበሯት::

††† መድኃኔ ዓለም ከታላቁ አባ ስምዖንና ከቅዱሳት አንስት በረከትን ያድለን:: ትዕግስታቸውንም ያሳድርብን::

††† ነሐሴ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ አባ ስምዖን ዘዓምድ
2.ቅድስት ሶፍያ ቡርክትና ደናግል ልጆቿ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
7.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)

††† "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል:: እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል::
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል:: በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ::
ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ:: ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ::" †††
(መዝ. ፺፩፥፲፪)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††