ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
ትንሣኤከ ለእለ አመነ
መዝሙረ ዳዊት በ Tlegeram
✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ

ትንሣኤከ ለእለ አመነ
ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ /2/

የትንሣኤው በኩር የሰው ልጆች ሕይወት
ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት
በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው
አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

የሲኦል መውጊያዋ ፍላጻው ተነስቷል
የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል
የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን
ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነፍሳቱን

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

ማርያም መግደላዊት የጠራሽ በስምሽ
በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ
መላእክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል
የነገራችሁን እዩት ተፈፅሟል

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

የሞት ኃይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ
በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አለኝታ
እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው
በትንሣኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

ለትንሣኤው ልጆች ለምናምን ለእኛ
ብርሃንን ላክልን ላይጨልም ዳግመኛ
እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ
ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

ዘማሪ
በሱፍቃድ አንዳርጋቸው

👉🏻@zekidanemeheret
👉🏻@zekidanemeheret
👉🏻@zekidanemeheret
††† እንኳን ለብጹዐን ጻድቃን: ቅዱስ ዞሲማስ እና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ብጹዐን ጻድቃን †††

††† በዚህ ቀን ብሔረ ብጹዐን ውስጥ የሚኖሩ ጻድቃን ይታሠባሉ::
በሃይማኖት ትምሕርት 5 ዓለማተ መሬት አሉ:: እነሱም አቀማመጣቸው ቢለያይም ከላይ ወደ ታች:-
1.ገነት (በምሥራቅ)
2.ብሔረ ሕያዋን (በሰሜን)
3.ብሔረ ብጹዐን (ብሔረ - አዛፍ - እረፍት) {በደቡብ}
4.የእኛዋ ምድር (ከመሐል) እና
5.ሲዖል (በምዕራብ) ናቸው::

††† ከእነዚሕ ዓለማት ባንዱ የሚኖሩ የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን:-
*ኃጢአትን የማይሠሩ::
*ለ1,000 ዓመታት የሚኖሩ::
*ሐዘን የሌለባቸው::
*በዘመናቸው 3 ልጆችን ወልደው (2 ወንድና አንድ ሴት) ሁለቱ ለጋብቻ: አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት የሚያውሉ ሰዎች ናቸው::

††† ቅዱሳኑ ወደዚሕ ቦታ የገቡት በነቢዩ ኤርምያስ እና በቅዱስ እዝራ ዘመን ሲሆን አንዴ የተወሰኑት በዘመነ ሰማዕታት ወጥተው በዚሕ ቀን ተሰይፈዋል::

††† በመጨረሻ ግን በሐሳዌ መሲሕ ዘመን ወጥተው ሰማዕትነትን ይቀበላሉ::

††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረቱና ይቅርታው ለምናምን ሁሉ ይደረግልን:: ከደግነታቸውም በረከትን አይንሳን::

+*" አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ "*+
=>አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ :
እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ
ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት
ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ "ስብሐት ለአብ
: ስብሐት ለወልድ : ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው
አመስግነዋል፡፡
+የስማቸው ትርጓሜ "የአብ : የወልድ : የመንፈስ ቅዱስ
እስትንፋስ" : አንድም "የክርስቶስ እስትንፋስ" ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ
እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን
ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት
ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው
ዐውቀዋል፡፡
+በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ
ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን
ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ
መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን
ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት
እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት : ለአባቶች
መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን
በማውጣት አገልግለዋል፡፡
+አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት
ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው
ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና
ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት
ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ
ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና
ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመስዋዕት
ወይኑን ለቁርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
+አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል
ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡
ጌታንም በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ
መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ
ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ
ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ ሁሉንም የኢትዮጵያን
ቅዱሳት ገዳማትንም ተዘዋውረው ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ
የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው
ነበር፡፡
+ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን
እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያስነሱ
ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ
ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው
የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ
ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን
ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት
የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
+ጻድቁ ወደ ደብረ አስጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ
ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
አውግዤሻለሁ፡፡ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ
አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን
አቁመዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አስጋጅ ሲደርሱ
ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ
ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት
ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት
አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡
+በአምላክ ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ፣
በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ
መልክአ ኢየሱስ ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤
እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል
ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች
በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ
የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡
በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት
ይደግማሉ፡፡
+ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን
ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ
ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔ ዓለምን
የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን
የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም
የሆነች ጸሎት "ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም" ብሎ
የሚጠራጠር ቢኖር ግን መንግሥተ ሰማያትን አያያትም፡፡
+ጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ታኅሳስ 9 ቀን ተወልው
ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ (ገድለ አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ)
=>አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ሃገራችንን
ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ሚያዝያ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
3.ቅዱስ ዞሲማስ ገዳማዊ (ብሔረ ብጹዐንን ያየ እና ዜናቸውን የጻፈ አባት)
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሕጻን ሰማዕት (ገና በ10 ወር ዕድሜው ሰማዕት የሆነ)
5.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
3.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)

††† "ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ::" †††
(1ዼጥ. 1:13-15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
እንኳን ለዕለተ "ማዕዶት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የትንሣኤ ሰኞ ስያሜ
+*"❇️ ማዕዶት❇️ "*+

=>ማዕዶት ማለት (ዐደወ-ተሻገረ) ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሣኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል::

+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ
*ከባርነት ወደ ነጻነት
*ከጨለማ ወደ ብርሃን
*ከሞት ወደ ሕይወት
*ከኃጢአት ወደ ጽድቅ
*ከሲዖል ወደ ገነት
*ከገሐነመ እሳት ወደ መንግሥተ ሰማያት
አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል::

+አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እንዲታሰብ ታዛለች::

+ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና::

=>አማናዊው ብርሃን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጨለማችንን በምሕረቱ ያብራልን::

=>+"+ ክርስቶስም እኮ ስለ ሰው ኃጢአት አንድ ጊዜ ሞቶአል:: ኃጢአት የሌለበት ክርስቶስ ጻድቁ ስለ እኛ ሞተ:: ስለ ኃጢአታችን እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ::
በሥጋ ሞተ: በመንፈስ ግን ሕያው ነው:: ነፍሳቸው ታስራ ወደ ነበረችበት ሔደ:: ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ነጻነትን ሰበከላቸው:: +"+ (1ዼጥ. 3:18)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ
#ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማክሰኞ
#ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ
#አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ
#አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ
#ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ
ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ
#ዳግም_ትንሣኤ _ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

👉🏻@zekidanemeheret
👉🏻@zekidanemeheret
👉🏻@zekidanemeheret
†††  እንኳን ለአባ ይስሐቅ ጻድቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ይስሐቅ ጻድቅ †††

††† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: በጊዜው ዝነኛ ከነበሩት ከታላቁ አባ ዕብሎይ (ቅዱስ ዕብሎይ) ተምረዋል:: መማር ብቻ ሳይሆንም ለ25 ዓመታት ያለ መታከት በተልዕኮ አገልግለዋል::

በእነዚህ ጊዜያትም ትሕርምትን : ተጋድሎን : ትምህርተ ቅድስናንና ሌሎች አስፈላጊ መንፈሳዊ ስንቆችን ሰንቀዋል:: በመታዘዛቸው በምድር አበውን : በሰማይ እግዚአብሔርን አስደስተዋል:: በዚህም ከእግዚአብሔር ጸጋውን : ከአበው ምርቃትን አትርፈዋል::

ጊዜው ደርሶም ታላቁ ዕብሎይ ሲያርፉ አባ ይስሐቅ በዓት ለይተው ደንበኛውን ተጋድሎ ጀምረዋል:: አምላካቸውን ለማስደሰትና በቅድስና ለመዝለቅም የአርምሞ ሰው ሁነዋል:: ለሚገባው ነገር ካልሆነ በቀር አያወሩም:: ምላሽም አይሰጡም:: "ለምን?" ሲባሉ
1."ለሁሉም ጊዜና ቦታ አለው::"
2."ሰው በከንቱ በማውራቱ ከጸጋ እግዚአብሔር ይርቃል" ይሉ ነበር::

አባ ይስሐቅ የክርስቶስ መድኃኒታችንን ሕማማት ለማዘከር ሁሌ ያነቡ (ያለቅሱ) ነበር:: ቅዳሴ ሲያስቀድሱ እጃቸው የሁዋሊት ታስሮ ነበር:: ቅዱሱ ሰው ለአዝማናት እንዲህ ተመላልሰው በመልካም ዕርግና ያረፉት በዚህ ቀን ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው አይለየን::

††† ሚያዝያ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ይስሐቅ ገዳማዊ (የታላቁ ዕብሎይ ደቀ መዝሙር)
2.አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† "የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ:
ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ::
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" †††
(ይሁዳ. 1:1)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
እንኩዋን ለበዓለ ዕለተ "ቶማስ ወአብርሃም" ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

=>ልክ የሰሙነ ሕማማቱ ዕለታት ስምና ምሥጢር እንዳላቸው ሁሉ ከትንሣኤ በሁዋላ የሚገኙ ዕለታትም ስምና ምሥጢር አላቸው::

+ሰኞን ቤተ ክርስቲያን "#ማዕዶት" ብላ እንደምታከብር ትናንት የተመለከትን ሲሆን ማግሰኞን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን "#ቶማስ" : አንድም "#አብርሃም" ብላ ታከብረዋለች::

1. +*" ቶማስ "*+

=>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ለጊዜው ትንሣኤ ሙታንን ከማያምኑ ሰዱቃውያን ወገን በመሆኑ የክርስቶስን ትንሣኤ ተጠራጥሮ ነበር::
ምሥጢሩ "ግን ካላየሁ : ካልዳሰስኩ አላምንም" ያለው ከፍቅሩ የተነሳ እውነት አልመስልህ ብሎት ነው::

+አንድም ጌታ መለኮታዊ ጎኑን እንዲዳስሰው ቢፈቅድለት ነው:: ይህች የቅዱስ ቶማስ እጅ ዛሬ ድረስ ሕያው ናት:: ተአምራትንም ታደርጋለች::

2. +*" አብርሃም "*+

=>ከጻድቃነ ብሊት (ብሉይ) አንዱ የሆነው አባታችን አብርሃም ከጽድቁ የተነሳ ርዕሰ አበው (የአባቶች አለቃ) ተብሏል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃም ፈጣሪ ሲሆን የአብርሃም ልጅ መባልን ወዷልና::

+በተለይ በከበረ ትንሣኤ የምናገኛትን መንግሥተ ሰማያት በስሙ (የአብርሃም ርስት ተብላ) ተጠርታለችና አባታችን በዚህ ቀን ይታሰባል::

=>እግዚአብሔር ከ2ቱ ታላላቅ ቅዱሳን ጸጋ በረከትን ያድለን::

"✞" እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ
በሰጠው ጊዜ። በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ
እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም
ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ፤
እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን
አገኘ።
ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥
ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ
ይሆናል፤
ስለዚህም እግዚአብሔር፥ የተስፋውን
ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ
ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል
በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ
ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ፥
በመሓላ በመካከል ገባ፡፡ "✞" (ዕብ. ፮:፲፫)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
​​የ7ተኛ ክፍሉና ባለብዙ ዲግሪዎች እና የሃሰተኛ ዶክትሬት ባለቤት፣ የንፁሐን ኢትዮጵያውያን የደም አፍሳሽ,ዘረኛው ፀረ ሰላም,የጥልቁ መንግሥት ምልምል የ አብይ አህመድ የ ትምሮ  ጉዳይ ውልደትና እድገት ።

አብይ አህመድ ነሐሴ ወር  በ 1968  በ9  ተወለደ ። የመጀመሪያ ስሙ አብዮት ነበር። በኋላ ላይ ነው ቆይቶ ከአብዮት ወደ ዐቢይ የተቀየረው። አባትየው አቶ አህመድ አሊም በሰጡት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይም እንደተናገሩት ።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በበሻሻ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት መከታተሉን እሱ ራሱ ተናግሯል። በበሻሻ እስከ ስድስተኛ ክፍል ከተማረ በኋላ ከበሻሻ 17 ኪሎ ሜትር ወደ ምትርቀው አጋሮ ከተማ ሄዶ ትምህርቱን እንደቀጠለም ተናግሯል። እንግዲህ  እስከ 7ተኛ ክፍል መማሩን ከመስማት ውጪ ከዚያ በኋላ ያለው የትምህርት  ታሪኩ የለም ትምህርቱን በለጋ ዕድሜው ጀመረ ብለን በ1976 ዓ.ም በ8 ዓመቱ አንደኛ ክፍል ገባ እንበል ና ከ1ኛ ክፍል ብንጀምር ሳያቋርጥ ተምሮ 7ተኛ ክፍል የሚደርሰው በ1982  ነው የሚሆነው ።

ስለ ውልደትና እድገቱ ከመዓዛ ብሩ ጋር በነበረው ቆይታ በ15  ዓመቴ ገደማ ሲሆነኝ (በ 1983 ኢህአዴግ እዚያ አካባቢ መጥቶ ስለነበር ኢህአዴግን እንደተቀላቀለ ይናገራል ። ልብ በሉ አሁንም ዐቢይ 1983 ዓ.ም ዕድሜው 15 የትምህርት ደረጃው 7ተኛ ክፍል ነው።  ዐቢይ ይቀጥልና ለተወሰነ ጊዜ  እዚያው በካድሬነት አገሬ ላይ ሳይሆን ራቅ ብዬ በጅማ ዞን ውስጥ ወደ አትናጎ አካባቢ ሊሙ የሚባል አካባቢ እሠራ ነበር። በጣም ልጅ ነኝ። ማንጁስ የሚባሉ ህጻናት ዓይነት የሚሠሩትን ዓይነት ሥራ ነበር የምሠራው እያለ  ይናገራል

አብይ ከ1983 እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ በኦህዴድ ካድሬነት አገልግሏል  በዚያው በ1985 ዓ.ም አብይ ዕድሜው 17 የትምህርት ደረጃውም 7ተኛ ክፍል ነበር። እንግዲህ ጨዋታው አሁን ነው የሚጀመረው። ይሄው  አብይ በዚያው ዓመት በ1985 ዓ.ም ትምህርቱን ካቋረጠበት ከ7ተኛ ክፍል ሳይቀጥል ማንጁስ እንደተባለ በቀጥታ በ17 ዓመቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ሠራዊት አባል ሆኖ ወደ ሩዋንዳ ተጓዘ።   አብይ ከ1985 ዓ.ም እስከ 1987 ዓ.ም ድረስ በሩዋንዳ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው በ1987 ነው። በዚህም ወቅት ከሩዋንዳ ሲመለስም ዕድሜው 19 ክፍሉም ያው 7ተኛ ክፍል ነበር። በትምሮ በኩል የተቀየረ ነገር የለም።

ቀጠለና 3 ዓመት ቆይታ በኋላ በ21 ዓመቱ በ1990 ዓ.ም እንደገና ሌላ ግዳጅ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ላይ ለመሳተፍ በቀጥታ ወደ ባድመ ዘመተ። ወደ ባድመም ሲዘምት አሁንም 7ተኛ ክፍል መሆኑን ያዙልኝ።  በዚያም በትግራይ በረሃ  ለ3 ዓመታት ያህል ቆይቶ በ1993 ዓ.ም አጋማሽ ግዳጁን ጨርሶ ከባድመ ተመለሰ። አሁንም ዕድሜው 24 የትምህርት ደረጃው 7ተኛ ክፍል

እንግዲህ ከባድመ መልስ እስከ 1993 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ በ24 ዓመቱም የ7 ተኛ ክፍል ተማሪ የነበረ ሰው ድንገት በ1994 ዓ.ም በዲግሪ መመረቁን ይነገረናል በሰፊው ጥያቄ የምንጀምረው ከዚህ በኋላ ነው።

አብይ አህመድ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በተሾመ ዕለት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባቀረበው አጭር የአብይ የሕይወት ታሪክ ላይ  በ1994 ዓ.ም በኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ይላል

የ1994 ዓ.ም ዲግሪ ተገርመን ሳናበቃ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) በአማርኛ ክፍል በኩል በሰራው ዜና ጭራሽ አብይ ዲግሪውን በፊንፊኔ በማይክሮ ሊንክ ኢንፍርሜሽን ኮሌጅ ያገኘው በ 1993 ዓ.ም ነው ብሎ ሌላ ታሪክ ላይ ይገባል።  

እንግዲህ አምላክ ያሳያቹ  ያ ከ7ተኛ ክፍል ትምህርቱን ያቋረጠው  ከዚያም ከሩዋንዳ ሽሬ ሽራሮ ሲንከራተት የከረመ ሰውዬ በሆነ ተአምር በ1993 እና በ1994 ዓ.ም በኮምፒዩተር ኢንጅነሪንግ እንደተመረቀ ተነገረ በ OBN ና ፓርላማ ላይ  fake degree ተሰጠው ምን ታመጣላቹ   ማንበባችሁን ቀጥሉ

በ EBS ቴሌቪዥን ላይ  የሚቀርበው ትዝታችንን በ Ebs  ፕሮግራም ስለቀድሞው SOS ትምህርት ቤት  ታሪካዊነት አንድ ፕሮግራም ሰርቶ ነበር  እናም ያ ት/ቤት  ካፈራቸው ታዋቂ ሰዎች መካከል ሲጠየቅ ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በ1996 ዓ.ም በ 27 ዓመቱ የ 12 B ክፍል ተማሪ እንደነበር የትምህርት ዶክመንቱን በማውጣት ያልታሰበውን ጉድ ዘርግፎታል።

ቅሌትህ ሲዘረገፍ በዓለም የትምሮ ታሪክ ዲግሪ ከጫንክ በኋላ ወደ ኋላ 3 ዓመት ተከልሰህ 12ኛ ክፍል የተማረ ብቸኛ ሰው  እንደ አብይ አሕመድ ትሆናለህ ።  አትገረሙ የዚን  ቅሌታም አጭበርባሪ ጉድ በዚ ሚያበቃ ብቻ አይደለም ።  በቅርቡ የአለም አቀፉ የሰላም ፋውንዴሽን ባወጣው ትልቅ መረጃ  አብይ አህመድን በ 2009 ዓ.ም የተቀበለው  የ PH degree "ሌብነት" ብሎታል!  ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዶክተሬት ዲግሪን ሊያሰርዝ የሚችል በቂ የጥናት “ስርቆት” ማስረጃ ማግኘቱን የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቋል፡፡  

ፋውንዴሽኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዶክተሬት ዲግሪ ላይ ሰፊ ማጣራት በማድረግ በሌሎች ጥናቶች ላይ የተጠቀሱ ጽሑፎች በቀጥታና በጥቂት ማሻሻያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናት ላይ ተደግመው መገኘታቸው በማስረጃ አስደግፎ አብራርቷል፡፡

ይህም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተሬት መመረቂያ ፅሑፍ ላይ “የሌብነት” ምልክቶች እንዳሉ ባደረገው ማጣራት መታዘቡን ፋውንዴሽኑ ይፋ ባደረገበት ጽሑፍ ላይ ገልፆ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጉዳዩን እንደገና እንዲመለከተው  ጠቁሟል፡፡

አብይ እንዲ እያጭበረበረ እዚ ደርሷል  ከ7 ተኛ ክፍል ዘሎ ዲግሪ ከዲግሪ በኋላ 12 ክፍል ከዛም  የተጭበረበረ  PHD   😁

ከታች  ስለተሰጠው የውሸት ዲግሪ  በ1996 12 ኛ ክፍል እንደነበር  የሚያሳዩትን ቪዲዮችን ተመልከቱ ።

©  zemedkun

@zekidanemeheret
2_5336933809482900763.mp4
3.1 MB
አንጀት ለመብላት ሲል ይሄ ከፊታችሁ ቆሞ ዕጣ የወደቀበት ሰው  ምናምን እያለ የሚሰክሰውን ትታቹ ከንግግሩ መውሰድ ያለብንን ጭብጥ እንመልከት እሱም

አብይ አህመድ  የተማረው እስከ 7ተኛ ክፍል ድረስ መሆኑ ከ7ተኛ ክፍል በኋላ ያሳለፈውን ሕይወት ሊነግረን እንደማይፈልግ ።  እኛኑ መልሶ  ከ7ተኛ ክፍል በኋላ ያለውን ሕይወቴን ታውቁታላችሁ ሲለን  ስለ ሃይስኩል  ስለ 8፣ 9፣ 10፣ 11፣ 12ተኛ ክፍል ያለው ማንነቱን የደበቀበትን ንግግሩ

@zekidanemeheret
2_5326002400455042671.mp4
2.3 MB
አብይ አህመድ ስለ ውልደትና እድገቱ ከመዓዛ ብሩ ጋር የነበረው ቆይታ

@zekidanemeheret
2_5328034229223695559.mp4
1.4 MB
አብይ ስለ ሩዋንዳ ቆይታው ከተናገረው

@zekidanemeheret