ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
799 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሶምሶን (መስፍነ እስራኤል) ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል †††

††† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል:-

*ከ7ቱ ሊቃናት አንዱ::
*በራማ አርባብ በሚባሉ 10 ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ::
*በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና::
*ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ::
*ሠለስቱ ደቂቅን : ዳንኤልን : ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::

ከምንም በላይ ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱን መልዐክ "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጉዋሜ "አምላክ ወሰብእ - እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::

መልዐኩ እመቤታችንን ከመጸነሷ ጀምሮ ባይለያትም መጋቢት 29 ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ አብስሯታል:: ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በማግስቱ በድምቀት እንዲከበር በወሰኑት መሠረት ዛሬ (በ30) ይከበራል::

††† ሶምሶን ረዓይታዊ †††

†††  እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን: ሀያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ: በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ: ነቢይና ካህን አድርጐ: ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው::

አባታችን አዳም ግን ስህተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በኋላም ለ100 ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድህነትን ሰጠው::

ስለዚህም ምክንያት ለ5,500 ዓመታት ትንቢት ሲነገር: ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር: ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ: የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ::

ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ::

ከእርሱም ይስሐቅ: ከዚያም ያዕቆብ (ደጋጉ) ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ: በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ርሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው::

በዚያም ለ215 ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው::

ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ9 መቅሰፍት: በ10ኛ ሞተ በኩር: በ11ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ::

አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ:: እንዲህ እንዲህ እያለም ከኃያል ሰው ሶምሶን ረዓይታዊ ደረሱ:: ይኸውም ከዓለም ፍጥረት 4,200 ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው::

በጊዜው እሥራኤል ጣዖትን እያመለኩ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑት ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር:: የአካባቢው መንግስታት እነ አሞን: አማሌቅ: ኢሎፍሊ ስንኳ ያኔ ዛሬም ቢሆን እንደምትመለከቱት ዶሮና ጥሬ ናቸው::

በጊዜውም የእሥራኤል ኃጢአት ስለ በዛ ኢሎፍላውያን (ፍልስጤማውያን) 40 ዓመት በባርነት ገዟቸው:: ንስሃ ሲገቡ ደግሞ ልጅ በማጣት ያዘኑ ማኑሄ እና ሚስቱ (እንትኩይ) : በቅዱስ ሚካኤል ተበሥረው ኃያሉን ሶምሶንን ወለዱላቸው::

እርሱም ናዝራዊ (ከእናቱ ማኅጸን ለጌታ የተለየ) ነበርና ፍልስጤማውያንን ቀጥቶ ወገኖቹን እስራኤልን ከባርነት : በአምላኩ ኃይል ታደገ:: ከኃይሉ ብዛት የተነሳም:-
¤አንበሳን እንደ ጠቦት ይገድል (መሣ. 14:5)
¤300 ቀበሮዎችን አባሮ ይይዝ (መሣ. 15:3)
¤በብርቱ ገመዶች ሲያስሩት እንደ ፈትል ይበጣጥሰው (መሣ. 15:14)
¤በአህያ መንጋጋ ሽህ ሰው ይገድል (መሣ. 15:15)
¤ጠባቂዎችን ከነ መቃናቸው ተሸክሞ ይወረውር ነበር:: (መሣ. 16:3)

ውኃ ሲጠማውም ከአህያ መንጋጋ ላይ ፈልቆለት ጠጥቷል:: (መሣ. 15:18) በፍጻሜው ግን ደሊላ በምትባል ሴት ተታልሎ ምሥጢሩን በመግለጡና ጸጉሩ በመላጨቱ ኃይሉን አጥቷል:: ጠላቶቹም ዐይኑን አውጥተው መዘባበቻ አድርገውታል::

በፍጻሜው ግን ኃይሉ እንዲመለስለት ፈጣሪውን ለምኖ : አሕዛብ ለጣኦት በዓል እንደተሰበሰቡ የአዳራሹን ምሰሶ አፍርሶ አጥፍቷቸው ዐርፏል:: (መሣ. 13--16)
ቅዱስ ሶምሶን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ (ምሳሌ) ነው::

†††  "ክፉ ናችሁ: ኃጢአታችሁ በዝቷል" የማይል ጌታ በመከራችን ሁሉ ተራዳኢ መልዐክን (ቅዱስ ገብርኤልን) ይዘዝልን:: ወርኀ መጋቢትን በሰላም እንዳስፈጸመ ወርኀ ሚያዝያን በምሕረቱ ይባርክልን::

††† መጋቢት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (እመቤታችንን ያበሠረበት መታሠቢያ)
2.ቅዱስ ሶምሶን (መስፍነ እስራኤል)
3.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ (ፍልሠቱ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘአክሱም (ድርሳነ ሚካኤልን መጻፉ የሚነገርለት አባት)
5.እግዚአብሔር ውሃን ከ3 ከፈለው (ጠፈርን ፈጠረ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
3.አባ ሣሉሲ ክቡር
4.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
5.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

††† ". . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም . . ." †††
(ዳን. 9:20)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
የሥነ ፍጥረት ፪ኛ ቀን

=>ቸሩ እግዚአብሔር በዚህች ቀን ውሃን ከ፫ ከፈለ፤ ጠፈርንም ፈጠረ፡፡ (ዘፍ. ፩፤ አክሲማሮስ)

" ቸርነቱ ፈጥኖ ይደረግልንና!


" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​መጋቢት 30/07/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፻፭፥፲፪(105፥12)
ወተአመኑ በቃሉ
ወሰብሕዎ በስብሐቲሁ
ወአፍጠኑ ረሲዐ ምግባሩ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘማርቆስ ፲፮፥፲፪-፲፭(16፥12-15)
ወእምዝ አስተርአዮሙ ለ፪ቱ...

ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብእ ዕብራውያን ፲፩፥፴፪-፴፭(11፥32-35)
ምንተ እንከ እብል…

👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፪ ም ፫፥፫-፮(3÷3-6)
ወዘንተኒ ቅድሙ አእምሮ…

👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፪፥፮-፲፰(12÷6-18)
ወበይእቲ ሌሊት እንተ ጸቢሖ…

📜ምስባክ ዘቅዳሴ

በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ
ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ
ወእገኒ ለስምከ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፴፯ ቊ. ፩ - ፪

፩ አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሁሉ ሰምተኸኛልና፤ በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።

፪ በቤተ መቅደስህም እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህም ስምህን አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።




📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የሉቃስ ወንጌል ም. ፩ ቊ. ፳፮ - ፴፱
ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ...

📜ቅዳሴ


👉ግሩም አው ዘእግዝእትነ




☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
#ንጉሥ_በአህያ_ላይ
(ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ)

"አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት።  የዚህች  በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው።  በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣  ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት።
ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት።

ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ  በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ። 

ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

"የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን  እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት  ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት?

ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም።

እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን  ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል።  መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም ሥልጣኑ እያላቸው  በትሕትና "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን።

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

https://t.me/zekidanemeheret
#ሆሳዕና
(የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት)

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራ ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በክብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡

በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተዋቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡

#ለምን_ዘንባባ_ያዙ_ቢባል፡-
ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም ሕያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡

#የተምር_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡-
ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው
ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አንተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምሥጢር አንተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡-
ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡

#ልብሳቸውንም_ማንጠፋቸው፡-
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡

#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡…..
ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል።

#መልዕክታት
ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡  (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ግብረ_ሐዋርያት
የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እነሆም÷   (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ምስባክ
"ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3
ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡
ወይም
"እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2
ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡

#ወንጌል
ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

ቅዳሴ ፡- ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡

https://t.me/zekidanemeheret
#ሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደስታ የምታስገኝ ሐዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ሕያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባሕርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው እኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳዕና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በኃጥያት የመረረውን ሕይወታችንን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪይ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪይ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንተ ባህሪይ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ኃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ሕይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ጊዜ የወይራ ዘይት ለመሥዋዕትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡

#ሼር

👉ለመቀላቀል 👇👇👇@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
††† እንኳን ከተባረከ ወር ሚያዝያ እና ከጻድቁ አባታችን ቅዱስ ስልዋኖስ ወቅዱስ አሮን ካህን ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ስልዋኖስ †††

††† ጻድቁ አባ ስልዋኖስ ግብፃዊ ሲሆኑ ከታላቁ መቃርስ መንፈሳዊ ልጆች አንዱ ናቸው:: ገና በሕጻንነታቸው ወደ ገዳም ገብተው ጾምን : ጸሎትን : ትሕርምትን ገንዘብ በማድረግ ታላቅ የንጽሕና ሰው ሁነዋል::

ከመካከለኛ እድሜአቸው ጀምረው ደግሞ የገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በመልካም እረኝነት አገልግለዋል:: ጻድቁን ለየት የሚያደርጉዋቸው አንዳንድ ተግባራት ነበሩ::

እርሳቸውን ጨምሮ ሁሉም ገዳማዊ ከጾምና ከጸሎት ባሻገር ሥራ ሠርቶ ማታ መመጽወት አለበት:: ያ ማለት ያለ ምጽዋት ውሎ ማደር አይፈቀድም ነበር:: ይሕም መነኮሳቱን ከጽድቅ ባለፈ ታታሪና ባተሌ አድርጉዋቸዋል::

አባ ስልዋኖስ በተሰጣቸው ጸጋ መላእክትን : ገነትና ሲዖልን ያዩ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ስለ ኃጥአን ከማልቀስ ዐይናቸው ቦዝኖ አያውቅም:: የዚሕን ዓለም ብርሃን አላይም ብለው ቆባቸውን ዓይናቸው ላይ ጥለው በመልካም ሽምግልና በዚሕች ቀን አርፈዋል::

††† አምላካችን ከጻድቁ በረከት ያሳትፈን::

††† ቅዱስ አሮን ካህን †††

††† ቅዱስ አሮን:-
~የሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ወንድም::
~የነቢዪት ማርያም ታናሽ::
~የዮካብድና ዕንበረም ልጅ::
~የእግዚአብሔር ካህን እና
~የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት ነው::

††† እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የነበረው የክህነት አገልግሎት ከእርሱ ዘር እንዳይወጣ ምሎለታል:: ዳታን : አቤሮንና ቆሬ ይህንን ቢቃወሙ ከነ ሕይወታቸው መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች:: በድፍረት "እናጥናለን" ብለው ወደ ደብተራ ኦሪት የገቡትንም እሳት ከሰማይ ወርዶ በልቷቸዋል::

ቅዱስ አሮንም በጌታ ትእዛዝ በትሩ ለምልማ : አብባና አፍርታ ተገኝታለች:: ይህም ለጊዜው ክህነት ከሱ ልጆች እንዳይወጣ ሲያደርግ በፍጻሜው ለድንግል ማርያም ምሳሌ ሆኗል::

የአሮን በትር ሳይተክሏት : ሳይደክሙባትና ውሃ ሳያጠጣት አብባና አፍርታ እንደተገኘች ድንግል ማርያምም የወንድ ዘር ምክንያት ሳይሆናት ፍሬ አፍርታለች (ክርስቶስን ወልዳለችና)::

††† አባ ሕርያቆስ "ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን:: ወዓዲ በትር እንተ ሠረጸት : ወጸገየት : ወፈረየት" እንዳለ:: (ቅዳሴ ማርያም)

ቅዱስ አሮን በማዕጠንቱና በመስዋዕቱ ፈጣሪውን አገልግሎ : ድውያንንም ፈውሶ : እስራኤል በበርሃ ሳሉ አርፎ ተቀብሯል:: (ዘኁ. 20:25)
(ለተጨማሪ ንባብ 3ቱን ብሔረ ኦሪት (ከኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ 4 ጀምረው እስከ ኦሪት ዘኁልቁ ምዕራፍ 20 ድረስ) ያንብቡ)

††† ክብሩ : በረከቱ ይደርብን::

††† ሚያዝያ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አሮን ካህን (የሊቀ ነቢያት ሙሴ ወንድም)
2.አባ ስልዋኖስ ጻድቅ
3.ቅዱሳን መነኮሳት
4.ቅድስት መጥሮንያ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

††† "ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል:: እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም::" †††
(ዕብ. 5:3)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
የሥነ ፍጥረት 3ኛ ቀን

=>በዚህ ቀን እግዚአብሔር 3 ፍጥረታትን፡-
1.አዝርዕትን
2.አትክልትን
3.እጽዋትን . . . ፈጥሯል::

=>እነዚህ ለሰው ልጅ ሁሉ ምግበ-ሥጋ : ምግበ-ነፍስ ናቸው::
"ወኩሉ ዘተፈጥረ ለመፍቅደ ነባብያን" እንዳለ አረጋዊ መንፈሳዊ:: (መጽሐፈ መነኮሳት ካልዕ)

የእግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን !!