ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት አሸገ፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት መታሸጉን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በፌስቡክ ገጽ አስነብቧል።

በትናንትናው ዕለት 3ቱ አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመናድ እና ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለመከፋፈል በማቀድ 26 መነኮሳትን ሾመናል በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
አንዲት ቤተ ክርስቲያን!
አንድ ሲኖዶስ!
አንድ ፓትርያርክ!
አንድ የሹመት ሥርዐት!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ቀኖናዊት ናት!

++++++++++++++++++++++
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የሰጠውን የመኖሪያ ቤት ውል አቋረጠ ቤቱንም አሸገ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ከጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠ ትዕዛዝ የተሰጣቸውን ከድርጅቱ የተሰጣቸውን መኖሪያ ቤት ውል በማቋረጥ ቤቱን ተረክቧል።

ድርጅቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ሕገ ወጥ መንገድ የቤተክርስቲያናችንን ቀኖናና ሕግጋት በመጣስ በትላንትናው እለት የተሰጠውን ሕገ ወጥ ሹመት ተከትሎ ዋነኛ አስተባባሪና ተሿሚ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ ነው።

ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የሚዛን ቴፒ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ቢሮ መታሸጉ ተገለጸ።


በነ 'አባ' ሳዊሮስ ሕገ ወጥ ሹመት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው የተሾሙት የሚዛን ቴፒ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አባ ሚካኤል ገብረ ማርያም ቢሮ መታሸጉ ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት የሿሚዎቹን ጳጳሳት ማረፊያ ቤትን ጨምሮ የተሿሚዎች ቢሮዎች እየታሸጉ መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል።
ኢ-ቀኖናዊ በሆነ መልኩ የተፈጸመውን ''ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት'' አስመልክቶ ከሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ
https://t.me/zekidanemeheret

🕐 ​ጥር 17/05/2015 ዓ.ም🕖

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፳፭፥፮-፯(25፥6-7)
ወአዐውድ ምሥዋዒከ እግዚኦ
ከመ እስማዕ ቃለ ስብሐቲከ
ወከመ እንግር ኵሎ መንክረከ

📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፩፥፳፬-፳፱(1፥24-29)
ወእለሰ ተፈነዉ...

ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፪ ም ፰፥፲፮-፳፬(8፥16-24)
እኩት እግዚአብሔር ዘወሀበነ ለነሂ...

👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፫፥፰-፲፭(3፥8-15)
ወማኅለቅቱሰ ለኵሉ...

👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፱፥፰-፲፩(19÷8-11)
ወቦአ ጳውሎስ ምኵራብ...

📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአከ
ከመ ይዕቀቡከ በኵሉ ፍናዊከ
ወበእደዊሆሙ ያነሥኡከ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፺ ቊ. ፲፩ - ፲፪

፲፩ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤

፲፪ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።


📜ወንጌል ዘቅዳሴ

ዓዲ፦ የማቴዎስ ወንጌል ም. ፭ ቊ.፩ - ፲፯
ወሶበ ርእየ ብዙኃነ ዐርገ ውስተ ደብር..

የማርቆስ ወንጌል ም. ፲፮ ቊ.፲፱ - ፳
ወእግዚእነሰ ኢየሱስ እምድኅረ...

📜ቅዳሴ


👉ዘዲዮስቆሮስ


☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

✞✞✞ ጥር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

" አበዊነ መክሲሞስ ወዱማቴዎስ "

=>እኒህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ በቤተ
ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ተወዳጅ አባቶች ናቸው::
ስንጠራቸውም "አበዊነ
ቅዱሳን: ወክቡራን: ሮማውያን: መስተጋድላን:
ወከዋክብት ብሩሃን" ብለን ነው::

+ይኸውም "እንደ ንጋት ኮከብ የምታበሩ: ተጋዳይ:
ቅዱሳንና ክቡራን የሆናችሁ ሮማውያን አባቶቻችን" ማለት
ነው:: ሃገረ
ሙላዳቸው ሮም ሁና አባታቸው ንጉሥ ለውንድዮስ
ይባላል::

+ይህ ንጉሥ ሮምን በምታክል ታላቅ ሃገር በ4ኛው መቶ
ክ/ዘመን ነግሦ ሳለ መልካም ሰው ሆኖ ተገኝቷል::
ከመልካም ሚስቱ
(ንግሥቲቱ) ከወለዳቸው መካከልም 2ቱ ከዋክብት
ይጠቀሳሉ:: 2ቱ ቅዱሳን በአጭር የጊዜ ልዩነት የተወለዱ
በመሆናቸው
እንደ መንትያ ይቆጠራሉ::

+ንጉሡ ለውንድዮስም ከእግዚአብሔር ዘንድ ላገኛቸው
ልጆቹ ስም ሲያወጣ ታላቁን መክሲሞስ: ታናሹን ደግሞ
ዱማቴዎስ
ብሎታል:: ቅዱሳኑ በንጉሥ አባታቸው መልካም ፈቃድ
ክርስትናን ተምረዋል::

+ምንም እንኳ የንጉሥ ልጆች እና ልዑላን ቢሆኑም
ተቀማጥለው አላደጉም:: ምቾት ብዙዎችን አጥፍቷልና::
ይህንን የተረዳ
አባታቸው ሞገስን በፈጣሪያቸው ዘንድ እንዲያገኙ እንዲህ
በበጐ ጐዳና አሳደጋቸው::

+ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ካደጉና ለአካለ መጠን
ከደረሱ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ ይተጉ ነበር::
በተለይ
ዜና ቅዱሳንን ከማንበብ አይጠግቡም ነበር::
እግዚአብሔርንም በፍቅር እያመለኩ በጾምና በጸሎት
ይገዙለት ነበር::

+ቅዱሳኑንም ለየት የሚያደርጋቸው አንዱ ይሔው ነው::
ወርቅና ብር በፊታቸው ፈሶ: በእግራቸው እየረገጡት:
አገሩና ምድሩ
እየሰገደላቸው: የላመ የጣመ ምግብ እየቀረበላቸው:
የሞቀ የደመቀ መኝታ እየተነጠፈላቸው . . . ሁሉንም ስለ
ፍቅረ
ክርስቶስ መናቃቸው ይደነቃል::

+እነርሱ በክርስቶስ ፍቅር ሆነው የዚህን ዓለም ጣዕም
ንቀዋልና የአባታቸውን ቤተ መንግስት ሊተዉ አሰቡ::
አሳባቸው
ደግሞ በመመካከር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት:
እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንዲሉ
አበው
በጌታ መሪነት ነው::

+ወደ በርሃ ሔደው ለፈጣሪ ለመገዛት ሲያስቡ መውጫ
መንገዳቸውን ይሹ ነበርና አንድ ጐዳና ተገለጠላቸው::
ከዚያም ለንጉሥ
አባታቸው ሔደው "አባ! እኛ ወደ ኒቅያ (ታናሽ እስያ)
ሔደን መባረክ እንፈልጋለን" ሲሉ ጠየቁት::

+ወቅቱ ቦታዋ ስለ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ሞገስን
ያገኘችበት ጊዜ ነበር:: አባታቸውም መንፈሳዊ ሰው ነበርና
ደስ
እያለው ፈቀደላቸው:: ብዙ ወርቅን ሰጥቶ: ሸልሞ ከብዙ
ሠራዊት ጋር ሸኛቸው::

+ቅዱሳኑ መክሲሞስና ዱማቴዎስም ለጥቂት ጊዜ
በኒቅያ ሲጸልዩና ሲባረኩ ሰነበቱ:: ቀጥለውም
የአባታቸውን ሰራዊት ሰብስበው
"እኛ ሱባኤ ልንይዝ ስለ ሆነ እንመጣለን" የሚል
ደብዳቤን ሰጥተው ወደ ሮም ሸኟቸው::

+ወታደሮችን ከሸኙ በኋላ ቅዱሳኑ በአካባቢው ወደ ሚገኝ
አንድ ገዳም ሒደው ለአንድ ደግ መናኝ ምሥጢራቸውን
ገለጹለት::
ልክ የንጉሡ ለውንድዮስ ልጆች መሆናቸውን ሲያውቅ
'አመንኩሰን' ያሉትን እንቢ አላቸው::

+"ለምን?" ሲሉት "ደጉን አባታችሁን ማሳዘን
አልፈልግም:: ግን ፈቃዳችሁ እንዲፈጸምላችሁ ወደ ሶርያ
ዝለቁ:: በዚያ
አባ አጋብዮስ የሚባል ጻድቅ ገዳማዊ ሰው ታገኛላችሁ"
ብሎ ወደ ሶርያ አሰናበታቸው::

+በምድረ ሮም: በተለይም በቤተ መንግስቱ አካባቢ የ2ቱ
ልዑላን መጥፋት (መሰወር) ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ
ተደረገ::
ንጉሡ አባታቸው በወታደሮቹ ዓለምን ቢያካልልም
ሊያገኛቸው አልቻለም:: እርሱ ፈጽሞ ሲያዝን እናታቸው
ፈጽማ መጽናናትን
እንቢ አለች::

+መክሲሞስና ዱማቴዎስ ግን ምድረ ሶርያ ገብተው
የጻድቁ አባ አጋብዮስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ:: በእርሱም
ዘንድ ለምናኔ
የሚያስፈልጉ በጐ ምግባራትንና ትሩፋትን ከተማሩ በኋላ
2ቱንም አመነኮሳቸው:: በዚያ ቦታም እየታዘዙ: ፈጣሪን
እያመለኩ:
በጾም: በጸሎትና በትህትና ኖሩ::

+አንድ ቀን ግን አባ አጋብዮስ ጠርቶ "ልጆቼ! ተባረኩ!
በእናንተ ምክንያት ደስ ብሎኛልና:: በዚህች ሌሊት
የመነኮሳት
ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ በራዕይ ተገልጦ: ልጆች
እንዲሆኑኝ ስጠኝ ብሎኛልና እኔ ሳርፍ ወደ ግብጽ ገዳመ
አስቄጥስ
እንድትሔዱ" አላቸው::

+አባ አጋብዮስ ካረፈ በኋላ ግን እንደ ትዕዛዙ
አልሔዱም:: ውዳሴ ከንቱን ይፈሩ ነበርና:: በዚያው
በምድረ ሶርያ ግን
በጥቂት ጊዜ: ገና በወጣትነት ከብቃት መዓርግ ስለ ደረሱ
በርካታ ተአምራትን ሠሩ:: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ
ሆኑ::

+ስም አጠራራቸውም ሶርያን መላት:: በዘመኑ
በአካባቢው አንድ ግዙፍ ዘንዶ ተነስቶ ሰውንም
እንስሶችንም ፈጃቸው::
ሕዝቡም ሒደው በቅዱሳኑ ፊት አለቀሱ:: ያን ጊዜ ቅዱስ
መክሲሞስ (ትልቁ) ክርታስ አውጥቶ "አንተ ዘንዶ ይህ
ክርታስ
ወደ አንተ ሲደርስ ከማደሪያህ ውጣ: ሙት: ወፎችም
ይብሉህ" ሲል ጻፈበት::

+"ሒዳችሁ በበሩ ጣሉት" አላቸው:: አንድ ደፋር ሰው
ተነስቶ ሰዎች ሁሉ እያዩት ወስዶ በዘንዶው መውጫ ላይ
ጣለው::
በቅጽበትም ዘንዶው ወጥቶ ሞተ:: አሞሮችም ተሰብስበው
በሉት:: ከዚህ ድንቅ ተአምር የተነሳ ሕዝቡ የቅዱሳኑን
አምላክ አከበረ::

+ከዚህ በተረፈም በቅዱሳኑ ስም ታላላቅ ተአምራት
ተደረጉ:: ርኩሳት መናፍስት ሁሉ ስማቸውን እየሰሙ
ይሸሹ ነበርና::
ድውያን እነሱ በሌሉበት ስማቸው ሲጠራላቸው ይፈወሱ
ነበር:: የአካባቢው ሰው ስማቸውን እየጠራ: በእነርሱም
እየተማጸነ
ከመከራው ሁሉ ይድን ነበርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሞገስ
ሆኑ::

+መርከበኞች ደግሞ ከማዕበል ለመዳን የቅዱሳኑን ስም
በጀልባዎቻቸው ላይ ይጽፉ ነበር:: አንድ ቀን ግን የንጉሡ
ለውንድዮስ ባለሟል ይህንን ጽሑፍ ተመልክቶ ስለ
ጠረጠረ መርከበኛውን በንጉሡ ፊት አቀረበው::

+ንጉሡም መርከበኛውን "የጻፍከው የማንን ስም ነው?"
ቢለው "በሶርያ የሚገኙ 2 ወንድማማች ቅዱሳን ስም
ነው" አለው::
ልጆቹ እንደ ሆኑ ገምቶ በመርከበኛው መሪነት
ንግሥቲቱንና ሴት ልጁን ላካቸው:: እነርሱ በሐዘን
ተሰብረው ነበርና::

+ወደ ሶርያ ወርደው ባገኟቸው ጊዜም ከናፍቆትና ደስታ
የተነሳ ታላቅ ጩኸትን እየጮሁ አለቀሱ:: "እንሒድ ወደ
ሮም"
ሲሏቸው ግን ቅዱሳኑ "የለም! እኛ የክርስቶስ ነን" ብለው
እንቢ ስላሏቸው እያዘኑ ተመለሱ:: ንጉሡ ግን ይህንን
ሲሰማ
ደስ አለው:: "እነርሱ የዚህን ዓለም ኃላፊነት ተረድተዋል"
ሲልም አወደሳቸው::

+በኋላ ግን "የሮሜ ሊቀ ዻዻሳት መሆን አለባችሁ"
የሚል ነገር ሲሰማ ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ
ከሶርያ ወጥተው ወደ
ግብጽ ወረዱ:: ከታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዘንድ ደርሰውም
ልጆቹ እንዲሆኑ ለመኑት::

+"ልጆቼ! በርሃ አይከብዳችሁም?" ቢላቸው "ግዴለም!"
አሉት:: በዚያም ከተራራው ሥር በዓት ሠርቶላቸው ለ3
ዓመታት
በአርምሞ ቆዩ:: አንድ ቀንም ቅዱሳኑ እየጸለዩ ከአፋቸው
የወጣ የብርሃን ምሰሶ ከመንበረ ጸባኦት ሲደርስ አይቶ
ታላቁ
መቃርስ አደነቀ::

+በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢም ጥር 14
ቀን ታላቁ ቅዱስ መክሲሞስ ዐረፈ:: በዕለቱም የሰማይ
ቅዱሳን ሁሉ
ወርደው እየዘመሩ ወሰዱት:: ከ3 ቀን በኋላ ደግሞ ቅዱስ
ዱማቴዎስ ዐረፈ::
+በተመሳሳይ ቅዱሳኑ ሲወስዱት 2ቱንም ቅዱሳን ታላቁ
መቃርስ በበዓታቸው ቀብሯቸዋል:: ቦታውም ደብረ
ብርስም (በርሞስ)
ተብሏል:: ትርጉሙም የሮማውያኑ ቅዱሳን ደብር እንደ
ማለት ነው::

✞አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም
ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን::
ክብራቸውንም አያጉድልብን::

✞ጥር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን እና ክቡራን የሚሆኑ አባቶቻችን "መክሲሞስ
እና ዱማቴዎስ"

በ 17 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

++"+ ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር
አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም::
ብቻዬን
ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን
አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ
ደስ
አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን
ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል:: +"+ (1ቆሮ. 13:4)

✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
ቡኖ በደሌ ተመደበ የተባለውን ሰው አላውቀው፤ አልቀበለውም የሚመጣ ካለ ኃላፊነቱን አልወስድም የለሁበትምም ብሏል።
ከዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም ሰበካ ጉባኤ ጽ/ ቤት የተሰጠ የአቋም መግለጫ
በምስካዬ ኅዙናን የሚገኘው የአባ ሳዊሮስ ቢሮ እና መገልገያ ቤቶች ታሽገዋል።