https://t.me/zekidanemeheret
🕐 መስከረም 05/01/2015 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፴፱፥፭(39፥5)
ብዙኅ ገበርከ እግዚኦ አምላኪየ መንክረከ
ወአልቦ ዘይመስሎ ለሕሊናከ
አይደዕኩ ወነገርኩ ወበዝኃ እምኈልቊ
📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፩፥፲፭-፳፭(1፥15-25)
ዮሐንስ ሰማዕቱ በእንቲአሁ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ጢሞቴዎስ ፩ ም ፭፥፩-፯(5፥1-7)
ሊቃናተ ኢታመጕጽ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፫፥፭-፲(3፥5-10)
ወከማሁ ትካትኒ ቅዱሳት አንስት…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፲፮፥፰-፲፮(16፥8-16)
ወሐሊፎሙ እምነ ሚስያ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
አዋልደ ንግሥት ለክብርከ
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፱
፱ የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፫ ቊ. ፴፩ - ፵፬
ካልእተ ምሳሌ አምጽአ ሎሙ...
📜ቅዳሴ
👉ዘሠለስቱ ምዕት (ግሩም)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️

እንዴት አላችሁ ነገ ማታ 3 ሰዓት ላይ በ online ለምትከታተሉ ክርስቲያናዊ ሥነምግባር ማጠቃለያ ፈተና ስላላችሁ እንድትዘጋጁ ይሁን።
👉ቅዳሜ ማታ 3 ሰዓት ላይ ደግሞ ሥርዓተ ጸሎት ከክፍል 1-4 ፈተና ስለሚኖራችሁ ተዘጋጁ።

🛑 ክርስቲያናዊ ሥነምግባር 🛑
ክፍል1👉https://t.me/zekidanemeheret/3566
ክፍል2👉https://t.me/zekidanemeheret/3601
ክፍል3👉https://t.me/zekidanemeheret/3634
ክፍል 4👉https://t.me/zekidanemeheret/3665
ክፍል 5👉https://t.me/zekidanemeheret/3722
ክፍል 6👉https://t.me/zekidanemeheret/3755
ክፍል 7👉https://t.me/zekidanemeheret/3794
ክፍል 8👉https://t.me/zekidanemeheret/3822
👉@zekidanemeheret
ክፍል1👉https://t.me/zekidanemeheret/3566
ክፍል2👉https://t.me/zekidanemeheret/3601
ክፍል3👉https://t.me/zekidanemeheret/3634
ክፍል 4👉https://t.me/zekidanemeheret/3665
ክፍል 5👉https://t.me/zekidanemeheret/3722
ክፍል 6👉https://t.me/zekidanemeheret/3755
ክፍል 7👉https://t.me/zekidanemeheret/3794
ክፍል 8👉https://t.me/zekidanemeheret/3822
👉@zekidanemeheret
Telegram
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/
✝"" ክርስቲያናዊ ሥነምግባር - ✝
🛑 ክፍል ፩🛑
(ሐምሌ 4 - 2014 ዓ.ም)
🕊https://t.me/zekidanemeheret
✝"" ክርስቲያናዊ ሥነምግባር - ✝
🛑 ክፍል ፩🛑
(ሐምሌ 4 - 2014 ዓ.ም)
🕊https://t.me/zekidanemeheret
‹‹‹‹ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤››››
መስከረም 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+" ቅዱስ ኢሳይያስ ነቢይ "+
+በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የኢሳይያስን ያህል ትንቢት የተናገረ ነቢይ አይገኝም:: ከትንቢቱ ብዛትና ከምስጢሩ ጉልህነት የተነሳ: አንድም ደፋር ስለ ነበር 'ልዑለ ቃል' ተብሎ ተጠርቷል:: ቅዱስ ኢሳይያስ የተወለደው ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመታት በፊት ሲሆን ለነቢይነት የተመረጠው ገና በወጣትነቱ ነበር::
+ወላጆቹ 'ኢሳይያስ' (መድኃኒት) ያሉት በትምሕርቱ: በትንቢቱ የጸጋ መድኃኒትነት ስላለው ነው:: እርሱ በነቢይነት በተሾመበት ወራት ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ: ንጉሡ ደግሞ ዖዝያን ይባሉ ነበር:: በሊቀ ካህናቱና በንጉሡ መካከል በተነሳ ጠብ ንጉሡ የበላይነቱን ለማሳየት ሃብተ ክህነት ሳይኖረው ሊያጥን ወደ ቤተ መቅደስ ገባ::
+ይህንን የተመለከተው ኢሳይያስ ሊገስጸው ሲገባ 'ወዳጄ ነው' በሚል ዝም አለው:: ፈታሒ እግዚአብሔር ግን ዖዝያንን በለምጽ መታው:: የግንባሩን ለምጽ በሻሽ ቢሸፍነው ከሻሹ ላይ ወጣበት:: በእሥራኤል ለምጽ ያለበት እንኩዋን በዙፋን ከተማ ውስጥም መቀመጥ አይችልምና አስወጡት:: በእርሱ ፈንታም ኢዮአታም ነግሷል::
+ኢሳይያስ ደግሞ እግዚአብሔር በሰጠው አንደበት ሙያ አልሠራበትምና ከንፈሩ ላይ ለምጽ ወጣበት:: እርሱንም ወስደው ጨለማ ቤት ዘጉበት:: ሃብተ ትንቢቱንም ተቀማ:: ቅዱሳን ትልቁ ሃብታቸው ንስሃቸው ነውና በዚያው ሆኖ ንስሃ ገባ: ተማለለ: ጾመ: ጸለየ::
+እግዚአብሔርም ንስሃውን ተመለከተለት:: ከዚያም ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት ኢሳይያስ እግዚአብሔርን በረዥም (ልዑል) ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ: ኪሩቤል ተሸክመውት: ሱራፌል (24ቱ ካህናተ ሰማይ) "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ሲያመሰግኑት ተመለከተ:: (ኢሳ. 6:1)
+አበው ሲተረጉሙ "አንተ ያፈርከው ዖዝያን እነሆ ሞተ:: እኔ ግን መንግስቴ የዘለዓለም ነው" ሲለው ነው ይላሉ:: ያን ጊዜ እግዚአብሔር "ወደ ሕዝቤ ማንን እልካለሁ?" አለ:: ኢሳይያስም "ጌታየ! እኔ ከንፈሮቼ የረከሱ አለሁ" አለው:: እግዚአብሔርም ሱራፊን ላከለት:: መልአኩም ፍሕም (እሳት) በጉጠት አምጥቶ ከንፈሩን ቢዳስሰው ነጻ:: ሃብተ ትንቢቱም ተመለሰለት:: ይኸውም የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው::
+ከዚህች ቀን በኋላ ግን ኢሳይያስ የተለየ ሰው ሆነ:: ማንንም የማይፈራ እውነተኛ የልዑል ወታደር ሆነ:: ከኦዝያን በሁዋላ በየዘመናቸው 4ቱንም ነገሥታት ገሰጸ:: እነዚህም ኢዮአታም: አካዝ: ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው::
+ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት:: ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::
+ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ: ቅዱስ ስሙንም ተገዳደረ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::
+መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ::"
+በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ:: (1ነገ. 18:13, 19:1)
+ታላቁ ነቢይ ልዑለ ቃል ኢሳይያስ ሐረገ ትንቢትን ያፈስ ነበርና ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ "ድንግል ትጸንሳለች: ወንድ ልጅም ትወልዳለች" የሚል ነበር:: (ኢሳ. 7:14)
+በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ መካሪዎች ቀርበው ንጉሡን በውዳሴ ከንቱ ጠለፉት:: "ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ:: እንዳንተ ያለ ማንም የለም:: ነቢዩ የተናገረው ትንቢትም እኮ ላንተ ነው:: 'ድንግል' የተባለች ኢየሩሳሌም ስትሆን 'ወልድ-ወንድ ልጅ' የተባልክ ደግሞ አንተ ነህ" አሉት::
+ይሕንን ጠማማ ትርጉም እህ ብሎ የሰማቸው ቅዱስ ሕዝቅያስ አልወቀሳቸውም:: በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው:: ነቢዩም መጥቶ ንጉሡን አለው:- "ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ::"
+ወዲያውኑ ሕዝቅያስ ታመመ: ደከመ:: ንጉሡ ወደ ፈጣሪ:- "ጌታ ሆይ! እንደ ቸርነትሕ በፊትህ በቅን መንገድ መሔዴን አስብና ይቅር በለኝ" ሲል ተማጸነ:: ይህ ሲሆን ቅዱስ ኢሳይያስ ገና ከንጉሡ አካባቢ አልራቀም ነበርና የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ::
+ሕዝቅያስን በለው:- "ጸሎትህን ሰምቼ: ስለ ባለሟሌ ስለ ዳዊት ብየ ምሬሐለሁ:: በዘመንህም ላይ 15 ዓመታትን ጨምሬልሃለሁ በለው" አለው:: ነቢዩም ወደ ንጉሡ ተመልሶ ይሕንኑ ነግሮ "እስከ 3 ቀን ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ ድነህ ትመለሳለህ" አለው::
+ቅዱስ ሕዝቅያስ "ይሕ እንደሚደረግ በምን አውቃለሁ?" አለው:: ኢሳይያስም ፀሐይን ዓለም እያየ 10 መዓርጋትን ወደ ሁዋላ መለሳት::
+ልዑለ ቃል ቅዱስ ኢሳይያስ ለ70 ዘመናት ሕዝቡን አስተምሮ: ነገሥታቱን ገስጾ: 68 ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ጽፎ አረጀ:: በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ምናሴ ግን ይባስ ብሎ ጣዖትን አቆመ: ለጣዖትም ሰገደ:: ቅዱሱ ይህንን ሲያደርግ ዝም አላለውም:: በአደባባይ ገሰጸው እንጂ::
+በዚህ የተበሳጨ ምናሴም ሽማግሌውን ነቢይ በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው:: ቅዱስ ኢሳይያስ በዚህ ዓይነት ሞት በጐ ሕይወቱንና ሩጫውን ፈጸመ:: የተናገራቸው ትንቢቶች ግልጽ ስለ ሆኑ 'ደረቅ ሐዲስ' በመባል ይታወቃሉ::
+ቸሩ አምላክ 'ደሃ ተበደለ: ፍርድ ተጉዋደለ' የሚሉ መምሕራን አባቶችን አይንሳን:: ከነቢዩም በረከቱን ይክፈለን::
+መስከረም 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኢሳይያስ ነቢይ (ልዑለ ቃል)
2.ቅድስት ሰብልትንያ ሰማዕት
3.አባ ያዕቆብ ገዳማዊ
4.ቅዱስ አናቲሞስ ኤዺስ ቆዾስ
በ 06 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
++"+ ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር:: ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች:: እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች:: እሺ ብትሉ: ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ:: እንቢ ብትሉ ግን: ብታምጹም ሰይፍ ይበላቹሃል:: የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና:: +"+ (ኢሳ. 1:18)
‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››
(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
Photo
በዚህች ቀን የዋልድባው የአቡነ ሳሙኤል ዐፅማቸው ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ የፈለሰበት ዕለት ነው፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
🕐 መስከረም 06/01/2015 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፳፰፥፰(28፥8)
ቃለ እግዚአብሔር ያድለቀልቆ ለገዳም
ወያድለቀልቆ እግዚአብሔር ለሐቅለ ቃዴስ
ቃለ እግዚአብሔር ያጸንዖሙ ለኀየላት…
📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፫፥፩-፯(3፥1-7)
ወአመ ፲ወ፭ቱ ዓመተ መንግሥቱ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፱፥፳፭-፴፪(9፥25-32)
በከመ ይቤ ሆሴዕ ነቢይ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፪ ም ፩፥፲፱-፳፩(1፥19-21)
ወብነ ዓዲ ዘእምዝኒ ይቀድም…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፰፥፳፭-፴፩(28፥25-31)
ወቦ እለሂ አምንዎ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ
ኢትግሥሡ መሲሓንየ
ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፬ ቊ. ፲፬-፲፭
፲፬-፲፭ ...ስለ እነርሱም ነገሥታቱን ገሠጸ።
የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ም. ፲፪ ቊ. ፴፮ - ፶
ወዘንተ ብሂሎ እግዚእ ኢየሱስ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
🕐 መስከረም 06/01/2015 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፳፰፥፰(28፥8)
ቃለ እግዚአብሔር ያድለቀልቆ ለገዳም
ወያድለቀልቆ እግዚአብሔር ለሐቅለ ቃዴስ
ቃለ እግዚአብሔር ያጸንዖሙ ለኀየላት…
📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፫፥፩-፯(3፥1-7)
ወአመ ፲ወ፭ቱ ዓመተ መንግሥቱ…
ምንባባት ዘቅዳሴ
👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፱፥፳፭-፴፪(9፥25-32)
በከመ ይቤ ሆሴዕ ነቢይ…
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፪ ም ፩፥፲፱-፳፩(1፥19-21)
ወብነ ዓዲ ዘእምዝኒ ይቀድም…
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፰፥፳፭-፴፩(28፥25-31)
ወቦ እለሂ አምንዎ…
📜ምስባክ ዘቅዳሴ
ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ
ኢትግሥሡ መሲሓንየ
ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ
👉ትርጉም
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፬ ቊ. ፲፬-፲፭
፲፬-፲፭ ...ስለ እነርሱም ነገሥታቱን ገሠጸ።
የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።
📜ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ም. ፲፪ ቊ. ፴፮ - ፶
ወዘንተ ብሂሎ እግዚእ ኢየሱስ...
📜ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
☘️ ☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️ @zekidanemeheret ☘️
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️
የክረምት ኮርስ ክርስቲያናዊ ሥነምግባር ፈተና (50%)
ስማችሁን፦
ከተማችሁን፦
መልሳችሁን @zetaodokos
ላይ አስቀምጡ።
ትእዛዝ ➊ ትክክለኛ መልስ የያዘውን
ሆሄ ብቻ ምረጡ። (15%)
1.በጎ ለማድረግ አውቆ አለመሥራት ኃጢአት ነው?
ሀ. እውነት
ለ.ሐሰት
2.በክርስቲያናዊ ሥነምግባር አንድ ሰው የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ ሲል መዋሸት ይችላል?
ሀ. እውነት
ለ. ሐሰት
3. "እርሱ ያገኘው ከእኔ ተሽሎ አይደለምና የእርሱ የሆነው ለኔ ሊሆን ይገባል" ብሎ ማሰብ [አትመኝ]የሚለውን ትእዛዝ አያፈርስም።
ሀ. እውነት
ለ.ሐሰት
4.ፍችን ከሚፈቅዱት ሕጎች ውስጥ አንዱ መካንነት ነው።
ሀ.እውነት
ለ.ሐሰት
5.ክርስቲያን ማክበር ያለበት የጋብቻ ሕግ የቱን ነው?
ሀ.የራስ ሃይማኖት ተከታይ የሆነን ብቻ ማግባት
ለ.በክርስቲያናዊ ሥርዓት ጋብቻን መፈጸም
ሐ.ዝምድናን ማክበር
መ.ሁሉም
6.እግዚአብሔር አምላክ መጀመሪያ የጻፈው ትእዛዝ የትኛውን ነው?
ሀ.የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ
ለ.አባትህን እና እናትህን አክብር
ሐ.አትግደል
መ.ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አታምልክ
7. የጋብቻ መሠረታዊ ዓላማ የሆነው የቱ ነው?
ሀ.ከዝሙት ለመጠበቅ
ለ.በሚስት ላይ ለመሰልጠን
ሐ.አርፎ ለመብላት
መ.በማኅበረሰቡ ዘንድ ለመከበር
8.ቅዱሳን ስዕላት እንዲሳሉ እግዚአብሔር አምላክ አቅጣጫ የሰጠበት ጥቅስ የቱ ነው ❓
ሀ/ ዘጸ 37÷7
ለ/ 1ኛ ነገ 6÷23-29
ሐ/ ዘጸ 25÷19-20
መ/ ሁሉም
ሠ/መልስ አልተሰጠም
9.አንድ ሰው ክርስቲያናዊ ሥነምግባር እየሠራ ነው የምንለው ምን ሲያደርግ ነው?
ሀ.እንዳይታሰር በመፍራት ከሰው ጋር የማይጣላ ሲሆን
ለ.ለእግዚአብሔር የሚያስደስትን ነገር ብቻ ሚሠራ ሲሆን
ሐ.ሲሰጥ ብድርን እያሰበ የሚሰጥ ከሆነ
መ.ሁሉም
10.ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ.ከክርስቶስ
ለ.ለክርስቶስ
ሐ.እንደክርስቶስ
መ.ሁሉም
ሠ.መልስ አልተሰጠም
11.መጽሐፍ ቅዱስ ............ ያሉትን የሥጋ አባቶች ብሎ ይጠራቸዋል።
ሀ.በአንድ አይነት የኑሮ ወገን ለ.ካሕናት ሐ.አሳዳጊ(ሞግዚት) መ.ሀ እና ሐ
12.የዘማዊነት መንስኤ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ.የፍትወት ምስሎችን (ፊልሞችን) ማየት ለ.የጠበቀ የጾታ መቀራረብ
ሐ.ዘፈን መ.ሁሉም
13.የተገዢነት፣ የአክብሮት ፣ የትህትና መግለጫ የሆነው.................... ነው።
ሀ.ስግደት ለ.ጸሎት ሐ.ምጽዋት መ.እግዚአብሔርን መውደድ
14.ቅዱሳንን ማክበር ከእግዚአብሔር ውጪ የሆነ ልዩ አምልኮት ተብሎ አይቆጠርም።
ሀ.እውነት
ለ.ሐሰት
15.የእግዚአብሔር ወልድ ስም ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ.አማኑኤል ለ.ኢየሱስ ሐ.መሲህ መ.መልስ የለም
ትእዛዝ ➋ አዛምዱ (8%)
ሀ
16.እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠው ቀዳማዊ ትዕዛዝ
17.የሰው ሕይወት ሊድንበት የሚችል ነገርን መከልከል
18.አምልኮታችንን በተግባር የምንገልጽበት መንገድ
19.ስለንብረት መጠበቅ የተሰጠ ሕግ
20.የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ከምንጠራበት መንገድ
21.የጾታ ሕይወት በተቀደሰ ጋብቻ ተጠብቆ እንዲኖር የተሰጠ ሕግ
22.በተለየ ሁኔታ እድሜ የሚያስረዝም ትዕዛዝ
23.ስለሰው ልጆች ስማቸው ክብራቸው እንዲጠበቅ የተሰጠ ሕግ
ለ
ሀ.አታመንዝር ለ.ሰንበትን ማክበር ሐ.እናትና አባትን ማክበር መ.አትስረቅ
ሠ.ጸሎት
ረ.በሐሰት መማል ሰ.አትግደል
ሸ.በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር
ትእዛዝ ❸ በአጭሩ መልሱ።
24.ክርስቲያናዊ ሥነምግባር በመማራችሁ ያገኛችሁትን ጥቅም ከእውቀት አንጻር እና ከሕይወት አንጻር በሁለት ከፍላችሁ ጻፉ። (15%)
25.በ10ቱ ትእዛዛት ራሳችሁን መዝኑ። (15%)
መልስ ሠርታችሁ የምትልኩልኝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በፈለጋችኹት ሰዓት እስከ ነገ #አርብ_ማታ_3_ሰዓት ድረስ #ብቻ ይኾናል። ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ መላክ እንዳለመላክ ይቈጠራል።
(መልመጃውን ሠርቶ ለመላክ 24 ሰዓታት ተሰጥቷችኋል ማለት ነው።)
#አርብ_ማታ 3:30 ሰዓት ላይ ትክክለኛውን
መልስ እልክላችኋለሁ።

✝✝✝ እንኩዋን ለቅድስት ኤልሳቤጥ: ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ እና አባ ሳዊርያኖስ ክቡር ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
✝✝✝ ቅድስት ኤልሳቤጥ ✝✝✝
=>በወንጌላዊው አንደበት የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ ትውልዷ ከነገደ ሌዊ ነው:: ሐረገ ሙላዷም ከቅዱስ አሮን ካህን ወገን ይመዘዛል:: ከአሮን በቴክታና በጥሪቃ ወርዶ ሔርሜላ ላይ ይደርሳል::
+ይህቺ ሔርሜላ የምትባል ደግ ሴት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል የተባረከ ሰው አግብታ 3 ቡሩካት ልጆችን ወለደች:: የመጀመሪያዋን 'ማርያም' አሏት:: እርሷ ቅድስት ሰሎሜን ወለደች:: ሁለተኛዋን 'ሶፍያ' አሏት:: እርሷ ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች::
+ሦስተኛዋ ግን የተለየች ናት:: 'ሐና' ብለው ሰየሟት:: እርሷም የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ወለደች:: በዚህም መሠረት ድንግል ማርያም: ቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሰሎሜ የእህትማማች ልጆች ናቸው::
+ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ጊዜ ስም አጠራሩ የከበረ: ደግ ካህን ለሆነ: ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት:: እርሷ የሊቀ ካህናቱ ሚስት ናትና ክብሯ ከፍ ያለ ነበር:: ምንም ልጅ ባይኖራትም ዘወትር በጸሎትና በጾም: ምጽዋትንም በማዘውተር: ነዳያንንም በማሰብ የምትኖር እናትም ነበረች::
+ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
+ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ቅድስቲቷ መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች::
+ድንግል እመቤታችን ወደ እርሷ መጥታ 'ሰላም' ባለቻት ጊዜ ምንም ያሳደገቻት ልጇ ማለት ብትሆን: መንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላባት እመ ብርሃንን አመስግናታለች:: ቡርክት: ብጽእት: ከፍጥረተ ዓለሙ የከበረች መሆኗንም መስክራለች::
+በማሕጸኗ ያለ የ6 ወር ጽንስም የእመ አምላክን ድምጽ ቢሰማ በደስታ ዘሏል:: ለፈጣሪውም ስግደተ-ስባሔ አቅርቧል:: ቅድስት ኤልሳቤጥ አክላም "ወምንትኑ አነ ከመ ትምጽኢ ኀቤየ እሙ ለእግዚእየ-የጌታየ እናቱ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይገባኛል?" ስትል በትኅትና ተናግራለች:: ከጌታ እናት ጋር ለ3 ወራት በአንድ ቤት ቆይታለች::
+ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
+እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: ኤልሳቤጥ ማለት 'እግዚአብሔር መሐላየ ነው': አንድም 'የጌታ አገልጋይ' ማለት ነው::
+" ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ "+
=>ይህ አባት የተዋሕዶ ሃይማኖታችን ምሰሶ ነው:: በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ ተወልዶ አድጐ: በልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ: የምናኔ ሕይወትን መርጧል:: ቆይቶም የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ቄርሎስ ረድእ ሆኖ ተምሯል: አገልግሎታል::
+በጉባኤ ኤፌሶን ጊዜም ቅዱስ ቄርሎስን ተከትሎ ሒዶ ተሳትፏል:: በ444 ዓ/ም ታላቁን ሊቅ ተክቶ የእስክንድርያ 25ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሹሟል:: ለ7 ዓመታትም መጽሐፈ ቅዳሴውን (እምቅድመ ዓለምን) ጨምሮ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመልካም እረኝነትም ሕዝቡን ጠብቇል::
+ዘመነ ሰማዕታትን ተከትሎ የመጣው የመናፍቃን ዘመን ሲሆን ለ150 ዓመታት ያህል መናፍቃን እንደ አሸን ፈልተዋል:: በዚያው ልክ ከዋክብት ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና በየጊዜው ጉባኤያትን እየሠሩ: መናፍቃንን አሳፍረዋል:: ምዕመናንንም አጽንተዋል::
+በ451 ዓ/ም የተፈጸመው ድርጊት ግን ዛሬም ድረስ ጠባሳው የሚለቅ አልሃነም:: ንጉሡ መርቅያንና ዻዻሱ ልዮን የንስጥሮስን ትምሕርት አለባብሰው ሊያስተምሩ ሲሞክሩ ግጭት በመፈጠሩ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ 2 ተከፈለች::
+በጉባኤው የነበሩ 636 ዻዻሳት ስቃይና ሞትን ፈርተው በኑፋቄ መጽሐፍ ላይ በመፈረማቸው "መለካውያን" (ከእግዚአብሔር ይልቅ ለንጉሥ የሚታዘዙ) ተባሉ:: ጉባኤውም "ጉባኤ ከለባት" (የውሾች ስብሰባ): "ጉባኤ አብዳን" (የሰነፎች ጉባኤ) ተብሏል::
+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ግን "በኑፋቄው ላይ አልፈርምም" ከማለቱ አልፎ መናፍቃኑን አወገዛቸው:: በዚህ ምክንያት ወደ ጋግራ ደሴት ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋር አሳደዱት:: በዚያም ለ3 ዓመታት ቆይቶ በ454 ዓ/ም ዐረፈ::
+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ከማረፉ በፊት በተሰደደባት ደሴተ ጋግራ ለ3 ዓመታት ብዙ መከራ ከመናፍቃን ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱና በትምሕርቱ ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሷል::
+ቤተ ክርስቲያን እርሱን 'አበ ተዋሕዶ' (የተዋሕዶ እምነት አባትና አርበኛ) ትለዋለች:: የተነጨ ጺሙ: የረገፉ ጥርሶቹና የፈሰሰ ደሙ ዛሬም ድረስ ትልቅ ምስክርና የሃይማኖት ፍሬ ነውና::
"ያስተጻንዕ ህየ እለ ኀለዉ ደቂቀ:
ዘተነጽየ እምነ ጽሕሙ ወእም አስናኒሁ ዘወድቀ:
ፍሬ ሃይማኖቱ ፈነወ ብሔረ ርሑቀ" እንዲል::
+" ታላቁ አባ ሳዊርያኖስ "+
=>የዚህን ቅዱስ ሰው ስም የሚጠራ አፍ ክቡር ነው:: ጣዕመ ሕይወቱ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም:: እርሱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የበቀለ: 30: 60: 100 ፍሬዎችን ያፈራ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ነው:: በትውልድ ሮማዊ ሲሆን የተወለደው በ309 ዓ/ም ነው::
+ወላጆቹ በዚህ የንጉሥ ዘመዶች: በዚያ ደግሞ ባለጠጐች ነበሩ:: እነርሱ ለልጃቸው ጥበብን መርጠዋልና የግሪክን ፍልስፍና: የዮናናውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ:: ከዚያ በአንድ ልቡ ብሉይን: ሐዲስን ተምሮ ሲጠነቅቅ ወላጆቹ ዐረፉ::
+ቅዱሱ ሳዊርያኖስም "የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መስጠት አለብኝ" ብሎ ቀን ቀን ያለፈውን: ያገደመውን ሁሉ ሲያበላ: ሲያጠጣ: ነዳያንን ሲጐበኝ ይውላል:: ምሽት ሲል ደግሞ ወደ ቅዱሱ ንጉሥ (አኖሬዎስ) ቤተ መንግስት ገብቶ: ወገቡን ታጥቆ ከንጉሡ ጋር ሲጸልይና ሲሰግድ ያድራል::
+ውዳሴ ከንቱ ሲበዛበት ንብረቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ገብላ ወደምትባል ሃገር ሒዶ መነኮሰ:: ባጭር ጊዜም የብዙ ነፍሳት አባት ሆነ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: ትንሽ ቆይቶ ደግሞ የገብላ (ኤላ) ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: በዘመነ ሲመቱም እንቅልፍን አልተመለከተም:: ባጭር ታጥቆ ያላመኑትን ለማሳመን ደከመ እንጂ::

+ጌታ ከእርሱ ጋር ነውና አይሁድን: መተተኞችንና አሕዛብን ሁሉ አሳምኖ ኤላ (ገብላ) አንድ የክርስቶስ መንጋ ሆነች:: የሚገርመው ከደግነቱ የተነሳ ሰይጣንን እንዳይገባ ከልክሎት በመንገድ ላይ ቁሞ ሲያለቅስ ይታይ ነበር:: ቅዱስ ሳዊርያኖስ ብዙ ድርሳናትን ደርሶ: እልፍ ፍሬንም አፍርቶ: በተወለደ በ100 ዓመቱ በ408 ዓ/ም ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::
=>የእነዚህ ሁሉ ከዋክብት ቅዱሳን አምላክ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን:: ክፉውንም ሁሉ ያርቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>መስከረም 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ
2.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ (የተዋሕዶ ሃይማኖት አባት)
3.ታላቁ ቅዱስ ሳዊርያኖስ
4.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት-ልደቷ ነው)
5.ቅዱሳን አጋቶን: ዼጥሮስ: ዮሐንስ: አሞንና እናታቸው ራፊቃ (ሰማዕታት)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች:- 'አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማሕጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? . . . ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት:: +"+ (ሉቃ. 1:41)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

🌿🌿🌿የክረምት ኮርስ ክርስቲያናዊ ሥነምግባር ፈተና መልስ🌿🌿🌿
ሰላም ለኵልክሙ!
በኢትዮጵያ ሰዓት አቈጣጠር አኹን አርብ መስከረም 6 ማታ 3:30 ሰዓት ነው።
ትእዛዝ ➊ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ሆሄ ብቻ ምረጡ።
1. ሀ
2. ለ
3. ለ
4. ለ
5. መ
6. መ
7. ሀ
8. መ
9. ለ
10. መ
11.መ
12. መ
13. ሀ
14. ሀ
15. መ
❷ አዛምድ
16. ለ
17. ሰ
18. ሠ
19. መ
20. ረ
21. ሀ
22. ሐ
23. ሸ
ትእዛዝ ❸ በአጭሩ መልሱ።
ተራ ቁጥር 24 እና 25 እንዳመላለሳችሁ ውጤት ተሰጥቷል።
🌿 🌿 🌿 መልስ መስጫ 🌿 🌿 🌿