ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
ከዕረፍታቸው በኋላ የተደረጉ በርካታ ታላላቅ ተአምራት አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ እርሳቸው ካረፉ ከትንሽ ቀናት በኋላ በመቃብራቸው ላይ ዘይት ፈለቀ፡፡ ከዚያም በእንጨት በተሰራ መቅጃ እየተቀዳ ወደ ትልቅ መጠራቀምያ ገብቶ ለቤተ መቅደስ መብራት በ12 ተቅዋም ተደርጎ ከዓመት እስከ ዓመት ይበራ ጀመር፡፡ ከተጠራቀመ ዘይቱም ለታመሙ ይቀቡትና ከተለያዩ ሕመሞች ይድናሉ፡ ያዕ 5:14፡፡ ዳግመኛም ኤርትራ በሚገኙት በሌሎቹ በአባታችን ደብር ውስጥ ከብዙ ጊዜ በኋላ በደብረ ሣህል ደብራቸውና በደብረ ጽጌ ፈለቀ፡፡ ቅብዓ ኑጉም ለታመሙ ፈውስ እየሰጠ ለቤተ መቅደስም መብራት ሆነ፡፡

ዳግመኛም ከተደረጉት ተአምራት ውስጥ አንዱ እንደ ቤተክርስቲያን ሕግጋት ጻድቁ ካረፉ በኋላ ለጸሎትና ለኑዛዜ ሰዎች ተሰብስቦው እህል እና ውሃ ተዘጋጅቶ በነበረበት ሰዓት "በዚ ቀን ሁሉ ሰው ተገኝቶ ያለሥጋ ዋልን›› ሲሉ ሦስት የተለያዩ ሚዳቆዎች በአቡነ ዮናስ ጸሎት ድንገት መጥተው በሰዎቹ መሐል ተገኙ፡፡ ሰዎቹም ሚዳቆዎቹን አረደው በሉ፡፡

ጻድቁ በስማቸው የተገደሙ ገዳማት (ደብረ ድኁኃንበ-ቆሓይን፣ ደብረ ጽጌ ትምዛእ፣ ደብረ ጽዮን ዓዲ ወሰኽ፣ ደብረ ጸሪቅ ትግራይ፣ እና ደብረ ሣህል ዓረዛ) ይባላሉ፡፡

አቡነ ዮናስ ያረፉት መጋቢት 17 ቀን ሲሆን ይህ ወቅት ታላቁ ዐቢይ ጾም የሚውልበት ስለሆነ በዓለ ዕረፍታቸውን ጥር 21 ቀን እንዲያከብሩ ለልጆቻቸው አስቀድመው ነግረዋቸዋል፡፡ በመሆኑም በዚሁ ዕለት ጥር 21 ቀን በሁሉም ገዳማቸው ውስጥ በታላቅ ክብረ በዓል ታስበው ውለዋል፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)
"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"

#ቅዱስ_ፓሲዮስ
††† እንኳን ለቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኤስድሮስ †††

††† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው::
"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም:: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት::" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ!

በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

ቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮዽያዊውን የጐንደር ዘመን ሊቅ ጨምሮ በዚህ ስም የምትዘክራቸው አያሌ ቅዱሳንና ሊቃውንት አሏት::

ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ኤስድሮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ: ቅዱስ ፃና የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው: ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ::

በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር::
በመከራ ዘመን (ዘመነ-ሰማዕታት) ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል::

በዚህች ቀንም አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::

††† ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን::

††† መጋቢት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

††† "የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" †††
(መክ. 12:1-9)

††† "ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል:: እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ:: ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ:: ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ::" †††
(1ዼጥ. 4:7)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ pinned «"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።" #ቅዱስ_ፓሲዮስ»
#ዕለተ_ምጽአት (ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ)

አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ የተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ድጅም እንጸናለን እንጂ። አንተ ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም ብለሃልና።

በእለተ ምጽዓት አምላክ ሲመጣ ሦስት ጊዜ ታላቅ የሆነ የመለከት መነፋት ይሆናል። ይህ የመለከት ድምጽም ሙታንን ሁሉ የሚያነቃ ነው።

በመጀመሪያው አዋጅ መለከት ሲነፋ በዓለም ዳርቻ ሁሉ የተበተነ የሥጋ ትቢያ ይሰበሰባል። በላይ ያለውና በታች ያለው በባሕር ያለውና በየብስ ያለው በአራዊትም ሆድ ያለው በልዩ ልዩ ሞት ፈጽሞ ያረጀና የጠፋ በምድር ላይ የወደቀ የሥጋ ቅርፍትም ሁሉ ወደ ቀደመ መገናኛው ይሰበሰባል።

በሁለተኛው አዋጅ መለከት ሲነፋ አጥንቶች ከሥጋና ከደም ጋር ይያያዛሉ ያለመንቀሳቀስ ያለመናወጥም እስከ ጊዜው ድረስ ፍጹም በድን ይሆናል።

በሦስተኛው አዋጅ መለከት ሲነፋ ሙታን እንደ ዓይን ጥቅሻ ፈጥነው ይነሳሉ ጻጽቃንና ኃጥአን ክፉም ቢሆን በጎም በጎም ቢሆን በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ የሠሩትን ከምድር የተከተላቸውን ሥራቸውን ተሸክመው ይነሣሉ ጻድቃንን በቀኝ ኃጥአንንም በግራህ ታቆማለህ። ለመረጥካቸውም በምሥጋና ቃል ትናገራቸዋለህ እንዲህ ብለህ፥-

እናንተ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥተ ሰማያት ትወርሱ ዘንድ ወደ እኔ ኑ ብራብ አብልታችሁኛልና፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛልና፣ እንግዳ ብሆን አሳድራችሁኛልና፣ ብታረዝ አልብሳችሁኛልና፣ ብታመም ጎብኝታችሁኛልና፣ ብታሠር መጥታችሁ ጠይቃችሁኛልና በማለት (ማቴ. 25፥34-36) እንደተነገር ሁሉ ዳግመኛም ወደ ግራው ተመልሰህ በወቀሳ ቃል እንዲህ ትላቸዋለህ ብራብ አላበላችሁኝምና፣ ብጠማ አላጠጣችሁኝምና፣ እንግዳ ብሆን አላሳደራችሁኝምና፣ ብራቆት አላለበሳችሁኝምና፣ ብታመም አልጎበኛችሁኝምና፣ ብታሠር አልጠየቃችሁኝምና በማለት (ማቴ 25፥ 42-23) ያን ጊዜ ዓመጽና ሽንገላን ይናገር የነበረ አፍና አንደበት ሁሉ ይሸጋል። ያንጊዜ ኃዘን ይደረጋል፡ የማይጠቅም ኃዘን ነው። ያንጊዜ ጩኸት ይደረጋል የማይጠቅም ጩኸት ነው። ያንጊዜ ፍጅት ይሆናል የማይጠቅም ፍጅት ነው። ያንጊዜ ለቅሶ ይሆናል የማይጠቅም ለቅሶ ነው። የሚያስደነግጥ የነጐድጓድ ቃል የሚቆርጥና የሚከፍል የሚለይ ብርቱ ብልጭልጭታም ወደነርሱ ይላካል ይኸውም የኃጥአን ዕድላቸው ነው።

ያን ጊዜም ምድር አደራዋን ትመልሳለች እናትም የሴት ልጅዋን ጩኸት አትሰማም። ያን ጊዜ በሕይወትዋ ዘመን የሰራችው የነፍስ ሥራዋ ይገለጻል።

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ያን ጊዜ ትምረን ዘንድ ይቅርም ትለን ዘንድ በበላነው በቅዱስ ሥጋ በጠጣነው በክቡር ደምክ እንማጸንሃለን። ስለ እናት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ስለ ሁሉ ቅዱሳን መላእክት ጻድቃን ሰማህታት ነብያት ሐዋርያት እንዲሁም ደናግላን መነኮሳት እንማጸንሃለን። አምላክ ሆይ ያን ጊዜ ማረን እራራልንም ይቅርም በለን።

ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ
#መጋቢት_19

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች እለት #ሐዋርያ_አርስጥቦሎስ ሐዋርያ አረፈ፣ #ቅዱስ_አስከናፍርና የሚስቱ ማርታ የልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ፣ #የሰባቱ_ሰማዕታት መታሰቢያቸው ሆነ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አርስጦቦሎስ_ሐዋርያ

መጋቢት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች እለት የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር አርስጥቦሎስ ሐዋርያ አረፈ። እርሱም ጌታችን ከመረጣቸውና ከመከራው በፊት እንዲሰብኩ ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።

በሃምሳኛው ቀን በዓልም መንፈስ ቅዱስ በላዮ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ ሕይወት በሚገኝበት በወንጌል ትምህርት ሐዋርያትን ተከትሎ በመሔድ አገለገላቸው።

ብዙዎችንም ወደ ድኀነት መንገድ መልሶ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጥምቆ የአምላክን ሕግና ትእዛዝ ከማስጠበቁ የተነሣ ነፍሳቸውን አዳነ።

አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህን ቅዱስ አብራጣብያስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። ወደርሷም ሒዶ በውስጥዋ ወንጌልን ሰበከ ብዙዎቹንም በቀናች ሃይማኖት እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው።

በፊታቸውም ድንቆች ተአምራትን በማድረግ በሃይማኖት አጸናቸው ነገር ግን ከአይሁድና ከዮናናውያን ብዙ መከራ ደረሰበት።

ብዙ ጊዜም ወደ ፈረጆች አደባባይ ወስደው በደንጊያ ወገሩት ጌታችንም ከመከራው ሁሉ ጠብቆ አዳ ነው መልካም ተጋድሎውንም በፈጸመ ጊዜ በሰላም በፍቅር አረፈ። እነሆ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ሐዋርያ ጳውሎስ አስታውሶታል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አስከናፍር

በዚህችም ቀን ደግሞ ቅዱስ አስከናፍርና የሚስቱ ማርታ የልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ። ይህም አስከናፍር ብዙ ገንዘብ ያለው ባለጠጋ ነው ለእግዚአብሔርም ሕግ የሚጠነቀቅ ነበር ልጆቹንም መንፈሳዊ ምክርና ተግሣጽ በማስተማር አሳደጋቸው።

በአደጉም ጊዜ የጥበብንና የተግሣጽን ትምህርት እንዲማሩ ተይሩት ወደምትባል አገር ሰደዳቸውና ትምህርታቸውን በፈጸሙ ጊዜ ሊድራቸውና በሰርጋቸው ደስ ሊለው ሽቶ ያመጡአቸው ዘንድ ላከ በመርከብም ሁነው ሲመጡ ማዕበል ተነሥቶ መርከቡ ተሰበረ። እግዚአብሔርም ከስጥመት አድኖ በየብስ አወጣቸው ዮሐንስ የተባለውን በአንድ ቦታ ማዕበሉ አውጥቶ ጣለው።

ዮሐንስም ተስፋ በቆረጠ ጊዜ ወደ ቅዱሳን ገዳም ሒዶ መነኰሰ። ስለ ወንድሙ ስለአርቃድዮስም እንደሞተ ተጠራጥሮ በጸም በጸሎትና በስግደትም ሥጋውን አደከመ። አርቃድዮስም ወደ ዮርዳኖስ ገዳም ገብቶ ከአንድ ቅዱስ አረጋዊ ሰው ዘንድ መንኲሶ እየተጋደለ ሦስት ዓመት ኖረ።

አስከናፍር ግን ልጆቹ በማዕበል እንደሰጠሙ በሰማ ጊዜ ከሚስቱ ጋራ ማቅ ለብሰው አመድ አንጥፈው እያለቀሱ ተቀመጡ። በአንዲት ሌሊትም አስከናፍር በሕልሙ ልጁ ዮሐንስን በራሱ ላይ ከዕንቊ የተሠራ አክሊል ተቀዳጅቶ መስቀል ይዞ አየው።

አርቃድዮስንም በኮከብ አምሳል የሆነ አክሊል በራሱ ላይ ደፍቶ አየ ከእንቅልፉም ነቅቶ ለሚስቱ ያየውን ነገራት። ከዚያም በኋላ በየአድባራቱና በየገዳማቱ የልጆቻችንን ወሬ እንመረምር ዘንድ ተነሺ እንሒድ አላትና ወደ ዮርዳኖስ ሒደው ከመጥምቁ ዮሐንስ ገዳም ደረሱ።

ልጃቸውን አርቃዴዎስን ያመነኰሰውን አረጋዊ አባትን አገኙት ችግራቸውን ነገሩት እርሱም የክርስቶስ ወዳጆች አትዘኑ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመለሱ ልጆቻችሁን በሕይወት ታገኛላችሁ አላቸው ደስ እያላቸውም ተመለሱ።

ዮሐንስም በመስቀል በዓል ሊሳለም መጣ አረጋዊውም ጠርቶ ከአርቃድዮስ ከወንድሙ አገናኘው ተያይዘውም አለቀሱ። ደግሞ አስከናፍርን ከሚስቱ ጋራ ጠርቶ ከልጆቻቸው ጋራ አገናኛቸውና በላያቸው ወድቀው እየሳሟቸው አለቀሱ።

ከዚህ በኋላ ከዚያ አረጋዊ ዘንድ የምንኲስና ልብስ ለበሱ ሚስቱን ማርታንም ከሴቶች ገዳም አስገባት አገልጋዮችንም ነፃ አውጥቶ አሰናበተ። ገንዘቡንም ለድኆችና ለችግረኞች በተነ ከገዳምም ገብቶ በጾም በጸሎት ተወሰነ እንዲሁም የተባረኩ ልጆቹ በገደል በትሩፋት የተጠመዱ ሁነው ኖሩ ጌታችንንም ደስ አሰኙት በፍቅር አንድነትም አረፉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሰባቱ_ቅዱሳን_ሰማዕታት

በዚህችም ቀን ደግሞ የሰባቱ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ሆነ፡፡ እንርሱም የግብጽ ሰው እለእስክንድሮስና እስክንድሮስ ከጋዛ መንደር አጋብዮስ ከቡንጥስ ከተማ ኒሞላስ ከጠራልብስ ዲዮናስዮስ ሮሜሎስና ተላስዮስ ከግብጽ አውራጃዎች የሆኑ ናቸው።

እነርሱም በመንፈሳዊ ፍቅር ጸንተው ስለ ሃይማኖት ምስክሮች ሊሆኑ ተስማሙ። በፍልስጥዔም ውስጥ ወደ አለው ቂሣርያ ደርሰው በመኰንኑ ፍት ቆሙ።

በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማመናቸውን ገለጡ መኰንኑም በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃይቶ ገደላቸው። የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
Audio
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/

"" የቅዱሳን አበው ታሪክ -
🛑 ክፍል 1🛑

(መጋቢት 18- 2014 ዓ.ም)

ትላንት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰጠች ትምህርት ናት ከሆነ ሰዓት በኋላ ስልካችን ቦታ ስላልነበረው ብትቋረጥም እንደምንም ስሟት ትጠቅማችኋለች

https://t.me/zekidanemeheret
#መጋቢት_20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ሃያ በዚህችም ዕለት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #ጻድቅ_አልዓዛር ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ ላስነሳበት መታሰቢያ ነው፣ የእስክንድርያ ሃምሳ ሰባተኛ ሊቃነ ጳጳሳት የሆነ #ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ሚካኤል አረፈ፣የተመሰገነችና የከበረች ተጋዳይም የሆነች #ቅድስት_አስጠራጦኒቃ ስለ ክርስቶስ ምስክር ሁና ሞተች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አልዓዛር_ጻድቅ_ሐዋርያ

መጋቢት ሃያ በዚህችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ ሰው አልዓዛርን ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ አስነስቶት ነበርና ስለዚች ምልክት ገናናነት ብዙዎች አመኑበት።

ይህም ጻድቅ ሰው ከእስራኤል ልጆች ውስጥ ነው ማርያና ማርታ የተባሉ ሁለት እኅቶች አሉት። ማርያም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሸቱ የቀባችው ናት። እነርሱም ለጌታ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው ስለ ምግባራቸውም ጌታችን ይወዳቸዋል ሁሉም ያላገቡ ድናግል ናቸው። በሰው ወገን ሁሉ ላይ የተቆረጠና የተወሰነው ሰዎችም ሊጠጡት ያላቸው የሞት ጻዋን የሚጠጣበትና እጁን ለሞት የሚሰጥበት ለዚህ ጻድቅ ጊዜው ሲደርስ እርሱም እጁን በመስጠት አረፈ።

የክብር ባለቤት ጌታችን ግን የሚሠራውን ያውቃልና መጀመርያ ከሞት አላዳነውም ጠርቶ እስከሚአሥነሣው ድረስ ሙቶ በመቃብር አራት ቀን እንዲኖር በዚህ በአራት ቀንም የጻድቃንን ማደሪያዎችንና የኃጥአንን የሥቃይ ቦታዎች እንዲያይ ተወው እንጂ አላዳነውም ያን ጊዜም ታላቅ ምልክት ትሆናለች።

ከአራት ቀኖችም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ አልዓዛር አልዓዛር ና ውጣ ብሎ ከመቃብር ውስጥ ጠራው ያን ጊዜ አጆቹና እግሮቹ እንደታሠሩ ሙታኖችንም እንደሚጠቀልሏቸው በሰበን ፊቱ ተጠቅልሎ ወጣ።

እጆቹና እግሮቹ እንደ ተጠቀለሉና እንደ ታሠሩ ከመቃብር የመውጣቱ ምክንያት ሰዎች ሁሉ መሞቱን እንዲረዱ ሌሎችም ይህ በመካከላቸው በስምምነት የሆነ ነው ብለው እንዳያሰቡ። ስለዚህም እንደ ገነዙት ሁኖ እንዲወጣ ጌታችን አዘዘው ይችም ምልክት እንድትሆን።

ከሀዲዎችም በመቃብር ውስጥ ሕያው እንደ ነበር ቢያስቡም እጆቹና እግሮቹ ፊቱም እንደ ተጠቀለሉ እንዴት ይወጣ ነበር እኛ የክርስቲያን ወገኖች ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአራት ቀኖች በኋላ አልዓዛርን ያስነሣው እርሱ እንደሆነ እናምናለን። እንታመናለንም እርሱ በሥራው ሁሉ ላይ ችሎታ አለውና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሚካኤል_ሊቀ_ዻዻሳት

በዚህች ቀን በእስክንድርያ ከተሾሙ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃምሳ ሰባተኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል አረፈ።

ይህም አባት በሹመቱ ወራት ብዙ ኀዘንና መከራ ደረሰበት ጎሕ በሚባል አገር የተሾመ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ክብር የሚወድ አንድ ክፉ ኤጲስቆጶስ ነበረ። በሀገረ ስብከቱም ውስጥ ደነውስር በሚባል አገር ያሉ ምእመናን የቤተ ክርስቲያናቸውን ሕንፃዋን አደሱ ሊአከብሩዋትም በፈለጉ ጊዜ የአገር ታላላቆች ከእርሳቸው ሊባረኩ ወደው ሊቀ ጳጳሳቱና በአገሩ ዙሪያ ያሉትን ኤጲስቆጶሳት ልኮ እንዲአስመጣቸው ይህን ክፉ ኤጲስቆጶስ ለመኑት እርሱ ግን እምቢ አላቸው ልመናቸውን መቀበል አልወደደም።

እነርሱም በራሳቸው ፈቃድ ይህ ክፉ ኤጲስቆጶስ ሳይፈቅድ ሊቀ ጳጳሳቱንና ኤጲስቆጶሳቱን ሁሉ ልከው አስመጡአቸው። ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልና ኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ በመጡ ጊዜ ምሳ አዘጋጅላቸዋለሁ ብሎ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትቶአቸው ሔደ። ማርታ ማርታ ብዙ በማዘጋጀት ብዙ ትደክሚያለሽ ግን ጥቂቱ ይበቃል ያለውን የጌታችንን ቃል አላሰበም።

የቍርባን ጊዜ ሊያልፍ ስለሆነ ሊቃውንቱና ኤጲስቆጶሳቱ የቅዳሴውን ሥርዓት ይጀምር ዘንድ ሊቀ ጳጳሳቱን ለመኑት ግድ ባሉትም ጊዜ በሊቀ ጵጵስና ማዕረግና ክብር ተሠይሞ ተነሣ እርሱ ለሁሉ አባት የሆነ ሥልጣኑም ከሥልጣናቸው በላይ ነውና የቅዳሴውንም ሥርዓት ጀመረ።

ያ ክፉ ኤጲስቆጶስም በሰማ ጊዜ በልቡ ሰይጣን አደረበትና ተቆጥቶ መጣ። መሥዋዕቱንም ከመቅደስ ገብቶ ከጻሕሉ ውስጥ ነጥቆ ወደ ምድር ወረወረው ሊቀ ጳጳሳቱም ሌላ መሥዋዕት አምጡ ብሎ አዘዘ አምጥተውለትም ቀድሶ ለሕዝቡ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸውና አሰናበታቸውም።

በማግሥቱም ይህ አባት አባ ሚካኤል ሕዝቡን ሰበሰበ ከእርሱ ጋራ ያሉትንም ኤጲስቆጶሳት ካህናቱንና የምእመናንን አንድነት ሰብስቦ ይህን ክፉ ኤጲስቆጶስ ከሹመቱ ሽረው በእርሱ ፈንታ ሌላ ኤጲስቆጶስ ሾሙ።

ይህም ለአስቆሮቱ ሰው ለይሁዳ ሁለተኛው የሆነ የምስርን አገር ወደ ሚገዛ ስሙ አሕመድ ወልደ በጥሎን ወደተባለው ሹም ሔደ ይህን አባት አባ ሚካኤልን እንዲህ ሲል ነገር ሠራበት። በሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ ብዙ የወርቅና የብር ገንዘብ እንዳለ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት የወርቅና የብር ንዋየ ቅድሳትን የተመሉ እንደሆኑ መኰንን ሆይ ዕወቅ አለው።

መኰንኑም ይህን አባት ወደርሱ አስቀርቦ ንዋየ ቅድሳቱን እንዲሰጠው ፈለገ እርሱም ሥጋዬን እንደፈለግህ አድርግ ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር እጅ ናት በሎ ከለከለው። እጆቹንና እግሮቹን አሥረው በእሥር ቤት እንዲጥሉት አዘዘ በእሥር ቤትም ከአንድ ዓመት በላይ ኖረ በእሥር ቤት ውስጥ በኖረበት መጠን ከለምለም እንጀራና ከጨው ከበሰለ አተር በቀር ሳይበላ ሁል ጊዜ ይጾም ነበር።

ከዚህም በኋላ አንድ ጸሐፊ ምእመን ዮሐንስ የሚባል መጥቶ ለዚህ ለከበረ አባት አባ ሚካኤል ዋስ ሆነው ለመኰንኑ አባ ሚካኤል ሃያ ሽህ የወርቅ ዲናር እንዲሰጠው ሁኖ ከወህኒ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሔደ ጥቂት ቀን ተቀመጠ ታላላቆች ምእመናንና የአስቄጥስ ገዳም መነኰሳት ዐሥር ሽህ የወርቅ ዲናር ሰበሰቡ ደግሞ የእስክንድርያ አገር ሰዎች ከምድራቸው አንዱን ለዐሥር ሽህ ዲናር ሸጡ ሃያ ሽህ እስከሚሞላ ሰበሰቡ።

ሊቀ ጳጳሳቱም ለመኰንኑ ይህን ሃያ ሽህ የወርቅ ዲናር ሰጠው መኰንኑም ዐሥር ዐሥር ሽህ የወርቅ ዲናር እንደ ግብር ሁኖ በየዓመቱ እንዲከፈል ጽፎ አስፈረመው።

ጊዜውም ሲቀርብ ይህ አባት አባ ሚካኤል ከምእመናን ሊለምን ተነሥቶ ወጣ በልበይስ ወደተባለም አገር ደርሶ አንዲት ቀን ዋለ ወደርሱም አንድ ምስኪን ድኃ መነኰሴ ገባ። ከሊቀ ጳጳሳቱም ቡራኬ ተቀብሎ ተመልሶ በበር አጠገብ ከረድኡ ጐን ቆሞ አትዘን በልብህም አትተክዝ ከዛሬዪቱ ዕለት እስከ አርባ ቀኖች ትድናለህ በላይህ ያለውን የዕዳ ደብዳቤ ትቀበላለህና ለመኰንኑ ምንም አትሰጠውም ብለህ ለአባት ሊቀ ጳጳሳት ንገረው አለው ያ ረድኡም እንዳለው ነገረው ድኃውን መነኲሴ ፈለጉት ግን አላገኙትም።

አርባ ቀኖችም ሳይፈጸሙ ያ መኰንን በክፉ አሟሟት ሞተ በእርሱ ፈንታም ልጁ ተሾመ ለዚህም አባት ያንን የዕዳ ደብዳቤ መለሰለት ይህም አባት ድኃው መነኰስ ትንቢት እንደ ተናገረ ደብዳቤውን ተቀብሎ ቀደደው ከዕዳም ዳነ። ይህም አባት በታላቅ መከራና በኀዘን በሹመቱ ዘመን ሃያ ዘጠኝ ዓመት ከኖረ በኋላ በፍቅር በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስትና_ሰማዕት_አስጠራጦኒቃ

በዚህችም ዕለት የተመሰገነችና የከበረች ተጋዳይም የሆነች አስጠራጦኒቃ ስለ ክርስቶስ ምስክር ሁና ሞተች። የዚች ቅድስት አባቷ ጣዖት አምላኪ ነው እርሷ ግን በክብር ባለቤት በክርስቶስ የምታምን ናት ሥጋዋም እስቲከሣና እስቲደርቅ መልኳም እስቲለወጥ ድረስ በሥውር ትጾማለች ትጸልያለችም።
ዐሥራ አምስት ዓመት በሆናት ጊዜ እናትና አባቷ ምን ያከሣሻል አሏት እርሷም እኔስ ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እጸልያለሁ አለቻቸው። አባቷም በሰማ ጊዜ ወደ ጢባርዮስ ሒዶ የልጁን ሥራ ነገረው እርሱም ወታደሮች ልኮ ወደ ርሱ አስመጣት። ለጣዖትም እንድትሰግድ መኰንኑ አባበላት እምቢ በአለችም ጊዜ ወደ ወህኒ ቤት አስገቧት እናቷም ክርስቲያናዊት ናት እየመጣች በክብር ባለቤት በክርስቶስ እምነት ታበረታታት ነበር።

ከዚህ በኋላ የብረት የሆነ የሰሌዳ ክርታስ ይሠሩላት ዘንድ በእሳትም አግለው ክንዶቿ ከወገቦቿ ጋራ አንድ እስቲሆኑ እንዲአጣብቋት አዘዘ ይህንንም በአደረጉባት ጊዜ ያንን የብረት ክርታስ ሰብራ በደኅና ወጣች ሕዝቡም ይህን አይተው በክብር ባለቤት በክርስቶስ አራት ሺህ ሰባት መቶ ያህል አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕታትንም አክሊል ተቀበሉ።

ሁለተኛም ደግመው ከእሥር ቤት አስገቧት ጥፍሮች ያሉት የብረት በሬ ሠሩላት ሆዷን ያስወጓት ዘንድ ሊሰቅሏትም ወደርሷ አቀረቡት ይህንንም በአደረጉባት ጊዜ በጌታ ኃይል በሬው ወዲያና ወዲህ ተከፈለ ሕዝቡም ይህን በአዩ ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታችን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ያህል ሰው አምነው በሰማዕትነት አረፉ።

ከዚህም በኋላ መርዝን ከተመሉ እባቦች ጉድጓድ ውስጥ ጨመሩዋት በጸለየችም ጊዜ እንደ ትቢያ ሆኑ። ሁለተኛም አራት ሰዎች የሚሸከሙትን ከባድ ደንጊያ አምጥተው በአንገቷ ላይ ሰቀሉ በጸለየችም ጊዜ ደንጊያው ወደ ሦስት ተከፈለ። ብዙዎች አረማውያንም በክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት አረፉ።

ለቅድስቲቱ ግን የብረት ምንቸት አዘጋጁላት በውስጡ የፈላ እርሳስ በላይዋ ያፈሱባት ዘንድ በነኩት ጊዜ በላያቸው ተሰብሮ የሚያሠቃዩአትን ገደላቸው። ንጉሡም አይቶ ተቆጣ ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።

ምስክርነቷን ከምትፈጸምበት ቦታም በደረሰች ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች አስጠራጢኒቃ ሆይ አንቺ ብፅዕት ነሽ ስምሽ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፏልና የሚል ቃል መጣላት ከዚያም በኋላ በሰይፍ ተቆረጠች።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
#መጋቢት_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ሃያ አንድ በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስንሳው ወደ #አልዓዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ የሔደበት ነው፣ ተአምረኛው አባት #አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ ዓለምን ፍጹም በመናቅ የመነኑበት ነው፣ የማቱሳላ ልጅ #ጻድቁ_ላሜህ መታሰቢያው ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቤተሰብ (አልዓዛር፣ ማርያና ማርታ)

መጋቢት ሃያ አንድ በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስንሳው ወደ አልዓዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ሔደ በዚያም ምሳ አዘጋጂለት ማርታም ምግብ በማቅረብ ታገለግላቸው ነበር።

ሁለተኛዋ ማርያም ግን እግሮቹን ሽቱ እየቀባች በጸጕሩዋ ታሸው ነበር። ጌታችንም አመሰገናት እርሷ ከመቀበሪያዬ ጠብቃዋለች በማለት ስለ ቅርብ ሞቱ አመለከተ።

ዳግመኛም ድኆች ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉ እኔ ግን ከእናንተ ጋራ አልኖርም አለ በዚህም ተሰቅሎ የሚሞትበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ዳግመኛም በዚችም ቀን አልዓዛርን ሊገሉት የካህናት አለቆች ተማከሩ ገናና ስለሆነች ምልክት በእርሱ ምክንያት ብዙዎች በጌታችን የሚያምኑ ሁነዋልና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ

በዚችም ዕለት ከዐለት ላይ ውኃ እያፈለቁ ድውያንን የሚፈውሱት ተአምረኛውና አባት አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ ዓለምን ፍጹም በመናቅ መንነዋል፡፡ እርሳቸውም የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳም ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› በስማቸው የተሰየመላቸው ናቸው፡፡ አባ ሊባኖስ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ይባላሉ፡፡ እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የበለጸጉ ሮማዊ ናቸው፡፡ ልጃቸውን አባ ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ እርሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ወደጫጉላቤትም መግባትን እምቢ አለ፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም እግዚአብሔር ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና ‹‹ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ወዴት እሄዳለሁ? ምንስ ላድርግ?›› ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም ለአባ ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን፣ አስኬማ መላእክትን፣ ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ አባ ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድለህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ፡፡ በአክሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአክሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡

ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአክሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው ‹‹ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል›› አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አክሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም ‹‹ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ›› አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹ሊባኖስ ዘመጣዕ›› የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው ዐፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡

ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቁ_ላሜህ

በዚችም ዕለት የማቱሳላ ልጅ የላሜህ መታሰቢያው ነው። እርሱም አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኑሮ ኖኀን ወለደው ከወለደውም በኋላ አምስት መቶ ስልሳ አምስት አመት ኖረ።

በድምር ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርንም አገልግሎት በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)
"ሰላም ለኪ ዘትፌጽሚ መፍቅደ::
~ለዘኀሠሠ ቤተኪ ወለዘጐድጐደ::
~ማርያም ፍትሒ እምክሳድየ ሐዲደ::
~እንዘ ምሕረተኪ እስእል ፈድፋደ::
~በብረከ ልብየ እሰግድ ሰጊደ::"

(ቤትሽን ለሚሻ : ደጅሽንም ለሚመታ ሁሉ ፍቃዱን የምትፈጽሚ እመቤቴ ሆይ! ሰላምታ ይገባሻል!
~ማርያም ሆይ! የኃጢአት ሠንሠለትን ከአንገቴ ላይ ፍቺ!
~ያንችን ምሕረት አብዝቼ እየፈለግሁ በልቤ ጉልበት እሰግድልሻለሁና!)

<< አርኬ ዘመጋቢት 21 >>

https://t.me/zikirekdusn
#መጋቢት_22

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ሃያ ሁለት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ግልገል ተቀምጦ የገባበት #ሆሣዕና እያሉ ያመሰገኑበት ነው፣ የከበረ አባት ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#በዓለ_ሆሳዕና

መጋቢት ሃያ ሁለት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብቶ ቤተ መቅደሱን በአህያ ግልገል ተቀምጦ በመዞር ሆሣዕና እያሉ እንዲአመሰግኑት አድርጓል። ይህም ስለርሱ እየአንዳንዳቸው በዘመናቸው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው።

ያዕቆብም በክርስቶስ ስለ ተመሰለው ስለ ልጁ ይሁዳ አህያውን በዘይት ዕንጨት ላይ ያሥራል ውርንጫውንም በወይን አረግ አለ። ዘካርያስም የጽዮን ልጅ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣል አለ።

ኢሳይያስም ንጉሥሽ ጻድቅ የዋህ የሆነ ይመጣል ዋጋውም ከእርሱ ጋራ ነው ሥራውም በፊቱ የተገለጠ ነው በአህያ ግልገልም ላይ ይቀመጣል አለ። አብርሃምም የሰሌን ዝንጣፊ ይዞ መሠውያውን በዞረ ጊዜ ይቺን ዕለት ተድላ ደስታ የሚደረግባት የእግዚአብሔር በዓል ብሎ ጠራት።

ዳዊትም ከሕፃናትና ከልጆች አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ አለ። ሰሎሞንም የሕፃናት አንደበታቸው የተቃናች ሆነች አለ ሁለተኛም ልጆችና ሽማግሌዎች በኢየሩሳሌም ይጫወታሉ ምርጕዛቸውም በእጃቻቸው ውስጥ ነው አለ። ደግሞ መትከያዎችሽን አስፍተሽ ድንኳኖችሽን ዘርጊ ያለም አለ።

ይህንንም የትንቢት ነገር ለመፈጸም በከበረ ወንጌል እንደተጻፈ ጌታ በአህያዋና በውርንጭላዋ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ወደ ኢየሩሳሌም ሊገባ በቀረበ ጊዜ የደብረ ዘይት አጠገብ ከምትሆን ቤተ ፋጌ ደረሰ ደብረ ዘይት ወደሚባል ቢታንያም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከ።

ወደ ፊታችሁ ወዳለ አገር ሒዱ። በገባችሁም ጊዜ ሰው ያልተቀመጠበት ያህያ ግልገል ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ለምን ትፈቱታላችሁ የሚል ሰው ቢኖር ጌታው ይሻዋል በሉ። የተላኩትም በሔዱ ጊዜ እንደነገራቸው አገኙ። የአህያውንም ግልገል ፈቱ ጌቶቹም ለምን ትፈቱታላችሁ አሏቸው። ጌታው ይሻዋል አሉ።

ወደ ጌታ ኢየሱስም ይዘውት ሔዱ ልብሳቸውንም በአህያው ግልገል ላይ ጐዘጐዙ ጌታንም አስቀመጡት። ቅጠል ቆርጠው በመንገድ ላይ የጐዘጐዙ ብዙዎች ናቸው። ልብሳቸውንም በመንገድ ላይ ያነጠፉ አሉ። በፊትም በኋላ ይሔዱ የነበሩት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ መድኃኒት ነው ብለው አሰምተው ተናገሩ። በእግዚአብሔር ስን የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥትም የተባረከች ናት።

ጌታ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ገባ ሕዝቡም ሁሉ አዩት በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ አርድእት ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ። በነጋውም ከቢታንያ በወጣ ጊዜ ተራበ። በሩቅም ቅጠል ያላትን በለስ አየ። በርሷ ፍሬ ያገኝ እንደሆነ ሊያይ ሔደ ወደርሷም በደረሰ ጊዜ ከቅጠል ብቻ በቀር ያገኘው የለም የበለስ ወራቱ አልነበረምና። ለዘላለም ካንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር አላት ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ።

ወደ ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በምኲራቡም ግቢ የሚገበያዩትን ያስወጣ ጀመረ የለዋጮችንም ሰደቃቸውን ገለበጠ ርግብ የሚሸጡትንም ወንበራቸውን ። ወደ ምኲራብ ለንግድ ገንዘብ ይዘው እንዳይገቡ ከለከለ። ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይሁን የሚል ጽሑፍ ያለ አይደለምን እናንተ ግን የሌቦችና የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት ብሎ አስተማራቸው።

ዮሐንስም እንዲህ አለ አልዓዛርን ከሙታን ለይቶ ካስነሳው በኋላ። በነጋውም እሑድ ለበዓል የመጡ ሰዎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ በሰሙ ጊዜ። የሰሌን ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ከኢየሩሳሌም ፈጥነው ወጡ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ከአርያም የተገኘ መድኃኒት የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ እየጮኹ ተቀበሉት።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የአህያ ግልገል አገኘ። ተቀመጠበትም እንደ ተጻፈ እንዲህ ሲል። የጽዮን ልጅ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ግልግል ተቀምጦ ይመጣል።

አስቀድሞ ግን ደቀ መዛሙርቱ ይህን ነገር አላወቁም ነበር ጌታ ሳይሰቀል ። ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ይህ የተጻፈ ስለ እርሱ እንደሆነ ያን ጊዜ አወቁት እንጂ እንዲህም አደረጉለት።

አልዓዛር አልዓዛር ብሎ ከሙታን ለይቶ እንዳስነሣው ባስነሣው ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መሰከሩለት። ስለዚህም ሕዝቡ አመኑበት። ያደረገውን ተአምራት ሰምተዋልና የሕፃናቱንም ምስጋና ደግሞ አልዓዛርን ማስነሣቱን።

የካህናቱ አለቆችና ፈሪሳውያን ግን እርስ በርሳቸው የምታገኙት ረብሕ ጥቅም እንደሌለ አታውቁምን እነሆ ሰው ሁሉ አመነበት አሉ። ማቴዎስና ማርቆስ የሰሌንን ነገር አላወሱም ሌሎች ከእጨንቶች ቅጠሎችን እየቆረጠ በመንገድ ውስጥ ጐዘጐዙ አሉ እንጂ።

ሉቃስም ቅጠልን ወይም ሰሌንን አላወሳም ሲሔዱ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ ይጐዘጒዙ ነበር አለ እንጂ። ዮሐንስ ግን ለብቻው ከኢየሩሳሌም ከሰሌን ዛፍ ላይ ዘንባባ ቆርጠው ያዙ አለ። ሰሌንም በኢየሩሳሌም አልነበረም ጌታችን ሕፃን ሁኖ ሳለ ወደ ግብጽ በወረደ ጊዜ ከእናቱ ቡርክት ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጋር እስሙናይን ከሚባል አገር ደረሱ ከዚያም ሰሌን አገኙ።

ጌታችንም ከሥርዋ ተነቅላ ሒዳ በደብረ ዘይት ላይ እንድትተከል አዘዛት ያንጊዜ ወደ አየር ወጥታ በረረች ሒዳም በዚያ በደብረ ዘይት ተተከለች ከእርስዋም ወስደው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀበሉት። ጌታችንም የሆሣዕናን ዑደት በአሳየ ጊዜ የአይሁድ ወገን ቅናት ይዟቸው በሚገድሉት ገንዘብ ምክንያት ፈለጉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘኢየሩሳሌም

በዚችም ዕለት የከበረው መንፈሳዊ አባት የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ ቄርሎስ አረፈ። ይህም አባት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በመማር ያደገና እጅግ አዋቂ ምሁር ሆነ።

ከእርሱ በፊት የነበረ ኤጲስቆጶስ አባ በርኪሶስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት። በተሾመም ጊዜ ከመናንያንና ከአርዮሳውያን ተኵላዎች በመልካም አጠባበቅ ሕዝቡን ጠበቀ።

የኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በሰርድቄ በተሰበሰበ ጊዜ ይህ አባት ከዚያ ደርሶ አርዮሳውያንን ተከራከራቸው ምላሽ አሳጥቶም አውግዞ አሳደዳቸው አካክዮስንም ከቂሣርያ ሀገረ ስብከቱ መንበር አሳደደው።

አካክዮስም ወደ ታናሹ አርዮሳዊ ወደ ሆነው ቆስጠንጢኖስ ሒዶ ከማኀበሩ ስለ ደረሰበት ውግዘትና ስደት ይልቁንም ከዚህ አባት ቄርሎስ የደረሰበትን ሁሉ በመናገር ከሰሰው። ስለዚህም አርዮሳዊ ንጉሥ ይህን አባት ከኢየሩሳሌም አሳደደው ሌሎችንም ብዙዎች ኤጲስቆጶሳትን ከሀገረ ስብከት መንበራቸው አሳደዳቸው።

ይህም አባት ቄርሎስ ወደ ተርሴስ ከተማ ሒዶ ከአገሩ ኤጲስቆጶስ ከስልዋኖስ ጋራ ተገናኘ። እርሱም ተራዳው ጥቂት ቀኖችም ከእርሱ ዘንድ አስቀመጠው።

በሉክያኖስ ስብሰባ በሆነ ጊዜም ይህ አባት ከተሰበሰቡት ውስጥ አንዱ እርሱ ነው አካክዮስንም ደግመው አወገዙት ረገሙትም፡፡ ዳግመኛ ወደ ንጉሥ ሒዶ በዚህ በቅዱስ ቄርሎስ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወታደሮች ልኮ ከዚያም ካለበተረ አሳደደው።

ከዚህም በኋላ ይህ መናፍቅ ቈስጠንጢኖስ ሞተ። ልጁ ሦስተኛው ቈስጠንጢኖስ ነገሠ ይህንንም አባት ከተሰደደበት ወደ መንበረ ጵጵስናው መለሰው አባቱ ያሳደዳቸውን ኤጲስቆጶሳት ሁሉንም መለሳቸው። ይህም አባት የተረፈውን ዘመን በሰላምና በጸጥታ ኖረ።
ታላቁ ቴዎዶስዮስም በነገሠ ጊዜ ስለ መቅዶንዮስ ስለ ሰባልዮስና ስለ አቡሊናርዮስ በቊስጥንጥንያ መቶ ሃምሳ ኤጲስቆጶሳትን በአንድነት ሰበሰበ። ይህም አባት በጉባኤው ውስጥ አንዱ እርሱ ነበር መናፍቃንም መመለስን እንቢ በአሉ ጊዜ ከወገኖቹ ጋር ረገማቸው አውግዞም ለያቸው።

ሃይማኖትን ያቀኑ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ በሠሩት በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም ከሚለው ቀጥሎ እንዲህ የሚል ጨመረ። "የባሕርይ ገዢ በሚሆን በሚያድን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን። ከአብ የተገኘ ከአብ ከወልድ ጋር እንስገድለት እናመሰግነውም በነቢያት አድሮ የተናገረ።

ሐዋርያት ሰብስበው አንድ በአደረጓት ከሁሉ በላይ በምትሆን ክብርት ንጽሕት ጽንዕት ልዩ በምትሆን በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም የዘላለም ሕይውት።"

ከዚህም በኋላ ይህ አባት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ። ሁለተኛም ስለ ጸሎተ ሃይማኖትና ስለ ትርጓሜው ሌላ በውስጡ ዐሥራ ስምንት ያህል ድርሳን ያለው መጽሐፍ ደረሰ። እርሱም ጥበብን እውቀትን ሁሉ የተመላ እጅግ የሚጠቅም ነው። በጵጵስናውም መንበር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
"ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ"
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ
ከወንዙ በወድያኛው ዳር
ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።
ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ።
በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።

ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?"
አለው።

ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?"
በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም
የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም
የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።

ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው
መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም።
ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ
ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው
ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡
ስለዚህ የሰዎችን የሕይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ሕይወት አምጥተን ለመተግበር
ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሳችሁ!

በዓለ ጥንተ ዑደተ ሆሳዕና (ወቅዱስ ቄርሎስ መንፈሳዊ)
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn
"ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አረገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡

እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርግዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡

ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??”

ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡

ልወልድ የምችለዉ በሁለት ዓመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ኃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ፡፡”

⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑⭕️🛑

ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ለሁሉም ጊዜ ና ቦታ አለው።

https://t.me/zekidanemeheret
#መጋቢት_23

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ሃያ ሦስት በዚች ቀን #ታላቁ_ነቢይ_ዳንኤል አረፈ፣ የደብረ ሊባኖሱ #አቡነ_ፊሊጶስ ፍልሰተ ዐፅማቸው በክብር ተከናወነ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነቢዩ_ቅዱስ_ዳንኤል

መጋቢት ሃያ ሦስት በዚች ቀን የዮናኪር ሴት ልጁ የወለደችው ታላቅ ነቢይ ዳንኤል አረፈ። ናቡከደናጾርም ኢየሩሳሌምን በወረራት ጊዜ አባታቸው ዮናኪር አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ሦስቱን ልጆቹን የልጁን ልጅ ዳንኤልንም ወሰዳቸው ከእንርሱም ጋር ከእስራኤል ልጆች ብዙ ሰዎች ተማረኩ ።

ይህም ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም ልጅ ነው። ኢሳይያስ ለሕዝቅያስ ንጉሥ ትንቢት እንደተናገረ የቤተ መንግሥቱንና የቤተ እግዚአብሔርን ዕቃ ሁሉ ናቡከደነጾር ወደ ባቢሎን ወሰደ።

ይህ ዳንኤል ያን ጊዜ በዕድሜው ታናሽ ነበር ፍጹም የሆነ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ የእግዚአብሔር መንፈስም አድሮበት በባቢሎን አገር ትንቢት ሲናገር ኖረ።

ምርኮ በሆነ በአራተኛው ዓመት ናቡከደነጾር የምታስፈራ ራእይን አየ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ያቺን ሕልም ረሳት። በባቢሎን የሚኖሩትን ሁሉን ጥበበኞች ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ያቺን ራእይና ትርጓሜዋንም እንዲነግሩት ፈለገ እንርሱ ግን ያቺን ራእይና ትርጓሜዋን ሊያውቋት አልቻሉም።

የባቢሎንን ጥበበኞች ሁሉ እርሱንና ባልንጀሮቹ ሠለስቱ ደቂቅን ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሥ አዘዘ። ዳንኤልም ይህን ነገር ሰምቶ የዘበኞችን አለቃ ስለ ምን እንዲህ ያለ ትእዛዝ ከንጉሥ ዘንድ ታዘዘ ብሎ ጠየቀው። እርሱም ንጉሥ ስለ አያት ራእይ ነው የባቢሎንና የግብጽ ጠቢባን ሁሉ እርሷን ራእዩን ትርጓሜዋንም ሊነግሩት አልተቻላቸውምና ብሎ መለሰለት።

ዳንኤልም የዘበኞቹን አለቃ እኔ ለንጉሥ ሕልሙን እንደምነግረውና ፍቺውንም እንደምተረጕምለት ስለ እኔ ንገርው እሊህንም ተዋቸው አለው ። ከዚህ በኋላም ዳንኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ባልንጀሮቹ ሠለስቱ ደቂቅም ከእርሱ ጋር የንጉሡን ሕልም ፍቺዋንም ይገለጥላቸው ዘንድ በአንድነት ማለዱ።

እግዚአብሔርም ገለጠላቸው ዳንኤልም ወደንጉሥ ገብቶ ሕልሙንና ፍችዋን ነገረው። ከእርሱ በኋላም ስለሚነሡ ነገሥታት ከእንርሱም ከየአንዳንዳቸው የሚሆነውንም ገለጠለት። የዳንኤል ቃል ናቡከደነጾርን ደስ አሰኘው በፊቱም ሰገደ ብዙ እጅ መንሻንም ሰጠው ታላቅ ክብርንም ሰጥቶ በባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው።

ከዚህም በኋላ ናቡከደነጾር ሌላ ሕልም አየ ያንንም ተረጐመለት እንዲህም ብሎ አስረዳው ስለታበይክ እግዚአብሔር ከሰው መካከል አውጥቶ ከአራዊት ጋራ በዱር ሰባት ዓመት ያኖርህ ዘንድ አለው። እንደ እንስሳም ሣር ትበላለህ ከሰባት ዓመትም በኋላ ወደ መንግሥትህ ይመልስሃል ፈ በማለት ይህም ተፈጸመበት።

ናቡከደነጾር ከሞተ በኋላ መልአክ በግድግዳ ላይ የጻፋትን ለልጁ ለብልጣሶር ተረጐመለት በቤተ እግዚአብሔር ዕቃ በጠጣ ጊዜ ጽሑፉ የተቆጠረ የተመጠነ የተመዘነ እንደሆነ ትርጓሜውም ዙፋኑንና መንግሥቱን እግዚአብሔር ለሌላ የሰጠው መሆኑን ገለጠለት። እንዲህም አለው ቢመዝንህ ጐደሎ ሆነህ አገኘህ መንግሥትህንም ለፋርስ አሳልፎ ሰጠ ትንቢቱም ተፈጸመች።

እግዚአብሔርም እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚነግሡትን ነገሥታት በራእይ አሳየው የሐሳዊ መሲሕንም መገለጥ አሳየው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርነቱን ክብር ልዕልናውን ጌትነቱን አሳየው። የክበር ባለቤት ክርስቶስን ወደ ዓለም መምጣቱን ትንቢት ተናገረ ሱባኤዎችንም ወሰነ እንዚያ ሱባኤዎችም በተፈጸሙ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ።

ክርስቶስ ይመጣል ይገድሉታልም ለኢየሩሳሌምም መዳኛዋ ይሆናታል ብሎ ትንቢት እንደ ተናገረ። የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በኋላ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ቤተ መቅደስም እንደሚፈርስ የተናገረው ትንቢት ሁሉ ተፈጸመ።

በባቢሎን አገርም ቤል የሚባል ጣዖት ነበረ ምግብንም ሁልጊዜ ዐሥራ ሁለት ጫን በሚፈጅ ቻል ዐሥራ ሁለት መስፈሪያ ስንዴ አርባ በግ ሰባት ፊቀን የወይን ጠጅ እያወጣጡ ይሰጡት ነበር። ንጉሡም ሁልጊዜ ይሰግድለታል ቤል ጣዖትም ከንጉሡ ቤት የሚሰጡትን የሚበላና የሚጠጣ ይመስለው ነበር ።

ንጉሡም ዳንኤልን ለቤል የማትሰግድ ለምንድን ነው አለው። ዳንኤልም ንጉሡን እኔስ ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ፍጥረቱንም ሁሉ በሕያውነት ለሚያኖር አምላክ እንጂ የሰው እጅ ለሠራው ጣዖት አልሰግድም አለው።

ንጉሡም ቤል ሕያው ያልሆነ ይመስላሃልን በየነጋታው እንዲበላ እንዲጠጣ አታይምን አለው። ዳንኤልም በንጉሡ ሳቀበት ንጉሥ ሆይ ይበላል ይጠጣል እያሉ አያታሉህ ይህ ውስጡ ጭቃ ላዩ ናስ ነው ምንም ምን አይበላም አይጠጣም አለው። ንጉሡም ተቆጣ የጣዖቱንም ካህናት ጠራቸው እውነት ነውን ቤል አምላክ አይበላም አይጠጣምን አላቸው። ሁልጊዜ የምንሰጠውን በዕውነት ይበላል ይጠጣል አሉት።

ከዚህም በኋላ በመሸ ጊዜ ከጣዖቱ ዘንድ መብሉንና መጠጡን ሁሉ ንጉሡ እየተመለከተ ካህናቱ አስቀምጠው ወጡ። የጣዖቱ ካህናትም ከወጡ በኋላ ዳንኤል አመድ አምጡ ብሎ አዘዘ አመጡለትም። ንጉሡም ከዚያ ሁኖ እያየ በጣዖቱ ቤት ውስጥ ነሰነሰው። ንጉሡም በቁልፉ ከዳንኤል ጋር በአንድነት ቈለፉት አተሙትም ወደ ማደሪያቸውም ሔዱ። የጣዖቱ ካህናት ግን ከምድር በታች ውስጥ ለውስጥ መግቢያ ቀዳዳ ነበራቸው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ በሌሊት በዚያ ገብተው በሉ ጠጡ በመጡበትም ተመለሱ።

በማግሥቱም ንጉሡ መጥቶ የጣዖቱን ቤት ከፈተ ራሱ ከአኖረው መብሎች ምንም አላገኘም ንጉሥም ቤል ሆይ ፈጣሪዬ ዳንኤልን ያሳፈርከው አንተ ገናና ነህ ብሎ ጮኸ። ዳንኤልም ሳቀ ለንጉሡም የወንዶችና የሴቶችን የልጆችንም ፍለጋቸውን በአመድ ላይ አሳየው። ንጉሡም የጣዖቱን ካህናት ይዞ መረመራቸው እነርሱም ውስጥ ለውስጥ ተሠውረው የሚገቡበትንና የሚወጡበትን ለንጉሡ አሳዩት። ያን ጊዜ ንጉሡ ተቆጥቶ የጣዖቱን ካህናት ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ ገደላቸው ጣዖቱንም ለዳንኤል ሰጠው። ዳንኤልም ሰበረው ምኲራቡንም አፈረሰ።

ከዚህ በኋላ ደግሞ የባቢሎን ሰዎች የሚአመልኩትና የሚሰግዱለት ታላቅ ዘንዶ ነበር ንጉሡም ዳንኤልን ይህንንስ አምላክ አይደለም ትለዋለህን እነሆ ሕያው ነው ይበላል ይጠጣል ናስ ነው ትለው ዘንድ አትችልምና ስገድለት እንጂ አለው።

ደንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔስ በሕያውነት ከሚኖር ከእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አልሰግድም ግን ያለ ሰይፍና ያለ በትር ይህን ከይሲ እገድለው ዘንድ አሰነሰብተኝ አለው። ንጉሥም አሰናበትኩህ አለው።

ዳንኤልም ጠጉርና አደሮ ማር ወስዶ እንደ እንቁላልም አድበልብሎ በእሳት አጋለው በሞራም ጠቅልሎ ለከይሲው አጐረሰው በዋጠውም ጊዜ ሆዱ ተሰንጥቆ ሞተ ዳንኤልም የባቢሎን ሰዎች ሆይ አምላካችሁን ተመልከቱ አላቸው።

የባቢሎን ሰዎችም በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ ወደ ንጉሡም ተሰብስበው አይሁዳዊው ዳንኤል ነግሦአልን እነሆ ቤልን ሰበረው ካህናቶቹንም ገደላቸው ከዚያም ደግሞ ዘንዶውን ገደለው አሁን እርሱን ዳንኤልን እንድንገድለው ካልሰጠህን አንተን ቤተ ሰብህንም እንገድላለን አሉት።

ንጉሡንም እጅግ በአስጨነቁት ጊዜ ስለ ዳንኤል አዘነ ግን ዳንኤልን ሰጣቸው እነርሱም በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት በዚያም ሰባት ቀን ኖረ። ከረኀብ ጽናትም የተነሣ እንዲበሉት በሌላ ጊዜ የሚሰጧቸውን በእነዚያ ቀኖች ምንም ምን አልሰጧቸውም ነበር።
እግዚአብሔርም መልአኩን ወደ እንባቆም ላከው እርሱም በኢየሩሳሌም ውስጥ ለአጫጅዎች ምሳ ተሸክም ሲሔድ በራስ ጠጉሩ ተሸከመው። ወስዶም ዳንኤል በአለበት ጉድጓድ ውስጥ አኖረው። ዳንኤልም ተመግቦ እግዚአብሔርን አመሰገነው በዕንባቆምም ቃል ተረጋጋ በዚያችም ሰዓት እግዚአብሔር የላከው መልአክ ወደ አገሩ ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አደረሰው።

በሰባተኛዪቱ ቀንም ስለ ዳንኤል እያለቀሰ ንጉሡ ወደ ጕድጓድ መጣ ዳንኤል ሙቶ አንበሶች የበሉት መስሎት ነበርና። ወደ ጕድጓዱም ሲመለከት ዳንኤልን አየው አንበሶችም እንደ ድመቶች እግሮቹን እየላሱ ከእግሮቹ በታች እጥፍጥፍ ብለው ተኝተው ነበር።

ንጉሡም እግሮቹን እስከሚልሱ እንደ ድመቶች አንበሶችን ያገረመለትና ያሰገዛለት የዳንኤል አምላክ ታላቅ ነው ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ። በዚያን ጊዜ ዳንኤልን ከጕድጓድ እንዲያወጡት እነዚያንም የዳንኤልን ጠላቶች ይዘው ለአንበሶች ወደ ጕድጓድ እንዲጥሉአቸው ንጉሥ አዘዘ ወዲያው እነዚያ አንበሶች በንጉሡ ፊት በሏቸው።

ዳንኤልም የእስራኤል ልጆች ወደ ኢየሩሳሌም እስከ ሚመለሱበት ጊዜ በባቢሎን ኖረ እርሷም ሰባ ዘመን ናት ከዚያም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ፊሊጶስ_ዘደብረ_ሊባኖስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን የአቡነ ፊሊጶስ ፍልሰተ ዐፅማቸው በክብር ተከናወነ፡፡ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ፊሊጶስ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው በምናኔ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገቡ፡፡ ከብዙ ጊዜ አገልግሎትም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት እጅ መንኩሰው ከእርሳቸውም ዕረፍት በኋላ ሦስተኛ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከተወለዱት የመጀመሪያ ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ አባታቸው ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በመንፈቀ ኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ነበር፡፡ በመጀመሪያ የአቡነ ፊሊጶስን የጽድቅ ሕይወትና ሹመታቸውን በተመለከተ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድልና በራሳቸው በአቡነ ፊሊጶስ ገድል ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- ‹‹ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚህ ዓለም ተለይቶ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ ‹ከአንተ በኋላ አንተን ተክቶ በዙፋንህ የሚቀመጥ ማነው?› አሉት፡፡ እርሱም ‹ብዙ ዘመን አይኖርም እንጂ ኤልሳዕ በእኔ ተተክቶ ይቀመጥ› አለ፡፡ ስለ ፊሊጶስ ግን አላነሳም፣ ኤልሳዕ ካረፈ በኋላ በእርሱ ተተክቶ አባት ይሆን ዘንድ ጌታችን የተሸለመ ፊሊጶስን እንደመረጠው ስም አጠራሩ ለልጅ ልጅ ዘመን እንደሚጸና ያውቅ ነበርና ስለዚህ ‹አልሳዕ በእኔ ተተክቶ አባት ይሁናችሁ› አለ፡፡ ክቡር አባታችንም በታላቅ ክብር ዐረፈ፡፡ አንድ ቀን አንድ ዲያቆን ዐረፈና ሬሳውን ገንዘው አጠቡት፣ ይቀብሩትም ዘንድ አስክሬኑን ይዘው ሲሄዱ በአልጋ ላይ ሳለ አስክሬኑ ተንቀሳቀሰ፡፡ የተሸከሙትም ደንግጠው መሬት ላይ አስቀመጡትና ከመግነዙ ፈቱት፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሦስት ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ወንድሞችም ‹ምን እያልክ ነው?፣ ወዴትስ ነበርክ?› አሉት፡፡ ያ የከበረና የተመረጠ ዲያቆንም ‹ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት ‹ኤልሳዕ ወደኔ ይምጣ፣ ፊሊጶስ ስለ እኔ ተሹሞ በወንበሬ ይቀመጥ እርሱ ለብዙዎች አሕዛብ አባት ይሆናልና የክርስቶስንም መንጋ በጽድቅና በቅን ይጠብቃል› ብሎኛል› ብሎ ይህን ተናግሮ ተመልሶ ዐረፈ፡፡ ወንድሞችም ኤልሳዕ እንደልማዱ ጎኑን ሳያሳርፍ በወንበር ላይ እንደተደገፈ በሞት ማረፉን አላወቁም ነበር፡፡››
ወደ ጻድቁ የልጅነት ገድላቸው እንመለስና አቡነ ፊሊጶስ በእግዚአብሔር ተመርጠው የመንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ሆነዋልና ገና በሕፃንነታቸው በተወለዱባት ሰላሌ ክፍለ ሀገር ዝማ በምትባል ልዩ ቦታ ውስጥ ሰይጣን በጠንቋይ ላይ አድሮ በነደደ በእሳት ውስጥ በመግባትና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ በአካባቢው ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን በእሳት ውስጥ እንዳለ በስመ ሥላሴ አማትበውበት አመድ አድርገውታል፡፡ በዚህ በአቡነ ፊሊጶስ ድንቅ ተአምር የጠንቋዩ ቤተሰቦችና የአካባቢው ሰዎችም አምነው ሊጠመቁ ችለዋል፡፡ ይህንንም ያደረገው ገና ሕፃን ሳለ ነው፡፡ መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦለት የትውልድ መንደሩን ትቶ ወደ ግራርያ ሀገር ደብረ አስቦ ሄዶ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን እንዲያገኝ በነገረው መሠረት አንድ ቀን ያህል ተጉዞ ተክለሃይማኖትን አገኛቸውና ባርከውት ከመነኮሳት ጋር እንዲያርፍ አደረጉት፡፡ ሦስት ዓመት እነርሱን በመልካም ሥራ ፍጹም ሆኖ ሲያገለግላቸው ከቆየ በኋላ ‹‹ሁሉም በአንድነት አሁን ልብሰ ምንኩስና ይገባዋል›› አሉ፡፡ ቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖትም የምንኩስናን ሥራ የሚያሠራ ቅድስናን ሰጠው፡፡

በሌላም ጊዜ ቅስናን ይቀበል ዘንድ ወደ ጳጳሱ ዘንድ ላኩት፡፡ አቡነ ፊሊጶስ በንጉሥ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ሲገረፉ ደማቸው እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያሳደደ ቅዱስና ጻዲቅ አባት ናቸው፡፡ ንጉሥ አምደ ጽዮን በክፉ ጠንቋዮች ምክር ተታሎ ‹‹ያልወለደችህን የአባትህን ሚስት ብታገባ መንግሥትህ ትፀናለች›› ብለው ክፉ ምክርን መክረውት የእንጀራ እናቱን አገባትና ንግሥት አደረጋት፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ይህን ሲሰሙ ነቢዩ ኤልያስ ንጉሡ አክአብንና አልዛቤልን በድፍረት እንደገሠጻቸው እርሳቸውም በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ዘልፈው ገሠጹት፡፡ ወደ ንጉሡም ከመሄዳቸውም በፊት በዚህ ምክንያት ሰማዕት እንደሚሆኑ አውቀውት ነበርና ልጆቻቸውን ተሰናብተውና የሚተካቸውን ሰው ነግረዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ንጉሡ አምደ ጽዮንም አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ አስገረፋቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም መሬት ላይ እየተቆረሰ የወደቀውን ሥጋቸውን እያነሱ ለበረከት ወሰዱት፡፡ ደማቸውም እንደ እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያቃጥላቸው ነበር፡፡ 300 አንስራ ውኃ አምጥተው ከደሙ በወጣው እሳት ላይ ቢያፈሱትም የውኃው ብዛት እሳቱን ማጥፋት አልቻለም፡፡ ንጉሡም በፍርሃት ከዙፋኑ ላይ ወርዶ ሸሸ፡፡

የንጉሡ ጭፍሮች ግን በጋለ ማረሻ ጀርባና ግንባራቸውን ደረታቸውንም ተኮሷቸው፡፡ ኃፍረታቸውንም እንዳይሸፍኑ እጆቻቸውን ወደ ኋላ አስረው ራቁታቸውንም በከተማው ሁሉ ሲያዞሯቸው ዋሉ፡፡ ማታም ንጉሡ ‹ታስረው ለኖሩ ኃይለኛ ውሾች ስጡት› ብሎ በማዘዝ ውሾቹ እንዲቦጫጭቋቸው ቢያደርጉም ውሾቹ ግን ከእግራቸው ስር ሰግደዋል፣ እርሳቸውም በእግራቸው ባረኳቸው፡፡ አማካሪዎቹም ንጉሡን ‹‹ከዚህ መነኩሴ ጋር ምን አጨቃጨቀህ በግዞት አርቀህ ስደደው ብለው›› ብለው መክረውት ‹‹እስከ ቆርቆራ አገር አውጥታችሁ ወደ ትግሬ አገር ውሰዱት›› ብሎ አዘዘ፡፡ እርሳቸውም ንጉሡን ከ3 ዓመት በኋላ ትሞታለህ ብለው ትንቢት ነገረውት በወታደሮች ተወሰዱ፡፡ በግርፋት ብዛት የተቆረሰ ሥጋቸው ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ደማቸውም አስረው የሚወስዷቸውን የአንዱን ወታደር አንድ ስውር ዐይኑን ፈወሰለትና ወታደሮቹም አምነው ከእርሳቸው ጋር በዚያው ተሰደው መከራን ተቀብለዋል፡፡ እሳቸው በትግራይ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ ሲያስተምሩ በትንቢታቸው መሠረትም ንጉሡ ከሦስት ዓመት በኋላ ሞተና ልጁ ነገሠ፡፡ ልጁም አባታችንን ከስደት መለሳቸውና ከተክለሃይማኖት መቃብር ደብረ አስቦ ገቡ፡፡ የነገሠውንም ልጅ አንድ ክፉ ሰው ‹‹ከአንድ በላይ ማግባት ትችላለህ፣ በገና ወቅትም ረቡዕና አርብን መጾም ተገቢ አይደለም›› ብሎ ስለመከረው ጳጳሱን ወደ ሀገራቸው ግብፅ እንዲሰደዱ ሲያደርግ አቡነ ፊሊጶስን ደግሞ ‹‹ረቡዕና አርብን በጠዋት ካልቀደስክ›› ብሎ ወደ ደራ ተሰደው እንዲሄዱ አደረገ፡፡ አባታችን በአጠቃላይ አምስት ጊዜ ተሰደው በትግራይ፣ በደራ፣ በዝዋይ ባሕረ ደሴት፣ በዳሞት ገማስቄ እና በወለቃ በስደት ቆይተዋል፡፡ ጳጳሱን አባ