🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻቹ🙏
"ጉርሻ ሊያስተምረን የመጣው ሁሉ ምግባችንን ይነጥቀናል ብለን የምንፈራው ለምንድነው?"
//አቤል ብርሀኑ(የወይኗ ልጅ)//
እንደምን አመሻቹ?
አንድ እህል የጫነ መኪና በመንገድ ሲያልፍ ከተጫኑት እህሎች የአንዱ ኩንታል ማዳበሪያ ተቀዶ ብዙ ስንዴ አስፓልት ላይ ይደፋል፡፡ ሹፌሩ መኪናውን አቁሞ የቀረውን አስሮ የተደፋውን ትቶት ይሄዳል። አንዲት ልጅ የተደፋውን ስንዴ በቻለችው አቅም በእጇ ትለቅማለች። ነገር ግን ሁለቱም መዳፎቿ ስለሞሉ አንዱን ስታነሳ ከያዘችው አንድ ትጥላለች። እየለቀመች ትጥላለች።
በመንገዱ ሲያልፉ የነበሩ አንድ አባት አይተዋት ጎንብስ ብለው መልቀሙን እያገዟት እንዲህ አሏት። ልጄ ከንቱ ድካም እየደከምሽ ነው ያለሽው፡፡ አንድ ለቅምሽ አንድ እየጣልሽ ነው፡፡ እስኪ የለቀምሽውን እዚያ ዳር ላይ አስቀምጪውና በባዶ እጅሽ ድጋሚ ልቀሚ እሏት።
እሷም ምንቅር ብላ ኧረ እኔ ላስቀምጥ ስሄድ እርሶ ለራሶ ለቅመው ሊሄዱ አለቻቸው። እሳቸውም ሳቅ ብለው በቻሉት ፍጥነት እየለቀሙ በመዳፋቸው ሲሞላ ዳር ላይ ወስደው አስቀምጠውት ይመጣሉ፡፡ አሁንም ለቅመው ዳር እያስቀመጡ ሌላ ይለቅማሉ። ከሁለት መዳፏ በላይ መያዝ ያልቻለችው ወጣት ሰውዬው የሚያደርጉትን ነገር መድገም ጀመረች፡፡ እያለቀመች ዳር እያስቀመጠች ሌላ ትለቅም ጀመረ።
ከብዙ ቆይታ በኋላ ስንዴውን ጨረሱት። ሰውዬ ፌስታል ፈልገው የለቀሙትን ስንዴ በፌስታል ሰብስበው ይኸው ልጄ ለአንቺ ነው የለቀምኩት ውስጅው አሏት። እያፈረች ተቀበለቻቸው እሷም የለቀመችውን ፌስታሉ ውስጥ እንድትከት አደረጓት።
ቀጥለው እንዲህ አሏት "ልጄ መንገድ ያሳየሽን ሁሉ መንገድ ሊዘጋብኝ ነው ብለሽ አታስቢ።
አጎራረስን የሚያሳይሽ ሰው ምግብሽን ሊቀማሽ እንዳይመስልሽ፡፡ ማጉረስ የሚያጠግባቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ማመን አለብሽ። ብዙ ክፉ ሰዎች ቢያጋጥሙሽም የሚያጋጥሙሽን ሁሉ ክፉ አታድርጊ። ክፋታቸውን የማያውቁ ብዙ ሰዎች አሉና ክፉ ነህ እያልሽ ክፋታቸውን አትቀስቅሺ። ሰዎች ሁሉ ክፉ ናቸው ስትይ ክፋታቸው ይወርስሻል፡፡ ስለነሱ ብዙ ስታወሪ ወሬው ታሪካቸው ያንቺ እየሆነ ይሄዳል። ደሞ ሌላው በቃኝን ልመጂ፡፡ እጅሽ ከሞላ ይብቃሽ፤ ወድቆ በነፃ ስላገኘሽ ብቻ ሆድሽን እጅሽን አትጠቅጠቂ፤ በቃኝን ልመጂ፡፡ እጅሽ ከሞላ ኪስሽ ከሞላ ዳር ላይ ማስቀመጥ ልመጂ። እጅሽ እየሞላ እንድ እየጣልሽ አንድ ስታነሺ ከኖርሽ ስግብግብ ትሆኛለሽ። ወድቆ ያገኘሽው ነገር ሁሉ ያንቺ አይደለም። እጅሽ ሲሞላ፣ ሆድሽ ሲሞላ፣ ኪሲሽ ሲሞላ የጎደለበትን አስቢ ባዶ የሆነበትን አስቢ። እኔ ለቅሜ የሰጠሁሽ ስለማልፈልገው አይደለም፤ አንቺ የበለጠ ስለሚያስፈልግሽ ነው ብለዋት ሄዱ።"
እና ነገሩን ስናደማው...ለቅመን ለቅመን እጃችን እየሞላ ድጋሚ ለመልቅም የምንሞክር ሰዎች እየበዛን ነው። ስግብግብነት እየበዛ ነው። እጃችን እየሞላ ዳር ላይ ባዶ እጁን ፣ ባዶ አፉን ፣ ባዶ ኪሱን የተቀመጠ ሰው እያየን አንድ እያነሳን አንድ በማይረባ ነገር እየጣልን እየኖርን ነው። የቀረበን ሁሉ ሊጎዳን ይመስለናል፡፡ መጥፎ የትላንት ታሪክ ስላሰረን ሁሌም ስለሰዎች ስናስብ ሰዎች መጥፎ እንደሆኑ ነው የምናስበው፡፡ እውነቱ ግን ይህ ነው፡፡ ማንም ሰው ሲፈጠር መልካም ነው፡፡ ሰውን ክፉ የሚያደርጉት መጥፎ አጋጣሚዎች ናቸው፡፡ እናም ሁሌ መልካም መልካሙን እናስብ፤ ቀና ቀናውን እንናገር፡፡ መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና፡፡
🙌መልካም አዳር እና ውሎ🙌

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ጥያቄ፡
አንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ከሌላ የእምነት ድርጅት ተከታይ ጋር የፍቅር ግንኙነት ቢጀምር ወይም ቢያገባ ችግሩ ምንድንነው?
መልስ፡
⚜ ምስጢር ያፋልሳል።
አምላካችን ቅዱሱን ጋብቻ ሲሰጠን በውስጡ ምስጢር አለበት። ይህም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው ጋብቻ የኢየሱስ ክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ ባል ሚስቱን የሚወዳትን ያህል ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ይወዳታል። ሚስት ለባልዋ የምትታዘዘውን ያህል ቤተ ክርስቲያንም ለክርስቶስ ትታዘዛለች። (ኤፌ 5፥23) ጋብቻ በሚያምኑና በማያምኑ ሰዎች መካከል ከተፈጸመ ምሥጢሩ ከክርስቶስና ከቤተ ክርስቲያን ተዋሕዶ ጋር አይስማማም፡፡ ከዚህም አልፎ ባልና ሚስት በጋራ መፈጸም ያለባቸውን ምስጢራት (ምስጢረ ተክሊል፡ ምስጢረ ቍርባን...) የማይፈጽሙ ይሆናሉ።
⚜ የጌታችንና የአባቶቻችን ትዕዛዝን ይጣረሳል።
📖 "እግዚአብሔር እስራኤልን ከሰባቱ አሕዛብ ጋር አትጋባ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ" (ዘዳ 7፥3) ስለዚህ የጌታችንን ትዕዛዝ ከመተላለፍ ባለፈ አምላካችንን የካደን ሰው ስናገባ ለአምላካችን ያለን ፍቅርን ጥያቄ ውስጥ ይከታል።
ቅዱስ ጳውሎስም በተደጋጋሚ ከሌላ የእምነት ድርጅት ተከታዮች ጋር ያለንን ከልክ ያለፈ ግንኙነት ያወግዛል። "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመድ ጽድቅ ከአመጽ ጋር ምን ተካፋይነት አለው? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ወይስ ከሚያምኑ ከማያምን ጋር ክፍል አለው?" (2ኛ ቆሮ 6÷14) "ከእነርሱ ጋራ እንዳትተባበሩ፣
እንደነዚህ ካሉት ጋር መብል እንኳ እንዳትበሉ እጽፍላችኋለሀ" (1ቆሮ 5÷11-12)
⚜ መልካም አመልን ያጠፋል።
አባቶቻችን ሲያስተምሩ ሰው ውሎውን ጓደኛውን ይመስላል "ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፣ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፣ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ" (መዝ 17÷26) "አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።"(1ኛ ቆሮ 15÷33) በመሆኑም ከአሕዛብ የተጋባ መጨረሻው አሕዛብ መሆን ነው። ለዚህም ትልቁ ማሳያ በምድራችን ከእርሱ በላይ ጠቢብ ያልነበረ አባታችን ሰሎሞን ነው። ሰሎሞን ፍቅር አዘንብሎት የአሕዛብን ሴቶች አገባ በመጨረሻም አምላኩን ረስቶ ለጣዖቶቻቸው ሰግዷል። (1ኛ ነገ 11፥4-8) ስለዚህ "እሷም በሃይማኖቷ እኔም በሃይማኖቴ" የሚለውን አባባል ከተለያዩ ማኅበረ ሰብእ ለመኖር እንጂ ለትዳር እንደማይሆን አውቀን ቢቻል እምነታችንን ሊያዳብርልን ከሚችል ሰው ጋር ነው መጋባት ያለብን።
⚜ ክፉ ፍሬ ይወጣበታል፡፡
የተለያየ እምነት ያላቸው ሰዎች የሚወልዱት ልጅ ሃይማኖት ለመምረጥ ይቸገራል። ብዙ ጊዜ እምነት የለሽ ወይም የአሕዛቡን እምነት ተከታይ ይሆናል። "እግዚአብሔር እስራኤልን ከሰባቱ አሕዛብ ጋር አትጋባ... እኔን እንዳያመልክ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና" (ዘዳ 7፥3)
⚜ በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ዘንድ ቁጣ እና መቅሰፍት ያስከትላል።
"እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ እናንተም ወደ እነርሱ እነርሱም ወደ እናንተ ብትደራረሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህችም ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፋ ድረስ መውደቂያና ወጥመድ በጎናችሁ መግረፊያ በአይናችሁ እሾህ ይሆንባችኋል…." (ኢያ 23÷12-13)
👉🏻 በእርግጥ ከአሕዛብ ወይም ከመናፍቃን ወገን የትዳር አጋር የመረጥን ካለን ትምህርተ ሃይማኖትን እንዲማሩና የክርስትና ጥምቀትን እንዲጠመቁ በማድረግ ቀድሰን ማግባት እንችላለን። "ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።" (1ኛ ቆሮ 7:14፤) (ፍት. አን. ፳፬፣ ቍ. ፱፻፲፪-፱፻፲፭)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!

"ፍቅር የበጎነት ሥራዎች ሁሉ ቁንጮ"
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንደጻፉት አያሌው ዘኢየሰሱ እንደተረጎመው
"ፍቅር በሥጋ ላይ ብቻ ሊያተኩር ይችላል በዚህ ጊዜ ፍቅር ምኞት ሆኖ ይለወጣል። እንዲህ ያለውን ነገር አንዳንዶች ፍቅር ብለው ይጥሩት እንጂ ምኞት ወይም ዝሙት ነው። ያንንም ይሁን ያን ራሱንም ሆነ የወደደውን ሰው ይጎዳል። የሚጎዳውም መንፈሳዊ ጉዳት ወይም ሌሎች ማናቸውንም ዓይነት ጉዳቶችን ነው። የጀግናው ሶምሶን ፍቅርና የደረሰበት ጉዳት ለዚህ ምሳሌ ሊሆን ይችላል (መሳ. 16፥4) እርሱ ለእግዚአብሔር የገባውን ቃል ኪዳን አፍርሷል ፍልስጥኤማውያን ማርከው ወስደውታል አዋርደውታል ዓይኖቹንም አውጥተዋቸዋል። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን እግዚአብሔር አምላክ ተለይቶታል (ምሳ16፥19) በሶምሶንና በደሊላ ላይ የደረሰው ነገር በዳዊትና በቤርሳቤህ ላይ ከደረሰው ነገር ጋር ይመሳሰላል። ይህ ምኞት ወይም ሥጋዊ ፍቅር ዳዊትን ወደ ማመንዘርና ወደ መግደል መርቶታል። በመሆኑም በዚህ ምክንያት እጅግ ከባድ ቅጣት ከእግዚአብሔር ተቀብሏል (2ኛ ሳሙ 12፥7) ስለ ሥጋዊ ፍቅር ሐዋርያው ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር "...እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት.."(1ኛ ዮሐ 2፥16) ናቸው ብሏል። እርሱ ይህ ነገር የሚያልፈው ዓለምና ምኞት አንድ ክፍል እንደ ሆነ ተናግሯል። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ትኩረት የሚሰጠው ለደስታ ለምቾትና ለቅንጦት ነው።"

ቶ
(ሣልሳዊ ቴዎድሮስ እየመጣ ነው)
////ሼር\\\\
እነሆ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ሀ ብሎ ሊጀምር በጣት
የሚቆጠሩ በጣም ጥቂት ዓመታት ብቻ ቀርተዋል።
ነገርግን ከትንሣኤው አስቀድሞ መከራ አለ፣ ግርፋት አለ፣
መዋረድ አለ፣ መራብና መጠማት አለ፣ ስቅለትና ሞት
አለ። ይኸው የመከራው ጊዜ አሐዱ ብሎ ጀምሯል።
በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮችና ኢትዮጵያን 'ከልባቸው
የሚወዱ' ኹሉ ጽኑ መከራ ያገኛቸዋል። ወቅቱ ለአሕዛብ
የጥጋብ ወቅት ነው። አሕዛብ የንጹሐንን ደም ያፈሳሉ።
ምድሪቱ በጽኑ መከራ ትመታለች። ርሀብና ቸነፈር
ጦርነትም ይሆናል። ታላቅ መናወጥ ይሆናል። ስንዴው
ከእንክርዳዱ እስከሚለይ ድረስ ታላቅ ሽብር ይሆናል።
ፍሬው ከገለባው እስከሚለይ ድረስ ኢትዮጵያ መሪር
ዕንባን ታነባለች። ይህን የመከራ ዘመን የሚያልፈው
ከሮጠ የቆመ፣ ከቆመ የተቀመጠ፣ ከተቀመጠ የተኛ ብቻ
ነው። ልጆቼ ሆይ ለመጥፎ ነገር አትሩጡ ይልቁንም
ለኃጢአት የዘገያችሁ ሁኑ።
እነዚህን የመከራ ዓመታትን በሰላም ታልፉ ዘንድ ንስሐ
ግቡ፣ ሥጋውንና ደሙን ተቀበሉ፣ አዘውትራችሁ
ወደእግዚአብሔር ቤት ገስግሡ። የኢትዮጵያን ትንሣኤ ታዩ
ዘንድ ትጉና ጸልዩ።
.
ከእነዚህ ጥቂት (ሦስት) የመከራ ዓመታት በኋላ አስቀድሞ
በቅዱሳን ስለ ንጉሥ ቶ
"ንጉሥ ከምሥራቅ ይነሳል። ከኤረር አብራክ ይወጣል።
በጣና ደሴትም ዘውድ ይደፋል። በግርማም በዙፋኑ ላይ
ይቀመጣል። ያን ጊዜ ኢትዮጵያ እንደ ደጀን ተራራ
ትገዝፋለች። ምልክቷም ከአርማዎች ሁሉ በላይ ጎልቶ
ይታያል። ዝናዋ እንደ አዜብ ነፋስ ዓለምን ይመላል።
ክብሯም እንደ ግዮን ወንዝ በምድር ሁሉ ይፈሳል።
የተጠሙትም ይጠጡ ዘንድ ወደ እርሷ ይመጣሉ። በዚያን
ዘመን እንኳን የሰው የዛፍ ጠማማ አይኖርም። በምድሪቱ
ሰላም ይሰፍናል። ርሀብና ቸነፈር ለቅሶና ሀዘን ጠፍቶ
ደስታና ምስጋና በአገሪቱ ይመላል። ከንጉሡ ግርማ የተነሣ
የሚፈታተኗት ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ። ያንጊዜም የኢትዮጵያ
ጠላቶች ይከስማሉ። የናቋትም ሁሉ ወደ እግሯ ጫማ
ይሰግዳሉ። ያን ጊዜም የግዮን ልጆች ሁሉ ከኦፊር ወርቅ
ይልቅ ያማረ ከግዮንም ማዕድን በላይ የከበረ ምስጋናን
ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ ልጆች ከደስታቸው
ብዛት የተነሣ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ በመቅደሱ
ዙሪያ ይሰባሰባሉ። ትንሣኤዋን ዐይተዋልና ንሴብሖ
እያሉም ይዘምራሉ።" ተብሎ የተነገረው ትንቢት
ይፈጸማል።
.
አሜን ቶሎ ና!!!
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር!!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅልን።
(ሣልሳዊ ቴዎድሮስ እየመጣ ነው)
////ሼር\\\\
እነሆ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ሀ ብሎ ሊጀምር በጣት
የሚቆጠሩ በጣም ጥቂት ዓመታት ብቻ ቀርተዋል።
ነገርግን ከትንሣኤው አስቀድሞ መከራ አለ፣ ግርፋት አለ፣
መዋረድ አለ፣ መራብና መጠማት አለ፣ ስቅለትና ሞት
አለ። ይኸው የመከራው ጊዜ አሐዱ ብሎ ጀምሯል።
በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮችና ኢትዮጵያን 'ከልባቸው
የሚወዱ' ኹሉ ጽኑ መከራ ያገኛቸዋል። ወቅቱ ለአሕዛብ
የጥጋብ ወቅት ነው። አሕዛብ የንጹሐንን ደም ያፈሳሉ።
ምድሪቱ በጽኑ መከራ ትመታለች። ርሀብና ቸነፈር
ጦርነትም ይሆናል። ታላቅ መናወጥ ይሆናል። ስንዴው
ከእንክርዳዱ እስከሚለይ ድረስ ታላቅ ሽብር ይሆናል።
ፍሬው ከገለባው እስከሚለይ ድረስ ኢትዮጵያ መሪር
ዕንባን ታነባለች። ይህን የመከራ ዘመን የሚያልፈው
ከሮጠ የቆመ፣ ከቆመ የተቀመጠ፣ ከተቀመጠ የተኛ ብቻ
ነው። ልጆቼ ሆይ ለመጥፎ ነገር አትሩጡ ይልቁንም
ለኃጢአት የዘገያችሁ ሁኑ።
እነዚህን የመከራ ዓመታትን በሰላም ታልፉ ዘንድ ንስሐ
ግቡ፣ ሥጋውንና ደሙን ተቀበሉ፣ አዘውትራችሁ
ወደእግዚአብሔር ቤት ገስግሡ። የኢትዮጵያን ትንሣኤ ታዩ
ዘንድ ትጉና ጸልዩ።
.
ከእነዚህ ጥቂት (ሦስት) የመከራ ዓመታት በኋላ አስቀድሞ
በቅዱሳን ስለ ንጉሥ ቶ
"ንጉሥ ከምሥራቅ ይነሳል። ከኤረር አብራክ ይወጣል።
በጣና ደሴትም ዘውድ ይደፋል። በግርማም በዙፋኑ ላይ
ይቀመጣል። ያን ጊዜ ኢትዮጵያ እንደ ደጀን ተራራ
ትገዝፋለች። ምልክቷም ከአርማዎች ሁሉ በላይ ጎልቶ
ይታያል። ዝናዋ እንደ አዜብ ነፋስ ዓለምን ይመላል።
ክብሯም እንደ ግዮን ወንዝ በምድር ሁሉ ይፈሳል።
የተጠሙትም ይጠጡ ዘንድ ወደ እርሷ ይመጣሉ። በዚያን
ዘመን እንኳን የሰው የዛፍ ጠማማ አይኖርም። በምድሪቱ
ሰላም ይሰፍናል። ርሀብና ቸነፈር ለቅሶና ሀዘን ጠፍቶ
ደስታና ምስጋና በአገሪቱ ይመላል። ከንጉሡ ግርማ የተነሣ
የሚፈታተኗት ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ። ያንጊዜም የኢትዮጵያ
ጠላቶች ይከስማሉ። የናቋትም ሁሉ ወደ እግሯ ጫማ
ይሰግዳሉ። ያን ጊዜም የግዮን ልጆች ሁሉ ከኦፊር ወርቅ
ይልቅ ያማረ ከግዮንም ማዕድን በላይ የከበረ ምስጋናን
ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ ልጆች ከደስታቸው
ብዛት የተነሣ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ በመቅደሱ
ዙሪያ ይሰባሰባሉ። ትንሣኤዋን ዐይተዋልና ንሴብሖ
እያሉም ይዘምራሉ።" ተብሎ የተነገረው ትንቢት
ይፈጸማል።
.
አሜን ቶሎ ና!!!
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር!!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅልን።
"የንስሐ አባት መያዝ ለምን ያስፈልጋል?"
(ክብረ ክህነት - በዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ)
✟ክፍል ፩✟
ጌታችን " በወንጌል በቀን የሚሄድ ሰው አይሰናከልም የዚህን አለም ብርሃን ያያልና በጨለማ የሚሄድ ግን ይሰናከላል!!” ብሎ ተናግሯል:: የዚህ ቃል ትርጉም አንድም በምክረ ካህን በ ፈቃደ ካህን የሚኖር ሰው ነፍሱ ከሃጢአት እንደምትጠበቅ ያስረዳል፡፡ የዚህ አለም ብርሃን የተባሉት ጌታችን “እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ” ያላቸው ካህናት ሲሆኑ "በቀን የሚሄድ" የተባለው ደግሞ በምክረ ካህን የሚኖር ሰው ነው፡፡
በወንጌል “ ለወይን ስፍራዉ ሰራተኞችን ይቀጥር ዘንድ በማለዳ ወጣ በአስራ አንድ ሰአትም ቀጠረ” የሚለዉ ምሳሌ፡ ማለዳ በተባለ የልጅነት እድሜ ላይ የሚጠብቅ የሚኮተኩት መምህረ ንስሃ መያዝ እንደሚያስፈልግ ያሳያል፡፡ ዕድሜያችን ለሀጢአት በደረሰችበት ቅፅበት ለንስሃም (ለኑዛዜም) ትደርሳለችና፡፡
በሲራክ 6÷6 ላይ “ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡” የሚለው ቃል ምእምናን ስለ ሐይማኖትና ምግባር የሚያስተምራቸው ብዙ ካህናት ሊኖሩዋቸው ቢችሉም ከብዙዎች አንዱ ግን ንስሃቸውን የሚናዘዙለት መምህረ ንስሃ ሊሆናቸው እንደሚገባ ያጠይቃል፡፡
አዳም በገነት ለሰባት አመታት ከቆየ በሁዋላ በዲያቢሎስ ተፈትኖ እንደወደቀ፡ በሃጢያት መፈተንና መዉደቅ ለሰው የሚፀናበት ዕድሜ ከሰባት አመት ጀምሮ ስለሆነ ወደ ንስሃ አባት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
በምክረ ካህን መኖር ራሱ ትልቅ መንፈሳዊ ማእረግ ነው የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ሰዎች የሚከብሩትን ያህል በምክረ ካህን የሚኖሩ ምእምናን ከአማኒያን በላይ የከበሩ ናቸዉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ 12 አመቱ ከመምህራን ጋር መገናኘቱ እኛም ከልጅነታችን ጀምሮ ከ መምህራን አባቶች ጋር እንድንገናኝ አብነት ይሆን ዘንድ ነዉ፡፡ ማቴ. 20÷2
#ሀጢያትን_መናዘዝ_ለምን_አስፈለገ?
ሀጢያትን ለእግዚአብሄር በካህን በኩል መናዘዝ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለዉ ጠቃሚ ጉዳይ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር አዳም በበደለ ጊዜ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ?” ብሎ የጠየቀዉ አዳም እንዲናዘዝ ስለፈለገ እንጂ አዳም ያደረገዉን ሳያዉቅ ቀርቶ አልነበረም፡፡ “እምቅድመ ይፍጥሮ ለአዳም የአምር ግብሮ” ”አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ስራዉን ያዉቃል” እንዲል፡፡ አዳምም እግዚአብሔር በጠየቀዉ ጊዜ ”ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” በማለት ተናዝዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች ሀጢያታቸዉን ይናዘዙ እንደነበር በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልጿል፡፡ ሐዋ 19÷18 ፡ ማቴ 3÷5-6፡ ዘሌ 5÷16፡ ኢያ 2÷19፡፡ ይሁን እንጂ “ሀጢያቴን ለመተዉ ከፈቀድኩ አይበቃም ወይ? መናዘዙ ለምን አስፈለገ?” የሚሉ ሰዎች አሉ ሀጢያትን በካህን ፊት መናዘዝ ግን የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት፡- ሀጢያትን በዝርዝር በካህን ፊት መናዘዝ ዳግመኛ በዚያ ሀጢያት ላለመያዝ ሀይልን ይሰጣል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በበደሉ ላይ ድፍረትና ሽንገላን የሚጨምር (ሀጢያት ሰርቶ እንዳልሰራ ዝም የሚል) ከዚያች ሀጢያት መጠበቅ አይችልም፡፡ እርስዋን በምትመስል ሀጢያት ከመዉደቅም አይድንም” እንዳለ፡፡
ንጉስ የሚሽረዉና የሚሾመዉን ግራና ቀኝ አቁሞ የሚሽረዉን ወቅሶ የሚሾመዉን አሞግሶ እንደሚያከብር ያለፈ ሀጢያታችንን በካሕኑ ፊት ስንዘረዝርም ያለፈዉን ሀጢያታችንን ሽረን በሚመጣዉም ህይወት ያንን ሀጢያት ላለመድገም እየወሰንን ነው፡፡
ኑዛዜ ያሳቅቃል፡፡ መሳቀቁ ደግሞ ለሰራነዉ ሀጢያት ዋጋ ነዉ፡፡ በፍርድ ቀን ጌታ በሰማይ መላእክት ፊት ሀጢያታችንን ገልጦ ከሚያሰቅቀን ይልቅ እኛዉ እራሳችን እዚሁ እንደኛዉ ደካማ ሰዉ በሆነው በካህኑ ፊት በመናዘዝ ለሰራነው እጅግ ግዙፍ ሃጢያት የምንቀበለው ኢምንት ቅጣት ነው፡፡
በሽታውን የደበቀ መድሃኒት የለውም እንደሚባለው የነፍሱን ደዌ ሀጢያቱን የሚደብቅም እንዲሁ መፍትሄ አያገኝም፡፡ የካህኑን ፀሎትና ምክርም ያጣል፡፡ “ሀጢያቱን የሚደብቅ /የሚሰውር አይለማም፡ የሚናዘዛትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል” እንደተባለ ፡፡ ምሳ 28÷13
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @zekidanemeheret
☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝

+++ሳያቋርጡ የመጸለይ ጥበብ+++
የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ ሲኖር ለቅጽበትም ቢሆን አእምሮው ሊረሳውና ሊያቋርጠው የማይችለው ነገር ምን እንደሆነ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ሰውነቱ በእንቅልፍ ተሸንፎ እንኳን ቢተኛም እያንቀላፋ አስታውሶ የሚያደርገው ክንውን የትኛው እንደሆነ አስተውላችኋል? እንደው አይሆንም እንጂ ሆኖለት ለደቂቃዎች ሰውነቱ ይህንን ተግባር በመርሳት ባያከናውነው ሕልውናው አጠያያቂ ሁኔታ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ይህ ሰውነታችን ልምድ ያደረገውና ለአፍታ እንኳን መቋረጥ የማይፈልገው ተግባር አየር ማስገባትና ማስወጣት ወይም መተንፈስ ነው፡፡
ለዚህ ጽሑፍ ይህን የተፈጥሮ እውነት እንደ መነሻ የተጠቀምነው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጸሎትን እንደ ነፍስ እስትንፋስ ይቆጥሯታል፡፡ አየር ያጠረው ወይም ወደ ሰውነቱ የማያስገባ ሰው በሕይወት የመቆየት ዕድሉ ጠባብ እንደሆነ ፤ እንዲሁ ከጸሎት የተለየች ነፍስም ወደ ሞት መንደር የመውረዷ ነገር የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ነፍሳችን ሕያዊት የምትሰኘው በአረጋዊ መንፈሳዊ መጽሐፍ ላይ ‹የነፍሴ ነፍሷ› ተብሎ ከተጠራው መንፈስ ቅዱስ ጋር በጸሎት ትስስርን ስትመሰርት ነው፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙም እንደሚያስተምረው ሰው ከእስትንፋሱ የበለጠ ዘወትር ፈጣሪውን በጸሎት ሊያስታውስ ይገባዋል፡፡
ጸሎት ማለት ምን ማለት ነው? ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 14 ላይ ‹ጸሎትስ ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገራት ነገር ናት› ሲሉ የጸሎትን ትርጉም ይነግሩናል፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ አይነት መንገድ ሊያናግራቸው ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በራእይ በመገለጥ ወይም ቅዱስ ዳዊት ‹እግዚአብሔር ለሕዝቡ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል› ሲል እንደ ዘመረው በመጽሐፍ በኩል ማናገር ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡ የሰው ልጆች ደግሞ ከፈጣሪያቸው ጋር የሚነጋገሩት ጸሎት በተባለ ድልድይ አማካኝነት ያነጋግሩታል፡፡
መተንፈስ ለሥጋዊው አካላችን የዕለት ተዕለት የማይቋረጥ ሥራው እንደሆነ ሁሉ የነፍስ እስትንፋስ የተባለች ጸሎትም ለክርስቲያን የየዕለት መንፈሳዊ ተግባር ናት፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹ሳታቋርጡ ጸልዩ› በማለት የሚመክረን (1ኛ ተሰ 5፡17)፡፡
በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ሶርያዊው አባ ይስሐቅ (ማር ይስሐቅ) ቅዱሳን ምንም ዓይናቸው በእንቅልፍ ሽፋሽፍት ቢያዝ እንኳን ነፍሳቸው ግን ከእግዚአብሔር ጋር በሚደረግ የማይቋረጥ ንግግር (ጸሎት) ውስጥ ስለምትገኝ ተኝተውም ቢሆን ጸሎትን እንደማያስታጉሉ ይናገራል፡፡ እኛ በዓለም የምንኖር ግን የሥጋ ድካም ስላለብን ቀኑንም ፣ማታውንም በጸሎት የማሳለፍ ብርታቱ የለንም፡፡ በመሆኑም ‹ሳታቋርጡ ጸልዩ› የሚለው የሐዋርያው ትዕዛዝ ይከብድብናል፡፡
በዚህም ምክንያት እንደ እኛ ሥጋ ለባሽ የሆኑ አባቶቻችን ይህን ድካማችንን አይተው ቀኑን ሁሉ በጸሎት ማሳለፍ ባትችሉ እንኳን ቢያንስ በቀን ሰባት ጊዜ እግዚአብሔርን ስለ እውነተኛ ፍርዱ አመስግኑት ሲሉ ሰባት የጸሎት ጊዜያቶች ወስነውልናል (መዝ 119፡164)፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አሁንም ከፈጣሪው ጋር ቀኑን ሙሉ በጸሎት የማሳለፍ ጽኑዕ ፍላጎት ላለው ክርስቲያን አባቶች የሚያስተምሩት ሌላ ‹ሳያቋርጡ የመጸለይ ጥበብ› አለ፡፡ ይህንን ጥበብ የምናገኘው ቅዱስ ጰላድዮስ (St. Palladius) የተባለው አባት ባሰባሰበውና የብዙ አባቶችን ዜና ሕይወት ይዞ በሚገኘው ‹መጽሐፈ ገነት› ላይ ነው፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው ፡-
በአንድ ወቅት አባ ሉቅዮስን (Abba Lucius) ለማየት የመጡ ጥቂት መነኮሳት እንዲህ አሉት ‹በእጃችን ምንም አይነት ሥራን አንሠራም፡፡ የቅዱስ ጳውሎስን ትዕዛዝ በማክበር ሳናቋርጥ እንጸልያለን እንጂ!›፡፡ አረጋዊው መነኩሴ አባ ሉቅዮስም ‹አትመገቡም? ወይም አትተኙምን?› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ‹አዎን! እንተኛለን ፤ እንመገባለን› ሲሉ መለሱ፡፡ አባ ሉቅዮስም ‹ወንድሞቼ ይቅርታ አድርጉልኝና የምትሉትን ነገር (ሳያቋርጡ መጸለይን) እየፈጸማችሁ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ በእጆቼ ሥራን እየሠራሁ እንዴት ሳላቋርጥ እንደምጸልይ አሳያችኋለሁ፡፡ ዘወትር ጠዋት በእግዚአብሔር እርዳታ የዘንባባ ዛፍ ቅሪቶችን እሰበስብና እነርሱን ሽጬ አሥራ ስድስት ሳንቲሞችን አገኛለሁ፡፡ ከዚያም ሁለቱን ሳንቲሞች ከቤቴ በር ደጃፍ ላይ አስቀምጥና በቀረው ምግብ እገዛበታለሁ፡፡ የገዛሁትንም ምግብ ተመግቤ ስተኛ ፤ ያ ከቤቴ ደጃፍ ላይ ሁለቱን ሳንቲሞች የወሰደው ነዳይ ደግሞ ስለ እኔ ይጸልያል፡፡ እንዲህ እያደረግሁ በእግዚአብሔር ረድዔት ሳላቋርጥ እጸልያለሁ› በማለት ልምዱን አካፈላቸው፡፡
ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ከጸሎት ጋር በቀን ማከናወን ያለበትን ሥራ ሥርቶ ከጨረሰ በኋላ አመሻሽ ላይ ከሚያገኘው ትርፍ ለነዳይ ቢመጸውት ብዙውን ሰዓት በእንቅልፍ የሚያሳልፍበትን ሌሊት በምጽዋት እያካካሰ ሳያቋርጥ ሊጸልይ ይችላል ማለት ነው፡፡
ሳናቋርጥ እንጸልይ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን

የአሳብ ውጊያ
አባ ዮሴፍ ስለ ክፉ አሳቦች ጠየቀና አባ ጳኵሚስ እንዲህ አለው፡- “ልክ አንድ ሰው ማሰሮ ውስጥ እባብና ጊንጥ እንደሚያስቀምጠው አፉንም እንደሚያትመው እባቡና ጊንጡም በጊዜ ሂደት እንደሚሞቱ ልክ እንደዚሁ ርኵስ አሳብም በትዕግሥት ስንጸና ይመክናል ።” (ጳኵሚስ ቊ. 20)
የሰው ልጅ አንድ ጊዜ ወይም በተደጋጋሚ ከሚያልፍባቸው ፈተናዎች አንዱ የአሳብ ውጊያ ነው ። በአሳብ ላይ የሚነሡ የተለያዩ የውጊያ ዓይነቶች ምእመኑን ያሳቅቁታል ። ገልጦ ለመናገር ስለሚያፍር በውስጡ ብርቱ ዝለት ይገጥመዋል ። ከራሱ ለመሸሽ ሙከራ ቢያደርግም ከራስ መሸሽ ስለማይቻል ግራ ይጋባል ። እነዚህ አሳቦች በውስጡ ስለሚጮኹ ዕረፍት የለሽ ይሆናል ።እነዚህን አሳቦች ለማጥፋት አንዳንድ ጊዜ ጾምና ጸሎት ቢይዝም ነገር ግን የማይወገዱ ይሆናሉ ። በዚህ ምክንያት ምንም መፍትሔ የለም ብሎ ተስፋ ወደ መቊረጥ ይደርሳል ። በዚህ የተነሣ ምእመኑ ራሱን እየጠላ ይመጣል ። ራሱን ስለሚጠላም ከሰዎች ጋር መገናኘት እያስጠላው ይመጣል ። እግዚአብሔር የረድኤት እጁን ከእርሱ ላይ እንዳነሣ ብቻውን ለመታገል የተተወ እንደሆነ ይሰማዋል ። በዚህም ሆደ ባሻነትና ምስኪንነት የሚያሰቃየው ይሆናል ። በእነዚህ ርኵስ አሳቦች የሚያልፍ ክርስቲያን በቀላሉ ወደ ድብርት ውስጥ ይገባል ። የራሱ እየመሰሉት ስለሚጨነቅም ለሕመም እየተጋለጠ ይመጣል ። አሳቦቹን ተከትሎም የጠላት ክስ ስለሚመጣ የመቆም አቅም እያጣ ይመጣል ። በዚህ ምክንያት ምእመን ከጸሎት ፣ አገልጋይ ከአገልግሎት ፣ መነኩሴ ከምንኩስናው ሊወጡ ይሰናዳሉ ።
የእነዚህ ርኵስ አሳቦች ምንጫቸውን ባለማወቁ ምክንያት ከወዳጆቹና ከቤተ ክርስቲያን ከአገልግሎቱም እየራቀ ይመጣል ። እነዚህን ርኩስ አሳቦች ለመናገር ወደ መንፈሳዊ መምህራን ዘንድ ቢሄድም ብዙ ጊዜ ሳይናገር አፍሮ ይመለሳል ። እርሱ ብቻ በዚህ ውስጥ የሚያልፍ እየመሰለው ይጨነቃል ። እንዴት እኔ ይህን አሰብሁ በማለት ይረበሻል ። በመንፈሳዊ ወንድሙና እህቱ ላይ የተቀረጸበትን ርኵስ አሳብ እያስታወሰ ይሸማቀቃል ። የተግባር ምንጩ አሳብ ነው ሲባል ስለሰማም የፈጸመው ያህል መሸበር ይጀምራል ። በዚህ ውስጥ አንድ ነገር መገንዘቡ አይቀርም ። ገና ያልደረሰበት መንፈሳዊ ውጊያ እንዳለ ያውቃል ። እነዚህ ርኩስ አሳቦች የሚያመጡት ስጋት ፡-
• ከእግዚአብሔር መንግሥት ብለይስ ?
• እግዚአብሔር ቢያዝንብኝስ ?
• ድንገት ወደ ተግባር ቢለወጡስ ?
• በውስጤ ያለውን ሰው ቢያውቀውስ ? እያለ መጨነቅ ይጀምራል ።
እነዚህ አሳቦች ብዙ ዓይነት ናቸው ።
1- በእግዚአብሔር ላይ የሚነሣሡ ክፉ አሳቦች፡- የእግዚአብሔርን ህልውና እንዲጠራጠር ፣ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃላት እንዲናገር የሚመጡ ርኵስ አሳቦች አሉ ።
2- እንዲህ ቢሆንስ የሚሉ ክፉ አሳቦች፡- ለሁሉም ነገር ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች እንዲህ ቢሆንስ ? የሚል ጭንቀት ውስጥ ፈጥነው ይገባሉ ። ያላደረጉትን ባደርገውስ ቀጥሎ ምን እባላለሁ ? የሚል ስሜት በውስጣቸው ይፈጠራል ። እጅግም ጥንቃቄ ከስህተት ይጥላል ። ባልተጨበጡ አሳቦች መናጥ የብዙ ሰዎች ፈተና ነው ።
3- ሕይወትን የሚያስጠሉ ክፉ አሳቦች፡- ሰውዬው መኖሩን እንዲጠላ ፣ ራሱን እንዲያጠፋ ጭምር የሚመጡ ክፉና ሰይጣናዊ አሳቦች አሉ ።ይህ አሳብ ትልልቅ የእግዚአብሔር ሰዎችን ሳይቀር ሞግቷል ።
4- ዋጋ የለኝም የሚል ርኵስ አሳብ፡- ሰይጣን ኃጢአትን አባብሎ ያሠራናል ፤ ከሠራን በኋላ ወዲያው ቅድም እንዳልነበረ ሁኖ ይከስሰናል ። የሚያሠራን ቅድስናችን እንዲጎድፍ ነው ፤ የሚከስሰን ንስሐ እንዳንገባ ነው ።
እነዚህ ርኩስ አሳቦች በውስጣችን ሲፈጠሩ መሸሽ ባለድል አያደርገንም ። በልባችን እየጸለይን መጋፈጥ ያስፈልገናል ። እነዚህ አሳቦች የእኛ እንደሆኑ ገምተን ስንጨነቅ ሰይጣን ግራ በመጋባታችን ይስቃል ። እነዚህ አሳቦች በምንም መንገድ የእኛ አይደሉም ። የሰው ልጅ አወቅሁ ብሎ የሚያስባቸው ክፉ አሳቦች እንዳሉ እናውቃለን ። ባለቤቱ እየቀፈፈው በውስጡ የሚነሡ አሳቦች ግን ከሰይጣን ናቸው ። ሰይጣን እነዚህን አሳቦች ቢያስብ አይረበሽም ። ምክንያቱም ሁለንተናው ረክሷል ። በእነዚህ አሳቦች መረበሻችን ሕሊናና መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር እንዳሉ ደግሞም የመቀደስ አሳብ እንዳለን የሚያሳዩ ናቸው ። እነዚህ ርኵስ አሳቦች በውስጣችን ለዕለታት ፣ ለሳምንታትና ለወራት አንዳንዴም ለዓመታት ሊቆዩ ይችላሉ ። ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ካሰብሁት ያደረግሁት ያህል ነው ብለን ወደ ተግባር እንዳንለውጣቸው ነው ። እነዚህን ርኵስ አሳቦች ከምናሸንፍበት መንገዶች ጥቂቶቹን እንጥቀስ፡-
1- በአሳቦቹ ተጠያቂ እንደሆንን አድርገን ማሰብ የለብንም ። የምንጠየቀው በተግባር ስንለውጣቸው ብቻ ነው ።
2- ላለማሰብ በጣም ጥረት ባደረግን ቊጥር እያሰብናቸው እንመጣለን ። አሳብ በአሳብ ይሻራልና የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ይገባናል ።
3- በጊዜ ውስጥ አሳቦቹ እየበነኑ ይመጣሉ ። ስለዚህ በትዕግሥት መጠበቅ ይገባል ።
4- የእግዚአብሔርን ስም በመጥራት ሰይጣንን አሳብህን አንስተዉም ብለን መገሠጽ ይገባል ።
5- በመንገድ ስንሄድ መኪና ውኃ ቢረጨን እንበሳጫለን እንጂ አንጸጸትም ። የእኛ ችግር አይደለም ። በሕይወት መንገድ ላይ ሰይጣን ክፉና የቆሸሹ አሳቦችን ቢረጨን መጨነቅ የለብንም ።
በክፉ አሳብ እየተንገላታ ላለ ወንድም አባ ጳኵሚስ ሲመክረው እንዲህ ብሏል፡- “በዚህ ርኵስ አሳብ አትደንግጥ ። ብዙ ጊዜ ሥጋዊ ውጊያዎች ግድየለሽ በመሆናችን ይመጡብናል ፤ ነገር ግን ይህ ርኵስ አሳብ ግድየለሽ በመሆናችን ምክንያት የሚመጣ አይደለም ። ይህ የእባቡ የራሱ ማታለያ ውጊያ ነው። ይህ ርኵስ አሳብ ሲመጣብህ ተነሥና ጸልይ ፣ አማትብ በውስጥህ ለጠላታችን እንደምትናገረው ሁነህ እንዲህ በል ‘እግዚአብሔር ሁሉንም እየመገበ እንደሚኖር አምናለሁና አንተና ስድብህ የተወገዛችሁ ሁኑ! ሰይጣን ይህ ያንተ ነውና ስም ማጉደፉ በራስህ ላይ ይሁን ! ይህ ርኩሱ አሳብ ርኩስ ከሆንከው ካንተ እንጂ ከእኔ አይደለም ።’ እግዚአብሔርም ከዚህ ውጊያ ነጻ እንደሚያደርግህ አምናለሁ ።”
ክፉ አሳቦች በእባብና በጊንጥ ተመስለዋል ። እባብ ለስላሳ ነው ፣ ልክ እንደ እባቡ አታላይ የሆኑ ፣ ለደስታ የሚጠቅሙ የሚመስሉ አሳቦችን ሰይጣን ይረጫል ። በዚህ መንገድ እንቢ ስንለው ደግሞ እንደ ጊንጥ የሚናከሱ ክፉ አሳቦችን ሊያጣብቅብን ይመጣል ። ለስላሳ የሆኑ አሳቦችን ሰውዬው ተግባራዊ ካደረገ በኋላ ውስጡ በክስ መሰቃየት ይጀምራል ። ሁልጊዜም እየወደቀ ማልቀስ ሥራው እንዲሆን ጠላት ያደባበታል ። እንደ ጊንጥ ያሉ አሳቦችን ደግሞ ነክሰው እንዲይዙትና በእምነቱ ተስፋ እንዲቆርጥ ይገፋፉታል ። ተስፋ ከቆረጠ የሚደሰተው በኃጢአት ነው ። የክፉ አሳቦች አመጣጥ ስልቱ የተለያየ ቢሆንም ግቡ ግን እኛን በኃጢአት መጣል ነው ። እግዚአብሔር ግን በትዕግሥት ከሠራን በኋላ ፈተናውን ያርቅልናል ።
ጸሎት
የልቤ አምላክ ፣ ነፍሴን የምታስደስት አንተ ነህ ። ባልተፈተነ ሕይወት ክርስቲያን ነኝ ማለት ቀላል ነው ። ጌታ ሆይ ውጫዊ ሰይፍ ሲበርድ ያለውን ውስጣዊ ሙግት እንዳውቀውና እንድዋጋው እርዳኝ ። አሳቤ የተበከለ ሲመስለኝ በስምህ የሚገኘውን ድል እንድለማመድ አግዘኝ ። አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ። እኔንም ለእኔ አትተወኝ ። በዘላለማዊ ምክርህ አሜን ።

✝✞✝ እንኩዋን ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝
✝✞✝ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ✝✞✝
=>ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::
+ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::
+በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)
+ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::
+"+ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ +"+
=>ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን እንደ ረዳው ታስተምራለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 5 ላይ እንደ ተጻፈው ቅዱሱ መልአክ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: እሥራኤልን በምድረ በዳ የመራ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሲያርፍ ታላቅ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር::
+እግዚአብሔር ግን ኢያሱን አስነስቶ አረጋግቷቸዋል:: ቅዱስ ሚካኤል 40ውን ዘመን እሥራኤልን ደመና ጋርዶ: መና አውርዶ: ክንፉን ዘርግቶ: ጠላትን መክቶ ከሙሴ ጋ እንደ መራቸው ከኢያሱ ጋርም ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወረደ::
+በኢያሪኮ አካባቢም የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በግርማ ለኢያሱ ታየው:: ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ "አንተ ከእኛ ወገን ነህን? ወይስ ከጠላቶቻችን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ ሚካኤልም መልሶ "እረዳህ ዘንድ እነሆ የሠራዊት አለቃ ሆኜ ተሹሜ መጥተቻለሁ" አለው::
+ያን ጊዜ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰገደለት:: ቅዱሱ መልአክም አክሎ "ፍታሕ ቶታነ አሳዕኒከ እም እገሪከ: እስመ ምድር እንተ ትከይዳ ቅድስት ይዕቲ - የረገጥካት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ" አለው::
+ኢያሱም የተባለውን አደረገ:: ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን "ለመላእክት የጸጋ (የአክብሮ) ስግደት ይገባል: በቅዱሳኑ ፊትም ጫማ ተለብሶ አይቆምም" የምትለው:: ያ መሬት ሊቀ መላእክት ቢቆምበት ተቀድሷል:: ዛሬም ቤቱ በታነጸበት: ታቦቱ በተቀረጸበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱ መልአክ አለና ጫማን አውልቆ: ባጭሩ ታጥቆ መግባት ይገባል::
+ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከኢያሱ ጋር ሆኖ አማሌቅን ጨምሮ የእሥራኤልን ጠላት አጥፍቷል:: ጥቅመ ኢያሪኮን (ቅጥሩን) አፍርሷል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: በገባኦን ፀሐይን: በቆላተ ኤሎምም ጨረቃን ሲያቆም ከእርሱ ጋር ሆኖ ረድቶታል::
+"+ ዱራታኦስና ቴዎብስታ +"+
=>ቅዱሳኑ ዱራታኦስ (ዶርታኦስ) እና ቴዎብስታ (ቴዎብስትያ) የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ:: በድርሳነ ሚካኤልና በመጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ እንደምናገኘው 2ቱ ቅዱሳን በተቀደሰ ትዳር ተወስነው: ሕጉን ትዕዛዙን ፈጽመው: ለነዳያን ራርተው: ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ ነበሩ::
+ይልቁኑ ግን የጌታችን: የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያለማስታጐል ያደርጉ ነበር:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ሐብት ንብረታቸው አልቆ ተቸገሩ:: ግን የጨነቃቸው መቸገራቸው ሳይሆን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ሊያቆሙ መሆናቸው ነው::
+አማራጭ ሲያጡ ተቀምጠው ተመካከሩ:: የቅዱሱ መልአክ ዝክር ከሚቀር ልብሳቸውን (ያውም የክብር ልብሳቸውን) ሊሸጡ ተስማሙ:: በዚህ መሰረት ቅዱስ ዱራታኦስ ወደ ገበያ ሲሔድ ወዳጁ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወረደለት::
+መንገድ ላይም የጦር መኮንን ሃገረ ገዢ መስሎ ተገናኝቶ አጫወተው:: ችግሩን ጠይቆም መፍትሔውን ነገረው:: "እኔ እዋስሃለሁና ለበዓል የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሁሉ ገዝተህ አሰናዳ" አለው::
+"እኔ ወደ ቤትህ መጥቼ ስለምስተናገድ አንድ አሣ አምጥተህ አቆየኝ:: እኔ ሳልመጣ ግን አትረደው" አለው:: ቅዱስ ዱራታኦስ የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ ወደ ቤቱ ሲሔድ ድንቅ ነገርን ተመለከተ:: ሚስቱ ቅድስት ቴዎብስታ በቤቱ መካከል ሁና ቤቱ በበረከት ሞልቷል::
+ማሩ: ቅቤው: እሕሉ ሁሉ በየሥፍራው ሞልቷል:: ባልና ሚስቱ ደስ ብሏቸው:: ነዳያንን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ዋሉ:: በሁዋላ ያ መኮንን (ቅዱስ ሚካኤል) በቤታቸው መጥቶ ተስተናገደ::
+በእርሱ ትዕዛዝ የአሣው ራስ (ሆድ) ሲከፈት በውስጡ 300 ዲናር ወርቅ (እንቁ) ተገኘ:: ቅዱሳኑ ይህን ተመልክተው ሲደነግጡ ቅዱስ ሚካኤል ክንፉን ዘርግቶ ራሱን ገለጸላቸው:: ደንግጠው በግንባራቸው ተደፉ::
+እርሱ ግን "በተገኘው ሃብት እዳችሁን ክፈሉ:: ከዚህ በሁዋላ ግን በምድር አትቸገሩም:: በሰማይም ክፍላችሁ ከእኔ ጋር ነው" ብሎ ባርኩዋቸው ወደ ሰማይ ዐረገ:: እነርሱም በሐሴትና በበጐ ምግባር ኖረው ዐርፈዋል:: ለርስቱም በቅተዋል::
+"+ ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ +"+
=>የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::
*በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
*በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
*በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
*ምጽዋትን ያዘወተረ::
*አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::
+"+ አፄ በእደ ማርያም +"+
=>"በዕደ ማርያም" ማለት "በማርያም እጅ" እንደ ማለት ነው:: እኒህ ሰው የኢትዮዽያ ንጉሥ ሲሆኑ የነገሡትም በ1460 ዓ/ም ነው:: ደጉ አባታቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሲያርፉ በመንግስቱ ተተክተው ሃገራችንን አስተዳድረዋል:: ድርሰት ደርሰዋል:: አብያተ መቃድስ አንጸዋል::
+በተለይ ለቅኔ ትምሕርት ማበብ ልዩ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይነገራል:: ልክ በነገሡ በ10 ዓመታቸው ግን መንግስተ ምድር በቃኝ ብለው በምናኔ በርሃ ገብተዋል:: በዙፋናቸውም አፄ እስክንድር ተተክተዋል:: ጻድቁ ንጉሥ ግን ቅዱስ ሚካኤልን ይወዱት ነበርና በዚህች ቀን ዐርፈዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም አይለየን::
=>ኅዳር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ
3.ቅዱሳን ዱራታኦስና ቴዎብስታ
4.አፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
6.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
7.አባ ፊላታዎስ ሊቀ ዻዻሳት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
4.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
5.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
6.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
👉ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በዙሪያህ ሶስት አይነት ሰዎች ቢኖሩ ጥሩ ነው።
የሚበልጥህ ሰው… ልትማርበት።
ከአንተ ተመጣጣኝ እኩል የሆነ ሰው… እግር በእግር አብረሀው ልትሄድ።
የምትበልጠው ሰው… የነበርክበትን ልታስታውስበትና ልታስተምረው አንተ ጋር ልታደርሰው።
ግን
በሚበልጥህ ከቀናህ… በእኩያህ ከተመቀኘህ… በምትበልጠው ከተኮፈስክ… አንተ ሰው ወደፊት ለመሄድ የሆነ ነገር አጉድለሃል።
ሰናይ ለሊት !!!

☆•♥• ☆ #ቅዳሴ ☆•♥• ☆
♥ በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
♥ 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?
♥ ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
♥ እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
♥ አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?
አውቀነው እንጠቀምበት ዘንድ ይነበብ.....ለሌሎች ሰማያዊ ምሥጢርን አካፍለን የተሰጠንን መክሊት እናተርፍበት ዘንድ እንትጋ +
☆•♥• ☆ #ቅዳሴ ☆•♥• ☆
ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡♥
፩. የቁርባን መስዋዕት፡-
+
በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡
፪. የከንፈር መስዋዕት፡- +
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡
፫. የመብራት መስዋዕት፡- +
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጦፍ ለእግዚአብሔር
የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨላመ ለሆነ ዓለም
ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡
፬. የዕጣን መስዋዕት፡- +
የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ በደሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡
፭. የሰውነት መስዋዕትነት፡- +
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
ይህ የፀሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላ
፩. የዝግጅት ክፍል
፪. የንባብና የትምህርት ክፍል
፫. ፍሬ ቅዳሴ
እዚህ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው እነዚህም፡-
፫.፩. ሥርዓተ ቅዳሴ
፫.፪. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
፫.፫. ቅዳሴ እግዚእ
፫.፬. ቅዳሴ ማርያም
፫.፭. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
፫.፮. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
፫.፯. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
፫.፰. ቅዳሴ ባስልዮስ
፫.፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፫.፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
፫.፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
፫.፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
፫.፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
፫.፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
-የጌታችን በዓል ከሆነ … (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጶጉሜ እሁድ ቀን ከዋለች ሰንበት … (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም … (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ … (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት … (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
ቅዳሴን ለመቀደስ ብዙ ጊዜ ፭ሆነው ይቀድሳሉ ይህው የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሣሌ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከዚያም በሚያንስም ሆነ በሚበዛ ሰው ቅዳሴን መቀደስ ይቻላል ለምሳሌ ፯ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ይመስላሉ ፲፫ በ12ቱ ሐዋርያት እና በጌታችን ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ፤ 24 በሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይህ የሚሆነው እንደ ካህናቱ ብዛት ነው ጭራሽ ካህን ከጠፋ ደግሞ 1 ቄስና 1 ዲያቆን ሆነው መቀደስ ይችላሉ ሁለትነታቸው የመለኮትና የትስብዕት (የሥጋ) ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ በሦስት ከሆነ በሦስቱ ሥላሴዎች አራት ከሆኑ በ4ቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ ከሁለት ባነሰ ግን 1 ሆኖ ግን ቅዳሴ አይቀደስም ቀኖናው የቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ይከለክላል፡፡
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
“ጸልዩ” ይህ የቅዳሴው የፀሎት ዓይነት ሲሆን ለ13 ጊዜያት ይባላል፡፡
በሦስተኛው ክፍለ ቅዳሴ 4 ጊዜ ይባላል ፀልዩን ዲያቆኑ ሲያውጅ ፊቱን ወደ ህዝቡ ይመልስና እንዲጸልዩ ያውጃል፡፡ በዚህ ጊዜ ተሰጥዖ ካለ ተሰጥዖ ይመለሳል ከሌለ ግን “አቡነ ዘበሰማያት” ሕዝቡ እንዲደግሙ ያውጃል፡፡+
ለምሳሌ፡-
ንፍቁ ዲያቆን “ፀልዩ በእንተ እለያበዕኡ መባዕ … መባን ስለሚያገቡ
ሰዎች ፀልዩ” ሲል በዚህ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት አይደገምም ምክንያቱም
የራሱ ተሰጥዖ ስላለው “ተወከፍ መባዖሙ ለአሃው ወተወከፍ መባዖን…”
ይህ አቡነ ዘበሰማያት የሚተካ ፀሎት ነው፡፡
ድርገት ሲወርዱ “ፀልዩ በእንቲአነ” በሚባልበት ጊዜ እንድንጸልየው
የሚያዘው የዳዊትን መዝሙር 150ኛውን መዝሙር ነው፡፡ ፀልዩ ብሎ
ያዘዘው በዚህ ክፍል ያለ የዳዊትን 150ኛውን የመዝሙር ክፍል ነው
ማለት ነው፡፡
☆•♥• ☆ •♥• ☆•♥• ☆
እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር
1ኛ የኃጢአት ሥርየት ይገኛል ምክንያቱም በአንቃዕዶ ሕሊና ይቅርታን ስለሚጠይቅ፣
2ኛ በነፍስም በስጋም በረከትን ያገኛል፣
3ኛ ጸሎቱም ይደመጣል፣
4ኛ የመላእክትን በረከት በቀጥታ እንሳተፋልን ቅዳሴን አስቀድሶ ሥጋ ወደሙ ሲቀበል የዘለዓለምን በረከት ያገኛል፡፡ +
በተጨማሪም ቅዳሴ በማስቀደስ
4 ነገሮች ይገኛሉ እነዚህም፡-
፩. ትምህርት+
የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ እና የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ትምህርት በቅዳሴ ገዚ ያገኛል፡፡ ለምሳሌ የማርያምን ቅዳሴ አባ ሕርያቆስ የደረሰውን ይህን ቅዳሴ ሲቀደስ በውስጡ ምሥጢረ ሥላሴ፣ እና ምሥጢረ ሥጋዊ እና ነገረ ማርያምን አምልቶ ይነግራል፡፡
፪. ታሪክ+
14ቱንም ቅዳሴ የሚያስቀድስ ሰው የቤተክርስቲያንን ታሪክ በቅዳሴ ውስጥ እንማራለን፡፡
፫. ምክር+
በቅዳሴ ውስጥ ተፋቀሩ፣ መጽውቱ፣ ተስማሙ፣ ጹሙ፣ ጸልዩ እየተባለ በቅዳሴ ውስጥ ሰፋ ባለመልኩ ምክር ይሰጣል ስለዚህ ቅዳሴን በማስቀደስ ምክርን ማግኝት ይቻላል ማለት ነው፡፡
፬. ተግሣጽ+
ቅዳሴ ውስጡ ተግሣጽን ይዞ እናገኝዋለን ለምሳሌ በቅዳሴ እግዚእ ላይ ከወንድሙ ጋር የተጣለ ቢኖር ይተውለት ይላል በዚህ የቅዳሴ ክፍል ውስጥ ራሳችንን ምን ላይ እንደቆምን ከሰዎች ጋር ያለንን ኅብረት ስምምነት ለፈጣሪ ራሳችንን ማስገዛታችንን እየገሠፀ ይነግረናል፡፡ እነዚህን መሠረታዊ የሆኑትን ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ቅዳሴ በማስቀደስ እናገኛቸዋለን፡፡
-ቅዳሴ ንባብም ዜማም የሚቀርብበት የፀሎት ክፍል ነው፡፡ ሁላችንም የምንሳተፍበት ቄሱም ዲያቆኑም ምእመኑም የሚሳተፉበት ነው፡፡
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች

እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
ቤተክርስቲያን ሆይ! ከአንቺ ወደ ማን እንሄዳለን?
የነፍሳችን ዓለም የሆነችው ቤተክርስቲያን በነገር ሁሉ ባንደሰት፣ ኃያላን ቢደቁሱን፣ ደስ አይሉም የምንላቸው ዘመናት ብዙ ቢሆኑም፤ ሀገር ብታረጅም፣ ሀብት ንብረት ቢጠፋም፣ ብቸኝነት ቢጫነንም፣ በሁሉም ቋንቋ ጸሎትን የሚሰማ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ግን የመጨረሻ መጠጊያችን መሆኗን አንርሳ፡፡
በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ወድቀን የደጁን ጠበል ተስፋ አድርገን ብዙ ሌሊቶችን የምንገፋው ይህቺንው ቤታችንን ተስፋ አድርግን ነው፡፡ በማይድን የሥጋ ደዌ ብንያዝ እንኳን በንስሓ ታጥበን ግሩም የሆነውን የመቅደሱን የዕጣን መስዋእት እያሸተትን ክቡር ሥጋውን ቅዱስ ደሙን ተቀብለን ወደ ባለቤቱ እንድምንሄድ የምናስብባት የምናምንባት ቤታችን ናት፡፡ በሞት ጥላ ውስጥ እንኳን በማይጠፋ ተስፋ ቆመን የገነትን መዓዛ እያሸተትን ወደማይቀረው የዘላለም ቤታችን እንደምንጓዝ አምነን በደስታ የምንኖርባት ቤታችን ናት፡፡
ፖለቲካ ይለዋጣል፤ ይጠፋል፡፡ ቋንቋም ይከስማል፡፡ ከዚህ የሚበልጥ እውነት ለክርስቲያን የለውም፡፡ ስለዚህ ሁሉም የቤተክርስቲያን ቤተሰቦች በቋንቋ፣ በፖለቲካ አመለካካት፣ በኃላፊነትና በኑሮ ደረጃ፣ በእውቀት ደረጃ…ሳይለያዩ በመቆም ከፋፋይ ከሆነው ከኢጣሊያ ሴራ፣ ፀረ ሃይማኖት ከሆነው ከአቢያተኞች ሴራ ትውልድ ጠብቆ ያሻገራትን የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለቀጣይ ትውልድ እውነተኛውን የክርስትና አስተምህሮ እንድታደርስ እኛ ደግሞ ዛሬ በጽናት ልንቆምላት ይገባል፡፡ ‹‹ቤተክርስቲያን ሆይ! ከአንቺ ወደ ማን እንሄዳለን?›› እንበላት፡፡
(ዲያቆን ማለደ ከጻፈው የተወሰደ- ማኅበረ ቅዱሳን)
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡

ጾመ ነቢያት ምንጊዜም ኅዳር 15 ይጀምራል
ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ጌና (ገና)፣ ጾመ ልደት በመባል ይጠራል፡፡ ጾመ ሙሴም ብለው የሚጠሩት አሉ፡፡ በዘመነ ማቴዎስ፣ በዘመነ ማርቆስ እና በዘመነ ሉቃስ ልደት የሚውለው በታኅሣስ 29 ነው፡፡ ስለዚህም ጦሙ ኅዳር 15 መግባቱ አያወዛግብም ነበር፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ ዘመነ ዮሐንስን ምክንያት አድርጎ የጌታ ልደት ታኅሣስ 28 ስለሚከበር የጦሙም መግቢያ በአንድ ቀን ተስቦ በኅዳር 14 ይጀምር የሚሉ ወገኖች ነበሩ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ውጣ ውረድ ተመልክቶ ምእመናን ግራ እንዳይጋቡ በሚል የጾሙን መያዣ ቀኖና በማያሻማ ሁኔታ ከደነገገ በርካታ ዓመታት አልፈዋል፡፡ በዚህም ቀኖናዊ ድንጋጌ መሠረት ጾመ ነቢያት በዐራቱም ወንጌላውያን ወንበር ወይም ምን ጊዜም የሚጀምረው ኅዳር 15 ነው፡፡ በዚህ ሳንወዛገብ ጦማችንን እንጡም፡፡ በየጊዜው የኦርቶዶክሳውያንን ልብ የሚከፍሉ አስተያየቶች ዝም እየተባሉ ብዙ ድንግርግር ያስከትላሉ፡፡ ያልተስማሙ ሰዎች እንኳ ቢኖሩ ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲታይላቸው ጥያቄአቸውን ያቅርቡ እንጅ የሕዝቡን ልብ መክፈል አይገባቸውም፡፡
አንዳንዶች ይህንን ጉዳይ የዶግማ ያኸል ይዘውት በሌላ ጽንፍ ቆመዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ውሣኔውን ሳይሰሙ በተዘጋ ቤት ውስጥ ኖረው ኖረው ያችኑ ጥንት የሚያውቋትን ላለመልቀቅ ይንገዛገዛሉ፡፡ ለማንኛውም በዘመነ ዮሐንስም ኾነ በሌሎችም ወንበሮች የጦሙ መግቢያ አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ኅዳር 15 ነው፡፡ በዚህም መሠረት እሑድ የፊታችን ሰንበት ቅበላው ሲኾን ጦሙ ሰኞ ይጀምራል፡፡ በዘመነ ዮሐንስ የሚቀየረው ልደት የሚከበርበት ቀን ሲኾን እርሱም ታኅሣስ 28 ነው፡፡
#ዲያቆን_አባይነህ_ካሴ
#Share it, please.

✟ክፍል ፪✟
#ሀጢያታችንን_ለምን_በቀጥታ_ለእግዚአብሄር_ብቻ_አንናዘዝምን?
ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር አለመናዘዝ አይደለም፡፡ ሀጢያትን ለካህን መንገር ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7÷19፡፡ ኢያሱ “ክብርን ስጥ” ያለው ለእግዚአብሄር “ተናገር” ያለው ግን ለራሱ መሆኑ ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ይህም ምንም በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ ”ሁለት ወይም ሶስት በሚሆኑበት በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ” ብሎ ቃል የገባ አምላክ በአናዛዚው ካህንና በተናዛዚው ምእምን መካከል ሆኖ ይሰማል፡ ስርየትንም ይሰጣል፡፡
ሰው ሲታመም ሀኪም ቤት ሄዶ በሀኪሙ ፊት ”ቆረጠኝ ወጋኝ ” እያለ ህመሙን እንደሚያብራራው ሁሉ፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉት ካህናትም የነፍስ ሀኪሞች ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ (ሀጢያት) በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን እንዳልሆነው ሁሉ በካህናት ፊት የምንናዘዘውም የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል የሚገባው ”ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አገባቤ አይደለም” ነው (ፀሎተ ምናሴ)፡፡
በወንጌል እግዚአብሔር ”እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው የሰው ልጅ ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ስለፈለገ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ሳይል የሰራውን ሀጢያት እንዴት እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ብሎ ይናዘዛል? እነዚህ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን የሚፈሩትን መጽሐፍ እንዲህ ይላቸዋል ”እስመ ዐይነ ሰብእ ያፈርሆሙ ወኢየአምሩ ከመ አይነ እግዚአብሔር ያበርህ እምእዕላፍ ፀሀይ” ”የሰው ዐይን ያስፈራቸዋል የእግዚአብሔር አይን ግን ከብዙ አእላፍ ፀሀያት ይልቅ እንደሚያበራ አያውቁም!!!”
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
(ክብረ ክህነት - በዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ)
✟ክፍል ፪✟
#ሀጢያታችንን_ለምን_በቀጥታ_ለእግዚአብሄር_ብቻ_አንናዘዝምን?
ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር አለመናዘዝ አይደለም፡፡ ሀጢያትን ለካህን መንገር ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7÷19፡፡ ኢያሱ “ክብርን ስጥ” ያለው ለእግዚአብሄር “ተናገር” ያለው ግን ለራሱ መሆኑ ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ይህም ምንም በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ ”ሁለት ወይም ሶስት በሚሆኑበት በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ” ብሎ ቃል የገባ አምላክ በአናዛዚው ካህንና በተናዛዚው ምእምን መካከል ሆኖ ይሰማል፡ ስርየትንም ይሰጣል፡፡
ሰው ሲታመም ሀኪም ቤት ሄዶ በሀኪሙ ፊት ”ቆረጠኝ ወጋኝ ” እያለ ህመሙን እንደሚያብራራው ሁሉ፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉት ካህናትም የነፍስ ሀኪሞች ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ (ሀጢያት) በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን እንዳልሆነው ሁሉ በካህናት ፊት የምንናዘዘውም የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል የሚገባው ”ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አገባቤ አይደለም” ነው (ፀሎተ ምናሴ)፡፡
በወንጌል እግዚአብሔር ”እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው የሰው ልጅ ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ስለፈለገ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ሳይል የሰራውን ሀጢያት እንዴት እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ብሎ ይናዘዛል? እነዚህ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን የሚፈሩትን መጽሐፍ እንዲህ ይላቸዋል ”እስመ ዐይነ ሰብእ ያፈርሆሙ ወኢየአምሩ ከመ አይነ እግዚአብሔር ያበርህ እምእዕላፍ ፀሀይ” ”የሰው ዐይን ያስፈራቸዋል የእግዚአብሔር አይን ግን ከብዙ አእላፍ ፀሀያት ይልቅ እንደሚያበራ አያውቁም!!!”
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
"የንስሐ አባት መያዝ ለምን ያስፈልጋል?"
(ክብረ ክህነት - በዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ)
✟ክፍል ፫✟
(የመጨረሻ ክፍል)
#ስለ_ንስሐ_ሊያውቁአቸው_የሚገቡ_አንኳር_ጉዳዮች፡-
አንድ ምእመን ንስሃ በሚገባበት ጊዜ ሃጢያቱን ሳያድበሰብስ በዝርዝር ለካህኑ በሚገባ መልኩ መናዘዝ አለበት ፡፡ እንዳው በደፈናው “እኔ ያልሰራሁት ሃጢያት የለም” "አድርጉ ከተባለው ውስጥ ያደረግኩት አንድም መልካም ነገር የለም!" እያሉ የብልጠት ኑዛዜ መናዘዝ አይገባም፡፡ አንድ በሽተኛ በሃኪም ፊት ”ታምሜአለሁ!” "በሽታ የተባለ ሁሉ አለብኝ!" በማለት መድሃኒት እንደማያገኝ ሁሉ ሃጢያቱን በዝርዝር እና በግልፅ ያልተናገረም በትክክል ስርየት አያገኝም፡፡
አንድ ምእመን ስለ ሃጢያቱ በግልፅ ሊናገር እና ሊዘረዝር ይገባል ሲባል ግን በሆነው ባልሆነው ”እኔ ሃጢያተኛ ነኝ” ሊል ይገባል ማለት አይደለም፡፡ ”ድሃ ድህነቱን በአፉ ይጠላታል” ሲራ. 13÷24 እንዳለ ”እንደኔ ሃጢያተኛ ማን አለ?” እያሉ ሃጢያትን በአፍ መጥላት ገና ከሀጢያት ፍቅር ያለመላቀቅ ምልክት ነው፡፡ ሃጢያትን የሚጠላት በንስሃ ይርቃታልና፡፡ ሃጢያተኛ ነኝ እያሉ በማወጅ ንጹሃን ትሁታን የሚመስላቸው አሉ፡፡ ትሁታን ግን ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ እንዳለው ሃጢያተኛ ነኝ የሚሉት ሳይሆኑ ሃጢያተኛ ሲባሉ የሚታገሱት ናቸው፡፡
በኑዛዜ ወቅት ትንኝን እያጠሩ ግመልን እንደ መዋጥ ታላላቅ ሃጢያቶቻችንን ከጎን ትተን ጥቃቅኑን ብቻ መናገር ስህተት ነው፡፡ ሲሰሩት ያልፈሩትን ሃጢያት ሲናገሩት መፍራት አይገባምና፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን ዘረቡዕ እንዲህ እንዳለ ”ሃጢያቴን ለመናገር ለምን አፍራለሁ? አለመናዘዜስ ለምንድን ነው? እኔ ሀጢያቴን ብሰውረው ሃጢያቴ ራሱ ሊከሰኝ ይጮሃል፡፡ እንኪያስ እንዳልበደለ ለምን ዝም እላለሁ? የሰራሁትን ክፉ ስራዬ ያሳጣኛል እኔ እንዳልሰራ ለምን እሆናለሁ? የሚዘልፈኝ አልሻም፡፡ እኔ ራሴ ለራሴ የራሴን ዘለፋ አነባለሁ እንጂ”፡
በኑዛዜ ወቅት ለሀጢያት ምክንያት መደርደርና የሌሎችን ሀጢያት አክሎ መናገር አይገባም ”እገሌ እንዲህ አድርጎ ስለገፋፋኝ እንዲህ አድርጌ ነበር” አያሉ ሌላውን መክሰስና ምክንያት መስጠት ይቅር ሳይሉ ይቅርታ መሻት ነውና፡፡ ጌታችንም በወንጌል ”ከሳሾችሽ ወዴት አሉ?” ያላትን ሴት ”አኔም አልፈርድብሽም” ብሎ በይቅርታ ያሰናበታት ስለ ከሳሾችዋ አንዳች ባለመናገሩዋ ነበር ዮሀ. 8÷11፡፡
ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይጨስ የለምና እንዲሉ ሰው ሁልጊዜ ከበደል ንጹህ ይሆን ዘንድ አይችልም በንስሃ ሃጢያቱን የሚናዘዝ ሰው ዳግመኛ አይበድልም ማለት አይደለም፡፡ ከንስሃ በሁዋላ በሃጢያት ተፈትነን ብንወድቅ ተስፋ ሳንቆርጥ ወዲያው ንስሃ ልንገባ ይገባል ”መልሼ ልበድል ለምን ንስሃ እገባለሁ” ማለት ግን ”መልሶ ለሚርበኝ ለምን እበላለሁ” ”መልሼ ለምቆሽሽ ለምን እታጠባለሁ” እንደ ማለት ነው ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ”መውደቅ አዳማዊ ነው ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያቢሎሳዊ ነው” እንዳለው ተሰፋ ቆርጦ በንስሃ መነሳት ይኖርብናል እግዚአብሄር ይቅር ማለት ሳይሰለቸዉ ሰው ይቅር በለኝ ማለት ሊሰለቸው አይገባም፡፡

#ናፈቀኝ ....
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
የማለዳ ተመስጦ ... ውዳሴ ማርያም መድገሜ
በልጅነት ልመጣልህ .. ጧት ማታ መፍገምገሜ
ዛሬ ግን ናፍቆት ሆነብኝ .. ተዘረረብኝ አቅሜ
እንቅልፌ ሰላም አጣ .... እባብ ሆነብኝ ሕልሜ ።
.
"እግዚኦ" ሲባል ሰምቼ .. ሳልነሳ ከትራሴ
ድንጋጤ ወረረኝ .. ከእግሬ ጥፍር እስከራሴ
ሰዓታቱን እየሰማሁ ... ተቀሰቀሰ መንፈሴ
ትዝዝ አለኝ ማኅሌቱ ... ስትዋብበት ነፍሴ
የእናቴ ስም ናፈቀኝ ...... የሕርያቆስ ቅዳሴ
.
እራሴንም ስላጣሁት ..... ከቤትህ በመራቄ
እንደ ሎጥ ሚስት መሰልኩኝ ፤ አደባባይ ደርቄ
.
የመዝሙረ-ዳዊት ጸሎት .. አነከተኝ በትዝታ
ነፍሴን ስላስጠማኋት ... አነባችብኝ አብዝታ
እሪሪሪ ብላ አለቀሰች ... በስጋ ወንጭፍ ተገዝታ
.
ናፈቀኝ ትምህርቱ ... የቅዱስ ያሬድ ጸጋ
ቁጥር ዜማ መጮሄ .... አንደበቴ እስኪዘጋ
ዛሬ ላለው ማንነቴ .. ምን ይሆን የ'ኔ ዋጋ ??
.
በከበሮ በጽናጽል ... መዘመሩ ማሸብሸቡ
ጃኖ ለብሶ በመሰለፍ ... ማመርገዱ መወረቡ
የትውስታ ስለት ይዘው ፤ ወደ ልቤ ሰርገው ገቡ
.
አምላኬንም ሳመሰግን .. ወደ ሰማይ አንጋጥጬ
እንዲህ ዛሬ ልቀብረው .. በልቤ ውስጥ ረግጬ
አገልግሎቴ ናፈቀኝ ... ከሁሉ በላይ አስበልጬ
ኮርስ ስማር ትዝ አለኝ ... በዛፉ ስር ተቀምጬ
.
አንገቴ ላይ የታሰረው .. ለምን ነበር ማኅተቤ
ዛሬ ለምን አታለልኩት .. በምክንያት ተንተብትቤ ?
.
ምኑ ነው የሆነብኝ .. ለቤተ መቅደስ እንቅፋት ?
ትዳር ለምን መሰለኝ .. ሜዳ ሆኖ ተዳፋት ?
ልቤ ከብዶ እስከመቼ .. እኖራለሁ በጥፋት ?
ነፍሴንስ ምንበወጣት ... በ'ሳት ጅራፍ ላስገርፋት
.
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ሰው መስዬ ሲመግቡኝ .. ባ'ይኔ ብሌን አይቻለሁ
ታዲያ ግን ምን ዋጋ አለው .. ማንበብ እንደሁ ትቻለሁ
.
እውነት ነው አይካድም .. አውደ ምኅረት መቀመጤ
ወንጌሉንም እየሰማሁ .... ሳላስበው መመሰጤ
ትዝ ይለኛል አጀንዳዬ ... ከንፈሮቼንም መምጠጤ
.
ጽዋ ቢሉ ዝክረ ሰንበት .. እንዳያልፈን ስንጣራ
ዓርብ ጸሎት ስንሰለፍ .. ነጭ ለብሰን በጋራ
ከትንሹም ከትልቁም ... ስለድኅነት ስናወራ
"ጉዞ" ብለን በባዶ እግር .. ሳንደክም በተራራ
ነጭ ለብሰን ጧፍ ይዘን .. እንደ ኮከብ ስናበራ
አዎ! አስታውሳለሁ ... ስልሳ ፍሬ ስናፈራ
.
ጾም ጸሎቱ ትዝ ይለኛል .. በላያችን ስናጌጠው
በስግደት ተሽቀዳድመን ... ሳጥናኤን ስናመልጠው
ብዙ ነበር በንስሐው ... በቁርባኑ የሚገልጠው
.
ጌታ ሆይ!
ተመልሶ ይላክልኝ ... መንፈሳዊ ጀግንነቴ
በመቅደስህ ዋጋ ይክፈል .. የናቡቴ ልጅነቴ
"እሺ" ብሎ እንዳልሰራው .. አይሁንብኝ ማንነቴ
.
ቀራኒዮ አይረሳኝ ... ችንካር ያለው መስቀሉ
በክቡር ደም ተነክሮ .. ቀይ ሆኖ መንቀልቀሉ
.
እመ ብርሐን በልደቷ .. ትመልሰኝ ወደ ጥንቱ
የቅዱሳን ጥበቃቸው .... አይለየኝ በረከቱ
ናፈቀኝ
ሰነፍ ልቤ እየገዛኝ .. በሞት ሰይፍ በጫጨቀኝ
ይቅር በለኝ አምላኬ! ... ከመቅደስህ አታርቀኝ
በግራ መቆም መረረኝ ፤ አሰልፈኝ በልጅህ ቀኝ
አብርሃምን ላክና ... መልስህን ቶሎ አሳውቀኝ
በራሴ አይን ስደናበር.. መታዘብህ አስጨነቀኝ
የምኅረት ቃል አንደበትህ ፤ ፅኑ ፍቅርህ ናፈቀኝ።
#ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
__________________

ጸሎት ለማድረግ አታቅማማ፤ ሥጋ ከምግብ በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች፡፡ (አቡነ ማቴዎስ ግብፃዊ)
ስለሁሉም ነገር ሳታቋርጥ ጸልይ፤ እንዲህ ካላደረግክ ምንም ነገር ያለ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ የማታከናውን ትሆናለህ፡፡ ያለጸሎት ራሱን በማንኛውም ዓለማዊ ጉዳዮች የሚያደክም ሰው በመጨረሻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡ (አባ አጋቶን)
እግዚአብሔር ለሰው ምሕረትን ሲያድል አንድ ሰው እንዲጸልይለት ያነሣሣዋል፡፡ በዚህ ጸሎት አማካኝነትም ይረዳዋል፡፡ በመከራ ጊዜ ያለማቋረጥ መሓሪውን አምላክ በጸሎት ጥራው፡፡ ባለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ለነፍስ ቁስል መድኃኒት ነው፡፡ ሰው በታመመ ጊዜ ዶክተሩ ፍቱን መድኃኒትን ፈልጎ ለበሽተኛው እንደሚሰጠው መድኃኒቱም ወደ ሰውነቱ ገብቶ ሥራ ሲሠራ እንጂ እንዴት እንደሚሰራ እንደማናውቀው በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ስም አዘውትረን ስንጠራ እንዴት ጸሎታችን እንደሰራ ሳናውቅ የእግዚአብሔርን ፍቅር ምህረትና ርኅራኄ በእኛ ላይ ሲደረግ እንመለከታለን፡፡ (አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ)

السلام للعجائبي مار مينا الأمين السلام للبطل القوي الشفيع المؤمنين.
(((("ሰላምታ ለድንቅ አድራጊውን ለታማኙ ማር ሚና ( ሚናስ) ይገባል። ሰላምታ ለኃያሉ አርበኛ ለምዕመናን አማላጅ ይገባል።"))))
ይህ ከላይ በዓረብኛ የተተረጎመው ምስጋና በግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጠዋት ጠዋት መዝሙረ ዳዊት ተነቦ ካለቀ በኋላ የየቅዱሳኑ ሰላምታ በሚሰጥበት ጊዜ ከሚጠሩት ቅዱሳን ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ማር ሚና ነው።እና የሱን ምስጋና ነው የተረጎምኩላችሁ። እንደምትባረኩበት ምኞቴ ነው።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። በዛሬው ዕለት (ህዳር 15) ታላቁ የድንቅ አድራጊው የተዓምረኛው የፈጥኖ ደራሹ የየዋሁ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ማር ሚና ( ሚናስ) የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ማር ሚና የስሙ ትርጉም "የታመነ ብሩክ" ማለት ነው።
የሚያደርጋቸው ተዓምራት እጅግ በጣም ብዙ ነው። ባልተጠበቀ ጊዜ በማታስቡት ሰዓት በተጨነቃችሁ ጊዜ እጅግ በጣም ፈጥኖ ይደርሳል። ማር ሚና ስሙን ስትጠሩ በስሙ ስትጸልዩ ውስጣችሁ እንዲረጋጋ ደስ እንዲላችሁ ያደርጋል። ማር ሚና በእናንተ ላይ ሰይጣናት ያደሩባቸው ሰዎች በውሸት ከከሰሷችሁ እና በውሸት በውሸት ደፍረው በቅዱስ ማር ሚና ስም ከማሉ ሰኮንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፈጥኖ ውሸታቸውን ያጋልጠዋል ከጌታችን የተሰጠው ቃል ኪዳን ይህ ነው። ማር ሚና ለኛ ለወጣቶች እንደ ታላቅ ወንድም ለሽማግሌዎች እንደ ልጅ ሆኖ የሚፈልጉትን ነገር ያደርግላቸዋል ከሰማያውያን ቅዱሳን ጋር ቤተሰባዊነት እንዲኖራችሁ ሁሌም የሰማዩን መንግስት እንድትናፍቁ ያደርጋችኋል።ክርስትያኖች ሁሌም የቅዱስ ማር ሚናን አማላጅነት ጠይቁ ሁሌም ከሰከንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ እናንተ ሲመጣ ሲባርካችሁ በአማላጅነቱ ስትፈወሱ ለጥያቄያችሁ መልስ ሲሰጣችሁ ታገኙታላችሁ። ቅዱስ ማር ሚና ለኔ በቅርብ ለማውቀው ወዳጄ ተዓምራት አድርጎለታል የኔ ወዳጅ ማርዮት ( "ማርዮት" በግብጽ አገር በእስክንድርያ ከተማ የሚገኝ ወረዳ ነው።) በሚገኘው የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ማር ሚና ገዳም ሄዶ የታላቁን ሰማዕት ቅዱስ አካል ተሳልሞ በቤተክርስትያን ውስጥ ተቀምጦ ጸሎት ሲያደረግ አንድ ወጣት ከታች እንደምትመለከቱት ሥዕል የወታደር ዓይነት ልብስ የለበሰ ሰው መጥቶ ለወዳጄ መስቀል ሰጠው ወዳጄ ስላልገባው ምንድነው ብሎ ሲጠይቀው ወጣቱ ተሰወረ። ከዚያም ወዳጄ የተሰጠው መስቀል ጠፋበት። በመቀጠል በሌላ ጊዜ አሁንም ወደ ገዳሙ ሲሄድ አሁንም እንደ ባለፈው ቀን የወታደር ልብስ የለበሰ ወጣት ልጅ መስቀል ይዞ መጥቶ ሰጠው ከዚያም ተሰወረ። ወዳጄ መስቀሉን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሄደ ። ከዚያም የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ ማር ሚናን ሥዕል ትኩር ብሎ ሲያየው ያ መስቀል የሰጠው ወጣት ልክ እንደ ሥዕሉ ነበር የለበሰው እና ወዳጄ ተገርሞ ደንግጦ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ልክ እንደ ጓደኛዬ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ማር ሚና በገዳሙ ለሚመጡ እና በቤታቸው ሆነው ሥሙን ለሚጠሩ ምዕመናን መስቀል የተቀደሰ ዘይት ( ቅብዓ ቅዱስ) እንደዚሁም ወደ ገዳሙ የሚመጡበትን የመጓጓዣ ገንዘብ ምግብ እና መጠጥ ለሚያስፈልጋቸው ማለትም በእጃቸው መብላት መጠጣት ለማይችሉ ደግሞ የሚበሉትን የሚጠጡትን ይዞ ይመጣል። ለዚህ ነው ማር ሚና ቤተሰባችን ነው ያልኩት።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቁ በተዓምርና ድንቅ አድራጊው በየዋሁ በፈጥኖ ደራሹ በታላቁ ሰማዕት በቅዱስ ማር ሚና ጸሎት ይማረን ። በረከቱም ከእኛ ጋር ጸንቶ ይኑር አሜን። አሜን። አሜን። ፍኖተ መንግስተ ሰማያት

“አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡ ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"
(ቅዱስ ኤፍሬም)