#እውነተኛ_ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡
አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?
ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡
ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም " አለ ዮሐ 14:6
#ይህን_ለምን_አለ ?
ጌታችን እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ የአንድነትና የሶስትነት መገለጫ እኔ ነኝ ማለቱ ነበር ። ምክንያቱም ጌታችን በስጋ ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔርን አንድ እግዚአብሔር ከማለት ውጪ የአካል ሶስትነት ማለትም አብ፣ ወልድ ፣ መንፈስቅዱስ አይታወቅም ነበርና ። ጌታችን በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ያለው ታዲያ ለምንድነው ? ያልን እንደሆነ ፦ የወልድን ልጅነት ያላመነ የአብን አባትነት አያምንም ፤ የላከውን ልጁን ያልተቀበለ አብን አያውቅምና የአባትነት ማንነት በልጅ ስለሚታወቅ የእኔን ወልድነት "#ተወላዲነት" ካላመነ አብ በደመና የምወደው ልጄ ይህ ነውና በእርሱ እመኑ ብሎ ሲመሰክር ሰምቶ ካላመነ አይድንም ሲል ነው ።ዮሐ 14:7፣ 14:1 ፣14:21 ይመልከቱ ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታ ላይ ስለ #መንገድ ተጠቅሷል ። መናፍቃን ስለሌላው መንገድ በሚገባ ለምን እንደተባለ ሳያብራሩ ጌታ የተናገረውን በመጥቀስ ብቻ እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ አማላጅ ነኝ ማለቱ ነው ይላሉ። እስቲ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለመንገድ ከተጠቀሱት ጥቂቱን እንመልከት፦
#1."እግዚአብሔር እንዲህ ይላል #በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም #መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላቹ " ት.ኤር 6:16
#2."ሀሳቤ እንደ ሀሳባችሁ #መንገዳችሁም እንደ #መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር " ኢሳ 55:8
#3."ካዘዝኀቸው #መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ "ዘዳ 32:8
#4."በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ በምትወርሷትም ምድር እድሜአችሁ እንዲረዝም አምላካችሁ ባዘዛችሁ #መንገድ ሁሉ ሂዱ " ዘዳ 5:33
#5."ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ #መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱ የሚገቡ ብዙዎች ናቸው " ማቴ 7:13 እንግዲህ #መንገድ የሚለው በጥሬው አገላለጽ በርካታ ትርጉሞችን ይዞ እናገኘዋለን መናፍቃን እንደሚሉት ግን በዚህ ጥቅስ ውስጥ ስለ አማላጅነት የተነገረ አንዳችም ነገር የለም ይልቅ በወልድ ልጅነት በማመን ወደ አብ መድረስ እንደሚቻል የተነገረ የሕይወት ቃል ነው ። ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች መንገድ ሃይማኖት ነው ፣ መንገድ ትዕዛዘ እግዚአብሔር ነው ፣ መንገድ ፍቃደ እግዚአብሔር ነው ፣ መንገድ ወንጌል ነው
ደግሞም ምልጃ የሚያስፈልገው ምህረትን ለማግኘት ነው
ምሕረት ደግሞ ለመዳን ሲሆን መዳን ማለት ደግሞ የዘላለም ሕይወት ማለት ከሆነ ጌታችን ደግሞ "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ "እያለ "በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም " የሚለው ቃል እንዴት አማላጅ ተብሎ ይተረጓማል ? መናፍቃን እንደሚሉት አማላጅ ተብሎ የሚተረጎም ከሆነ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትን የሚሰጥ ሕይወት መሆኑ ቀርቶ ሕይወት አሰጪ መሆኑ ነው ይሄ ደግሞ የክህደት ክህደት ነው። ጌታችን መንገድ ነኝ ያለበት ሌላው ም/ት፦ መንገድ ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ የሚያደርስ ፣ የሚወስድ ማለት ነው ። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በመገረፋ ፣ በመቁሰሉ ፣ በመመታቱ ፣ መስቀል ላይ ስለኛ ሀጢአት በመሰቀሉ ፣ በደላችንን ሁሉ ተሸክሞ በፍቅሩ እኛን ወደ እርሱ በመጥራቱ ከነበርንበት የዘላለም ሞት አውጥቶ ወደ ዘላለም ሕይወት አሻገረን አደረሰን
ይህም እውነተኛውና ብቸኛው የመዳናችን መንገድ እርሱ በመሆኑ ነው ።አዳምና ሔዋን ዕፀ በለስን እንደበሉ ከተፈረደባቸው ቡሃላ "እግዚአብሔር አምላክም አለ ...እጁን እንዳይዘረጋ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ ...ከገነት አስወጣው ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም #መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔደን ገነት ምስራቅ አስቀመጠ። " ዘፍ 3:22 እንግዲህ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደው #መንገድ ስለተዘጋ ወደ ሕይወት የሚያደርሰን #መንገድ ያስፈልገን ነበር ። ስለዚህም እርሱ ሕይወት ነውና #መንገድ በመሆኑ ተዘግታ የነበረችውን ገነት አስከፈተልን መከፈቱንም ሊያረጋግጥልን በቀኙ ተሰቅሎ የነበው ወንበዴ " በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ " ሲለው "ኢየሱስ እውነት እልሃለው ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ "አለው ሉቃ 23:42
ሌላው መንገድ ነኝ ያለበት ፦ "ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው " ዮሐ6:5 ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እኛን ከኀጢአት ሞት ወደ ዘልዓለማዊ ሕይወት የሚያሻግረን ስለሆነ እኔ መንገድ ነኝ አለ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት ለምልጃ የተጠቀሰ ቃል አይደለም
ለአስተያየት 👉 @zekidanemeheretbot
🕊👉@zekidanemeheret

"አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው #መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው "1ጢሞ 2:5
ይህንን ጥቅስ መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ ለማለት ከሚጠቅሱት አንዱ ነው ። ለመሆኑ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ማለት ምን ማለት ነው ?
1ኛ.ጌታችንን የነሳው ስጋና ነፍስ የሰው ነው። ይኸውም ትምክህታችን ከምትሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ነው ሉቃ 1:26-45 ስጋውን ከሰው ባይነሳው ኖሮ "#ሰው" ሊባል አይችልም ነበር ። የሰውና የእግዚአብሔር መካከለኛ ሊባልም አይገባውም ነበር። አምላክ የሆነ ሰው ፤ ሰው የሆነ አምላክ ከእርሱ በቀር የለምና "#መካከለኛ" የተባለ ወልደ እግዚአብሔር የነሳው ስጋ የሰው ስለሆነ ነው
ጌታችን ከድንግል ከተወለደ በኀላ ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ሆኗል ። በመለኮት ብቻ እንዳይጠራ የሚዳሰስ ፣ የሚጨበጥ፣ የሚበላ ፣ የሚጠጣ፣ የሚራብ፣የሚጠማ የሚደክም ሰው ሇኗል ። "#ሰው" ብቻ እንዳንል ነፋሳትን ማዕበላትን እንደ ነቢያት እንደ ሐዋርያት በእግዚአብሔር ስም ሳይሆን በራሱ ስልጣን ጸጥ የሚያደርጋቸው አጋንንትንም በስልጣኑ የሚያስወጣቸው በደረቅ ግንባር ላይ ዐይንን የፈጠረ ውሃውን ወደ ወይን የለወጠ ነው ። ስለዚህም ሰው ብቻ ነው አምላክ ብቻ ነው ማለት አይቻልም
ከዚህም የተነሳ እርሱ አንድ ጊዜ #በተዋህዶ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነውና #መካከለኛ ተባለ ።ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔርን በመበደሉ በመከራና በጩኸት መካከል የነበረውን የሰውን ልጅለማዳን በመካከል በመሆን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ራሱ መስዋዕት ተቀባይ ፣ ራሱ መስዋዕት አቅራቢ ሆኖ አስታረቀን ። አስታረቀን ስንል ከራሱ ጋር ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስቅዱስ ጋር ነው ። የታረቅነውም በክርስቶስ ሞት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነው ። "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔርም በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ" 2ኛቆሮ 5:18-20 ስለዚህም መካከለኛ የሚለው ቃል ወልድ ዋሕድ ማለት እንጂ አማላጅ ማለት አይደለም
ሌላው ክርስቶስ መካከለኛ መባሉ በእለተ አርብ በተሰቀለ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አድርጎ በሰጠ ጊዜ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለውን ኀጢአት ለማፍረስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል በመስቀል ላይ በመዋሉ ነው ። "እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልኩ እንደሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለው "ዮሐ 12:32 "እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉስ ነው በምድር መካከልም መድኀኒትን አደረገ "መዝ 73:14 ከዚህ የተነሳ ንጉስ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን ሊሽር በምድር ማዕከል በምትሆን በቀራንዮ በመስቀል ላይ በመካከል ቆመ ። ስለዚህ በዚህ ምክንያት መካከለኛ ተባለ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት በሰውና በእግዚአብሔር ለምልጃ የሚቆም መካከለኛ አይደለም
Comment @zekidanemeheretbot

ሱባዔና ሥርዓቱ
ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ
ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡
ሱባዔ ምንድን ነው?
ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡
ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ሱባዔ መቼ ተጀመረ?
ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ሲል ቃልን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ አራት/፡፡
#ይቀጥላል ....

ሱባዔ ለምን?
#ክፍል_ሁለት
የሰው ልጅ፤ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡
በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ.7.22-25፡፡
ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ /ሱባዔ/ ይገባል፡፡
እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡
ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው? በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡
ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡
አኃው ለተልእኮ በወጡበት አንዱን ድቀት አግኝቶት ያድሯል፡፡ በነጋው ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ አለው፡፡እኔም እንዲሁ አግኝቶኛል፤ ይልቁንስ ሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደ ቀደመው ኾነን እንኖራለን ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡
ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢገብረ እኁከል፤ ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡
ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባት ቀን/ እንደ ጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡
ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡
#ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል ሱባዔ ለመግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት?
©ፈረንሳይ ጉራራ ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት
ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ

ኃጢአት መሥራት በራሱ አስቀያሚ ነው፤ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዚያ ኃጢአት መታበይ ግን እጅግ ጽኑ ደዌ ነው፡፡ ጽድቅን ሠርተው በዚያ በሠሩት ጽድቅ ከተኩራሩበት ጽድቁን ያጡታል፡፡ ይህ በኃጢአት ሲኾን ደግሞ የባሰ ነው፤ ወደ ከፋ ጥፋት ይወስደናልና፡፡ ከሠራነው ኃጢአት ይልቅ በሠራነው ኃጢአት መታበይ የሚያመጣው ፍዳ ኵነኔ እጅግ ጽኑ ነውና፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ንስሓና ምጽዋት - በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ንስሓና ምጽዋት - በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
ሱባኤ ለመግባት መደረግ ያለበት ዝግጅት
ክፍል ሦስት
ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት ኣስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት ኣስፈላጊ ነው፡፡
ቅድመ ዝግጅት
ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/ በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኣንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት ኣለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሓ ኣባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በኣባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ ኣባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኣንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሓ ኣባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡
ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ ኣቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው ኣንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዓቅምንና ችሎታን ኣገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡
ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በኣብዛኛው ሱባዔ የሚገባው ኣጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን ኣለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በኣጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሓራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በኣጽዋማት ወቅት ብዙ ኣባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከኣባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ ኣይያዝም» የሚል ኣቋም ለመያዝ ኣይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ካጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግልናል ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ ኣያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና ኣድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡
በክፍል 4 :- በሱባዔ ጊዜ ምን እናድርግ?

ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/
በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሓራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢኣቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡
ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/
ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡
ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማጸን መጽናት ይኖርብናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወንድም እህቶቻችን ይማሩበት ዘንድ አጋሩ

✝✝✝††† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† ✝✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝✝ †††
††† ✝✝ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም✝✝ †††
††† ቸር #እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ #ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ #ጽድቅ መድረስ አይቻልም::
ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::
"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን " #ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: #እመ_ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::
ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው #ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::
ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::
*የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::
*ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::
*የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል::
†††✝✝ በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::
††† #ጽንዕት_በድንግልና: #ሥርጉት_በቅድስና #እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: <3
*ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::*
††† ✝✝ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ✝✝ †††
††† እጅግ የተወደዱ: ሞገስ የሞላላቸውና ፈጣሪያቸውን በክብር ገንዘው የቀበሩ አባቶች ናቸው::
††† ቅዱስ ዮሴፍ ዘአርማትያስ †††
††† ቅዱሱ በእሥራኤል ምድር ተወልዶ ያደገ: ኦሪትን የተማረ ባለጠጋ ሰው ነው:: የተማረ ደግ ሰው ነውና የክርስቶስን መምጣት በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ባገኘውም ጊዜ በአዳኝነቱ (በመሲህነቱ) አምኖ በስውር ተከታዩ ነበር::
†††✝✝ ቅዱስ ኒቆዲሞስ ✝✝†††
††† ወንጌል እንደሚነግረን ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ: መምሕር: ዳኛ እና ሃብታም ሰው ነበር:: እነዚህ ሁሉ ማነቆዎች ግን እርሱን ከፈጣሪው ሊያስቀሩት አልቻሉም:: ሌሊት እየመጣ ከጌታችን እግር ይማር ዘንድም አድሎታል:: በመካከልም ከአይሁድ ጋር ብዙ ተጋጭቷል::
ሁለቱ አባቶች መድኃኒታችን ስለ እኛ ሲል ሞቶ ባለበት ሰዓት ላይ በእርሱ የደረሰ ይደርስብናል ሳይሉ በድፍረት ሥጋውን ከዺላጦስ ተካሠው ለመኑ:: እንባቸው በፊታቸው እየወረደ ከመስቀል አውርደው በዮሴፍ በፍታና በኒቆዲሞስ ሽቱ ገነዙት::
እንዲህ እያሉ:-
"ሙታንን የምታስነሳ ጌታ አንተ ሞትክን?! ደካሞችን የምታጸና ቸር አንተ ደከምክን?!"
*በዚያች ሰዓት ጐልጐታ አካባቢ ዝማሬ መላእክትን እየሰሙ የክብር ባለቤትን ቀብረውታል:: ጌታችንም ከተነሳ በሁዋላ በንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::
"እየሳማችሁ አክብራችሁ እንደ ገነዛችሁኝ እኔም በሰማይ በእንቁ ዙፋን ላይ አስቀምጣቹሃለሁ" ብሏቸዋል:: "አነ አብረክሙ ዲበ መንበረ ሶፎር" እንዲል:: ጻድቃን አበው ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በተረፈ ዘመናቸው ወንጌልን ሰብከው: ከአይሁድ መከራን ታግሰው: በበጐ ሽምግልና ዐርፈዋል::
††† ✝✝ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት✝✝ †††
††† ቅዱስ አቦሊ የሰማዕታቱ #ቅዱስ_ዮስጦስና #ቅድስት_ታውክልያ ልጅ ሲሆን በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ያበራ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ሰማዕት ነው:: የሚገርመኝ ሦስቱ የግማሹ ዓለም አስተዳዳሪዎች ነበሩ:: ዮስጦስ ንጉሥ: ታውክልያ ንግሥት: አቦሊ ደግሞ ልዑል ነው::
ነገር ግን ይህንን ክብራቸውን #በክርስቶስ ፍቅር ጐን: ሚዛን ላይ ቢያኖሩት በጣም ቀሎ ታያቸው:: 3ቱም ከዙፋናቸው ወርደው: ወገባቸውንም ታጥቀው: ባሮቻቸው በነበሩ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ብዙ ተንገላቱ:: መራራ ሞትንም ታገሱ::
በተለይ ቅዱስ አቦሊ ከአንጾኪያ ወደ ግብጽ (ብስጣ) ይዘው አምጥተው ክርስትናውን እንዲተው ያላደረጉት የለም:: በቁሙ ቆዳውን ገፈው: በቆዳው አቅማዳ ሰፍተው: ያንንም አሸክመው: የተገፈፈ አካሉን ጨውና ኮምጣጤ እየቀቡ አዙረውታል::
እርሱ ግን ጌታ በላከለት ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ረዳትነት ሁሉን ችሎታል:: በዘመኑ ብዙ ተአምራትን የሠራ ሲሆን አንድ ጊዜ ቤት ተንዶ 16 ሰዎች ቢያልቁ የተገፈፈ ቆዳውን እየጣለባቸው ተነስተዋል:: በተአምራቱና በተጋድሎውም ብዙ ሺህ አሕዛብን ለክርስትና: ብሎም ለሰማዕትነት አብቅቷል::
እርሱም ከብዙ የመከራ ጊዜያት በሁዋላ በዚህች ቀን አንገቱን ተከልሏል:: ጌታችን "ዜናሕን የጻፈውን: ያነበበውንና የሰማውን ይቅር እለዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጥቶታል::
††† ፈጣሪ ከጻድቃንና ሰማዕታት በረከትን አይለይብን:: ወርሐ ነሐሴንም ለበረከት ይቀድስልን::
††† ነሐሴ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
††† "የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ #ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ:: ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ #ጌታ_ኢየሱስ መጥቶ የነበረ #ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት::" †††
(ዮሐ. 19:38)
††† "በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" †††
(ኢዩ. 2:15)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

4_5861612468970719711.pdf
15.6 MB
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜው ወይም አንድምታው #ውዳሴ_ማርያም ላይ ያሉትን ቃላትና ሃሳብ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት የሚያብራራ እና የሚተነትን የውዳሴ ማርያምን #ትርጉም ማወቅ የሚፈልግ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ መፅሐፍ ነው ።
comment @zekidanemeheretbot
🕊👉 @zekidanemeheret
comment @zekidanemeheretbot
🕊👉 @zekidanemeheret
Audio
"" 🛑መልእክት ለወጣቶች፤ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች🛑 ""
✝በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ
✝በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ