ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
870 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
ግሩም ምስጢር ያለው ወፍ
"ከራድዮን ወፍ ይባላል
ከራድዮን ነጭ ወፍ ሲሆን በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው። ጠቢባን በድካም ፈልገው አድነው ይይዙታል፣ የታመመ ሰው ቢኖር ያቀርቡታል ፤ እሱም በሽተኛውን ትኩር ብሎ ያየዋል የማይድን ለሞት የቀረበ ከሆነ ፊቱን አዙሮ ይመለሳል፣ ቀኑ ገና ከሆነ ግን አፉን ከፍቶ ከበሽተኛው አፍ እስትንፋሱን ይወስዳል፣ በልዑል እግዚአብሔር ኃይል የሰውየው ደዌ ሙሉ ለሙሉ ወደ ወፉ በእስትንፋሱ ይተላለፋል። ሰውየው ይድናል ወፉ ይታመማል።
ፊት ነጭ የነበረው እንደ ከሰል ይጠቁራል፣ ህመም ሲሰማው ወደ አየር ይነጠቃል ሲብስበት ወደ ባህር ራሱን ይወረውራል። በባህር 3 መዓልት 3 ሌሊት ቆይቶ ጽጉሩን መልጦ አዲስ ተክቶ፣ድኖ፣ታድሶ፣ኃያል ሆኖ ይወጣል።
ይህ ፍጥረት በዕለተ። ሃሙስ እግዚአብሔር ፈጥሮታል።
ስለምን ፈጠርው ቢሉ የወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስን ሞትና ትንሳዔ ለማያምኑ ትምህርት ምሳሌ አብነት ይሆን ዘንድ ሥላሴ ይህን ወፍ የማዳን ኃይል ሰተው ፈጥረውታል።
ትንታኔ፦
ከራድዮን ወፍ ---- የክርስቶስ ምሳሌ
የታመመው ሰው --- የአዳም ዘር ምሳሌ ሲሆን
ወፉ በዐይኑ መመልከቱ --- በክርስቶስ ላመነ ሁሉ ድኅነት ምህረት ማግኘቱ ምሳሌ
ወፉ መታመሙ---- ክርስቶስ ስለ እኛ በደል መታመሙ ምሳሌ።
መጥቆሩ ---- ስለእኛ ቤዛ ከኀጢአተኛ የመቆጠሩ ምሳሌ
ወፉ ወደ ላይ መውጣቱ---- ክርስቶስ ከፍ ብሎ መሰቀሉ ምሳሌ
ወፉ በባህር 3ቀን 3ሌሊት መኖሩ ----ክርስቶስ በከርሰ መቃብር 3ቀን 3 ሌሊት መቆየቱ ምሳሌ
ከራድዮን ወፍ ታድሶ ኃያል ሆኖ ከባህር መውጣቱ ---ክርስቶስ በሲዖል የነበሩ ነፍሳትን አድሶ አንጽቶ ገነት አስገብቶ፤ እርሱም ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በለበሰው ሥጋ ወደ ቀደሞ መለኮታዊ ሥልጣኑ ኃይሉ መቀመጡ ምሳሌ ነው።
..........
እንግዲህ ምን እንላለን ሥላሴ አስቀድመው የአዳምን መበደል ሞትም እንዲመጣበት ያውቃሉና ገና ዓለም ሲፈጠር እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ እንደ ነበር የከራዲዮን ወፍ አፈጣጠር ምስክር ሆነን። እግዚአብሔር ፍቅር ነው የምንለው ለዚህ ነው።
ይቆየን
ቸርነቱ ፍቅሩ ምህረቱ አይለየን
ምንጭ የሥነ ፍጥረት አንድምታ፣ መጽሐፈ አክሲማሮስ፤
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
"ያልጠተለወጠ ለውጥ"
(ክፍል ሦስት)
👉ኢትዮፒካ ሚዲያ👈
💚💛
.... ባለፉት ኹለት ተከታታይ ክፍሎች ያልተለወጠው ለውጥ በፖለቲካውና በሚዲያው ዘርፍ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ለመዳሰስ ሞክረናል።
2. ምጣኔ ሀብታዊ ፈተና
ሌላው በዚህ ለውጥ ተብሎ በተጠቀሰው ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከደረሱት መከራዎች መካከል አንዱ ልጆቿ ዕድሜያቸውን ሙሉ ያፈሩትን ሃብት ማጣታቸው ነው፡፡ ከ2010 መጋቢት ወር እስከ ጥቅምት 2012 ዓ.ም ድረስ 1355 ምዕመናን ሃብትና ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ ወድሞ ጥገኛ ሆነዋል፡፡ከአካባቢያቸውየተፈናቀሉ እና የተሰደዱትን ሳይጨምር ፡፡ በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ የተፈናቀሉ ኦሮቶዶክሳውያንን ለማቋቋም ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ በተለይም በሶማሌ፤ በሐረር፤ ድሬዳዋ ፤ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ፤ ባሌ ፤ ደዶላ፤ ፤ኮፈሌ፤ ጅማ፤ መቱ፤ አጣዬ፤ ሲዳማ ፤ ኢሊባቡር ፤ አምቦ ፤ ወለጋ ላይ
የተዘረፉት ባለሀብቶች እና የወደመ ንብረት በዚህ ዘመን ይተካል ተብሎ የማይገመት ነው።
3. የውስጥ መከፋፈል
መንግስት የከፈተላቸውን መልካም ዕድል በመጠቀም ቤተ ክርስቲያንን ለማፈራረስ የተነሱት እነኚሁ አካላት ከላይ የዘረዘርናቸው ውጫዊ መከራዎች አልበቃ ብሏቸው ወደውስጧ ገብተው አንድነቷን ሊበትኑ መንገዶችን መፍጠር ጀመሩ፡፡ ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ የኦሮምያ ቤተ ክህነት በማለት ያቋቋሙትን ሕገ ወጥ ቡድን በገንዘብ እና በሐሳብ በመደገፍ ቤተ ክርስቲያንን ለመበታተን እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ በይበልጥ የተከበሩ አቶ ታዬ ደንድአ ጉዳዩን
ሲቃወሙት አላየንም ፡፡ ይህ ሕገ ወጥ ቡድን በቤተ ክርስቲያን በኩል ተቀባይነትን ቢያጣም ባሉት የመንግስት ባለስልጣናት ድጋፍ አማካኝነት የጥፋት ተልእኮውን በማካሄድ ላይ
ይገኛል፡፡ለዚህ ደግሞ ትልቅ ማሳያ የሚሆነን በአምቦ ጃጄ ወረዳ ያለው ሁኔታ ነው፡፡በዚህ ወረዳ ውስጥ የኦሮምያ ቤተ ክህነት አደራጆች ሥራቸውን ለማከናወንም ሆነ የተንኮል ሴራቸውን ለመመካከር የሚጠቀሙት የወረዳው አስተዳዳሪ የአቶ ከበርኩምን ቢሮ ነው፡፡ የትግራይ ቤተ ክህነት እናቋቁማለን ያሉት ንም አንረሳቸውም።

4. የኃይል እርምጃ
የአረብ ሀገራት ከለውጡ በኋላ ባገኙት ዕድል አማካኝነት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ሀገራችሁን አስከብሩ እስከዛሬ ስትገፉ ኖራችኋል በሚል የሐሰት ትርክት በመበረዝ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ በሆነ ጭካኔ መከራን እንዲያደርሱ ትልቅ ስራ ሰርተዋል፡፡
ከ2010 ዓ.ም ወዲህ በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን የግፍ ዓይነት እስከዛሬ እንሰማው የነበረው በሩቁ በራሳቸው በአረቦቹ ዓለም ነበር፡፡ዛሬ ግን ወደኛ ሲመጡ ይህንንም ይዘውልን መጡ፡፡ይህንን ሐሳብ እንዲያጠነክርልን በአንዳንድ አካባቢዎች በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸሙ መከራዎችን እንይ፡፡
1ኛ). ሁሉም ኢትዮጵያዊ የማይረሳው ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በጅግጅጋ የደረሰው
ግፍ እና መከራ ነው፡፡ይህንን አሰቃቂ ድርጊት ለመፈጸም እራሳቸውን ሂጎ በማለት
የሰየሙት እና ከመንግስት ጀምሮ መዋቅር የተዘረጋላቸው ቡድኖች የጥፋት
ዕቅድ በማዘጋጀት እና ሥራዎችን በመከፋፈል ያከናወኑት ሲሆን በወቅቱ አብያተ
ክርስቲያናት ተቃጥለዋል ክርስቲያኖች ተገለዋል፣ተሰደዋል፣ ካህናት በቤተ
መቅደስ ውስጥ ታርደው አስክሬናቸው እንዳይለይ በእሳት ተቃጥለዋል ከ አዛውንት የ70 ዓመት አረጋዊ ከሕጻናት የ9 ዓመት ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍረዋል፡፡ የምዕመናን አስክሬን እንዳይገኝ ከከተማው አውጥተው በአንድ ላይ ቀብረዋቸዋል፡፡ይህ ሁሉ የተፈጠረው ከለውጥ በኋላ ነው፡፡
2. በዶዶላ በቅርብ ጊዜ የደረሰው የቤተ ክርስቲያን መከራ ፍትሕ ምን ያህል
እንደራቀች ያሳየናል፡፡በቦታው በተፈጠረ ሁከት አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈው ክርስቲያኖች ተገለዋል፡፡በጣም የሚገርመው ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው ኦርቶዶክሳውያን ከገቡበት ሐዘን ሳይወጡ ጥፋተኛ ናችሁ ተብለው ደግሞ አሁን እስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም የሆነው ከለውጡ በኋላ ነው።
3. ወዳጅ ዘመዶቻቸው የሞቱባቸው ኦርቶዶክሳውያን የሟቾችን አስክሬን መቅበር
እንዳይችሉ ሲደረጉ ፍትሕ የሚሰጣቸው አካል አልነበረም፡፡ በምስራቅ ሐረርጌ ቦረዳ ከተማ አንድን የቤተ ክርስቲያን ልጅ ገድለው "አስከሬኑን እናቃጥለዋለን እንጂ በኛ መሬት ላይ አይቀበርም" በማለት አስክሬኑን ደብቀው የፌደራል ፖሊስ በ3ኛው ቀን ማታ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እዛው ቦረዳ ውስጥ
ቀብሮታል፡፡
•እነኚህን ጉዳዮች እንደ ማሳያ አቀረብናቸው እንጂ የደረሱት መከራዎች ብዙናቸው በቀጣይ ጸሑፎቻችን ሁሉንም በዝርዝር እናቀርብላችኋለን፡፡ በተለይ ለቤተ ክርስቲያን ለሀገራቸው እና ለቤተሰቦቻቸው የስስት ልጆች የሆኑት የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ላይ የተፈጸሙት ግፎች
ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የሚለውን ቅኔ በደንብ የሚያሳይ ነው፡፡
•ለዚህም በሐረማያ በወለጋ እና በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን በመሆናቸው ብቻ የተገደሉ እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወጣት ወንድም እና እህቶቻችንን ማየት በቂ ነው፡፡ይባስ ብሎ ችግሩን የፈጠሩት ሌሎች ሆነው ሳለ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ግን ከዩኑቨርስቲ እንዲባረሩ ተደርገዋል ፡፡
በዚህ የለውጥ ጊዜ እየተባለ በሚዘመርበት ወቅት ብቻ ከ142 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ተገለዋል፣ 35 አብያተ ክርስቲያናት ታጥለዋል ፈርሰዋል፣ ከ1355 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሃብት ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ቤት ንብረታቸውን ትተው ተሰደዋል፡፡ ጋዜጠኞች ይህንን የቤተ ክርስቲያንን መከራ እንዳይዘግቡ ተዋንያን እና ፊልም ሰሪዎች ማህተብ እንዳይደርጉ የተደረጉት በዚህ ጊዜ ነው ፡፡

ምሥጋና
በዚህ የሁለት ዓመት የለውጥ ጉዞ ለቤተ ክርስቲያን ከተደረጉት ነገሮች መካከል
ለተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት የይዞታ ማረጋገጫ መሰጠቱ እና ከዚህ በፊት
መንግስት እራሱ አለያይቷቸው የነበሩትን የሲኖዶስ አባላት አንድ እንዲሆኑ እጁን
አንስቷል፡፡ይህንን ሳናመሰግን አናልፍም ውለታም አንረሳምና። ይቀጥላል...

👉 ሼር ይደረግ!!!
"ኹሉን መርምሩ ፥ መልካሙንም ያዙ!"

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
🔥💥የደም ቃል🔥💥
💔💔💔💔💔💔💔
ክፍል አስራ አንድ

ትእይንት 3

(ኤርሚያስ ሲገባ በእጁ ሁለት ነገሮችን ይዟል በብርጭቆ ውሃና ገመድ)

አይ አንቺ አለም እንደሰው ልብ በወረትና በንዋይ የተከበብሽ፣ ብልጭልጭ ነገሮች ወዳሉበት ብቻ ምትዞሪ ወረተኛና ከሃዲ ነሽ......(ከት ብሎ እየሳቀ)

በእስከዛሬ ህይወቴ አኩኩሉ ተጫወትሽ አንቅረሽ እንደተፋሽኝ ሁሉ እኔም አንቅሬ እተፋሻለሁ (እየተፋ) ቱ.....የማትረቢ (ገመድና ብርጭቆውን እያሳየ) እስከዛሬ አንገቴን ደፍቼ እንደኖርኩብሽ አልለይሽም (ገመዱን ከፍ አርጎ ) ከሰው በላይ ከፍ ብዬ ገመዴን ሰረጋላ አርጌ ልታይብሽ ወይስ (ብርጭቆውን ከፍ አድርጎ) በስስት እንዳልረገጥኩሽ ዛሬ ደግሞ ተንፈራግጬብሽ ተይቼሽ ልሒድ። ምርጫውን ላንቺ ትቼልሻለሁ። (ጸጥታ ይሰፍናል)

ማንም ሳያውቅና ማንም ሳይነቃ ጸጥ የሚያረገው ይሄ ነው ( ብርጭቆውን እያሳየ መርዝ ጨምሮ እየበጠበጠ ) አለም ወረተኛዋ በይ እንግዲህ ቻው ድንገት በምጽአት ቀን እንደወረቀት ተጠቅልለሽ ትመጪ የለ? ያን ጊዜ በዳኛ ፊት እንወቃቀሳለን። ዛሬ ግን ተሸንፌያለሁና እስከዚያው ቻው እንግዲህ ቻ.....ው...(የሆነ ነገር ትዝ ይለውና) አለም ካንቺ ምንም አልፈልግም መገነዥያዬንም አዘጋጅቼ ነው የምሞተው ( ወደ መኝታ ክፍል ይገባል)

(ዳንኤል ከውጭ እየተጣራ ይገባል)

ዳኒ፡- ኤርሚያስ.....ኤርሚያስ የትሄደው ነው? እማማ እማማ? ( መልስ በማጣቱ ወደ ጓዳ ሲገባ ኤርሚያስ በሌላኛው በር ጋቢ ይዞ ይገባል)

ኤርሚ፡-( የአባቱን ፎቶ ፊት ለፊት እያየ)አባ.....አንተ ስትሞት ሞትህን በጸጋ ነው የተቀበልከው ወይስ ፈርተሃል? ( ብርጭቆውን አንስቶ እያሳየው) እኔ ግን አልፈራም አብረን መሆን ስላለብን አልፈራም..

(ዳንኤል የሚሆነውን ከኋላ ሲመለከት ነበር ኤርሚያስ ብርጭቆውን ሲያስቀምጠው ቀስ ብሎ ከጓዳ በሌላ ብርጭቆ ውሃ ይቀይረዋል ይህ ሁሉ ሲሆን ኤርሚያስ አባቱ ፎቶ ላይ አተኩሮ አላስተዋለም)

ኤርሚ፡- በቃ መጥቻለሁ አባዬ ተቀበለኝ (ብርጭቆውን አንስቶ ጅው አርጎ ይጠጣዋል ጋቢውንም ለብሶ ይተኛል) (ቢጠብቅ ቢጠብቅ ምንም ነገር የለም) ይነሳና )

መርዝም እንደሰው ማዳላት ጀመረ እንዴ ? (ዳንኤል አጠገቡ መጥቶ ያየዋል) እንዴ ከየት ተገኘህ?

ዳኒ፡- ከዚሁ

ኤርሚ፡- አልተቀየምከኝም ማለት ነው። እኔኮ መቼም የምናገኝ አልመሰለኝም ነበር

ዳኒ፡- ምን አስቀየመኝ! ለመሆኑ እንዲህ ለማድረግ ማንነው የገፋፋህ?

ኤርሚ፡- እንዴት?

ዳኒ፡- እስካሁን እንዳደረከው

ኤርሚ፡- ሕይወት፣ ኑሮ፣ መከራ፣ ችግር እነዚህ ሁሉ

ዳኒ፡- እነ እዮብ ምን ይበሉ፣ እነ ሰማዕቱ እስጢፋኖስ ምን ይበሉ። ከነሱ የበለጠ መከራ ተቀብለሃል? እነሱ ምን ይበል?

ኤርሚ፡- የፈለጉትን ይበሉ

ዳኒኤል፡- ቅድም የጠጣኸው እኔ የቀየርኩትን ንጹህ ውሃ ነው( ብርጭቆውን እያሳየው) ለመሆኑ ይሄ ልትጠጣው የነበረው ምንድነው?

ኤርሚ፡- ጸበል

ዳኒ፡- ምን አይነት ጸበል

ኤርሚ፡- ነፍስን ከዚህች ከሃዲ አለም የሚነጥል ጸበል

ዳኒ፡- ለምን ግን ኤርሚ? መከራህን መከራዬን አድርጌ መመልከት የማልችል ይመስልሃል? በስጋ ባንተሳሰርም በነፍስ ግን ወንድሜ ነህ ለምን እንደባዳ ትመለከተለኛለህ ?

ኤርሚ፡- (እንባ እያናቀው) ኤርሚ እኔ ምንም የማልጠቅም ሰው ነኝ ካሁን በኋላ ጓደኛ አለኝ ብለህ አታስብ መንገዴ የጠፋብኝ አንድ ልቃሚ ሰው ነኝ

ዳኒ፡- የሆነውን ሁሉ ሰምቼያለሁ እናትህ አባትህን እንደገደሉ....

ኤርሚ፡- (ደንገጥ ብሎ) ማን ነገረህ?

ዳኒ፡- ማንም እናትህን ባለፈው ስትነዘንዛቸው ነው የሰማሁት .....ግን ውሸት ነው እናትህ ፈጽሞ አልገደሉትም

ኤርሚ፡- ራሷ ናት( እየጮኸ) ከትልስ ሰው ነው የሰማሁት

ዳኒ፡- እኔም ከአባዬ ጓደኞችና እንዲሁም ከራሱ ከአባዬ ሰምቻለሁ ?

ኤርሚ፡- ምኑን?

ዳኒ፡- ተዋበች ባላን እንደገደለች...

ኤርሚ፡- (ተናዶ) ካሁን በኌላ እናትየሚባል የለኝም አልፈልግም

ዳኒ፡- ተረጋጋ እንጂ ኤርሚ

ኤርሚ፡- ተወኝ (ግብግብ ሲፈጥሩ አባ ይገባሉ)

አባ፡- ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን....ምን ሆናችሁ ነው

ኤርሚ፡- (ወደ አባ እየመጣ) አንተ ከሃዲ......

(ይቀጥላል).......
💥🔥የደም ቃል💥🔥
💔💔💔💔💔💔💔
ክፍል 12

አባ፡- ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን.... ምን ሆናችሁ ነው

ኤርሚ፡- (ወደ አባ እየመጣ) አንተ ከሃዲ ብለህ ብለህ መጣህ ሁለታችሁንም አጠፋችኋለሁ (ያንቃቸዋል)

ዳኒኤል፡- (ለማገላገል እየታገለ) ኤርሚያስ.....ተው ...ልቀቃቸው

አባ፡- መጀመርያ እውነቱን እወቅ

ኤርሚ፡- ዝም በል!

ዳንኤል፡- ኤርሚያስ ልቀቃቸው አልኩህ....(ያስለቅቃቸዋል) ምን ሆነህ ነው ኤርሚያስ?

ኤርሚ፡- ያቺንም ርኩስ አጠፋታለሁ

አባ፡- ተው የእኔ ልጅ እኔ ሁሉንም ግልጥልጥ አድርጌ እነግርሃለሁ....በእናትህ ላይ እጅህን አታንሳ ኋላ ይቆጭሃል....።

ኤርሚ፡-- እሺ በሉአ የእምነት ክህደት ቃላችሁን ልስማ! አውራ

አባ፡- እናትህ እስካሁን ያልነገረችህ በሆዱ ቂም በቀል ይይዛል ብላ በማሰቧ ነው እንጅ የባሏን ነፍስ አጥፍታ አይደለም....የአባትህን ገዳይ ፎቶውን አሳይሃለሁ......የእናንተ ፎቶ ማስቀመጫ ውሥጥ አለ አምጣው እስኪ.....

ዳንኤል፡- ቆይ እኔ ላምጣው (ብሎ ይገባና ሲመለስ ፎቶውብ አውጥቶ በኪሱ ውስጥ ይደብቀዋል) ....ይኸው.....

አባ፡- የአባትህ ገዳይ ፎቶ እዚህ ውስጥ ነው ያለው (እያገላበጡ ይፈልጋሉ) (ፈልገው ፈልገው ሲያጡ ይደነግጣሉ)

ኤርሚያስ፡- የት አለ ያሳዩኛ

አባ፡- እዚህ ውስጥ ነበረ( በድንጋጤ ይፈልጋሉ

ዳንኤል፡- አጡት እንዴ አባ?

አባ፡- እዚህ ነበርኮ

ኤርሚ፡- ከነበረ ታድያ የት ሄደ? ወይስ በእስትንፋስዎት እፍ ብለው ነፍስ ዘርተውለት አበረሩት?

አባ፡- (የሆነ ነገር ትዝ ብሏቸው ፊታቸው ፈካ) ተወው የእኔ ልጅ አንዱ ቢጠፋ ሌላ አይጠፋም( ወደ ኪሳቸው እየገቡ) እዚህ ውስጥ ከአባትህ ጋር የተነሱት ፎቶ ነበር

ዳንኤል፡- (ደንግጦ) ኧረ የለም

አባ፡- (ግራ ተጋብተው) አንተ ስለእኔ ኪስ ምን ታውቃለህ? (ይስቃሉ)

ዳንኤል፡- ተገኘ ለማለት ፈልጌ ነው

አባ፡- አይ ወጣትነት ለነገሮች ሁሉ ችኩሎች ናችሁ

ኤርሚያስ፡- አባ አያሹፉ! ፎቶውን ብቻ ያሳዩኝ

አባ፡- ( እየፈለጉ ያጡትና) እንዴ

ኤርሚያስ፡- የለም?

አባ፡- እዚህ ውስጥ ነበር ያስቀመጥኩት

ዳንኤል፡- (ደስ እያለው) እኔ'ኮ....

ኤርሚያስ፡- የርሶንና የእናቴን ፎቶ ለማሳየት ፈሩ አይደል?

አባ፡' (እየፈለጉ) እዚህ ውስጥ ነበር

ኤርሚያስ፡- ( ተናዶ) ታድያ የት ሄደ?

አባ፡- (ያገኙትና ሳቅ ብለው) አገኘሁት

ዳንኤል፡- (ደንግጦ) ውሸት... ውሸት ነው..

አባ፡- ምኑ?

ዳንኤል፡- እስከዛሬ ኤርሚያስ የሰማው ታሪክ

አባ፡- ( ፎቶውን እያሳዩት) ይሄ ነው የአባትህ ገዳይ

ኤርሚ፡- (ማመም እይምቃተው) አቶ....አሸብር

አባ፡- የት ታውቀዋለህ? ይሄ አሸብር ሳይሆን ተዘራ ነው?

ዳንኤል፡- ማን ነው ያሉት?

አባ፡- ተዘራ

ኤርሚ፡- እንካ እስኪ እየው ታውቀዋለህ?

ዳንኤል፡-(ሳያየው) አይ አላውቀውም

ኤርሚ፡- መች አየኸው?

ዳንኤል፡- እኔ ነፍሰ ገዳይ ማየት አልወድም

ኤርሚ፡- ይሄማ አቶ አሸብር ነው

አባ፡- ተዘራ ነው ብልጥ መሆን አለብህ ልጄ ስሙን ቀይሮ ነግሮህ ይሆናል ካለዚያ ሊታወቅበት እንደሚችል ስለተጠራጠረ ነው ...ብልጥ ሁን እንጂ...

ኤርሚ፡- አጠመደኝ ማለት ነው?

አባ፡- እኔ እንደውም በጣም ትናደዳለህ ብዬ ነበር ነገር ግን ልብ ገዝተሃል ጎበዝ የእኔ ልጅ ራስህን ግዛ! ራስህን ስትገዛ ነው እግዚአብሔር ዓለምን የሚያስገዛልህ( እየተነሱ) እህተ ማርያምን ይዤያት እመጣለሁ እስከዛ ተጫወቱ

ዳንኤል፡- እሺ

ኤርሚ፡- አንድ ተራ ሽማግሌ ይሸውደኛል? ተዘራ የነበረው አሸብር ሆኖ ያታልለኛል? የሞትኩ ነኝ !!! ከሰው በታች ሆና ያሳደገችኝን እናቴን በተንኮለኞች ሴራ እኔው ራሴ ጠላት ልሁናት? .....አባቴ የቀመሰውን ጽዋ እሱ ራሱ እንዲቀምስ ማድረግ አያቅተኝም.....(ተናዶ ወደ ውስጥ ይገባል)

ዳንኤል፡- (መግባቱን ሲያይ) ሞኝ የሞኝ ልጅ እኔ እያለሁ አባቴን ልትገለው? መጀመርያውን በሞት ጀምራችሁታል መጨረሻችሁ ደግሞ ምን ሊሆን ይችላል? ከኪሱ ውስጥ የተጠቀለለ ወረቀት ያወጣል.....(በሐሳቡ አባቱ የተናገረው ትዝ ይለዋል.....ተዘራ፡- ይቺን መድሃኒት ከሚጠጣው ወይ ከሚበላው ነገር ጋር ትንሽ ቀላቅለህ ስጠው ከትንሽ ሰዓታት በኋላ ሁለመናው ይተሳሰራል፣ መናገር አይችልም፣ መራመድ አይችል እጁን ብቻ ቢያንቀሳቅስ ነው...ማንም እንዳያውቅብህ ደግሞ እሺ ...ጎሽ የእኔ ልጅ.....ያሉት ትዝ ይለዋል)

ኤርሚያስ ለመታሰር ራስህን አዘጋጅ...........

ይቀጥላል............
💥🔥የደም ቃል💥🔥
💔💔💔💔💔💔💔
ክፍል 13

ዳንኤል፡- ኤርሚ ለመታሰር ራስህን አዘጋጅ

ኤርሚ፡- (ትልቅ ዱላ ይዞ ይወጣና) በዚህ ጨፍጭፌ ነው ምገለው

ዳንኤል፡- ራስህን ተቆጣጠር ኤርሚያስ

ኤርሚ፡- ተወኝ! አለቀውም፣ የደሃ ጉልበቴን አሳየዋለሁ

ዳንኤል፡- ተው እንጂ ኤርሚያስ የሚሆነውንና ማይሆነውን ለይተህ ማወቅ አለብህ

ኤርሚ፡- አሳልፈኝ ...ልኩን አሳየዋለሁ( ይጮኸል)

ዳኒ፡- (እንደምንም ታግሎ ዱላውን እየተቀበለ ) ኤርሚያስ አስተውል ሰውየው ካንተ የበለጠ ሐይለኛና ብልጥ ሰው ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የምታደርገውን ሁሉ በጥንቃቄ አስተውለው ። እገላለሁ ብለህ ወጥተህ ልትሞትም እንደምትችል አትዘንጋ.....ምክንያቱም በየቦታው የሱ ሰዎች ስላሉ...በዚህ ሰዓት ራሱ ያወራነውን ሁሉ ሊሰማ ይችል ይሆናል....እና ረጋ ብለህ አስብ

ኤርሚያስ፡- (ራሱን ይዞ) ራሴ ሊፈነዳ ነው! ተቃጠልኩኝ

ዳንኤል፡- ውሃ ላምጣልህ?

ኤርሚያስ፡- አዎ ......እሺ

ዳንኤል፡- (በአጋጣሚው ደስ እያለው) ራስህን መግዛት አትዘንጋ (ይገባል)

ኤርሚያስ፡- ወይኔ እናቴ!.....(ብሎ ይተኛል)

ዳንኤል፡- (ውሃውን ይዞ ይመጣል) ኤርሚያስ እንካ ጠጣ

ኤርሚያስ፡- (ይቀበልና ያስቀምጠዋል)

ዳንኤል፡- ጠጣ እንጂ

ኤርሚያስ፡- ይቅርብኝ ባክህ

ዳንኤል፡- ውስጥህ ያለውን ግለት ቀዝቀዝ ያረግልሃል ጠጣ (ይሰጠዋል)

ኤርሚያስ፡- እሺ.....(ተቀብሎ ይጠጣል).

ዳንኤል፡- (እየተነሳ) በል ኤርሚ እቤት ስለሚጠብቁኝ ልሂድ (ይወጣል)..

ኤርሚያስ ሕመም እየተሰማው መጣ.. እግሩ ሲተሳሰር ይታወቀዋል...እግሩን እያነቃቃ ሊያፍታታቸው ሞከረ....ድንገት አባ እና እናቱ ከውጭ ገቡ

አባ፡- ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን

ኤርሚያስ፡- (እናቱን ሲያያት ተነስቶ) እማ ይቅር በይኝ (እግሯ ስር ይወድቃል

ተዋበች፡-ተነስ የእኔ ልጅ.....እኔ በአንተ አልከፋም ተነስ(ልታነሳው እየታገለች)

አባ፡- ኤርሚያስ ተነስ አለችህ አይደል? ተነሳ በቃ

ኤርሚያስ መነሳት አቅቶት መንፈራገጥ ይጀምራል....መሬት ላይ ተዘርሮ አረፋ መድፈቅ ጀመረ.....

ተዋበች፡- (ኡኡ ብለው እየጮኹ) ወይኔ ልጄ! .....አበባዬ.....ልጄ.....(ወደ አባ ዞራ) አባ.....አባቴ ልጄን፣ ተስፋዬን ...የቤቴን ምሰሶ ገደልኩት (ታለቅሳለች) ቀሪ ሐብቴ እኮ ነው አባ.....ኡኡኡኡ.....

አባ፡- (ግራ ግብት ብሏቸው) ምንም አይሆንን አይዞሽ መጀመርያ ተረጋጊ

ተዋበች፡- ልጄ....ሞተ እኮ ኣባ.......ኧረ መላ በሉኝ አባ( ከአንገቱ ቀና አርጋው እያለቀሰች)

አባ፡- እህተ ማርያም መጀመርያ አንቺ ተረጋጊ ( ቀና አርገውት )ኤርሚያስ....ኤርሚያስ..

ተዋበች፡- ምነው ድንግል ማርያም ምን አረኩሽ? ከልጄ በፊት እኔን አስቀድመኝ ፈጣሪ....(ታለቅሳለች)

አባ፡- ወደ ሃኪም እንውሰደው.....(ተሸክመውት ይወጣሉ)


ትዕይንት አራት

ወ/ሮ ተዋበች በሐዘን ድባብ ኩርምት ብለው ተቀምጠዋል፣ ኤርሚያስ ሁለመናው አልንቀሳቀስ ብሎት ከዊልቸር ላይ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል፣ መራመድ፣ መናገር አይችልም። እጁ ትንሽ ትንሽ ይንቀሳቅስለታል። የሚያስፈልገውን ነገር እጅ በማንቀሳቀስ ብቻ ነው ሚገልጸው ወ/ሮ ተዋበች በልጃቸው በሽታ ቅስማቸው ተሰብሯል።

ኤርሚያስ፡- (እጁን እያንቀሳቀሰ በምልክት ውሃ እንደፈለገ ለእናቱ ይገልጻቸዋል)

ተዋበች፡- ምንድነው የፈለከው? እንቅልፍህ መጣ?

ኤርሚያስ፡- (ጭንቅላቱን በአሉታ እየነቀነቀ ....አሁንም በማይገባ ምልክት ውሃ እንደፈለገ ይገልጻቸዋል)

ተዋበች፡- (ግራ ገባቸው) እራበህ? የሚበላ ፈልገህ ነው? ግራ ገብቶኝ'ኮ ነው የእኔ ልጅ አይዞህ....ቸሩ መድኃኔዓለም.. ..(እንባ ይቀድማታል)

ኤርሚ፡- (በምልክት ነይ ብሎ በምልክት ይጠራትና...ስትጠጋው እጁ አንገቱ ላይ ተጣሟ እንደተጣበቀ በአንድ ጣቱ ፊቷን(እንባዋን) ይጠርገዋል

ተዋበች፡- እሽ አላለቅስም

ኤርሚ፡- ( ቀስ ብሎ ውሃ እንደፈለገ ያስረዳታል)

ተዋበች፡- ውሃ ነው የፈለገው...እኔን መች ገባኝ እስካሁን....ቆይ ላምጣልህ(ትገባለች)

ኤርሚያስ፡- (ወደ ስዕለ አድህኖ ዞሮ በልመና አይነት መልክ ያለቅሳል)

ተዋበች፡- (ስትገባ ልጇ ወደ ስዕሉ ዞሮ እያለቀሰ ነው...ውሃውን ሳትሰጠው እሷም ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች...

ኤርሚ፡- (ያያትና ለቅሶውን አቁሞ በምልክት ይጠራታል....

ተዋበች፡- ወዬ የእኔ ልጅ (አንገቱ ስር ትገባለች)

ኤርሚ፡- (እንባዋን ይጠርግላታል)

ተዋበች፡- እሺ የእኔ ውድ ልጅ አላለቅስም...

ኤርሚ፡- በምልክት ውሃውን ያሳያታል

ተዋበች፡- (እየሳቀች)አይ የእኔ ነገር......(ታጠጣዋለች)

ኤርሚ፡- ከልቡ ባይሆንም እናቱን ለማስደሰት ይስቃል........።

የተዘራ ሚስት ወ/ሮ መዓዛና ዳንኤል ወደ እነኤርሚያስ ቤት ይመጣሉ.......

ይቀጥላል
🔥💥የደም ቃል💥🔥
💔💔💔💔💔💔💔
ክፍል አስራ አራት

የተዘራ ሚስት ወ/ሮ መዓዛና ዳንኤል ወደ እነ ኤርሚያስ ቤት ይመጣሉ፣ ያንኳኳሉ)

ተዋበች፡- ማን ነው ይግቡ....

ዳንኤል፡- እንደምን ዋላችሁ....

ተዋበች፡- እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ግቡ...ዳንኤል እንዴት ነህ

ዳንኤል፡- (እየጨበጣቸው) እንዴት ነዎት እማማ?....ኤርሚ እንዴት ነህ? ተሻለህ?

ኤርሚ፡- ( ዳንኤልን ሲያየው ደስ እያለው እንደተሻለው በምልክት ገለጸለት)

ዳንኤል፡- አይዞህ እሱ መድኃኔዓለም መንቀያ መድኃኒቱን አዘጋጅቶልህ ይሆናል....(ራሱን ያሻሻዋል)

ተዋበች፡- አዎ ከእሱ ከፈጣሪ በቀር ልጄን የሚያድንልኝ የለም።

መዓዛ፡- ሐኪሞች ጋር ወስደውሽ ነበር?

ተዋበች፡- ወስጄው ነበር። ነገር ግን አንችልም ይሔ ከአቅማችን በላይ ነው አሉኝ።

መዓዛ፡- አይዞሽ በርታ ማለት ነው አሁን ከዚህ የባሰ መከራ ሊመጣብሽ ነው። ግን በጣም እያዘንኩ ነው ይሄን የማደርገው...

ተዋበች፡- (ግራ ተጋብታ) የምን መከራ?

መዓዛ፡- ለብቻችን ሆነን ብናወራው መልካም መሰለኝ ....

ተዋበች፡- ዳንዬ እስኪ ያዘውና ወደ ጓዳ ግቡ፣ የምናወራው ትንሽ ነገር ስላለ ነው

ዳንኤል፡- እንዴ ከዚህ በፊት ትተዋወቃላችሁ እንዴ ? እኔ'ኮ ላስተዋውቃችሁ ነበር አመጣጤ

ተዋበች፡- ያው አሁን ተዋወቅን አይደለ ?
(ዳንኤል ኤርሚያስን እየገፋው ወደ ውስጥ ይገባሉ)

መዓዛ፡- ምን መሰለሽ ወ/ሮ ተዋበች የሆነች አንድ ትንሽ ቤት ለንግድ እንደምፈልግ ለመንደሩ አስተዳደር ነግሬያቸው ነበር እንደሚፈልጉልኝም ነግረውኝ ተለያየን። እናም አንድ ጊዜ እንዲህ በሩቁ "ያንን" ቤት እንዳገኙልኝ በምልክት አሳዩኝ ቤቱን ከማግኘቴ በፊት ግን ክፍያውን መክፈል እንዳለብኝና ብሩም በማንኛው ሳንካ ተመላሽ እንደማይሆን ነግረውኝ ከፈልኩ.....ያ ያሳዩኝ ቤት ይህን ነበር....

ተዋበች፡- (ደንግጣ) ምን??????

መአዛ፡- በጣም ነው ማዝነው መጀመርያውኑ የዳንኤል የልብ ጓደኛ ቤት መሆኑን ባውቅ ኖሮ መች ይሄን አረግ ነበር.....አሁን ግን.....

ተዋበች፡- አሁን ግን ምን?

መአዛ፡- አሁንማ ብሩም ተመላሽ ስለማይሆንልኝ ቤቱን መረከብ አለብኝ

ተዋበች፡- እኔና ልጄስ?....እኔን ተይኝ ልጄስ?

መአዛ፡- እንግዲህ ምን ማረግ ይቻላል? የሆነ መጠጊያ ፈልጊያ

ተዋበች፡- ምንም ዘመድ የለኝ፣ ዘመዴም ጎረቤቴም ልጄን ነበር እንደምታይው እሱም.......

መአዛ፡- ምንም ልረዳሽ አልችልም

ተዋበች፡- (እያለቀሰች) ኧረ በወላዲተ አምላክ ብለሽ

መአዛ፡- ከሁለት ያጣሁ መሆን የለብኝም (ቆጣ ብላ)

ተዋበች፡- አውቃለሁ ግን በፈጠረሽ ሜዳ ላይ አትጣይን

መአዛ፡- (ቆጣ ብላ) ለምን አይገባሽም? ብትችይ በሁለት ወይም በሶስት ቀን ውስጥ ብትለቂ ደስ ይለኛል

ተዋበች፡- በሶስት ቀን ውስጥ? (እያለቀስ0ች) እኔስ በረንዳ አድራለሁ ልጄ እንኳን እስኪሻለው እዚህ ይሁን እባክሽን?

መአዛ፡- ነገርኩሽ እኮ ወ/ሮ ተዋበች....ቤቱን ቀጥታ ወደ ንግፍ ሥራ ማስገባት ስለምፈልግ.....

ተዋበች፡- (እግሯ ስር ተደፍታ) ሴት አይደለሽ? በሴት ልጅ አምላክ?

መአዛ፡- (ጮክ ብላ) አይሆንም በቃ

ተዋበች፡-(ወደ ምድር ድፍት ብላ) መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ እኔን መግደል ያቅትሃል?....በቃ ግደለኝ.....ግደለኝ

(ዳንኤል ይወጣና ምንም የማያውቅ በመምሰል)

ዳንኤል፡- ምን ሆናችሁ ነው?

ተዋበች፡- (ዳንኤል እግር ስር ወድቃ) ጉድ ተሰራሁ ልጄ እስኪ አንተ ከቻልክ አስታርቀን

ዳንኤል፡-(ግራ የተጋባ በመምሰል)ምንድነው ችግሩ?

ተዋበች፡- እናትህ ቤቱን ስለገዛሁት ውጪ አሉኝ

ዳንኤል፡- ማን እማዬ?

ተዋበች፡- አዎ

ዳንኤል፡- እንዲህማ ማድረግ የለብሽም እማዬ

መአዛ፡- መሆን ስላለበት ነው ያደረኩት

ዳንኤል፡- ኤርሚያስ እኮ ጓደኛዬ ነው...እሱ ዛሬ በሽተኛ ሆኖ መንቀሳቀስ ስላቃተው ቤቱን በላዩ ላይ መሸጥ አለብን እንዴ?

መአዛ፡- እኔስ ብሬን ሜዳ ላይ በትኜ ሜዳ ላይ መቅረት አለብኝ ?

ዳንኤል፡- እማዬ እኔ በአንቺ እተማመናለሁ እንዲህ አታረጊም እርግጠኛ ነኝ

መአዛ፡- በዚህማ አትተማመን አደርገዋለሁ

ዳንኤል፡- እንዲህ ካረግሽ እኔም ልጅሽ አይደለሁም አንቺም እናቴ አይደለሽም

መአዛ፡- በቃ በዚህ ጉዳይ ማውራትም መደራደርም አልፈልግም አሁን እንሂድ።..

ዳንኤል፡- (ቆጣ ብሎ)አልሄድም ኤርሚን እንድንጠይቅ እንጂ ተስፋ ለማሳጣት አልመጣሁም ስለዚህ መሄድ ትችያለሽ

መአዛ፡- ነው? ጥሩ (ለመሄድ ዞር ስትል)

ተዋበች፡- (ተንደርድራ እግሯ ስር ትወድቃለች) ስለ እግዚአብሔር ብለሽ.....እንደው በአንድ ልጅሽ ይዤሻለሁ........

መአዛ፡- ዞር በይ ባክሽ( አመናጭቃት ትወጣለች)...


ይቀጥላል።
💥🔥የደም ቃል🔥💥
💔💔💔💔💔💔💔
ክፍል አስራ አምስት

ተዋበች፡- (ከወደቀችበት ሆና ታለቅሳለች) አለማየሁ ልጅህን ቀና ብለህ ለአፍታ ምነው ባየኸው....የት ላድርገው? እስኪ ነገረኝ

ዳንኤል፡- ተነሱ.....እኔ እንደምንም ብዬ አሳምናታለሁ

ተዋበች፡- አትሰማህማ

ዳንኤል፡- አይዞዎት እንደምንም ብዬ አስረዳታለሁ...እሺ ትለኛለች አሁን ኤርሚያስ እንዳይሰማ! በበሽታድ ላይ ይህን ቢሰማህ መልካም አይደለም። ስለዚህ ተነሱና ፎትዎትን ተጣጠቡ....ተነሱ....እኔም ኤርሚያስን ትንሽ ላጫውተው (ይገባሉ ወደ ጓዳ)

አባ ይመጣሉ እቤት ሲገቡ ያው የተለመደ ሰላምታቸውን አስቀድመው ነው።

አባ፡- ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን.....

ተዋበች፡- (ከጓዳ እየገባች አባን ስታይ እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት) አባ ጉድ ተሰራሁ

አባ፡- ምን ነካሽ? ምን ሆንሽ? (ግራ እየገባቸው)

ተዋበች፡- ልጄን እሜዳ ላይ ጣልኩት ......ጉድ ተሰራሁ

አባ፡- ምን ሆነሽ ነው?

ተዋበች፡- ቤቱን በላዬ ላይ ሸጡት

አባ፡- እነማን?

ተዋበች፡- የመንደሩ አስተዳዳሪ (ታለቅሳለች)

አባ፡- ይሄማ ማይሆን ነገር ነው

ተዋበች፡- ሆነ እንጂ አባቴ.....ካሁን በኋላ ዋጋ የለኝም

አባ፡- ይህማ በህይወት እያለው ፈጽሞ አይሆንም ይህን ከማየቴ በፊት ሞቴን እመርጣለሁ
(ዳንኤል ከጓዳ እየገባ)

ዳንኤል፡- እማማ አያልቅሱ እኔ አሳምናታለሁ አይደል እንዴ?

ተዋበች፡' መቼም እሺ አትልም

አባ፡- ተይው እኔ ጠቅላይ አዛዡ ጋር ሄጄ አቤት እላለሁ። እሳቸው ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ሰው ናቸው ( ለመሄድ ሲነሱ)

ዳንኤል፡- እኔ አግባባታለው እያልኩ አባ

አባ፡- (ቆጣ ብለው) ተወኝ ባክህ ይህ የሕይወት ጉዳይ ነው። (ይወጣሉ)

ዳንኤል፡- (ይደናገጣል) እማማ ያስረዷቸው እንጂ

ተዋበች፡- ተዋቸው ይሂዱ ዳንኤል (ተክዘው ይቀመጣሉ)

ዳንኤል፡- ይሻላል ካሉ......(ወደ ውስጥ ገብቶ ዳንኤልን ይዞ ይመጣል) በሉ እማማ ደህና ዋሉ ልሂድ

ተዋበች፡- ልትሄድ ነው እንዴ? ቆይ አንዴ እዚህ ጎረቤት ጋር መልእክት ነግሬ ልምጣ እስክመጣ ዳንኤልን ጠብቅልኝ

ዳንኤል፡- እሺ

ተዋበች፡- ኤርሚ መጣሁ እሺ (ግንባሩን ስማው ትወጣለች)

(ዳንኤልና ኤርሚያስ ብቻ ቁጭ ብለው ሳለ ዳንኤል ብድግ ብሎ)

ዳንኤል፡- (እየተንጎራደደ) ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ? ዳንኤል ተዘራ....የተዘራ አራጌ ልጅ....ተዘራ ማለት ደግሞ የአንተ ቀንደኛ ጠላት....

ኤርሚያስ፡- (እየተወራጨ በሚሰማው ነገር መናደዱን ገለጸ).

ዳንኤል፡' አሁን ብትዘል፣ ብትፈርጥ ምንም አታመጣም። በቤተሰቤ የሚመጣብኝን ከማጥፋት ወደ ኋላ አልልም....ቀስ እያልኩ መላ ቤተሰብህብ አጠፋልሃለሁ...በመጀመርያ ግን ያንን አቃጣሪ ሽማግሌ ነው የማጠፋው....እንዲህ መላ አካላትህን እንዲታሰር ያደረኩት እኔ ነኝ...ትዝ ይልሃል "ውሃ አምጣልኝ"ብለኸኝ የወጣው ጊዜ ያኔ ነው መድኃኒት ያበላውህ (ከት ብሎ ይስቃል)

አሁን ያንን ቄስ ተብዬ ከመንገዱ ማስቀረት ስላለብኝ ጊዜ አላባክን ካጣሁት ግን አይንህ እያየ ነው እናትህን ሲጥ ማረጋቸው።

ኤርሚያስ፡-(በንዴት እጅግ ተወራጨ ፣ ምንም ሊያመጣ አልቻለም)

ዳንኤል፡- (ከት ብሎ እየሳቀ) በቃ ተናደድሽ ማለት ነው? በጥፊ ይመታዋል) (ሊወጣ ሲል አቶ ተዘራ መጡ)

ዳንኤል፡- አባዬ ያ የተረገመ ቄስ ጠቅላይ አዛዡ ጋር ሄደዋል

ተዘራ፡ ምን (በንዴት) ተከትልና አንቀህ ገደል ጨምረው....

ዳንኤል፡- አይቀርለትም (ይወጣል)

ተዘራ፡- (ኤርሚያስን በጥፊ ይመታውና) አንተ ውሻ የውሻ ልጅ ጋና ዘር ማንዘርህን ነው ማጠፋልህ.....

ኤርሚያስ፡- (እጅግ እያነባ በምልክት ምን እንዳረገው ጠየቀው)

ተዘራ፡- እኔ ያንተ የወፍ ቋንቋ አይገባኝም......ያቺ መናጢ እናትህ ወዴት ናት..........

ይቀጥላል.......
🔥💥የደም ቃል🔥💥
💔💔💔💔💔💔💔
ክፍል አስራ ስድስት

ተዘራ፡- እኔ የአንተ የወፍ ቋንቋ አይገባኝም....ያቺ መናጢ እናትህ ወዴት ናት

ኤርሚያስ፡- (እንባው እየወረደ እየተንቀጠቀጠ በምልክት ተዋት ይላል)

ተዘራ፡- አንተ አርፈህ ተቀመጥ አትንቀጥቀጥብኝ (በያዘው ከዘራ ይመታዋል)

ተዋበች፡- ኤርሚ ቆየሁብህ አይደል ? (ስትገባ እንግዳ በማየቷ) ደህና ዋሉ?

ተዘራ፡- ነይ ተቀመጭ ! (ይጮህባትና ጎትቶ ያስቀምጣታል) አወቅሽኝ?

ተዋበሽ፡- አላወኩዎትም

ተዘራ፡- ተዘራ እባላለሁ የባልሽ......።

ተዋበች፡- (እንባዋ እየመጣ) ዛሬ ደግሞ ምን ቀረህ

ተዘራ፡- ምን አባሽ እንዲቀረኝ ትፈልጊያለሽ? በሄድኩበት ሁሉ እየተከተልሽ መኖርያ አሳጣሽኝ

ተዋበች፡- እኔ'ኮ ትቼሃለሁ! አንተህ ነህ መርዘኛ እባብ ሆነህ አላስቀምጥ ያልከኝ፣ የቤቴን ደስታ ያደፈረስከው አንተ ነህ

ተዘራ፡- አንቺ ወና አፍ ዝም በይ(በከዘራ ይመታታል) ያንን መናጢ ባልሽን በአጉል ትዕቢቱ ነው የደፋሁት፣ ቀጥሎ ልጅሽን በመተት አሰርኩት፣ ቀጥሎ አንቺን መጨረስ ብቻ ነው የቀረኝ...ከዛ በፊት ግን ይህን የማይረባ ልጅሽን መስበር አለብኝ (በያዘው ከዘራ እየመታው ሳለ)

ተዋበች፡- ስለ እግዚአብሔር ብለህ ተወው....(እያለቀሰች ተጠመጠመችበት)

ተዘራ፡- ዞር በይ(ገፈተራት)

ኤርሚያስ ህመሙ ሳይሆን የእናቱን መገፍተር ሲያይ እየተንቀጠቀጠ እጅግ ተወራጨ

ተዋበች፡- ስለመድኃኔዓለም ብለህ በእማ አምላክ

ተዘራ፡- ዞር በይ .....ሰው በሚለው የሚመራ ልጅ ለሀገር አይጠቅምም (ይመታዋል)

ተዋበች፡- በፈጠረህ ....እንደው በገብርኤል ይዤሃለሁ(እያለቀሰች)

ተዘራ፡- (አንስቶ እያነቃት) ዞር በይ ስትባይ ስትባይ ካልሰማሽ ትሞቻለሽ

(ኤርሚያስ እናቱ ታንቃ ሲያይ ከዊልቸሩ መውረድ ቃጣው)

ተዋበች፡- (እንደታነቀች) ልጄን ብቻ ተወው እኔን ግደለኝ

ተዘራ፡- (ጥብቅ አድርጎ እያነቃት) ጸጥ ነው ማረግሽ የማትረቢ

ኤርሚያስ ተወራጨ መፍትሄ ግን አጣ

ተዘራ፡- ሞትሽ ናፍቆሽ ነው አይደለ(ሲለቃት ተዘለፍልፋ ወደቀች)
አንተንም አሰናብትሃለሁ

(ዳንኤል ተመልሶ እየለከለከ መጣ)

ዳንኤል፡-- አባባ አላገኝኋቸውም

ተዘራ፡- ተዋቸው የትም አይገቡን (እየሄደ) እነርሱን ጠብቃቸው ቄሱን ማስቆም አያቅተኝም (ይወጣል)

ዳንኤል፡- አንተ ማትረባ ቤተሰቤን በጠበጥክ አይደል? በመርዝ እንደጀመርኩህ በመርዝ እጨርሳሀለሁ ( አውጥቶ ይበጠብጣል) ....አሁን አፍክን ክፈት.....

ኤርሚያስ፡- (በእንቢታ አንገቱን አነቃነቀ )

ዳንኤል፡- አሃ...እንቢ ማለትህ ነው (ለመጋት እየታገለ)

ኤርሚያስ ፡- (አፉን ዘግቶ ተወራጨ)

ዳንኤል፡' (በንዴት መታው) አንተ የውሻ ልጅ

(አቶ ተዘራ ከውጪ ድንገት መጡና)

ተዘራ፡- አሁን እሱን ተወውና ሔደህ እናትህንና አቶ ዘለቀን ጥራቸው። ከዚያም እቃቸውንም እነሱንም አብረን አውጥተን እንወረውራቸዋለን...

ዳንኤል፡- (ብርጭቆውን እያስቀመጠ) እሺ (ይወጣሉ)

ኤርሚያስ፡- (እናቱ መሬት ላይ እያያት ወደሷ ለመሄድ ሲወራጭ ከዊልቸሩ ላይ ወደቀ.....በደረቱ እየተሳበ ሄዶ አጠገቧ ሆኖ አለቀሰ..... ምላሽ ሲያጣ መርዙን ሊጠጣ ወደ መርዙ መሳብ ጀመረ.....ድንገት እናቱ ስታስል በመስማቱ ፊቱን ወደሷ አዙሮ አለቀሰ.......

ተዋበች፡- (ተነስታ ልጇን በሐዘን ፊት እያየች ከመሬት ሳትነሳ ወደ ልጇ ተጠግታ.)....ለምን ታለቅሳለህ ኤርሚ? አይዞህ(እየጠረገችለት) እነሱን ሳላሳድራቸድ አልሞትም .....ኤርሚ አታልቅስ ከእንባህ ጉልበቴን አትሸርሽረው ....ስትስቅ ሃይሎ ይታደሳል....አታልቀስብኝ ልጄ

ኤርሚ፡- (እሺታውን በአንገቱ እንቅስቃሴ እየገለጸ፣ ከልቡም ባይሆንም ለእናቱ ደስታ ሲም ፈገግ ይላል) እናቱም ቀና አድርጋ ታቅፈዋለች

ተዋበች፡- የእኔ ልጅ አሁን የመጨረሻዎቹ ሰዓታት እየመጡ ነው። አይዞህ የእኔ ልጅ ሞታችን በህይወት ይለወጣል.....አሊያም ሞታችንን በሞት እንቀበለዋለን ....በርታ በል አታልቅስ ደግሞ እንባ የሽንፈት ምልክት ነው....ጠላቶቻችን እንባችንን ሲያዩ ረዳት የሌለን ዳግም ላንነሳ የወደቅን አድርገው ነው የሚቆጥሩት ...እኛ ግን ጥላ የማትጥል ትልቅ እናት ጽዮን ማርያም አለችን.....ካሁን በኋላ ኣልቅሰህ እንዳትስለቅሰኝ ....።.

አባ ተመልሰው መጡ የተካለቸው ጉዳይ እንደተሰካላቸድ ለመገመት አያዳግትም...

አባ፡- ሰላም ለዚህ ቤት (ሲገቡ እናትና ልጅ መሬት ላይ ተቀምጠዋል ግራ እየተጋቡ) ምነው እህተ ማርያም ቅዝቃዜ አይደል እንዴ......ለምን መሬት ላይ አስቀመጥሽው

ተዋበች፡- አባቴ መጡ እንዴ?....ምን እኔ አስቀምጠዋለሁ

አባ፡- ታድያ ማንነው

ተዋበች፡- የእናቱን ሽንፈት ፣ የእናቱን ውድቀት ማየት ቢሳነው ተነስቶ አጠገቤ አብሮኝ ወደቀ....

አባ፡- የምን ሽንፈት...እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ፈጽሞ ሽንፈት የሚባል ነገር አያውቀንም ሁሉን በጊዜው ያስተካክለዋል

ኤርሚያስ፡-(የሄዱበት ነገር እንደተሳካላቸው በምልክት ጠየቃቸው)

አባ፡- መጀመርያ ከመሬቱ ተነስና እነግርሃለሁ (ያነሱታል)

ይቀጥላል.....

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
🔥💥የደም ቃል💥🔥
💔💔💔💔💔💔💔
የመጨረሻ ክፍል

አባ፡- መጀመርያ ከመሬቱ ተነስና እነግርሃለሁ(ያነሱታል)

ተዋበች፡- የሄዱበት ነገርስ እንዴት ሆነ

አባ፡- እግዚአብሔር መልካም ነው ሁሉም ለበጎ ነው የሚፈጸመው። መቼም በስንዴ መሃል አይጠፋም ። ይሔ የሕይወት እውነታ ነው። ጠቅላይ አስተዳዳሪው እንዴት ደግ ሰው መሰሉሽ

ተዋበች:- ምን አሉ (በጉጉት)

አባ፡- የሆነውን ሁሉ በግልጽ ነገርኳቸው፣ በነገሩም በጣም ተበሳጭተው ሕዝበ እግዚአብሔርን የሚበድል እርሱ ወዳጄ ሊሆን አይችልም አሉኝ በኋላ ራሳቸው እቤት ድረስ እንደሚመጡ ነግረውኝ ነው የመጣሁት

ተዋበች፡- (እንባ እየተናነቃት ) የእኔን የመናጢ ድሃ ቤት እንዴት አወቁት

አባ፡- እንደዚህ አይባል እህተማርያም .....ጊዜ የጣለውን እግዚአብሔር ያነሳዋል

(ዳንኤል መጣ....ከዚያም እቤት ውስጥ ሁሉም ስላሉ አጥፊው ልበ በደስታ ተሞልታ...)

ዳንኤል፡- እንደምን ዋሉ እማማ?

ተዋበች፡- ደህና እግዚአብሔር ይመስገን ዳንኤል እንዴት ነህ?

ዳንኤል፡- (እያሽሟጠጠ) አባ ይፍቱኝ

አባ፡- ተባረክ ልጄ እግዚአብሔር ይፍታህ

(ኤርሚያስ ዳንኤልን ሲያየው በጣም ተናዶ መወራጨት ጀመረ)

ዳንኤል፡- (በሃዘኔታ አይነት) ብዙ አትወራጭ ትሰበራለህ.....

ተዋበች፡- እውነቱን እኮ ነው ኤርሚ....የሱ መምጣት እንደዚህ ያስደስትሃል እንዴ?

(ኤርሚያስ ማንም ስላልተረዳው እያዘነ ሳለ ቤቱን በላያቸው ሊሸጡት የነበሩት አስተዳዳሪ አቶ ዘለቀ፣ አቶ ተዘራና ባለቤታቸው ወ/ሮ መዓዛ ተከታትለው ይገባሉ)

አቶ ዘለቀ፡- አባ እንኳን በሰላም አገናኘን....እንደምን ዋሉ አባቴ(እያፌዘ)..

አባ፡- እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን

ተዘራ፡- የሄዱበት ጉዳይ ተሳካልዎት

አባ፡- የትኛው ጉዳይ የእኔ ልጅ

ተዘራ፡- ጠቅላይ አስተዳዳሪው ጋር የሄዱበት

አባ፡- የምን ጠቅላይ አስተዳዳሪ

ተዘራ፡- አፌዙ ማለት ነው?

አባ፡- ኧረ እኔ አላፌዝኩም

ዘለቀ፡- መሸዋወዱ መልካም አይመስለኝም አሁን ሰዓቱ አልቋል መጨረሻው ደቂቃ ላይ ነው ያላችሁት የምትጠቅቁትን ብቻ በግልጽ ተናገሩ

መአዛ፡- መናገር ካልፈለጋችሁ ደግሞ (በዐይኗ ወደ ዳንኤል አሳየቻቸው)

ዳንኤል፡- ዝግጁ ነኝ(ብሎ ጩቤ ኤርሚያስ አንገት ላይ ያደርጋል)

ተዋበች፡- (ደንግጣ) ዳ.....ን...ኤ.....ል?..

ዳንኤል፡- አቤት ወ/ሮ ተዋበች

ተዋበች፡- አንተም....ልጄን?

ዳንኤል፡-እ..... እኔ ልጅሽን ምን አደረኩት? ምንም?

ተዋበች፡- ግን ለምን ልጄ(ወደ ዳንኤል ዞራ)

ዳንኤል፡- የቤተሰብ ፍቅር ነው፣ ምን ላድርግህ በእነሱ የሚመጣብኝን ምንም ነገር እቀበላለሁ እናም ወ/ሮ ተዋበች በእኔ አይዘኑ በእድልዎት ብቻ ይዘኑ.....ማድረግ ያለብኝን ከማድረግ ወደ ኋላ አልልም (ጩቤውን እሷ አንገት ላይ ያደርጋል)

(ኤርሚያስ ይወራጫል)

አባ፡- (ደንግጠው) እሷን ተዋት እኔ ሁሉንም በግልጽ እነግራችኋለሁ.....እሷን ግን ተዋት

ዘለቀ፡- (ተደላድሎ እየተቀመጠ) ቀጥል

አባ፡- እኔ እንኳን የሄድኩት ....(ዝም ይላሉ)

ተዘራ፡- እርሷ እንኳን የሄዱት?....የት ነው እ?

አባ፡- እኔ እንኳን የሄድኩት ጽዮን ማርያም ነበር

ተዘራ፡- (ከት ብሎ እየሳቀ) ፅ...ዮ...ን ማርያም?

መአዛ፡- አንገቷን ቆርጠህ ስታስቀምጥላቸው እውነቱን ያወራሉ

ዘለቀ፡- (በንዴት) ሲጥ አድርግና አሳያቸው

ዳንኤል፡- እሺ (ኤርሚያስን ተንደርድሮ ሊያንቀው ሲል)

አባ፡- ለምን ዝምብላችሁ ብዙ ታናግሩናላችሁ....እኛን ለማጥፋት ከፈለጋችሁ እኛን አጥፉን ...እሱን ተውት....እኔ እንኳን የሄድኩት ጠቅላይ አዛዡ ጋር ነው...

ዘለቀ፡- ምን?.....ከዛስ?

አባ፡- ከዛማ እየደረሰብን ያለውን ግፍ ነገርኳቸው....

ዘለቀ፡- አንተ አቃጣሪ ሽማግሌ.....አሁን ምን ልናደርግ ነው እሺ? አለቀልኝ....

ተዘራ፡- ሁሉንም ተራ በተራ እንጨርሳቸው.......

(ጩቤ አውጥተው ሁሉንም ሊወጉ ሲሉ የከተማው ጠቅላይ አዛዥ ከወታደሮቻቸው ጋር ይገባሉ)

ፖሊስ፡- እንዳትንቀሳቀሱ ሁላችሁም ባላችሁበት ቁሙ(ይደቅኑባቸዋል) (እነ ተዘራ ሁሉም መሬት ተንበረከኩ) (ተዋበች በእልልታ ቤቱን አናጋችው)

ጠቅላይ አዛዥ፡- እናንት ጨካኞች ለስራችሁ ሚገባችሁን ቅጣት ታገኛላችሁ....

ዘለቀ፡- ሁሉንም ያቀናበረው እሱ ነው(ወደ ተዘራ እየጠቆመ)

ጠቅላይ አዛዥ፡- ሌባ ሲሰርቅ እንጂ ሲካፈል አይስማም አሉ በል ተንቀሳቀሱ....(ይዘዋቸው ይወጣሉ አባም ተከትለው ይወጣሉ )

ተዋበች ኤርሚያስን አቅፋው ተላቀሱ ...አየህ ኤርሚ እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ ነው ለሁሉም ጊዜ አለው.....(ብላ እጅግ ውሃ ስለጠማት ዳንኤል በጥብጦ ያስቀመጠውን መርዝ ጠጣችው(ኤርሚያስ ሊነግራት ቢወራጭም ስላልተረዳችው ጠጣችው ....ተዝለፍልፋ ወደቀች.....ኤርሚያስ ያለቅሳል .....

(አባ ሲገቡ ኤርሚያስ ሲያለቅስ አዩት ተዋበችም ወድቃለች......ከጓዳ አምጥተው ጸበል አጠጧት፣ ለእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሰጠውን መርዝ ወደ ውሃ የቀየረ አምላክ መርዙን አረከሰላት....እየተነሳች እግዚአብሔርን አመሰገነች.......)

አባ፡- (እያቀፏት) ልጄ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል
" እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ። ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።"
(የማቴዎስ ወንጌል 17:20) አይደል ሚለው ቃሉ ....አይዞሽ ልጄ::

ኤርሚያስንም ስመ ሥላሴን፣ስመ ድንግል ማርያምንና ስመ ቅዱሳንን እየጠሩ አጠመቁት በመተት የተያዘውም አጋንንቱ እየጮሁ ወጡ

ተፈጸመ

እግዚአብሔር አምላካችን ምንም ማይሳነው ኤልሻዳይ፣ ሁሉን የሚያድል ባለጸጋ፣ ቸር ይቅር ባይ አምላክ ነው።

አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስጨረሰን ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
በመሸነፍ ውስጥ ማሸነፍን አሳይቶን
ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልጦልን
ጨለማውን ፍቆ ብርሃኑን ለገሰን
የትንሣኤው ብርሃን ህይወትን ለእኛ ሰጠን
ኢዮአታም
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፡፡
መልካም በዓል
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማግሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡


#እንኳን ለብርሃነ
#ትንሳኤው በሰላም
#አደረሳችሁ ::
ማሳሰቢያ

እባካችሁ ቻናል ያላቹ ግሩፕ ያላችሁ ሼር ሼር ሼር በማድረግ ለወገን እንድረስ


የተከበራችሁ የተዋህዶ ልጆች እዚህ ላይ ጉባኤ ቅዱሳን በሚል የተከፈተ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ስረዓተ ቤተክርስትያንን የማይወክል የትምህርት ዓላማ ያለውና ሰውን ለማታለል በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም ወይም በድርቅና ኦርቶዶክስ ነን የሚሉ ሰዎች የከፈቱት የቴሌግራም ቻናል ነውና ሳታውቁ የገባችሁ አሁኑኑ ውጡ።
ለምን እዛ ሆኜ አልጋፈጠውም እውነታውን ካላችሁተሳስታችኋል ምክንያቱም ይሄ ግሩፕ ሳይሆን ቻናል ነው።
የአስተሳሰብ ለውጥ በአእምሯችሁ ውስጥ በመፍጠር ልክ በፍልስፍናዊ ዘዴ እናንተን ማውጣት ነው።

እንንቃ እንጠብቅ።

ሼር ሼር

አይታችሁ በማርያም እንዳታልፉ🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏🙏ሜሳሰቢያ🎤🎤🎤

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እራሳችንንና ቤተክርስትያናችንን ለመታደግ በምናደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ እናንተም የድርሻችሁን እንድትወጡ እንፈልጋለ

ሆኖም አላስፈላጊ ክርክር የምታመጡ ሰዎችም አላችሁ

እውነት በማርያም ስም ምዬ እላችኋለሁ እኔ ማንንም ለማጥላላት እና የራሴን አባላት ለሜብዛት የማደርገው አንዳችም ነገር የለኝመ።

ስለዚህ እንደዚህ አይነት ምክንያት እያቀረቡ አንድትጠራጠሩ ሊያደርጓችሁ እንደማችሉ አውቃለሁ
እኔና እናንት ግን መተማመን አለብን

ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ግሩፖች እና ቻናሎች ውስጥ ያላችሁ ሰዎች አሁኑኑ ብትወጡ መልካም ነው።

1,ጉባኤ ቅዱሳን ቻናል
2,ጉባኤ ቅዱሳን ግሩፕ
3,a user (hidden sender) channel
4,Daily meditation channel
5,Orthodox vs Tehadso channel
6,እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ግሩፕ
7,የክርስትያኖች ህብረት ግሩፕ


ሌሎችም አሉ እያጣራን ነው።

በግሩፕ ውስጥ የሚከራከራቸውና መልስ የሚሰጣቸውን ሰው ብሎክ በማድረግም ደካማውን እየበዘበዙት ነው እንድረስ ሳያውቁ አይጥፉ።
እኔ በግሌ በ 3 የተለያያ አካውንት በሙሉ ብሎክ አድርገውኛል።

እባካችሁ ውጡ ልስማቸው እንዳትሉ
ምን ያመጣሉ እንዳትሉ
አይጠቅመንም


ሼር ሼር ይደረግ
ሞክሼ ፊደላትን ጠብቁ!
💚💛
ትንሳኤ = መከልከል
ትንሳዔ = ትርጉም የለሽ
ትንሣኤ = መነሣት
በአል = ጣዖት
በዓል = የተከበረ (የከበረ) ቀን

@zekidanemeheret
በእንተ በዓላት ዘኦርቶዶክስ
(በኦርቶዶክሳዊ በዓላት ላይ የሚሠራ ሴራ)
💚💛
ቅድስት ርትዕት ቀደምት ኵላዊትና አንዲት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ጊዜያት የምታከብራቸው ታላላቅ በዓላት አሏት። ከእነዚህ በዓላት መካከል በመንግሥት ደረጃ ዕውቅና የተሰጣቸውን ጥቂቶቹን ብንጠቅስ ልደተ እግዚእ (ገና) ፣ ጥምቀተ እግዚእ ፣ ስቅለተ እግዚእ ፣ ትንሣኤ ፣ መስቀልና የዘመን መለወጫ (ቅዱስ ዮሐንስ) የመሳሰሉት ይገኛሉ። እነዚህ በዓላት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዘንድ እጅግ በታላቅ ክብር የሚከበሩ መንፈሳዊ በዓላት ናቸው። ይሁን እንጂ እነዚህ መንፈሳዊ በዓላት በሚከበሩባቸው ጊዜያት (ዕለታት) በኹሉም የኢትዮጵያ የመንግሥትና የግል ሚዲያዎች ላይ የሚስተዋል ስሑት አሠራር (የተሳሳተ የበዓል አከባበር) አለ።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥኖችና የሬዲዮ ጣቢያዎች ኹልጊዜ የኦርቶዶክስ በዓላት ሲመጡ በዓላቱ መንፈሳዊ ሆነው እያለ የሚያዘጋጇቸውን ልዩ የበዓል መርሐ ግብራት አስተውላችሁ ከሆነ ለበዓላቱ ባለቤቶች እጅግ በጣም የሚያናድዱና የሚያሳፍሩ ናቸው! ለበዓል ከሚጋብዟቸው እንግዶች ጀምሮ ኹሉም ጣቢያዎች ስለበዓላቱ ምንም የማያውቁ ጨፋሪዎችን ዘፋኞችን (አርቲስት የተባሉ ዓለማዊያንን) እንግዳ አድርገው ያቀርቡልንና እንድንከታተል ይጋብዙናል። ለምሳሌ ኹሌም በየዓመቱ በዕለተ ትንሣኤ በኹሉም ጣቢያዎች የሚተላለፉ ዝግጅቶች በሙሉ ስለመብላትና መጠጣት (ስለሆድ) የሚገልጹ ከመሆናቸው በተጨማሪ ፣ 'የማያዉቁ ታዋቂዎችን' (አርቲስቶችን) የሆነ ቦታ ወስደው ሲያላግጡ ወይም ስቱዲዮ ቁጭ አድርገው ሲያዘፍኑና እስክስታ ሲያስወርዱ ይውላሉ። ለይስሙላ ለአምስት ደቂቃ ስለበዓላቱ ከሚያስተላልፉት ነገር ውጪ በዕለቱ ያሉት ሙሉ ዝግጅቶቻቸው የበዓሉን ይዘት ያልጠበቁ ፣ በዓሉን ሥጋዊ በዓል የሚያደርጉ ፣ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ የሚያፌዙና የሚሳለቁ ናቸው። በኹሉም ጣቢያዎች ቀኑን ሙሉ ዘፈንና ጭፈራ ሲተላለፍ ይውላል። በእኛ በዓላት የእስፖንሰር ጋጋታ ያገኛሉ ማስታወቂያዎች ይጎርፉላቸዋል በእኛ ያተርፋሉ እኛና እኛን ግን ያፌዙብናል!። ግን እስከመቼ?
በእርግጥ ዘፋኞቹም ፌዘኞቹም ጋዜጠኞቹም የሚዲያው ባለቤቶችም ቢሆኑ የመብራት ፖል የሚያክል ወፍራም ክር በአንገታቸው ሊኖር ይችላል። ነገርግን የማዕተባቸውን ትርጉም ፈጽሞ አያውቁትም። ቢያውቁትማ ኖሮ እግዚአብሔር በሚከበርበት ዕለት ሉሲፈርን ሲያወድሱ ባልዋሉ ነበር።

የሙስሊሞች በዓላት ሲመጡ ግን ኹሉም ሚዲያዎች ታጥቀውና አደግድገው ይጠብቃሉ። በሙስሊሞች በዓላት ሚዲያዎች አንድም ቀን እንደኦርቶዶክሳዊ በዓላት ሲቀልዱና ከበዓሉ ይዘት ውጪ የሆነ መርሐ ግብር ሲያስተላልፉ አይታዩም። ኹሉም ጣቢያዎች ስለበዓሉ የበዓሉን ባለቤቶች ነው የሚጋብዙት። ጋዜጠኞቹም ከአለባበስ ጀምሮ ይጠነቀቃሉ። ዕለቱን በዓሉን የሚገልጽ ያደርጉታል። ለእረፍት እንኳን ዘፈን (ጭፈራ) ጋብዘው አያውቁም የእስልምና መዝሙሮችን (መንዙማ) እንጂ። ኦርቶዶክስ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ሙስሊም እስኪመስሉን ድረስ የእስልምና ልብስ ለብሰው በዓላቱን ያከብራሉ። ይኸ ለምን ይሆናል? አንልም! (እናበረታታለን እንጂ)። ጋዜጠኞቹና አዘጋጆቹ የራሳቸው በዓላት ላይ (ኦርቶዶክሳዊ በዓላት ላይ) ግን ዘፋኝና ቧልተኛ ጋብዘው የሚቀልዱትን ነገር አጥብቀን እንቃወማለን! ይህ ለምን ይሆናል? እስከመቼ? እንላለን!

ወያኔ መራሹ ኢህአዴግ በታሪክ አጋጣሚ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ጀምሮ ሚዲያዎች የኦርቶዶክሳዊ በዓላትን ይዘት የማይገልጹ መርሐ ግብሮችን ሲያስተላልፉ ኖረዋል እያስተላለፉም ነው። ይህ ደግሞ ኦርቶዶቶዶክሳዊያን ላይ የተሸረበ ሥውር ሴራ ስለመሆኑ አያጠራጥርም (ብዙ ማስረጃዎች አሉ)። ከዚህም ባለፈ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ራሳችን በራሳችን በዓላት ላይ የሚቀርቡ ፀረ-ክርስትና መርሐ ግብሮችን ባለማወቅም በየዋኅነትም በግዴለሽነትም ከመከታተላችንም በተጨማሪ እንድንለምዳቸውና ከበዓላቱ ይልቅ በበዓላቱ የሚቀርቡ ሥጋዊ መርሐ ግብራትን እንድንለምዳቸው ተደርገናል። የምንጓጓውም ለበዓላቱ መንፈሳዊ በረከት ሳይሆን በበዓላቱ ዕለት ለሚቀርቡ ቧልቶች ሆኗል። እኛ ኦርቶዶክሶች እስካልነቃን ድረስ በኦርቶዶክስ ላይ የሚደረገው በደልና ግፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ግን እስከመቼ? እስከመቼ ነው የሚቀለድብን? እስከመቼ ነው ግፍ የሚሠራብን? እኛስ እስከመቼ ነው የምንተኛው? እባካችሁ በአካልም በመንፈስም እንንቃ! እግዚአብሔር የነቃ ልቡናን ያድለን። ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያና ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ! አሜን።
👉 ሼር ይደረግ!

"ኹሉን መርምሩ ፥ መልካሙንም ያዙ!"
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
ብዙዎች በእለተ ስቅለቱ በእለተ ትንሣኤ መልካም ዜና ተሰማ ይሉና; "በዛሬው እለት እንግሊዝ የመከላከያ ቁሳቁሱዋን ለኢትዮጵያ ላከች..ረዳች..." አይነት ዜና ያቀርባሉ::
ወገኔ በእለተ ስቅለቱ ለኢትዮጵያ መልካም ዜና የተሰማው ከላይ ነው!
ሌላው ቁሳቁስ የምስራች ሳይሆን መርዶ ነው::ተጭኖ የሚመጣው ቫይረስ ነው!
PPE ማለት personal protective equipment ማለት ነው::"ለኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች PPE መንግስት ያቅርብልን" ብለው በአሜሪካ ካሊፎርኒያና በእንግሊዝ ለንደን ጎዳናዎች የህክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ ተራው ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣበት ጉዳይ ነው::shortage of PPE በእንግሊዝም በአሜሪካም በቻይናም በሁሉም በቫይረሱ መጠነ ሰፊ ጉዳት እየደረሰባቸው ባሉ ስልጡን አገሮች ላይ አለ::እጥረት ላይ ናቸው::ይህ በሆነበት ሁኔታ ነው ለእኛ ብቻ ቁሳቁሱ በነጻ እየጎረፈልን ያለው::እነዚህ አገሮች ለራሳቸው ዜጋ ማዳረስ ያልቻሉትን ቁሳቁስ ለእኛ በገፍ እንዲዳረስ የፈለጉበትን ምክንያት ስንረዳ ነው የምስራቹ መርዶ እንደሆነ የምናውቀው::
እነዚህ ሁለት ዜናዎች የትናንት እና የዛሬ ማለትም የሚያዚያ 8 እና 9 ዜናዎች ናቸው::
"የቻይና የህክምና ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ገቡ::ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የተላኩ የቻይና የህክምና ባለሙያዎችን አዲስ አበባ ገብተዋል።በውስጡ 12 ልኡካንን የያዘው የቻይና የህክምና ባለሙያዎች ቡድን በዛሬው እለት ነው አዲስ አበባ የገቡት።የህክምና ባለሙያዎቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አቀባበል አድርገውላቸዋል...." ይላል_አንደኛው መርዶ
ሁለተኛው መርዶ ደግሞ "እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የህክምና ቁሳቁስ በካርጎ ላከች::የሚለው ነው::
"እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚረዱ የህክምና ቁሳቁሶችን ልካለች። የህክምና ቁሳቁሶች ዛሬ አዲስ አበባ የደረሱ ሲሆን፥ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መሆናቸውን ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። የህክምና ቁሳቁሶቹ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት…" እያለ ይቀጥላል::
ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም እንጂ ከዚህ በፊት ያወራናቸውን
"ቢልጌትስ 200 ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ ለገሰ.."
"ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ 15 ሜትሪክ ቶን ቁሳቁስ ላከች.."
"ቻይናዊው የአሊባባ ግሩፕ ባለቤት ጃክ ማ 5 ሚሊዮን ቁሳቁስ ለኢትዮጵያ ላከ..."የሚሉትን ጨምሮ በርካታ አገሮችን መጥቀስ መዘርዘር ደግሞ ደጋግሞ ማካተትና ማስታወስ ይቻላል::
አሜሪካ ቻይና አረብ ኢምሬትስ እንግሊዝ ሌሎችም "ኢትዮጵያችን ኢትዮጵያችን" የሚሉ አገሮች የራሳቸው ድስት አርሮባቸው ገና አማስለው ያልጨረሱና ገና ያላረረባትን የኢትዮጵያን ድስት ለማማሰል የወጥ እንጨት ክምር ተሸክመው የሚመጡት, መምጣት ያልቻሉት በትልልቅ ካርጎ አሸክመው የሚልኩት ቁሳቁስ ነው ብሎ የምስራች መንገር አይቻልም::አገራቸው ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የሚውጣባቸው ይህን ቁሳቁስ ስጡን በሚል ነው::የዜጎቻቸውን ጥያቄ ሳይመልሱ እንዴት ለእኛ ይሰጣሉ?የሚለው ብቻውን የዜናውን መርዶነት ካላሳወቀን እንዳሰቡት እንደምናልቅላቸው ከፋሲካ በፊት መረዳት አለብን! ደግሞ የእንግሊዝ ይግረም እንጂ!እንግሊዝ የሞት ቁጥሩዋ ጨምሮ እንደተጨነቀች እናውቃለን:: አሜሪካም ቻይናም ኤምሬትስም ወዘተም ያው ናቸው::ኢትዮጵያ ገና 3 ሰው እሱንም ከእነዚሁ ከተጨነቁልን አገራት የመጡ ዜጎቻችን ይዘውት የገቡት ነው::
ሌላ የከፋ ነገር እስካሁን የለም::ለወደፊቱ ጥንቃቄ ከሆነ ለምን ለእኛ ብቻ ይጠነቀቃሉ?አፍሪካ ውስጥ እነ አልጀሪያ እነ ሳውዝ አፍሪካ እነ ወዘተ ያውም ቅኝ የገዙዋቸው አገሮች የራሳቸው ዜጎች በገፍ የሚገኙባቸው የአፍሪካ አገራት አሉ::በሞትም በልክፍትም ከኢትዮጵያ የባሱ::ለምን እነሱን አይረዱም?ለምን ለእነሱ ቅድሚያ አይሰጡም?እያልኩ ስሞግታችሁ አልኖርም!
ይልቁንም ይህ ሁሉ ጋጋታ አልሞት ስላልናችው ነው ወደሚለው ሃቅ እንድንመጣ ያስገድደናልና የእርዳታው ቁሳቁስ መርዶ መሆኑን ደግማችሁ እወቁት!በእርግጥም የኢትዮጵያ ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንዳሰቡት ሊያልቅላችው አልቻለም!ያንን ለማጥናትና ክፍተቱን ደፍኖ ለመፈጸም ካልሆነ በምንም ምክንያት ወደዚህ ሁሉ ጋጋታ ሊገቡ አይችሉም!ይህ ካልሆነ በምንም ምክንያት የራሳችው አርሮ የእኛን ያላረረ ድስት ሊያማስሉ አይንጋጉም!ቁሳቁሱንም አያንጋጉም!የኢትዮጵያ ድስት ያላረረበትን ሚስጥር ለማወቅ ብቻ ነው::ድስቱ ላይ የማፍጠጥ ቅልውጥ ነው ወገኔ!
በአንድ ወቅት መንግስቱ ኅይለማርያም ወደ አሜሪካ ይሄድና እርዳታ ይጠይቃል:: የአሜሪካው መሪ የሰጡት መልስ "ይቅርታ ጉዋድ መንግስቱ በቬትናም ጉዳይ ስለተወጠርን ለጊዜው አፍሪካ ላይ ትኩረት ልናደርግ አንችልም"ብለው አሰናበቱት::መንጌ በዚያው አድርጎ ወደ ቻይና ሄደ::በዚያውም ወደ ሩሲያ.." ከአሜሪካ የተነፈገውን እርዳታ ከሶሻሊስት አገሮች አገኘ ርእዮቱንም ሶሻሊዝም አደረገ:: ምእራባውያን ብቻም ሳይሆኑ ማናቸውም ረጅ አገሮች በራሳቸው ጉዳይ በተወጠሩበት ሁኔታ ትኩረታቸውን አፍሪካ ላይ ሊያደርጉ አይችሉም::በአገራት ደረጃ ብቻም ሳይሆን በግለሰብ ወዳጅነትም ብንሄድ የየራሳችን ችግር ሳንፈታ የሌሎችን ችግር ወደመፍታት ልናልፍ አንችልም::ጭራሽ ደግሞ ተመሳሳይ ችግር!ጭራሽ ደግሞ የእኛ ችግር የባሰ በሆነበት ሁኔታ!ይህ እብደት ነው ክቡራን!የሞት ዜናቸውን ተናግረው ያልጨረሱ,ሬሳቸውን አንስተው, ቆጥረው,ቀብረው,ያልጨረሱ አገራት ናቸው!ስለ ራሳቸው ኮሮና መልስ ያላገኙ መፍትሄ ያላበጁ ለዜጎቻቸው ግላቭና ሳኒታይዘር አድለው አዳርሰው ያልጨረሱ ናቸው!በዚህ ፋታ ቢስ በሆነ ሁኔታ ስለ እኛ ትንሽየ ኮረና መጨነቅ እንዴት እንዳሰብነው ሳይሆን ቀረ?
ለምን አልሞቱም?ብሎ ምክንያቱን የማወቅና የስርጭት ፍጥነቱን የማሻሻል ስራውን ለማሳለጥ ካልሆነ የሃዘን እርዳታ ሊሆን አይችልም::ስለዚህ መልካም ዜና ከወደ እንግሊዝ እያላችሁ ዜና የምታቀርቡ ወገኖች "በቅርቡ የሞትና የልክፍት ቁጥራችን ጨምሮ ከሃያላኑ ተርታ እንድንሰለፍ የሚያደርጉ ቁሳቁሶች በገፍ እየገቡልን ነውና ደስ ይበላችሁ..." እያላችሁ እንደሆነ ተገንዝባችሁት ተጠንቀቁ፡፡
"ባዶ ነን ምንም ነገር የሌለን!"
💚💛
👉 ለጋሾች (ረጂዎች) ቢያኮርፉን ለኹለት ወራት የሚያቆይ ኢኮኖሚ የለንም። በርሀብ እናልቃለን። በጀታችንን በብድር ላይ የተመሠረተ አድርገነዋል። እንደሀገርም እንደሕዝብም መሥዋዕትነት ከፍለንም ቢሆን ራሳችንን ለመቻል ሐሳቡም ፍላጎቱም የለንም።
👉 አገራት ነዳጅ ለእናንተ አንሸጥም ቢሉን ከሳምንት በኋላ የትም መሄድ አንችልም። እስክንሞት ድረስ ባለንበት ቦታ ተወስነን እንኖር ዘንድ እንገደዳለን። (በአህያ መንቀሳቀስ ካልጀመርን)። ነዳጅ በከርሰ ምድር ውስጥ ሞልቶናል ፥ እናወጣው ዘንድ ግን ዐቅምም መሻትም የለንም።
👉 ልብስ (ጨርቃጨርቅ) ወደ አገራችን ማስገባት ቢከለከል ከሦስት ወራት በኋላ የለበስናቸውን ጨርሰን እርቃናችንን እንሄዳለን። ለስንት ሺህ ዓመታት የቆየውን ጥበባችንን ጥለን፣ ሽመናችንን ጥለን በዘመናዊ ቀይረነዋል።
👉 የእህል ማዳበሪያ ወደ አገራችን እንዳይገባ ቢታገድ ከዓመት በኋላ የምርት እጥረት አጋጥሞን በርሃብ እናልቃለን። መሬታችንን በእነርሱ ኬሚካል በክለን በየዓመቱ ለችርቻሮ በሚያቀርቡልን ማዳበሪያ ላይ ጥገኛ አድርገነዋል።
👉 አገራት 'ሳትላይታችንን' አናከራይም ቢሉን ስለምንም ነገር መረጃ የሌለን በሚዳሰስ ጨለማ ውስጥ የምንኖር ደናቁርት ምስኪኖች ነን። ራዲዮ ቴሌቪዥን ቴሌኮሙኒኬሽን ወዘተ አይኖረንም።
👉 ምርጥ ዘር አንሰጥም ቢሉን መሬታችን ጾሙን ያድራል። በርሃብ አለንጋ ክፉኛ እንገረፋለን። የእኛን የእህልና የእንስሳት ዘሮች አጥፍተን በእነርሱ ተክተናቸዋልና።
👉 የውጪ ፊልሞችንና መጽሐፍትን እንዳናገኝ ብንከለከል ምንም ዓይነት ድርሰት መጻፍ አንችልም። ኹሉ ነገራችን ከእነርሱ የተኮረጀ ነው። (ከተወሰኑት በቀር)
👉 እስኪ የራሳችን ከራሳችን በራሳችን የሆነ ምን አለን? ሦስቱንም የሚያሟላ ምን አለን?
👉 መንግሥታችን በእነርሱ ተመርጦ የተሾመብን እንጂ እኛ መርጠን የሾምነው አይደለም።
👉 ፖሊሲዎቻችን የእነርሱ፣ ሕጎቻችን የእነርሱ፣ ደንቦቻችን የእነርሱ፣ ዐዋጆቻችን የእነርሱ፣ ኹሉም ከእነርሱ የተኮረጁ እንጂ የእኛን የአኗኗርና ሃይማኖታዊ ሥርዓት መሠረት አድርገው የተዘጋጁ አይደሉም።
👉 መንግሥታዊና ሃይማኖታዊ የሹመት መጠሪያዎቻችን ሳይቀሩ የተኮረጁ ናቸው። ለምሳሌ፦ በመከላከያ ዘርፍ ጄኔራል፣ ኮሎኔል፣ ሌትና ኮሎኔል፣ ሜጄር ጀኔራል፣ ካፕቴን ማርሻል ወዘተ
በሲቪል ዘርፍ ሚንስቴር፣ ፕሬዚደንት፣ ኢንጂነር፣ ዶክተር፣ አርቲስት፣ ኮሜዲያን፣ አትሌት ወዘተ
በሃይማኖት ዘርፍ ፓትርያርክ ጳጳስ ካቴድራል ሼህ ወዘተ ኹሉም መጤዎች ናቸው።
👉 አረቄያችንን ማዘመን ሲገባን የእኛን ትተን የእነርሱን ቮድካ ብላክ ሌቭል እንጋታለን። ጠላችንን ማሳደግ ሲገባን የእነርሱን ቢራ እያመረትን እንጋታለን። ኬኔቷችንን ማሳወቅ ሲገባን የእነርሱን ቀመሩን የማናውቀውን ለስላሳ መጠጥ እንጠጣለን። 👉 የእኛን መስጠት ሲገባን የራሳችንን እየጣልን የእነርሱን እንቀበላለን።
👉 የምንማረው የእነርሱን ፍልስፍና፣ የእነርሱን ፍላጎት፣ የእነርሱን ሳይንስ ወዘተ ብቻ
👉 የምንማረው በእነርሱ ቋንቋ፣ ተምረን ስንጨርስ የምንቀበለው ማዕረግ የእነርሱ (ዲግሪው፣ ማሰሰተርሱ፣ ፒኤች ዲው፣ ፕሮፌሰርነቱ ኹሉ የእነርሱ...)፣ የመመረቂያ ጋውናችን ሳይቀር የእነርሱ፣ 'ለፕሮቶኮል' የምንለብሰው ልብሳችን የእነርሱ፣
👉 ውኃ ከH2 እና ከኦክሲጅን የተገኘ እንደሆነ እንጂ አምርተን አይተነው አናውቅም።
👉 መኪናዎቻችን ባቡሮቻችን አውሮፕላኖቻችን ጋሪዎቻችን ብስክሌቶቻችን ሳይቀሩ ከእነርሱ ተመርተው የሚመጡ ናቸው።
👉 መንገዶቻችን የእነርሱ፣ ግድቦቻችን የእነርሱ (ከዓባይ በቀር)፣ ፋብሪካዎቻችን የእነርሱ
👉 ፍልስፍናችን (የሕይወታችን መርሕ) የእነርሱን መከተልና፣ በሄዱበት መሄድ፣ የእነርሱን መቀበል እንጂ የእኛን ማሳደግና በራሳችን መንገድ መሄድ አይደለም። ማርያም አታማልድም ሲሉን እኛም አታማልድም እንላለን። ታማልዳለች ሲሉንም ታማልዳለች እንላለን። ፈጣሪ የለም ሲሉን የለም እንላለን። ለኹሉ ነገራችን ማረጋገጫችን እነርሱ ናቸው።
👉 እስኪ እናስተውል! የለበስነው ልብስ፣ በእጃችን ያሠርነው ሰዓት፣ የተጫማነው ጫማ፣ የማን ነው? የውስጥ ሱሪያችን ሳይቀር የእነርሱ ነው። ቁሳቁሱን እንተወውና ሐሳባችንስ የማን ነው? የእነርሱ አይደለምን? የራሳችን የሆነ ሐሳብ እንኳን የለንም። እስኪ ፖለቲከኞችንና አርቲስቶቻችንን ተመልከቱ! ኹሉ ነገራቸው የተኮረጀ ነው። የታለ አዲስ ፍልስፍና? የታለ ኢትዮጵያዊ እሳቤ?
👉 ብሔርተኝነታችን የእነርሱ፣ አንድነታችን የእነርሱ፣ ትርክታችን የእነርሱ፣ ታሪካችን የእነርሱ
👉 ዓላማችን የእነርሱ፣ ዕቅዳችን የእነርሱ፣ ሕልማችን የእነርሱ፣ ራእያችን የእነርሱ
👉 መድኃኒታችን የእነርሱ፣ በሽታችን እነርሱ
👉 አይ እኛ! !!!!!
👉 እኛ ኢትዮጵያዊያን ኹሉም ነገር አለን፣ ነገርግን ባዶ ነን ምንም ነገር የሌለን!
👉 ሃይማኖት አለን ፥ እምነት ግን የለንም!
👉 ቋንቋ አለን ፥ መግባቢያ ግን የለንም!
👉 ራስ አለን ፥ ጭንቅላት ግን የለንም!
👉 ስሜት አለን ፥ ስሌት ግን የለንም!
👉 የተፈጥሮ ጸጋ አለን ፥ ትጋትና ብልሃት ግን የለንም!
👉 ጥበብ አለን ፥ ማስተዋል ግን የለንም!
👉 ኹሉ ነገር አለን ፥ ነገርግን ባዶ ነን ምንም ነገር የሌለን!
👉 ግን እስከመቼ?????????????????????
👉 ይኸንን ጽሑፍ አንብቦ ራሱን ከሚመረምረው ይልቅ አፉን ለስድብ ከፍቶ ባዶ ጭንቅላቱን ያለሀፍረት የሚያሳየኝ ይበዛል!
👉 የእኔን ስሜት (ምን ለማለት እንደፈለግሁ) ከሚረዳኝ ይልቅ የራሱን ስሜት መረዳት የሚፈልገው ብዙ ነው።
👉 ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ "እግዚአብሔር ሆይ፦ ወይ ሕዝብህን አንቃው ፥ ወይ እኔን ግደለኝ!" ብሎ የጸለየው ወዶ አልነበረም ለካ!
👉 እነርሱና እኛ በጣም እንለያያለን። የሕይወታችን መመሪያም ተቃራኒ ነው። እነርሱ ነገሮችን በማረጋገጥ ይጀምሩና ካረጋገጡት በኋላ እናምናለን። እኛ ግን በማመን እንጀምርና እናረጋግጣለን። እነርሱ የራሳቸውን በእኛ ላይ መጫን ይፈልጋሉ ፤ እኛ ግን የራሳችንን ጥለን የእነርሱን እንቀበላለን። ዘርዝሬ ላልጨርሰው ቢበቃኝ ነው የሚሻለኝ።
👉 እግዚአብሔር ሆይ እባክህን ሕዝብህን አንቃው!
(ይኸንን ማንም ሰው ሼር እንደማያደርገው አውቃለሁ። ምክንያቱም የእያንዳንዱን ገመና የሚገልጥ እውነት ስለሆነ)
👉 ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
መናፍቃንና መጽሐፍ ቅዱስ ሆድና ጀርባ

መሆናቸውን የሚያሳዩ 60 ነጥቦች

1. መናፍቃን፡- የጻድቃን መታሰቢያ በዓል መከበር የለበትም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- መዝ.112፡6 ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል፡፡›› …. መጽ.ምሳ.10፡7 ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው››

2. መናፍቃን፡- ቅዱሳን አማላጅና አስታራቂ አይደሉም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 2ኛ ቆሮ.5፡20 ‹‹እግዚአብሔር ...በእኛ እንደሚማለድ… ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን፡፡›› …. 2ኛ ቆሮ.5፡18-19 ‹‹በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ፡፡››

3. መናፍቃን፡- ኢየሱስ ዛሬም አማላጅ ነው፡፡

v መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዮሐ.16፥26 ‹‹በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም›› …… 2ኛ ቆሮ.5፡15 ‹‹ክርስቶስንም በሥጋ እንደሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፣ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም፡፡›› … ሮሜ 14፡10 ‹‹ሁላችን …በክርስቶስ ፍርድ… ወንበር ፊት እንቆማለን››

4. መናፍቃን፡- ሥራ አያጸድቅም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ያዕ.2፡17 ‹‹ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡›› …… ያዕ.2፡21 ‹‹አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ ...በሥራ... የጸደቀ አልነበረምን?››

5. መናፍቃን፡- ጾም አያስፈልግም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ት.ኢዮ.1፡14 ‹‹ጾምን ቀድሱ፣ ጉባኤውንም አውጁ››

6. መናፍቃን፡- መጽሐፍ ቅዱስ 66ቱ ብቻ ነው፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 2ኛ.ጢሞ.3፡16-17 ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት … መጽሐፍ ሁሉ … ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ …ይጠቅማል፡፡… ››

7. መናፍቃን፡- ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ አትባልም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ኢሳ.9፥6 ‹‹ሕፃን ….ተወልዶልናልና…፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል ….አምላክ…፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።››

8. መናፍቃን፡- ሐይማኖት አያስፈልግም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ኤፌ.4፡5 ‹‹አንድ ሃይማኖት›› ... ይሁ.1፡3 ‹‹ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ፡፡›› …. 2ኛ.ጢሞ.4፡7 ‹‹ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ››

9. መናፍቃን፡- ጥምቀት ለድህነት አይጠቅምም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዮሐ.3፡5 ‹‹ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡››

10.መናፍቃን፡- የጌታ ስጋና ደም (ቁርባን) ምሳሌ ብቻ ነው፡፡

ü መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዮሐ.6፡55 ‹‹ሥጋዬ …እውነተኛ… መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፡፡››

11. መናፍቃን፡- ታቦት በአዲስ ኪዳን ተሽሯል፡፡

Ø መጽሐፍ ቅዱስ፡- የዮሐ.ራዕ.11፡19 ‹‹በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፣ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ››

12. መናፍቃን፡- ቤተ መቅደስ በአዲስ ኪዳን አያስፈልግም፡፡

Ø መጽሐፍ ቅዱስ፡- 2ኛ.ዜና.መዋ.7፡16 ‹‹አሁንም ስሜ ….ለዘላለም…. በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ፡፡›› …. ማቴ.21፡13 ‹‹ቤቴ የፀሎት ቤት ትባላለች፡፡››

13. መናፍቃን፡- መስቀል መያዝ/መጠቀም አይገባም፡፡

ü መጽሐፍ ቅዱስ፡- ገላ.6፡14 ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ፡፡›› … 1ኛ.ቆሮ.1፡17 ‹‹የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን››

14. መናፍቃን፡- ማህተብ በአንገት ማሰር አያስፈልግም፡፡

* መጽሐፍ ቅዱስ፡- ምሳ.6፡21 ‹‹በአንገትህም እሰረው፡፡››

15. መናፍቃን፡- ሕፃናት መጠመቅ የለባቸውም፡፡

· መጽሐፍ ቅዱስ፡- ማቴ.19፡14 ‹‹ሕፃናትን ተውአቸው፣ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ …አትከልክሉአቸው…፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ›› … የሐዋ.ሥራ.16፡33 ‹‹እርሱ ከቤተ ሰዎቹ …ሁሉ… ጋር ተጠመቀ››

16. መናፍቃን፡- ለሞተ ሰው መጸለይ አይገባም፡፡

· መጽሐፍ ቅዱስ፡- መጽ.ነገ.ካልዕ.4፡33-36 ….. ሰቆ.ኤር.3፡22 …. ዮሐ.14፡14 ‹‹ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ፡፡››

17. መናፍቃን፡- በቅዱሳን ስም መዘከር/ምጽዋት መስጠት አያስፈልግም፡፡

vመጽሐፍ ቅዱስ፡- ‹‹ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል፡፡ ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ዋጋው አይጠፋበትም፡፡›› ማቴ 10:40-42

18. መናፍቃን፡- በቅዱሳን ስም ቤተ ክርስቲያንን መሰየም ትክክል አይደለም፡፡

vመጽሐፍ ቅዱስ፡- ትን.ኢሳ.56፡5 ‹‹በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ፡፡››

19. መናፍቃን፡- ቅዱሳት ስዕላት አያስፈልጉም፡፡

ü መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዘጸ.25፡18 ‹‹ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ››

20. መናፍቃን፡- ቅዱሳን መላእክት አማላጅ አይደሉም፡፡

· መጽሐፍ ቅዱስ፡- ት.ዳን.12:1 “ …ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው… ታላቁ አለቃ ሚካኤል” …. ት.ዘካ.1፡12-17 ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፣ አቤቱ፣ የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ፡፡›› ….. ዕብ.1፡14 ‹‹ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?››

21. መናፍቃን፡- የጌታ እናት አልተነሣችም፡፡

v መጽሐፍ ቅዱስ፡- መዝ.131/132፡8 ‹‹አቤቱ፣ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፣ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› ….. መዝ.44/45፡9 ‹‹በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች፡፡››

22. መናፍቃን፡- የጌታ እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት /ጥንተ አብሶ/ አለባት፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ትን.ኢሣ 1፡9 ‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር …ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ…፣ እንደ ሰዶም በሆን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር፡፡›› … መዝ.45/46፡4 ‹‹…ልዑል… ማደሪያውን ቀደሰ፡፡››

23. መናፍቃን፡- ኃጢአትን ለካህን መናገር/መናዘዝ አይገባም፡፡

vመጽሐፍ ቅዱስ፡- ማቴ.8፡4 ‹‹ሔደህ ራስህን ለካህን አሳይ›› …. ዮሐ.20፡23 ‹‹ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፣ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል›› …. ኢያሱ.7፡19

24. መናፍቃን፡- ስግደት አያስፈልግም፡፡

vመጽሐፍ ቅዱስ፡- መዝ.29፡2 ‹‹በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ፡፡››

25. መናፍቃን፡- ሴት መድረክ ላይ በህዝብ መካከል ወጥታ ሰባኪ መሆን ይፈቀድላታል፡፡

* መጽሐፍ ቅዱስ፡- 1ኛ.ጢሞ.2፡12 ‹‹ሴት ግን … ልታስተምር ….. አልፈቅድም፡፡›› …. 1ኛ ቆሮ.14፡35 ‹‹ለሴቶች በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነው››

26. መናፍቃን፡- ሴት ፀጉሯን ሳትሸፍን መጸለይ ትችላለች፡፡

* መጽሐፍ ቅዱስ፡- 1ኛ ቆሮ.11፡5 ‹‹ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች››

27. መናፍቃን፡- ሴት የወንድን ልብስ ብትለብስ አትከለከልም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ኦ.ዘዳ.22፡5 ‹‹ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፣ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤
ይህን የሚያደ
ርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና፡፡››

26. መናፍቃን፡ ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ነጭ ልብስ መልበስ አያስፈልግም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- የዮሐ.ራዕ.3፡4 ‹‹የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ፡፡››

27. መናፍቃን፡- ልሳን ማለት ለሰዎች የማይሰማና የማይረዱት ነገር ነው፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- የሐዋ.ሥራ.2፡8 ‹‹እኛም እያንዳንዳችን ….የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን… እንዴት እንሰማለን?››

28. መናፍቃን፡- ገዳም መግባት ስህተት ነው፡፡

vመጽሐፍ ቅዱስ፡- ማቴ.5፡10 ‹‹ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው፤ መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡›› …. ማቴ.19፡29

29. መናፍቃን፡- ቅዱሳን በስጋ ከሞቱ በኋላ ከንቱ ናቸው፤ ምንም አያደርጉም፡፡

· መጽሐፍ ቅዱስ፡- መዝ.116፡15 ‹‹የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው፡፡›› ….. 2ኛ.ነገ.13፡20-21 ‹‹ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ፡፡›› … ማቴ.22፡31-32

30. መናፍቃን፡- ለቅዱሳን አይሰገድም፡፡

ü መጽሐፍ ቅዱስ፡- ኦ.ዘፍ.27፡29 ‹‹ሕዝብም ይስገዱልህ›› … የዮሐ.ራዕ.3፡8-9 ‹‹በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ፡፡›› …. ት.ዳን.2፡46 ‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር በግንባሩ ተደፍቶ ለዳንኤል ሰገደለት፡፡››

31. መናፍቃን፡- አይንን ጨፍኖ መጸለይ የጸሎት ስርዓት ነው፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- መጽ.ምሳ.16፡30 ‹‹ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ ሀሳብን ያስባል›› ….. መዝ.122/123፡1

32. መናፍቃን፡- መዝሙርን በዓለማዊ የሙዚቃ መሣሪያ፣ የሙዘቃ ዳንስና የሙዚቃ ዜማ ተጠቅሞ መዘመር ይቻላል፡፡

· መጽሐፍ ቅዱስ፡- መዝ.149፡3 ‹‹በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት፡፡›› …. መዝ.33፡2 ‹‹እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፣ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት፡፡››

33. መናፍቃን፡- ትውፊትን አንቀበልም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 2ኛ.ተሰ.2፡15 ‹‹…በቃላችንም… ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ፡፡››

34. መናፍቃን፡- ለታቦት መስገድ አይገባም፡፡

vመጽሐፍ ቅዱስ፡- ኢያ.7፡6 ‹‹በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ››

35. መናፍቃን፡- የጌታ እናት ዘላለማዊ ድንግል አይደለችም፡፡

* መጽሐፍ ቅዱስ፡- ት.ሕዝ.44፡1-2 ‹‹ወደ ምሥራቅም ወደ ሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር፡፡ እግዚአብሔርም፣ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፣ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፡፡››

36. መናፍቃን፡- የጌታ እናት አማላጅ አይደለችም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዮሐ.2፡3 ‹‹የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ ..የኢየሱስ እናት..፣ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለቸው፡፡›› …. መዝ.44/45፡9 ‹‹በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ..ትቆማለች..፡፡››

37. መናፍቃን፡- የጌታ እናት እናታችን አይደለችም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዮሐ.19፡26 ‹‹እነሆ ልጅሽ አላት፡፡›› …. ዮሐ.19፡27 ‹‹እናትህ እነኋት አለው፡፡››

38. መናፍቃን፡- የጌታ እናት ክብር እንደ እኛ እኩል ነው፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ሉቃ.1፡28 ‹‹መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፣ ደስ ይበልሽ፣ ….ጸጋ የሞላብሽ ሆይ…..፣ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፣ አንቺ ከሴቶች መካከል …..የተባረክሽ ነሽ…… አላት፡፡››

39. መናፍቃን፡- መጽሐፍ ቅዱስን ማንም እንደገባው መተርጎም ይችላል፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 2ኛ.ጴጥ.1፡20 ‹‹በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም››

40. መናፍቃን፡- ጌታ የግል አዳኝ ነው፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዮሐ.4፡42 ‹‹እርሱም በእውነት ክርስቶስ …የዓለም መድኃኒት…. እንደሆነ እናውቃለን››

41. መናፍቃን፡- እኛ አሁን ጸድቀናል፤ ከእኛ የሚጠበቅ ነገር የለም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ገላ.5፡5 ‹‹እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ …እንጠባበቃለን…›› ….. 2ኛ.ጢሞ.4፡8 ‹‹--ወደ ፊት-- የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል››

42. መናፍቃን፡- እኛ ቅዱስ ነን፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ምሳ.30፡12 ‹‹ለራሱ ንጹሕ የሆነ የሚመስለው ከርኩሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ፡፡››

43. መናፍቃን፡- ፀበል መጠመቅ አያስፈልግም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዮሐ.9፡6-7 ‹‹ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ …. ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ፡፡››

44. መናፍቃን፡- እምነት መቀባት አይገባም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ኦ.ዘጸ.30፡29 ‹‹ሁሉንም ትቀድሳቸዋለህ፣ ቅድስተ ቅዱሳንም ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል፡፡›› …. 2ኛ.ነገ.5፡17 ‹‹ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር እንድወስድ እሺ ትለኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡››

45. መናፍቃን፡- ብሉይ ኪዳን በጌታ ተሽሯል፡፡

o መጽሐፍ ቅዱስ፡- ማቴ.5፡17 ‹‹እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም፡፡››

46. መናፍቃን፡- የዘላለም ህይወት የሚገኘው በእምነት ብቻ ነው፡፡

o መጽሐፍ ቅዱስ፡- ያዕ.2፡24 ‹‹ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ፡፡›› …. ዮሐ.6፡54 ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም የዘላለም ሕይወት አለው››

47. መናፍቃን፡- ለመዳን መከራ መቀበል አይገባም፡፡

vመጽሐፍ ቅዱስ፡- የሐዋ.ሥራ.14፡21-22 ‹‹ወደ እግዚአብሔር መንግሥት …በብዙ መከራ… እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል››

48. መናፍቃን፡- የክርስትና ስም ማውጣት/መሰየም አያስፈልግም፡፡

ü መጽሐፍ ቅዱስ፡-የሐዋ.ሥራ.13፡9 ‹‹ጳውሎስ የተባለው ሳውል›› …… ማቴ.16፡16-17 ኬፋ/ስምዖን የተባለው ጴጥሮስ ….. ኦ.ዘፍ.17፡5 ‹‹ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፣ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል››

49. መናፍቃን፡- የቅዱሳንን ገድልና ድርሳን አንቀበልም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 1ኛ.ጢሞ.6፡12 ‹‹መልካሙን የእምነት …ገድል ተጋደል… ›› ….. መዝ.101/102፡18 ‹‹ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ››

50. መናፍቃን፡- ሰው ሲኦል ከገባ በኋላ ሊወጣ አይችልም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 1ኛ.ሳሙ.2፡6 ‹‹እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፣ …ያወጣል፡፡….››

51. መናፍቃን፡- ሰይጣን በካራቴ ይወጣል፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ማር.9:29 ‹‹በጸሎትና በፆም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም፡፡››

52. መናፍቃን፡- ከኢየሱስ ጋር በስልክ አወራን፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 1ኛ.ጢሞ.4፡7 ‹‹ነገር ግን … ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ፡፡››

53. መናፍቃን፡- ወይንን ፈጽሞ መጠጣት አይፈቀድም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- 1ኛ.ጢሞ.5፡23 ‹‹ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፣ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ፡፡››

54. መናፍቃን፡- በቤተ መቅደስ ዕጣን ማጤስ አያስፈልግም፡፡

† መጽሐፍ ቅዱስ፡- ዘጸ.30፡7 ‹‹እጣን ይጠንበት›› … ዘጸ.40፡27 ‹‹የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ዐጠነበት፡፡›› … የዮሐ.ራዕ.8፡3-4 ‹‹ዕጣን ተሰጠው፡፡ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ፡፡››

55. መናፍቃን፡- ቤተ መቅደስን መሳለም /ሰላም ለኪ ማለት/ አያስፈልግም፡፡

· መጽሐፍ ቅዱስ፡- የሐዋ.ሥራ 18፡22 "ወደ