ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
800 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
👆👆👆👆85 % ሕዝቧ ማንበብና መጻፍ በማይችልባት አገር ኢትዮጵያ 666 የአውሬው ቁጥር በምክር ቤት ጸድቋል?

"የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ዅሉ ሊያስገድላቸው፣ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው። ታናናሾችና ታላላቆችም፣ ባለ ጠጋዎችና ድሆችም፣ ጌታዎችና ባሪያዎችም ዅሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፤ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፡፡ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው፤" (ራእ. ፲፫፥፲፮-፲፰)፡፡

ይህ የቅዱስ ዮሐንስ ራእይ ከሚመሠጠርበት ትርጕም ውስጥ አንዲት ቅንጣት ብቻ ከዘመኑ አንጻር ብናይ "የሚናገር የአውሬው ምስል" ማለት ለእርሱ ያልተገዙትን ወይም ቁጥሩን ያልያዙትን የሚናገርባቸው፤ "ምልክቱን ያልተቀበሉትን ሊገዙና ሊሸጡ እንዳይችሉ ያደርግል" ማለት መኖር፣ መሥራት፣ መሸጥ፣ መለወጥ ወዘተ የሚያግዳቸው ሲል ነው፡፡ ይህም አሁን ባለው የዚህ ዓለም አኗኗር አንጻር ሲታይ ተመሳሳይ ጉዳዮች አሉ፡፡ ለምሳሌ መታወቂያ ወረቀት፣ ፓስፖርት፣ ቪዛ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ወዘተ በዓለም አጠቃላይ አሠራር እና ባንድ ሰው የመኖር ማንነት ሚና ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ መታወቂያ ወረቀቶች የሌሉት ሰው ካለበት የትም መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ ከዚህም በላይ ጉዳዩን ስናሰፋው በሠለጠኑት ዓለማት አሠራር የእያንዳንዱ ሰው የጣት አሻራ በዘመናዊ (ኮምፒውተራይዝድ) መንገድ የተደራጀ በመኾኑ፣ ከዚህ አደረጃጀት ውስጥ ካልተካተተ በቀር ማንም ሰው በዚያች አገር ሊኖር፣ ሊዘዋወር፣ ሊሠራ፣ ሊነግድ ወዘተ. አይችልም፡፡ በዚህ የኮምፒውተር ድር አደረጃጀት ውስጥ ያለ አንድ ሰው ወደ የትኛውም ዓለም ቢንቀሳቀስ በጣቱ አሻራ ይታወቃል፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ በትንቢቱ፡- "አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፤ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው፤" የሚለውም ይህን ጉዳይ የሚያደራጀው ሌላ አካል ሳይኾን የሰው ልጅ መኾኑን የሚያመለክት ነው። ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት" የሚለው ቍጥር የሰው ልጅ የጅማት ቁጥር ነውና፡፡

አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ መታወቂያ ዲጂታል ሊሆን ነው። የመገበያያ ሥርዓቱም ዲጂታል ሊሆን ነው። ይኸውም በምክር ቤት ጸድቋል። በዲጂታል የመታወቂያና የመገበያያ ሥርዓት የወረቀት መታወቂያና የወረቀት ገንዘብ ይወገድና በአሻራችንና በእጆቻችን በሚቀበርሉን ኮዶች በቤታችንና ሆነን መገበያየት እንችላለን። ከዚህ ሲስተም ውጪ ያለ ሰው "የለውጥ አደናቃፊ፣ የድሮ ሥርዓት ናፋቂ፣ ያልገባው፣ ኋላ ቀር ወዘተ" እየተባለ እንዳይኖርና እንዳይገበያይ ይደረጋል። ሐቁ ይህ ነው። ከዘረኝነትና ከፖለቲካ ጥገኝነት ወጥታችሁ የቅዱሳት መጽሐፍትን ድምጽ ካልሰማችሁ የዘመኑ ርኩሰት ሰለባ ከመሆን አትድኑም።

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አድርሱ አሳውቁ!

ተወዳጆች ሆይ ነገ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸውና ለጊዜው የምንታቀባቸው ጸሎቶች አሉ።

በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው።

ወለላይቱ እመቤት በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን።

የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን።

ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን።

ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን።

ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርያም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወስዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪ አርጋኖንና ጸሎተ ባርቶስን ልዩ ፈተና ያለብንና እመቤታችንን የምንወድ መጸለይ አንከለከልም። ዋናው ትኩረታችን የጌታ መከራ ስቅለት እና ሞት ላይ ማድረጉን ሳንረሳ።

በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው።

በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እንዲህ ያስጨነቀን መግቢያ መውጫ የከለከለን ቤተ-ክርስትያናችንን ያዘጋብን ወረርሽን ከእነሱ ለእኛ የተረፈን ነው። ስለዚህ እነሱ ሲለበለቡ እኛ መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው።

#ኢትዝክር_ለነ_አበሳነ_ዘትካት

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
​​#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ_ሥርዓቶች

1, #ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, #ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, #ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, #አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. #አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, #ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, #ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, #ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።
#ሰሙነ_ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽሐፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

#አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና

ይቆየን.......

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
ብሞትም እንኳ ይቅር አልለዉም

ወዳጄ ሆይ እስቲ ለአንድ አፍታ ቆም ብለህ አስታዉስ
በምንም ምክንያት ልብህ ይቅር ሊለዉ ያልቻለ
እጅግ ያስቀየመህ አንድ ሰዉ የለም ይሆን?ገና
ስታስበዉ የሚያንገሸግሽህ ፡ ሥሙ ሲነሳብህ
የሚያንቀጠቅጥህ፡ ሠዉ የለምን? ምንአልባት
ያደረሰብህ በደሎችን ዘርዝረህ አትጨርሳቸዉም
ይሆናል፡ ዳግመኛ አይኑን ላለማየትም ከበቂ በላይ
ምክንያት ይኖርህ ይሆናል፡ እንግዲህ "#ይቅር"
በለዉና ዉደደዉ ስለ እርሱም ፀልይ የተባልኸዉ
ይሄንን ሰዉ ነዉ።

ምንአልባት ከበደሉ መደጋገም የተነሳ ሥንት ጊዜ
ይቅር ልበለዉ ? ይቅርታ ሳደርግለት እየባሰበት
እየናቀኝ አይደለምን? ትል ይሆናል ። ይህ የጴጥሮስም ጥያቄ ነበር። ወንድሜ ቢበድለኝ
ስንት ጊዜ ልተዉለት? ሰባት ጊዜ ነዉን? ብሎ
ጌታችንን ሲጠይቅ ፡ ሰባ ጊዜ ሰባት ብሎ መልሶለት
ነበር። 490 ጊዜ ብቻ ይቅር በለዉ ማለቱ ሳይሆን
ፍፁም ቢበድልህ ፍፁም ይቅር በለዉ ሲል ነዉ።።።
ይኼ ከበዛብህ ወንድምህን ፈጣሪ ይቅር እንዲልህ
በምትፈልገዉ መጠን ብቻ ይቅር በለዉ።" ብሞት
እንኳ ይቅር አልለዉም" የምትል ከሆነ ግን በሞቱ
ይቅር ስላለህ አምላክ ሕማምና መከራ የሚናገረዉ
ይህን ን መፅሐፍ ምን ሊጠቅመኝ ብለህ ታነበዋለህ?

የበደለህ ሰዉ ምንም ቢበድልህ እንደ አይሁድ
በመስቀል ላይ ቸንክሮ አልሰቀለህም፡ እረ ቸንክሮ
ከመስቀልም አይተናነስም የምትል ከሆነ ደግሞ
ጠላትህ እንደ አይሁድ ቢከፋብህ፡ አንተ ግን እንደ
ክርሥቶሥ ንፁኽ አይደለህም። ንፁሑ ክርስቶሥ
ገና የእሾህ አክሊል ከራሱ ላይ ሳይወርድ ፡ የችንካሩ
ሚሥማር ከእጆቹ ዉስጥ ሳይነቀል፡ አባት ሆይ
የሚያደርጉትን አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ እያለ
ሲጮህ አይታይህምን?

ይቅርታ ማድረግ ተሸናፊነት አይደለም፡ አሸናፊዉ
እግዚአብሔር በመስቀል ላይ ሆኖ ይቅርታን ያደረገዉ
ኃይል አጥቶ አልነበረም።

ይቅር እንድንባል ይቅር እንባባል
#ሕማማት
(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
"አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"
📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


               ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ትምህርቱ ለሌሎችም ይጠቅማልና ሼር ያድርጉ!

      
ኦርቶዶክሳዊ የምህላ ጸሎት የሚተላለፍባቸው የቴሌቪዥን ቻናሎች. ከዚህ በታች ባለው ፕሮግራም ነው ይቺን ሳምንት ሁላችን በህማማቱ እንታመም ዘንድ እናሳስባለን

ዘወትር ከምሽቱ
3:00-4:00
____
◈ሰኞ➾ኢቴቪ
◈ማክሰኞ➾ፋና ቴቪ
◈ረቡዕ ➾አዲስ ቴቪ
◈ሐሙስ ➾ዋልታ
◈አርብ ➾ኢቴቪ
◈ቅዳሜ ➾ፋና
◈እሁድ ➾አዲስ ቴቪ

አምላካችን ጸሎት ልመናችንን በእውነት ይቀበልልን

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

እግዚአብሔር በሰላም
ያለ ደዌና ያለሕማም
ያለጻእርና ያለድካም
ለብርሃነ ትንሣኤው ያድርሰን ያድርሳችኹ።"

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@finotmengiste
@finotmengiste @finotmengiste
አንተ ወሬኛ!
💚💛
ስለምን ትጮሃለህ? ስለምን ቤተክርስቲያን እንዳልሄድ ተከለከልኩ ትላለህ? ቤተክርስቲያን እንዳትሄድ ከተከለከልክ ቤትክን ቤተክርስቲያን አድርገው። ማን ያውቃል? ሲኖዶስ ይኸን የወሰነው በኃጢአት የቆሸሸውን ቤትህንና ኑሮህን ለማጽዳት ቢሆንስ? አሁን በአባቶች ላይ መጮህክን ተውና በራስህ ላይ ጩህ! እምነት ባይኖራቸው ነው ቤተክርስቲያንን የዘጓት ማለትህን ተውና እኔ እምነት ስለሌለኛና በሥራዬም ኃጢአተኛ ስለሆንኩ ነው ቤተክርስቲያን እንዳልሄድ የተከለከልኩት በል። በእነርሱ ምክንያት ተከለከልኩ ማለትህን ተውና በእኔ ምክንያት ይህ ሆነ በል።

መፍትሔው ማን ነው? ብለህ አትጠይቅ! መፍትሔው አንተ ራስህ ነህና! አዎ አንተ ራስህ! እኔ እንዴት መፍትሔ ልሆን እችላለሁ ካልክ በሚከተሉት ሦስት መንገዶች እልሃለሁ። የመጀመሪያው ማመን ነው። ከዚያ ንጽሕና። ሦስተኛ ሥራ። አልገባህም አይደል? አብራራልሃለሁ።

፩ኛ). እመን! እግዚአብሔር በአንተ ላይ ሥራውን እንደሚሠራ፣ እግዚአብሔር ጸሎትህን እንደሚሰማ፣ ቅዱሳን በምልጃቸው እንደሚረዱህ፣ ኮሮናም ሆነ ማንኛውም ችግር ከመስቀሉ ኃይል እንደማይበልጥ፣ አምላክህ እግዚአብሔር የሠለስቱ ደቂቅና የነዳንኤል አምላክ እንደሆነ የእነቅዱስ ጊዮርጊስም አምላክ እንደሆነ፣ ኃይልን በሚሰጥህ በክርስቶስ ሁሉን ማድረግና ማሸነፍም እንደምትችል (ፊል ፬÷፲፫) እመን። ዓለምን የምታሸንፈው በእምነትህ እንደሆነ (፩ኛ ዮሐ ፭÷፬)፣ ያለኢየሱስ ክርስቶስ ያለ እግዚአብሔር ምንም ማድረግ እንደማትችል (ዮሐ ፲፭÷፭) በእርሱ ግን ኹሉን ማድረግ እንደምትችል እመን።

፪ኛ). ንጹሕ ኹን፦ ከዚህ ቀደም በሐሳብ በቃልና በተግባር፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፣ በስሕተትም ሆነ በድፍረት የሠራኸውን ኃጢአት ፤ ነፍስህንና ሰውነትህንም ያቆሸሸውን ኃጢአት፣ ከእግዚአብሔር ጉያ ያራቀህን፣ ጸሎትህ ቅድመ እግዚአብሔር እንዳይቀርብ የሚያደርግብህን ኃጢአትህን ኹሉ አንድም ሳታስቀር በንስሐ አስወግደው። እግዚአብሔር ንጹሕ ነውና ንጹሕ አምሐ ይፈልጋል። ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደውን መሥዋዕት ለማቅረብ፣ እርሱ የሚቀበለውን ጸሎት ለመጸለይ፣ እንደአቤል መልካም መሥዋዕትን ለማቅረብ፣ በእርሱ እርዳታ ጠላትን ለማሸነፍ ልብን በንስሐ ማንጻት ያስፈልጋል።

፫ኛ). ሥራ፦ በንስሐ ከታጠብህና እምነትህንም ሙሉ ካደረግህ በኋላ ከአንተ የሚጠበቀውን ማድረግ ይገባሃል። ይኸውም በጊዜውና ያለጊዜውም ጸንቶ (፪ኛ ጢሞ ፬÷፪) እና ተግቶ መጸለይ (ማቴ ፳፮÷፵፩)፣ እንደ ጴጥሮስና እንደዳዊት በመረረ ለቅሶ (መዝ ፮÷፮) የእግዚአብሔርን ምሕረት መጠየቅ አለብህ። እንደአባቶችህ መጸለይ አለብህ።

እውነተኛ ክርስቲያን ከሆንክ ቤተክርስቲያን እንዳትዘጋ እንድትከፈትም ለማድረግ አንተ በቂ ነህ። አዎ! እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን አንተ እና እኔ በቂ ነን!ስለሆነው ኹሉ የእውነት ብንጸልይ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይሰማናል። ስለጽድቃችን ሳይሆን ስለቸርነቱ እግዚአብሔር ይሰማናል። የምንሻውንም ያደርግልናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ሰው የአገርንና የዓለምን ታሪክ ሲቀይር ዐይተናል። እኛም በፍጹም እምነትና ትሕትና በፈሪሃ እግዚአብሔር ሆነን እንደፈቃዱ ብንጸልይ እግዚአብሔር ቸር ነውና ይሰማናል። (ኃጢአተኞች ብንሆንም ንስሐ ገብተን ስለሀገራችንና ስለቤተክርስቲያናችን ብንጸልይ ብናለቅስ ቸር ነውና ይሰማናል።) ቤተክርስቲያን የምትፈልገው ፈተና በገጠማት ጊዜ በግብታዊነት ወይም በስሜት ሳይሆን በእምነት እግዚአብሔርን ይዘው የሚታገሉላት እንደዚህ ዓይነት ልጆችን ነው። ስለዚህ መደናገጥና መናደዱን ትተን በእግዚአብሔር ፍጹም እምነት ሊኖረንና ተግተንም ልንጸልይ ያስፈልጋል። አሁን ያሉት የቤተክርስቲያኑቱ ሰዎችና ምእመናን (ኹሉን ማለቴ አይደለም) "የደግ ቀን አርበኞች" ናቸው። ክፉ ቀን ሲመጣ ሊታገሉላትና ሊታደጓት የሚችሉ አይደሉም። ይኸንንም ዐይተነዋል። ስለዚህ ሲኖዶሱ ላይና አባቶች ላይ እንዲሁም ምእመናን ላይ ጣታችንን መቀሰራችንን አቁመን ከእያንዳንዳችን የሚጠበቀውን እናድርግ። "እነርሱ ምን አደረጉ?" የሚለውን ትተን "እኛ ምን አደረግን? እኔስ ምን አደረግሁ?" እንበል። ቤተክርስቲያንን የምንታደጋት አንተም እኔም እንደዚህ ስናደርግ ነው። ያንጊዜ እግዚአብሔር ሥራውን ይሠራል! እስኪ የመዳን ምስጢር የሚፈጸምበት ቀራንዮን እንሁንና ዓለም ኹሉ ይዳንብን! እስኪ ዓለም ኹሉ የሚድንበት የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚሠራብን ንጹሕ ሥፍራ እንሁን!!! እግዚአብሔር ከመዓቱ በምሕረቱ ይሠውረን! አሜን።

👉 ሼር ይደረግ!
© ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
💚 ለመቀላቀል @Zekidanemeheret
💛 ለአስተያይት @zetaodokos
ለመወያየት @finotmengiste ን ይጠቀሙ!
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👇መንግሥት በኮሮና እንዳይመርዘን እንጠንቀቅ!
#Share #Share #Share

መንግሥት በሰጠው መግለጫ መሠረት በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የሕክምና ባለሙያዎች ቤት ለቤት በመዞር የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በሚል የሰውነት ሙቀት የመለካት ምርመራ ሊያደርጉ ነው። በዚሁ መሠረት አሁን እያየናቸው ያሉት የምርመራ አሠራሮች ይበልጥ የኮሮና ወረርሽኝን ከአንዱ ወደ ሌላው የሚያስተላልፍ ነው። ይህ ስህተት ከተሠራ ልክ እንደ ኒዎርክ በሽታውን ለማስፋፋትና ሕዝቡን ለመጨረስ ቆርጠው የተነሡ ነው የሚመስለው።

ከላይ በምሥሉ እንደምትመለከቱት የሙቀት መለኪያውን የግለሰቦች ግንባር ላይ ደቅኖ ነው ሙቀት እየለካ ያለው። የሙቀት መለኪያው ግን በዚህ መልኩ አይደለም መሆን ያለበት። የሙቀት መለኪያው በሃያ ሳንቲ ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ ሙቀትን መለካት ስለሚችል በርቀት ነው መለካት ያለበት። ብዙ ሰዎችን በአንድ የሙቀት መለኪያ ግንባር ላይ በመደቀን የሙቀት መለካት ሥራ ከተሠራ ግን እጅ አደገኛ ነው። በሽታው ደግሞ ምልክት የማያሳይባቸው ሰዎችም አሉ። ስለዚህ መለኪያው በሽታን ከአንዱ ወደ አንዱ የሚተላለፍበት መንገድ ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው። በተጠቀሰው ርቀት ላይ ቆሞ ከመለካትም ባሻገር፤ ማንኛውም ሰው ከመለካቱ በፊት በተመርማሪው ሳኒታይዘር ወይም አልኮል መመርመሪያው በፊታችሁ እንዲጸዳ ማድረግን እንዳትዘነጉ!

ቫይረሱ በፈስ እንደሚተላለፍም ተነግሯል። እሱን በምን እንደሚመረምሩት ግን እንጃላቸው!

እግዚአብሔር ይጠብቀን፥ አሜን።

👉ለመቀላቀል👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

#ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

#አምንስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

Join
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ሰሙነ_ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽሐፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

#አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

#ማግሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

#የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

#ረቡዕ
#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በስምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባስጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

#የእንባ_ቀን_ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

#ሐሙስ
#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#ቅዳሜ
#ቀዳም_ስዑር_ትባላለች
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

#ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

#ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

(ስምዐ ጽድቅ መጋቢት ፳፻፪ ዓ.ም)

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
ክርስቶስ ሰውን ወዶ፦

እስከ ሞት ደረሰ።

ሰማዕታት ክርስቶስን ወደው ደማቸውን አፈሰሱ።

~እርሱ ደሙን አፍስሶ ሰውን ገንዘብ አደረገ። ሰማዕታት አካላቸውን ሰጥተው ክርስቶስን ገንዘብ አደረጉ።

~እኛ ክርስቶስን መውደዳችን እሰከ ምን አደረሰን? ስለክርስቶስ ብለን ያጣነው ነገር ከሌለን እርሱን መውደዳችን ወዴት አለ?
አባ ገብረ ኪዳን
🔥💥የደም ቃል💥🔥
💔💔💔💔💔💔💔
ክፍል አንድ

አቶ ተዘራ ወደ ቀደመው ሐሳባቸው ተመለሱ፣ ከወዲያ ወዲህ ይንጎራደዳሉ፣ ይቆማሉ፣ ይቀመጣሉ፣ የሚያደርጉት ጠፍቶባቸዋል።

ይህ ጉዳይ በቀላሉ የሚታለፍ አይመስለኝም። በስህተት ከአንደበቴ አንዲት ቃል ወጣች ማለት ቤተሰቤ ተበተነ ማለት ነው። እሱ ብቻ አይደለም ውርደቴን በአደባባይ መከናነቤ አይቀሬ ነው። ከዚያማ የሰው መጠቋቋሚያ ሆኜ "እዩት ተዘራ ሌላው እዬት ይኼን አጭበርባሪ" እያሉ በቁሜ ሲቦጫጭቁኝ እኔን ያየ ይቀጣ" እያልኩ በአደባባይ ስዞር ይልና ከት ብሎ ይስቃል።

እንደዚህማ መሆን የለበትም ክብሬን ለማስጠበቅ ስል የማላደርገው ምንም ነገር ሊኖር አይችልም አዳሜ መከራዋን አብልቼ ነው የምጨርሳት። ይሄ የክብር ጉዳይ ነው ክብር ደግሞ ከአንዲት ልቃሚ ድኃ ነፍስ ጋር እኩል ልትነመዘን አይገባትም እያለ ወደላይ ያንጋጥጣል። አቤቱ አምላኬ ሆይ የማደርገውን አላቅምና ይቅር በለኝ አለ እየሳቀ።

በዚህን ጊዜ የአቶ ተዘራ ባለቤት ወ/ሮ መዓዛ ወደ ውስጥ ትገባለች ምን እንደሚያወራ ግራ ስለገባት ለማጣራት ነው የመጣችው።

መዓዛ፡- ምን ሆነህ ነው እንደዚህ ለብቻህ የምትለፈልፈው? ስትል ጠየቀችው እዱም እየተቆጣ ምን ሆንሽ የምትሠሪው ሥራ የለሽም?

መዓዛ:- ኧረ አለኝ
ተዘራ:- ታድያ የምትሠሪው እያለሽ ነው የእኔን ወሬ ተለጥፈሽ ምታዳምጪው? በቃ አንቺ የወሬ ባላባት ሆንሽ አይደል?

መዓዛ:- ኧረ እኔስ ለዚያ አይደለም የመጣሁት ብቻህን ስታወራ ምን ሆነ ብዬ ነው? እስኪ ንገረኝ መፍትሄ ካለው አብረን እንፍታው?

ተዘራ:- ምን ሆነህ መሰለሽ። አንድ እባብ ነበር ይሄ እባብ እሱን የመሰለ አንድ ጓደኛ ነበረው። የሚበሉት ምግብ፣ የሚጠጡት ውኃ፣ የሚተነፍሱት አየር፣ የሚረግጡት መሬት አንድ ሆኖ ሳለ አንደኛው እባብ ግን ከዕለት ወደ ዕለት የሚያመነጨው መርዝና የሚረግጠው መሬት ከአንደኛው እየተለየ መጣ። በዚህም ምክንያት ያኛው እባብ ለሕይወቱ ሠጋ ...ሳትቀደም ቅደም ነውና ነገሩ ያኛው መርዝ የሚያመነጭ እባብ ለሕይወቱ በመፍራቱ መንገድ ላይ ጠብቆ አንቆ ይገለዋል። ከዚያ በኋላ ግብዐተ መሬቱ ተከናወነ ማለት ነው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ግን ይሕ የሞተና የተቀበረ ነገር ከአዲስ ሊነሳ እየተውተረተረ ነው።

መዓዛ:- መቼም ለመነሳት የሆነ በቂ ምክንያት ሊኖረው ይገባል

ተዘራ፡- እባቡ እባቡን ከገደለ በኋላ መቅበር አልነበረበትም ምክንያቱም " እባብ አፈር ልሶ ይነሳል" የሚለውን የአባቶቼን አባባል ባለመቀበሉ ነበር። ነገር ግን ልሶ ይሁን በልቶ አሁን እየተነሳ ነው።

መዓዛ፡- እሺ እኔ ምን እንድረዳህ ትፈልጋለህ? ሁሉ ነገር ግልጽ የሆነልኝ መሰለኝ ከዛሬ ፳ ዓመት የሠራነው ሥራ...........

ተዘራ፡- /በንዴት እያቋረጣት፡- የሠራሁት ሥራ በይ ......እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የከተትሽኝ አንቺ ነሽ

መዓዛ፡- /ለስለስ ባለ ድምጽ/ ውዴ .....የዛን ጊዜ እኮ ጥሩ አድርገሃል። አንተ ባትቀድመው እሱ ይቀድምህ ነበር። ሕይወት ደግሞ ውድድር ናት፣ ታሸንፋለህ ወይ ትሸነፋለህ

ተዘራ፡- በቃሽ! አሁን መፍትሄ ነው ብለሽ የምታስቢውን ነገር ሁሉ ማድረግ ትችያለሽ። ሴትየዋ እዚህ እኛ አገር መጥታ መኖር ከጀመረች ሰንበትበት ብላለች። ማንና ምን እንደሆንን አጣርታ ስለምታውቅ ቶሎ ቶሎ ብለሽ ቅደሚያት። ከዚያ ጥሩ የሆነ አጋጣሚን ተጠቅመን ከምድረ ገጽ ማጥፋት ነው ያለብን።

🕯🕯🕯🕯🕯🕯
🕯🕯ይቀጥላል🕯
🕯🕯🕯🕯🕯🕯