ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት እና መስፋፋትን ለመግታት
በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተሰጠ ማብራሪያ።

በመላው ዓለም ለምትገኙ ወገኖቻችን በሙሉ!

የወቅቱ የዓለማችን ሥጋት በመሆን በፍጥነት እየተስፋፋ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት በርካታ ሀገሮች ብሔራዊ ሥጋት ስላደረባቸው እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ናቸው፡፡

በሽታውን እንዳይዛመት ከመከላከል ውጭ የሚፈውስ መድኀኒት ስለሌለው፣ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ስለሚዛመት፣ ጾታና የዕድሜ ክልል ሳይለይ ይልቁን አረጋውያንን ስለሚያጠቃ፣ ሁሉም ሀገሮች የመተላለፊያ መንገዶች በመለየት ሥርጭቱን ለመግታት ዝርዝር መግለጫ በማውጣት ሕዝባቸው ከሞት፣ ሀገራቸውን ከጥፋት ለመከላከል እየጣሩ ይገኛሉ፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጸሎትና ምሕላ አጠናክሮ ከማድረግ በተጨማሪ ጤነኞችን የመጠበቅ፣ ሕሙማን የመንከባከብና የማጽናናት ኃላፊነት ስላለባት ቋሚ ሲኖዶስ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡-

1. ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በየደረጃው የሚዋቀር ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከጤና ባለሙያዎች የተውጣጣ ግብር ኃይል ተቋቁሟል፤
2. ግብረ ኃይሉ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰናዳት በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰነ ተግባራዊ እንዲያደርግ፣
3. ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና ጋር የማይጋጩ የመከላከያ መንገዶች ማለትም የእጅ ለእጅ መጨባበጥን ማቆም፣ እጅን በሚገባ መታጠብ፣ ሳይጠጋጉ ዘርዘር ብሎ መቆም፣ በመሳልና በማስነጠስ ጊዜ መጠንቀቅ፣ በመሳሳም ምትክ እማሄ ወይም ሰላምታ መስጠት በየአጥቢያው፣ በየገዳማቱና በያለንበት ሁሉ ተግባራዊ እንዲደረጉ፤
4. መንፈሣዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤያት፣ የመንፈሳዊ ጉዞ መርሐ ግብሮች ለጥቂት ቀናት እንዲቆሙ፣ በቅዳሴና በምሕላ ጸሎት ጊዜ በውስጥም ሆነ በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ዘርዘር ብሎ በመቆም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እንዲፈጸሙ፣
5. ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መምህራን፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ ከተሳሳቱ መረጃዎች ተቆጥባችሁ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ መመሪያዎችን በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ እንድታስፈጽሙ፣
6. ለራሳችንና ለወገኖቻችን በመቆርቆርና በመተዛዘን፣ አረጋውያንን በመጠበቅ፣ ነዳያን በማሰብ የበሽታውን ሥርጭት ተባብረን እንድናስቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ይኽንን አስከፊ በሽታ ከዓለማችን እንዲያጠፋልን በማያልቅ ቸርነቱና በቅድስት እናቱ ድንግል ማርያም አማላጅነት በምኅረቱና በይቅርታው ብዛት ይማረን፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
EOTC TV
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
††† መጋቢት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ጋኔን ያደረባት ሴትን ፈውሶ አሕዛብን ያሳመነበት)
2.ቅዱስ አባ ባጥል ትሩፈ ምግባር (ባንድ ወቅት ከእስክንድርያ ዝሙትን ለማጥፋት የተጋደሉ ጻድቅና አረጋዊ አባት)
3.ቅዱስ ሲኖዳ (ሺኖዳ) ሰማዕት
4.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

💒የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡፻፮፥፵፪
"ይርአዩ ራትዓን ወይፈሥሑ ወትትፈፀም እፋሃ ኲላ ዐመፃ መኑ ጠቢብ ዘየዐቅቦ ለዝ"
ዘቅዳሴ💒💒
#፩ቆሮ፡ ፯፥፱--ፍ.ም
#ያዕቆ፡ ፬፥፮--ፍ.ም
#ግብሐዋ፡ ፮፥፩--፰
#ምስ_መዝሙ፡ 1
፹፫፥፮
"እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል ወያስተርኢ አምላከ በጽዮን"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ማቴ፡ ፯፥፩--፲፭
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ዘባስልዮ ነው መልካም በዓል ይሁንልን ።



††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል_9
@zekidanemeheret
#7 አትስረቅ
🖊መስረቅ ማለት የሌላውን ገንዘብና ንብረት መውሰድ ሲሆን አወሳሰዱም ባለቤቱ ሳያውቅ ወይም በማታለል ወይም በኀይል ይፈፀማል።
🖊ጉቦኝነትም ሰዎች በሥልጣናቸው አማካኝነት የሌላውን ገንዘብ የሚወስዱበት ወይም ጥቅም የሚያገኙበት መንገድ እስከሆነ ድረስ ስውር ስርቆት ነው ማለት ይቻላል። 🖊ሚዛንም ስርቆት ነው ። "ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው ፡ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም " ተብሎ ተፅፏል ። ( ምሳ፳÷፳፫) 🖊የሰውን ገንዘብ ከመውሰድ የከፋ ነገር ቢኖር የቤተክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት መስረቅ ነው ። ም/ቱም ይህንን ያደረገው ሰው ከስርቆት ወንጀል ሌላ የእግዚአብሔርን ስም አቃሏል ፤ ሃይማኖቱንም ክዷል ማለት ይቻላል። ስለዚህ አድራጎቱ የበደል በደል ነው ። እንደዚህ አይነት ሰው ባልንጀራውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው የበደለው። 🖊ሌሎችም እንደስርቆት የሚቆጠሩ ነገሮች አሉ ። በምቀኝነትም ይሁን በተንኮል ወይም በግፍ የሰውን ገንዘብና ንብረት ማስቀረት ወይም መቀነስ ወይም ማቆየት ነው ። 🖊የሰራተኞችን ደመወዝ ማስቀረት ወይም አለአግባብ ደመወዛቸውን መቁረጥ አሰሪዎችን በደለኞች ያደርጋቸዋል። ቅዱስ ያዕቆብ "እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮሀል ፡ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባኦት ጆሮ ገብቷል ። " (ያዕ፭÷፬)
🖊ሌላው የአደራ ገንዘብን መብላትና የተዋሱትን የተበደሩትን ገንዘብ አለመመለስም እንደ ስርቆት ይቆጠራል። የተሳሉትን ስዕለት ፣ የገቡትን ብፅዓት አለመፈፀም እግዚአብሔርን መበደል ነው ። ልንፈፅመው የማንችለውን ነገር ቃል አለመግባት ይሻላል። አስራት በኩራትን ማስቀረት እግዚአብሔርን መስረቅ ነው {ት-ሚል፫÷፰}።
🖊ሰውን ወደ መስረቅ ምን ያደርሰዋል
# ድህነት
# በተንኮል
# በምቀኝነት
# በልማድ{በልምድ} ፤
# ምኞት
# በሰይጣን ግፌት ፤
# አለማመን {እግዚአብሔርን አለማወቅ } ወዘተ ናቸው።
🖊 ከመስረቅ እንዴት እንቆጠባለን
# በማመን
# ይበቃኛል ማለት ፤
# በፃም
# በፀሎት
# በስግደት እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ መፅሐፍት ማንበብ ናቸው።
🖊ሰዎች ሁሉ እንኳን የሌላውን ገንዘብ መስረቅ ቀርቶ የራሳቸውንም እንዲያካፍሉ ታዘዋል ። ስለዚህ የቀማን መልሰን የበደልን ክሰን ያለንን አካፍለን ከስርቆት ተቆጥበን ልንኖር ይገባል።
@zekidanemeheret

ይቀጥላል....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
👉 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
"እውነተኛ ክርስቲያን አባቱ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሰደባል እንጂ አይሳደብም፡፡ የጠፉትን ፍለጋ ይደክማል እንጂ ይባስ ብሎ አይገፈትርም፡፡ በወንድሙ ውድቀት ያለቅሳል እንጂ አይደሰትም፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን አባቱ ሌላ ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና በጊዜውም ያለ ጊዜውም ሊሆን ይገባል፡፡ ባገኘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባጣንም ጊዜ፤ ባለጤና በሆንን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በታመምንም ጊዜ፤ ሲሳካልን ብቻ ሳይሆን ባልተሳካልንም ጊዜ ማመስገን መለማመድ አለብን፡፡ የምስጋናችን ምንጭ የሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን ስለ አምላካችን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ ስንለማመድ በክብር ላይ ክብር ይጨመርልናል፤ እንደ አባታችን ኢዮብ የዲያብሎስን አፍ እንዘጋለን፡፡
ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን?” እንኪያስ "በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
✝️መጾሙን ይጾማል✝️

መጾሙን ይጾማል ሁሉም የአዳም ልጅ /2x/
የጊዜውን መድረስ የሚያውቅ የለም እንጂ /3x/
ይደርሳል ሰዓቱ ሳስብ ሌላ ሌላ /2x/
የተሰቀለውን ሥጋውን ሣልበላ /3x/
ድጓ ጾመ ድጓ ተሰቅሎ ከቤቴ /2x/
አወይ አለማወቅ ሳልማር መቅረቴ /3x/
ደግሞ ደግሜ ቀረኝ አሌፋቱ /2x/
አድኀነኒ ሣልል አትጥራኝ በከንቱ /3x/
እኔስ እሄዳለሁ አጣቢ ፍለጋ /2x/
በጣም አድፎብኛል የለበስኩት ሥጋ /3x/
ዳዊት እንዴት ይሙት ሳንተዋወቀው /2x/
የሚመጣውን ሁሉ በገና የሚያውቀው /3x/
ዐርብ ረቡዕን ገደፍኩ በሥጋ በአዋዜ /2x/
እንዲህ ለሚደርሰው ለማይቆየው ጊዜ /3x/
ከሥጋው ሳልበላ ተጠይፌ ደሙን /2x/
ማን ይችለው ይሆን የላይ ቤት ረሃቡን /3/
ከንብረቴ ሁሉ አልጋዬ ነው ሀብቴ /2x/
አድርሶኝ ይመጣል ከዘላለም ቤቴ /3x/
ብልህ ነው ስትሉኝ እዩት ሞኝነቱን /2x/
በራሴ ላይ ሆኖ አላውቀውም ሞቴን /3x/
መማሩንስ ዳዊት ተምሬ ነበረ /2x/
ከአምላኪየ ሳልደርሰ ልቤ ሰንፎ ቀረ /3x/
እንኳን ነአኩተከ በስመ አብም ቸገረኝ /2x/
ዳዊት እንዴት ተማርክ እባክህ ንገረኝ /3x/
💚💚💚💚💚💚💚💚💚
💛 @zekidanemeheret 💛
💛 @zekidanemeheret 💛
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሰይጣን ራሳችንን ስንገዛና ከራሳችን ጋር ስንሆን ኃጢአታችንንም ስናስተውል ስለንሰሐም ስናስብ ይፈራል።በዚህ ጊዜ ከእርሱ ማምለጥ ይቻላል።

በእናንተ ሳይፈረድባችሁ አስቀድማችሁ እናንተ በራሳችሁ ላይ ፍረዱ” ቅዱስ መቃርዮስ
እንባህ ከመፍሰስ እንዳይቆም ከወደድህ በጸሎት ጽሙድ ሁን አንድም በተዘክሮ ጽሙድ ሁነህ ኑር።


መከራ መጥቶብህ መከራውን ለማራቅ ከምትጸልየው ጸሎት አስቀድሞ ለሚገባ ንሰሀ ተዘጋጅ።

እኛ ሀጢአታችንን ያስታወስን እንደሆነ እግዚአብሔር ይተዋቸዋል። እኛ ግን ኃጢአታችንን የዘነጋን እንደሆነ እግዚአብሔር ያስታውሰናል”
ቅዱስ እንጦስ
""""""""""""""""""""
በንሰሀ ሕየወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም።
አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

አንተ ሌሎችን የምትምር ከሆነ እግዚአብሔርም አንተን ይምርሃል። ነገር ግን አንተ ቁጡና ጨካኝ ሆነህ ሳለህ የእጅህን ዋጋ ብታገኝ እንዳታማርር።
አቡነ ሺኖዳ

የዋህ ሰው ሰለ እርሱ ሰዎች ይከላከሉለታል እንጂ እርሱ አይከላከልም።
አቡነ ሺኖዳ

ክርስቲያን በተፈጥሮው የማስተዋል የአርምሞ የጥንቃቄና የሰላም ሰው ነው።

አንተ ካስፈለገህ ሁለት ጊዜ ከተጠየቅህ በመጠኑ ተናገር፣ መልስህም በጥንቃቄ እና በ’እውቀት ባጭሩ የሰዎችን አእምሮ የማያስጨንቅ ይሁን።

እውነትን ከመስማት የበለጠ ለጆሮውች ጌጣጌጥ የላቸውምና ሴቶች ለምድራዊ ጌጣጌጦች ጆሯቸውን አይብሱ፣ እውነትን ለመስማት የተበሱ ጆሮዎች ቅዱስ ነገርን መለኮታዊ ቃልን ያደምጣሉና።

አንደበትህ በአርምሞ በዝምታ የተመላ ይሁን ልብህን በእርጋታ አኑረው የሁሉም መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ፣ ለከንቱ ንግግር (ወሬ) ዘገምተኛ እና ሰነፍ ሁን፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድህነት የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን።

ማንኛውንም ነገር ለማወቅ የክፋት መርዝ በአዕምሮህ እንዳይሰራጭ ጉጉት አይደርብህ

የመንፈስ ስጦታዎች ልዩ ልዩ እንደመሆናቸው መጠን እና አንዱ አገልጋይ ሁሉንም ገንዘብ ማድረግ ሰለሚችል በተሰጠው ጸጋ በማመስገን ቢቀመጥ መልካም ነው።

ለመስበክ የተመረጠው ሰባኪ ወንጌልን ለመስበክ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይጠብቅ እንጂ የራሱን አይደለም

ሰነፍ ሰው ሲስቅ ይጮሀል ድምጹንም ከፍ ከፍ ያደርጋል።

የሚስት አክሊሏ ባሏ ነው፣ ፣የባልም ጋብቻው ለሁለቱም የጋብቻቸው አበባም አንድነታቸው ልጆቻቸው ናቸው። ይኸውም በመለኮታዊ አመሰራረት ከስጋ እርሻ የተገኘ ነው ።

ድንቁርና በሃጢአት እንድንወድቅ ስለሚያደርግ እውነትንም በግልጽ የምናይበትን ችሎታን ስለማይሰጥ ጨለማ ነው።
እውቀት ግን የድንቁርናን ጨለማ አስወግዶ እውቀትን ሰለሚያጎናጽፈን ብርሃን ነው።


ትህትና

መድኅን ነው ከሰይጣን አሽክላ ያድንሃል።
/አባ እንጦንስ/
ትህትና
የሰው ዘመድ ነው። / አባ አሞን/
ትህትና
የማይናድ ደልዳላ መሬት ነው። /አባአርሳንዮስ/
ትህትና
ክርስቲያናዊ ምልክት ነው። /አባ መቃርስ/
ትህትና
ከትሩፋት ሁሉ ይበልጣል። /አባ አሞን/
ትህትና
መስቀል ነው። /አባ ታድራ/
ትህትና
የሰው ሁሉ ጋሻ ጦር ነው። /አባ በሐይ/
ትህትና
ግድግዳን የሚያስጌጥ የአፈር ወይዘሮ ነው።/አባ አጋቶን/
ትህትና
የመንግስተ ሰማያት መመላለሻ በር ነው። /አባ ሚልኪ/
ትህትና
ሕፀጽን የሚያስታውቅ መስታወት ነው። /አባጰርዬ/
ትህትና
የነፍሳት ወደብ ነው። /አባ ዮሐንስ/
ትህትና
የወንጌል ትእዛዝ መጀመሪያ ነው። /አባዮሐንስ ሐፂር/
ትህትና
ወደ ንፁሐ ልቡና ሰገነት የሚወጡበት ዕፀሕይወት ናት።/አባመቃርስ/
የእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት
ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
ዛሬስ ምን እያልን ምን እያረግን ይሆን?
፻-----በዘረኝነት እና በድንበር ጥማት የተቃጠልን ህዝብ ዛሬ በእያንዳንዳችን አካል ላይ እቤታችን ገብቶ ድንበር የሚጥልም እንዳለ ስናይ ምን ብለን ይሆን?
፪----በቃል ኪዳን የከበሩ ቅዱሳን ገዳም ኑ እየተባልን ስንጠራ አልመጣም ብለን የሚያስጨንቅ ቀን መቶ እንዳትመጡ ስንባል ምን አስበን ይሆን?
፫---ጥበበኛውን አምላክ ንቃ የጥበብ መሰረት ነኝ ላለች አለም ስንጓጓ ስንንበረከክ የነበርን ዛሬ ጥበብ ርቋት ተጨንቃ ቤቷን ስትዘጋ ስናይ ምን ብለን ይሆን?
፬---ልባችሁን አጥሩ በንስሀ ታጠቡ ስንባል እምቢ ብለን በፍርሀት እና ጭንቀት እጃችንን ስንታጠብ የምንውል እኛ ዛሬስ ምን እያልን ይሆን?
፭---ምድር እንኳን ለአምላኳ ታዛ በቁጣ ማእበል ስትንቀጠቀጥ፣ ሰማያት እሳትና በረዶ ሲያዘንቡ ዛሬ እኛስ ምን እያረግን ይሆን?
፮----አለም እንደ ፈርኦን በመቅሰፍት ስትናወጥ እኛ ዛሬስ ምን እያረግን ይሆን? ዛሬም የአየር መዛባት ነው? ዛሬም እኛን አይነካንም? ዛሬም ይህን አለም የሚያስተዳድር አምላክ የለም? ዛሬም አንመለስም? ዛሬም በመርከብ ውስጥ አንገባም? አቤቱ የተሰበረ ልብ ይስጠን።

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ህይወት_ስትጨልምብን
ህይወት የሁለት ነገሮች ድምር ውጤት ናት ። ማግኘት አለ ማጣት አለ ፣ መወለድ አለ መሞት አለ ፣ ደስታ አለ ሀዘን አለ ፣ እንባ አለ ሳቅ አለ ሁለቱም የህይወት አካሎች ናቸው። አንዳንዴ ህይወት እንደ ሸማኔ መወርወሪያ የሁለቱንም ጫፍ እያስነካች ትመልሰናለች። አንድ ቀን 24 ሰዓት አለው። 12ቱ ሰዓት ብርሃን 12ቱ ሰዓት ጨለማ ነው። አይ እኔ ጨለማ አልወድምና ለሊቱ ይቅርብኝ ብንል ቀናችን ጎዶሎ ነው ሚሆነው ። አንድ አመትም ክረምትና በጋ አለው። አይ ጭቃ አልወድምና ክረምቱ ይቅርብኝ ብንል አመታችንም ጎዶሎ ነው ሚሆንብን ። ስለዚህ ህይወትም ያለ ችግር ደስታውን ብቻ እንኑረው ብንል ጎዶሎ ህይወት ነው ምንኖረው። አንዳንዴ ፈጣሪ ችግር ውስጥ ሚከተን ህይወታችንን ሙሉ ለማድረግ ነው ። ከለሊት ቡሃላ ንጋት እንጂ ሌላ ሌሊት አይመጣም ። ከመከራ ቡሃላም ደስታ እንጂ ሌላ መከራ አይመጣምና ታገስ። ወዳጄ አንድ ኮኮብ ዙሪያው በጨለመ ቁጥር እሱ ይበልጥ ይበራል። ህይወትህ የጨለመብህ ይበልጥ እንድታበራ ነውና ተደሰት። እህቴ በተለያየ ሀገር በተለያየ ስራ ውስጥ እራስሽን ለመለወጥ በተለያየ አይነት ችግር ውስጥ ተወጥረሽ ይሆናል። ግን የረገበ የክራር ክር ሙዚቃ ማውጣት አይችልም። አንድ ክራር ሙዚቃ ከማውጣቱ በፊት መጀመሪያ ክሩ በደንብ መወጠር አለበት። ህይወት አንቺንም የወጠረችሽ ሚያምር ማንነትሽን ለማውጣት ነው። ወንድሜ እራስህን ለመለወጥ ስትሞክር ብዙ ነገሮች ቅጥል አርገውህ እርር ብለህ ይሆናል። ግን አስታውስ አንድ መዓዛው የሚያምር እጣን ይሸተን ዘንድ መጀመሪያ እሳት ውስጥ ገብቶ መቃጠል አለበት። አንተንም ህይወት ያቃጠለችህ ሚያምር ማንነትህ እንዲወጣ ነውና ተደሰት።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
ራሳችንን እንጠብቅ፤ እኛ በዚህች ምድር እየኖርን ያለን ሥጋ ለባሾች ነን። ሥጋ ለባሽ እስከሆንን ድረስ ደግሞ በዓለም ላይ ለተቃጣ ጥፋት ሁሉ ተቋዳሽ ነኝ። ጉዳዩ ለማንም የወረደ ይሁን፤ እኛ የዓለም ክፍሎች ነንና የዓለም እሾኽ አይወጋንም ብለን ራሳችንን ከማታለል እንቆጠብ።
የመጣው በሽታ ማንንም የሚምር አይደለም። ሥጋ ለባሽ የሆነን ሁሉ የሚጠርግ አውሎ ነፋስ ነው። በመታበይ ፊት ለፊት መጋፈጥ ዋጋ ያስከፍላል። ራስን ቤት ማዋል ነውርም ሐጢአትም አይደለም። በብቸኝነት ውስጥ ጾምና ጸሎት አለ። ብሕትውና እንኳን ያለው ከሰው በመለየት ነው። ፍርሀትን በመታበይ ለመሸሸግ ካልሞከርን በስተቀር ለጥንቃቄ የሚተላለፉ መመሪያዎች ከሃይማኖት ጋር ፈጽሞ አይጋጩም። አካሄዳችን በስልትና በጥበብ ካልሆነ ነገ ቆራቢም አቁራቢም ማጣታችን አይቀርም። ገድላቱን፣ ድርሳናቱን፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሁሉ እያነበብን በያለንበት ጸንተን እንቁም። ሃይማኖት በእልህ ሳይሆን በጥበብ ነው። አባቶቻችን ስለ ሃይማኖታቸው ፊት ለፊት የሚጋፈጡት አስፈላጊ በሆነበት ሰአት ነው፤ መጋፈጥ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ሲረዱ ግን ሃይማኖትን ለማስቀጠል እንኳን ከቤት መዋል ሀገር ጥለውም ይሰደዳሉ። ለተወሰኑ ቀናት መመሪያ አንቀበልም ብለን በሚመጣው ጥፋት የረጅም ጊዜ ዋጋ እንከፍላለን። ጥቂት ጊዜ ብንታገሥ ግን ፈተናውን አልፈን ረጅሙን አገልግሎት እናስቀጥላለን። በስሜታዊነት መጓዝ ዋጋ ያስከፍላል። እባካችሁ ጥንቃቄ እናድርግ።

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
††† መጋቢት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሰለፍኮስ ሰማዕት
2.እናታችን ቅድስት ሣራ ጻድቅት (ግብፃዊት)
3.አባ ሕልያስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አፈ በረከት
3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
4.ቅድስት እንባ መሪና
5.ቅድስት ክርስጢና


💒የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡፶፭፥፲፫
"እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት ወለአእይንትየኒ እምአንብዕ ወለእገርየኒ እምዳህፅ"
#ወንጌል_ማር፡ ፱፥፵፫--ፍ.ም
ዘቅዳሴ💒💒
#ኤፌ፡ ፭፥፳፩--ፍ.ም
#፩ዮሐ፡ ፭፥፲፬--ፍ.ም
#ግብሐዋ፡ ፳፮፥፩--ፍ.ም
#ምስ_መዝሙ፡ ፴፮፥፳፱
"ጻድቃንሰ ይወርስዋ ለምድር ወይነብሩ ውስቴታ ለዓለም ዓለም አፉሁ ለጻድቅ ይትሜሃር ጥበበ"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ሉቃስ፡ ፲፥፲፱
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ዘባስልዮስ ነው መልካም በዓል ይሁንልን ።



††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
የቅዱስ ሲኖዶስ ሁለተኛ መግለጫ
____

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ የኖብል ኮሮና ቫይረስ በሰው ዘር ላይ የደቀነውን አስከፊ አደጋ በውል በማጤን ምእመናንን እና ሀገርን ከመከራ ሥጋ ለመጠበቅ በድጋሚ ዘርዘር ያለ መመሪያ አውጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶሱን በማማከር እና ጥናት በማቅረብ የደከማችሁ የጤና ባለሙያዎች እና ምሁራን ልትመሠገኑ ይገባል። የሲኖዶስን ውሳኔ ለማስፈጸም በተለይ በየ አጥቢያው ያላችሁ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ ምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ታሪካዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት ህዝባችንንእና ሀገራችንን ከወቅታዊው አደጋ ልንታደግ ይገባል።
______

1. መጨባበጥ እንዲቀር።

2. ማንኛውም መንፈሳዊ ጉዞዎች እና መንፈሳዊ የስብከት መርሐግብሮች እንዲቆሙ።

3. አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎችም ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን ስንገባ እጆቻችንን በመታጠብ ዘርዘር ብለን በመቆም እንድናስቀድስ።

4. ዓመታዊ የንግስ በዓላት በቅዳሴ እና በማኅሌት ታስበው ክብረ በዓላቱ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ።

5. የጉንፋን ምልክት የታየባቸው ምእመናን እና ካህናት በየቤታቸው ተለይተው እንዲቆዩ።

6. በቋሚ ሲኖዶስ ሥር የተቋቋመው ግብር ኃይል (Task Force) እስከ አጥቢያ ድረስ ተደራጅቶ እንዲሠራ።

........ ሁለተኛ መግለጫ


7. ቅዳሴን በተመለከተ፤

• ልዑካኑ ብቻ በመቅደሱ እንዲያገለግሉ
• ቆራቢዎች ብቻ መደ ቤተመቅደስ እንዲገቡ
• አረጋውያን ወጣቶች እና ሕጻናት ለቁርባን በፈረቃ ወደመቅደስ እንዲገቡ
• ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ሁለት የትልቅ ሰው እርምጃ ያህል ተራርቀው በመቆም እንዲያስቀድሱ
• ምእመናን የራሳቸውን የቅዳሴ ጠበል መጠጫ እቃ ለብቻ እንዲጠቀሙ።

8. ስብሐተ ነግህ እና ሌሎች አገልግሎቶች ለአገልግሎቱ አስፈላጊ በሆኑ አነስተኛ የምእመናን ቁጥር እና በውሱን ሊቃውንት ብቻ በተራ እንዲፈጸም።

9. ካህናት ብቻ በቤተ መቅደስ በዓውደ ምህረት እና በቤተ ክርስቲያን ጸሎተ እጣን እንዲያደርሱ።

10. በደስታ እና በሐዘን የሚፈጸሙ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ለበሽታው ጥንቃቄ ሲባል በውሱን የሰው ቁጥር በጥንቃቄ እንዲፈጸም።

11. ምእመናን የውጭ ሀገር ዜጎችንም ሆነ በቫይረሱ የተጠቁት ወገኖቻቸውን እንዳያገሏቸው።

12. በየአጥቢያው ለተቸገሩ እና ለነዳያን ድጋፍ እንዲደረግ።

13. ቤተክርስቲያንን ከማይወክሉ አሳሳች መረጃዎች ምእመናን እንዲቆጠቡ።

(መልእክቱን ለሌሎችም በማጋራት ኃላፊነታችንን እንወጣ)

______

#እጆቻችንን_በሳሙና_እንታጠብ
#ከመተፋፈግ_እንከልከል
#እራሳችንን ለካህን እናሳይ
_______

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret
ውሎህ የት ነው?

ሕይወት ሥነ ምህዳር ነው። የሰጠኸው ነገር ተመልሶ ይመጣል።

የዘራኸውን ታጭዳለህ የምትሰጠውን ታገኛለህ በሌሎች ውስጥ የምታየውን በአንተ ውስጥ ታገኘዋለህ ፡፡ ሕይወት ሁሌ የሰጠሀትን መልሳ ትሰጥሀለች መልካም አድርግ መልካም ታገኛለህ እንደሚባለው ሁሉ።


ውሎህ አንተን ይገልፃል መልካም ቦታ ከተገኘህ በመልካም ይገለፃል በመጥፎ ቦታ
ከዋልክ እንዲሁ!!! ይሄንን የሚገልፅ ልናስተውለው የሚገባ አንድ ተረት አለ እንዲህ ይላል አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሬያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::


አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት ውሎሽ የት ነው?


ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ ውሏችን ተመልሶ እኛነታችንን ይገልፃል ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ሀሳባችን ስራችንን ስራችን ውጤታችንን ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናልና።
የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለችና ራስን መፈተሽ መልካምም ነውና ውሎህ የት ነው?

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል_10
#8 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር
@zekidanemeheret
🖊ይህ ቃል የሚሰራው በሐሰት ለሚመሰክር ብቻ አይደለም ሐሰትንም ለሚቀበል ነው። ማቴ ፰÷፵፩
ምሳ ፲፪÷፳፪ ፤ ፩ነገ ፳÷፲፫ ፤ መሳፍ ፲፱÷፭
🇪🇹ምስክርነት ምን ማለት ነው ? በሐሰት መመስከርስ እንዴት ነው ?
🖊 #ምስክርነት ማለት በዳኛ ፊት ወይም በባለሥልጣን ፊት ወይም በአስታራቂ ሽማግሌዎች ወይም ስለ ሥነ ስርዓት ጉዳይ በተሰየመ ጉባኤ ፊት የቀረበውን ሙግትና ክርክር በትክክል ለመፍረድና ለመወሰን የሚረዳ የቃል ማረጋገጫና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያመለክት ነው ። በእውነት የሚቀርበው ምስክርነት በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ያስመሰግናል። ነገር ግን ሰዎች በልዩ ልዩ ጥቅም ተገዝተው ወይም ባልንጀራን አለአግባብ ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲባል እውነቱን ነገር በመሸሸግ ሐሰት ነገር በመፍጠር ያልተነገረውን ተነገረ ያልተደረገውን ተደረገ በማለት በመሐላም ሆነ ያለ መሐላ የሚቀርበው የውሸት ማስረጃ ሁሉ የሐሰት ምስክርነት ይባላል። በኀብረተሰቡ ውስጥ እውነትና ሐቅ ጠፍቶ ፍርድ ጎድሎ ድሀ ተበድሎ ሰዎች ሁሉ ጊዜያቸውንና ኃይላቸውን ገንዘባቸውንም በክርክርና በጠብ እንዳያጠፋና ሰላማቸውን እንዳያጡ በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ በማሰብ እግዚአብሔር "በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር" የሚለውን ትእዛዝ እንድንጠብቀው ሰጥቶናል።
🖊ይህን ትዕዛዝ መተላለፍ ትልቅ በደል ነው ።
#በመጀመሪያ መስካሪው እውነት እመሰክራለው ብሎ የገባውን ቃል ኪዳን ወይም መሐላ አፍርሶ ውሸት በመናገሩ ፣
#2ኛ ዳኛውን በማሳሳት የሐሰት ፍርድ በማስፈረዱ ፣
#3ኛ የተፈረደበትን ሰው ሳያጠፋ በማስቀጣቱ በደሉ ብዙ ነው።
🖊ይህ ትዕዛዝ ቀጥታ ምስክሮችን ብቻ የሚመለከት አይደለም ። ልዩ ልዩ የሐሰት መረጃዎችን በማዘጋጀት ፡ ሰነዶችንና መዝገቦችን በማጭበርበርና በማዘዋወር አስመስሎ በመፈረምና በተሰረቁ ማኀተሞች በመጠቀም እንደዚሁም ሌሎች ይኽን የመሰሉ በተንኮል የተቀናበሩትን ሁኔታዎች በማመቻቸት የሚያስፈርዱትንና የሚፈርዱትንም ሁሉ ይመለከታል።
🖊ስለዚህ ምስክርነታችን ሁሉ #በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ።
@zekidanemeheret

ይቀጥላል.....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
††† መጋቢት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
7.አባ ዳንኤል ጻድቅ

💒የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡፲፮፥፵፫
"ወተስይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ ሕዝብ ዚኢየአምር ተቀንየ ሊተ ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥወኒ"
#ወንጌል_ሉቃስ፡ ፲፱፥፲፪--፳፰
ዘቅዳሴ💒💒
#፩ጢሞ፡ ፬፥፩--ፍ.ም
#፪ጴጥ፡ ፩፥፲፪--፲፱
#ግብሐዋ፡፲፩፥፳፫--፳፯
#ምስ_መዝሙ፡ ፷፯፥፴
"ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ ይምጽኡ ተናብልት እምግብጽ ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ሉቃስ፡ ፲፬፥፳፰ፍ.ም
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ዘሠለስቱ_ምዕት_ግሩም ነው መልካም በዓል ይሁንልን ።


††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል-11
#9 የባልንጀራህን _ሚስት{ቤት} _ንብረት_አትመኝ አትግደል ፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ ፣በሐሰት አትመስክር በማለት
ክፉ አድራጎትን ወይም የጥፋት ሥራዎችን የሐሰት ንግግሮችን ይከለክላል።
🖊 #አትመኝ በማለቱ ደግሞ ክፉ ምኞትንና መጥፎ ሐሳብን ይከለክላል። በውጭ በተግባር የሚደረጉት ከውስጥ በልቡናችን ከሚፈፀሙት ጋር ማለት ከምኞትና ከሐሳብ ጋር እንደሚታየው እንደ ግንዱ የተያያዙ ናቸው ። ሥሩ ደኀና ከሆነ ግንዱም ደኀና ይሆናል ። አንድ ነገር በድርጊት ከመፈፀሙ በፊት ነገሩ የሚጠነሰሰውና የሚጀመረው በምኞትና በሐሳብ ውስጥ ውስጡን ነው ። ክፉ ሰው ከልቡ ክፉ ነገርን ያወጣል ፤ ደግ ሰው ግን ከልቡ ደጋግ ነገሮችን ያወጣል።
🖊 #መመኘት ማለት የሌላውን ሰው ሚስት / ባልና ሀብት ለራስ እንዲሆን መፈለግና ማሰብ ስለሆነ አንድ ነገርን የተመኘ ሰው ጊዜና ቦታ ባይገድበውና ሁኔታዎች ቢመቻቹለት በልቡ የፈለገውን በሐሳብ ያቀደውን ፣ በስሜቱ የፈቀደውን ከማድረግ አይመለስም።
🖊 ስለዚህ የኀጢአት ምንጩ የወንጀል አባቱ በልቡና የሚገኘው ክፉ #ምኞት ነው ። ስለዚህ የሰውን ንብረት ከመመኘት መታቀብ አለብን ።
🖊ይህንንም ለማጥፋት እና ኀሊናን ለማፅዳት መትጋት አለብን ። የሕግ ሁሉ ፍፃሜና ማጠቃለያ #ፍቅር ነው ። ሁሉም ትዕዛዞች በፍቅር ይጠቃለላሉ። 🖊ባልንጀራውንም አምላኩንም የሚወድ ህግን ይጠብቃል።
ዘፍ፫ ፤ ማር፯÷፳፩-፳፫ ፤ ሮሜ፩÷፳፱ ኢያ፯÷፮-፳፮ ፤ ፪ኛሳሙ፲፩÷፲፬-፲፯/፲፪÷፲፭ ፤ መክ ፪÷፲/፩÷፯-፲ ፤ ዘፍ ፳፭÷፳፱-፴ ፤ ዘኁ ፲፩÷፬-፭ /፲፩÷፬ ፤ መዝ ፵፰/፵፱/፲፪÷፲፯ ፤ ሉቃ ፲፪÷፲፭ ፤ ፩ጢሞ ፮÷፱ ፤ ኤፌ ፭÷፭ ፤ ፩ኛቆሮ፲፪÷፩ /፲፬÷፩ ፤ ገላ፭÷፲፯
@zekidanemeheret

ይቀጥላል....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር
#ክፍል-12
#10 ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ።›› ዘሌ 19÷18፡፡
@zekidanemeheret
🖊“አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ዘሌ ፲፱÷፲፰
🖊ባልንጀራህን ውደድ የተባለው በሥላሴ አርአያ የተፈጠረውን ሰው በሰውነቱ መውደድ እንደሚገባ ለማመልከት ነው፡፡
‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።›› ማቴ ፭÷፵፪-፵፰፡፡
🖊ጌታችን ትእዛዛትን ዘርዝሮ ባስረዳበት ክፍል ‹‹ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡፡›› ብሎአል፡፡ ማቴ ፲፱÷፲፰፡፡ባልንጀራን መውደድ ለሰው መልካም ሉቃ ፲÷፳፭-፴፯፣ ነፍሱ የምትድንበትን ያዕ ፪÷፰-፱ ማድረግን ያካትታል፡፡ባልንጀራንም መውደድ ለራስ የሚሹትን መልካም ነገር ለባልንጀራ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ‹‹እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።›› ማቴ ፯÷፲፪፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ነገረንም ባልንጀራን መውደድ ከራስ ጥቅምም የባልንጀራን ጥቅም መመልከትንም የተመለከተ ነው፡፡
@zekidanemeheret
‹‹እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድስ እንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ፡፡››፩ ቆሮ ፲÷፳፬፣ ፊል ፪÷፪-፬ ባልንጀራውን የሚወድ ሰው ሰውነቱን በዝሙት፣ ሀብቱን በስርቆት፣ ስሙን በሐሰት በማጥፋት ወይም በሐሰት በመመስከር ባልንጀራው የሚጠፋበትን አያደርግም፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፡፡››፩ ጢሞ ፩÷፭ ፡፡ እንዳለን፡፡ጌታችን ‹‹… ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።… በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።›› ማር ፲፪÷፴፩-፴፫፡፡እግዚአብሔርን መውደድና ባልንጀራን መውደድ አይነጣጠሉም፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን። ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።›› ፩ዮሓ ፭÷፪-፫ ‹‹እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል።
ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።››፩ዮሐ ፫÷፲፬-፲፰፡፡ ‹‹በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ። ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል
ማሰናከያም የለበትም፤ ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥
ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።›› ዮሐ ፪÷፱-፲፩፡፡እግዚአብሔርንና ባልንጀራን መውደድ የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ነው፡፡
‹‹ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን
እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።›› ፩ዮሐ ፬÷፳-፳፩፡፡ እንደተባልነው እንደራሳችን ባልንጀሮቻችንን እንድንወድ ይገባል፡፡ ‹‹ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው።›› ገላ ፭÷፲፬፡፡ ‹‹ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።›› ፊል ፪÷፫-፬፡፡ ‹‹አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።›› ማቴ ፲፱÷፲፱፡፡
‹‹ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።›› ማቴ ፳፪÷፴፱፡፡
• ‹‹ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ ፡፡›› ዘካ ፰÷፲፯

@zekidanemeheret
ይቀጥላል....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret