እኛ ማን ነን⁉️
✍በዲ/ን አሸናፊ መኰንን
👉ሰውዬው ድንኳን ሰባሪ ነው፡፡ ሁለት ቦታ የአቡዬ ድግስ እንዳለ ይሰማል፡፡ ሰዓቱ ሲደርስ እንደ ተጠራ ሰው የክት ልብሱን ለብሶ ይወጣል፡፡ የሁለቱም ድግስ የተለያየ ቦታ ነበር፡፡ ወደ አንደኛው እየሄደ ሳለ የዚያኛው ድግስ ቢበልጥስ ብሎ ተመለሰ፡፡ ወደዚያም ጉዞ እንደ ጀመረ የዚህኛው ምስር ሆኖ ያኛው ቁርጥ ቢሆንስ ብሎ እንደገና ተመለሰ፡፡ እንዲህ ሲያመነታ ሰዓቱ እያለፈበት ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ በመካከለኛ መንገድ ላይ ቆመና በጭንቀት ‹‹አቡዬ የዛሬን ብቻ ለሁለት ይሰንጥቁኝ›› ብሎ ጸለየ ይባላል፡፡
😁😁😁
🔵ዓለምንም እግዚአብሔርንም መያዝ አይቻልም፡፡ ሁለት አባሮም አንድ መያዝ አይቻልም፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎም ሁለት ዛፍ አይወጣም፡፡ አንዷ ብትጠፋ አንዷ ትዳን የምትባል ሁለት ነፍስም የያዘ የለም፡፡ ከካደው ይልቅ መሐል ሰፋሪው የመመለስ ዕድሉ የመነመነ ነው፡፡ ዛሬ አብያተ ክርስቲያናትን ያጣበቡ ‹‹ምንም ይሁን ሰላም ይስጠኝ እንጂ›› ብለው የመጡ ናቸው፡፡ ዛሬን እንቅልፍ መተኛት እንጂ ዘላለማዊ ሕይወት ማግኘት አይፈልጉም፡፡ ተባብረው ያድኗቸው እንጂ ፍጡርና ፈጣሪን፣ እግዚአብሔርንና ጠንቋይን አይለዩም፡፡ የሚያሳስባቸው ጉዳያቸው እንጂ የእግዚአብሔር ፍቅር አይደለም፡፡ ማዕዱን ትተው በፍርፋሪ ለመጥገብ የሚመኙ ሚና አጥተው ሁሉ ቦታ አሉ፡፡ ከቤታቸው ወጥተው ያሰቡበት አይደርሱም፡፡ ሁሉ ይጎትታቸዋል፡፡ የሚያዩት የሚሰሙት አፍዞ ያስቀራቸዋል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ክርስትና አቋም ሳይሆን ፋሽን ነው፡፡ ክርስትና ቃል ኪዳናቸው ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ሊተውት የሚችሉት ነገር ነው፡፡ የንስሓ ዝማሬ፣ ጸሎትና የተሰበረ ሕይወት ‹‹አይመቸንም›› ይላሉ፡፡ መቆዘም የማይፈልጉ ሁልጊዜ የግርግር ደስታን ከ‹‹ሃሌ ሉያ›› የተራቡ ናቸው፡፡
🔴ጌታ ስለ ጠፉት ሦስት ወገኖች ሲናገር አንደኛው ጠፊ ድሪሙ (ገንዘቡ) እቤት ውስጥ የጠፋ ነበር (ሉቃ 15÷8)፡፡ ዛሬም በቤቱ የጠፉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሳይድኑ ለማዳን የሚሰብኩ፣ መመራትን ሳያውቁ የሚመሩ፣ ግጥም ገዝተው የሚዘምሩ፣ የገዛ ድምፃቸው አስለቅሷቸው የሚወርዱ ብዙ የጠፉ ወገኖች ዛሬም በቤቱ አሉ፡፡
⚫️በድንበር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ቋንቋቸው የተደባለቀ ነው፡፡ የንግድ ልውውጡም የደራ ነው፡፡ ሁለት አገር መሆናቸውን የሚያውቁት ፖሊስ ሲያዩ ነው፡፡ ዛሬም የድንበር ክርስትናን የሚገፉ፣ አንድ እግራቸው ዓለም፣ አንድ እግራቸው ቤተ ክርስቲያን የሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ በሰማበት ጣዱኝ የሚሉ፣ ቋንቋቸው የተደባለቀ ሕዝቦች ዛሬም በቤቱ አሉ፡፡ ክርስትናቸውን የሚያስታውሱት ሰባኪ ሲያዩ ነው፡፡ ግን እኛ ማን ነን❓
🔶ከእስራኤል ልጆች የሮቤልና የጋድ ነገድ ዮርዳኖስን ተሻግረው መውረስን አልፈለጉም፡፡ ከሚወርድ ጅረት ጋር መታገልን፣ ኢያሪኮን ማፍረስን፣ ጠላትን መደምሰስን አልፈለጉም፡፡ በከነዓን ትይዩ መቀመጥን ፈለጉ (ዘኁ.32)፡፡ ውጤታቸው ግን ያለ ወንድሞቻቸው በበረሃ ተጠቅተው ቀሩ፡ ዛሬም ከክርስትናው ትይዩ አቅጣጫቸውን እያስተካከሉ የሚኖሩ፣ ዳር ዳር እየተጓዙ የሚቃርሙ ብዙዎች ናቸው፡፡ ውጤታቸው ግን እንዲሁ መና ሆነው መቅረት ነው፡፡ ላመኑበት ዋጋ ለመክፈል የሚፈሩ ለመኖርም ብቁ አይደሉም፡፡
🔻ጌታ፡- ‹‹ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ÷ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ፦ እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል ...›› (ማቴ. 11÷16-19) ብሏል፡፡
🔹ወንጌል ሲሰበክለት የእኔ አይደለም የሚል፣ ፍርድ ሲሰበክለት እግዚአብሔር አይጨክንም የሚል ትውልድ ምሳሌው ምንድነው? ቃሉን እንደ ኪኒን፣ መዝሙርን እንደ ዘፈን መለወጫ የሚጠቀም ትውልድ ምን ዓይነት ትውልድ ነው? እና ማን ነን? ማን እንደ ሆንን የምንጠየቀው ከውስጥ ነው፡፡ ደጁን ስናንኳኳ ማን ነው? ስንባል ‹‹እኔ ነኝ›› ካላልን የሚከፍትልን የለም፡፡ ‹‹እኔ ነኝ›› ማለት ካልቻልንም ሕይወት ደጇን አትከፍትልንም፡፡ ሰዎች ማን እንደሆኑ እናውቃለን እንላለን፡፡
ግን እኛ ማን ነን❓❓
ሁልጊዜ ጠቃሚ የቤተክርስቲያንን ጽሁፍ ለማግኘት ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
#share
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret

#ኮሮና_ኮቪድ_19
👉 ከ27 ዲግሪ ሙቀት በላይ ካገኘ ቫይረሱ መኖር አይችልም ተባለ ኧረ እንደ ሳውዲ እና ኢምሬት ያሉ ሀገራት ነዋሪዎች ለምን ተያዙ? 👉 👉ብዙ ህዝብ የተሰበሰበበት አካባቢ ይተላለፋል ተባለ ለምን በቤተመንግስት ለብቻቸው የሚኖሩትን ያዘ? 👉 መታጠብ እንዳይዝ ይረዳል ተባለ ለምን ሁሌ ሶፍት እና ውሀ የማይለያቸውን ሚኒስቴሮችን አጠቃ?👉 የሰውነት እንቅስቃሴ ጥሩ ነው ተባለ ለምን እስፖርተኞቹ አላመለጡም? 👉 ነጭ ሽንኩርት ከምግባቸው የማይለያቸው ሀገራት ምነው ተሸነፉ? 👉 ሁሉን እችላለው ምንም የሚያግደኝ የለም ሚመጣውንም አውቃለሁ ያለው አለም በፍርሀት ለምን ተዋጠ? ታዲያ ይሄ መቅሰፍት አይደለም? በፍርሀት የተዋጠው አለም ቤቱን ዘግቶ ተቀምጧል ጊዜው ደርሶ ከቤቱ ሲወጣ አለኝ የሚለው ሀብት/ ኢኮኖሚ/ ባዶ እንደሚሆን ለማስተካከልም እንደሚቸገር ለማወቅ እውቀት አይጠይቅም። ታዲያ ይህ መቅሰፍት አይደለም?
ለይቶ ከሚቀስፍ መቅሰፍት የሚዳነው የእግዚአብሔር ቃል እንደነገረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ወደ እግዚአብሔር በንስሀ በመቅረብ ብቻ ነው ። ሰምቶ ከመጥፋት ያድነን
" አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።" (ኢዮ 2÷12) ደግሞም እንዲህ ይላል "ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዘው ፥ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድ ፥በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ ፥ፊቴንም ቢፈልጉ፥ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥በሰማይ ኾኜ እሰማለኹ፥ኀጢአታቸውንም ይቅር እላለኹ፥ምድራቸውንም እፈውሳለኹ።
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 2 ምዕ 7 ቁ 13-14)
ደግሞም "እሺ ብትሉና ለኔ ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላቹ እንቢ ብትሉ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችዋል" ብሏል ።ስለዚህ ይህን ያመጣብን ሀጢአታችን ፣ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በብሔር መከፋፈላችን ፣ ካህናትን አለማክበራችን ፣ ቃሉን አለመስማታችን ነውና ፡ መድሀኒቱም ወደ እግዚአብሔር መመለስ ንስሐ ገብቶ ከሐጢአት መታጠብና መቁረብ ነው ።
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
💚 @zekidanemeheret 💚
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️ @zekidanemeheret ❤️

"እየጾማችሁ ነውን?"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
እንግዲያስ መጾማችሁን በተግባር አሳዩኝ፡፡ "እንዴት አድርገን እናሳይህ?" ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስላችኋለሁ፡- ድኻው እርዳታችሁን ፈልጎ እንደሆነ ቸርነትን አድርጉለት፤ የጠላችሁትን ሰው ካያችሁት ከእርሱ ጋር ፈጥናችሁ ታረቁ፤ ባልጀራችሁ ተሳክቶለት ስታዩት በእርሱ ላይ ቅናት አትያዙ፤ ቆነጃጅትን በመንገድ ሲያልፉ ስታዩ በዝሙት ዓይን አትመኙ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያደረጋችሁ በትክክል መጾማችሁን አሳዩኝ፡፡
በሌላ አገላለጽ አፋችሁ ብቻ ሳይሆን ዐይናችሁ፣ እግራችሁ፣ እጃችሁ፣ በአጠቃላይ የሰውነታችሁ ሕዋሳቶች በሙሉ መጾም አለባቸው፡፡
+ እጆቻችሁ ከመስረቅና የእናንተ ያልሆነውን ከመውሰድ ይጹሙ፤
+ እግሮቻችሁ የኃጢአት ሥራን ለመፈፀም ከመፋጠን ይጹሙ፤
+ ዐይኖቻችሁ ውጫዊ በሆነ ውበት ምክንያት ከመቅበዝበዝ ይጹሙ፡፡
ጥሉላትን (የፍስክ ምግብ) እየበላችሁ አይደለም አይደል? እንግዲያስ በዐይኖቻችሁም ክፉ ነገርን አትብሉ፡፡ የሚታዩ ነገሮች ለዐይን ምግቦች ናቸውና፡፡ ጀሮዎቻችሁም ይጹሙ፡፡ የጀሮ ጾም ሐሰተኛ ወሬንና ሐሜትን አለመስማትና ይህን የመሳሰለ ነው አንደበታችሁም ከከንቱ ንግግር ይጹም፡፡ ዓሣንና ሌሎች ጥሉላትን ከመብላት ተከልክለን ሳለ ነገር ግን ወንድሞቻችንን በሐሜት የምናኝካቸውና የምንበላቸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው?
ወንድሙን የሚያማና የሚነቅፍ ሰው እርሱ የወንድሙን አካል ያቆስላል፤ ሥጋውንም ይበላል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ይህን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በእርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" /ገላ.5÷15/፡፡ ስታሙ በጥርሳችሁ የወንድማችሁን ሥጋ አትነክሱም፡፡ በክፉ ንግግራችሁ ግን የወንድማችሁን ነፍስ ትነክሳላችሁ፤ ታቆስሉትማላችሁ፡፡ እንዲህ በማድረጋችሁ ራሳችሁን፣ ወንድማችሁንና ሌሎች ብዙ ሰዎችን ትጎዳላችሁ፡፡
አንደበታችሁ ክፉ ነገርን ከመናገር ካልጾመ ጉዳቱ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በሐሜታችሁ እናንተን የሚሰማ ወንድማችሁም የሐሜታችሁ ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርጉታላችሁ ማለት ነው፡፡ እርሱም የራሱን ኃጢአት እንዳይመለከት ስላደረጋችሁት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ በዚህም የሌሎች ወንድሞቹን ድካም እየተመለከተ እርሱ ግን በመጾሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል ስለዚህ አንደበታችሁም ክፉ ከመናገር ይጹም፡፡

🇪🇹ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር🇪🇹
#ክፍል_4
#2 የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
🖊ስም ሲባል አንድ ነገር ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት መጠሪያ ነው ። ስም ጠባይን ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ ሆኖ ሊሰየም ይችላል ። እግዚአብሔርም ባሕርዩን ሕልውናውን ግብሩን የገለፁ ብዙ ስም አለው ። በሐዲስ ኪዳንም እግዚአብሔር ወልድ በስጋ ሲገለጥ #ኢየሱስ #ክርስቶስ
#አማኑኤል ት-ኢሳ ፯÷፲፬ ማቴ ፩÷፳፫ በሚባሉ ስሞች ተጠርቷል።
የእግዚአብሔር ስም ባዶ ቃል አይደለም። ኃይሉን ግርማውን ይዞ ይገኛል ። የማይታየው እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በስሙ አማካኝነት ነው። በተለይም ክርስቶስ በስጋ በተገለጠ ጊዜ ስሙን ለዓለም አስታውቋል ። / ዮሐ ፲፯:፳፮/ ስሙም ከሁሉ በላይ ነው ። /ፊል ፪:፱/ ስሙ #ቅዱስ ነውና አክብረን ልንይዘውና ልንቀድሰው ይገባል እንጂ በከንቱ ልንጠራው አይገባም ።
መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሚያመሰግኑት አምላክ መሆኑን አውቀን ስሙን በከንቱ ከመጥራት ልንቆጠብ ይገባል ። 🖊በማህበር ስንኖር ከሳሽ ተከሳሽ ስለሚኖር የክርክሩ መፈፀሚያ የእውነት ማረጋገጫ መሐላ ስለሆነ ዳኛው እንዲምል ካስገደደው መማል ይፈቀዳል ። /ዘፀ፳፪:፲፩ ዕብ፮:፲፫/ ከዚህ ሌላ ቃል ለመግባት አንድ ነገርን ለመስራት መሐላ መማል ቃል መስጠት የእግዚአብሔር ስም መጥራት የሚያስፈልግባቸው ጊዜ አለ ። እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማገልገል ሲሉ ብፅዓት የሚያደርግ አለ ይኸውም በቤተክርስቲያን ስርዓት የተፈቀደ ነው። ለምሳሌ በድንግልና ለመኖር።
🖊 #በከንቱ_አትጥራ
ከንቱ ማለት በእግዚአብሔር የተናቀ የማይገባ ነገር ማለት ነው ። የእግዚአብሔርን ስም በእንዲህ አይነት ሁኔታ መጥራት እንደማይገባ ይህ ትዕዛዝ ያስተምረናል ። እነሱም ፦
፩.ጣኦትን ማምለክ ኢሳ፵፬÷፱ ፪ነገ ፭÷፲፯
፪.በሐሰት በመማል ት-ዘካ ፭÷፩
፫.በእግዚአብሔር ስም መራገም ማቴ ፭÷፵፬ {የሚያሳድዳችሁን መርቁ እንጅ አትርገሙ ሮሜ ፲፪÷፲፬}
፬.በእግዚአብሔር ስም መጠንቆል ... በነዚህ ሁሉ ስሙን መጥራት በከንቱ መጥራት ነውና በማስተዋል ልንጠብቀው ይገባል።
🖊 #የእግዚአብሔርን_ስም_የምንጠቀመው_ምን_ጊዜ_ነው ?
፩.በፀሎት ጊዜ
፪.በሰላምታ ጊዜ ጴጥ፩÷፩-፪
፫.በአምልኮ ጊዜ ዮሓ ፲፬÷፲፬ መዝ ፻፴፬÷፫
፬.በቡራኬ ጊዜ ኦ-ዘሁ ፮÷፳፪-፳፯ ፪ቆሮ ፲፫÷፲፫
ይቀጥላል....
ለወዳጆችዎ ያጋሩ
👉ለመቀላቀል👇👇👇

ማንም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ
(በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ)
ከመጀመርያ ጀምሮ መልካም ነገርን መምረጥ ክፉ አይደለም፤ በመልካምነት አለመቀጠል ግን ብዙ ወቀሳን ያመጣል፡፡ የብዙ ሰዎች ክፉ መሆን በዚሁ የሚመደብ ነው፤ ብዙዎች ሕይወታቸውን በመልካም ጀምረው በኋላ ግን በክፋት መርዝ ተጠምቀው ሲሰክሩ ተመልክቻለሁና፡፡
እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ፡፡ ምንም እንኳን አሁን ወደ ክፋት ጥልቅ ወርዳችሁ ቢሆንም “ከዚሁ ተመልሰን መነሣት አይቻለንም፤ መለወጥም አይሆንልንም” በማለት ተስፋ የምትቈርጡ አትሁኑ፡፡እናንተ ስትፈቅዱ እግዚአብሔርም ሲረዳችሁ ከክፋት ዐዘቅት መውጣት በእጅጉ ቀላል ነውና፡፡ ከሁሉም በላይ አመንዝራ ተብላ በከተማው ዘንድ ትታወቅ የነበረችውን ሴት በመልካምነቷ እንዴት እንደምትወደስ አልሰማችሁምን? እየነገርኳችሁ ያለሁት በዮሐንስ ወንጌል ላይ ስለተጠቀሰችው ሴት አይደለም፡፡ በእኛ ዘመን ስላለችውና ፍኒሳ ከተባለችው ጋጠ ወጥ ከተማ ስለተገኘችው ሴት እንጂ፡፡ ይህች ሴት አስቀድማ በመካከላችን በአመንዝራነቷ ትታወቅ ነበር፡፡
በክብር ቦታ ሁሉ የመጀመርያን ስፍራ የምትይዝ ሴት ነበረች፤ ስሟ በሀገሩ ሁሉ የገነነ ነበር፤ በእኛ ከተማ ብቻ ሳይሆን በሲልስያ እና በቀጰዶቅያም ጭምር እንጂ፡፡ ይህች ሴት ብዙ ከተሞችን አፍርሳለች፤ የብዙ ወላጅ አልባ ሕፃናትን ንብረት በልታለች፡፡ ብዙዎችም “መተተኛ ናት” ይሏታል፤ ውበቷን ብቻ ሳይሆን መድኃኒትም ጭምር ትጠቀም ነበርና፡፡ ከዚሁ የተነሣ በአንዱ ቀን የንግሥቲቱን ልጅ እስከ ማማለል ደርሳለች፡፡ ጭካኔዋ የክፉ ክፉ ነበር፡፡
ከዕለታት በአንዲቱ ቀን ግን ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ሆኖም ግን በዓይኔ ፍጹም ተለውጣ ራሷን በእግዚአብሔር የጸጋው ዙፋን ፊት ድፍት አድርጋ ስታለቅስ አየኋት፡፡ አሁን የቀድሞ ክፉ ሥራዎቿን ሁሉ እርግፍ አድርጋ ትታለች፤ በእርሷ ላይ ከነበሩት
የአጋንንት ጭፍራ ተፋትታ አሁን የክርስቶስ ሙሽሪት ሆናለች፡፡
በእውነት ከእርሷ የሚከፋ ሰው በዐይኔ አላየሁም፡፡ በኋላ ግን ራሷን ከእንደዚህ ዓይነቱ ክፉ ሥራ ከለከለች፡፡ ከዚህ በፊት ስትለብሳቸው የነበሩት የምንዝር ጌጦች ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ አሁን ግን እነዚህ ሁሉ በእርሷ ዘንድ ቦታ የላቸውም፡፡ እነዚህን ሁሉ አወላልቃ ጥላ ለእግዚአብሔር በሚገባ የማቅ ልብስ ለብሳ ራሷን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር አድርጋለች፡፡ ይህችን ሴት ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ለመመለስ የሀገሪቱ መኳንንት ከዙፋናቸው ወርደው ለምነዋት ነበር፤ ወታደሮች ትጥቃቸውን ታጥቀው በመምጣት አስፈራርተው ሊወስዷት ሞክረው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ሊመልሷት አልተቻላቸውም፤ ከተቀበሏት ደናግላን በዓት ሊያስወጧት አልተቻላቸውም፡፡ ይህች ሴት ከዚያ አስነዋሪ ሕይወቷ ተመልሳ ለቅዱስ ቁርባን በቅታለች፤ ለእግዚአብሔር ጸጋ የተገባ ሆና ተገኝታለች፤ ኃጢአቷን ሁሉ በጸጋው አጥባለች፤ ከተጠመቀች በኋላ ራሷን መግዛት ችላለች፡፡ ይህች ሴት የቀድሞ ሕይወቷን፣ ገላዋን ለብዙ ወዳጆቿ ያሳየችበትን ሕይወት “የእስር ቤት ሕይወት” ብላ ትጠራዋለች፡፡ በእውነት “ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ” የሚለው የከበረው የጌታ ቃል በእርሷ ሲፈጸም አየነው፤ መለወጥ ከፈለግን እኛን ማሰናከል የሚቻለው ኃይል እንደሌለ አወቅን ተረዳን፡፡
እንግዲያስ ተወዳጆች ሆይ! ተስፋ በመቁረጥ በኃጢአት ዐዘቅት ሰምጠን የምንቀር አንሁን፡፡ ከእኛ መካከል በጽድቅ በረሀነት የሚኖር ማንም አይገኝ፡፡ ፊተኛ ነኝ የሚልም ከቶ አይኑር፤ ብዙ አመንዝሮች እርሱን አልፈዉት ሊሄዱ ይችላሉና፡፡ ማንምም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ፤ ከልቡ ከተጸጸተና ከተመለሰ ፊተኛ መሆን ይቻለዋልና፡፡
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- “ይህም ሁሉ ካደረገች በኋላ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፡፡ ነገር ግን አልተመለሰችም” /ኤር.3÷7/፡፡
ወደ እግዚአብሔር ስንመለስ የቀድሞ ኃጢአታችንን
አያስበውም፤ እግዚአብሔር እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለምና፡፡ በእውነት እርሱ በቀድሞ ኃጢአታችን የሚወቅሰን አይደለም፡፡ እርሱ እንደ ሰው አይደለምና፡- “እስከ አሁኑ ሰዓት ወዴት ነበርክ?” የሚለን አይደለም፡፡ ብቻ እኛ እንመለስ እንጂ እርሱ እንዲህ ያለ አምላክ አይደለም፡፡
ይህን እንድናደርግ ሰውን በመውደድ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!

††† መጋቢት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኩትን ሐዋርያ
2.ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት
3.ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት
4."2,000" ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማሕበር)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ)
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
💒✝የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች✝💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡፸፯፥፳፮
"እግዚአብሔር መክፈልትየ ለዓለም እስመ ናሁ እለ ይርኅቁ እምኔከ ይትሐጒሉ ወሠረውኮሙ ለኲሎሙ እለ ይዜምዉ እምኔከ"
#ወንጌል_ማቴ፡ ፱፥፲፬--፲፰
✝✝ዘቅዳሴ💒💒
#ገላ፡ ፩፥፩--፲፩
#ያዕቆ፡ ፪፥፩--፲፬
#ግብሐዋ፡ ፬፥፲፫--፲፱
#ምስ_መዝሙ፡ ፴፫፥፲፩
"ፈሪሀ እግዚአብሔር አምሀርክሙ መኑ ውእቱ ብእሲ ዘይፈቅድ ሐይወ ወያፍቅር ይርአይ መዋዕለ ሠናያተ"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ማር፡ ፩፥፳፫--፳፱
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ቄርሎስ ነው መልካም በዓል ይሁንልን ።
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

እስቲ እንዲህ እያልን እንጸልይ !!
*~★★★~*
• አትፍሩ ለጓደኞቻችሁ በሙሉ #SHARE አድርጉት።
አትፈሩም። አትሳቀቁ።
#ETHIOPIA | ~ ይህቺ አጭር ጸሎት ናት። ማታ ከመኝታ በፊት
ጸሎት የጀመርን የተዋሕዶ ልጆች ይህቺን አጭር ጸሎት በጸሎታችን
ማሳረጊያ ላይ ሰብሰብ ብለን በጋራ በአንድ ድምጽ ብንጸልያት
መልካም ነው። በቃላችን ልንይዘው የምንችለው አጭር ጸሎት
ነው። አይጎዳንም አያደክመንም። ሌላ ሌላውን ደግሞ እያየን
እንጨምራለን።
•••
ፍጹም በሆነ ሙሉ እምነት፥
ፍጹም በተመስጦ ልቦና ፥
በፍጹም መጸጸት ፥ በንፁህ ልቦና
እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐተ ስግደተ (×፫)
እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ
ይሤለሱ በአካላት ወይትወሐዱ በመለኮት
እሰግድ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ
ክቡር
መስቀል ኃይልነ፥
መስቀል ጽንዕነ፥
መስቀል ቤዛነ፥
መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ፥
አይሁድ ክህዱ ንኅነሰ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ
•••
አምላኬ ሆይ
ስላደረግህልኝ ነገር
ስለምታደርግልኝ ነገር
ስላላደረክልኝና ስለማታደርግልኝም ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ።
ምንም ብበድልህ በፍጹም ቸርነትህና ፍቅርህ ጠብቀህ በሕይወቴ
ላይ ይቺን ሰዓት ጨምረህ በተቀደሰው ስፍራህ ስላቆምከኝ
አመሰግንሃለሁ።
መላእክትን በጽርሃ አርያም፥
ሰማዕታትን በደም፥
ሐዋርያትን በአጽናፈ ዓለም፥
ጻድቃንን በገዳም ያጸናህ አምላክ፥ እኔንም በሃይማኖት በጾም
በጸሎት በምግባር እንድታጸናኝ እለምንሃለሁ።
አምላኬ ሆይ ምንም ዓይነት ፈተና ቢመጣብኝ እስከ መጨረሻዋ
የህይወቴ ህቅታ ድረስ አንተን በማመን እንድታጸናኝ፣ በሕይወቴ
ሁሉ አንተን በመፍራት እንድኖር፥ ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና
ዕድሜ ለንስሐና ለቅዱስ ቁርባን እንድታበቃኝ እለምንሃለሁ፡፡
•••
እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ፥ የእናት ልመና ፊት
አያስመልስም፥ አንገትም አያስቀልስምና ከልጅሽ ከወዳጅሽ
ተማልደሽ አማልጅኝ።
ለአባ ህርያቆስ
ለአባ ኤፍሬም
ለቅዱስ ያሬድ
ለቅዱስ ደቅስዮስ
ለበላኤሰብ የተለመንሽ እመአምላክ ለእኔም ለደካማው ለጎስቋላው
ባሪያሽ ተለመኝኝ።
እናቴ ሆይ ምስጋናሽ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ
ተመግቤው እንደ ውኃ ጠጥቼው እኖር ዘንድ እርጅኝ።
የኔ ኃጢአት ያንቺን ንጽህና አያረክሰውምና በብርሃን እጆሽሽ ዳሰሽ
ለነፍሴ የድኅነትን ምክንያት ሁኚያት።
•••
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እስራኤላውያንን ከግብፅ
ባርነት መርተህ ያወጣህ እኔንም ከዚህ ዓለም ባርነት ነፃ
እንድታወጣኝ እለምንህሃለሁ።
የባህራን ወዳጅ የአፎምያ ረዳት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እኔን
ደካማው አገልጋይህን እርዳኝ
የሚፈታተነኝን ሰይጣን ዲያቢሎስን በበትረ መስቀልህ ከእግሬ ስር
ቀጥቅጠህ እንድትጥልልኝ በሄድኩበትም ሁሉ እንድትጠብቀኝ
እማፀንሃለሁ፡፡
•••
አምላከ ነቢያት፥
አምላከ ሐዋርያት፥
አምላከ ደናግል፥
አምላከ መነኮሳት
ለቅዱሳንህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ ፥ ለያዕቆብ የገባሃውን ቃልኪዳን
አስበህ እንደ ክፋቴ፣ እንደ ጥፋቴ፣ እንደ በደሌ ሳይሆን እንደ
ቸርነትህ ትምረኝ ዘንድ ቤተሰቦቼን፣ ሃገራችንን ህዝባችንን፣
ቤተክርስቲያናችንንና ሃይማኖታችንን ትጠብቅልን ዘንድ
ዝማሬ ዳዊትን፣
ተልዕኮ አርድዕትን ፤
ቅዳሴ መላዕክትን ፤
መስዋዕተ አቤልን ፤
ዕጣነ ዘካርያስን የተቀበልክ አምላክ የኔንም ጸሎት ትቀበል ዘንድ
እለምንሃለሁ
• አባታችን ሆይ……

እንደምን አረፈዳችሁ 🙏🙏🙏ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ ካላችሁ 👉ኢዮአታም👈 ላይ አድርሱን፡፡የእናንተ አስተያየት ብዙ እንድንሰራ ስለሚያደርገን ቸል አትበሉ 👉ኢዮአታም👈 ላይ አድርሱን፡፡
=>መጋቢት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
2.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
3.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
4.ቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሳሌም
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
💒✝የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች✝💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡ ፹፫፥፮
"እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"
#ወንጌል_ማቴ፡ ፮፥፩--፲፯
✝✝ዘቅዳሴ💒💒
# ገላ፡ ፮፥፩--ፍ.ም
#ያዕቆ፡ ፬፥፩--፲፩
#ግብሐዋ፡ ፬፥፩--፲፫
#ምስ_መዝሙ፡ ፶፱፥፬
"ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቀሥት(ቅስጥ) ወይድኅኑ ፍቁራኒከ"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ማቴ፡ ፲፯፥፳፬--ፍ.ም
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ነው መልካም በዓል ይሁንልን ።
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
1.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
2.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
3.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
4.ቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሳሌም
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
💒✝የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች✝💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡ ፹፫፥፮
"እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"
#ወንጌል_ማቴ፡ ፮፥፩--፲፯
✝✝ዘቅዳሴ💒💒
# ገላ፡ ፮፥፩--ፍ.ም
#ያዕቆ፡ ፬፥፩--፲፩
#ግብሐዋ፡ ፬፥፩--፲፫
#ምስ_መዝሙ፡ ፶፱፥፬
"ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቀሥት(ቅስጥ) ወይድኅኑ ፍቁራኒከ"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ማቴ፡ ፲፯፥፳፬--ፍ.ም
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ነው መልካም በዓል ይሁንልን ።
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
🇪🇹ፀሎታችን ለምን አይሰማም🇪🇹
1.የተቸገሩ ሰዎችን የማንረዳ ከሆነ፡-
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :-
🖊 ''ሰው የድኾችን ጩኽት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም'' ምሳሌ 21÷13
🖊ስለዚህ የደሀን ለቅሶ የማንሰማ ከሆነ እግዚአብሔርም የኛን ጩኸት አይሰማም ።
2. ሚስት ባሏን የምትበድል ከሆነ ወይም ባል ሚስቱን የሚበድል ከሆነ
🖊 ''በተመሳሳይም እናንተ ባሎች ከእነሱ ጋር በእውቀት አብራችሁ ኑሩ ። እነሱም ከእናንተ ጋር የሕይወትን ጸጋ አብረው ስለሚወርሱ ጸሎታችሁ እንዳይታገድ ከእናንተ ይበልጥ እንደ ተሰባሪ ዕቃ የሆኑትን ሴቶችን አክብሯቸው ''
1ኛ ጼጥሮስ 3÷7
3. በመጠራጠርና ባለማመን ስንጸልይ፦
🖊 ''ነገር ግን አምኖ ይለምን፤ አይጠራጠርም፤ የሚጠራጠር በነፋስ የሚገፋና የሚነዋወጥ የባሕር ማዕበልን ይመስላልና:: ለዚያ ሰው ከእግዚአብሔር ምንም የሚያገኝ አይምሰለው''
ያዕቆብ 1÷6
5.የሰራናቸውን ጥሩ ስራዎች እግዚአብሔር እንዲያስታውስልንና በዚህም ልጁ እንደሆንን እያሰብን የምንፀልይ ከሆነ፦
🖊ይህ ግብዝነት ነው፡፡ ስንፀልይ ሀጢያቶቻችን እያስታወስንና እየተናዘዝን እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት የማንረባ መናኛ እንደሆንን እያሰብን መፀለይ ይኖርብናል፡፡
5. ከተጣላነው ሰው ጋር ሳንታረቅ የምንጸልይ ከሆነ:-
🖊 ጸሎታችን እንዲሰማ የበደልነውን ሰው ይቅርታ መጠየቅና የበደሉንንም ይቅር ማለት አለብን ።
6. የሰውን እቃ ሳናስፈቅድ ከወሰድን፦
🖊 ይህን እግዚአብሔር እንደ ሌብነት ይቆጥረዋል ። ስለዚህ ጸሎታችን እንዲሰማ እቃውን ሳናስፈቅድ የወሰድንበትን ሰው መጀመሪያ ማሳወቅ ይኖርብናል ።
7. ችግሮቻችንን እየቆጠርንና እግዚአብሔርን እያማረርን ስንጸልይ፦
🖊ጸሎታችን እንዲሰማ ምንም እንኳ ችግሮች ቢኖርብንም እግዚአብሔርን እያመሰገንን መጸለይ ይኖርብናል ።
8. አንድን ነገር ለማግኘት ብለን ካገኘነውም በኋላ ሰዎች እንዲያይሉን ብቻ ብለን የምንጸልይ ከሆነ ፦
🖊 '' ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፤ ለራሳችሁ ሥጋዊ ደስታ በማሰብ በክፉ ምኞት ትለምናላችሁና '' ያዕቆብ 4÷3
9.እግዚአብሔርን ባለማመስገን እና በሚስጥር የተደበቀ ሀጥያትን ይዞ የሚጸለይ ጸሎት ዋጋ አይኖረውም ።
10.የጎዱንና የሚያሳድዱንን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲበቀልልን የምንጸልይ ከሆነ፦
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል
🖊 ''እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ '' ማቴ 5÷44
11.ሁልጊዜ በሃጢአት የምንኖር ከሆነ :-
🖊ጸሎታችን እንዲሰማ ቅድስናን መምረጥና ሀጥያትንም መጸየፍ ይኖርብናል ።
12.ምናልባት ጸሎታችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ካልሆነ፦
🖊ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ፈቃድ በህይወታችን እንዲሆን መጸለይ አለብን ።
13. ያለ ትዕግስትና ቶሎ ተስፋ በመቁረጥ የምንጸልይ ከሆነ፦
🖊ጸሎታችን በትእግስት ፣ባለመሰልቸትና ባለማቋረጥ መሆን አለበት ።
14.የበደሉንን ይቅር ሳንል ቂም ይዘን ምንጸልይ ከሆነ ፦
ክርስቶስ እንዲህ ብሏል 🖊ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት'' ማር 11÷25
15.በጸሎታችን እግዚአብሔርን ያልጠየቅነውን መልስ እንዲሰጠን ስንፈልግ ፦
🖊እግዚአብሔር ያልጠየቅነውን አይመልስልንም ።
16.የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ቀን ማወቅ ስለማንችል፦
🖊አንዳንድ ጸሎቶቻችን አይሰሙም ። ምክንያቱም እግዚአብሔር የራሱ ቀን ስላለው
17.ሁልጊዜ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት ከሌለን፦
🖊''እናንተ ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ከጠበቃችሁና ቃሌ በልባችሁ ከኖረ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ብትጠይቁ ይፈጸምላችኋል''
ዮሐ 15÷7
18. ልክ እንደ ግብዞች ሰው እንዲያይልን ብለን የምንጸልይ ከሆነ፦
🖊“በተጨማሪም በምትጸልዩበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነሱ ሰዎች እንዲያዩአቸው በምኩራቦችና በየአውራ ጎዳናው ማዕዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና። እውነት እላችኋለሁ፣ እነሱ ሙሉ ብድራታቸውን ተቀብለዋል ''
ማቴ 6÷5
19.ከሰው ጋር ተጣልተን በንዴት የምንጸልይ ከሆነ

#ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር
#ክፍል_5
#3የሰንበትን_ቀን_ትቀድሰው_ዘንድ_አስብ
🖊 የቃሉ ትርጉም አቆመ አረፈ ማለት ነው ። ይህ ማለት የሰው ልጅ ከጌታ ጋር የሚቀራረብበት መገናኛ መንገድ ነው ። ከማንኛውም ስጋዊ ተግባር የምናርፍበት ፣ ትርጓሜው የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናስታውስ የሚያደርግበት ቀን ነው ።
🖊 #ሰንበት የመንግስተ ሰማይ ምሳሌ ነች። የሰው ልጅ በዓለም ሠርቶ ወርዶ በመልካም ሥራው የሚያርፍበት ቦታ ናት ።
🖊ሰው ዕረፍት ያስፈልገዋል የሰንበት ቀን የተፈጠረውም ለዚህ ነው ። የሰንበት ቀን የዕረፍት ቀን ስለሆነ የሚከተሉትን ሁለት ነገሮች ያሳስበናል ።
#፩ኛ ሰው በኀጢአት ከመውደቁ በፊት ከአምላኩ ጋር ያለውን ግንኙነት የነበረውን ዕረፍት
#፪ኛ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን ዘላለማዊ የነፍስ እረፍት ።
🖊በሐዲስ ኪዳን ሰንበት ሁለት ናቸው #ቅዳሜና_እሁድ ። #ቅዳሜ ማለት የበፊቷ የቀደመችው ማለት ነው ። #እሑድ ማለት ደግሞ መጀመሪያ 🖊ስለሆነ ከዚህ ጀምረን ስንቆጥር ቅዳሜ ሰባተኛ ቀን ይሆናል ። በ፫ኛው ትዕዛዝ እንዲከበር የታዘዘው ይህ ቀን ነው ። ፈሪሳውያን በሰንበት ቀን እግር ከዘረጉ አያጥፉም ፣ ከአጠፉም አይዘረጉም መልካምም ሥራ ቢሆን አይሰሩም ።
#እሑድ ሥነፍጥረት የጀመረበት ፣ ኀላም ጌታ የተነሳበት፣ መንፈስቅዱስ የወረደበት እንዲሁም ጌታ የሚመጣበት ዕለት ነው ። ስለዚህ እናከብረዋለን ። በቤተክርስቲያን ታሪክ ደግሞ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ቀን ስለሆነች ሥራ እንዳይሰራ በ፫፻፳፩ ዓ-ም በሕገመንግስቱ አፅድቆ እንዳወጀና እንደወሰነ ይነገራል ። ስለዚህ ሰንበት የእረፍት ቀን ነው ስለተባለ ሥራ ፈተን መዋል የለብንም ። በእግዚአብሔር ቤት በመገኘት ማስቀደስ ፣ ቃሉን መማር ፣ መዘመርና ማመስገን አለብን ። ከዚህም ሌላ ጌታ በሰንበት መልካም ሥራ ማድረግ ተፈቅዷል ስላለ የታመመና የታሰረ መጠየቅ ፣ የተጣላ ማስታረቅ ፣ ያዘነ ማፅናናት ፣ ለተቸገረ ደግሞ ምፅዋት መመፅወት አለብን ። እንግዲህ በክርስትና ሰንበት የሚከበረው እንዲህ ነው ።
🇪🇹ሠንበትን ለምን እናከብራለን
፩ ፦ከቀናት ሁሉ ተለይታ ለበረከት ለቅድስና ለማመስገን ትሆን የተፈጠረች ነች
፪ ፦ሰውን ስለ ወደደ ለዕረፍት የሠራት ቀን ናት
፫ ፦በእግዚአብሔር ና በህዝብ መካከል ምልክት ናት
፬ ፦የሚያምን ከማያምን መለየት ኩፋ ፫÷፭-፱
፭ ፦እግዚአብሔር አምላክ ለህዝቡ የሠጠው የመጀመሪያው ህግ ናት ዘፍ፲፮÷፳፫
ይቀጥላል...
Share👇share👇share

††† መጋቢት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አሌፍ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱስ ቴዎቄጤኖስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ባስሊዖስ (ዻዻስና ሰማዕት)
4.አባ ኤፍሬም ሰማዕት
5.አባ ኤልያስ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
5.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
💒✝የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች✝💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡፬፥፯
"እምፍሬ ሥርናይ ወወይን ወቅብዕ በዝኀ በሰላም ቦቱ እሰክብ ወእነውም እስመ አንተ እግዚኦ በተስፋ ባሕቲትከ አኅደርከኒ "
#ወንጌል_ሉቃስ፡ ፭፥፴፮--ፍ.ም
✝✝ዘቅዳሴ💒💒
#ቲቶ፡ ፩፥፩--፮
#ያዕቆ፡ ፪፥፲፬--ፍ.ም
#ግብሐዋ፡ ፳፯፥፳፪--፳፯
#ምስ_መዝሙ፡ ፳፭፥፩
"ፍታህ ሊተ እግዚኦ እስመ አንሰ በየውሃትየ አሐውር ወተወከልኩ በእግዚአብሔር ከመኢይድክም ፍትነኒ እግዚኦ ወአመክረኒ"
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ማቴ፡ ፲፰፥፩--፲፪
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ዘባስልዮስ ነው መልካም በዓል ይሁንልን ።

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር
#ክፍል_6
#4 አባትህንና_እናትህን_አክብር
🖊ለሰው ልጅ ከተሰጠ ህጉች የመጀመሪያው ህግ ነው። ዘፀ ፳፩÷፲፭
🖊ይህ ትዕዛዝ የፍቅረ ቢፅ መጀመሪያ ነው ። አባትና እናት ሲል የወለዱንን ብቻ ሳይሆን በአርአያ #ሥላሴ የተፈጠረ ሁሉ እንድናከብር ነው ። እነዚህም የሥጋ አባቶችና የመንፈስ አባት በማለት ለሁለት ይከፈላሉ። #1.የስጋ አባት የምንላቸው ፦
-ወላጆቻችን
-የቀለም አባቶች
-የሀገር መሪዎች
-ሽማግሌዎች
-የጡት አባት/እናት
-የእንጀራ አባት/እናት ፣
-አሳዳጊዎች
ምሳ፮÷፳ ዘፀ፳÷፳፪ ኤፌ፫÷፩-፫ ምሳ፳፫÷፳፭
#2.የመንፈስ_አባት ፦
-የንስሀ አባት
-ካህናት
-ሰባኪ ወንጌሎች
-የክርስትና እናትና አባት
-ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ናቸው። 🖊አክብር ማለት መውደድ ፣ መታዘዝ ፣ መርዳት ፣ አለማቃለል ማለት ነው ። በሁሉ ለወላጆቻችሁ ሲል በሁሉ የሚለው ቃል ብዙ ነገሮችን ያመለክታል። ይኸውም #ሀ ምክራቸውን በመስማት
#ለ በተቸገሩ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን በመስጠት
#ሐ በሌላቸው ጊዜ የሚረዱበትን መንገድ ማዘጋጀት
#መ በጠቅላላው ለወላጆች ብድራትን መመለስ ። ወላጆቻችንም ሆኑ ሌሎችን የሥጋና የመንፈስ አባቶችን ሲኖራቸውም ፣ሲያጡም ፣ ጤና ቢሆኑ ፣ ቢታመሙም ፣ባረጁ ጊዜ ልንረዳቸውና ልናከብራቸው ይገባል። ይሁንና ወላጆችም ሆኑ ሌሎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣላና የሚያጋጭ ትዕዛዝ ቢያዙን ግን እንቢ ልንላቸው ይገባል።
ይቀጥላል.....
share👇share👇share

††† መጋቢት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት (ደንግልናው የተገለጠበት)
2.ቅድስት ልዕልተ ወይን
3.ቅዱስ መላዚ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት (ጠንቁዋዩን በለዓምን የገሰጸበትና አህያዋን እንድትናገር ያደረገበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
💒✝የዕለቱ ምንባባት እና ምስባኮች✝💒
#ዘነግህ_(የጠዋት)ምስ.መዝሙ፡፻፥፮
"አእይንትየሰ ኀበ መሃይምናነ ምድር ከመ አንብሮሙ ምስሌየ ዘየሐውር በፍኖት ንጽሕ ውእቱ ይትለእከኒ ወሶበ ርእየ ብዙኃነ አሕዛብ"
#ወንጌል_ማቴ፡ ፭፥፩--፲፯
✝✝ዘቅዳሴ💒💒
#፩ቆሮ፡ ፯፥፩--፰
#፪ጴጥ፡ ፪፥፱--ፍ.ም
#ግብሐዋ፡ ፳፯፥፩--፲፩
#ምስ_መዝሙ፡ ፴፫፥፯
"ይትዐየን መልአክ እግዚአብሔር ዐውዶሙ ለእለ ይፈርሀዎ ወያድኅኖሙ ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር'
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
#ወንጌለ_ማቴ ፡ ፲፰፥፲--፳፩
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
#የሚቀደሰው_ቅዳሴ_ያዕቆብ ዘሥሩግ መልካም በዓል ይሁንልን ።

ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ ካላችሁ 👉@zetaodokos👈 ላይ አድርሱን፡፡የእናንተ አስተያየት ብዙ እንድንሰራ ስለሚያደርገን ቸል አትበሉ 👉@zetaodokos👈 ላይ አድርሱን፡፡
✍ይድረስ ለኮሮና
🙏እስኪምረን ድረስ🙏
የእናታችን የማርያምን ታሪክ እየሰማን ነው ያደግነው፡፡ አክስሞ የሚያስቀር ማየ ዘለፋን ብትጠጣም ፊቷ እንደፀዳል ማብራቱን ሰምተናል እናምናለንም፡፡
@zekidanemeheret
የጊዮርጊስን ታሪክ በልቤ ቀርጫለሁ ፡ የጠጣው መርዝ እንደ ውሃ ሁኖ ሰውነቱን እንዳልጎዳው ሞቱን እንዳላፋጠነው ሰምቻለሁ አምናለሁ፡፡
@zekidanemeheret
እንደ ንጽሕት ድንግል ማርያም በንጽሕና አላጌጥንም ይሆናል፡ እንደ ጊዮርጊስ ለልዑል አምላክ ራሳችንን አልሰጠን ይሆናል ዳሩ ግን ከሰነፍ ሰውነታችን የምትንጠፈጠፍ ጥቂት እምነት አለች፡፡
@zekidanemeheret
ጸሎታችንም በከመ ምሕረትከ ናት፡፡ እስኪምረን ድረስ በደላችን ቀሎ እስከ አመ ይሰአለነ ወደፊቱ እንወድቃለን፡፡
@zekidanemeheret
ከመ መጻጉዕ ተስፋ የሚያስቆርጡ 37 ዓመታት አልፈው በ38ኛው ዓመት እስኪምረን ድረስ እንማልደዋለን፡፡
@zekidanemeheret
ከተኛንበት የመከራ አልጋ እስከሚያነሣን ድረስ በእምነት እንጠብቃለን
@zekidanemeheret
እጆቻችንን ከእድፍ ልቦናችንን ከኃጢአት እያጠብን እስኪምረን ድረስ በቃልኪዳናቸው
በእንተ ማርያም
በእንተ ጊዮርጊስ
በእንተ አቡነ ሀብተ ማርያም እያልን እንለምነዋለን፡፡
@zekidanemeheret
እም አይቴ ይምጻእ ረድኤትየ
ረድኤትየሰ እም ኀበ እግዚአብሔር
ዘገብረ ሰማየ ወምድረ

††† መጋቢት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ-ስደቱ)
2.ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ
3.40 ቅዱሳን ሰማዕታት (ከሃገረ ስብስጥያ)
4.ቅዱስ ዲዮናስዮስ (ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
🔔 ግጻዌ 🔔
፨ ዘደብረ ዘይት ፨
📜 ምንባብ ወምስባክ ዘመጋቢት ፲፫ (13) 📜
🎚 መዝሙር ዘደብረ ዘይት እንዘ ይነብር እግዚእነ 🎚
📢 የዕለቱ ምስባክ
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ ፡፡
ወአምላክነሂ ኢያረምም ፡፡
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ ፡፡
መዝ ፵፱፥፫
ትርጒም፦ እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል ፡፡
አምላካችን ዝም አይልም ፡፡
እሳት በፊቱ ይነዳል ፡፡
📖 የዕለቱ ወንጌል 📖
፨ ማቴዎስ ፳፬ ፥ ፩ - ፴፮ ( በምስራቅ ይነበባል )
📚 የቅዳሴው አይነት 📚
፨ ዘአትናቴዎስ

#እመን
አንድ የተነፉ ፊኞችን በመሸጥ የሚተዳደር ሰው ነበር። ገበያ ሲቀዘቅዝበትም ፊኞችን እየነፉ ወደ ላይ ይለቃቸዋል ። ልጆችም ያንን ሲያዩ መጥተው ይገዙታል ። ይህንን ተግባሩን ከሩቅ ሆኖ ሲመለከት የነበረ አንድ ህፃንም ወደሱ ቀረብ ብሎ ጥቁር ፊኛም እንደነሱ በአየር ላይ መንሳፈፍ ይችላል ? ብሎ ጠየቀው ። ሰውዬውም ማሙሽዬ ፊኞቹ በአየር ላይ እንዲንሳፈፉ የሚያደርጋቸው እኮ ቀለማቸው አይደለም ። በውስጣቸው ያለው አየር ነው አለው ። እኛንም በህይወት ላይ በኑራችን በስራችን በምናደርጋቸው ነገሮች ላይ በስኬትና በአሸናፊነት እንድንንሳፈፍ የሚያደርገን ውስጣችንን የሞላው እምነታችንና አመለካከት ነው። መልካም ነገሮች ሁሉ ይገቡኛል ። ጥሩ ስራ ጥሩ ፍቅረኛ መልካም ትዳር ይገቡኛል የሚል እምነት ያስፈልገናል። መፅሀፉስ ቢሆን " አለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው " ፣ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አይደል የሚለው ። ወዳጄ አንተ ነኝ የምትለውን አይደለህም አንተ ሰዎች ነህ የሚሉህንም አይደለህም በቃ አንተ ማለት ፈጣሪ ነህ ያለህን ነህ ። ፈጣሪ ለትልቅ ነገር እንደ ፈጠረህ እመን። እኔ አልረባም ዋጋ የለኝም አትበል ። የደም ዋጋ ተከፍሎልሀል። ብኖር ባልኖር ማልጠቅም ሰው ነኝ አትበል ። 1 ጄኔራል ታንከኛ በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ እግረኛ ልኮ ወታደሮቹን አያስፈጃቸውም ። ከጀነራል በላይ ሚያስበው ፈጣሪም በማታስፈልግበት ጊዜ ላይ አምጥቶ አያስፈጅህም። አንተ አሁን የተፈጠርከው አንተ የምታስፈልግበት ጊዜ አሁን ስለሆነ ነው በፈጣሪህ እምነት ይኑርህ ። በራስህ ተማመን ። ለትልቅ ህይወት እንደ ተፈጠርክ አስብ ። ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ እስከ ሞት የወደደክ አምላክህ በሚሻግት እንጀራ በሚቀደድ በሚቀየር ብር አይጠረጠርም ። እመን መልካም ነገሮች ሁሉ ይገቡሃል ።

+++አባቶች ስለ ጸሎት እንዲህ አሉ!+++
+ ሰው ጸሎትን በተወ ጊዜ የሞት መሣሪያውን መሥራት ይጀምራል።
(ከአበው አንዱ)
@zekidanemeheret
+ ሁልጊዜ ጸሎት ለማድረግ የሚታገል ሰው በመለኮታዊ ኃይል የተቃጠለ ፤ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ በመንፈሳዊ ፍቅር በጽኑዕ የሚፈልግ ይሆናል።
(ቅዱስ መቃርዮስ)
@zekidanemeheret
+ የጸሎትን በትር በእጃችሁ ከጨበጣችሁ አትወድቁም ፤ ብትወድቁም አወዳደቃችሁ ለሞት የሚያደርስ አይሆንም።
(ቅዱስ ዮሐንስ ቅሊማቆስ)
@zekidanemeheret
+ ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ጸሎትን የማታደርግ ነፍስም ሕይወት የላትም።
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
@zekidanemeheret
+ የማይጸልይ ሰው ቅጽር የሌላት ሀገርን ይመስላል። ያቺን ሀገር ማንም እየገባ እንደሚዘርፋት ፤ እርሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል።
(ማር ይስሐቅ)
@zekidanemeheret
+ አንድን መልካም ነገር ከግብ ለማድረስም ሆነ ቀና እርምጃዎችን ለመውሰድ መጀመሪያ መሆን የሚገባው ጸሎት ነው።
(ቅዱስ መቃርዮስ)
+++
@zekidanemeheret
ለመብላት ፣ ለመጠጣት ፣ ለመማር ፣ ለመሥራት ፣ ለመዝናናት እና ለብዙ ጉዳዮች ጊዜ ኖሮን ፤ ለጸሎት "ጊዜ የለኝም" ለምንል ለእኛ ፤ ብጹእ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንዲህ ይጠይቁናል . . . "ባርያ ለጌታው ፤ እንዴት ጊዜ የለኝም ይላል?"
@zekidanemeheret
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

#ክፍል_7
@zekidanemeheret
#5 አትግደል
🖊ይህ ትዕዛዝ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት አትግደል ማለት ነው።ይህም ማለት የሥላሴን መቅደስ አታጥፋ ማለት ነው።
🖊ኃጥያት በሦስት መንገድ ይሰራል
፩፦በመናገር
፪፦በተግባር
፫፦በማሰብ ናቸው።
🖊ሕይወት በአጋጣሚ ፣ በልማድና በእንዝሕላልነት የምትገኝ አይደለችም። ሕይወት ለራሱ ምክንያትና አስገኝ ከሌለው እግዚአብሔር የተገኘች ገንዘብ ነች። ሕይወትን ማንም ሊያዝባት እንደፈለገው ሊያደርጋት አይችልም። ለምን ? የእርሱ አይደለችምና ለዚህ ነው #አትግደል የተባለው ።
🖊መግደል ማለት በተለያዩ መንገዶች ተጠቅሞ የሰው ሕይወት እንዲሞት ማድረግ ነው ።
🖊መግደል ከውስጥ ከሰው የሚወጡ ሰውንም የሚያረክሱ ብሎ ጌታችን ከዘረዘራቸው ክፉ ሥራዎች አንዱ ነው ። ማቴ፲፭:፲፱ ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ ላይ ከዘረዘራቸው ፲፮ የስጋ ስራዎች አንዱ መግደል ነው ።
🖊በሕይወት ላይ ስልጣን ያለው #እግዚአብሔር ብቻ ነው ። ሰውን ቢያድንም ቢገድልም ስልጣኑ የእርሱ ብቻ ነው ።
🖊መግደል ሲባል ፊት ለፊት ሄዶ የሰውን ሕይወት ማጥፋት ብቻ ሳይሆን ሰውን ለሞት የሚያበቁትን ነገሮች ሁሉ ነው ። ይኸውም፦
#ሀ በተለያዩ ሁኔታ (በቃላትና በመጠቆም) አጥፊውን መርዳት
#ለ የሰው ሕይወት ሊድን የሚችልበትን መረጃ በመከልከል #ሐ በሽታና ድካምን ሌላም ችግርን እያዩ ለሞት የሚያደርስ ስራ ማሰራት
#መ ለሞት የሚያደርስ ረሀብና ጥም አይተን አለመርዳት
#ሠ ሰውን በስጋ ብቻ ሳይሆን በነፍሱ መከራ የሚያመጣበትን መንገድ መፍጠር መግደል ነው ።
#ረ ዓለማውያንን በመንፈስ ባዶ ቀፎ ሆነው የተበላሹትን ወደ እናት ቤተክርስቲያን አለማምጣት ነፍስን መግደል ነው ።
🖊ወደ መግደል የሚያደርሱ ብዙ ነገሮች አሉ እነሱም ፦
#ቅንዓት
#ምቀኝነት
#ስድብ
#ጥላቻ
#ቁጣ ጥቂቶቹ ናቸው።
🖊 እራሳችንን በመግዛት እና ወንድማችንን በመውደድ ከዚ ድርጊት ልንቆጠብ ይገባናል። መሞት እንደማንፈልገው ሁሉ የሰው ነፍስ ማጥፋት የለብንም።
@zekidanemeheret
ይቀጥላል....
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት

አምስተኛ ሰንበት(ሳምንት)
፨፨፨፨፨፨፨፨✞፨፨፨፨፨፨፨
ደብረ ዘይት ተብሎ ይታወቃል።
በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም
ምፅአቱ) ይሰበካል። ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ
መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል፡፡