Sime Tech
486 subscribers
139 photos
5 videos
221 files
123 links
በቻናሉ ውስጥ
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች
📢 ተወዳጅ አፖች
📢 የሶፍትዌር ትሪኮች
📢 የwebsite ጥቆማዎች
📢 የኮምፒውተር ትምህርቶች
📢 የሳተላይት ዲሽ መረጃ
📢 በቪዲዮየተደገፉ
📢የTech መረጃዎችንና
📢ሌሎች ትምህርቶችን በስፋትና በጥራት
ያገኛሉ
Download Telegram
ስለ VLC Media (ቪዲዮ) ማጫወቻ #ስውር እና #ድብቅ 5 ነገሮች!!

1. የኮምፒውተሮን ዴስክቶፕ መቀረፅ
የኮምፒውተሮን ዴስክቶፕ በመቅረፅ እንደ screen recorder ያገለግለናል፡፡ይህን ለማከናወን VLCን በመክፈት Media ከዛን Convert/Save በመንካት ከሚመጣው ሳጥን Capture Device ታብን በመምረጥ Capture mode ሳጥን ውስጥ ካሉት ዝርዝር ውስጥ ዴስክቶፕ (Desktop)የሚለውን ምርጫ በማድግ መቅዳት ይቻላል፡፡ desired frame rate for the capture ከሚለው ፍሬም ሬቱን 15 በማድረግ ወይም ደግሞ 30 ለፈጣን እንቅስቃሴ አድርገን መቅረፅ እንችላለን፡፡

2. የቪዲዮ ፋይል ፎርማት ወይም ይዘትን መቀየር Convert Video
Media የሚለውን ሜኑ በመምረጥ ካሉት ዝርዝሮች Convert/Save ላይ አድርገን file ታብ ላይ Add የሚለውን በመምረጥ የምንፈልገውን የቪዲዮ ፋይል አስገብተን ወደ ምንፈልገው file format መቀየር እንችላለን፡፡

3. የ YouTube ቪዲዮችን ማጫወት እና ዳውንሎድ ማድረግ (Play and (Safely) Download YouTube Videos)
ይህ ሲባል በቀጥታ የYouTubeን ቪዲዮ ዳውንሎድ ማድረግ ሳይሆን በቅድሚያ ከ YouTube ሊንኩን ኮፒ አድርገን VLC ላይ File ውስጥ Open Network Stream በመክፈት ቪዲዮውን ማጫወት ይቻላል፡፡

ይህንን ቪዲዮ ዳውንሎድ ለማድረግ ደግሞ እየተጫተ Tools ውስጥ በመግባት Codec Information የሚል ዝርዝር በመጫን ከሚከፈተው ቦክስ ወይም ዲያሎግ ከስር Location box ውስጥ ያለውን ሊንክ ኮፒ በማድረግ የሚንጠቀመውን ብሮውሰር (browser) ክሮም ወይም ሞዚላ ላይ እንዲሁም ላይቭ እንድንሰማ አገልግሎትን ይሰጠናል፡፡ View ውስጥ በመግባት Playlist የሚለውን ዝርዝር እንነካለን፤ በመቀጠልም ወደ ታች ስንወርድ Podcasts በመንካት የ “+” ምልክት በመጫን የምንፈልገውን ሊንክ ማስገባት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ This American Life , TED Radio Hour የመሳሰሉ አሉ ወይም ይህን ሊነክ ተጭነው የማያቋርጥ ሙዚቃዎችን ያዳምጡ፡፡
ተከታታዮቻችን እነዚህ የVLC # ስውር እና # ድብቅ 5 ነገሮች ብለን የቀረቡት ነጥቦች ምርጦቹን ሲሆን VLC ብዙ #ስውር እና #ድብቅ የሆኑ ጥሩ ፊቸሮች (features) አሉት፡፡ለዛሬ እናነተ የምታውቋቸውን ስውር እና ድብቅ ነገሮች በኮሜንት ላይ ያካፍሉን፡፡
◄◄ሼር▻▻ይደረግ ብዙ ማወቅ የሚፈልጉ
#ወንድም #እህቶች አሉን!
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው @simetube Dont share without credit
💢ሰላም ውድ የ Sime Tech ቤተሰቦች ዛሬ ስለ Software አንዳንድ ነገር እናያለን።

🔰Software ማለት ስልካችን የሚሰራበት ፕሮግራም ሲሆን computer ፣ flasher box እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን እንዲሁም ኮዶችን በመጠቀም የምንሰራው ስራ የ software ጥገና እንለዋለን።

❖ Software በመጠቀም የምናስተካክላቸው የተለያዩ የስልክ ችግሮች አሉ። ለምሳሌ
☛ በራሱ በርቶ የሚጠፋ ስልክ
☛ ምንም የማይበራ ስልክ
☛ አንድ የምንፈልገውን ፕሮግራም ስንከፍት ብቻ የሚጠፍ እና ሌሎች ፕሮግራሞችን ግን በ አግባቡ የሚሰራ ስልክ
☛ በ security የተዘጋ ስልክ
☛ network መከፈት የሚፈልግ ስልክ እና የመሳሰሉትን ሊያካተት ይችላል።

🔺 Software መስራት የሚከትሉትን ያካትታል።
►flash ማድረግ
►restore ማድረግ
►format ማድረግ
►የተዘጋ ስልክ መክፈት
►iphone jailbreak ማድረግ
► internet መክፈት
►music ፣ video እና game መጫን ወዘተ....

✏️ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት ለማከናወን computer ፣ flasher box እና የተለያዩ software ፕሮግራሞች ያስፈልጉናል።

🔺 FLASHER BOX ማለት ስልካችንን ከ computeራችን ጋር እንዲገናኝ የሚያደርግ መሳሪያ ነው።
የተለያዩ የsoftware ቦክሰሮች ገበያ ላይ ይገኛሉ። አንድ software box ከሌላው ቦክስ የሚለየው በሚሰራቸው የስልክ አይነቶች ነው።

ቀጥሎ የምታዩት የ "software" ቦክሶች አይነት የተለያዩ ስልክ መስራት የሚያስችሉ ሲሆኑ በተለያየ ፕሮግራም ይዘንላችሁ እንቀርባለን።
◻️ UFS
◻️ Z3X
◻️ Cyclone
◻️ Infinity
◻️Avator
◻️Volcano
◻️Farous....etc

‼️ Join & Share...
📢 @simetube
@simetube
አይ ሲ ማለት ምን ማለት ነው ?

ከሞባይል ጋርስ ምን ያገናኛዋል?
አይ ሲ ማለት ብዙ ኮመፖነቶች የሚገኙበት ክፍል ነው::
በውሰጡም Resistor capacitor inductor diode ሌሎቹም ኮምፖነቶች ሊኖሩበት ይችላሉ::

የአይሲ ስራው ብዙ ነው ብቻ ኮምፖነቶችን በመሰብሰብ አንድና ክዛ በለይ የሆነን ስራ ይሰራልናል ለምሳሌ ሞባይል ላይም ሆነ ቲቪ ላይ ኦዲዬ አይ ሲ፣ ፓወር አይሲ እና ሌሎች አይሲወች ይኖራሉ:: እነዚህ አይሲዎች የራሳቸው ስራ አላቸው ለምሳሌ ፓወር አይሲ የፓወርን አክቲቪቲ ይቆጣጠራል ኦዲዬ አይሲ ደሞ የኦዲዬ አክቲቪቲ ይቀጣጠራል ስለ አይሲ ይህን ካለን ይበቃናል ወደ ሞባይል ስንገባ ሞባይል ላይም አይሲዎች በብዛት ይገኛሉ::

ማንኛውም ሞባይል ማለትም ሞባይል ከተፈጠረ ጀመሮ እስካሁን ያሉት ሞባይል 9 አይ ሲች አሉት ከድሮ ዳስተር ሞባይል አንስቶ እስከ አይፎን 6+ ደርስ ካሁን በሆላም ለሚፈጠሩት ስልኮች 9 አይሲዎች አሉት ዘጠኙ አይሲ ደሞ ለ3 እንከፍላቸዋለን
1 ) power and logic part ላይ (6 ic)
2) transmition part of ላይ (2 ic)
3) reception part of ic ላይ (1 ic)
4) power and logic part of ic
5) cpu ic (central processing unit )
ሲ ፒ ዩ ማለት የሞባይላችን ሁሉንም እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር የሞባይል አይሲ ነው በአጭሩ የሞባይላችን አእምሮ ይባላል

*የሲፒዩ መበላሸት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and
etc….

*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ

* የሲፒዩ ቦታ
በኖኪያ እና በሳምሰንግ ላይ አይሲው በወርቃማ ፍሬም ተከቦ ይገኛል በቻይና ስልክ ደሞ እላዩ ላይ M ወይም speed trum ተብሎ ይጻፍበታል

6) memory ic
ሚሞሪ አይሲ ዳታ እስቶሬጅ ዲቫይስ ነው

ለሁለት ይከፈላሉ
a) ROM ( read only memory ) it is permanent data storage ሮም ማለት የስልካችን ዋናው ፕሮግራም ወይም operating system የሚቀመጥበት ማለት ነው buraakiller

* የሮም መበላሸት
Dead phone, black or white screen, dim light
እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት
ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ

* የሮም ቦታ
ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነውይገኛል square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ buraakiller

b) RAM (randomly access memory) it is
temporary data storage ራም ማለት የስልካችን ሚሴጅ ኮንታክቶች ሚስኮሎች ሌሎችም ልንደልታቸው የምንችላቸው ነገሮች የሚቀመጥበት ነው

* የራም መበላሸት
No miscall. no dilledcall. no received call . no store photo and music etc…

*እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ

* የራም ቦታ ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነው square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ ይገኛል

*note ---- ኖኪያ ስልክ ለይ 1 እሰከ 5 ሮም እና ራም አይሲዎች ይገኝሉ በብዛት ከሮም ራም ያንሳል ልላው ደግሞ ለሰፒዩ በጣም የሚቀርበው ሮም ነው ራም ደግሞ በሳይዝ ከሮም ያንሳል ራም እና ሮም ሚቀመጡበት ቦታ ከኮምፖነት የጸዳ ነው

3) POWER IC
ፓወር አይሲ ዋናው ስራ ከባትሪ ቮለቴጅ ተቀብሎ ለተለያዩ አይሲዎች ፓወር መስጠት ነው
ለምሳሌ ከባትሪ 3.7 ቮልቴጅ ይቀበልና ለሲፒዩ 1.5 ቮልቴጅ ለሚሞሪ አይሲ ደግሞ 2.8ቮልቴጅ ያከፋፍላል

*የፓወር አይሲ መበላሽት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and etc….

*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ

***የፓወር አይሲ ቦታ
በኖኪያ ስላክ ለይ ለሁለት ዕንከፍለዋለን

a) የድሮ ኖኪያዎች ከሆኑ ማለትም 1st generation ከሆነ ብቻ ፓወር አይሲ ለብቻው ተነጠወሎ እናገኘዋለን ከአጠገቡም RTC የተባለ ኮሞፖነት እናገኛለን::

b) አሁን የሚገኙ ኖኪያዎች ደግሞ አራት አየሲዎች በአንድ አይሲ ተጠቃለው ይገኛሉ የዚ አይሲ ስምUEM(universal energy management) ይባላል እዚ አይሲ ላይ አራት አይሲዎች ይገኛሉ እነሱም Power ic, audio ic, charge ic, ui ic ይገኛሉ ይሄ አይሲ የምነለየው RTC አጠገቡ በመኖሩ ነው::

ቻይና ስልክ ላይ ደሞ አሁንም ልክ እንደ ሚሞሪ አይሲ ከሲፒዩ ጋር አብር ይገኛል ብቻ ሁሉም ስልክ ላይ RTC የተባለው ኮምፖንት አብሮት ይገኛል ጥያቄ ካለ ኢንቦክስ አድርጉልን::
@simetube @simetube
@simetube @simetube
@simetube @simetube
✳️ ይህንን ያውቃሉ? | Did you know?

◽️ በቅርቡ ስልካችንን ስልክዎን በየ3 ወሩ ብቻ ኃይል መሙላት ወይም ቻርጅ ማድረግ የሚጠበቅብን ምክንያቱም ከሰሞኑ ተመራማሪዎች ይፋ እንዳረጉት "magnetoelectric multiferroic" ተብሎ የሚጠራ አዲስ ቁሳቁስ የተገኘ ሲሆን የስማርትፎን ባትሪ ለሶስት ወር ያህል እንዲቆይ የማድረግ አቅም አለው።

🏷 @simetube
@simetube
@simetube
#SD_CARD
የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መካከል ስለ #ሜሞሪ_ካርድ ወይም SD(Secure Digital) CARD በጥቂቱ:

◽️ ይህች SD(Secure Digital) Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ #ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮንፒውተሮች፣ በታብሌቶች ፣በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

◽️ የሚሞሪ ካርድ #በመጀመሪያ ወደ አለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሚሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

◽️ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሚሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በእንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡ አብዛሃኞቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

◽️ ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሚሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media, እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

◽️ በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሚሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ Compact Flash, የተባለው የሚሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡ እነዚህ የሚሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

◽️ እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሚሞሪ እስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ sd CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

◽️ አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1 TB ወይም 1000 GB መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB ነበረ ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡ ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-
🔳16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
🔊7500 ሙዚቃዎችን
🔲3200 ፎቶዎችን
🔽 ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡

ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ! @simetube
@simetube
@simetube
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ቴሌግራምን እንዴት አድርገን እንደምንቆልፈው ነው። app lock ሳንጠቀም በራሱ በቴሌግራም መቆለፍ ይቻላል።

የሚክተሉትን መንገዶችን መጠቅም ፦
1 setting የሚለው ውስጥ እንገባለን።
2.privacy and security የሚለውን
3.passcode lock የሚለውን ነክተን እንገባለን....
4.....ከዛም በመቀጠልም passcode lock እናበራዋለን።
5.pin(ባለ 4 ይለፍቃል) ይጠይቀናል......የምንፈልገውን ቁጥር እንስጠዋለን።
6. ሞልተን ከጨረስን በኋላ Auto lock የሚለው ውስጥ ገብተን የምንፍልገውን እንመርጣል....
7.በመቀጠልም ከመረጥን በኋላ ወደ ዋናው እንመለሳለን.....
8.ከዛም ቴሌግራም ከሚለው አጠገብ Unlock የነበረውን ወደ Lock እንቀይረዋለን።
9.በመጨረሻም ይሄ ሁሉ ካደረግን በኋላ ከቴሌግራም እንውጣለለን.....ከዛም ተመልሰን ስንገባ......የሞላነውን pin (ባለ 4 ይለፍቃል) ይጠይቀናል።.....
.
መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላቹ።
🙏🙏🙏🙏🙏

Join us 👇👇👇👇
👉👉👉@simetube
💻 ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች 💻

💽📀የሀርድዌር መቃረን📀🔌

ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

📼የተበላሸ ራም📼

ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡

📟ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)📟

እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡

🐞ቫይረስ🐞
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡

⚡️መጋል⚡️
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ

@simetube
@simetube
5G ምንድን ነው?

1 ጂ የአናሎግ ሴሉላር ነበር።
እንደ CDMA ፣ GSM እና TDMA ያሉ 2G ቴክኖሎጂዎች የዲጂታል ሴሉላር ቴክኖሎጂዎች የመጀመሪያ ትውልድ ነበሩ ፡፡
እንደ ኢቪዲኦ ፣ ኤችኤስፒኤ እና UMTS ያሉ የ 3 ጂ ቴክኖሎጂዎች ከሴኮንድ ከ 200 ኪባ / ሴ ወደ ጥቂት ሜጋባይት ፍጥነቶች አምጥተዋል ፡፡
እንደ WiMAX እና LTE ያሉ 4G ቴክኖሎጂዎች ቀጣዩ ነበር

• 5G እናም አሁን እስከ መቶ ሜጋባይት እና ሌላው ቀርቶ የጊጋቢት-ደረጃ ፍጥነቶች እየፈጠሩ ነው።
•5G የሞባይል ኔትወርክ 5 ኛ ትውልድ ነው
•ለታዳጊዎች የ 4G LTE ኔትወርክ ጉልህ ለውጥ አለው።
• 5G በአሁኑ ጊዜ ባለው የዘመናዊው ማህበረሰብ ማህበረሰብ
• መኪናዎች እና ቴሌቪዥኖች ፣ እና በከተማ ላይ ጎዳናዎች ያሉ የተገናኙ መብራቶች ያሉ ሌሎች ነገሮች ብዙ ኢንተርኔት ጋር የሚገናኙበት መንገድ ለመቀየር ያግዛል።

• በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የተገናኙ መሣሪያዎች እና የነገው ፈጠራዎች በጣም ትልቅ እድገት እና ግኑኙነት በጣም ከፍተኛ እድገት እንዲያሟላ ሆኖ የተሰራ ነው።

• ማህበረሰባችንን የሚያገናኝ እና wave ለማስተላለፍ እና ለመቀበል 5G የሬዲዮ ሞገድ ወይም የሬዲዮ ሞገድ (አር ኤፍ) ኃይልን ይጠቀማል ፡፡

• የ 3 ጂ ኔትወርክ አንድ 100 ሚሊሰከንዶች የሚሆን የምላሽ ጊዜ ነበራቸው
• 4G ወደ 30 ሚሊሰከንዶች ያህል ነው
• 5G እንደ 1 ሚሊሰከንድ ዝቅ ይላል
• 5G በቢሊዮን ለሚቆጠሩ መሣሪያዎች ፈጣን ትስስር ያስገኛል
የመጀመሪያው የአለማችን ላፕቶፕ ኦዝቦርን 1 የሚባል ሲሆን ላፕቶፑን ለአለም ያበረከተውም አሜሪካዊው ፀሀፊ እና የሶፍትዌር ዲዛይነር የሆነው በአዳም ኦዝቦርን እ.ኤ.አ በ1981 ነበር። ይህ የመጀመሪያው የአለማችን ላፕቶፕ ራሙም (RAM) 64 KB ብቻ ነበር 😳

@Simetube
#tech_facts

👉 የጉግል የመጀመሪያ መጠሪያ "Backrub" ይባል ነበር።

👉 ጉግል ማፕን በመጠቀም የከርሰ ምድር ሒዎትን መመልከት ይችላል።

👉 ሰዎች ኢንተርኔት ላይ ያሉትን ነገሮች በፍጥነት የመርሳት ችግር "Google Effect" በመባል ይታወቃል።

👉 ፌስብክ ተጠቃሚዎቹ በሚሞቱበት ወቅት አካውንታቸውን የሚያስተዳድርላቸውን ሰው መሰየም የሚያስችል አሰራር አለው።

👉 እ.ኤ.አ 2013 ነሐሴ 16 ጉግል ለ 5 ደቂቃ አይሰራም ነበር።

👉 ከ ሶስት አንድ ሰው ፌስቡክ ተጠቅመው ሲጨርሱ በሒወታቸው ደስተኛ እንዳልሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ።

👉 የፌስቡክ የ"like" በተን መጣሪያው "awesome" ተብሎ ሊሰየም ነበር።

#share

© @Simetube
🍎🍎 📱💻🖥 🚬🚬

አፕል ኮምፒውተሮች አካባቢ ሲጋራ ማጨስ ካምፓኒው የሰጠህን የኮምፒውተሩን ዋስትና ያሳጣሀል፡፡

@Simetube
💻 0101 👦

'ቢል ጌትስ' የ ኮምፒውተር ፕሮግራምን የጀመረው ከ 13 አመቱ ጀምሮ ነው።

@Simetube
📡 SDና HD ሪሲቨር ልዩነት ምንድን ነው?
በሁለቱ መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት
Standard Definition (የመደበኛ ጥራት) (ኤስዲ) ወይም High Definition (ከፍተኛ ጥራት (ኤች ዲ)) ያላቸውን የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለማሳየት መቻላቸው ነው ፡፡
የኤስዲ(SD) ሪሲቨር ሣጥን መደበኛ ጥራት(Standard Definition) የቴሌቪዥን ቻናል ስርጭቶችን ብቻ ማሳየት ይችላል።
ኤችዲ(HD) ሪሲቨር High Definition (ከፍተኛ ጥራት) ደግሞ ሁለቱንም መደበኛ ጥራት እና ከፍተኛ ጥራት ቻናሎችን ያሳያል ፡፡ ኤችዲ ሪሲቨር እንደ HDTV ማሳያ እንዲጠቀሙባቸው ከኮምፒዩተር ማሳያዎች(ሞኒተር) ጋር ማያያዝም ይቻላል ፡፡
◄◄◄◄◄◄🔹🔹🔹▻▻▻▻▻▻▻▻
ሪሲቨር ስንገዛ ምን ምን ነገሮችን ማየት አለብን ☜
መጀመሪያ ድ ሪሲቨር ለመግዛት ወደገበያ
ስንወጣ ማየት ያለብን ብዙ ነገሮች አሉ
አለበለዚያ በቸልተኝነት ያገኘነዉ ሪሲቨር ገዝተን
ሪሲቨሩ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ የሚፈልጉት
ነገሮች ባይሰራ ወይም ሪሲቨሩ ብዙም
ሳይጠቀሙበት ቢበላሽ በተጨማሪ ወጪ መጋለጦ አይቀሬ ነዉ፡፡
1. መጀመሪያ ሪሲቨሮን ከሶኬት ጀምሮ ማየት ነዉ የሪሲቨሩ ስኬት ቶሎ ሚቆረጥ ሊሆን ስለሚችል ነዉ
2. በመቀጠል ሪሞቱን እናያለን እቤታችን ዉስጥ ህፃናት ካሉ ሪሞት አይበረክትም ስለዚህ የሪሞቱን ጥንካሬ ልብብሎ ማየት ነዉ ሪሞቱ ቢበላሽ ገበያ ላይ በቀላሉ ማግኘት መቻሎትንም ማረጋገጥ አለቦት
3. ሪሲቨሩ በአሁን ሰአት በሪሲቨር
ቴክኖሎጂ ዉስጥ ያሉትን አዳዲስ ነገሮች መያዙን ማየት ወይም መጠየቅ ነዉ
✿ለምሳሌ በቤትዎ ነፃ የኳስ
ቻናል ማየት ቢፈልጉ በቀላሉ ያለ ሶፍትዌር biss key , Tandbrge የመሳሰሉትን ያለ ሶፍትዌር ማየት አለቦት
4. ሌላኛዉ ነገር ሪሞታችን ባይሰራ ሪሲቨሩ ላይ ሙሉ በተን አለዉ ወይ ? ብላችሁ ማየት ጠቃሚ ነገር አለያቸዉ ላይ ምንም በተን የላቸዉ
✿ለምሳሌ እርሶ ቻናል
ለመቀየር ወይም ድምጽ ለመጨመር ፈልገው ሪሞቱ ምንም አልሰራ ቢለዎትስ ሪሲቨሩ ምንም በተን ባይኖረዉ በሰአቱ በጣም ይናደዳሉ በተን ካለዉ ግን ሪሞት እስክንገዛ ሪሲቨሩ ላይ ባለዉ በተን እየነካን እንጠቀማለን
5. እንደዚሁም ሪሲቨሩ
ሚያጫዉታቸዉ የvideo format ማየት ነዉ፡፡
✿ለምሳሌ FLV ,MPGMPG4 ,3GP , ETC
የመሳሰሉትን SUPPORT ማድረጉን ማየት
6. ሌላኛዉ በተለያዩ ጊዜዋች
አዳዲስ ነገሮች የመጡ ሶፍትዌሮች ቶሎየ ሚለቀቅለት ሪሲቨር መሆን አለበት
7. የሪሲቨሩ ግራፊክስ ማየት አለብን


#ሼር_ይደረግ

◻️JOIN👉 @@Simetube
ሰላም ውድ የsime Tech ቤተሰቦች

ዛሬ የምናየው ከስል ወደ ስልክ ቻርጅ ማድረግ ይሆናል

💢ስልካችሁ📱 ላይ የሆነ #አስቸኳይ ነገር ልትሰሩ ፈልጋችሁ ቻርጅ ዘጋባችሁ📵 እንበል፤ ቻርጀር ደግሞ በአካባቢያችሁ የለም።

ለዚህ መፍትሄ የሚሆን እንዴት ከሌላ ስልክ📲 ላይ ቻርጅ #ማስተላለፍ እንደምትችሉ አሳያችኋለሁ።
💢ስልካችንን📲 እንዴት ከሌላ ስልክ ላይ ቻርጅ ማድረግ እንችላለን?

#አስፈላጊ ነገሮች⬇️⬇️⬇️

ሌላኛው ስልክ
OTG
data cable

1⃣. አሰራር፦ ኬብሉን #OTG ላይ ይሰኩና በቀላሉ #OTG ያለበትን ጫፍ ቻርጅ ሰጪው ስልክ📲 ላይ ይሰኩት።

2⃣. ሌላኛውን ጫፍ ቻርጅ ማድረግ የሚፈልጉት ስልክ ላይ ይሰኩት።

አለቀ፤ ዳይ ወደ ዘረፋ

#ሼር ያድርጉ ሁሌም አዳዲስ የቴክኖሎች እውነታዎችን ያገኙበታል::

#join_us👇#join_us
@Simetube @Simetube
@Simetube @Simetube
@Simetube @Simetube
የስልካችሁ #ባትሪ ለምን እንደ #ሚሞቅ (እንደሚያብጥ) ታውቃላችሁ? እንግዲያስ ተከታተሉን

◼️Litium-ion ባትሪዎች ሀይል ለማመንጨት #Chemical #Reaction ይጠቀማሉ!

◼️የባትሪያችን እድሜ እየቆየ ሲሄድ ይሄ #Chemical #Reaction በትክክል አይካሄድም ይህም #ጋዝ ይፈጥርና ባትሪያችን እንዲያብጥ ያደርገዋል!

◼️በተጨማሪ ባትሪያችን ጉዳት ሲደርስበት የባትሪውን የዉስጠኛ #Layer በትክክል መለያየት አይችልም! በዚህ ጊዜ ጋዝ ማዉጣት፣ ማበጥ እንዲሁም መፈንዳት ይከሰታል! በቅርቡ እንኳን በ #Samsung #Galaxy #Note 7 የተከሰተዉ ፍንዳታ በዚሁ ምክንያት ነበር!

🛃ባትሪያችን እንዳይሞቅ ወይም እንዳያብጥ ለማድርግ ማወቅ ያለብን ጥንቃቄ

▪️ባትሪያችን እንዳያብጥ ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ሳናደርገዉ መቆየት የለብንም ምክንያቱንም ባትሪዉ ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ካልተደረገ #ጋዝ እንዲፈጠር ያደርጋል!

▪️ባትሪያችንን ለከፍተኛ ሙቀት ማጋለጥና ከመጠን በላይ ቻርጅ ማድረግ የለብንም!

▪️ጥራት ያለው ባትሪ እና ቻርጀር መግዛት (ስልኮን ሁል ጊዜ ከስልኩ ጋር አብሮ በመጣዉ ቻርጀር ቻርጅ ያድርጉ)

▪️#Internet ብዙ አለመጠቀም #Data ባበራን ቁጥር ስልካችን እየጋለ ነው የሚሄደው ይህ ደሞ ባትሪያችንን ከጥቅም ውጪ ያደርገዋል!

▪️ቻርጀር ሰክቶ በፍፁም አለ መጠቀም፣ ስልኩ ሊፈነዳ ሁላ ስለሚችል ጥንቃቂ ማርግ አለብን!

⚠️መረጃዎቻችን በቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችን #Mute ያደረጋችሁ #Unmute በማድረግ መረጃዎችን ያግኙ
@simetube @simetube
@simetube @simetube
ዛሬ እንዴት ሳምሰንግ ስልኮች ፌክ ወይም ሪል መሆኑን ማወቅ እንደምንችል እናያለን።

ስማርት ስልኮች ተፈላጊነታቸሳምሰንግዉ እየጨመረ በመጣ መጠን ሳምሰንግ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ ፌክ የሳምሰንግ ስልኮችም በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡

ሳምሰንግ የጎግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይጠቃማል፣የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል ፍቃድ
ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች ከኦርጂናሉ ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡

ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን ከባለፈው ፕሮግራማችን በተጨማሪ ከዚህ በታች የምናቀርበውን የመለያ መንገዶችን በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።

1⃣ የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም ፌክ ሳምሰንግ ስልክ!!

👉🏽 የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
👉🏽 ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
👉🏽 ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
👉🏽 የሳምሰንግ ሎጎ(ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ ይሻክራል፣በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
👉🏽 ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ ባትሪዉ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን

2⃣ የስልኩን ፍጥነት እና የትእዛዞች አፈጻፀም በመገምገም!!

👉🏿 በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣በፌክ ሳምሰንግ ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ስልኮች
👉🏿 በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን ለመክፈት ይሞክሩ፣ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡
👉🏿 ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም።
3⃣ የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም!!

👉🏻 ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps) የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ
👉🏻 ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን ይጫኑ
👉🏻 ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች
በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
👉🏻 እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number ጎግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ የተጠቀሱትን
ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

4⃣‼️የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም‼️

ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን መደወያ በተን ሳይጫኑ፤ ስልኩ ያስገቡትን ኮድ አዉቆ automatically መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡
🔘 ስማርት ስልኮች ከ 309 ኮዶች በላይ እንዳሉት Google ይነግረናል ነገር ግን ኦርጂናል እና ፌክ ስልኮችን የምንለይበት ስድስት ኮዶች (Top six) ብሎ የሚያስቀምጣቸውን ለእናንት አቅርበናል።
↓↓↓↓
1)▒▓⇨ *#0*#
አጠቃላይ መገምገሚያ(Enter Service Menu)
2)▒▓⇨ *#1234#
ስልኩ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ
3)▒▓⇨ *#12580*369#
ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ
4)▒▓⇨ *#06#
የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር ( IMEI Number) ከከፈተልን እና▫️ Part One▫️ ላይ ያቀረብንውን ማረጋገጥ ከቻለ።
5)▒▓⇨ *#34971539#
የስልኩን የካሜራ ስሪትና እድሳት (Camera Firmware Update) መረጃዎች ማወቂያ
6)▒▓⇨ *#9900#
የስልኩን ዋና ዋና System Dump Mode ማወቅያ
⚠️❗️⚠️ ምንም አይነት mode ከላይ በጠቀስናቸው code ገብተው እንዳይቀይሩ!

5⃣ ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም !!

ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡ሶፍትዌርን
1) Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ ይጫኑት የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገናኙት ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል።
⚠️ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሜ ይሞክሩት በድጋሜ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

@simetube
@simetube