Sime Tech
486 subscribers
139 photos
5 videos
221 files
123 links
በቻናሉ ውስጥ
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች
📢 ተወዳጅ አፖች
📢 የሶፍትዌር ትሪኮች
📢 የwebsite ጥቆማዎች
📢 የኮምፒውተር ትምህርቶች
📢 የሳተላይት ዲሽ መረጃ
📢 በቪዲዮየተደገፉ
📢የTech መረጃዎችንና
📢ሌሎች ትምህርቶችን በስፋትና በጥራት
ያገኛሉ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✳️ የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "Backup" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን?

◽️ በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች ለመያዝ የሚውሉ መገልገያዎችን እንጠቁምዎ:-

◽️ ፍሎፒ ዲስክ /Floppy
Disk/:- ትንሽና አነስተኛ መጠን ያለው ዲስክ ሲሆን አቅሙም 1.4 MB ነው፡፡ ጠቃሚ መረጃዎችን በፍሎፒ ዲስክ ለመያዝ በርካታ ዲስኮች ያስፈልጉናል፡፡ የድሮ ኮምፒውተሮች በብዛት ፍሎፒ ዲስክ መጠቀሚያ የነበራቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚመረቱ ኮምፒውተሮች አብዛኞቹ አገልግሎቱ የላቸውም፡፡

◽️ ዚፕ ድራይቭ /Zip
Drive/፡- ዚፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር MB መጠን ያላቸው ፋይሎችን /data/ የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ዚፕ ድራይቮችን ለመጠቀም የግድ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካት /hook up/ ይኖርባቸዋል፡፡

◽️ ቴፕ ድራይቭ / Tape Drive/፡- ቴፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር GB (በሺዎች የሚቆጠር MB) መጠን ያላቸው ፋይሎችን ይይዛል፡፡ ይህም ተጨማሪ ድራይቭ በመሆኑ የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት ይኖርበታል፡፡

◽️ ሲዲ በርነር /CD
Burner/፡- ሪከርድ የሚያደርጉ ሲዲዎች /CD-Rs/ እስከ 700 MB የሚሆኑ ፋይሎች የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አሁን ላይ የምንጠቀምባቸው አብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ሲዲ በርነር /CD Burner/ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹም ዲቪዲ በርነር /DVD Burners/ አላቸው፡፡ ዲቪ ዲ አር ኤስ /DVD-Rs/ እስከ 4.7 GB ፋይል የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ስለዚህ በአማራጭ የመጠባበቂያ ፋይል መያዣ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

◽️ ፍላሽ ድራይቭ /Flash
Drive/፣ የ ኤስ ቢ ድራይቭ /USB Drive/ እና ተምብ ድራይቭ /Thumb Drive/፡- ለአንድ ነገር የተለያየ ስያሜ ቢኖርም በኮምፒውተሮቻችን የዩ ኤስ ቢ /USB/ ፋይል መቀበያ በኩል በቀላሉ የሚሰኩ ተነቃይ ድራይቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድራይቨሮች ከ10 MB የሚጀምሩ ሲሆን 1 GB፣ 2 GB፣ 4 GB፣ 8 GB፣ 16 GB፣ 32 GB፣ 64 GB … እያሉ አሁን ላይ 4TB ፋይል የመያዝ አቅም ያላቸው ፍላሽ ድራይቮች በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍላሽ ዲስኮች በቀላሉ በኪስ የሚያዙና ተንቀሳቃሽ ቢሆኑም በቀላሉ ወድቀው ሊጠፉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡

◽️ ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ /External
hard Drive/:- ኤክስተርናል ሀርድ ድርይቭ በኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ውጪ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ፋይሎችን የምናስቀምጥበት መሣሪያ ነው፡፡ ይህ መሣሪያ /Drive/ ፋይሎችን ይዞ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እና ከኮምፒውተራችን ጋር በዩ ኤስ ቢ /USB/፣ በፋየርዋየር /Firewire/ ኮኔክሽን ወይም በገመድ አልባ /wirelesely/ ሊገናኝ የሚችል ነው፡፡

◽️ ታይም ማሽን /Time
Machine/፡- Time Mac ለተጠቃሚዎች አማራጭ የኤክስተርናል ፋይል መጠባበቂያ መያዣ መንገድ ነው፡፡ ይህ መጠባበቂያ መያዣ ዘዴ ለ24 ሰዓት በቀጥታ ፋይሎቻችንን ለማስቀመጥ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ፋይሎች ተረስተው ለጉዳት እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡ ታይም ማሽን በመጠባበቂያው የሚይዘው የተመረጡ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ድራይቨሩን ነው፡፡

◽️ ኔትወርክድ የሆነ የመረጃ ማካማቻ /Networked
Attached Storage/:- ይህ ከአንድ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች በኔትወርክ ተገናኝተው መረጃ የሚቀመጥበት ሥርዓት ሲሆን ይህም በስርዓት የተደረደሩ፣ ያልተደጋገሙ የፋይል ማከማቻ ኮኒቲነሮችን እና በርካታ የዲስክ ድራይቭ አካላትን የያዘ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት መረጃ ለማግኘት፣ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተዳደርና ለማስተካከል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡

◽️ ስውር የበይነ መረብ መረጃ ማከማቻ /Cloud
Storage/:- ይህ የፋይል ማከማቻ ዓለም አቀፍ የመረጃ ማከማቻ ሥርዓት ሲሆን በኔትወርክ አማካኝነት በመገናኘት መረጃዎቻችን ክላውድ ተብሎ በሚጠራ የመረጃ መጠባበቂያ ሥርዓት /Cloud Server/ ውስጥ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡ በርካታ የክላውድ ማማቻ ዓይነቶች በበየነ-መረብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም በነጻ ወይም በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ iCloud፣ Dropbox፣ Google Drive እና OneDrive የታወቁ የመረጃ ማከማቻ መንገዶች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚከማቹበት ሥፋራ በመራጃ በለቤቶቹ ቁጥጥር ሥር ባለመሆኑ የመረጃዎቹ ደህንነት አስተማማኝ እንደስጋት ይታያል፡፡

◽️ ፕሪንት ማድረግ /Printing/:- ምንም አንኳን መረጃዎቻችን በሶፍት ኮፒ የምናስቀምጠውን የህል የተማቹ ባይሆኑ ኮምፒውተሮቻችን በተለያየ ምክንያት ለቀናት አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ፕሪንት ያደረግናቸው ፋይሎች እጅጉን ይጠቅሙናል፡፡

https://telegram.me/Simetube
https://telegram.me/Simetube
✳️ አርቴፊሻል ዝናብ በዱባይ

◽️ UAE - ዱባይ በአርቴፊሻል ደመና ወይም በተሰረቀ ደመና / Cloud Seeding/ ያገኝችው አርቴፊሻል ዝናም መሬቷን እያረሰረሰው አይቷት የማያውቀው ውርጭም ዛሬ አስኮርፏታል። የደመና ስርቆሽ /Cloud
seeding/ በዱባይና አካባቢው እየተለመደ የመጣ ደመናን ለመሰብሰብ እና አልፎም ዝናብን ለማግኘት ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቅ ሳይንሳዊ ሂደት ነው።

◽️ ይህ የደመና ስርቆሽ የተለያዩ ኬሚካሎችን / silver iodide, potassium iodide and dry ice (solid carbon dioxide), Liquid propane /ከአውሮፕላን ላይ በመርጨት በሰማይ ላይ ያሉ ጥቂት ደመናዎችን በአንድ ላይ በመሰብሰብ እና ከፍተኛ ቅዝቃዜን እንዲፈጥሩ በማስቻል ዝናብ የመስጠት ሃይል እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

◽️ ይህ ሂደት ጥቅምም ጉዳትም ያለው ሆኖ ነገር ግን ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ሂደት ነው። ለምሳሌ ፣ በኬሚካሎቹ ምክንያት የሚከሰት ችግር እና ያልተጠበቀ ጎርፍ ወይም ከባድ ውሽንፍር ይጠቀሳሉ ።

◽️ እንደ አንዳንድ ዘገባዎች በ2015 ብቻ እንኳን UAE ከግማሽ ሚሊየን ድርሃም በላይ ወደ 558000 aed አውጥታለች። በአሁኑ ሰአት ደግሞ ኬሚካሎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ አንድ አውሮፕላን ተነስቶ ኬሚካል ረጭቶ እስከሚያርፍ ድረስ ብቻ ወደ መቶ ምናምን ሺ ድርሃም ያስወጣል። በዛሬው እለት ብቻ የዘነበውን ዝናብ ለመፍጠር ትላንትና ከ 5-6 የሚሆኑ የአውሮፕላን በረራዎች ተደርገዋል።

ምንጭ : Gulf News


https://telegram.me/Simetube
https://telegram.me/Simetube
ቴሌግራም 'Video Call' ጀመረ!

ቴሌግራም ትላንት ሰባተኛ ዓመቱን ይዟል፤ ይህ መተግበሪያ አገልግሎት መሰጠት የጀመረበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አዲስ ይዘት ይዞ ቀርቧል ይኸውም 'Video Call' ነው።

ቴሌግራም አሁን ላይ በዓለም '400 ሚሊዮን' ተጠቃሚዎች ያሉት እና ከ10 በብዛት ዳውንሎድ ከተደረጉ መተገበሪያዎች አንዱ መሆን ችሏል።

ቴሌግራም Video Call ለመጠቀም በመጀመሪያ አሁን ላይ እየተጠቀማችሁ የምትገኙትን መተግበሪያ PlayStore ላይ ገብታችሁ #update ልታደርጉት ይገባል።

https://telegram.me/Simetube
https://telegram.me/Simetube
✳️ሰላም የsim Tech ቤተሰቦች በዛሬው ዝግጅታችን ስለሳተላይት እናያለን!

🔺ሳተላይት ምንድ ነው?

◽️ ሳተላይት ማለት Space ላይ የሚሽከረከር እቃ ሆኖ ከመሬት Signal ተቀብሎ የመጣለትን Signal Amplify አርጎ ወደ መሬት መልሶ የሚልክልን መሳሪያ ነው።

◽️ ሁለት የሳተላይት አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም Passive እና Active ይባላሉ። Passive የምንለው ከአንድ የመሬት መአዘን ወደ ሌላኛው የምድር ክፍል Microwave Signal ተቀብሎ የሚልክ ሲሆን ለምሳሌ በተፈጥሮ ጨርቃ Passive ነው።

◽️ Active የሚባለው በአለም ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን Microwave Signal ወደ Space ልኮ የተላከውን Signal ሳተላይቱ Amplify አርጎ መልሶ ወደ መሬት የሚልክልን ነው። Active ሳተላይት ላይ Antenna System, Transmitter, Power Supply, Receiver እና የመሳሰሉት ኮምፖነንቶችን ይይዛል።

◽️ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳተላይትን ሀገር Soviet union (Russia) ስትሆን ይሄም የሆነው በ1957 ነው። ስሙም Sputnik 1 ተብሎ ይጠራ ነበር። ይህ ሳተላይት 58cm Diameter ሲኖረው 4 antenna እንዲሁም አነስተኛ ሞገድ (low frequency) የሆነ Signal ነበረው። Signal ያስተላለፈው ለ22 ቀን ሲሆን ከዛ በሃላ ባትሪው አልቆ ከጥቅም ውጪ ሊሆን ችላል።

◽️ በቀጣዩ አመት አሜሪካ ያስወነጨፈችው ሳተላይት ከመጀመሪው አንጻር ስኬታማ የሆነ ነበር። ይህች ሳተላይት የድምጽ ሞገድ ያስተላለፈች ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ አሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት Dwight D. Eisenhower ለአለም ህዝብ "Peace on earth and good will toward men everywhere." የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ችለው ነበር።

◽️ ከዚህ በሃላ የተለያዩ ሀገራት የተለያዩ አይነት ሳተላይቶችን ሰርተው ማስመንጠቅ እና ማምጠቅ ችለዋል። በአሁኑ ሰአት በአለማችን ላይ ከ 2000 በላይ ሳተላይቶች በጠፈር ላይ ይገኛሉ። በ ኢኮኖሚ ደካማ የሆኑ ሀገራት ሳተላይትን ከበለጸጉ ሀገራት እየተከራዩ ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ሀገራችን ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ በኪራይ የምትጠቀም ሲሆን ከጥቂት አመታት በሃላ የራሳን ለመስራት እየታተረች ትገኛለች።

◽️ በነገራችን ላይ ሳተላይትን መስራት ብቻውን ዋጋ የለውም የተሰራውን ሳተላይት የማመንጠቂያ መዐከል ያስፈልገዋል። ይሄ የመንኮራኮር ማመንጠቂያ ማእከል ያላቸው ሀገራት በጣት የሚቆጠሩ ሲሆን አብዛኛው የአለም ሀገራት የ ሩሲያ እና የአሜሪካንን ማመንጠቂያ ስፍራ ይጠቀማሉ። ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ ከመንግስት አልፎ የግል ኩባንያዎችም በዚህ ዘርፍ ላይ በስፋት ተሰማርተዋል።

◽️ እንዴት ትርፋማ ይሆናሉ ብሎ የሚያስብ ይኖራል። እንዴት መሰላቹ የተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያውች በየአመቱ የሚከፍሉት ገንዘብ አለ ለሳተላይቱ ባለቤቶች።

◽️ ለምሳሌ EBS Nile sat ላይ ይጠቀማል በዚህ ምክንያት በየአመቱ ከ500000 ብር በላይ ይከፍላል። አብዛኞቹ የ አፍሪካ ሀገራት የተቃዋሚዎቻቸውን ቻናል Jam አድርጎ ማጥፋት ሲያቅታቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላሮችን ለ ሳተላይት ባለንብረቶች እየከፈሉ ከአየር ላይ ያስወርዳሉ።

◽️ በሀገራችን ሁኔታም ይሄ በስፋት የተለመደ ነው። በፊት ESATን የመሰሉ የመንግስት ተቃዋሚ ቻናሎችን ለማውረድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን እያወጡ ነበር ።


https://telegram.me/Simetube
Forwarded from አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹
የኢትዮ ቴሌኮም ቅናሽ!

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 35 በመቶ ቅናሽ ተደረገ። እንዲሁም በቤትዎ ይቆዮ የጥቅል አገልግሎትም 59 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘገበ።

የድምፅ ጥቅል አገልግሎት ላይም የ29 በመቶ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን አገልግሎቱም ከነገ ነሐሴ 21/2012 ጀምሮ በስራ ላይ ይውላል።

በተያያዘም እስከ 11 የሚደርሱ ሀገራት ላይ የውጭ ጥሪ አገልግሎት 50 በመቶ ቅናሽ መደረጉም ታውቋል። ከውጭ አለም አቀፍ ጥሪ ለሚቀበሉ ደንበኞች ከኢትዮ ቴሌኮም ስጦታ ይበረከትላቸዋል።

ነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም

https://t.me/Asrat_News
https://t.me/Asrat_News
Forwarded from አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹
የኢትዮ ቴሌኮም የምስጋና ስጦታ!

ኢትዮ ቴሌኮም ከነገ ሐሙስ ነሐሴ 21/2012 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ የምስጋና ስጦታ ማዘጋጀቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የድርጅቱ ደንበኞች 1 GB የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ፣ 40 ደቂቃ ድምጽ አገልግሎት ፣ 100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት በነጻ እንደሚያገኙ መገለፁን ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም

https://t.me/Asrat_News
https://t.me/Asrat_News
📲 ሞባይል ስልካችሁ በቫይረስ እየተጠቃ ተቸግራችኃል?

🖱 ስለ ቫይረስ ምንያህል ያውቃሉ?

🎥#Virus ማለት የ Computer Code ወይም Program ሲሆን ብዙ ግዜ የሚሰራው ወይም
የሚፈጠረው የ Computer እውቀት ባላቸው ሰወች እና ስለ Computer ጠልቀው በ ተማሩ ሰወች ነው
📵 ቫይረስ ስንል ብዙ አይነት ቫይረሶች አሉ
➲Spyware Virus
➲Malware Virus
➲Ransonware Virus
➲Adware Virus
➲Trojan Horse Virus ናቸው
እንደ ስማቸው ሁሉ ስራቸውም ይለያያል።

🖱 ቫይረስ ለመስራት ስለ Computer ብዙ መማር እና ማወቅ ያስፈልጋል

🖱 የ#Virus ዋና አላማው እና ስራው ምን ምን ናቸው ?

፩ ስልካችንን ማበላሸት (Damage) ማድረግ
የስልኩን Software ቫይረሱ በሚያጠቃበት ግዜ ስልኩ Dead ይሆናል ይህ ማለት ስልካችን Samsung ከሆነ ስንከፍተው Samsung ይልና ቀጥ ብሎ ይቆማል አይከፈትም ማለት ነው

፪ በጣም ጠቃሚ ፋይል ማጥፋት እና መደበቅ

ስልካችን ላይ ሆነ MemoryCard ላይ ያሉትን ማንኛውም (File)
ለምሳሌ 👇👇👇👇
Music Photo Video Application Document ያለ ምንም ምህረት ያጠፋል (Format) ያደረጋቸዋል ያለኛ ትዛዝ እና ፍቃድ

፫ ስልካችንን በማናውቀው Password ወይም Pattern መቆለፍ እና መዝጋት
ይህ ማለት ስልካችንን የዘጋንበትን የሚስጥር Password ይቀይርና የራሱን Password
በማስገባት ይቆልፍብናል ማለትም ስልካችንን
ሙሉ በ ሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር ያደርገዋል እኛ ስልኩን ማዘዝ አንችልም ማለት ነው

፬ የስልካችንን(OS)Operating System ስራ ማዛባት እና ስልኩ እንዲዘባርቅ ማድረግ
ይህ ማለት ስልካችን ስራውን በትክክል እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናል። በሌላ አነጋገር እኛ ስልኩን
ሳንነካው ሳናዘው በራሱ (File)መክፈት መዝጋት
ስልኩን Flight Mode ላይ ማድረግ
ስልኩን Switch Off ማድረግ ከዛ ስልኩን መልሶ መክፈት. ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን በራሱ ይሰራል

፭ Software File ማጥፋት
የ ስልካችንን Software File Delete ማድረግ
=> Software File Delete ከሆነ ስልኩን ማስተካከል ከባድ ይሆናል

ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ ያለ ባለቤቱ ፍቃድ በራሱ መብት ይሰራል.
🖱 ስለ #ቫይረስ አደገኛነት ጉዳት እና አላማ ይህን ካልን ስለ መከላከያው እና ስለ መፍትሄው ደግሞ እናውጋ

እንዴት አድርገን ስልካችንን ከአደገኛ ቫይረስ መጠበቅ እና መከላከል እንችላለን
PerCaution
🖱 ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት ማንኛውንም ነገር ከ ማውረድ መቆጠብ
👉ለምሳሌ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ
ዌብሳይት Application ወይም File (Download) በምናደርግበት time #ቫይረሱ Download ከምናረገው Application ወይም File ጋር አብሮ ወደ ስልካችን በቀላሉ ይገባል
ለምን ቢባል Fake የሆኑ #ድረገጾች ላይ #ቫይረሶች ብዙግዜ ስለሚለቀቁ ነው ሰለዚህ ከታወቀ እና ታማኝነት ካለው ዌብሳይት ብቻ የምንፈልገውን File ማውረድ ይጠበቅብናል

🖱 Bluetoothl እና G-mail ክፍት አድርጎ አለመተው ተጠቅመን ከ ጨረስን ቦሀላ መዘጋቱን #Check Up ማድረግ

⌨️ የስልካችንን #Software Update ማድረግ
በሰአቱ እና በግዜው
ስልካችን የSoftware Update ጥያቄ ሲጠይቀን #ችላ አለማለት ወድያውኑ ስልኩን Update መድረግ
የስልካችን Software Update ከተደረገ ስልካችን በ ቫይረስ የመጠቃት እድል በጣም ዝቅተኛ ነው
የ ስልካችንን Software Update ለማድረግ መጀመሪያ #Setting ውስጥ እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ #About Phone
የሚል አለ እሱን እንዴ #Click እንላለን ከዛ
Software Update የሚለውን #Click ማለት

💻 ትክክለኛ እና #Original Antivirus መጠቀም
ስልካችን ላይ ያለውን ሁሉኑም Application እና File #Scan ማድረግ Scan በምናደርግበት ግዜ Virus ያለበት Application ወይም File ከተገኘ ወዲያውኑ ማጥፋት #Remove ማድረግ

⌨️ ከሚከተሉትOriginal Antivirus የወደዳችሁትን ከ PlayStore በ ማዉረድ ተጠቀሙ
➷➷➷➷➷➷
#Norton Antivirus
#KasperskyAntiVirus
#BT Virus Protect: Mobile Anti-Virus & Security App
👆👆👆እነዚህ Antivirusሶች የሚሰሩት በ Data እና በ Wifi Connection

⌨️ ቫይረስ በዋናነት ከሚገባበት መንገድ አንዱ በ #Email ወይምበ #G-mail ነው
Email እና በ G-mail በምንጠቀምበት ግዜ ከማናውቃቸው ሰወች #Link ሲላክልን ቶሎ መክፈት የለብንም ምክንያቱም የተላከው ከ #Hackerሮች (Linkኩም) ቫይረስ ሊሆን ስለሚችል በፍፁም መክፍት የለብንም

💾 ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉኑም Application #Update ማድረግ

📟 Wifi በምንጠቀምበት ግዜ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ
Wifi ከፍተን በምንጠቀምበት ሰአት ብዙ
Notification ወደ ስልካችን ይገባሉ በዚህ ግዜ
ወድያውኑ Notificationኑ ፍቃድ ይጠይቀናል
(Allow or Decline) ብሎ ይጠይቀናል ?
Notificationኑ ቫይረስ ይሁን አይሁን እኛ
አናውቅም ነገርግን እኛ ችላ በማለት ወይም ትኩረት ባለመስጠት (Allow) ብለን እንፈቅዳለን በዛን ሰአት Notification መስሎ የመጣው #ቫረስ በፍጥነት ወደ ስልካችን በመግባት ስልካችንን ያበላሻል ። ስለዚህ ማንኛውንም Notification ወደ ስልካችን ሲመጣ ዝምብለን ከመክፈት መታቀብ አለብን

📹 ማንኛውንም Application ከሰው ስንቀበል
ስለ Applicationኑ ምንነት እና ስራ በደንብ መረዳት አለብን ይህ ማለት Applicationኑ ጎጂ ሆነ ጥሩ የሚለውን እንድናውቅ ይረዳናል።ስለዚህ ማንኛውንም Application ስልካችን ላይ ከመጫናችን እና ከ መቀበላችን በፊት ስለ Applicationኑ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል


https://telegram.me/Simetube
How to fix your laptop 💻💻if it won't start? I will explain it briefly and follow these steps carefully.

Step 1. First you have to check the charger. if it's not the charger follow the next step.

Step 2. Unplug the battery and the charger then press and hold the power button for 30 second.

Step 3. Now plug the battery and and the charger and turn it on by pressing the power button. If it didn't work follow the next step.

Step 4. If all these 3 steps didn't turn your laptop on you need to remove your cmos battery and put it back.

Step 5. Now turn your laptop on and go to bios setting and configure your time and date .

Note: If those steps didn't turn your laptop on you better take it to maintenance shop.

#Share

https://telegram.me/Simetube
✳️ የቴክኖሎጂ እውነታዎች

◽️ ዛሬ ከ3.8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች Internet ይጠቀማሉ ይህም ከዓለም ህዝብ 40 በመቶው ነው።

◽️ በየ57 ደቂቃው ከ570 በላይ አዳዲስ Websites ይፈጠራሉ።

◽️ በየቀኑ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ Google Search ይደረጋል።

◽️ በ2020 ቪዲዮ ከሁሉም ከInternet ትራፊክ 80% ያህሉን ይይዛል።

◽️ 40,000 የTweeter ትዊቶች በደቂቃ ይላካሉ በቀን 500 ሚሊዮን ትዊቶች ማለት ነው።

◽️ በAmerica ከሚደረጉ ከ7 ፍቺዎች መካከል ለአንዱ ፌስቡክ ተጠያቂ ነው።

◽️ በ2020 ከ8.2 ቢሊዮን በላይ መረጃዎች ተሰርቀዋል ወይም Hack ተደርገዋል።

◽️ የመጀመሪያው ኮምፒዩተር ወደ 2.5 ሜትር የሚጠጋ ቁመት ያለው ሲሆን ክብደቱ ወደ 30,000 ኪ.ግ. ይመዝናል።

◽️ NASA ውስጥ የInternet ፍጥነት በሰከንድ 90GB ነው።

◽️ በዓለም ትልቁ ሃርድ ድራይቭ 60TB SSD ነው።

◽️ Bluetooth ኖርዌይን እና ዴንማርክን አንድ ባደረገው ሃራልድ ብሉቱዝ በተባለ ንጉስ ተሰየመ ነው።

◽️ የጉግል መሥራቾች እ.ኤ.አ. በ1999 ጉግል ን በ1 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ፈቃደኞች ቢሆኑም Excite ግን አልተቀበላቸውም። ጉግል አሁን 527 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው።

©SimeTech

◻️JOIN👉 @simetube
📟 #ኦርጂናል(Original) እና #ፌክ(ፎርጂድ) #ሚሞሪ(Memory) ካርድ እንዴት መለየት ይቻላል?

🎞ኦርጂናል ሚሞሪ ከፌኩ በምን ይለያል?

📟1ኛ. ኦርጂናል ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን ውስጥ በማስገባት ፎርማት(Format)
ማድረግ ነው። ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ ምንም
ችግር ይጨርሳል።ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኤረር(Error) ቦክስ ያሳያችሁና
ይቋረጣል።

📟2ኛ.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ ወይም በስልኮ ወደ ሚሞሪው ፍይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን
ፊልም ወይም ሌላ ፍይል ወደ ገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት
ማወቅ ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ
ይወስዳል ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 - 30 ደቂቃ ሊወስድ ይችላል። ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ ነው ማለት ነው።
📟3ኛ.ሶስተኛው መንገድ ደሞ ስልካችን ውስጥ በማስገባት ይህን SD insight የተባለ አፕፕ(App) ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን።አፑን ዳውንሎድ ካደረግን በኋላ ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕፕ ስንከፍተው ስለ ሚሞሪው ምርት
መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል ነው ማለት ነው።
ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የትአይነት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለቴ ነው ። ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም መረጃ አያሳየንም ። ይህ ማለት ሚሞሪው
የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው። ስለዚህ የማይታወቅ ሚሞሪ ነው ማለት ነው።
#SimeTech
🧑🏽‍💻@simetube
📱በስልካችን ቪዲዮዎችን በማቀናበር ፕሮፊሽናል ኤዲተር መሆንእንዴት እንችላለን?
📱ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም! ዘመን አፈራሽ የሆነው ስልክዎ ከኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮዎችን ለማቀናበር አንዲያደርጉ ያስችሎታል!

📱 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 8 አፖች እነሆ!

1ኛ፦ FilmoraGo
በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የAndroid ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው! የመቁረጥ (Trim/Cut) ገጽታዎችን መቀየር፣ሙዚቃን ወዘተ... የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ በዚህ መተግበሪያ ሊያከናወኑ ይችላሉ!

2ኛ፦ VideoShow
ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ አስደናቂ መተግበሪያ ሲሆን PlayStore ውስጥ ከሚገኙ ነፃ ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው! ለአጠቃቀም ቀላል ነው! ከዋና ዋና ተግባራቶቹ ውስጥ ፊልተሮችን፣ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም በቀጥታ ስርጭት ጊዜ ቪዲዮዎን መቆጣጠር፣ማስዋብ ይችላሉ!

3ኛ፦ PowerDirector
ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ገራሚ የቪዲዮ ኤዲተር ነው! በቸኮሉ ጊዜ አልያም ፈጣን ግዜያዊ (ቋሚ) ቪዲዮዎችን በሰአታት ውስጥ ለመስራት ግሩም የሆነ አማራጭ ነው!

4ኛ፦ KineMaster
ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነ-ገጽ ጋር በመጣመር #KineMaster ለAndroid ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው! የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ ❝Copy Paste❞ አገልግሎትን መጠቀም ይችላሉ! ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር የKineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ተመራጭ ነው! የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን (ብሎግ) ማስገባት ይችላሉ! ብቻ ይሄ መተግበሪያ የግድ ስልክዎ ላይ ሊኖር ይገባል! የኤዲቲንግ ፍላጎት ካላችሁ!

5ኛ፦ Quik
እጅግ በጣም ገራሚ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ሌላው ብልጥ መንገድ ነው! ፈጣን እና ነፃ ነው። የራሳችሁን ታሪክ በQuik ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ! ሌላው #ለQuik ይተውት! በጣም ጥሩው ነገር ደግሞ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎን ማሳደግ መቻሉ ነው! ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ውስጥ ቪዲዮዎችን #Crop ማድረግ፣ማሳመሪያዎችን፣ጽሑፎችን መጨመር እና ቪዲዮዎችን ከሙዚቃ ጋር ለማመሳሰል ፈጣን የሆነ አማራጭ ነው!
6ኛ፦ VivaVideo
ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት! መተግበሪያው በቀጥታ በስልክዎ ፕሮፌሽናል የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው! ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ! በውስጡ ዘገምተኛ (#SlowMotion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ስሪት እና የተንሸራታች ማሳያ #SlideshowMaker አለው!

7ኛ፦ FuniMate Video Editor
በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል! የዕለት ተዕለት ኑሮዎን በቀጥታ ወደ ፈጠራ ቪዲዮዎች ለመለወጥ እና የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት! አጭር ቪዲዮዎችን #ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ የላቁ አማራጮች አሉት!

8ኛ፦ Magisto
መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው! ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፎቶግራፎችን ሙዚቃን ጽሑፎችን (የቪዲዮ ውጤቶችን) እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል!
#SimeTech
👨‍💻 @simetube @simetube
#ዶክተር_ሮቦት

👨‍🏫የሮቦት ዶክተር ወደፊት ወረርሽኝ ሲከሰት የህክምና እርዳታ መስጠት እንደሚችል ባለሙያወች ተናገሩ።
በኤነድብራህ የሚገኙ የሮቦቲክስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራማሪዎች የዓለማችን የመጀመሪያ የሆነ በአንድ ጊዜ ከአንድ ሰው በላይ የህክምና እርዳታ የሚሰጥ ሮቦት ለመፍጠር እየሰሩ ይገኛሉ።

ሮቦቱ በእድሜ የገፉ ሰዎችን ለማገዝ በማሰብ መስራት ቢጀመርም ወደፊት ግን እንደ ኮሮና ያሉ ወረርሽኞች በሚከሰቱበት ጊዜ ሊያገለግሉ ይችላሉ ነው የተባለው።

አዲሱ ፕሮጀክት በአውሮፓ ህብረት ሆሪዞን 2020 የሚደገፍ ሲሆን፥ ሮቦቶች ከሰው ልጅ በተሻለ ፍጥነትና ክዋኔ በአንድ ጊዜ ከበርካታ ሰወች ጋር ውይይት በማድረግ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉትን ወረርሽኞች ለመቆጣጠር ሊረዱ እንደሚችሉ ነው የኤድንበርግ የዘርፉ ባለሙያዎች የገለጹት።

ፕሮጀክቱ በመጀመሪያ ይዞት የተነሳው ዋና ዓላማ ይህ አልነበረም ያሉት የሄርዮት ዋት የኮምፒዩተር ሳይንስ ፕሮፌሰር ኦሊቨር ሌመን ሆኖም አሁን አለምን እያስጨነቀ ካለው ወረርሽኝ ጋር ተያያዠነት እንዳለው ተናግረዋል።

ሮቦቶቹ ቀደም ብለው በአንዳንድ ሆስፒታሎች ውስጥ እየሠሩ ቢሆንም፤ በአብዛኛው የተለያዩ እቃወችን ማቅረብ እና ታካሚወችን የሚመዘግቡ ብቻ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

ፕሮጀክቱ ማህበራዊ መስተጋብር ሊፈጥሩ የሚችሉ አዳዲስ ሮቦቶችን በመፍጠር ለህክምናው ዘርፍ እንዲረዱ ይደረጋል ተብሏል።

ሮቦቶች ከእጅ እና ከተለያዩ ንክኪወች ነጻ ስለሚሆኑም ተፈላጊ መሆናቸው በተደጋጋሚ ይነሳል።

ምንጭ፦ FBC

#SimeTech
👨‍💻@simetube @simetube
🌻የሞባይል ስልካችን #ዳታ #ኮኔክሽን እየጠፋ ወይም ሲግናሉ ደካማ እየሆነ ሲያስቸግረን ምን ማድረግ ይኖርብናል!!

🌻ኢንተርኔት እየተጠቀምን የሞባይል ዳታ ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ እንቸገራለን፡፡አንዳንዴ አስቸካይ ስራ ለምስራት ፈልገን የኢንተርኔት ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ ወይም ጭራሽ እየጠፋ መስራት የምንፈልገውን ስራ ለመስራት እንቸገራለን፡፡
🌻የዳታ ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ ወይም እየጠፋ በሚያስቸግረን ሰዓት ኮኔክሽናችን እንዲሻሻል(BOOST) ለማድረግ የሚያስችሉ 3 ቲፖችን ላካፍላችሁ፦

1ኛ፡- የሞባይላችሁ Airplane Modeን “ON” ማድረግና “OFF” ማድረግ፦
Airplane Modeን “ON” ካደረጋችሁ በሃላ ቢያንስ 30 ሰከንድ ጠብቃችሁ Airplane Modeን “OFF” አድርጉት፡፡አሁን ዳታ ኮኔክሽናችሁ የተሻለ ይሆናል፡፡

2ኛ፡- ሞባይል ስልካችንን (#Restart) ማድረግ፦
ሞባይል ስልኮች miniature computers በመሆናቸው ማለትም ባህሪያቸው እንደኮምፒውተር በመሆኑ አንዳንድ ችግሮች ሲገጥሙን ስልካችንን አጥፍተን ስናበራ የገጠሙን ችግሮች ይስተካከላሉ፡፡ የኮኔክሽን ችግር ሲገጥመንም ስልካችንን #ሪስታርት ስናረገው ኮኔክሽናችን ይሻሻላል፡፡

3ኛ፡- ሲም ካርዳችን ከስልካችን ማውጣት(Remove your SIM card)፡
ሞባይል ስልካችንን #ሳናጠፋ ሲምካርዳችን አውጥተን መልሰን ማስገባት፡፡

🌻ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን በማድረግ ኮኔክሽንናችን እንዲሻሻል ማድረግ እንችላለን።
#SimeTech
@Simetube
✳️ ኮምፒውተራችሁን ፍጥነት ለመጨመር እነዚህን ዘዴዎች ይሞክሩ

🔺Power option

◽️ Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

🔺Disable unwanted start up programs

◽️ ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው።

◽️ Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

🔺Defragmentation and optimize

◽️ Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ።

🔺Delete unnecessary temporary file

◽️ Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን %temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት

🔺Clean up Memory

◽️ This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box OK ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት።

🔺Reduce run time service

◽️ Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all Microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ።

🔺Registry tweaks

◽️ Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር። እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay Valueን ወደ 10 መቀየር።

🔺Visual effects

◽️ Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ። ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ

#SimeTech
@simetube
📌አሪፍ ያልኮቸውን‍ የስልክና የኮምፒዩተር አፕሊኬሽን ልጠቁማችሁ

▫️ኮምፒውተር የለኝም ፅሑፍ በምን ላቀናብር ብሎ ነገር ቀረ።

በጣም በሚገርምና በሚደንቅ ሁኔታ በነዚህ ሁለት አፕ ፅሁፎችን ማቀናበር ከዛም ለወዳጅ ዘመድ መላክ ይችላሉ!!

1⃣Amharic tools(update የተደረገ) // 10.1MB
➼Text on phot // 17.3MB

2⃣RemoveR 3.7MB
➨Youcam perfect
➼ ጥቅማቸውም በሆነ ፈቶ/ፅሁፍ ላይ ማትፈልጉት ነገር ቢኖር እንደ ላጲስ በእጅ ማጥፋት ትችላላችሁ።

4⃣Photomath 16.3MB
➼ ጥቅሙም ሂሳብ እየሰራችሁ የከበዳችሁ ጥያቄ ቢኖር በስልካችሁ ካሜራ በማሳየት ብቻ ከነ አሰራሩ የሚሰራ አፕ ነው።

5⃣MalMath
➼ጥቅሙም Algebra
➼Integration
➼Derivative
➼Limit
➼Trigonomatric function
➨እነዚህን ከነ አሰራራቸው የሚሰራ ነው።
➨አሰራሩን እንዲያሳያችሁ ገፈለካችሁ Show steps ሚለውን ንኩ።

7⃣Faststone_Capture 3.5MB
➼Icecream. Screen video recorder 53.3MB
ጥቅሙም ኮምፒዩተር Screen ላይ ቪድዮ መቅረፅ የሚችል ነው(የራሳችሁንም ድምፅ ማስገባት ትችላላችሁ)

ለሰው የሆነ ነገር ማስረዳት ብትፈልጉ ኮምፕዩተር ላይ በነዚህ አፕ በቪድዮ ቦታውን እየገባችሁ ማረግ ያለበትን/ያለባትን ነገር ማሳየት ትችላላችሁ።


8⃣AZ screen video recorder
➼ጥቅሙም በስልክ Screen ላይ ቪድዮ መቅረፅ የሚችል ነው(የራሳችሁንም ድምፅ ማስገባት ትችላላችሁ)

9⃣WPS office
➨Officsuite
➼ጥቅማቸውም እንደ ኮምፕዩተራችን ላይ እንዳለው Microsoft office word ስልክ ላይ አገልግሎት ይሰጣሉ።
ለምሳሌ፦ Microsoft word, PowerPoint, Excel የመሳሰሉት ይገኙበታል።

🔟Clipboard
➼ጥቅሙም የሆነን ፅሑፍ Copy ብናደርግ Paste ሳንለውም ይህ አፕ ሴፍ አርጎ ያስቀምጥልናል
➼እንዲሁም Google translate አለው
➼Clipboard ገብተንም ለጓደኞቻችን ፅሁፉን መላክ እንችላለን።

1⃣1⃣▸kinemaster
▸cupcut (ይሄ ምንም watermark የለውም)
▸vivavideo
▸videoshow

➼ጥቅማቸውም video ለማቀናበር

1⃣2⃣▸PicsArt
▸Polarr
▸Snapseed
▸photodirector
▸adobe photoshop

➼ጥቅማቸውም ፎቶ ለማቀናበር


▫️ከላይ የጠቀስኳቸውን የስልክ አፕሊክሽኖች Google play store ላይ ማግኘት ይችላሉ
https://telegram.me/Simetube
@simetube
@simetube
@simetube
🔥ታዋቂው አልጄሪያዊ የ24 አመት ወጣት ሀከር ሀምዛ ቢንድላድ

📌በቅፅል ስሙ ሳቂታው ሀከር ተብሎ የሚጠራው ሀምዛ ከሀከርነቱ ጎን ለጎን የፍልስጤም ደጋፊ አክትቪስት ነው። ብቻውን ሆኖ የፍልስጤኖችን ሉአላዊነት በCyber ሲታገል የኖረው ወጣት አክቲቪስት ሀምዛ ለአመታት አሜሪካና እስራኤል ላይ ከባድ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።

📌አሜሪካን ፍልስጤምን እንደ አገር ሉአላዊነት አልሰጥም ማለቷ አሜሪካንን የሀክ ታርጌት እንዲያደርግ አድርጎታል።

📌ሀምዛ የሚጠቀመው #spyEYE Botnet የተባለ ማልዌር ነበር። በእርግጥ Hamza የማልዌሩን Source ኮድ ከአደገኛ ራሺያዊ ሀከር ላይ ነበር የገዛው ፤ FBI በሀምዛ ላይ ባቀረበው ክስ ከአሜሪካ እስራኤልን በገንዘብ ከሚደግፉ ባንኮች የ217 አካውንቶችን ገንዘብ ሀክ አደርጎ ወደ 4 ቢልዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ሀክ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል።

ሀምዛ ለአፍሪካና ለፍልስጤም NGO 280 ሚልዮን ዶላር ረድቷል ፤ በፈረንሳይና በአጠቃላይ ኢሮፕ 8000 የመንግስት ሳይቶችን ሀክ ማድረግ ችሏል ከንዚህም አንዱ የUN foreign minster ሳይትን ሀክ አድርጎ ለበርካታ የአልጄሪያ ወጣቶች የኢሮፕ ቪዛን ሰጥቷል.....

@simetube @simetube
💐#ኮምፒውተራችን ላይ የፈለግነውን #FOLDER_ፎልደር#PASSWORD_ፖስዎርድ እንዴት መቆለፍ እንደምንችል እንይ

💐ኮምፒውተራችን ላይ ሚስጥራዊ ፋይሎች ሊኖሩን ይችላል። እነዚህ ፋይሎች ከኛ ውጪ ሌላ ሰው እንዳያያቸው ከፈለግን የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል ፋይሎቻችንን በፓስዎርድ መቆለፍ እንችላለን።

1=> መቆለፍ የፈለግነውን FOLDER ወይም FILE እንመርጣለን

2=> የመረጥነውን FILE ወይም FOLDER Right-click በማድረግ Properties የሚለውን እንመርጣለን ከዛ General Tab ውስጥ ያስገባናል

3=> ከዛም General tab ውስጥ Advanced button ሚለውን Click እናደርጋለን

4=> በመቀጠል "Encrypt contents to secure data" ሚለውን Option ፈልገን እዛ ውስጥ መስጠት የምንፈልገውን Password እናስገባለን

5=> በመጨረሻም Apply የሚለውን በመንካት OK ሚለውን እንጫናለን

😎አሁን የምንፈልገው FOLDER ወይም FILE ተቆልፏል ወደ ፎልደሩ መግባት ስንፈልግ ቅድም ያስገባነውን Password መጠቀም እንችላለን።
@simetube
የሞባይል ስልክን በሚጠቀሙበት ወቅት አማራሪ ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱና ዋነኛው ነገር
የሞሉትን #የዳታ መጠን ወይም ካርድ በቶሎ ማለቅ ነው
በአብዛኛው ጊዜ የሞባይል ካርድ በቶሎ የሚጨርሰው ዳታ ሲከፈት ሲሆን የዚህም ምክንያት
ተጠቃሚው በማያቀው (በማያየው ) መንገድ #ከበስተጀርባ አፕሊኬሽኖች #ፕሮሰስ ሲያደርጉና
ሞባይሉ እራሱን #አፕዴት ሲደርግ ነው ። ታዲያ ይህንን ችግር ለመቅረፍ #ከታች የተዘረዘሩት
አፕሊኬሽኖች መርጦ በመጫን እና #ፕሮሰስ እንዲያርጉ የማይፈለጉትን አፕሊኬሽኖች #መዝጋት
መፍትሔ ማግኘት ይቻላል።

1. Datally
2. My Data Manager
3. Data Usage Monitor
4. DataEye
5. GlassWire
6. Net-Guard
7. Data Monitor
8. InternetGuard
9. Data Saver
10. Data Manager

#መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። 💻 ᏚᎻᎪᎡᎬ & JᏫᏆN ᏌᏚ 📲
@simetube
ስልክዎት በጣም ይግላልእንግዲያውስ ይህንን ብቻ ያድርጉ

➡️.በስልክዎ ለረጀም ስአት ጌም ከመጫወት ይቆጠቡ (የሚጫወቱበትን ሰአት ይቀንሱ)

➡️.ስልክዎት ተጥልፎ ከሆነ በተለይ ካሜራው አካባቢ ግለት ካለው ተጠልፎ ሊሆን ስለሚችል ለባለሙያ ያሳዩት

➡️.ከዚህ በፊት እንደነገርናችሁ ስልክዎን በማይጠቀሙበት ጊዜ(አዳር) #Switch_Off ያድርጉት፤ እድሜውን ያረዝማሉ።

‼️ያስታውሱ: ካለዎት ከየትኛውም ነገር (ከኮምፒውተርዎ፣ ከፍሪጅዎ ጭምር) ከ24 ሰአት ያለ ዕረፍት የሚሰራው #ስልክዎ ነው።

➡️.መኪናዎ ውስጥ ቻርጅ ከማድረግ ይቆጠቡ power ic'ውን፣ ቦርዱን ጭምር ሊያጡት ይችላሉ።

➡️.Hardware (Power Ic) ችግር ሊሆን ስለሚችል ለባለሙያ ያሳዩት
➡️. Background ላይ እየሰሩ ያሉ አፖችን ያስቁሙ።‼️

💯 @simetube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✔️ አሪፍ የፈጠራ ቪዲዮ ተጋበዙልን፡

✔️ አብዛኛውን ጊዜ ስለቴክኖሎጂ ሲነሳ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው ስልክ ፣ ኮምፒውተር ኢንተርኔትና ሌሎች እሌክትሮኒክ ፈጠራዎች ናቸው ፤ ነገርግን ቴክኖሎጂ ማለት የሰው ልጆችን ህይወት ማቅለል የሚችል ማንኛውም ፈጠራ ማለት ነው።