Sime Tech
486 subscribers
139 photos
5 videos
221 files
123 links
በቻናሉ ውስጥ
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች
📢 ተወዳጅ አፖች
📢 የሶፍትዌር ትሪኮች
📢 የwebsite ጥቆማዎች
📢 የኮምፒውተር ትምህርቶች
📢 የሳተላይት ዲሽ መረጃ
📢 በቪዲዮየተደገፉ
📢የTech መረጃዎችንና
📢ሌሎች ትምህርቶችን በስፋትና በጥራት
ያገኛሉ
Download Telegram
👋 ሰላም ሰላም የSime Tech ተከታታዮች ዛሬ በቴክኖሎጂ አለም የምንበቀማተውን ምፅአረ ቃላት ጥቂቶቹን ስሞቻቸውን እናያለን።

◽️
PAN - permanent account number.
◽️
PDF - portable document format.
◽️
SIM - Subscriber Identity Module.
◽️
ATM - Automated Teller machine.
◽️
IFSC - Indian Financial System Code.
◽️
FSSAI(Fssai) - Food Safety & Standards Authority of India.
◽️
Wi-Fi - Wireless fidelity.
◽️
GOOGLE - Global Organization Of Oriented Group Language Of Earth.
◽️
YAHOO - Yet Another Hierarchical Officious Oracle.
◽️
WINDOW - Wide Interactive Network
Development for Office work Solution.
◽️
COMPUTER - Common Oriented Machine.
Particularly United and used under Technical
and Educational Research.
◽️
VIRUS - Vital Information Resources
Under Siege.
◽️
UMTS - Universal Mobile Telecommunications System.
◽️
AMOLED - Active -matrix organic light - emitting diode.
◽️
OLED - Organic light-emitting diode.
◽️
IMEI - International Mobile Equipment
Identity.
◽️
ESN - Electronic Serial Number.
◽️
UPS - Uninterruptible power supply.
◽️
HDMI - High-Definition Multimedia
Interface.
◽️
VPN - Virtual private network.
◽️
APN - Access Point Name.
◽️
LED - Light emitting diode.
◽️
DLNA - Digital Living Network Alliance.
◽️
RAM - Random access memory.
◽️
ROM - Read only memory.
◽️
VGA - Video Graphics Array.
◽️
QVGA - Quarter Video Graphics Array.
◽️
WVGA - Wide video graphics array.
◽️
WXGA - Wide screen Extended Graphics
Array.
◽️
USB - Universal serial Bus.


https://telegram.me/Simetube
👋ሰላም ሰላም የSime Techተከታታዮች ዛሬ በ Android ስልካችን WIFI ተጠቅመን Forget ያልነውን የ WIFI Password እንዴት መልሰን ማግኘት እንደምንችል እናያለን።

✳️ File Manager:

◽️ በመጀመሪያ ፣ ወደ ስርወ አቃፊው (ንባብ) ንባብ የሚነግርዎት የፋይል አሳሽ ያስፈልግዎታል ፡፡ ነባር file manager እርስዎ ወደ root folder የሚነበብ መዳረሻ የማይሰጥዎት ከሆነ ከዚያ የስርዓት አቃፊውን እንዲደርሱበት የበላይ አለቃዎን የሚሰጠውን Root Explorer ወይም Manager አስተዳዳሪን መጫን ይችላሉ።

◽️ ወደ data / misc / wifi folder ይሂዱ ፣ እና wpa_supplicant.conf የተባለ ፋይል ያገኛሉ።

◽️ ፋይሉን ይክፈቱ እና ለስራው አብሮ በተሰራ ፅሁፍ / HTMLviewer ውስጥ ፋይሉን መክፈትዎን ያረጋግጡ ፡፡ አሁን በዚህ ፋይል ውስጥ አውታረመረቡን(network) ኤስኤስኤስዲ እና password ከጎኑ ማየት ይችላሉ ፡፡

◽️ አሁን የኔትዎርክን ስም እና password ያስታውሱ ፡፡ በዚህ መንገድ በ Android መሣሪያ ላይ ሁሉንም የተቀመጠ የ WiFi ይለፍ ቃል ማየት ይችላሉ።

✳️ ES File explorer:

◽️ በእርስዎ የ Android መሣሪያ ላይ የ ES ፋይል አሳሽ መተግበሪያን ያውርዱ እና ይጫኑ እና መተግበሪያውን ይክፈቱ።

◽️ አሁን በ ኤስ ኤስ ፋይል አሳሽ ውስጥ የ root Explorer አማራጭን enable ማድረግ አለብዎት።

◽️ አሁን በኤኤስ ፋይል ኤክስፕሎረር ውስጥ ወደሚገኘው የ root folder ውስጥ መሄድ ያስፈልግዎታል እና ዳታ ተብሎ የሚጠራ directory መፈለግ ያስፈልግዎታል።

◽️ አሁን በ data ስር misc(ማህደሩን) መፈለግ አለብዎት

◽️ አሁን በ WiFi folder ስር ፋይሉን በስም wpa_supplicant.conf መፈለግ አለብዎት። ፋይሉን በኤኤስ ፋይል ኤክስፕሎረር አብሮ በተሰራ ጽሑፍ / ኤችቲኤምኤል መመልከቻ በቀላሉ ይክፈቱ።

◽️ አሁን ሁሉንም የእርስዎን SSID (የአውታር ስም) ከ PSK (ይለፍ ቃል) ጋር ከጎኑ ማየት እና ፋይሉን መዝጋት ይችላሉ ፡፡


🏷share and join here

https://telegram.me/Simetube
ዒድ ሙባረክ!


. Sime Tech

እንኳን ለ1441ኛው ለታላቁ የዒድ አል-አድሐ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን!

በዚህ አጋጣሚ በዓሉን ስናከብር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ የመከላከያ መንገዶችን መተግበር #እንዳንዘነጋ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

ሐምሌ 24 ቀን 2012 ዓ.ም

https://telegram.me/Simetube
https://telegram.me/Simetube
Forwarded from 🌐 📶 ቴክኖሎጅ Technology🌐📶
መረጃ ህይወት ነው!!

በተለይ በዚህ ወቅት ብዙ የተሳሳተ መረጃዎች የሚያሰራጩ ሚዲያዎች በበዙበት ሰአት ትክክለኛ መረጃዎችን የሚያቀርቡትን ማግኘት ምናልባት መታደል ሊሆን ይችላል!!

👉 @Asrat_News
👉 @Asrat_News
👉 @Asrat_News
👉 @Asrat_News
👆👆👆👆👆👆👆
እኛም የተለያዩ ጥቆማዎች ወደእናንተ ማድረሳችንን ቀጥለናል ለዛሬ አንድ የቴሌግራም ቻናል ልንጠቁማቹ ወደድን ማስፈንጠሪያውን ( click link below) ይጫኑ
👇👇
👉@Asrat_News
👉@Asrat_News
👉@Asrat_News
👉@Asrat_News
✳️ MotherBoard:

◽️Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

◽️ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ (Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አ
ይችልም፡፡
#share_and_join
https://telegram.me/Simetube
✳️ Central Processing Unit (CPU):

◽️ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡

◽️ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡

◽️ የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል
፡፡

#share_and_join
https://telegram.me/Simetube
✳️ Random Access Memory (RAM):

◽️RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡

◽️RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

◽️የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል

#share_and_join
https://telegram.me/Simetube
✳️ Hard Drive:

◽️Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ ሙዚቃዎችን፤ ምስሎችን፤ ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡

◽️Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው
፡፡

#share_and_join
https://telegram.me/Simetube
✳️ Power Supply Unit:

◽️Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡

#share_and_join
https://telegram.me/Simetube
✳️ ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች፡

ኮምፒውተር ሲዘገይ በጣም ያበሳጫል አንዳንዴ ስበሩት ስበሩት ያሰኛል። ስንት ገንዘብ የከሰከሱበትን ኮምፒውተር ከመስበርዎ በፊት ግን እነዚህን
ዘዴዎች ይተግብሯቸው። እርስዎን ከብስጭት፣ ኮምፒውተርዎንም
ከመሰበር ይታደግዎታል፡፡

◽️ ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶወች (ዋልፔፐር) አይጠቀሙ፡፡
◽️ ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
◽️ አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
◽️ የማይጠቀሙበት አፕሊኬሽን ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-
ኢንስታል) ያድርጉት።
◽️ ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
◽️ ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፒ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
◽️ Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
◽️ ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
◽️ ብዙ አፕሊኬሽን ባንዴ አይክፈቱ::

#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን↘️

https://telegram.me/Simetube
👋 ሰላም ሰላም የSime Tech ተከታታዮች ዛሬ ኮምፒዉተር በራሱ የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበትን 5 ምክንያቶች በጥቂቱ እናያለን።

◽️የሀርድዌር መቃረን፡
ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡
እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ (interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡

ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1

እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

◽️የተበላሸ ራም፡
ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር ( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡
በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡

◽️ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)፡
እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡

◽️ቫይረስ፡
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡

◽️መጋል፡
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል።


#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን↘️

https://telegram.me/Simetube
👋ሰላም ሰላም የSime Tech ቤተሰቦች

✳️ ለዛሬ ዩቲዩበር ለመሆን ያሰባችሁ ልታውቋቸው የሚገቡ ነገሮችን እንጠቁማቹ

◽️ በአሁን ሰዓት ዩቲዩበር መሆን ከፍተኛ ስራ የሚጠይቅ ነገር ነው! ምክንያቱም YouTube በ2018 ያወጣው ህግ ብዙዎች ቻናል ለመክፈት ያሰቡ ሰዎችን ወደኋላ እንዲመለሱ ያደረገ ነገር ነው! በዛው ልክ ደግሞ በራሳቸው ፈጠራ እና ብርታት ለሚሰሩ Youtubers ትልቅ ደስታ ሆኗል..

◽️ህጉ ምን ነበር፡
አንድ ዩቲዩበር ከቻናሉ ላይ ብር ለማግኘት (Monetization : enable ለማድረግ) ቢያንስ እነዚህን ማሟላት አለበት!
▫️ቻናሉ ከተከፈተ 12ወር / 1አመት መሙላት አለበት!
▫️ቻናሉ ላይ የለቀቃቸው ቪዲዮዎች ተደማምረው 4000 ሰዓት መታየት አለባቸው!
▫️ቻናሉ ቢያንስ 1000 ሰብስክሪፕሽን ሊኖረው ይገባል (1ሺ ሰው ሰብስክራይብ ሊያረጉለት ይገባል)

◽️ትልቁ ራስ ምታት መስፈርቶቹ ትንሽ ከበድ የሚሉ ናቸው! ግን ትክክለኛ ታማኝ እንዲሁም ተፈላጊ መረጃ ለሚለቅ ሰው ቪዲዮዎቹ በ1-2 ቀን ውስጥ ሙሉ አለምን ሊያዳርሱ (Viral) ሊሆን ይችላል! ምክነያቱም አሪፍ Like, Share, Comment ስለሚያገኙ ዩቲዩብ ቪዲዮውን Score ያረገዋል።

◽️በፕላኔታችን ትልቁ የ YouTube ቻነል የህንድ የሙዚቃ ቪዲዮ ቻነል T-Series ሲሆን አሁን 120 million subscribers አሉት። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ትልቅ ሰብስክሪፕሽን ያየሁት የHope Entertainment ወደ 1.1 Million ነው!

አሁንም ለኢትዮጵያውያን ችግሩ ይበልጥ እየከበደ የሚመጣው ከጊዜ ወደ ጊዜ ዩቲዩብ ተጠቃሚ እየጨመረ ቢመጣም ግን Subscribe የሚያረግ ሰው ስለሌለ ነው! ስለዚህ ቻነል ያላችሁ ሰዎች ሰብስክራይብ የማድረግ ጥቅሙን በማስረዳት ብዙ Subscribers ማግኘት ይቻላል!

◽️ዩቲዩበሮች ምን ያክል ይከፈላቸዋል፡

T-Series ከ 200ሺ እስከ 1.2 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በወር እንደሚከፈለው መረጃዎች ያሳያሉ! ወደ ሀገራችን ስንመጣ የHope Entertaimemt በግምት ስናይ በወር ብቻ 840ሺ+ የኢትዮጵያ ብር በወር ያገኛል ማለት ነው! ስለዚህ ዩቲዩበር መሆን ለፈለጋችሁ ብር ለማግበስበስ ሳይሆን ምርጥ ነገር መስራት ላይ ብቻ ትኩረታችሁን ካደረጋችሁ ብሩ ሳትፈልጉት ይመጣል!

◽️የዩቲዩበሮች ትልቁ ችግር፡

ሰይብስክራይብ ከፈለክ አንተም ሰብስክራይብ አድርግ Comment ከፈለክ Comment አድርግ Like ከፈለክ አንተም የሌሎችን Like አድርግ!
እጅህን አጣጥፈህ ሌሎችን ብቻ የምትጠብቅ ከሆነ ስኬታማ አትሆንም!

◽️የተፎካካሪያቸውን ቪዲዮ ምንም ሳያዩት Dislike ማረግ! ( ለምሳሌ እኔ የTECH ቻነል አለኝ ሌላ ሰውም እነደዚሁ እና እኔ የሆነ ቪዲዮ Publish ሳረግ እሱ መጥቶ ምን ይሁን ምን ቪዲዮውን ሳያይ በደመነፍስ Dislike ማረግ አንዱ የዩቲዩበሮች ችግር ነው! በተለይ የኛ ኢትዮጵያውያን አብረን ለመብላት ብቻ አንድ መሆን የለብንም ምንም ሀሳብ መስጠት ካልፈለግን ዝም ብለን ማለፍ!

◽️የማይሆን እና ትክክለኛ ያልሆነ ቪዲዮ በመልቀቅ የሰውን ጊዜ ማቃጠል! ይህ ስኬት አይሆንም በቃ በትክክለኛው መንገድ መስራት ብቻ!

◽️ምርጥና ትክክለኛ ነገር ለሚሰሩ ዩቲዩበሮች በYoutube ላይ Copy Paste አይቻልም፡

ለምሳሌ እኔ ከ2 ሰዓት በፊት ቪዲዮ ለቀቄ አንዱ መጥቶ ቪዲዮውን ዳውንሎድ አድርጎ መልሶ በራሡ ቻነል ላይ ቢለቀው Even ቻናሉ እስከመጨረሻው ማስጠፋት እችላለሁ! REPORT በማድረግ ብቻ! የCopy Right መብቴን ተጋፍቷል ብዬ Report ሳደርግ YouTube ያንን ነገር በማጣራት ትክክል ከሆነ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል እምቢ ካለ Delete The Channel. በተመሳሳይ ሁኔታ በምቀኝነት ተነሳስቼ ይህ ቪዲዮ የኔ ነው ብዬ Report ባደርግ የራሴኑ ቻናል ያጠፉታል።

◽️ ሽልማት
የዩቲዩበሮች ሽልማት የዩቲዩብ Play Button ነው ሽልማቱ ግን የተለያየ አይነት ደረጃ አለው!

◽️ጥቅም፡

▫️Graphite - ከ1,000 በታች subscribers ላለው ቻነል
▫️Opal - 1,000 እና ከዚያ በላይ subscribers ላለው
▫️Bronze - ከ10,000 በላይ subscribers ላለው

◽️ሽልማት፡

▫️The Silver Creator Award - ከ100,000 በላይ Subscribers ላገኘ
▫️The Gold Creator Award - ከ1 million በላይ Subscribers ላለው
▫️The Diamond Creator Award - ከ10 million በላይ Subscribers ላገኘ
▫️The Custom Creator Award - ከ50 Million በላይ Subscription ላለፉ
▫️The Red Diamond Creator Award - ከ100 Million በላይ Subscribes ላላቸው


#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን↘️

https://telegram.me/Simetube
✳️HDMI cable ማለት ምን ማለት ነው?

◽️ HDMI cable ማለት ከስሙ እንደምንረዳው Cable/ገመድ ነገር ሲሆን እንደ አንዳንድ ኬብሎች ምስልና ድምፅ ከአንድ የElectronics Device ወደ ሌላ ለማስተላለፍ ይረዳል። ነገር ግን ለይት የሞያደርገው በጣም ከፍተኛ በሆነ ምስል ጥራት(HD QUALITY) ለማየት ይረዳል። ይህንንም ኬብል የምንጠቀመው ከ(Receiver, Laptop, DVD, Ps3, CPU, PSP)...ወደ ተለያዩ ምስልና ድምፅ ሊያወጡልን ወደሚችሉ መሳሪያዎች (TV, Projector, monitor) ለማስተላለፍ ነው።

✳️ አጠቃቀሙ እንደሚከተለው ነው፡

◽️ያለህ TV HD መሆን አለበት ወይም በሌላ አገላለፅ የ HDMI መቀበያ Port ያለውና Flat የሆነ መሆን አለበት።

◽️ያለህ ሪሲቨር HD መሆን አለበት።ነገር ግን አንዳነድ ሪሲቨሮች HD ሳይሆኑ እንደ TVው HDMI መቀበያ Port ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ።

◽️በቅድሚያ ኬብሉን በሪሲቨሩና በTvው ላይ በአግባቡ ይሰኩ።

◽️በTvው ላይ INPUT ወይም Source የሚለውን በመጫን የሰካህበትን Port (HDMI1, HDMI2..) ምረጡ።

◽️በምስሉ ላይ ብዙ የሚባል የጥራት ልዩነት ታያለህ። ያን ያህል ያልተጋወደ የምስል ጥራት ለውጥ ካለየህ ግን በሪሲቨሩ ላይ Video resolution/
የጥራቱን መጠን በመጨመር ወደ 1080i ድረስ አድርገህ የተሻለ ነገር ማግኘት ትችላላቹ።

#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን↘️

https://telegram.me/Simetube
👋ሰላም የSime Tech ቤተሰቦች ለዛሬ ፕሮፌሽናል ሀከር እንዴት መሆን እንችላለን የሚለውን ጥያቄ በጥቂቱ ለመመለስ እንሞክራለን።

✳️ ፕሮፌሽናል ሀከር ለመሆን ምን ምን ማወቅ አለብን?

1 | በመጀመሪያ ሃኪንግ ምን እንደሆነ ፣ ጥቅሙና ጉዳቱን እንዲሁም ስንት አይነት ሀከሮች እንዳሉ ለይቶ ማወቅ

2 | በቀጣይ ዋና ዋና የOperating System በደንብ ማወቅ | Windows, MacOS, Linux, Unix, Ubuntu,..

3 | ከሁሉም OS ጋር የሚስማሙ Programming Language መማር | perl, Python, C

4 | ሌሎች ዋና ዋና Programming Language መማር | HTML, PHP, JAVAscript, Swift, Ruby, ASP, XML, SQL, XSS, SQLI, RFI, LFI

5 | Networking እና DATA መማር | TCP/IP, Proxies, Socks, VPN, SSL, VPS, RDP, FTP, POP3, SMTP, Telnet, SSH

6 | Reverse Engineering መማር የጌሞችንና የሶፍትዌሮችን Serial key እንዴ Crack እንደሚደረግ | Ollydbg-x64dbg...

7 | Network installing, Scanning, Cracking እና Sniffing መማር

8 | Password Cracking, Bypassing እና ሌሎችንም መማር

9 | Carding መማር | Credit card, SIM, Website...

10 | Cryptosystem መማር | Cryptography,Cryptocurrencies....

11 | Attacking መማር | DDos, MitM, Brute Force, Phishing....

12 | የሀከር OS ማወቅና መማር | Kali linux, parrot, Blackarch, Blackbox...

13 | Virus & Malware Making መማር | conflicke, Trojan, Melissa...

14 | Attacking እና ጥቃትን መመለስ መማር | (ምክንያቱም Attacking ብቻ ተምረን Blackhat ብንሆን እኛም 1 ቀን ሀክ ልንደረግ እንችላለን ስለዚህ Whitehat ሁሉንም መማር Grayhat ለመሆን)

15 | የራስህን Operating System Program ማድረግ

16 | Games, Apps & Software Modding መማር | Software & app modification ከእንደገና እንዴት አሻሽሎ መስራት እንደሚቻል

17 | ዋና ዋና የሀኪንግ Tools ለይቶ ማወቅና መማር | Metasploit, Wireshark, Nmap, Hackchip...

18 | የተለያዩ የሀኪንግ መፅሀፍትን ማንበብ | The Hacker Playbook, Computer Revolution ...
እንዲሁም የተለያዩ የሀኪንግ ፊልሞችን ማየት | The algorithm, Matrix,...

19 | ከተለያዩ ሀከሮች ጋር Blog ላይ መወያየት እና መረጃ መለዋወጥ | በተለይም Darkweb forum ላይ ቢሆን ተመራጭ ነው።


📝 NOTE
ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ በ1 ሌሊት መማር አይቻልም በትንሹ ከ3-5+ አመት ይፈጃል ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ለመማር ደግሞ አሪፍ የinternet Connection እና አሪፍ PC/Mac ያስፈልጋል ምክነያቱም እያንዳንዱን ነገር በቲዮሪ ሳይሆን በሙከራ እየሞከርክ ስለምትማር።


#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን↘️

https://telegram.me/Simetube
✳️የስልኮትን ባትሪ ህይወት ሊያረዝሙ የሚችሉ 5 ጠቃሚ ምክሮች፡
የስልኮት ባትሪ በፍጥነት እያለቀ አስቸግሮታል? እንግዲያውስ የሚከተሉትን አማራጮችን ስክሎት ላይ በማስተካከል የባትሪዎትን ህይወት ማርዘም ይችላሉ፡፡

◽️ ለወራት ያልተቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖች ወይም መተግበሪያዎች ማጥፋት። ስልኮት ላይ ጭነዋቸው ነገር ግን ለወራት ምንም ጥቅም ላይ ሳያውሏች ግን ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ጊዜ ኖቲፊኬሽን እና የመሳሰሉትን የሚልኩ
አፕሊኬሽኖች የባትሪዎትን ህይወት ሊያሳጥሩት ይችላሉ፡፡ ስለዚህም እነኚህን አፕሊኬሽኖች ከስልኮት ላይ ማጥፋት የባትሪዎትን ህይወት ከማራዘም ባለፈ ከአላስፈላጊ የኢንተርኔት ወጪ ሊያድኖት ይችላል፡፡

◽️ ጠቃሚ ያለሆኑ አፕሊኬሽኖች Background data እንዳይጠቀሙ ማድረግ ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ጊዜ Background data የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን ሴቲንግ ውስጥ በመግባት Background data እንዳይጠቀሙ በማድረግ የባትሪዎትን ህይወት ማራዘም ይችላሉ፡፡ ስለዚህም ብዙ ጊዜ የማይጠቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖችን ወይም መተግበሪያዎች በመምረጥ Background data እንዳይጠቀሙ ማድረግ ይችላሉ፡፡

◽️ በተደጋጋሚ አፕሊኬሽኖችን ከመዝጋትና መክፈት መቆጠብ ብዙ ጊዜ እንደነ ኦፔራ ሚኒ፣ፌስ ቢክ የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖችን ተጠቅመን ስንጨርስ ዘግተን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መልሰን እንከፍታለን፡፡ ይህን ተግባር በተደጋጋሚ ባደረግን ቁጥር ለሞባይላችን ባትሪ ጠንቅ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህም ከተጠቀምን በኋላ የሆም በተኑን ተጠቅመን በመውጣት ሌላ ጊዜ መጠቀም ስንፈልግ ሞባይላችን ካቆመበት እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሞባይላችንን ባትሪ እድሜ እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡

◽️ የስልኮትን ቫይብሬሽን ማጥፋት ስልክን በሪንግቶን ብቻ መጠቀም ለብዙዎቻችን አስቸጋሪ እንደሚሆን ግልፅ ነው ሆኖም ግን የባትሪዎትን ህይወት ማስረዘም ሀሳብ ካለዎት ግን የስልኮን ቫይብሬሽን ማጥፋት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የስልኮት የድምፅ አማራጭ ላይ በመግባት የቫይብሬሽን አማራጭ ማጥፋት፡፡

◽️ የስልኮን ብሉቱዝ አማራጭ ማጥፋቶን ማረጋገጥ አብዛኛዎቻችን ምንፈልገውን ነገር ከወዳጆቻችን ጋር ብሉቱዝን በመጠቀም ከተላላክን በኋላ ብሉቱዛችንን ማጥፋት እንዘነጋለን ይህ ደግሞ ለባትሪያችን ህይወት ማጠር እንደ ምክንያት ይነሳል፡፡ ለዚህም እንደአማራጭ የቀረበው ሁልጊዜ ብሉቱዛችን መጥፋቱን ማረጋገጥ እንዲሁም ከሰዎች ጋር ዳታን ከተላላክን በኋላ ወዲያውኑ ማጥፋትን አለመዘንጋት ነው፡፡

#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን↘️

https://telegram.me/Simetube
👋ሰላም ሰላም ውድ የ sime Tech ቤተሰቦች ዛሬ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ከመግዛታችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮችን እንንገራቹ።

ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት ስንመርጥ ብዙ ነገሮችን አስበን ነው፤ ከነዚህ ውስጥ የተለመዱ ነገሮች አሉ ለምሳሌ አይነቱና ዋጋው፤ አሁን ግን የምናሳችሁ ምርጥ 10 ቲፖች ናችው: :

1. ካገለገለ ኮምፒውተር ይልቅ አዲስ ኮምፒውተር ይምረጡ

2. PCI Express x16 slot ያለው ማዘረቦርድ መሆን አለበት ይህም ሌሎች ካርዶችን ለመጨመር ይረዳዎታል::
ለምሳሌ ቲቪ ካርድ፣ ግራፊክስ ካርድና ሌሎች

3. ሚሞሪው ቢያንስ 4GB of RAM መሆን አለበት ይህም ኮምፒውተሮ እንዳይጨናነቅና ፈጣን እንዲሆን ያደርገዋል

4. ፕሮሰሰሩ Quad-core processor ያለውን ይምረጡ
ይህም ኮምፒውተሮ ፈጣንና ብዙ ፕሮግራሞችን ባንዴ የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል

5. ኮምፒውተሮን ለቤት ከሆነ የፈለጉት ፉኑ የማይጮህና የማይረብሽ ይምረጡ

6. An All-in-one PC ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ ኮምፒውተር ይምረጡ (ሞኒተሩ ፍላት ስክሪን፣ እና ሌሎችንም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች ያሟላ)

7. A single, high-powered graphics card ያለው ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ ይጠቅሞታል።

8. የሃርድ ዲስኩ ሳይዝ 500GB እና ከዛ በላይ ቢሆን ይመረጣል ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ብዙ ፋይሎችን የሚያስቀምጡ ከሆነ ነው።

9. ሃይል ቆጣቢና አነስተኛ ወጪ የሚያወጣ ይምረጡ

10. ኮምፒውተሮን ሲገዙ አብረው External hard drive ይግዙ ይህም ዳታዎችዎን ባክ አፕ (መጠባበቂያ) ለማረግ ነው።

#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን↘️

https://telegram.me/Simetube
#SimeTech #for_you
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆነ
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል
ይነገርለታል፡፡

2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm)፡በጣም ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm-45.72cm)፡ ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡

3. ሲፒዩ(CPU) የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ
Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡

4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡

5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡

6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝNይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080 የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡

7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡

8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን


https://telegram.me/Simetube
✳️ የGoogle አስገራሚ እውነታዎች፡

◽️ Googleን ከቀኝ ወደ ግራ ገልብጠን ብንፅፍ elgooG ይሆናል፡፡
elgooG.im ብለን የገፀ ድር አድራሻ ላይ ብንፅፍ የተገለበጠ የጎግል መፈለጊያን ማየት እንችላለን፡፡

◽️ Zerg rush ብለን ጎግል ላይ ሰርች ብናደርግ አስገራሚ ነገር እናያለን፡፡

◽️ አሁን የሚጠራበት ጎግል የሚለው ስያሜ በስህተት የቀረበ መሆኑን ያውቃሉ ካልሆነ ይህ መጠሪያው ትክክለኛው ሳይሆን በአጋጣሚ የመጣ መጠሪያው ነው። ይህ የሆነው መስራቾቹ Googol ብለው ለመጻፍ በማሰብ በስህተት Google ብለው ከሰየሙት በኋላ ነው፤ ይህ መጠሪያ ደግሞ በሂሳብ ከኋላው 1 መቶ ዜሮዎችን የሚያስከትል 1 ቁጥርን ይወክላል።

◽️ የጎግል ሰራተኞች Googlers የሚል መጠሪያ ሲኖራቸው አዲስ ተቀጣሪዎች ደግሞ Nooglers ይባላሉ።

◽️ የጎግል የመጀመሪያው ትክክለኛ መጠሪያ Backrub ይባል ነበር፤ ይህ የሆነው ደግሞ በማፈላለጊያ ገጹ ላይ ለሚፈለጉ አድራሻዎች በሚሰጠው አድራሻ እና ደረጃ አማካኝነት ነው።

◽️ ወደ ገጹ ገብተው ምናልባት “ራሴን ማጥፋት እፈልጋለሁ" I want to commit suicide የሚል ቃልን ቢጽፉ ይህን እንዳያደርጉ እና እርዳታ
የሚያገኙባቸውን በሚገኙበት አካባቢ እርዳታን እንዲያገኙ የሚያስችሉ ቁጥሮችንና መርጃ መንገዶች ያቀርብልዎታል።

◽️ ዘና ማለት ካሰኘዎት ደግሞ በጎግል ምስል መፈለጊያ ላይ ገብተው Atari breakout ብለው ይፈልጉና በሚመጣልዎት ጨዋታ ዘና ማለት ይችላሉ።

◽️ በመፈለጊያ አድራሻው ላይ የፈለጉትን ያክል ቁጥር እስከቻሉት ድረስ ይጻፉ ጎግል በፊደል እያስደገፈ ያቀርብልዎታል።

◽️ ጎግል ለፈለጉት ነገር ትክክለኝነት ማረጋገጫ 28 የተለያዩ ማረጋገጫ እና አምስት ማስጠንቀቂያ መንገዶችን ይከተላል።

◽️ አይበለውና አንድ የድርጅቱ ሰራተኛ ከዚህ አለም በሞት ቢለይ የሟቹ የፍቅር ወይም የትዳር አጋር፥ በየወሩ ከደሞዙ 50 በመቶውን ለ10 አመት ያክል መውሰድ ይችላል። ምናልባት ሟቹ ልጅ ካለው ደግሞ ልጁ 19 አመት እስከሚሞላው/ላት ድረስ በየወሩ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፈላቸዋል።

◽️ ከሚኖሩበት ምድር ወደ ላይ አልያም ወደ ላይ ከፍ ብለው ሰማየ ሰማያት ላይ ምን እንዳለ ማወቅ ከፈለጉ ደግሞ
www.google.com/sky . ከፍተው ይመልከቱ እና ጨረቃ፣ ከዋክብት አልያም የከዋክብት ስብስቦችን ይመልከቱ።

◽️ Google Maps ደግሞ የሚኖሩባትን ምድር የተለየ ገጽታ ማየት ያስችልዎታል።

◽️ ማወቅ አይከፋምና ወደ Google Mars ገብተው ስለ ቀይዋ ፕላኔት የፈለጉትን መረጃ ከየትኛውም ቦታ በተሻለ መልኩ ማግኘትም ይችላሉ።

◽️ እንዴት ነው የሚከፈላቸው የሚለው እንዳለ ሆኖ ግን፥ ይህ ኩባንያ ጎግል ማፕን ተጠቅሞ የበረሃን እይታ ለደንበኞቹ ለማድረስ ለዚህ ስራ ብቻ የሚያገለግል ግመልም ቀጥሯል። እናም ለተጠቃሚዎቹ እርካታ ጎግልም የበረሃዋን ግመል ቀጥሮ ያሰራል፤ እርሷም ደሞዝ ተከፋይ የጎግል ሰራተኛ ናት።


https://telegram.me/Simetube
✳️ ዛሬ በSimeTech ትውልደ ኔትዎርክ 1G, 2G, 2.5G, 3G, 4G, 5G እናያለን።

🔺1ጂ

◽️ ከ1980-1990
ፍጥነቱ 2.4Kbps ሚሰራዉ በ አንድ ሀገር ዉስጥ ብቻ ነዉ ሚጠቀመዉ የ ሞገድ አይነት አናሉግ ነዉ መጀመሪያ (USA) ዉሰጥ ነዉ ደካማ ጎኑ የድምፅ ጥራት የለዉም ባትሪ ይጨርሳል ስልኩ ትልቅ ነዉ ሴኪዩሪቲ የለዉም።

🔺2ጂ

◽️ የተጀመረዉ ፊንላንድ ነዉ በ 1991 ዲጂታል ሞገድ ነዉ ሚጠቀመዉ እስከ
#64kbps ደርስ ፍጥነት አለዉ መልእክት መላላኪያ አለዉ(SMS,MMS) ጥሩ የድምፅ ያሰማል። ደካማ ጎኑ ጠንካራ ሞገድ ይፈልጋል አንድ ቦታ ከተበላሸ ሌላ ቦታ ሞገዱ ይደክማል ብዙ ዳታ መላክ እና መቀበል አይችልም።

🔺2.5 ጂ

◽️ በ 2ጂ እና 3ጂ መካከል ይገኛል ኢሜል መላክ እና መቀበል ያስችለናል ኢንተርኔት ማስጠቀም ይችላል 64Kbps-144Kbps

🔺3ጂ

◽️በ 2000 አከባቢ ነዉ የተጀመረዉ ፍጥነቱ 144Kbps-2Mbps ትልቅ መጠን ያለዉ ኢሜል መላክ እና መቀበል ያስችላል እየተያዩ መደወል ይቻላል/3ዲ ጌሚንግ (3D GAMING) ቀጥታ ቲቪ ማየት/የስልክ ቲቪ ደካማ ጎኑ ዉድ ነዉ መስመሩን መዘርጋት ከባድነዉ ስልኮቹ ትልቅ/ዉድ ናቸዉ ብዙ ሞገድ ይጠቀማል

🔺4ጂ

◽️ፍጥነቱ ከ100Kbps-1Gbps ሌላ ስሙ #(MAGIC)
[M]obile Multimedia
[A]nytime Anywhere
[G]lobal Mobility Support
[I]ntegrated Wireless Solution
[C]ustomized Personal Services ደካማ ጎኑ ባትሪ በጣም ይጠቀማል ዉስብስብ የሆነ ስልክ ያስፈልጋል ዉድ አቃዎች ያስፈልጋሉ መስመሩን ለመዘርጋት

🔺5ጂ

◽️ከ 2010 ጀምሮ ነዉ ይሄ ሁሉን ነገሮች አሉት እንከን የለዉም ብዙ ነገር ይሰራል እያንዳንዱን ነገር ጥርት አርጎ ያሳያል (HD) ከሁሉም በጣም ፈጣን ነዉ በ አንድ ግዜ ብዙ ነገር ያስጠቅማል ከ 1Gbps በላይ ፍጥነት አለዉ ለ ማንኛዉም አገልግሎት በያዝነው 2020 እየቀረበ ይገኛል
::

https://telegram.me/Simetube
✳️ ውድ የSime Tech ቤተሰቦች በውስጥ መስመር በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ስለ Android ስልኮች CPU System በጥቂቱ እናያለን።

🔺 Automatic Meter Reading ( AMR )ምንድነው?

◽️ ይህ በመጀመሪያ እና በዋናነት የተንቀሳቃሽ ወይም CPU ሂደት ነው አንድሮይድ ዘመናዊ ስልኮች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሶስት ዋና ዋና የ CPU architectures አሉ AMR ፣ AMR 64 ፣ እና x 86 የሚባሉ ናቸው። አብዛኛዎቹ ዘመናዊ ስልኮች 64-ቢት ወይም ARM64 ናቸው። ማንኛው የአንድሮይድ ስልክ የራሱ የተሰሪለትAMR አለው። እና ማንኛውም አፕሊኬሽን ወይ ጌሞች ስታወርዱ በስልካቹሁ ARM አውቃቹ ቢሆን የተሻለ ነው ያለዛ ላይሰራ ይችላል።

🔺የ ARM ልዩነታቸው?

◽️ARM v 7 or armeabi
ይህም ARM አነስተኛ የሆነ ኃይል ነው ያለው።

◽️ ARM64 or AArch64 ይህም ARM ተመጣጣኝ ተመጣጣኝ የሆነ ኃይል ነው ያለው።

◽️ ARM86 or x86abi
ይህም ከሁለቱም ይሄ ARM CPU ዓይነቶች የበለጠ ኃይል አለው።

https://telegram.me/Simetube
🔰ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ ኮምፒትር እንዴት ፎርማት ማረግ እንደሚችሉ እናያለን🔰
🎃አስፈላጊ ነገሮች🎃
1. ፍላሽ ዲስክ (ከ4ጂቢ በላይ)

2. os(windows xp 7, 8, 10)

3. Format የሚደረግርው ኮምፒተር

አስራር
በመጀመሪያ Rufus የተባለ ፕሮግራም ከኢንተርኔት ላይ ዶውንሎድ ያርጉ

በመቀጠል ሶፍትዌሩን ሳትጭኑ ራይት ክሊክን በመጫን ''run as admin"የሚለውን ምርጫ ይምረጡ

ከዛ ያዛጋጀነውን ፍላሽ ዱስክ ኮምፒተሩ ላይ እንሰካለን ፕሮግራሙ ከተከፈተ በኅላ ፍላሽ ዲስኩን ዲቫይስ የሚለው ሜኑ ተጭነን እንመርጠዋለን።

ከዚህ ቡሃላ iso image የሚለው ቦታ ሄደን ቅድም ይዘጋጀነውን የዊንዶውስ ሶፍት ኮፒ አስገብተን ድራይቭ ሌተሩን እንመርጣለን።

✏️ ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ ራሱ ሁሉን ነገር አውቶማቲካሊ ስለሚያዘጋጅ ሌላ የምናስተካክለው ነገር የለም ማለት ነው።

🔰ከዛ start የሚለውን በተን ስንጫን ፍላሽ ላይ ያለ ማንኛውም ዳታ ይጠፋል ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል
የምንፈልግው ፍይል ፍላሽ ላይ ካለ ባክአፕ ማድረግ አለብን።
እሱን ካረጋገጥን በኅላ ok እንለዋለን🔰

🎓በስተመጨረሻ ፕሮግራሙ የዊንዶውን ሴትአፕ ወደ ፍላሽ ዲስኩ ኮፒ በማድረግ ስራውን መስራት ይጀምራል።

✏️ ፕሮግራሙ ኮፒ አድርጎ ሲጨርስ exit ኣርጎ መውጣት።

😘 USB ተጠቅሞ እንዴት ፎርማት ማረግ ይቻላል😘
1. ኮምፒተሮን shut down ያርጉ

2.ቅድም ከላይ ያዘጋጀነውን USB ፍላሽ አስገብትው turn on ያድርጉ።

3. F2 ወይም F12 ን (እንደ ኮምፒውተሩ ሞዴል ይለያያል) ይጫኑ እና ቀጣይ ትዕዛዙን ይከተሉ።

4." install windows " የሚለው ሲመጣልዎ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና ሌሎች ዝርዝሮችን ይሙሉ ከዛም next ን ክሊክ ያድርጉ።

5."Please read the license terms" የሚለው ሲመጣልዎ
"I accept the license terms" የሚለውን ክሊክ ያርጉ

6."Which type of installation do you want?" ሲልዎት Custom የሚለውን ይምረጡ።

7."Where do you want to install Windows?" የሚለው ፔጅ ላይ "Drive options" የሚለውን ክሊክ

8. ፎርማት ማድረግ የሚፈልጉትን "partition" ይምረጡና "format" ላይ ክሊክ ያድርጉ

9. ፎርማት አድርገው ሲጨርሱ "next" ላይ ክሊክ ያድርጉ

10. ከዛ በመቀጠል ትዕዛዙን (instruction ) በመከተል window install ያድርጉ።
═══════════════

https://telegram.me/Simetube