Sheger Press️️
39.9K subscribers
3.21K photos
44 videos
6 files
211 links
Official channel of sheger press

If you want to give a suggestion or comment, contact us 👉 @birukepromo
Download Telegram
650ሺህ ብር የተጠራው ሰንጋ😳

ታላቁ የሆሳዕና ገበያ በዘንድሮው አመት ያልተጠበቁ ሪከርዶችን ይዞ ተከስቷል። ወጣት ሚጥዬ ታደለ በእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ ነው። ወጣቱ በከብት ማድለብ ስራ ከተሰማራ በርካታ አመታትን አስቆጥሯል።

በ2016 ዓ.ም በእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣል የተባለውን በጣዕሙ እና በአይነቱ ልዩ የሆውን የጅሩ ሰንጋ በሬ አድልቧል።

ወጣት ሚጥዬ በንግግሩ በዘንድሮው አመት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆነን ሁላችንም የጅሩ አርሶ አደሮች ጣዕም ያለውን ሰንጋ አድልበናል ጊዜውን ጠብቀንም ለገበያ አምጥተናል ሲል ለእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ሚዲያ ተናግሯል።

650ሺህ ብር የተጠራው የጅሩስ ሰንጋ ስንት ብር ይሸጥ ይሆን? እየተባለ ገዢዎችን እየጠበቀ ነው።(FastMereja)

@sheger_press
@sheger_press
መልካምነት ለእራስ ነው 🥰

በአጋጣሚ ከማያቁት ሰው በርከት ያለ ገንዘብ በባንክ አካውንቱ ቢላክሎ ምን ያደርጋሉ ??? 🤔

ነገሩ እንዲህ ነው በአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ እንዲሁም በድለላ ስራ ቤተሰቡን የሚያስተዳደር የባቱ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ቱፋ ሰለሞን የተለመደውን ስራ ለመስራት የእለት እንጀራውን ለማግኝት በስራው ለይ እያለ ባጋጣሚ ወደ ባንክ አካውንቱ 2,000,000 ብር ይገባል።

የዚን ጊዜ ከየት የመጣ በረከት ነው ብሎ ብሩን አውጥቶ ለመጠቀም አይደልም ያሰበው ከየት እንደመጣ ለማውቅ ነው የቸኩለው በስህተትም ይሆናል ብሎ አስቦ ነበር።

ፈላጊው እስኪገኝ ድረስ ለ1 ወር ያክል ገንዘቡን ሳይነካ ባለቤቱ እስኪመጣ ሲጠባበቅ ነበር። በመጨረሻም ከ1 ወር ቁይታ በዋላ አብነት ግርማ የተባለች የአዲስ አበባ ነዋሪ በስህተት ወደ ቱፋ ሰለሞን አካውንት ማስገባቷ ከተረጋገጠ በዋላ አቶ ቱፋ ሰለሞን ገንዘቡን ለባለቤቷ በመመለስ ታማኝነታቸውን አሳይተዋል።

ለፍቶ አዳሪው አቶ ቱፋ ለታማኝነታቸው ምስጋና ይገባቸዋል 🙏🙏🙏

@sheger_press
@sheger_press
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በአገሪቱ የሚዘረጋቸውን የቴሌኮም ታዎሩች ብዛት በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በሦስት እጥፍ ለማሳደግ ማቀዱን እንደገለጠ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ኩባንያው ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 2 ሺህ 500 የቴሌኮም ታዎሮች ያሉት ሲኾን፣ 1 ሺህ 500ዎቹ ታዎሮች ከኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የተከራያቸው ናቸው። ኾኖም መላ አገሪቱን ለመሸፈን 7 ሺህ ታዎሮች እንደሚያስፈልጉት የኩባንያው ሃላፊዎች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል።

ዘገባው፣ በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ግን በኩባንያው እቅዶች ላይ ትልቅ እንቅፋት ደቅነውብኛል ማለቱንም ዜና ምንጩ አመልክቷል።

@sheger_press
@sheger_press
የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ ባይቶና፣ አፍሪካ ኅብረት እና አጋር አገራት፣ የትግራይን ግዛቶችና የትግራይን ነባራዊ ኹኔታ "በተሳሳተ አኳኋን" ገልጠውታል በማለት ወቅሷል።

የሰባት አጋር አገራት ኢምባሲዎች ከሳምንት በፊት እንዲኹም አፍሪካ ኅብረት ትናንት ባወጧቸው መግለጫዎች፣ የተወሰኑ የትግራይ ግዛቶችን "አወዛጋቢ" ብለው በመጥራት የፈጠሩትን "ስህተት ያርሙ" በማለት ጠይቋል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ በመግለጫቸው፣ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፍላ ወረዳዎችን ጨምሮ "በአወዛጋቢ አካባቢዎች ማኅበረሰቦች መካከል ሰሞኑን የተፈጠረው ውጥረት" እንዳሳሰባቸው ገልጠው ነበር።

አፍሪካ ኅብረት በሕገ-መንግስቱ የታወቁ የትግራይ ግዛቶችን "አወዛጋቢ" ብሎ መግለጡ፣ "ለፌደራሉ መንግሥት ያለውን ወገንተኝነት ያሳያል" በማለትም ፓርቲው ከሷል።

@sheger_press
@sheger_press
ፈተናው በኦላይን ይሰጣል ተብሏል

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።

@sheger_press
@sheger_press
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መከላከያ ሠራዊት ምዕራብ ኦሮሚያን "ከበባ ውስጥ በማስገባት ሕዝቡን በጅምላ እየቀጣ ነው" በማለት ከሷል።

ኦሮሚያ ክልል የአገሪቱ አብዛኛው ሃብት ምንጭ ናት ያለው አማጺው ቡድን፣ ኾኖም የፌደራሉ መንግሥት "ኦሮሚያን ለረጅም ጊዜ ሙሉ ከበባ ውስጥ ማስገባት አይችልም፤ አይፈልግምም" ብሏል።

መንግሥት ከምዕራብ ሸዋ ዞን ጀምሮ በመላው ምዕራብ ኦሮሚያ ባኹኑ ወቅት እየወሰደ ያለው ርምጃ፣ "የአማጺው ቡድን ተዋጊዎች ቤተሰቦችና ቡድኑን ይደግፋሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በመንግሥት የሕክምና ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ፍርድ ቤቶችና የቀብር ቦታዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ" እንደኾነ ቡድኑ ገልጧል።

@sheger_press
@sheger_press
ሆሳዕና በአርያም 🌴

እንኳን አደረሳችሁ

የ “ሆሳዕና በአርያም” በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዛሬ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

ሆሳዕና በአርያም ከፋሲካ በፊት ያለው እና የዐቢይ ጾም የመጨረሻው ሣምንት ሲሆን÷ “አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው” የሚሉ ትርጉሞችም እንዳሉት የዕምነቶቹ አባቶች ያስተምራሉ።

የዕምነቶቹ ተከታዮች በሆሳዕና በአርያም በዓል መሪው ተመሪውን ዝቅ ማለትን ያስተማረበት እና ተመሪውም የሚመራውን ጨርቁን እያነጠፈ እና ዘንባባ እየጎዘጎዘ ያከበረበት የትህትና እና የፍቅር በዓል ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡

ሆሳዕና በአርያም ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በተለይም÷ አረጋውያን፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወጣቶች እና ሕጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ ሆሳዕና በዓርያም” በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡

@sheger_press
@sheger_press
መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም፤ መተግበር አለበት።

በኢትዮጵያ መናናቅ እና የት ይደርሳል ማለት ችግር ሲፈጥር እየታየ መሆኑንም መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም።ውጤቱ መተግበር ይኖርበታል።

እንደ ሀገር የመወያየት ችግር ባይኖርም መሠረታዊ ችግሩ አፈፆፀም ላይ ነው።ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መስራት ያስፈልጋል።ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው  እንወያይ እንጋገር ከማለት የዘለለ አይደለም>>

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሴቶችን ተሳፎ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ከተናገሩት የተወሰደ

@sheger_press
@sheger_press
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል 👏🙄

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በመቀላቀል በርካቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን እየሰጡ ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤም የተጣራ የአንድ ወር ደመወዛቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ንቅናቄውን መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
ክለቤን በገንዘብ አለውጥም ያለው ተጨዋች👏

በትናትናው ዕለት ጅማ አባ ጅፋር እና ስልጤ ወራቤ ሊያደርጉት በነበረው ጨዋታ ላይ አንድ የጅማ ተወላጅ የሆነ አሰልጣኝ ለጅማ አባ ጅፋር ተጨዋች ለሆነው ማንያዘዋል (ቻፒ) ለሚባል ተጨዋች በመደወል "ገንዘብ ታገኛላቹ ተጎድተናል በሉ..እኔ ከስልጤ ወራቤ አመራሮች ጋር አውርቻለው እንደምለው ካደረጋቹ ጥሩ ገንዘብ ታገኛላቹ" ብሎ ለተጨዋቹ ይነግረዋል ተጨዋቹ ግን ከተነገረው በተቃራኒ ድምፆቹን በመቅዳት ለአመራሮች ቅጂውን በመስጠት ሁሉን ነገር ገሀድ አውጥቶታል::

@sheger_press
@sheger_press
በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@sheger_press
የአዉሮፓ ህብረት ፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር" ሲል ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ አጠበቀ

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ መክፈል አለባቸውም ተብሏል


የአዉሮፓ ህብረት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር ሲል ወቅሷል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቁን አስታዉቋል።

ዳጉ ጆርናል ከአሶሴትድ ፕረስ ዘገባ እንደተመለከተው ፤ የአውሮፓ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ ለመስራት የሚፈጅባቸዉን ጊዜ በሶስት እጥፍ መጨመሩን ነዉ።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊያን በ15 ቀናት ዉስጥ ቪዛ ያገኙ ነበር የተባለ ሲሆን በዚሁ ዉሳኔ መሰረት ወደ 45 ቀናት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ይህም የኢትዮጵያ መንግስትን በህገወጥ መንገድ በአዉሮፓ ይኖራሉ የተባሉ ዜጎችን እንዲመልስ ጫና ለመፍጠር ነዉ ብሏል ዘገባው።

ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከታዘዙ ሶስት ሰዎች መካከልም አንዱ ብቻ መመለሱ በህብረቱ የመንግስትን ተባባሪነት ጎድሎታል የሚለዉን ክስ ለማሳያነት ቀርቧል። ይህም በፈቃዳቸዉም ይሆን ካለፍላጎታቸዉ ህገወጦችን ለመመለስ የሚደረገዉን ሂደት አጓቶታል ብሏል።

በዚህ ዉሳኔ መሰረትም የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የቪዛ ቀናቸዉም ቢያልፍ የአዉሮፓ ምድርን ለቅቀዉ እንደማይወጡ ህብረቱ ገልጿል።

@sheger_press
@sheger_press
የግብጽ የውሃና መስኖ ሚንስትር ሃኒ ስዌለም፣ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የገነባችው "ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖ ከግምት ሳታስገባ" እና "የደኅንነት ማረጋገጫ ጥናት ሳታደርግ ነው" በማለት መክሰሳቸውን የግብጽ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የኢትዮጵያ ድርጊት "የተናጥል" እና "ዓለማቀፍ ሕጎችንና የሦስትዮሹን የመርሆዎች ስምምነት የጣሰ" መኾኑን ሚንስትሩ መግለጣቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ሚንስትሩ፣ ግድቡ በ150 ሚሊዮን ግብጻዊያን ሕልውና ላይ አደጋ መደቀኑንም በድጋሚ አውስተዋል ተብሏል።

ሚንስትሩ ይህን የተናገሩት፣ ሰሞኑን ባግዳድ ላይ በተካሄደ የዓረብ አገራት የውሃ ጉባዔ ላይ ነው።(ዋዜማ)

@sheger_press
@sheger_press
በአማራ ክልል ከ4.1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ሆነዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያ ቢሮ በአማራ ክልል ከ 4.1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች በግጭት ሳቢያ ትምህርት አቋርጠዋል ብሏል።

በክልሉ 4 ሺህ 178 ትምህርት ቤቶች አሁንም በቀጠለው የጸጥታ ችግር እና በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ምክንያት ተዘግተው እንደሚገኙ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

በተጨማሪም 300 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 350 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ናቸውም ብሏል። እንደ መንግስታቱ ድርጅት መስሪያ ቤት መረጃ ከሆነ በአማራ ክልል ከ1.5 ሚልየን የሚበልጡ ልጆች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ያስፈልጋቸዋልም ብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
ሹመት‼️

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለአብን ከፍተኛ አመራር ሹመት ሰጡ!

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር ለሆኑት ለአቶ መልካሙ ፀጋዬ ሹመት ሰጥተዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ አቶ መልካሙ ጸጋዬን የክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

@sheger_press
@sheger_press
በላሊበላ መንገድ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት መሐንዲሶች መገደላቸው ተሰማ።

ለመሐንዲሶቹ ግድያ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም ያሉት የዘ-ሐበሻ መንጮች፤ የመሀንዲሶችን ግድያ ተከትሎ የመንገድ ሥራ ግንባታው እንዳይቆም ስጋት አለ ተብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
አፍሪካ ኅብረት፣ ከኹለት ሳምንት በፊት በግቢው ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ለግንባታና ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በሚል በተጭበረበሩ ሰነዶች ሊወጣ የነበረው ገንዘብ 6 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጧል።

ኅብረቱ የተደረገበትን የማጭበርበር ሙከራ የፋይናንስ ሠራተኞቹ ማክሸፋቸውን ገልጦ፣ ሙከራው ግን በከፍተኛ አንክሮ የምመለከተው ክስተት ነው ብሏል። ኅብረቱ፣ የማጭበርበር ሙከራው በደኅንነት ሥርዓቱ ላይ ፍተሻ ለማድረግ በር እንደከፈተለትም ጠቅሷል።

በባንክ ሒሳቡ ላይ ወደፊት የማጭበርበር ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በትብብር እየሠራ መኾኑንም ኅብረቱ አስታውቋል።

@sheger_press
@sheger_press