𝚂𝚎𝚢𝚏𝚎𝚕𝙸𝚜𝚕𝚊𝚖 ሰይፈል ኢስላም!
383 subscribers
1.4K photos
142 videos
9 files
318 links
قال ابن تيمية -رحمه الله-:
{قوام الدين كتاب يهدي وسيف ينصر وكفى بربك هادياونصيرا}
مجموع الفتاوى [10/13]
Download Telegram
የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሃካን ፊዳን ከአሜሪካው አቻቸው አንቶኒ ብሊንከን ጋር በ #ጋዛ ሰርጥ ላይ እየተባባሱ ባሉ ጉዳዮች ላይ በስልክ ተወያይተዋል። ሁለቱ ሚኒስትሮች ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በስልክ ሲነጋገሩ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
#አልጀዚራ
#Update
ብራዚል በ#ጋዛ ላይ ያለውን ጦርነት አስመልክቶ የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንድጠራ አሳሰበች!
#Update
“እስራኤል በ #ጋዛ ውስጥ የጅምላ ቅጣት እየፈፀመች ነው!
ፈፅሞ ይሄን አይነት አለም አቀፍ ህግን የመጣስ መብት የላትም!”
የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር Leo
عبد العزيز بن محمد#Update
“እስራኤል በ #ጋዛ ውስጥ የጅምላ ቅጣት እየፈፀመች ነው!
ፈፅሞ ይሄን አይነት አለም አቀፍ ህግን የመጣስ መብት የላትም!”
የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር #ሊዮ_ቫራድካራ(Leo Varadkar)
#𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃_𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
#እስራኤል#ጋዛ ላይ ለ15 ቀናት የፈፀመችው በቁጥር...
√ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 248 ሰማዕታት
√ጥቃቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 4,400 ፍልስጤማዊያን ሸሂድ ሲሆኑ 1,756 ህጻናት እና 967 ሴቶች ናቸው! √ተፈናቃዮች 1,400,000 ሲሆኑ ግማሾቹ በመጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ። √ጥቃቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 13,600 ዜጎች ቆስለዋል!
√5,635 ህንፃዎች ሙሉ በሙሉ ፈርሰዋል!
√164 ሺህ ቤቶች ተበላሽተዋል!
√67 የመንግስት መስሪያ ቤት እና በደርዘን የሚቆጠሩ የህዝብና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ወድመዋል!
√30 ትምህርት ቤቶችሙሉ ለሙሉ የፈረሱ ሲሆን በ176 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።
#አልጀዚራ
#ጋዛ_እንዴት_አደረች?
አልጀዚራ የቀጥታ ስርጭት ከማታ ጀምሮ አዳሩን በሰበር ዜና ያሰራጫቸውን ዋናዋና ዜናዎች መራርጬ ወደ አማርኛ መልሼላችዃለሁ…መልካም ንባብ!
▶️የአልቀሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ #አቡ_ዑበይዳህ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
“ሰላም ለነዚያ ለጌታቸው ካልሆነ በቀር ጀርባቸውን በማያጎንብሱት ላይ ይሁን!” በማለት የጀመረው ሙጃሂድ አቡ ዑበይዳህ፣“ጥቅምት 7 ቀን የጠላት ምሽጎች እንደ ሸረሪት ድር ሲፈርሱ እና አንድ ተዋጊያችን ሶስት የጠላት ታንኮችን ሲያወድም የአሏህ እርዳታ በአይናችን አይተናል!”በማለት አክሏል።
▶️“ጠላት በመኖሪያ ሕንፃዎችና በሆስፒታሎች ላይ ማነጣጠሩ ውርደትንና ሽንፈትን እንጂ ሌላን አያመላክትም” ያለው የሙጃሂዶቹ ቃል አቀባይ ሙጃሂድ አቡዑበይዳህ አያይዞም
▶️“የጠላት ወታደራዊ እና የስለላ የበላይነት አለ የሚባልበት ዘመን አብቅቷል!እናም የጽዮናዊት የሽንፈት ዘመን ጀምሯል!”በማለት በኦክቶበር 7 ላይ ያስመዘገቡት ድል ትልቅ ሞራል እንደፈጠረላቸውና እስከመጨረሻው ለመዋጋት መወሰናቸውን እወቁልን ብሏል!ጠላት ከጠበቀው በላይ ሽንፈትን እንዲቀምስ እናደርጋለን በማለትም ዝቷል የጀግኖቹ የሚድያ ሀላፊ ጀግናው ሙጃሂድ #አቡ_ዑበይዳህ!
▶️የሐማስ ምክትል ሊቀመንበር ሳሌህ አል አሮሪ የፍልስጤም ተቃውሞ አሁንም የውጊያውን ሂደት እየተቆጣጠረ ነው እናም በዚህ ጦርነት ግቦቹን ከማሳካት ወደኋላ አይልም ብለዋል።
یَـٰلَیۡتَنِی كُنتُ مَعَهُمۡ فَأَفُوزَ فَوۡزًا عَظِیمࣰا
▶️ለአረብ መሪዎች ጠንከር ያለ መልእክት ያስተላለፈው አቡ ዑበይዳህ“እኛ የእናንተን ታንክ፣አውሮፕላንና ወታደር አንፈልግም…ቀቅላችሁ ብሉት አይነት…ነገር ግን ቢያንስ ቢያንስ ትንሽዬ ሀሞት ካላችሁ የእርዳታ ተሽከርካሪዎችን እንዲታንቀሳቅሱ እንጠይቃለን!”በማለት በአረቦች ደዩስነትና ተወዳዳሪ የሌለው ፍርሐት በጣም እንደተበሳጩባቸውና እንዳፈሩባቸው በሚያመላክት ንግግር ክፉኛ ተችቷቸዋል!
“እየሩሳሌምን ነፃ ለማውጣት እና የሀገሪቱን ክብር ለማደስ በታሪካችን ወሳኝ ጦርነት ገጥሞናል!”ያለው የጀግኖቹ ቃል አቀባይ ጀግናው ሙጃሂድ አቡዑበይዳህ
▶️“የፍልስጤም እስረኞች ከየእስር ቤቱ ካልተፈቱ በስተቀር የጠላት እስረኞችን መፍታት አይታሰብም!ጠላት የፍልስጢን እስረኞችን በአንድ ጊዜ ለመፍታት ከፈለገ እኛም ተዘጋጅተናል”በማለት ሰብኣዊ እርዳታ እንድገባ በሚል የፅዮናዊት እስረኞችን መልቀቅ ትክክልና ተገቢ እንዳልሆነ በገደምዳሜው ጠቁሟል!
▶️በጋዛ የሚገኘው የሃማስ እንቅስቃሴ ሃላፊ ያህያ ሲንዋር ለአል-አቅሳ ቲቪ እንደተናገሩት በተቃውሞው የተያዙ እስረኞችን በሙሉ ለመልቀቅ በወረራ የተያዙ እስረኞችን መፍታትን የሚያካትት የልውውጥ ስምምነት ለመደምደም ተዘጋጅተናል በማለት የአቡዑበይዳህን ንግግር ደግመዋል።
▶️የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ እስረኞቹን አስመልክቶ ለሐማስ መግለጫ በሰጠው መልስ“ሃማስ በእስራኤላውያን ላይ ጫና ለመፍጠር የስነ ልቦና ጦርነት እያካሄደ ነው!”ብሏል።
▶️በእየሩሳሌም የሚገኘው የእስረኞች ክለብ ሃላፊ ለአልጀዚራ ቀጥታ እንደተናገሩት ከጥቅምት 7 በፊት በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩት እስረኞች ቁጥር 5,200 ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 400 ህጻናት እና 32 ሴት እስረኞች ይገኙበታል።
▶️ትላንት ቅዳሜ በብዙ መቶሺህዎች በተገኙበት የኢስታንቡል ሰልፍ ላይ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጠንከር ያሉ ንግግሮችን በመናገራቸውና ሀማስ የነፃነት ታጋይ እንጅ ፈፅሞ አሸባሪ አይደለም…በዚህ አቋማችን እስራኤል ብትቀየምም የራሷ ጉዳይ…እንዳውም አሸባሪዋ ራሷ ፅዮናዊቷ መሆኗን ለዓለም ህዝብ እናሳውቃለን…በማለት በተናገሩት ንግግር ምክናየት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቱርክ ጋር ያለንን ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ እና ግንኙነት እንደገና እንገመግማለን!”በማለት ቲውተር(X)ላይ ፅፏል።ማን ሊጎዳ?
▶️በጋዛ ውስጥ የመንግስት ሚዲያ ኃላፊ“ፍልስጤማውያን ለወረራ ማስፈራሪያዎች አይንበረከኩም፣እስከ መጨረሻው እስትንፋስ ድረስ እንታገላለን!”ብሏል።

▶️የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ጋር በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በስልክ ተወያይተዋል።
▶️ሃማስ በጋዛ ውስጥ 8 ሩሲያውያን-እስራኤላውያን እስረኞችን ለማግኘት እየሞከረ ሲሆን ላቭሮቭ “ለአስር አመታት የሚቀጥል አደጋ” እንዳለ አስጠንቅቋል።
▶️የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ከሳዑዲ አቻቸው ጋር በጋዛ ወታደራዊ ዘመቻዎችን ማስፋፋት ያለውን አደጋ እና አፋጣኝ የእርቅ ስምምነት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተወያይተዋል።
▶️የኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ወረራ በጋዛ ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እና የአለም አቀፍ ህጎችን መጣስ ጥልቅ ስጋት እንዳለን እንገልፃለን ብሏል።
▶️የኳታር ኤሚር እና የኢራን ፕሬዝዳንት በፍልስጤም ስላሉ ለውጦች ተወያይተዋል!
የኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወራሪው ሀይል በጋዛ ሊፈጽመው ያሰበውን የመሬት ወታደራዊ ዘመቻ ውጤቱ የከፋ እንደሚሆንና ከአካባቢው አልፎ በአለም ላይ ከባድ አደጋዎችን እንደሚያስከትል በድጋሜ አስጠንቅቋል።
▶️የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንድደረግና አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ለማምጣት ኮሪደሮች እንዲከፈቱ እንጠይቃለን ያለ ሲሆን አያይዞም እስራኤል በጋዛ ያደረገችውን ​​የመሬት ኦፕሬሽን እናወግዛለን በማለት አክሏል።
▶️የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ ወረራ ለማድረግ በያዘው አቋም ላይ ያለንን ጥልቅ ስጋት እና አስከፊ ሰብአዊ መዘዝ የሚያስከትል አደገኛ ሙከራ መሆኑን እንገልፃለን ብሏል።
▶️የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ሆስፒታል፣እንዴ UNRWAአይነት የእርዳታ ማእከል ወይንም ትምህርት ቤት ለሽብር ተግባር የሚያገለግል ማንኛውንም ኢላማ አንተወውም በማለት ከዚህ በፊት በአንድ ግዜ ከ500 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የሆስፒታል ጥቃት በግዜው ያስተባበለች ቢሆንም ዛሬ ግን እርሱን በማመን ለወደፊቱም በእብሪቷ እንደምትቀጥል ይፋ አድርጋለች!
▶️በዋሽንግተን እና በኒውዮርክ የተካሄዱ ሰልፎች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት በማውገዝ ጦርነቱ እንዲያበቃ ጠይቀዋል።

︎የቀድሞ የቱርክ የፍትህ እና ልማት ፓርቲ ዋና አማካሪ የጋዛ ጦርነት የእስራኤል እና የምዕራባውያን አጋሮቿን ጭካኔ የተሞላበት ገጽታ ይፋ አድርጓል በማለት አውግዟል።
︎ በለንደን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ፍልስጤምን በመደገፍ እና በጋዛ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲያቆም ጠይቀዋል።
▶️“እናስታውሳለን” በሚል መሪ ቃል “የአይሁድ ድምፅ ለሰላም” ድርጅት ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2023 በእስራኤል የቦምብ ጥቃት የተገደሉ 2,913 የፍልስጤም ልጆችን ስም አውጥቷል።ድርጅቱ በጋዛ ላይ ለደረሰው አስደንጋጭ ነገር ተጠያቂ ናት ሲልም ዩናይትድ ስቴትስን ከሷል።ምክንያቱም በእስራኤል ጦር እጅ ህጻናትን ከሚገድሉት ቦምቦች 80% የሚሆኑት አሜሪካ ሰራሽ ናቸው።እያንዳንዱ ህይወት ውድ እንደሆነ እና ይህን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆም ሁሉም ሰው የተቻለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
▶️የእስራኤል ሚንስትር #ኤሎንመስክ በጋዛ ለሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት መወሰኑን አስመልክቶ ምላሽ ሰጥቷል።
#𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃_𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
https://t.me/Seyfel_Islam
ይቀጥላል👇
ከላይ የቀጠለ…
▶️የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ባለስልጣናት የጋዛን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ያሰበውን አረመኔያዊ ድርጊት ለማስቆም ለተኩስ አቁም ምላሽ እንዲሰጡ እንጠይቃለን ብሏል።
▶️ሮይተርስ ከዲፕሎማቶች አገኘሁት ባለው መረጃ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ሰኞ ይሰበሰባል።
▶️በጋዛ ሰርጥ የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ምስሎች የእስራኤል ወረራ በሆስፒታሉ አከባቢ ላይ ባደረሰው የቦምብ ጥቃት የደረሰውን ውድመት አሳይተዋል።
▶️የስፔን ሚንስትር ለአውሮፓውያን #ናታንያሁ የጦር ወንጀለኛ ነው.. በ #ጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ስፔንን ተባባሪ እንዳታደርጉን ብሏል።
▶️የእስራኤል እስረኞች ቤተሰቦች ከ # ናታንያሁ ጋር ከተገናኙ በኋላ ዘመዶቻችን እንዲመለሱ የፍልስጤም እስረኞችን ከእስር ቤት እንዲወጡ እንደግፋለን በማለት የሀማስን አቋም ተጋርተዋል።
▶️ግብፅ የእስራኤል መሰናክሎች እርዳታ ወደ #ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ እንቅፋት ሆነዋል በማለት እንደለመደችው ከሳለች።ክስ ብቻ!
▶️የፍልስጤም የዜና አገልግሎት ከራማላ በስተሰሜን በምትገኘው በቢት ሪማ ከተማ ከወራሪው ሃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት 6 ወጣቶች በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ቆስለዋል(ተገድለዋል?)
▶️የቤልጂየም ፓርላማ አባል የሆኑት ሲሞን ሞትኪን የ#አልጀዚራ ፎቶዎች ባይኖሩ ኖሮ በጋዛ የእስራኤል ዕለታዊ ወንጀሎች ወደ ምዕራቡ ዓለም አይደርሱም ነበር በማለት ለአልጀዚራ ያላቸውን አድናቆት የገለፁ ሲሆን እግረመንገዳቸውንም የምዕራቡ አለም ሚድያዎችን ተችተዋል።

▶️የፍልስጤም ቲቪ እንዳስታወቀው ኮሙኒኬሽን እና ኢንተርኔት ቀስ በቀስ ወደ ጋዛ ሰርጥ እየተመለሱ ነው ብሏል።
▶️አንድ ፈረንሳዊ #ጋዛን በሚደግፉ ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ከፈረንሳይ ፖሊስ ጋር ተጋጭቷል¡
▶️የፍልስጤም ቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች “ፓልቴል”እና “ጃዋል” የጥሪ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ቀስ በቀስ በጋዛ ሰርጥ ወደ ሥራ እየተመለሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
▶️በጋዛ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጋዛ በስተደቡብ በሚገኘው በካን ዩኒስ በሚገኘው የ"ታሞስ" ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ላይ የወረራ አውሮፕላኖች ባደረሱት የቦምብ ጥቃት 10 ሰማዕታት እና ከ25 በላይ
መቁሰላቸውን አስታውቋል።
#𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃_𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
https://t.me/Seyfel_Islam
#ጋዛ_እንዴት_አደረች?
አልጀዚራ አዳሩን በሰበር ዜና ከዘገባቸው ዜናዎች መካከል ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
https://t.me/Seyfel_Islam
▶️የሃማስ እስረኛ ፋይል ባለስልጣን ለአልጀዚራ ቀጥታ እንደተናገሩት ሃማስ በእስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ #ስድስትሺህ እስረኞችን የመልቀቅ ፍላጎት ያለው ቢሆንም ኔታንያሁ ግን የእስራኤል እስረኞች እንዲመለሱ አይፈልጉም ብሏል።
▶️አል ቁድስ ብርጌዶች አስቀላንን፣ ስዴሮትን፣ ኒር አምን፣ ማፍላሲምን፣ ክፋር አዛን እና ክፋር ሳድን በጠንካራ ሚሳኤል አደባየናቸው ብሏል።
▶️የቦሊቪያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአልጀዚራ የቀጥታ ስርጭት እንደተናገሩት መንግስታችን የዘር ማጥፋት እየተደረገበት ካለው የፍልስጤም ህዝብ አጋር በመሆን ከእስራኤል ጋር ያለውን ሙሉ ግንኙነት አቋርጧል ብሏል!
አይነ አንቱም ያሁከማኡልዐረብ ሚን #ቦሊቪያ?
▶️አቡ ዑበይዳህ“በጽዮናውያን የቦምብ ጥቃት ከ60 በላይ የእስራኤል እስረኞች የተገደሉ ሲሆን የ23ቱ አስከሬን በፍርስራሽ ውስጥ ጠፍቷል ብሏል!
▶️አልቃሳም ብርጌዶች ከካን ዩኒስ በስተምስራቅ ዘልቀው የገቡትን ሀይሎች በተለያዩ የጦር መሳሪያዎችነ ኢላማ ካደረግን በኋላ ሁለት የጽዮናውያን ታንኮችን አውድመናል ብሏል።
▶️የአል-አቅሳ ሰማዕታት ብርጌዶች ተዋጊዎቻችን ከናብሉስ በስተደቡብ በተቋቋመው ባርካ የፅዮናዊያን የጦር ሰፈር ውስጥ ጥቃት አድርሰው በሰላም ተመልሰዋል ብሏል!
▶️አልቁዱስ ብርጌዶች ከካን ዩኒስ ከተማ ወደ ምሥራቅ ለመዝመት የሞከሩትን የጠላት ተሽከርካሪዎች በሞርታር ተኩሰን አነጣጥረናል ብሏል!
▶️የሊባኖስ ሒዝቦላህ ለሜቱላ ሰፈራ ቤቶች ውስጥ በአንዱ የእስራኤል ወታደሮችን ስብስብ ኢላማ አድርገን ጉዳቱን አረጋግጠናል ብሏል።
▶️የሂዩማን ራይትስ ዎች የቀድሞ ዳይሬክተር ኬኔት ሮት ለአልጀዚራ ሙባሸር እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ በጋዛ ላይ ያለውን ጦርነት በተመለከተ በጣም #አስመሳይ አቋም ትወስዳለች።እስራኤል ከተጠያቂነት ማምለጧ ሌሎች ወንጀሎችን እንድትፈፅም ያበረታታል ያሉ ሲሆን በማያያዝም የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ጋዛን በተመለከተ በፍጥነት እርምጃ መውሰድ አለበት በማለት አሳስበዋል።
▶️እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እንዲያቆም ለመጠየቅ በአሜሪካ ዋና ከተማ እና በበርካታ የአውሮፓ ዋና ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል።
▶️የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ በእስራኤል በተፈጸመው ግፍ የተፈጸመ የቦምብ ጥቃት በጋዛ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎችን ገድሏል፤የቦምብ ጥቃቱ በሆስፒታሎች እና በስደተኞች ካምፖች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን አሁንም ቢሆን በአስቸኳይ መቆም አለበት በማለት ሀሳባቸውን ገልፀዋል!ሹክረን!
▶️እስማዔል ሃኒያህ በዋሽንግተን እና በሌሎችም የምዕራባውያን ከተሞች ሰልፍ የወጣው ህዝብ ከህዝባችን ጋር በመተባበር በጋዛ ያለው የዘር ማጥፋት ጦርነት እንዲያበቃ “ነፃነት ለፍልስጤም!ተቃውሞው ህጋዊ ነው!ወረራውም ማብቃት አለበት!”በማለት አጋርነታቸውን በማሳየታቸው አመስግነዋል!
▶️ሆሳም ባድራን ለአልጀዚራ ሙባሸር እንደተናገሩት የመቋቋም ሚሳኤሎቻችን አሁንም በሁሉም የተያዙ ከተሞች ላይ መድረስ ችለዋል፤አሁንም ጦርነቱን በስሌታችን ውስጥ እየመራን ነው ብሏል።
▶️ሀማስ የሆንዱራስ መንግስት ወራሪዋ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ህዝባችን ላይ እያደረሰች ባለው አረመኔያዊ ጥቃት ምክንያት አምባሳደሩን በማስጠራት ለወሰደው አቋም ደስ ብሎናል!እናመሰግናለን ብሏል።
▶️ፍልስጤምን ለመደገፍ እና የእስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም ለመጠየቅ በኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ ሰልፍ ተደርጓል።
▶️የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኔታኒያሁ በጋዛ ስላለው ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ እና አስፈላጊው ዕርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ በስልክ ነግሬዋለሁ ብሏል።
#𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃_𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
https://t.me/Seyfel_Islam
https://Ummalife.com/AbdelazizBinMuhammed
#ስለፍልስጢን_ምንአዲስ?
ዛሬ የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ከፍተኛ ባለስልጣን #ዒዘት_አልሪሽቅ መግለጫ ሰጥቷል!
ከንግግሮቹ መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው!👇
•ባይደን በጋዛ የዘር ማጥፋት ጦርነት ውስጥ #ሙሉ አጋር ነው! ህዝባችን ከእርሱ ምንም ጥሩ ነገር አይጠብቅም።
•ባይደን ስለ ፍልስጤም መንግስት ምስረታ እና የመንግስቱ መዋቅር ምን መምሰል እንዳለበት ለመናገር እየሞከረ ያለበት #ቅዠት ህዝባችንን አያታልለውም!
•እራሳቸውን እንደ ፍልስጤም ህዝብ ጠባቂ አድርገው የሚያስቡ አካላት(ማህሙድ ዐባስ የሚመራውን የፋታህ ሬብ አስተዳደር ለማለት ይመስለኛል)ለእነርሱ የሚስማማቸውን መንግስት መምረጥ ይፈልጋሉ።
•በጋዛ ሰርጥ እና በዌስት ባንክ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰማዕታት እና ቁስለኞች የፍልስጤም ህዝብ ለከፈሉት መስዋዕትነት #የሚመጥነውን በነጻነት እና በክብር የሚኖሩበትን ሃገራቸውን ይወርሳሉ!
•ከመቶ ቀናት በፊት የአሜሪካው ንግግር #ከሃማስ መወገድ በኋላ በ #ጋዛ ስለሚኖረው አስተዳደር ነበር!
ዛሬ ደግሞ ከ #ኔታንያሁ በኋላ ስለ #እስራኤል እጣ ፈንታ  ሆኗል!
https://t.me/Seyfel_Islam
𝚂𝚎𝚢𝚏𝚎𝚕𝙸𝚜𝚕𝚊𝚖 ሰይፈል ኢስላም!
Photo
ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ስለ ግብፅ ምን አለች ?

" በስምምነቱ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛውንም  የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንቃወማለን " - ሶማሌላንድ

ዛሬ የራስ ገዟ ሶማሌላንድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጣለች። በዚህ መግለጫም ስለ ለሰሞነኛው የግብፅ ሁኔታ ምላሽ ሰጥታለች።

ምን አለች ?

ሶማሌላንድ ፤ ከግብፅ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት ገልጻ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ያላትን ስጋትም እውቅና እንደምትሰጥ ገልጻለች።

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተከሰቱ ክስተቶች አንፃር ቀጠናዊ ጉዳዮችን በውይይት እና በትብብር ለመፍታት ያለኝን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለሁ " ብላለች።

ይሁን እንጂ በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እና በ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከል ከተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በኋላ የሚነሱ ማንኛውንም አይነት የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንድምትቃወም በድጋሚ አረጋግጣለች።

በመግለጫዋ ፤ " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር በተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አከብራለሁ " ስትል ገልጻለች።

" ሁሉም ፍላጎት ያላቸው አካላት ቀጠናዊ መረጋጋትን እና ገንቢ አጋርነትን በማስፈን ላይ እንዲያተኩሩ አበረታታለሁ " ያለችው ሶማሌለንድ ፤ " በዚህ መንፈስም #ግብፅ በቅርብ ጎረቤቶቿ እንደ ፦
* #ሱዳን
* #ሊቢያ
* #ጋዛ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫዋን እንድትቀይር እናበረታታታለን " ብላለች።

" እነዚህ አካባቢዎች (ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ጋዛ) በአሁኑ ጊዜ ጉልህ ከሆኑ ተግዳሮቶች ጋር #እየታገሉ ነው ፤ እናም የግብፅ ገንቢ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለን እናምናለን " ስትል ገልጻለች።

የሶማሌለንድ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማትን ለማስፈን ከሁሉም ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን እና ትብብርን ያደርጋል ስትል አሳውቃለች።

" የጋራ ጂኦፖለቲካዊ አካባቢያችንን ሁኔታ ለማሻሻል ከግብፅ እና ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር #በመከባበር እና #በጋራ_ጥቅም ላይ የተመሰረተ ገንቢ ግንኙነትን ለመፍጠር እንሰራለን " ስትል ገልጻለች።
Via TikvahEthiopia
#Breaking
"በ #ጋዛ ከተማ ውስጥ ከአል-ዘይቱን ሰፈር በስተደቡብ የሚገኘውን ሁለት ማኦዝ አጥፍቶ ጠፊ አውሮፕላኖችን ጨምሮ 3 የጽዮናውያን አውሮፕላኖችን ተቆጣጠርን!”
#አልቀሳም_ብርጌዶች!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዘዳንት #ሲሲ ወደ #ጋዛ የሚያሻግረውን #የራፋህ ማቋረጫ ለመክፈት ፍቃደኛ #አልነበሩም!
ነገር ግን መክፈት እንዳለበት እኔ በስልክ አሳምኜዋለሁ!”

#ጆ_ባይደን!
ይሄ ሞት ነው!ውርደት ነው!
إنالله وإنا إليه راجعون!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Heart_Touching😔😔
በማዕከላዊ #ጋዛ ሰርጥ በቡሬጅ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በሚገኘው የቤተሰብ መኖሪያ አጠገብ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ሕፃኗ ቃማር እና እናቷ ከባድ የእሳት ቃጠሎ ደርሶባቸዋል።

#አልጀዚራ ቀጥታ
https://t.me/Seyfel_Islam
“በሰሜን #ጋዛ ዛሬ በተደረገው ጦርነት 3 ወታደሮች የተገደሉብን ሲሆን አንደኛው የከፊር ብርጌድ መኮንን ነው!”
የእስራኤል ሚዲያ
አልሐምዱ ሊላህ